|
|
|
| View previous topic :: View next topic |
| Author |
Message |
ማይ ኔም

Joined: 17 Mar 2005 Posts: 165 Location: united states
|
Posted: Fri May 09, 2008 1:13 pm Post subject: አዲሱ ግንቦት ሰባት ፓርቲ ... |
|
|
ከቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲም ሆነ አሁን እንደአዲስ ከተቋቋመው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ራሳቸውን ያገለሉት ዶ /ር ብርሃኑ ነጋና አጋሮቻቸው ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በሚል ስያሜ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመው በመጭው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2000ዓ .ም . ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ መሆኑን ታማኝ ምንጮቻችን ገለጹ።
ግንቦት ስድስት ቀን የሚሰጠው ይፋ መግለጫ በአሜሪካን አገር በሚገኘው በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ኔትወርክ (ETN) ጣቢያ ሲሆን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጥራት በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ዶ /ር ብርሃኑን ጨምሮ የድርጅቱ መስራቾች እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የአሜሪካ ድምጽ፣ የጀርመን ሬዲዮ፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ ዌብ ሳይቶችና ሌሎች የተለያዩ ሚዲያዎች መጋበዛቸውን ለማወቅ ችለናል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ መመሥረትን በማስመልከት በሚዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ የግንቦት 7 ንቅናቄ አካል የሆኑ የድረ -ገፅ ፣የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ድርጅቱን፣ ራዲዮ ጣቢያውና የድረ ገጹም ስያሜ ከታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን ጋር ተያያዥነት እንዳለው የጠቆሙት ምንጮቻችን ሙሉ ስያሜውን ግንቦት 6 ቀን በሚሰጡት መግለጫ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እነ ዶ /ር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው ላይ በዝርዝር ያቀርቡታል ከተባለው ከንቅናቄው የፖለቲካ ግቦች መካከል ነው በማለት ምንጮች የጠቆሙት የመንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ ሳይሆን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያገባኛል የሚሉ ሁሉም ኃይሎች ጋር በመተባበር በሕዝብ ፍላጎትና ውሳኔ የሚገዛ ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ የፖለቲካ ሥልጣን አያያዝ ሂደት በኢትዮጵያ ለማስጀመር መሆኑን ይገልጻል፡፡
በመጪው ረቡዕ ግንቦት 6 በይፋ መመሥረቱን የሚያስታውቀው የግንቦት 7 ንቅናቄን የትግል ስልትና መርሆዎች አስመልክቶ ምንጮቻችን እንደጠቆሙት፤ ንቅናቄው ቀኖናዊ በሆነ መንገድ የሚከተለው የትግል ስልት አለመኖሩን ጠቁመው፣ የትግል ስልቱ የኢትዮጵያን ተጨባጭና የተለየ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሁለገብ የሆነ የትግል ሥልት በተግባር ላይ በማዋል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ 97 የተጎናጸፈውን የሞራል የበላይነት እንዲከበር ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን በጹሁፍ ማስፈራቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሞክሮ የነበረውን ሰላማዊ የትግል ሥልት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገም መስተካከል ያለበትን አስተካክሎ እንደ አስፈላጊነቱ በሥራ እንደሚያውል ይገልፃል፡፡ንቅናቄው ከዚህ ጋር በተያያዘ፤ ሰላማዊ ትግል ሲባል በሥልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ሰላማዊ ነው ብለው እንዳሻቸው የሚደነግጉት ነው ባሉት አፋኝ ሕግ የሚገዛ እንደማይሆን ማስፈራቸውን ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን፣ በአንፃሩ ሕገወጥ የሆኑ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን በቂ ዝግጅት በተደረገበት የሕዝባዊ ሰላማዊ እንቢተኝነት በመጣስ የሚከናወን መሆኑን ይጠቁማል፡፡
ታማኝ ምንጮቻችን ንቅናቄው ከሌሎች መሰል የፖለቲካ ኃይላት ጋር ለሚያደርገው ትብብር የሚገለገልባቸው መሠረታዊ እሴቶችን በተመለከተ እንደገለጹት፣የግንቦት 7 ንቅናቄ በቅድሚያ ማናቸውም በአገሪቱ ፖለቲካ ያገባኛል የሚሉ ኃይሎች፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥታዊ አገዛዝ ጨምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዜግነት እንጂ በተገዢነት መኖርን የማይቀበል መሆኑን ተረድተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዜግነቱም የሚገቡትን መብቶች ተከብረውለት ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚፈጠረው የሕዝብ ምስፍናን ላረጋገጠ መንግሥታዊ ሥርዓት ሁሉም በጋራ እንዲሠራ የሚጠይቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡
ከዚሁ በመቀጠል ንቅናቄው የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር ዋና ዓላማ ሥልጣን ያለውን መንግሥት ወደ ድርድር እንዲመጣ ወይም ከሥልጣን እንዲወርድ ብቻ ሳይሆን በቦታው ዲሞክራሲያዊ መንግሥታዊ አስተዳደር በኢትዮጵያ ለመተካት እስከሆነ ድረስ፣ የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር አባላት በሙሉ በጋራ የሚስማሙባቸውን የማይጣሱና የማይገሠጹ የትብብሩ የፖለቲካ እሴቶች በቅድሚያ መቀመጥ እንዳለባቸው በመግለጫቸው ለማተት መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡
እነዚህ የፖለቲካ እሴቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት መቀበል፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ በአገር አቀፍ ይሁን ከዚያ በታች በሚገኙ አስተዳደራዊ አሐዶች ውስጥ የሚያዘው ዜጎች በእኩልነት በሚሰጡት የአንድ ሰው አንድ ድምጽ ሥርዓት መሆኑን ማመን፣ የትብብሩ የትግል ዓላማ ሥልጣን ለመያዝ ሳይሆን ሥልጣን በሕዝብ ፈቃድ የሚያዝበትን ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ለማመቻቸት መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን በንቅናቄው የተጠቀሱትን መሠረታዊ እሴቶች ከተቀበሉ ማናቸውም ዓይነት ተመሳሳይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፖሊሲዎች ካሏቸው፣ የራሳቸውም የሆኑ አደረጃጀቶችን የሚጠቀሙና የትግል ሥልት የሚከተሉ የፖለቲካና ፖለቲካዊ ካልሆኑ ቡድኖች ጋር በትብብር ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኑን የምንጮቻችን ዘገባ ያስረዳል፡፡
ምንጭ ክ አ ያ ::::ETHIOPIA ZARE |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ጉግል

Joined: 20 Jul 2006 Posts: 1171
|
Posted: Fri May 09, 2008 1:47 pm Post subject: Re: አዲሱ ግንቦት ሰባት ፓርቲ ... |
|
|
| ማይ ኔም እንደጻፈ(ች)ው: |
የግንቦት 7 ንቅናቄ መመሥረትን በማስመልከት በሚዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ የግንቦት 7 ንቅናቄ አካል የሆኑ የድረ -ገፅ ፣የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ድርጅቱን፣ ራዲዮ ጣቢያውና የድረ ገጹም ስያሜ ከታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን ጋር ተያያዥነት እንዳለው የጠቆሙት ምንጮቻችን ሙሉ ስያሜውን ግንቦት 6 ቀን በሚሰጡት መግለጫ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ ክ አ ያ ::::ETHIOPIA ZARE |
በጣም ደስ የሚል ዜና ነው :: እሳቸውንም ሆነ ጓደኞቻቸውን እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን ግንቦት ሰባት አደረሳችሁ እላለሁ :: እግዜአብሄር ይህንን የተቀደሰ ዓላማቸውን አይቶ እሰከመጨረሻው በጽናት እንደሚያዘልቃቸው ምሀል ላይ ደከመኝ እንደማይሉ ምንም ጥርጥር የለኝም :: መንገዱን ስጋጃ ያድርገላቸው ::
በአጋጣሚ ከግንቦት ወር ጋር የሚያያዙ ክስተቶች
ግንቦት 1 --ልደታ (ዛሬ )
ግንቦት 7---የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ቅንጅትን የመረጠበት
ግንቦት 7---የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ግንቦት 7 ፓርቲ የሚቋቋምበት
ግንቦት 8---ተሞክሮ የከሽፈው መፍንቅለ መንግስት
ግንቦት 13--ፈሪው መንግስቱ ፈርቶ የፈረጠጠበት
ግንቦት 16--የኤርትራ ነጻ አውጪ አስመራ የገባበት
ግንቦት 20--የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ አዲስ አበባ የገባበት
ግንቦት 27/28--የትግራይ ነጻአውጪ አዲስ አበባን በፍንዳታ ያናወጠበት
እናዳይለየን እንዳይለየን እንዳይለየን
http://video.google.com/videoplay?docid=393285145991678959&hl=en |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ሐመሩ

Joined: 03 Feb 2008 Posts: 58
|
Posted: Fri May 09, 2008 2:31 pm Post subject: |
|
|
አምጫ አምጫ አምጫ አንጀቴ ቆስሎ ቆስሎ ተወለደ ይሉሀል ይሄ ነው !! _________________ Selam To ethiopia ! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ሌኒን

Joined: 01 Feb 2008 Posts: 39
|
Posted: Fri May 09, 2008 2:39 pm Post subject: |
|
|
| Quote: | | አምጫ አምጫ አምጫ አንጀቴ ቆስሎ ቆስሎ ተወለደ ይሉሀል ይሄ ነው !! |
ምኑ ????????????????????? |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ሌኒን

Joined: 01 Feb 2008 Posts: 39
|
Posted: Fri May 09, 2008 2:40 pm Post subject: |
|
|
| Quote: | በጣም ደስ የሚል ዜና ነው :: እሳቸውንም ሆነ ጓደኞቻቸውን እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን ግንቦት ሰባት አደረሳችሁ እላለሁ :: እግዜአብሄር ይህንን የተቀደሰ ዓላማቸውን አይቶ እሰከመጨረሻው በጽናት እንደሚያዘልቃቸው ምሀል ላይ ደከመኝ እንደማይሉ ምንም ጥርጥር የለኝም :: መንገዱን ስጋጃ ያድርገላቸው ::
|
በቃ ዝም ብለህ በነፈሰበት አብረህ ትነፍሳለህ አይደል !!! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ጉግል

Joined: 20 Jul 2006 Posts: 1171
|
Posted: Fri May 09, 2008 2:45 pm Post subject: |
|
|
አይደል ?!
አየቆየ ይገባሻል : ሽው ሽው ...  |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ስልኪ

Joined: 22 Aug 2007 Posts: 1082
|
Posted: Fri May 09, 2008 2:46 pm Post subject: Re: አዲሱ ግንቦት ሰባት ፓርቲ ... |
|
|
| ጉግል እንደጻፈ(ች)ው: |
ግንቦት 7---የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ግንቦት 7 ፓርቲ የሚቋቋምበት |
እርማት :- "የኒውዮርክ -ኒውስኩል ተራራ የወራት ሱባኤ የወለደው ግንቦት 7 ፓርቲ " ተብሎ ቢስተካከል :: አላማውም የዲያፖራው ላሜ ቦራ እያለቡ ለልጅ ልጅ የሚሆን ገንዘብ መሰብሰብ ነው !!! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ሐመሩ

Joined: 03 Feb 2008 Posts: 58
|
Posted: Fri May 09, 2008 3:27 pm Post subject: |
|
|
ስልኪ ገና ጉሮሮህ ተይዞ ህዝብ ፊት ትቀርባለህ ! አንተ ነፍስ በላ .......ቀጥል ድሮ ቀረ ከእናተ ጋር በዚህ ወጣ ወደዚህ ሄድ መባባሉ ቀረ አሁን እስኪገባህ ድረስ በዱላ ማድቀቅ ይሆናል ነገሩ ........!! _________________ Selam To ethiopia ! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ይከአሎ

Joined: 18 May 2005 Posts: 49
|
Posted: Fri May 09, 2008 3:49 pm Post subject: |
|
|
ስልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥ አለ ያገሬ ሰው _________________ Long live to tsion !!!! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ሐመሩ

Joined: 03 Feb 2008 Posts: 58
|
Posted: Fri May 09, 2008 4:06 pm Post subject: |
|
|
ይከአሎ .........ስልቻው ውስጥ ትገባለህ አንተ ነፍሰ በላ ሁላ _________________ Selam To ethiopia ! |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
Qorrat

Joined: 13 Apr 2008 Posts: 62
|
Posted: Fri May 09, 2008 6:53 pm Post subject: |
|
|
ቂቂቂቂቂ
አይ ተረት ........'ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ' ...
ወደ ቁምነገሩ ስንመለስ :: በኔ አመለካከት ከብዛት ጥራት ሊመጣ ይችል ይሆናልና እስቲ እንየው :: ለምንም ድል ከማይበቃ ስብስብ እንደዚህ በተናጥል ቢታይ ማን ማንን ይጎትት እንደነበረም የመታዘብያ እድል ነው ::
እስቲ የፈጣሪ ችሮታም Uገራችንን አይለያት
qorrat
| ይከአሎ እንደጻፈ(ች)ው: | | ስልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥ አለ ያገሬ ሰው |
|
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ማይ ኔም

Joined: 17 Mar 2005 Posts: 165 Location: united states
|
Posted: Fri May 09, 2008 8:52 pm Post subject: |
|
|
ዪሁን ብለናል , በርቱ ነዉ የምለዉ እነ ብርሀኑን , ባለን ሁሉ እንረዳለን ..በሁሉም ! ብቻ የተስተካከለ አመራር የሚሰጥ ስርአት ያለዉ የዘመኑ ፖለቲካ የገባቸዉ ቆራጥ ..ሰዎች ያስፈልጋሉ
ያለጊዜዉ ሊሆን ይችላል እንጂ ..የኔ ጥያቄ
1) ይሄ ፓርቲ ..በየትኛዉ አገር ህግ መሰረት ነዉ የሚቁ ..ዋመው .
..more questions to come |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ስሙ ይናገር

Joined: 14 Mar 2008 Posts: 379
|
Posted: Fri May 09, 2008 9:34 pm Post subject: Re: አዲሱ ግንቦት ሰባት ፓርቲ ... |
|
|
| ጉግል እንደጻፈ(ች)ው: | | ማይ ኔም እንደጻፈ(ች)ው: |
የግንቦት 7 ንቅናቄ መመሥረትን በማስመልከት በሚዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ የግንቦት 7 ንቅናቄ አካል የሆኑ የድረ -ገፅ ፣የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ድርጅቱን፣ ራዲዮ ጣቢያውና የድረ ገጹም ስያሜ ከታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን ጋር ተያያዥነት እንዳለው የጠቆሙት ምንጮቻችን ሙሉ ስያሜውን ግንቦት 6 ቀን በሚሰጡት መግለጫ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ ክ አ ያ ::::ETHIOPIA ZARE |
በጣም ደስ የሚል ዜና ነው :: እሳቸውንም ሆነ ጓደኞቻቸውን እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን ግንቦት ሰባት አደረሳችሁ እላለሁ :: እግዜአብሄር ይህንን የተቀደሰ ዓላማቸውን አይቶ እሰከመጨረሻው በጽናት እንደሚያዘልቃቸው ምሀል ላይ ደከመኝ እንደማይሉ ምንም ጥርጥር የለኝም :: መንገዱን ስጋጃ ያድርገላቸው ::
በአጋጣሚ ከግንቦት ወር ጋር የሚያያዙ ክስተቶች
ግንቦት 1 --ልደታ (ዛሬ )
ግንቦት 7---የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ቅንጅትን የመረጠበት
ግንቦት 7---የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ግንቦት 7 ፓርቲ የሚቋቋምበት
ግንቦት 8---ተሞክሮ የከሽፈው መፍንቅለ መንግስት
ግንቦት 13--ፈሪው መንግስቱ ፈርቶ የፈረጠጠበት
ግንቦት 16--የኤርትራ ነጻ አውጪ አስመራ የገባበት
ግንቦት 20--የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ አዲስ አበባ የገባበት
ግንቦት 27/28--የትግራይ ነጻአውጪ አዲስ አበባን በፍንዳታ ያናወጠበት
እናዳይለየን እንዳይለየን እንዳይለየን
http://video.google.com/videoplay?docid=393285145991678959&hl=en |
ወንድሜ ጉግል ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት ወያኔን በየ አቅጣጫው ማስጨነቅ ነው እንጂ :: አየህ አሁን ጠላትንና ወዳጅን እንለይበታለን ወያኔ መሀላችን ገብታ ስታባላን ከረመች አሁን ግን አስተያየትህን ሳነበው ወያኔን ከህዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥረን የምንጥልበት ጊዜ እንደተቃረበ ለመገመት ችያለሁ :: በርታ ወንድሜ ትግላችን ረዥም ና መራራ ነው :: በአስተያየትህ በጣም ደስ ብሎኝ ነው :: እንግዲህ በሁሉም አቅጣጫ የሚታገሉትን እንዳንገድላቸው ሁላችንም እንጠንቀቅ በርታልኝ _________________ God is Great |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ማይ ኔም

Joined: 17 Mar 2005 Posts: 165 Location: united states
|
Posted: Thu May 15, 2008 2:33 pm Post subject: |
|
|
ትግሉ ዪቀጥላል ...,
ግን ,
የፓርቲዉ መዋቅር ምን ዪመስላል , ?
መሪዎቹ , ሊቀምንበሩ ጸሀፊዉ .....እነማን ናቸዉ .. ?
ዋና ጽ / ቤቱ የት ነዉ ?
.... |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ጉግል

Joined: 20 Jul 2006 Posts: 1171
|
Posted: Thu May 15, 2008 2:57 pm Post subject: |
|
|
| ምን ዓይነት ጥያቄ ነው :: ፓሪቲው እኮ ኅቡዕ ነው ይባላል |