WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
__________///__________
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 3:09 am    Post subject: __________///__________ Reply with quote

እቺ የእኔ ክፍል ናት በቃ አለ አይደል የራሴ አንዳንድ ውስጤ ሊዘበራረቁ ያሉትን ፋይሎች አምጥቼ ምወረውርባት ማንም እንዲያነባት ፈልጌ አይደለም የከፈትኳት ዌስት ኦፍ ስፓም ...ምናምን እንዳትሉኝ ፕሊስ ግን ግን ማንበብ መብታቹ ነው አለ አይደል በሩ ያልተዘጋን የሰው ጊቢ ገርመም እንደማድረግ ዓይነት ታዲያ ለምን ሕዝብ በሚያነበው መድረክ ላይ አሰፈርከው ? ትሉኝ ይሆናል መብቴ ነው ብዬ ድርቅ ብል አያምርብኝ ይሆን እኔንጃ

ይሄ ሌላ ዋናው ነው ዋርክኛ ውስጥ ከምታውቁት የተለየ ዋናው ምትፅፈው አይገባም ካላችሁኝ ሆለፊልድኛ ነው ከማለት ውጪ ምንም ምላቹ አይኖረኝም (ወይም ደግሞ እናንተም አትገቡኝም እንዳለው ደራሲ ከማለት ውጪ )
እናም እርስ በእራሴ እመላለሳለሁ እራሴን እጠይቅና ነገ ደግሞ ዘኪዮስን ሆኜ እመጣለሁ በዘኪዮስ ውስጥ ብዙ ግርዶሽ ብዙ ጥላ ብዙ ጨረር ብዙ ሕልም ብዙ ቅዠትና ብዙ መንቀዥቀዥ ሠፍሮበት ....የስነፅሑፍ አንድምታ ምቱ ግራ ለሆነ ልበ -ድላቄ መስቲያት ቢሆን ብዬ መሞከር ፈልጌ ይሆን እንጃ ? (መስቲያት ...ያንድ ሠው አባባል ናት መስታወት እንደማለት )
ብዙ ብዙ ጊንጎዎች አሉ .....ጋንጢቶች አሉ ....ሙጠምጢሞች አሉ ....እነዚህ ሦስት መሠረታዊ የጥበብ አወሊያዎች በጨቅላ ቀለም እይታችን ውስጥ አረፋ እስኪያስደፍቀን ድረስ ምስጢረ -ምታቸዉን ጎልጉለን ነበር ....በነጮቹ ማንዳላንነታቸው ሕያው ሆኖ ስበተ ንፍስያችን በሙሀሩስጥ ሽክርክሮሽ እስክንጀምር ማለቴ ነው አቤት ' ያለው ደስታ በችሎታ እንደመጦዝ ምንኛ ሕሴት ይኖር ይሆን ....ታዲያ ወደዕውቀት ግስጋሴ ላይ እያለን .....!
የሸራሪትን ጥበብ እንደወረስን ሁሉ አየር ላይ እስትንፋስ ረጭተን ሀዲድ እንደሰራን ነበር ሚሠማን ....
አንድ ጊዜ ስዩም ተፈራ ሲጠየቅ ቀልዶች አያስቁኝም ግን እኔ ውስጄ ሰው አስቅባቸዋለሁ እንዳለው ዓይነት ግብዝና እኔያዊ ብሕራን እንዲወነጨፉብኝ ሕሳቤው ኖሮኝም አይደለም እቺን የራሴ የግሌ የእኔ አምድ የከፈትኳት ...! ካሁኑ ወደድኳት ድሮ ከወንድሞቼ በጋር ምጠቀምበት አንድ ፕሮፐር የትምሕርትቤት ዴስክ ነበረች ከዛ ሁሌ ስንጣላ ለእኔ ለራሴ ተገዛልኝ እንዴት ደስ እንዳለኝ ያቺን ዴስክ ውድድድድድድ እንዳረግኳት ነው እቺን ክፍል እየወደድኳት ያለው
እስቲ አሁን እንቅልፌ መጥቷ ልሞት ልሄድ ነው ከደቂቃዎች በኌላ አርጋለው (ትንሳሄ 'ዬን አላየዉምንጂ ) እቺን የእኔን ቤት ነገ ሽርፍራፊ ጊዜ ሳገኝ እፈነጭባታለሁ የሀሳብ ቡጊ ቡጊ ...የቅዠት ራጋ እወርድባታለው ....

ያለፊርማዬ

Last edited by ዋናው on Tue May 27, 2008 12:23 am; edited 6 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 3:48 am    Post subject: ቅቅቅ Reply with quote

የሌሊቱ የእለቱ ጥቅሥ ከዋናዉ !

"በችሎታ ዕንደ መጦዝ ምንኛ ሐሴት ይኖር ይኆን !! (ዋናዉ )200% ትክክል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
meote

ኮትኳች

Joined: 22 Apr 2006
Posts: 433
Location: warka

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 4:07 am    Post subject: Reply with quote

ዋንቾ ምነው በስላም ነው ግን ....................... Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing
_________________
LIFE IS A WOUNDERFUL THING.....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ifa

ኮትኳች

Joined: 09 Jul 2007
Posts: 115

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 5:07 am    Post subject: Reply with quote

እንዴ ይህ እውነት ታላቁ ዋናው ነው ወይስ ? እንዴ እንዴት ነው ሰቢን አደጋ ላይ በገዛሕኝ እጅ ጥሎ እሱ እዚህ የሚዝናናው ...እኔኮ "ልቤን ሰቅሎ ስራ መስራት አልቻልኩም .."ብዬ ልከሰው ብየ ያው ግሮሰሪው ቢዚ አድርጎት ይሆናል ብየ መልሼ ዋጥ አደረገኩት . ዋንች እንዴ እንዴት ነው ነገሩ ? እነ ዋኖስ ፍቅር ይዞት እንዳይጠፋ እጸልያለሁ እንተ ለካ ሽልክ ብለህ ሌላ መድረክ ከፍተሀል .....እባክህ
አድናቂህ አይፋ
የሰባዊት bodyguard
_________________
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴነሽ

ኮትኳች

Joined: 17 Mar 2005
Posts: 114

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 8:09 am    Post subject: Reply with quote

Last edited by እቴነሽ on Thu Aug 16, 2007 7:18 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘኪዮስ 5

አዲስ

Joined: 13 Aug 2006
Posts: 37

PostPosted: Wed Aug 15, 2007 10:43 pm    Post subject: Reply with quote

ያክሺማሽ .....(<ፖሊሽኛ መሆኑ ነው )
ዶብዠ ::
ያኔ ለአቅመ -ቀለማት ጥንገራ ስንደርስ ስዕል ምንለማመድበት ክፍል ነበረን የዘውትር አርብ ፕሮግራማችን እርስበርሳችን ፖርትሬይት በውኃ ቀለም መሳሳል ነበረ ታዲያ ይሄንን ፕሮግራም ስለምናውቅ ሁላችንም አርብ የውኃ ቀለም እናመጣለን አንዱ ፍሬንዳችን ቢጫ ቀለም ብቻ ይዞ መጣ ቅቅቅቅ ምነው ? ይሉታል እኔ ምስለው አስደሳችን ነው ብሎ አረፈው ቅቅቅ አስዱ ደግሞ ቢጭጭ ያለ ልጅ ነበር ተሳቀና በሱ ምክኒያት ሞኖ ቀለም አጥንተን ዋልን ትዝታ ሕሣቤን ክሊክ ያደርገው የለ ....? ምስሎች ሁላ ባንድ ዝርግ እይታ ሲታዩ ሁለት ድባባዊ ገፅ አላቸው እንደሁለት ዳይሜንሽን ታዲያ ምክኒያታዊ ገፅታ በሁላሁሉ ሆኖ ከነግሳንግስ ምክኚያት ተዘርዝሮና ተተርትሮ የሁልትዮሽ ጋጋታዉን እየዘበዘበ ይነጉዳል .....ብረሐን እና ጥላ ..... ማግኘትና ማጣት ....መሆን እና አለመሆን .....መሞትና መወለድ ምናምን ብዙ ብዙ ምናምኖች ....
ማንኛዉም መለኮታዊ ኃይል ሆነ ክስተታዊ ኃይል መጠኑን ምናውቀው አለ -ኃይል ሲኖር አይደል እናም እቺን የእኔ ቤት የእራሴ ብቻ .... ትላንትና በመሠጠረ ሌሊት ሳንፃት ውስጠ -እርጋታዬን ልለካባት መወዣበሬን ማያያ ስለሻው አይደል
ዛሬ አንዲት የሻገተች ርዕስ አስታውሼ ነው ዘኪዮስን ሆኜ የመጣዉት ዋናዉን ሆኜ ምመረምረው መልስ ሳዘጋጅ ቅቅቅቅ በውጪያኑ ጥበብተኞችም ሆነ በእኛዎቹ ፋና ወጊ ፅሐፍትና ሠዓሊያን የምትነሳ ጥያቄ አለች ==> አርት ሶሻል ፈንክሽኑ መቅደም አለበት ወይስ ፐርሰናል ፈንክሽኑ ...? የሚሉት ዓይነት ድሮ እነአቦስ ስብሀት በጉሩፕ ተከፋፍለው ይወያዩበት ነበር እቺን የሻገተች ሕሣቤ ቦርቀቅ ላድርጋትና እንደመዝገቡ ኪስ (<==ያዳም ረታ ግራጫ ቃጭሎች ውስጥ ያለው መዝጌን / አቤት ስወደው '/) እናም የጥበብ ድምምታው ቀልብን ሰቅሎ ትላንት እንዳልኩት ችሎታው በጡዘት ውስጣችንን ሲያርደው ማየቱን ማስቀደመምና ለሕሴት ተገዝቶ ለውስጠ -ነብይነት ምስክር የመሻት እንዲያው በግርድፉ ለስሜት መጠበብ ......ይቅደም ? ወይስ የተነሳንበት ትርምስምስ ማሕበረ -ሠብ ልበ -ትርታዉን በማየት የወዣበሩ ምስሎች ምክኒያታዊ ምስጢራቸዉን በማሠብ ከኤስቴቲክ ይልቅ ጥበብ ተናገሪ እንደሚባለው እንደነፓኑ ኮሚንዝማዊ መገልገያነቱ ....?
ዛሬ እቺን ያደፈች በነጪኛ ስኳሊድ መላምት ማንሳቴ ከዋንኛ ዋናው ጋር በእሠጥ -አገባ ሳይሆን በበላ ልበልሀ ሳይሆን በአፍርሳታ ሳይሆን አለ አይደል ጥጉን ሚያክኩት ሕሳቤዎችን እያንሸራሸርኩኝ ቢሆንድ -ፓዝ ውስጥ ሆኜ እንደቀሽሟ የለንደን ሠመር ጀንበር ቶሎ እንዳልጠልቅ በመፍራትና በመሰሰት መሀል ሆኜ በሁለትኛ ሙጠምጢም ጊንጎዋዊ ሙሐር ሽክርክሪት ልልበት በመፈለግ ነው ቅቅቅ የትኛው አድናቂዬ ነበር አንዳንድ አረፍተነገሮችህ ከፌርሙዝ አልወርድ እንዳለ አጃ ማለቂያ የላቸዉም ...ያለኝ (<== ስሟዘዝበት ) ግን ' ይሄ የእኔ የእራሴ ክፍል ነው ::
ነገ ዋንቾን ሆኘ እመጣና ደግሞ ቤቴን እንደቀትር እባብ እወራጭበታለሁ .....እኚያ ጦር ይዘው ዘራፍ እንዳሉት (<==የተድባብ ጥላሁን ላይ ማሕልዬ ላይ ያሉት ) እሸልልበታለሁ ... እንደሚስተር ቫርኮቪኒስኪ በፓራዶክሴ እኮነንበታለው (የዲዮስቶቭስኪው -ዴቭል ውስጥ )
በቃ ኃሙስን ሆኜ ሳልነቃ የገሀዱን ብሕሮቼን ዋናውን ሆኜ እዛ ሰፈር ላንሳ ::

ካምሳሚዳ (<== ኮሪያኛ መሆኑ ነው )
አሊቬ ደርቺ

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Aug 16, 2007 3:31 am    Post subject: Reply with quote

ላቫስ ሪታስ (በሉቲኒያኛ )

ምን ላድርግ በአገሬ ቢሆን ጀንበሯ የመኝታቤቴን የወየበ መጋረጃ ፈንቅላ በኩርኩም ብላ ዓይኖቼን ታሞጨሙጭ ነበር ኃሙስ ሚሆነው እዚህ ግን አሁኑኑ ኃሙስ ሆኖ ቁጭ ቅቅቅ <== አሁን ይሄ ሁሉ አሸንክታብ አዲሱ ቤቴ ብርቅ አልሆነብኝም ለማለት መሆኑ ነው ድንቄም ቅቅ
ትላንትና በእኛ ቅድም ...ዘኪዮስም አልነበርኩኝ ገና እንደማያ እቀያየራለው ትንሽ ዝብዝብ ላድርግ የትላንቱ እኔ ኤስተቲካል ቫሊዩ ቅድመ -ድርሻው ለመቸቱ ወይስ ለፈጣሪው በሚል ውዝግብ እንደአሮጌዎቹ ካቻምናዎች መላኛ ውስጥ መፈራገጥን ______::
አንዳንዴ ከውስጤ ዱብ ዱብ ብለው ብረሐን 'ሚጎናፀፉ ቀለማት ፓሌትና ብሩሽ ሳይደፍራቸው በነፃነት ይንሾሿሉ ልክ ቄዝ ጎበዝ በጥበቡ እንደሚያቃጭላይ ቄንጤኛ ፅናፅል ....ድምፅ ..... ወረባዊ ውዝዋዜዉን ትውስታ የነዳሞትን ዓይነ -ሕሊናን ሰጥቶኝ ባወሳው በምን እድሌ እዚችጋ ሸላይ ስንቀራ ይደረግባት ነበረ :: ዳሩ እኔ ዘኪዮስን 'ንጂ ዋኖስንም ዳሞትንም መሆን አልችልም አይደል የስንኝ ጉርብትናችን አብረን ፊደል ያጣጣናል 'ንጂ እናም አዎ ምን ነበር ማወራው ?? አዎ እነኚያ በረከቶች ገፀ -ሠፊው ሸራ ላይ ሂደው ምስል ሁላ ሳይሆኑ ውስጤን ማጦዛቸው ለእኔ ተብሎ የተሠጠ መክሊቶች ናቸው እላለሁ :: (ምከፍለው ወይም ማልከፍለው መክሊት ) አንዳንዴም ፍቅር እንዳናወዘው ኮበሌ ተብረክርኬ መስመሮችን ሳወሳስብ ቀለም ሳጥበረብር መስመር ሳወሳስብ ....ይሄ ሁሉ ጥበባዊ ግዴታ ...ውትድርና ተጋድሎ ...ለእኔ ልክ እንደዚች የእኔ ቤት ፍፁም ትሕፍሰቱ ውስጤ ብቻ ሚጎርፍ ይመስለኛል :: እናም ዘኪዮስዬ ጥበብ አሕደ -ጥቅሙ ለኔ ብቻ ብዬ ማስባቸው ጊዚያት የትየለሌ ናቸው <<እምጱዋ >> የሆነ ጥቅም ነዋ ለዛሁም ... አስረጂ ብዬ ልጀምርና ለምሳሌ ጥላ -ዓልባን እዚ ሠፈር መጥቼ ስዘበዝብ መነሾነቱም ሆነ የሕሳቤው ፍልቀተ ቅስፈት ለእኔ ነው ለዛም ነው ደስስስስስስስስስ ሲለኝ ምፅፈው ደስስስስስስስስስስ ባለኝ ጊዜ ማስታውሠው የዝብዘባዬ አንባቢ ጭብጨባ ደረቴን ሊያሳብጥ ቢዳዳኝም (አላሳበጥኩምን ' ቅቅቅ ) ታዲያ አተያዬ ፎቀቅ ሲል ይቀየራል የማክበሩና የአላፊነቱ ጉዳይ እስከጥግ ይንፏቀቃል ::

አንተ በምትደግፈው ደግሞ ልሂድ እበል አሉ ታዛቢ ነኝ አጨንቋሪ ነኝ ....እንበል አስተዋይ ነኝ እንበል .....እርጉምም መርማሪ ነኝ እንበል ......ደርሶ እንደአሕምሮ ማሕንዲስ የነፍሮይድን መላምት እንደጊዜቤት ሸምድጄ ሠዋዊና ቁሣዊ ተዛምዶን ጊዜና እስትንፋስ ቅመራ ብዬ ምክኒያታዊ ኮተቶችን አተናለሁ አሉ ....እንበል ነው ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ ይሄ ሁላሁሉ ውስጤን ሳንዠዋዥው ማኮብኮቤም አይደል ....በምናብ ልመጥቅ በዝግጅተ ሕሳብ ጲውውውውውው ልል እዛም ሆኜ ቅድም ጅማሬው ላይ ያሰከረኝን ልደርስበት ከዛም እንካቹ ብዬ ላቀብል .....
አዎ ያስኬድ ይሆናል ....መላምታዊ ጉእዛን እና እስትንፋሳን ጥንደ - ጭብጨባቸው ለንገር ይሆን ዘንድ መነሾነቱ ያጋጣሚ ስምዮሽ ተሹመው አንድ ጥግ ደርሰው እንደመግነጢስ የመሣሣባቸው ሚስጥር :::: ይሄ ይመስለኛል ወይም ነው ግን ባንተ <== ያቺ እዛ ሠዉ ሁሉ ሚጎርርበት ጊቢ ሆኜ አንድ መምሕሬ አራግቦ አራግቦ ያፈማት ትንሽ ድርቅና አለችብኝ አይደል መጩ ላይ አንድ የእውቀት ክፍል ነው ብሎ ፎተተኝ እንጂ ልክ ፒንክ ፍሎይድስ ግድግዳው በሚለው አልበማቸው ውስጥ ለጡቦቹ ተምሰሌትነት ባዜሙበት ሊሪክስ ውስጥ እንዳለው ጭብጠ -ሕሳቤ መሆኑ መሠለኝ ...ለነገሩ ረፍዳ አሁን ሆነች ' ...
አንዳንዴ ደግሞ እርጉምነት ሲያምረን ስለሠው ብለን ሠዉን ምናብ አድርገን እንቀዳ የለ ...ስለ ብሎ መሠዋት ስለ ብሎ መናገርና መዋሸት ዓይነት
ታዲያ ከላይ ያለው ንብርብራዊ ዝብዘባ ሁሉ ንሑስ ርዕስ ውስጥ እንደተጠቀሠው ውበታዊ ድባቡ ሁሌም የደጁን ፊት ገፅ መቆጣጠር አለበት ::ከሚሉት ራሴን ፈርጄ ነው :: ለውበትና ለቀልቤም የመስገዴም ጉዳይ ምድራዊ አጢያቴን ያበዛው አንዱ ግራክንፌ አይደል <== ኢጎና ሱፐር ኢጎ ብዬ ቀበሌያዊ ስነአሕምሮ አገላለፅ ከምል ብዬ ነው ቅቅቅ
ኃሙስ ሳላንኮራፋባት እንዳታመልጠኝ ደግሞ ሠሞናቱን የተሳልኩትን ስለት አያስረሳኝንጂ ድንቃድንቅ ሕልሞች ይጠብቁኛል በእነዛ የምንም ዓለም ውስጥ ያሉ ቅርድዶች መሀል ሆኜ ነፍሲያዬን ''ክሪሽና የኒው ኤጅ ''ዜማ እያንሳፈፍኳት በቃ መንሰፍረር ሁሉ ጀምሪያለሁ (መንሳፈፍ +መብረር ) ታዲያ ላንድ ቀን ዕንቅልፍ እንዲህ የተደሰትኩት ለዘለኣለሙማ ! ብሎ ሞትን እንደናፈቀው ዓይነት ሕልመ -ፍቅር አይደለም ....
ውቅሽ ደግሞ አዲስ ቤት ከፍቶልኛል ገርበብ ያደረግከው ቤት ውስጥ ዘው እንዳይሉብህ ብሎኝ ቅቅቅ የሱ ልጅ ግን መንቀዥቀዥ .....መንቀዥቀዥ ሚያምርበት ውቅሽን አየው ዥው ....ይልና አንድ ሁለት ቃል ጣል አድርጎ ላጥ :: ዘናጭ ልቦና እንዳለው ከመንቀዥቀዡስጥ ካነበብኩኝ ቆየው አሪፍ ነው ውስጤ ለእሱ የመሰልኩትን ቀለምና የሆነ ኤለምንት ታይቶኝ ....

ኸረ ኸረ ኃሙሲቱን ላንኮራፋባት ነገ ደግሞ ዘኪዮስን ሆኘ እመጣና እቺን አዲስ ቤቴን ............................
ታየኝ

______::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘኪዮስ 5

አዲስ

Joined: 13 Aug 2006
Posts: 37

PostPosted: Fri Aug 17, 2007 12:33 am    Post subject: Reply with quote

ጤንስ ?......(<==ጤና እንዴት ነው እንደማለት )
አሁንም በትኩሡ ለማወቅ የመስገብገብ ትኵሳት ውስጥ ሳለን የሆነውን መንዘፍዘፍ ላወሳው ነው የትላንቱማ አልተቋጨም የተቋጨ ሃሣብን ሠዓሊ አይወድም እንዲሉ .....አለያማ ሣይንሥ ሆነ ሣይንስ ደግሞ ሞት ነው ጥበብ ግን ሕይወት ነው .... ሳይንስ ጉበትን እና ሽንፍላን ቆጥሮ የስትንፋስን ቧንቧ ነግሮ ያዘጋጉን መንስሄ ካለቀ በኌላ አሊቬ ..ዴርቺ ስለነኳክብት ጉእዝነት ደግሞ እስከጥጉ ሊያወራ ይዘጋጃል ....ጥበብ ግን ቢሞትም ይነሳል ሀርጎም ይመጣል ...ብዙ ብዙ ...ሆኖ ይቀጥላል ምንኛ ፍንጭ ነበር እቺን አስፈንቅሎ ያስጎረጎረኝ ????
አዎ ዛሬ በዘኪዮስነቴ የቅድሙን እንቶፈንቶ ያወሳዉት አንድ ሰሞን ላሳድጋት የሞከርኳት ሸረሪት ትዝ ብሎኝ ነው ድንቅ የሆነ የምራቋን ውቅር አድንቄ አባበልኳትና በወረቀት አንሸራትቼ የማርማላት ብልቃጥ ውስጥ ዶልኳት ወገቧ እንደስምንት ቁጥር ሆኖ ቅልጥሞቿ ረጃጅም ነበሩ አንዳንዴ የሤትን ውበት የሚያደንቁ ለምን ሸረሪትን እንዳልመሰሏት ...ታዲያ ክዳኑን በሚስማር በሳሳውላት ትንፋሿ እንዲወጣ ::ከዛ ዝንብ እያደንኩኝ ስመግባት ቆየው በሶስተኛው ቀን ሳያት የእግሮቿን መፈራገጥ አስተዋልኩትና ኃይላቸው መቀነሳቸውን አየው ...ምናልባት የራሷ ማሕበራዊ ኑሮ ይኖራት ይሆናል ተካፍላ መብላት ይሆናል የለመደችው ....ምናልባትም አንድ ዝንብ ለሳምንት ይበቃት ይሆናል እኔ ግን የዝንብ ዓይነት መርጬ ነበር የሠጠዋት ወርቅማ አረንጓዴዉን ሲጮህ ድምፁ አምፕሊፋየር ያለው ሚመስለዉን ....... ቀጫጫ እግሮች ኖሮት አመዳም ክንፎች ያሉትን ...እንዲያዉም እሷን ልመግብ ስል ነው የዝንብ ዓይነቶችን ያጠናሁት ታዲያ እነኛ ሁሉ ሰንጋ ዝንቦች እሷን ሊያታልሉልኝ አልቻሉም ብልቃጡን ከፍቼ ስለቃት ግን የዳከሩ እግሮቿን ለማጠፍና ለመዘርጋት እንደተቸገረች ሁሉ እየጎተተች ሄደች :: ነፃነቷን መንፈጌ ተሠማኝ እየው ከዛን ጀመሮ ነፍስ ለማጥፋት በጣም ነው ምፈራው :: ግን ያቺ ዝንብ አካባቢያዊ ስነተዋልዶና ጉዕዛዊ ትስስሮች ምንኛ በራሳቸው የተቀማመሩ ተፈጥሮ መሆናቸሁን አስገንዝባኛለች አሁን እኔ እንደዛች ሸረሪት የሆንኩኝ ሁሉ ይመስለኛል የሸረሪት ቋንቋ በቻልኩና በሸረሪትኛ ይቅርታ በጠየቅኳት ... በወቅቱ አጭር እድሜ እንዳላት ባውቅም ያሟሟት ምክኒያቷ እኔ እንዳልሆን ስሻ ነበር ::
ይሄ አሁን ደግሞ ምዘበዝበው በልጅነቴ ስለገደልኳት ወፍ ነው :: የወንድሞቼን የተለጣጠፈ የብስክሌት ካለመዳሪ በምላጭ እንደታላቴሊ ተረተርኩና መንታ እግሮች ያሉት እርጥብ እንጨት ፈልጌ በአሮጌ የቆዳ ቀበቶ ቁራጭ በሽቦ እየጠመጠምኩኝ በወቅቱ ከሠፈሩ ሲወዳደር እኔ ነኝ ያለ ባላ ሠራሁኝ ባላዬን መመረቅ ነበረብኝና ዛፍ ፈልጌ የአዋፍ ዘር ማለም ጀመርኩኝ ድብልቡሉ ትንሽ ድንጋይ ከጎናቸው ዥውውው ብሎ ሲያልፍ በርግገው ይበራሉ ሲበሩ በጣም እናደዳለሁ መሳቴ ቀሽም እንደሆንኩ ሁሉ የተሸናፊነት ስሜት ይሠማኝ ነበር እንዲሁ በየጥጉ ያሉትን ትንንሽ ድንጋዮች በባላዋ እያሳፈርኳቸው ፈጀዋቸው ግን እርግብ ቀርቶ ቅጠል መበጠስ አልቻልኩም ...አመሻሹ ላይ አንዲት የተዘናጋች ወፍ አገኘሁና ተስፋ በቆረጠ ስሜ ድንጋዬን ዥውውውው ሳደርግ እግሬ ስር ደም ለብሳ ዱፍፍ !! አለች ባላዉን ወርውሬ ያዝኳት በድኗ አንገቷን መሸከም እንዳቃተው ሁሉ ወደ አንድ ትከሻዋ ድፍት ይልባታል ፊቶቿ አካባቢ ያሉት ቢጫ ቀለም ውብ ነበሩ ሆዷ መጠነኛ ሙቀት ነበረ ድንጋዩ የቦደሰባት ትከሻዋጋር ያሉት ስስ ትንንሽ ግሪ ላባዎች በድኗን ተሰናብተው ሊበሩ እንደተዘጋጁ ቆመዋሉ ...በጣም አሳዘነችኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ ነፍስ ማጥፋት እንጂ መመለስ አለመቻሌ በጨቅላ ሕሳቤ ንድድ አለኝ :: ቀበርኳትና ባላዉን ለንኩሮ ሚንቀለቀል ዕሳት ውስጥ ጨመርኩት እነኚያ ስለንፍስ የመኮነን ጨቅላ ድንግል ተመክሮዎች አንድ ሰባኪ ልቤን አድርቆት ከሚነግረኝ አስር ጊዜ የበለጡ ናቸው ምናልባት ሰማይ ቤት ስሄድ ከዛች ሸረሪት ጋር ሆነው ይጠብቁኝ ይሆን ?????????
አንዳንዴ ዘክዪስነቴ ውስጥ ያለ ገደብን ያለመሻት ፍላጎቴ በጥያቄ ምልክት እንደድለ ቢስ ዓሣ ከውስጠ ባሕሬ ጩልቅ አድርጌ አወጣውና ሲፈራገጥብኝ መልሼ እለቀዋለሁ ......በሊሪክስ ሕሳቤዎች ልቤ ይደልቅ የለ ....? የኢኒግማዎች ሴንሹዋሊቲ አልበማቸው ውስጥ ፑሽ -ሊሚት ሚለው ሕሳቤ አንዳንዴ ስጋዬን ያነርቨውና ነፍሴን ያጦዙታል ድምፁን ከፍ አድርጌ ካንዳች መላምት ጋር ስጯጯው ገፍትሬ ከውስጤ ላወጣው ምታገለው ገደብ ወይም በማሕበረሠብ ወይም ባስተዳደግ ተሸምቅቆ ይይዘኛል ያንን መበጠስ እብደት ነው ብለው የሰበኩኝ ቤተሠቦቼን ላለማስቀየም ይሁን በመስማት አንገቴን እደፋለሁ ግን ሚንቀለቀለው ውስጤ እንደተዳፈነ ዕሣት አለ ይኖራልም ታዲያ ከዛ ተሎክሦ አይደል አንዳንዴ እንደዚህ ቤቴ በጣም እንደምወዳት ቤቴ ውስጥ የንብርብራዊ ወዥባራ ኃሣቦችን ማንጠባጥብበት በቀደም ዋንቾን ሆኜ ያነሳዋቸው ሦስቱ አውታረ አወለያዎች ባላንስ እንዳደርግበት ይጠቅሙኛል ዮጋኛ ይሁን ወይም በሕገ -መግነጢስ (ሎው ኦፍ አትራክሽን ) መንሸዋረር ...ዋው ብቻ ይሄ ቅስፈት ዘኪዮስነቴን እንዴት አድርጎ እንደሚያስደስተኝ .....

እስቲ ደግሞ አርብ እየሆነ ነው ነገ መልካም ያልሆነ ቀን ይጠብቀኛል ድሮስ ለጌታ ያልሆነ ቀን .... ግን ትኩሡን አርብ ከቻልኩኝ ማታ የጀመርኩትን ሕልም እያየሁበት ላንኮራፋ ስጋዬን ዘፍዝፌ በነፍሴ ልክነፍ ታዲያ እቺን ቤት ነገ ደግሞ ዋንቾን ሆኜ እምቦጫረቅበት የለ ቅቅቅ ልክ ውጪ ተወልደው ለቫኬሽን አዲሳባ ይመጡ የነበሩ ጩጬዎች ጭቃ ሲያገኙ በደስታ እንደሚያንቦጭርቁት ዓይነት

ካሊኒታ ::

Last edited by ዘኪዮስ5 on Sun Aug 19, 2007 9:25 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Aug 18, 2007 1:52 am    Post subject: Reply with quote

''መኪና ትወጂያለሽ ሲሉኝ ሰምቼ ...ገደል ገባውልሽ ብስክሌት ነድቼ '' ቅቅ እቺ አንድ ሰሞን አዲሳባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማህከል ያቀነቀኗት የቮካል ዜማ ነበረች ብቻዬን ስሆን አፌ ላይ ተመጣለች ...እቺ ዜማ እና ሌላ የእነሱው ''ባዶ ቤት በክረም ባዶ ቤት ለቅዠት ...'' ምትለዋ አንዳንዴ ወፈፍ ታደርገኛልች
ዋንቾን ሆኜ እቺን ዜማ እያዜምኩኝ የመጣዉት ድምጻዊነት አምሮኝ ነው ? !!!! አይደለም አዎ ብስክሌቶቹን አስታውሼ ነው :: ውስጤ ብሽክሊሊት በጣም ልዩ ስፍራ አለው ላዩ ላይ ያሉት እያንዳንዳቸው ኤለመንቶች በስውጤ ሲምቦል አደርጋቸዋለሁ ክብ ነገር እውደ አይደል ሽክርክሪት ሙጠምጥሚት ምናምን ....ስጋን ከነስፍስያ ጋር አስታርቆ ውስጠ -ኃይልን ሚዘውር አንዳች ታሕምራዊ እስትንፋስ አለን ...ያን አንዳንዴ እልህ እንለዋለን አንዳንዴ ዛሬ ሴይጣኑ ተነስቶበታል እንላለን አንዳንዴም ይከፋና በደመንፍስ ተጀቡኖ ባክኖ ይቀራል ያቺ ብስክሌቴይቱ ስለሕያው ትንፋሠ -ኃይሌ ምልክትነት አንዳች መለኮታዊ ነገር እንዳዘዛት በቃ ከጥግ እስከጫፍ ትይዘዋለች ...ልክ ኮምፒውተሬን ዲፈራግመንት እንደማደርገው እኔ ውስጥ ያሉትን አሬንጅመንቶች የተሰባጠሩትን ትጠቁመኛለች ምናልባት አስማት ይሆን ? እንጃ ለነገሩ አስማትን ራሱ አስማት አይደል ሚፈጥረው
መች መሽከርከር ይቆምና አንዴ የቁም አንዴ የቄንጥ ስንፈናጠጥ በመንገድ ሚያጋጥሙንን ሁሉ ምናየው የግዴለሽዮሽ ከሆነማ በግድንግዱ ተሸውድን ....ሚገርመው ባልጠበቅኩት ሁናቴ የዚች ውስጤ ያለችው ብስክሌት ጉዳይ ለራሴም ግራ የሚሆንብኝ ጊዜ አለ :: አንዳንዴ አንድ ሕሣብ ውስጤ በወለድኩኝ ጊዜ ልቦናዬ ሚቀርፃቸው ምስሎች ውስጤ ያሉትን ፋይል ያዛቡታል : መወዣበር ልበለው ይሆን
አንዳንዴ ደግሞ ውስጤ የምስል ጋጋት ያንጋጋል ይሄ መጥፎ ፔሬድ ነው ለምንም ነገር ድግግሞሽ ብሎ ቅኔ ሕሳቤ ክምችታችንን ሚደበድብ መዶሻ ይመስለኛል ...የቱጋር ነኝ አሁን ....ፔዳሉ ላይ ነኝ መሠለኝ ...ለዛም ነው አንዳንዴ ሚዳግቱ ነገሮችን ውስጤ ሚሻው .... ያገራችን የኤኔትሬ ሹፌርስ ቢሆን ማርሽ ሳይቀይር ረጅም መንገድ ከሄደ ዕንቅልፉ መጥቶ ላደጋ ሚጋለጠው ለዚህ አይደል ...እናም ምስልን እንደማስታረቅ ....መስመርን እንደማሰባጠር ...ብረሀንን እና ጥላን እንደማዋሀድ ...እይታን እንደማጣፈጥ ...ምን ሱስ ይኖራል :: ለዛም አይደል በዚች ጣፋጭ ቤቴ ስወዣብር ነርቮቼ ተንሳፈው ሊያርጉ ሚደርሱት :: <<እምጱዋ !>> የሆነ መንሳፈፍ
የሎሪና ማክኔትን ሚስቲክ ድሪም የሚል ኒው ኤጅ እየሠማው በደቀደቀ ምሽት መስኮትና መጋረጃን ብርግድ አድርጌ ሙሉ ለመሆን እየተጋች ያለችዉን ጨረቃ ሳይ ሕልምን የገዛዉት ያህል ይሰማኛል : የሠካራሙን የካርሎስ ቲኦሪ ሕልምን ሴታፕ ስለማድረግ እንደእኔ እንደሰሞንኛው የዘበዘበዉን ጭብጥ የሞከርኩ ሁሉ ይሰማኛል ....
ይታያቹ እነኚህ ቦታ ሁሉ ምታፈናጥጠኝ ያቺ ብሽክሊሊት ነች ...መዘውሯ እንደእታዬ መንጎድ ነው .... ጎማዋ እነኛ አወሊያዎቼ አሉ አይደል ወይም ኑሮ ናቸው የሚመቹና የማይመቹ ግን ሚገሰግሱ እንደብሽክሊሊት ወደውኃላ የማይፈነጠጡ ....ወደሶስት መሐዘን የሚያደላው መቀመጫ ለጊዜው የያዝኩት ሕስቤዬ ነው ...ግን ድፍርስ ሕሳቤ ...የማይታይ ...ጠርቶ ድጋሚ አተላ የሚሆን ግን ደግሞ ሚጠራ ....አለ አይደል ጥርርርት ' ባይል ለዚህ ነው ውስጤ ያለችው ብሽክሊሊት ብዙ ጊዜ መሪዋና መቀመጫዋ የሚደበዝዙብኝ ወይም ማይታዩኝ .......ፍሬኗን በጥሼዋለሁ ...ትላንትና ዘኪዮስነቴ ስለግደብ ያለኝ አለ አይደል ....አንድ ቀን ነሸጥ ሲያደገኝ !! የታባቱ ::
ዛሬ ቀኑ እንደማይመቸኝ ትላንትና ታይቶኝ የለ ትንሽ እዚ መጥቼ ስዘበዝብ ተሻለኝ 'ንጂ እስቲ ደግሞ ወደነገ ለመሮጥ አልጋዬ ውስጥ ልወተፍ እቺን ብሽኪሊሊት የመያዙ አቅም ካለኝ እንጃ ግን እኔጋ የሚበቅል ንግርት እንደአረም ባጭደው ደስነው ሚለኝ ስለነገ ውሎዬ ስሜት የመተንቤይ መጥፎ ልምምዴን እጠለዋለሁ ሠው እንዴት ለራሱ ቡዳ ይሆናል ...ደግነቱ ቅዳሜ ሞኝ ነው ሰዉ እንዳዘዘው ነው ታዲያ ከዘኪዮስ ጋር ቀጥሮ አለኝ አይደል ነገ ...ስለክፉም ስለበጎም ቀኖች
<<አሪጋቶ >> ልበል ይሆን
አዲዮስ ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘኪዮስ 5

አዲስ

Joined: 13 Aug 2006
Posts: 37

PostPosted: Sun Aug 19, 2007 11:13 pm    Post subject: Reply with quote

አንዳንዴ ስለአንድ ነገር ማሠብን ራሱ ማሠብ ሚያዘው አንዳች ያልተገለፀ ኃይል ሚኖር ይመስለኛል ....
ትላንትና የት ነበርኩኝ ? አዎ ምንም ውስጥ ተወዝፌ ዕንቅልፋትን እያጠራቀምኪኝ ነበር ዘውትር ዊኬንድ አላጋዬ ትሠለቸኛለች
ዛሬ ውስጤ ዜማዎች ተተራምሠው አሰባጥሬ በጆሮዬ ቀልብ ላስተካክላቸው ብሻ አንዳች ማይገባኝ ሙዚቃ ሆብኝ የደም ዝውውሬ ትር ትር ትር ሲል ሕዋሳቶቼ ሲራወጡ ከውጪ ሚሹት ነገር አለ :: ሶፍትዌር አርድ ዌር እንደሚያስፈልገው ለዚ አስረጂ ዋርካ ፍቅር መሄድ ይኖርብኝ ይሆን ቅቅቅቅ እናም አንዳች ዜማ መስማትን እሻለሁ የኢኒግማን ሙዚቃ ደምስሬ ስከተው በሕሳቦች ጎርፍ ወደፊትም ወደውኃላም ያከንፈኛል በካርሎስ ሳንታና ጊታር ውስጠ -ጅማቴን ድውውው ሳደርገው አንዳች ኃይል እሞላለው በግሪንዴይስ ሆት ሮክ አሕምሮዬን ስንጠው አንዳች ያልደረስኩበት ስነ -አስተሳሰብ ቦዝዞ ይታየኛል በፒንክ ፍሎይድስ ሊሪክስ ስነ -ግምቴን እዘክራለሁ ...ብቻ ሁላሁሉም ሆኜ ያለዜማ ከሆንኩኝ እንደቀን ጨረቃ ይሆንኩኝ ይመስለኛል :: አንዳንዴ በጊታሮ ቅንብር በኤኒያ ለስላሳ ድምፅ ሌላ ዓለም እሮጣለሁ :: እነኚህ ሁላ ኒውኤጅ ሙዚቃዎች እንደኤዢያዊያን እግሬን አንሰላስዬ በዮጋስልት ሜዲቴት ባላደርግም የመስረፅ ኃይላቸው + ከእኔ ዜማዎችን የመቀበል ጋር ተደምሮ ስጋዬን አንሳፍፋለሁ ::
ሙዚቃዎች መስመሮች ናቸው በራሳቸው የተለያየ መልዕክት ያላቸው ምስል የመፍጠራቸው ኃይል ፈጣን ነው ለእኔ ለዘኪዮስነቴ ወደጨቅላ ምናቤ ስሮጥ በዓይኖቼ መጠን ውስጤ የቀረጽኳቸው ጉእዝ እና ፍጡራን ዕይታዎች ከተለበዱበት ጥጋጥግ ከተወሸቁበት ውስጠ -ጥጌ ስር ባንዳች መስሕብነት ሲንፏቀቁ ማየው በጆሮዬ በሚገቡት ምስሎች ቅስቀሳ ነው ...አለያም በፀጥታ ሙዚቃ :: ነገርን ጨዋታ ይኮረኩመዋልና ነው ወጌ ባንድ ወቅት ምንን ፍለጋ መሆኑን ማላስታውሰው ቅስፈቴ በጨለማ የመቀመጥና በዝናብ የመራመድ ልምዴ በጊዜው የሚሰጠኝ ስሜት ምናልባት አሁን ባለኝ ውስጤን የማዳመጥ አቅም ባገኘው አንዳች የተዳፈነ ኃይል ይኖረው ነበር :: ስንቶች ቅስፈታዊ የገቡን እንግዳ ነገሮች
ገደብ በሚባል ነገር ተደምስሰው ይሆን ? ምናልባት አሁን ሲቪላይዝድኛ ብለው በሚያመልኩት መላምቶች ውስጥ በራሱ ድርሻ ሊኖረው የሚችል መዳረሻ ይሆኑ ሁሉ ነበር ...ማን ነበር የሚራመድበት ፈርቶ ሲያይ ይሰጠመው ?......
ደግሞ እስቲ ነገ ዋንቾን ሆኜ ምዘበዝበው ሕሣቤ ላምጣ ይሄም ያረጀ ያደፈ ወግ ነው ግና በጊዜው መነፅር ሲታይ ጥጋጥጉ ያላረጀ ይሆንና የመታደስ እድል ይኖረዋል ታዲያ ይሄ ሁሉ በዘኪዮስነቴና በዋንቾነቴ መኃል ውስጥ ያለው የመታረቅ ወይም በጊንጎ ሙሀር በመግነጢስ የመንዠዋዠው ብቻ ነው :: ቤቱ የእኔም አይደል ? ቅቅቅ
ቀለም ያለብረሀን ምን እንደሚመስል ዓይነት ሕሳቤ ወይም ከቀለሙና ከብረሀን የቱ እንደሚቀድም .......ታዲያ ምስል ላይ ነው ባለሁለትም ሆነ ባለሶስት አውታር ይሁን ብቻ ምስል ላይ ::

ያልተዘገነለት ሳምንት ከፊቲ ኮሳትሮ ቆሞ ያየኛል ያለው በራሱ ምንም የማድረግ አቅም አለው አይደል ስለሁልስ ክስተት መንስሄው ቀን መሆኑ ቀረ
ልሂድና ልማረክለት ::

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed Aug 22, 2007 1:31 am    Post subject: Reply with quote

ዓይኖቼን አፍጥጬ አንድ ምስል ሳይ እቆይና ድንገት ድርግም ሳደርግ አንዳንዴ የማየው ምስል የተገላቢጥዮሽ ይሆናል ኦብስኩራ እንደማለት ...አለ አይደል የካሜራ ነጌቲቭ ብንለው ሸላይ ገላጭ አበጅለት ይሆን ታዲያ ይሄ ምስል ሁሉስጥም አለ ለልቦና ገስግሶ ሲነግረ ልቦና ባክህ አታሹፍ ብሎ ስለሚሟገትን ' አንዳንዴ ዓይኔ ነው ? ብለን ዓይኖቻችንን እንደምናብሰው ......
ብረሀን እና ጥላ የመፎካከራቸዉን ያህል ከላይ ዘኪዮስነቴ ያነሳብኝ ሕሳቤ ውስጤን ዝብዝብ ያደርጉት የለ ታዲያ ...ጥላ በራሱ መሸፈን ነው ግን የዛምስል መከሰት ምስክርነቱ ደግሞ ሁለተኛ ድርሻው ነው ኮንትራስት ማለት ነው ::
ብረሀን ማናቸውም ዕይታዎች ላይ ሲያርፍ የነዛ ዕይታዎች ነፀብራቅ መልሠው ዓይናችን ውስጥ ይገባሉ በዛኛው ግልባጭ ምልከታዬ ደግሞ ማናቸውም ምስሎች ተደብቀው ካሉበት ውስጥ ብረሀን ባዩ ጊዜ የፉክክር ዓይነት በሚመስል ቀደመው ዓይኔ ውስጥ ይገባሉ ብረሀኑን በሰወርኩባቸው ጊዜ ደግሞ ከብረሀኑ መጥፋት ዘግይተው እነሱም ይሰለባሉ እቺ ሕሳቢዬ አምላክ ሠማይና ምድረን ፈጠረ ከሚባለው ካታጎሪ እንዳይሰነቀርብኝ በመፍራት ይሁልኝና ሁለቱን ለማስታረቅ ያህል እንዲህ ሕሳቤን ላንሸራሽር ....በገዛ ቤቴ ቅቅቅቅ ታዲየ ግን ይሄን ቤቴን የራሴ ነው ብዬ ስለተናገርኩኝ አይደል ሠዉ ማያነብብኝ ቅቅቅ ከደጅ ሳየውኮ ከዚች ቤቴ ይልቅ ውቂቾ ያበረከተልኝ ያስተያየት መድረክን ብዙ ሠው ጎብኝቶታል ቅቅቅ
የኔ ነገር የተ የት ወዣበርኩኝ ? አዎ ስለቀለምና ብረሀንም አይደል ምዘበዝበው ያለሁት ምንም ነገር ያለቀለም አይፈጠርም መቼም እነኚያ ቀለማት ደግሞ ቀለም ለመሆን ብረሀን መጎናፀፍ አለባቸው በአንጻሩ ብረሀን ራሱ ብረሀን ለመባል ቀለማት ያስፈልገዋል ዕይታ ያስፈልገዋል ከእይታና ከቀለማት ውጪ የሆነ ነገር ቢኖር እንጃ ....አስቤውም አላውቅም
አንዴ ነው ደቡብ ኮሪያ ሄጄ የተዋወቅኳት ልጅ ያለችኝ ትዝ አለኝ ድንገት ውልብ ላለችብኝ ከላይ ለጠቀስኳት ቅስፈታዊ የሕሳቤ መንቀዥቀዥ አንድም የምሳሌ አንድም የማስታወስ ነው ....እና እቺ ዓይነ ጠባቢቱ ጉብል ስለኃይማኖት አለመኖር ብዙ ብዙ ብላ ( በዚ አጋጣሚ ደቡብ ኮሪያ በዓለማችን አንደኛ ዕምነት የሌለባት አገር ናት ከዛ ቀጥሎ ሁለተኛ እዚህ እንግሊዝ )...እናም ስለሞትና ሕይወት ስናወራ እኔ ልጅ እያለሁ ሞቼ አውቃለሁ አለችኝ ...''እንዴት ?'' ብላት በቃ ሬሳዬ ሊሸኝ ካለ በኌላ ነው የነቃዉት ''ምን ይመስላል ?'' አልኳት በጢንጡ በማመን በግድንግዱ ባለማመን እያየዋት
''አሁን እዚህ ምድር ብረሀን አለ አይደል .....እዛ አይቼ ከመጣዉት ጋር ሲነጻጸር ይሄ ጨለማ ነው ....እዛ እጅግ በጣም ብረሀን ነው ግን ዓይንህን አይወጋህም ''አለችኝ ....ሞትን ለሚናፍቅ ሂደሽ ሸውጂ አልኳት በሆዴ እናም ዛሬ ያንን ብረሀን ዝም ብዬ ስስለው አንዳች የተለየ ይሆናል ብዬ ገመትኩኝ አለ አይደል ብረሀን ለመባል ቀለማት የማያስፈልጉት ኮንፊደንሻል ወይም ኢንዲፐንደንት ላይት ልበልና ልመዝግበው ይሆን ቅቅቅ የሆኖ ሆኖ ግን ስለብረሀን እና ቀለማት እሽቅድድሞሹ ስመለስ የዶሮና የእንቁላሉን አድርጌ እንዳላንጠለጥለው ቀለማት ሚቀድሙ ይመስለኛል ለመከሠታቸው ለዓይናችን ዕይታ ግን ብረሀን ይቅድም ይሆናል
በሣይንስኛውም ስንሄድ ብረሀኑን በፕሪዝም ስናየው የቀለማት ውሕደት መሆኑን ነው :: ታዲያ በሠሙ የዚህን ያህል ከተንሰፈረርኩኝ በወርቁ ደግሞ እስቲ ትንሽ ልቀዣበር ብረሀን ዕውቀት ነው ቀለማት ደግሞ ችሎታ ነው :: ሁለቱም ያንድነት ልዩነታቸው የገጠጠ ነው :: ለቀለም ጨቅላ ሣለው ድንግል እርሳሶች ንፁ ላጲስ ይዤ ደጅ ስጠና እንዲህ ተብዬ ነበር ''አንተ በችሎታ ትበልጠናለህ በእውቀት ግን እኛ እንበልጥሀለን ....'' ችሎታ ማለት ትላንትናን ማሸነፍ ትላንትናን ጥሎ ዛሬን መብለጥ እንደማለት ነው :: በግስጋሴ ውስጥ የሚገኙ የንሑስ ለውጦች ክምችት ....እውቀት ደግሞ የሁላሁሉ ግንዛቤ መዳረሻዉን መተንበይ ጭርስ አድርጎ ታዲያ ሙጥጥጥ አይደለም የተሟጠጠ ለትማ ቪያ !! በቃ በቀይ ቀለም ሠክሮ ውስጥን እንደመረበሽ ያስፈራል አዙርኝ አታዙረኝ ብሎ ሚዛን በማይጠበቅ መልኩ መንገዳገድ ይመጣል :: ትልቁ ውስጠ -ጥበብ እነኚህን ሁሉ ማስታረቁ ላይ ነው ከዛ ! እሱ ' እሳት የላሠ ነው ይባልና የደራጎንን ሹመት መውሰድ ነው ያንን ማን ይጠላል ቅቅቅ ወይም እንደማላገጥ ዓይነት ለዚህ ነው የተፈጠረው ተብሎ የመሾም ....እነኒ አረፋፍጄ ያነሳዋቸው ሁለትነቶችን 'ኳን ምንም ጭቅጭቅ የላቸዉም ችሎታ ይቀድማል ዕውቀት ይከተላል ችሎታ ውስጥ ዕውቀት ላይኖር ይችላል ዕውቀት ውስጥ ግን መጠኑ ይቀንሳልን ' ችሎታ አለ :: ታዲያ አቋራጭ አላቸው ማለት ለሎች የዳገቱበት የግድ ላይሉ እንደመላ የመታደል .....
ሢገባን በቃ አለ አይደል ግልፅ ሲልልን እንዴት ነው ውሃ ዋና ስንችል ያልቻልንባቸውና የፈራንባቸው ጊዜዎች ያበሳጩን የለ ? እንደዛው ኸገለ ' የገባው ነው ስንል ግን ትንሽ የኔይቱን ቃል ያራክሳታል ልበል ...በተገናኝቶ መስመር ያልተላለፍን ብዙዎች እንደምንኖር ቡዳ ልሁን ? ''እንጃልኝ !!''

ዛሬ ደግሞ ዜመኛ ነፋስ አለ ሕልሞቼን ሊያጅብልኝ አስፈስፎ የእኔን መተኛት እየጠበቀ ነው ::

ጂንኩዬ !!!

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ndave

ኮትኳች

Joined: 22 Sep 2003
Posts: 436

PostPosted: Wed Aug 22, 2007 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

ሄይይ ወንድም ጋሼ እንዴት ሰንብተክልኛል ? በዚህች አጋጣሚ ሰላም ልበልህ እንጂ ::

አቦ ተመችተከኛል አትቦዝን !!!

:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዘኪዮስ 5

አዲስ

Joined: 13 Aug 2006
Posts: 37

PostPosted: Thu Aug 23, 2007 12:53 am    Post subject: Reply with quote

መጣው ደግሞ ዘኪዮስን ሆኜ .....
ይሄንን ስፅፍ የቺሊ ወይን እየጠጣው ነው ቅቅቅ ቅንድብ ያቆረፍድየለንዴ
ዛሬ መስመርና ሚስጥሩ ውስጤ ቢያጭርብኝ ነው የንፉዲዲ ብዬ ዝባዝንከዬ ውስጥ ልወላከፍ አመጣጤ መስመሮች ምናልባትም እንደየሠዉ የተለያየ መላምትነት ሚሰነቅር የተለያየ ምልከታ መኖሩ የግድ ነው :: ታዲያ 5ተኛ ክፍል ማቲማቲክስ መፀሐፍ ላይ ያለው አካዳሚካል መስመሮች አይደለም አይጠጌ እና አይነኬ ተብሎ እነአስምቶትን ሠሞንኛ አዳዲስ መዝገበቃላት የተቸራቸዉን ማለቴ ነው ...አለ አይደል የእኔ የራሴ መስመሮች የአግድምና የቁልቁል መዳረሻ ዲቃላዎች ይሆኑና በራሳቸው ሕሳቤ ውስጥ የራሳቸዉን ትርጉም ሊያቀብሉ የተሰባጠሩ ዓይነት ..... በሥዕልኝ የምንስማማበት ነገር አለ አግድም መስመር ፅናትን ሲገልጽ ቁልቁል መስመር ደግሞ ጥንካሬ ይገልፃል እንደሚባለው አመጣጡ ከሀይማኖታዊ መላ ምት እንደሆነ ይነገራል ማለት ....በመስቀሉ ምስክርነት የመስቀሉ አግድም ማለትም የጌታ እጆች የፊጢኝ የተቸነከሩበት የስቃዩን ፅናት ሲገልፁ የቁልቁሉ ደግሞ እግሮቹ የተቸነከሩበት ጥንካሬዉን መቻሉን ብቃቱን ይገልፃል (ያስኬዳል ) ...ታዲያ ይሄ አባባል ግንዛቤው ላልኖረ አያዪ (ተመልካች ) በትክክል ይግልፅለት ይሆን ሆይ ? ...ለዚህም አይደል የዘመናዊ ሥዕል እና ተመልካቹ ሆድና ጀርባ ሆኖ የቀረው ባንድምታ መተበቡ ለሕሴትነቱ ትሆነ ዘንዳ ...ማለቴ እንደያን ሰሞኑ ዝብዘባዬ ፐርሰናል ፈንክሽን ብለን ጥበብን ለሕሴት ይቅደም ላልን ውስጣችንን ለመናገር ገላጪ ነው :: እስቲ ሕሳቤዉን በመጠኑ ቦርቀቅ ላድርገዉና ቀጥዬ ዋንቾን ሆኘም ድምዳሜ የመስጠቱን ሳመቻች ......እናም ትንት ይመስለኛል እንጃ በእኔ የእድሜ ዘለላን 'ኳን ብዙም አልደረስኩበትም ብቻ ሕፃን ሳለው እሕቶቼና ወንድሞቼ ክፍላቸው ውስጥ ሚሰቅሉት የሆሊዉድ ፊልም አክተሮች ...እነ ጆንትራ ጥቁር ቦዲ አድርገው ....እነቻኩነርስ ክላሽ ይዘው እነራምቦ ስቴኪኒ ባፋቸው ሰክተው ...ምናምን ያሉትን ዓይነት ፖስተሮች አንጋደው ይሰቅሉ ነበር .... ታዲያ ምንን ፍልርጋ ነው ማለቴ ቀጥታውን ትተው ሥዕሎቹን አንጋደው የመለጠፋቸው ...አላዳመጡትን ' ውስጣቸው አንድ የፈለገው ነገር አለ ወጣ ያለን ነገር የመሻት ወይም ...እንጃ ብቻ ... መስመሮች እንደቀለማት ሁሉ በራሳቸው የመናገር አቅም አላቸው ለተመልካቻቸው ስነልቦናዊ ግንዛቤን የማጨበጥ .......ታዲያ ይሄ ሁሉ ስለትል መስመሮች ነው ማወራው ....
ምስል በራሱ የመስመሩች መሰባጠር ነው ወደዕይታ የመራቅና የመቅረብ .....የመክበድና የመቅለል እነኒ ሁሉ የመስመር ንግርቶች ናቸው ...ስለፐርስፔክቲቭ አንስቼ ትንታኔ የምስጠት መፈልግ ሆኖብኝ ሳይሆን መስመሮች ለእኛ ምን ድርሻ አላቸው በሚለው ሕሳቤ መንሸራሸርን የመፈለግ ነው ::
መስመር ሲነሳ አንድ ነገር ትዝ አለኝ መጣው

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Aug 28, 2007 1:43 am    Post subject: Reply with quote

ባለፈው ስለመስመሮች _____ገር ዝባዝንኬዬን ስዘበዝብ ቆይቼ ፖስት ሳደርገው ተሰለበ ለዝባዝንኬ ደግሞ ትናደዳለህ ወይ ? ብዬ ራሴን አጃጅዬ ዝምታዬን እንድቆሎ እየቃምኩኝ ከዋርካ ወጣው ደግሞ ሠንበቱን አውሮጳዊ ዋርከኞች አልተፈቀደላቸዉም ብለው ወጋ ወጋ አድርገዉን የለ ቅቅቅቅ ጠፍቼ ከረምኩኛ ምን እናድርግ ዝቅተኛ ኑሮ ይዘን ሰንበትን መቀላቀሉ አንገታችንን አስደፋንና እቺን ምወዳትን ቤቴንን 'ኳን አጮልቄ ሳላይ .....ግን አለ አይደል ቢያንስ የግሌ ፒሲ እንዳለኝ ለመጠቆም ገባ ብዬ ነበር
ጥሎብኝ የቀባጠውርኩትን መድገም አይቀናኝም በቃ ሁሉ መስመር ቪያ ! ዘኪዮስነቴን ይቅርታ ልበልንጂ አንዳንዴ ራሴን ይቅርታ ስል አስጠንቅቄው እሺ እላለሁ ራሴን ለራሴ ፎርጊቭ አደርጋለሁ ዳሩ ከራስህ ስትታረቅ ነው አምላክም ሚረዳህ ይላሉ የሐይማኖት ሳይንቲስቶች ::
ዛሬ ጠሐይቱ ሸላይ ነበረች ካርኒቫል ሳይ ውዬ መጣው ዕይታን ፊድ ማድረግ ጥሩ ነው ለወራት ሚሆን ዕይታ ውስጤ አለ :: አንድ ነገር በዛው አስታውሼ የሽኩርሚሚት ፈገግታዬ በልዝብ አልኩት
በፊት ነው ፎርሞችን በኪነ -እይታችን ለውስጠ -አፅንዖዎታችን ኮንቨርት ስናደርግ አለ አይደል ዓይነ ግቡ የሆኑት አንኳር ዕይታዎች በግርድፉ ከፋፈለን መንደፍ ስንጀመር ውስጣችን ሊያይ ሚታገለው ነገር ነበር ....እናም ያኔ በጠዋት ተነስቼ በታክሲ ስሄድ ወይም በእግሬ ስኳትን ጡት ብቻ ካየው ቀኑን ሙሉ ጡት ሳይ እውላለሁ ....ትልቅ ...ትንሽ ....የተራራቀ ..... የተጠጋጋ ....የላላ ....የተወጠረ .... የቆመ .....የተኛ ....የሠፋ ...አቤት ብዛቱ ለጉድ ነው እዛው ልብሳችው ውስጥ ሆኑ እይዘለለ በደረታቸው በኩል ሊያመልጥ ሚታገል ሁሉ አለ :: በተለይ ቆሎ የሚሸጡ እምቦቃቅላዎች ጡቶች አይረሱኝም ....
እንደዚሁ አንዳንዴ ጆሮ ማየት ከጀመርኩኝ ያገር ጆሮ ሳይ እውላለሁ የጆሮ ዓይነቱ አበዛዝ እራሱ ግርም ነው ሚለኝ ያንዳንዱ መዘርጠጥ ....ያንዳንዱ መስፋት .....አንዳንዴማ ለጢቢጢቢ እንደተቀጠፈ ቅጠል ሙሽሽ ያለ ሁሉ ማይበት ጊዜ ነበር :: ያንዳንዱ ደግሞ ከኣናቱ ሾል ይልና የቀንድ ሙድ አለው :: አንድ ቀን እንዲሁ ጆሮ የማየት ፕሮግራሜ ዕለት ሚኒባስ ውስጥ ያንዷን ጆሮ ሳየው ፍፁም ውብ ነበር አለ አይደል አጠቀላለሉ ...የቅጠሎቹ ቅርፅ ይውስጡ መስመሮች መስተካከል ...በቃ ብቻ የተዋጣለት ጆሮ አየው :: ቀስ ብዬ ስኬጅ ቡኬን አውጥቼ ስኬች ሳደርግ አይታኝ ግልምጥምጤን ስታወጣኝ ''ጆሮሽ በጣም ያምራል '' ስላት ታክሲው ውስጥ ያሉት ሁሉ ከትከት ብለው ሳቁብኝ ...አሁን እስቲ ምናለበት ጆሮ አንድ የሠውነታችን ክፍል አይደል ...ጥርስሽ ያምራል ....ዓይንሽ ያምራል ከንፈርሽ ያምራል ይባል የለ ...ታዲያ እኔም ጆሮን ነው ያደነቅኩት : ካምስቱ አውራ ሐዋሳት ውስጥ አንዱ ነው ...መነፅር ከምደገን እስከመንሿከኪያ ይጠቅማል ...ታዲያ ቢወደስ ቢደነቅ ምን ችግር አለው ::
አንዳንዴ ሠዎች የሚያስቃቸው ነገር ትዝ ይለኝና ግርም ይለኛል ከዚህ በፊት አንድ ዘውትር ቡና ልጋብዝህ እያለኝ የማወራዉን ቀብ እያደረገ እሱም ሂዶ ለሌላው በማውራት የተለከፈ ሠው ነበር :: አንድ ሰሞን ደበረኝ በቃ አለ አይደል አንዳንዴ ሠዎች ___ልቅ ጆሮ ብቻ ይዘው ሲመጡ ያስጠላል ሼር ካልተደራረጉ ' አይጥምም እና አንድ ቀን እኔ ለራሴ ራሴን ይቅርታ እየለምንኩኝ ኩርፊያዬን ላባርር ስታገል ''ቡና ልጋብዝህ አለኝ '' ንድድ ብሎኝ ''እኔ ማክሠኞ ማክሠኞ ጠዋት ቡና አልጠጣም '' ስለው ከትከት ብሎ ሳቀብኝ ምን ያስቃል አሁን እስቲ ቡና የማያሰኘኝን ሠኣት አጣርቼ ማወቄ ...
ኤዲያ ምን ነበር መንደርደሬ ...አዎ እና ስለማየት ስለማስተዋል ማየት ደስ ይላል አንዳንዴ ዲቴይል የሆኑ ነግሮችን ማየት ዘናጭ ነገር ነው ዕይታ በራሱ የብዙ እይታዎች ስብጥር አይደል ...እንደቡዳ ውስጠትን የመዝለቅ መርገምትም ሆነ ቁጣ ሳይሆን የማስተዋል ዓይነት ዕይታ ጉዕዝም ሆነ ሕያውነትን ሚሸቱ እይታዎች ለያንዳንዱ ንሑስ ዕይታዎች መከሠት የራሳቸው አስተዋፅዖ አላቸው ...አንዳንዴ ' ስናስተውል እንዲህ እንል የለ 'ዛሬ ኸገሌ የተናደደ ይመስላል ....ዛሬ ኸገሊት ! ነገር ያሳሰባት ትመስላለች ...ምናምን ...?'' ታዲያ ያንን ያነበብንበት የሰዎች ፊት ምን የተለየ እይታ አለው ? ቅድም ከላይ ካነሳሁት የራሳቸው ምክኒያት ያላቸው ንሑስ እይታዎች በቀር : እንዚህን ሚገልፁት ትንንሽ እይታዎች አይደሉ ለምሳሌ መናደድን ቅንድብ አካባቢ እጥፍ ብሎ ወደግንባር ተረተር የመቀልበስ ዓይኖች የመቅርዘዝ አፍንጫ የመነፋት ....ዓይነት ነገር
እነኚህ ሁላሁሉ የእይታዎች ተስተውሎት ዓይኔን ጭፈኜ ውስጤ ተዘባርቀው ከማገላብጣቸው ፋይሎች ይበልጥኑ ፈጣን የግንዛቤና የመንገር ኃይል አላቸው :: ከዛም ትንሽ ዘገን አድርጌ ደግሞ ካልደረስኩበት ምናብም ጨለፍ አድርጌ ባንድ ምስል ውስጤ ሳወዣብር ምስል አምጣ አምጣ ምትለዋን አድባር አስታውስና እስቃለሁ : ሲመለከቱት አር ኦኬ ? ተብሎ ሚያስቅ ዓይነት ሳቅ
በዓይን የመለካት ዕውቀት ሚገኘው ከብዙ ብዙ የእይታዎች ጥናት ነው ማንኛዉም ቁሣዊም ሆነ -ቁሣዊ እይታዎች የራሳቸዉን ካራክተር ሚገልፁበትን ቀልብ በውስጥ የማስፈር አያል ተሠጥኦ ያለው ቬንቺ ነበር :: ቤቱ ገብቶ ያያቸዉን ሠዎች ሁሉ አሳታውሶ የመሳል ችሎታ ነበረው :: ውስጡ ያለው የስቶሬጅ ካፓሲቲ ተፈጥሮ ያዳላችለት ዓይነት ነበርና (የቅናት ነው ::ቅቅ መንፈሳዊ ቅናት ) ማናቸዉም ነገሮች ላንድ ምክኒያዊ ነገሮች መመሳሰልና መፈጠርን የማወቅ ጥበብ ከባድ ነውንጂ እንዴት ደስ ይላል :: ልክ አለ አይደል በቁሳዊ እንደማስረጃ ልየዉና አንድ ነገር አንድ ሌላ ነገር ላይ የተቀመጠው ነገር ስለሚያስቀምጠው ነው ... ያስቀመጠው ነገርም ራሱ ለማስቀመጥ ሚቀመጥበት ሁኔታ ስላለ ነው ዓይነት ......
ታዲያ ' እነኚያንም ሆነ እነኚህ ተራ የራስ ምልልሶች ይዤ በዛ ቢሽክሊሊቴ የፊጥኝ የጊንጎኛ ስጥመለመል የዋሊዮሽን አላይ እንደሆን እንጂ ከፊቴ እየተከፈቱ ሚያሾልኩ ትንንሽ መስኮቶች አገኛለሁ ዕይታ ዕይታን ይወልዳል ዓይነት ሕሳቤ አለ አይደል (ታዲያ ሁሉ በምናብ ነው ) በእግሬ ማሽከረክረው ፔዳል ውስጥ ያለው ካቴና ሚመላለስ ሕሳቤ ይሆንብኛል ድግግሞሽ እጠላ የለ እንደፍሬኑ እሱንም ነቃቅዬ ብጥለው በዜሮ ይሆንብኝና ሠዋዊ ፍራቻዬ ደርሶ ድን --::

እስቲ የእይታዬን ቋት የንስፍስፎሽ አድርጌ በቦዘዘ መልኩ ወደሕልሜ ላጮልቅ (ታዲያ የሕልምዓልም አድባር ከታረቀችኝ ነው )

ሄድኩኝ ዝብዘባዬ ለሠማ ሁሉ ከላይ ያደነቅኩትን ጆሮ ለቸረ ''ካምሣሚዳ '' እያልኩኝ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
መንኮራኩር

ዋና ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2006
Posts: 528

PostPosted: Tue Aug 28, 2007 3:19 am    Post subject: Reply with quote

እእእ ....አይ ደደብ መሆን አልገባኝ አለ .... ወይስ መራቀቅም ከዓለም መራቅ ይሆን ......አንዳንዴ ደብለቅለቅ ያለ ሰው ሲናገር ይገርመኛል ::

በልጅነቴ ቀለም አትብዙ አፄፋሪስ አትቅመሱ ብለው የኔታ የሚመክሩንን ሳስብ ምን .....እእእ እያልኩ እንደናበራለሁ አይ የኔ ነገር ..................መቸስ .....ሁላችንም ኖረን እንሞት የለ ..... ግን አሪፍ ጫማ ሰፊን ሙያውን አድንቀንለት እናውቃለን ...................................የለም ..........ባማርኛችን ካልተመፃደቅን እንዴት ሆኖ ..................... እኔም እኮ ልርቅ ሆነ ..በቃኝ !
_________________
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 1 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia