WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ፈገግ ...ፈገግ ....ፈገግታ ...ላንድ ..አፍታ !!!
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 82, 83, 84  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 2:04 am    Post subject: Reply with quote

ሁለት ባልና ሚስት ሌሊት ተኝተው ሳለ አንድ ዘራፊ ሌባ ዘሎ ይገባ እና ሰተት ብሎ ከተኙበት መኝታ ቤት በመሄድ ሌባ ሚስቲቱ ላይ ሽጉጥ ይደግን እና በማስፈራራት ይጠይቃታል

ሌባ ************ ስምሽ ማን ነው ?????

ሚስት ******** <................> ፍራቻ

ሌባ ********** እሽ የሚስቴ ስም ስለሆነ ትቸሻለሁ ይላታል

ይቀጥል እና ወደ ባል ተብየው ሽጉጡን ይደግን እና

ሌባ ********** ስምህ ማን ነው ???/

ባል ********** ስሜ ሸምሱ ነው የሰፈር ሰዎች ግን ሙሽሪት ይሉኛል ......
ብሎት አረፈ
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 2:05 am    Post subject: Reply with quote

ሁለት ባልና ሚስት ሌሊት ተኝተው ሳለ አንድ ዘራፊ ሌባ ዘሎ ይገባ እና ሰተት ብሎ ከተኙበት መኝታ ቤት በመሄድ ሌባ ሚስቲቱ ላይ ሽጉጥ ይደግን እና በማስፈራራት ይጠይቃታል

ሌባ ************ ስምሽ ማን ነው ?????

ሚስት ******** < ..... .... ....... > ፍራቻ

ሌባ ********** እሽ የሚስቴ ስም ስለሆነ ትቸሻለሁ ይላታል

ይቀጥል እና ወደ ባል ተብየው ሽጉጡን ይደግን እና

ሌባ ********** ስምህ ማን ነው ???/

ባል ********** ስሜ ሸምሱ ነው የሰፈር ሰዎች ግን ሙሽሪት ይሉኛል ......
ብሎት አረፈ
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 5:59 am    Post subject: Reply with quote

አቤት አቤት Laughing Laughing እቺ ቤት ወዝታ ወረዛዝታ ጠበቀችኝ :: Cool አስቀናችሁኝ :: Laughing ከማን ልጀምር ዱዲሻ በሰካራሞች ላይ አኪር ይዘሀል Laughing የሰከረ ሰው 4 አይን አለው ብለህ ነው አይደል ? Laughing እኔ ግን ልንገርህ ሰካራም አራት አይን አራት እግር እንዳለው አረጋግጫለሁ :: Laughing ሙከራውን በራሴ ላይ ስርቼ ትክክል እንደሆነ አይቻለሁ :: Laughing በል ዱዲ አንድ ያጣላልና ሁለተኛውን ደግሞ እጠብቃለን :: Cool

ወዳጄ ኦሮሞ 1 እንደምን አለህ Cool ለሰላምታውና ለምርቃቱ እግዚአብሄር ያክብርልኝ አመሰግናለሁ :: Cool እኔ የምልህ እንጂ ቤት ሲመረቅ እኮ በባዶ እጅ አይመጣም :: Laughing በል ከፋሲካ በፊት አንድ ""ቀላድ "" ይዘህ እጠብቃለሁ :: Very Happy

ቡናማ እንደምን አለህ Laughing ግሩም ቀልድ ናት :: ባል ስለተባለው ሰውዬ አንዳንድ ያልተያዙ ክፍት ቦታዎችን እያሰብኩ ነበር :: Laughing ባል ከሚሆን ወንዝ አጠገብ የተተከለ ዛፍ ቢሆን ይሻላል ብዬ ገመትኩ ቢቆረጥ ጥሩ የአጥር እንጨት ይወጣዋል ብዬ በማሰብ ነው :: Laughing "" በወዳጅነታችን እንቀጥል "" የምትለው አባባልህ በጣም ትመቻለች :: Cool ሌላም ቀልድ ይዘህ ብቅ እንደምትል ተስፋዬ ነው :: Cool

አክዬ እኔ ብሆን አረ የእናቴም የእህቴም ስም ሙሽሪት ነበር ነው የምለው Laughing Laughing እኔ ግን ሙሽሪት ስለሚባለው ስም በጣም ግራ ተጋብቻለሁ :: ልጅ እያለሁ አግብታ 4 የወለደች ሙሽሪት የምትባል ጎረቤት ነበረችን :: የሰፈሩ ሰው ሁሉ ሙሽሪት ነው የሚላት :: ባለፈው ኢትዮጵያ ስሄድ የመጀመሪያ ልጇ አድጋ የኮሌጅ ተማሪ ሆናለች ሰላምታ ከተለወዋጥን በኌላ ስለእናቷ ደህንነት ስጠይቃት ""አዎ ሙሽሪት ናት ደህና ናት "" አለችኝ :: ራሷ እኮ ልትሞሸር ምንም አልቀራትም :: Cool ስለሙሽሪት የስም አሰያየም የሚያውቅ ቢያወያየን ፈያ ነበር :: Wink የናንተን ሁሉ ሰምቼ ዝም ብል ጸጸት ያዘኝ :: ካለችኝ ልፈልቅቅ እስኪ ::

ቀኑ እለተ አርብ ነው :: አቶ ባል ሁለቷን የእረፍት ቀን በሰላም ከሚስቱ ጋራ ለማሳለፍ መላ ሲፈልግ አንድ ዘዴ አገኘ :: ሀሳቡንም ስራ ላይ ለማዋል እንዲመቸው ለሚስቱ ወርቅ ቤት አብራው እንድትሄድና አይኗ ደስ ያለውን የአንገት ሀብል ሊገዛላት እንደፈለገ ገለጸላት :: ባልና ሚስት ተያይዘው ወርቅ ቤት ይገቡና ባለሱቁን "" እስቲ ጥሩ የአንገት ሀብል አሳየኝ "" ይለዋል :: ባለሱቁም የተለያዩ አይነት ሀብሎች አወጣለትና ሚስቱ በጣም ውድ የሆነውን መርጣ አቶ ባልም ቼክ ጻፈና ለባለ ሱቁ ሰጠው :: ባለሱቁም "" እንግዲህ ጎበዝ ይሄ ነገር ዋጋው ውድ ስለሆነ ባንክ ሄጄ ቼኩን ከመነዘርኩ በኌላ ሰኞ ሀብሉን ትወስዳላችሁ "" ብሏቸው ባልና ሚስትም ወደ ቤታቸው ሄዱ :: ሚስትም በባሏ ፍቅርና ቸርነት ፈንድቃ ሁለቱን ቀን ማለትም ቅዳሜንና እሁድን መኖሪያዋን ጉም ላይ አድርጋ ከረመች :: ሰኞ ጥዋት ባል ወርቅ ቤቱ ሲደርስ ባለሱቁ በንዴት እየጦፈ "" ምን አይነት ሰው ነህ የባንክ ሂሳብህ ውስጥ እኮ አምስት ሳንቲም የለም "" ቢለው ባልየውም "" እንደሌለኝ አውቃለሁ ግን ቅዳሜና እሁድን ጥሩ ጊዜ ከሚስቴ ጋር እንዳሳልፍ ስላደረከኝ አመሰግናለሁ "" አለው :: Laughing Laughing ሰላም Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እምባጋሊያኖ

አዲስ

Joined: 14 May 2007
Posts: 27

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 10:11 am    Post subject: Reply with quote

በፉፊ
Quote:
አንድ ሳዋ ሊሰለጥን የሄደ ኤርትራዊ እንግሊሽ ክላስ ላይ ስለተነባቢና አናባቢ እየተማሩ እያለ አንዳንድ ቦታ ላይ በጽሁፍ K ብትኖርም ግን አትነበብም ለምሳሌ knife ሲነበብ ናይፍ ነው የሚባለው ናይት ሲጻፍ knight ነው እያለ ሲያስተምራቸው ቆየና ሰውየው ሰውየው ይህን ከሰማ በሀላ መምህር ጥያቄ አለኝ እሞ ንክፍላይ ሀወይ ፍላይ ክንብሎ ዲና (እና ለክፍላይ ወንድሜ ፍላይ ልንለው ነው ) ብሎ ቁጭ .

ፉፊቲ አማን ነሽ ዎይ የለንደኗ ?

ሰላም መልከጻዲቅ
ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም እና እኔም አንድ ልበል

ጊዜው ሻዕቢያዎች አስማሪናን የተቆጣጠሩበት ጊዜ ነበር ሁለት የሻዕቢያ ወታደሮች የቀድሞውን ፊሊፕስ ባለማንጠልጠያ ሬድዮ ባንገታቼው አንግበው ድምጹን ከፍ በማድረግ በሁለትም ሬድዮ ጣቢያ የሚተላለፈውን አንድ አይነት ፕሮግራም ከፍተው ከተማውን ሰንጥቀው አንድ ሽኣይ ቤት ገብተው ሻይ ይጠጣሉ ከቆይታ በኋላ አንድ ወጣት ወደ ሻይ ቤቱ ዘልቆ ሲገባ የሁለቱ ወታደሮች ሁኔታ እንደመሳቅ አደረገው እና ቁጭ አለ ታዛዧ መጥታ ምን ልታዘዝ ስትለው አንድ ሻይ ከአንድ ሬድዮ ጋር ብሎ እሷንም አሳቃት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፉፊ

ኮትኳች

Joined: 11 Jan 2005
Posts: 209
Location: united states

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 12:10 pm    Post subject: Reply with quote

[i]ፉፊቲ አማን ነሽ ዎይ የለንደኗ ?

አማን ነኝ አምቢቾ አንተስ ?

አክዬ ደህና ነህልኝ ሰላም ይብዛልህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጥንቱ

አዲስ

Joined: 26 Dec 2007
Posts: 31

PostPosted: Wed Apr 23, 2008 3:55 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለቤቱ ባለቤት እንዲሁም ለታዳሚው

መሸሻ እና አንዳርጌ ሰፈራው ችግር አስወጋጅ ነው እየተባለ በተዘመረበት ዘመን ከወሎ ከቀያቼው ተፈናቅለው ጎንደር ከሰፈሩ ከጥቂት አመታት በኋላ የመሸሻ እናት ማረፋቸውን ጓደኛው አንዳርጌ እንዲያረዳው መላክት መጣ :: አመሻሹ ላይ መሸሻ ወደ አንዳርጌ ጠጋ ብሎ አይዋ ነገ ማለዳ እመጣለሁ ይለዋል ነገሩ ግር ያለው አንዳርጌ ለምን አርኬ ይለዋል እንዴው አንተ ደሞ አዲያ እኔ ማልጄ ብመጣ ምናለ ታይ ...... የለም ተመቸ መጥተህና ማልዶ አያያ ደህናም አይደለ ይለዋል በዚህን ጊዜ መሸሻ ኧረ ምን ይላል ይኼ ሰው ሲል አንዳርጌ ጠበቅ አርጎ ይይዘዋል አባቴ ነው ሲለው ....... ጠረጠረ አለ መሸሻ ቀጥሎም አይ እሱስ ደህና ነው ሲለው እንግዲያስ .......... ሲለው መሸሻም ............. ብሎ እዛው ከማሳቸው አረዳው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Thu Apr 24, 2008 2:09 am    Post subject: Reply with quote

የጥንቱ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለቤቱ ባለቤት እንዲሁም ለታዳሚው

መሸሻ እና አንዳርጌ ሰፈራው ችግር አስወጋጅ ነው እየተባለ በተዘመረበት ዘመን ከወሎ ከቀያቼው ተፈናቅለው ጎንደር ከሰፈሩ ከጥቂት አመታት በኋላ የመሸሻ እናት ማረፋቸውን ጓደኛው አንዳርጌ እንዲያረዳው መላክት መጣ :: አመሻሹ ላይ መሸሻ ወደ አንዳርጌ ጠጋ ብሎ አይዋ ነገ ማለዳ እመጣለሁ ይለዋል ነገሩ ግር ያለው አንዳርጌ ለምን አርኬ ይለዋል እንዴው አንተ ደሞ አዲያ እኔ ማልጄ ብመጣ ምናለ ታይ ...... የለም ተመቸ መጥተህና ማልዶ አያያ ደህናም አይደለ ይለዋል በዚህን ጊዜ መሸሻ ኧረ ምን ይላል ይኼ ሰው ሲል አንዳርጌ ጠበቅ አርጎ ይይዘዋል አባቴ ነው ሲለው ....... ጠረጠረ አለ መሸሻ ቀጥሎም አይ እሱስ ደህና ነው ሲለው እንግዲያስ .......... ሲለው መሸሻም ............. ብሎ እዛው ከማሳቸው አረዳው

Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes በፍጡም አልገባኝም Surprised Surprised Surprised Surprised Surprised Surprised
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Thu Apr 24, 2008 5:50 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ውድ የዚህ ቤት ታዳሚዎች Laughing Laughing
ከእምባጋሊያኖ ልጀምር Cool እረ እውነት ብለሀል ሰው ያለውን ከወረወረ ንፉግ አይባልም :: ሁለቱም መቼም የተለያየ ጣቢያ እየሰሙ ይሆናል እንጂ አንድ አይነት ጣቢያ ቢሆን የአንዱ ብቻ በቂ ነበር :: Laughing የልጁ ፈጣን መልስ ግን ያስቃል :: እስኪ እንግዲህ ይልመድብህ እምባጋሊያኖ አትጥፋ :: Cool

ፋፊ ብቅ ብለሽ ጠፋሽ Very Happy ሰዉ ሁሉ ናፍቆሻል :: የት ጠፋሽ እያሉሽ ነው Wink እኔም አንድ ጆክ ይዘሽ ብቅ በይ ልበላ እግረ -መንገዴን Very Happy

የጥንቱ ሰላም ብያለሁ Cool
የጅብ ችኩል ጭራ ይነክሳል ይባላል Laughing ወይም ደግሞ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ .. Laughing ብቻ ከሁለቱ አንዱ ለዚህ ቀልድ ተስማሚ ይሆናል ብዬ አስባለሁ :: ወዳጃችን አክዬ ቀልዱ ምንም አልገባኝም የሚል ስሞታ አስቀምጦልሀል Laughing እንግዲህ የምትለውን አብረን እንስማ :: Cool ታዲያ ስትመጣ አንድ ቀልድ ለመንገድ ሸጎጥ አድርግና Exclamation Laughing ሰላሙን እመኛለሁ የጥንቱ Cool እኔም ካገኘኌት አንድ ልወርውር እስኪ ::
ሰውየው ሆስፒታል ሄዶ ዶክተሩን "" ዶክተር ሰውነቴን ሁሉ ያመኛል "" አለው :: ዶክተሩም "" እስቲ ምንህ ነው የሚያምህ Question "" አለው :: ሰውየም በጣቱ በሙሉ የሰውነት ክፍሎቹን እየነካ የነካው ቦታ በሙሉ እንደሚያመው ነገረው :: ዶክተሩም መረመረውና "" ወንድም ጣትህ ተሰብሯል "" አለው :: Laughing Laughing
መልካም ቀን / ምሽት እመኛለሁ Cool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቻሉ

መንገደኛ

Joined: 11 Jan 2006
Posts: 7
Location: london

PostPosted: Thu Apr 24, 2008 11:18 am    Post subject: ቻሉ Reply with quote

Very Happy Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Wed Apr 30, 2008 5:31 am    Post subject: Reply with quote

የሰማሁትን አንድ ቀልድ ላካፍላችሁ ::

ሴትየዋ እንግዲህ ለጠንቌይ ያላቸው ግምት በጣም ከፍተኛ ነው :: ጠንቌይ ሁሉንም ነገር የሚያውቅ ሌላው የማያየውን ማየት የሚችል የተደበቀ ሚስጥር ለሱ ብቻ የሚገለጽለት ሱፐር ማን አይነት አድርገው ይገምቱት ነበር :: ታዲያ አንዱን ቀን "የተናገረው መሬት ጠብ አይልም " የሚባልለት ጠንቌይ ተጠቁመው ይሄዳሉ :: በር ላይ ደርሰው ሲያንኴኩ ጠንቌዩ ከውስጥ ሆኖ "ማን ልበል ....ማነህ ...? " ይላል :: ሴትየዋ በዚህ ጊዜ " አዬዬ አሁን ይሙት እኔ ጠፍቼህ ነው ማን ልበል የምትለው ?" አሉት አሉ :: Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Wed Apr 30, 2008 8:28 am    Post subject: Reply with quote

.....<<<<< አንድ በጣም ያረጀች ሴትዮ ናት በጣም ያረጀች መንገድ ላይ እየዞረች ትለምናለች ከሩቅ አንድ ላይ ተሰብስበው ወሬ የሚያወሩ ወጣቶች ነበሩ አንድ ላይ ሁነው ያወራሉ እነዚህ ወጣቶች ይህችን አሮጊት ሴትዮ ከሩቅ ይመለከቷት እና ........ አይ አንተ እግዚአብሄር እስኪ አሁን አሁንን ወጣት ወጣቱን በሞት ከምትቀስፍ እስኪ እንደዚች ያለች ሴትዮ ከምትሰቃይ ለምን አያስርፋትም እያሉ ሲወያዩ ሳሉ ይህች አሮጊት ወጣቶች ካሉበት ቦታ በመድረስ

አሮጊቷ :::-------- ልጆቸ ስለ ድንግል ..ያም ....... ..... የኔ ልጆች ..............ላች ...... ያላችሁን ስጡኝ እያለች (በተንተባተብ አማርኛ ) ትለምናቸዋለች

ወጣቶችም አስርም ሀምሳም አንድ ብርም ምናምን አድርገው አጠራቅመው ከሰጧት በሗላ ወጣቶች አንዱ ቀደም ይልና ይጠይቃታል

ወጣቱ .......... እማማ

አሮጊቷ ........... አቤት የኔል ልጅ

ወጣቱ ....... አሁን ይህንን የሰጠንዎትን ገንዘብ ምን ያደርጉታል ???

አሮጊቷ ............ ለእናቴ እሰጣታለሁ Laughing Laughing

ጭራሽ እናታቸውም አለሽ Laughing Laughing
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Wed Apr 30, 2008 8:30 am    Post subject: Reply with quote

.....<<<<< አንድ በጣም ያረጀች ሴትዮ ናት በጣም ያረጀች መንገድ ላይ እየዞረች ትለምናለች ከሩቅ አንድ ላይ ተሰብስበው ወሬ የሚያወሩ ወጣቶች ነበሩ አንድ ላይ ሁነው ያወራሉ እነዚህ ወጣቶች ይህችን አሮጊት ሴትዮ ከሩቅ ይመለከቷት እና ........ አይ አንተ እግዚአብሄር እስኪ አሁን አሁንን ወጣት ወጣቱን በሞት ከምትቀስፍ እስኪ እንደዚች ያለች ሴትዮ ከምትሰቃይ ለምን አያስርፋትም እያሉ ሲወያዩ ሳሉ ይህች አሮጊት ወጣቶች ካሉበት ቦታ በመድረስ

አሮጊቷ :::-------- ልጆቸ ስለ ድንግል . .ያም ..... .. ..... የኔ ልጆች ..... ... .. ....ላች ...... ያላችሁን ስጡኝ እያለች (በተንተባተብ አማርኛ ) ትለምናቸዋለች

ወጣቶችም አስርም ሀምሳም አንድ ብርም ምናምን አድርገው አጠራቅመው ከሰጧት በሗላ ወጣቶች አንዱ ቀደም ይልና ይጠይቃታል

ወጣቱ .......... እማማ

አሮጊቷ ........... አቤት የኔል ልጅ

ወጣቱ ....... አሁን ይህንን የሰጠንዎትን ገንዘብ ምን ያደርጉታል ???

አሮጊቷ ............ ለእናቴ እሰጣታለሁ

ጭራሽ እናታቸውም አለሽ
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃልቻው -ዝቄ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 09 Oct 2004
Posts: 66
Location: united states

PostPosted: Wed Apr 30, 2008 12:16 pm    Post subject: Reply with quote

አክየ እንደጻፈ(ች)ው:
.....<<<<< አንድ በጣም ያረጀች ሴትዮ ናት በጣም ያረጀች መንገድ ላይ እየዞረች ትለምናለች ከሩቅ አንድ ላይ ተሰብስበው ወሬ የሚያወሩ ወጣቶች ነበሩ አንድ ላይ ሁነው ያወራሉ እነዚህ ወጣቶች ይህችን አሮጊት ሴትዮ ከሩቅ ይመለከቷት እና ........ አይ አንተ እግዚአብሄር እስኪ አሁን አሁንን ወጣት ወጣቱን በሞት ከምትቀስፍ እስኪ እንደዚች ያለች ሴትዮ ከምትሰቃይ ለምን አያስርፋትም እያሉ ሲወያዩ ሳሉ ይህች አሮጊት ወጣቶች ካሉበት ቦታ በመድረስ

አሮጊቷ :::-------- ልጆቸ ስለ ድንግል . .ያም ..... .. ..... የኔ ልጆች ..... ... .. ....ላች ...... ያላችሁን ስጡኝ እያለች (በተንተባተብ አማርኛ ) ትለምናቸዋለች

ወጣቶችም አስርም ሀምሳም አንድ ብርም ምናምን አድርገው አጠራቅመው ከሰጧት በሗላ ወጣቶች አንዱ ቀደም ይልና ይጠይቃታል

ወጣቱ .......... እማማ

አሮጊቷ ........... አቤት የኔል ልጅ

ወጣቱ ....... አሁን ይህንን የሰጠንዎትን ገንዘብ ምን ያደርጉታል ???

አሮጊቷ ............ ለእናቴ እሰጣታለሁ

ጭራሽ እናታቸውም አለሽ

ተስፋዬ ካሳ ተነሳ እንዴ ??
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አዬ ጅሉ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Thu May 01, 2008 5:14 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም አክዬ Laughing ወይ ጉድ "" የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ "" የሚባለውን አባባል አስታወስከኝ :: Laughing ልጆቹ የአሮጊቷን እናት በህይወት መኖር ሲሰሙ እንዴት አይናቸው እንደፈጠጠ ሳስብ አስቆኛል :: Laughing ጥሩ ቀልድ ናት :: Cool እቺን ቤት እያደማመካት ነው አመሰግናለሁ :: እስኪ እኔም አንድ ልበጭቅ :: Laughing ይቺን ቃል ያገኘኌት ከታች ሰፈር ልጆች ነው :: መቼም ይገባሀል Question ምን ማለቴ እንደሆነ Laughing :: በነገራችን ላይ ዛሬ እታች ሰፈር ምን ተፈጥሯል Question Cool ረብሻ ነበር እንዴ Laughing ሱቅ ሁሉ በጊዜ ተዘግቷል :: Laughing እኔ እንኴን ዛሬ ማታ ትንሽ ማመሻሸት ስለፈለኩ ""ቆንጆ ቡና ሞኒካ ቤት አለ "" ሲሉ ስለሰማሁ ካፌ ላቴ ባገኝ ብዬ ሄጄ ነበር ግን አንዱ ሱቁን ሁሉ በጊዜ አዘግቶታል :: Laughing ""እንታይ ጉዱ "" Laughing ለማንኛውም ቀልዱን ስማኝ አክዬ Cool
አንዱ ነው እንግዲህ ገርል ፍሬንድ አለችው :: ታዲያ የአዲስ ፍቅር ቀንበጥ መቀነጣጠስ ጀምረው ነበርና የአንገት ሀብል አሰርቶ ስጦታ ሊሰጣት ፈለገ :: ከዛ ወርቅ ቤት ሄዶ ለወርቅ ሰሪው የሚፈልገውን አይነት ዲዛይን ከነገረው በኌላ " እና ሀብሉ መሀል ላይ እንዴት ነው ስሟን ልጻፍበት እንዴ ? " ሲለው አጅሬ አዲስ አፍቃሪ ሆዬ ጥቂት አሰበና "" አይ ..አይ ..ተው እንደዛ አትበል ...ዝም ብለህ "" ለምወድሽ "" ብለህ ጻፍበት አለው :: ወርቅ ሰሪውም ፈገግ ብሎ "" ለምን ልጄ ..."" ቢለው "አሀ ወንድሜ ምን ይታወቃል ብንጣላ ለሌላ ሴት ይሆነኛላ "" ብሎት እርፍ :: Laughing Laughing ሰላም Cool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Thu May 01, 2008 4:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ፒፕል .........ቀልዶቹ ተመችተውኝ እስኪ አንድ ልጣል ብዬ ነው :;

ልጁ ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሀገር ቤት ሲሄድ ለእናቱ እና አባቱ ወጣት የሚያደርግ መድሀኒት ይወስድላቸዋል :: በቀን አንድ አንድ እንዲውጡ ነግሯቸው ወደመጣበት ይመለሳል :: ከሁለት አመት ብኍላ ይሄው ልጅ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ ቤት ሲገባ እናቱን ሲያያቸው በጣም ተለውጠው 28 ዓመት ልጃገረድ መስለዋል :: በጣም ተገርሞ " እማምዬ እንዴት ነው ያማረብሽ ! ወይ ግሩም በዚህ ዓይነትማ አባዬ !"....ብሎ ሳይጨርስ እናትየው ከአፉ ነጥቀው " ወይ ልጄ ! አባትህማ የሰው ምክር አልሰማ ብሎ ጠርሙሱን ሙሉ መድሀኒት በአንድ ጊዜ ውጦት ጓዳ ሰራተኛዋ አዝላዋለች " ብለውት እርፍ Laughing
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 82, 83, 84  Next
Page 2 of 84

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia