WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
መልካም የልደት በአል ይሁንልኽ አባታችን ማንዴላ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 10:37 pm    Post subject: Reply with quote

1834 የእንግሊዝ መንግስት የጠረፍና ባህር ዳርቻ አካባቢዎችን በመቆጣጠር በደቡብ አፍሪካ የበላይነቱንና ቅኝ ገዢነቱን አስታወቀ ::ቀጥሎም የባሪያ ነጻነት በማወጅ 60,000 ባሪያዎችን ነጻ በማውጣቱ የተበሳጩት ቦይርስ (የሆላንድ ገበሬዎች )ከእንግሊዝ አገዛዝ ለመራቅ ሲሉ ወደ ሰሜን ምስራቅ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ ከአፍሪካውያን ጋር እየተዋጉና መሬት እያስለቀቁ ተጎአዙ ::እነዚህ ቦይርስ ያደረጉት የመስፋፋትና አፍሪካዊያንን መሬት አልባ የማድረግ ታላቅ ጉዞ (Great trek) እንደተሳካ ሁለት ከእንግሊዝ መንግስት ነጻ የሆኑ አሬንጅ ፍሪ ስቴትና ትራንስቫል የሚባሉ ሪፖብሊኮችን መሰረቱ ::በዚህ መሰረት በደቡብ አፍሪካ ዳርቻ አካባቢ የሚገኘው በእንግሊዝ መንግስት በቅኝ ግዛትነት የሚገዛው የናታል ግዛት ሲሆን በሁለተኛው በዳች ገበሬዎች የተቋቋሙት ሁለት ሪፖብሊኮች ናቸው ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Sat Jul 18, 2009 10:23 am    Post subject: Reply with quote

መልካም 91 አመት የልደት በአል ለታጋዮቹ ቁንጮ ለኔልሰን ማንዴላ ክብርነታችን ይመኛል .....

አባታችን ማንዴላ ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር አምላክ እንዲያድልንን ስንመኝ ሀፕይ በርዝደይ ሀፕይ በርዝ ደይ ሀፕይ በርዝ ደይ ሀፕይ በርዝ ደይ ሀፕይ በርዝደይ ኔልሰን ማንዴላ እያልን በመዝፈን ነው ::

ግምባርህ ላይ በፍቅርና ባክብሮት ከልቤ በመሆን ስሜሀለሁ

ሾተል ......ሁሌም የሚኮራብህ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
admasradio

ኮትኳች

Joined: 18 Mar 2008
Posts: 152

PostPosted: Sat Jul 18, 2009 1:40 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም አድማጮች

ዛሬ የኔልሰን ማንዴላ የልደት ቀን መሆኑን ከዚህ ብሎግ ተረድታችሁዋል :: አድማስ ሬዲዮ ደግሞ የማንዴላን የልጅነት ህይወትና እስር ቤት ቆይታ በአማርኛ በሰፊው እናቀርብላች ሁዋለን ::

አርቲስት አረጋኸኝ ወራሽም ሌላው እንግዳችን ነው ::
አድማስ ሬዲዮ
_________________
The #1 Ethiopian infotainment radio in USA

Every Saturday from 2-6 pm (Eastern time) @1100AM(Atlanta) .... or LIVE at www.admasradio.info or LIVE from your cell phone (951) 262 4343 code 193902#
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Thu Feb 11, 2010 6:13 pm    Post subject: Reply with quote

http://www.youtube.com/watch?v=GzUB2Vag8UI&feature=related

የዛሬ አስር አመት ለተፈታው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላ ይሁንልኝ ::

ሾተል ነን ....ጀግናን የነጻነት ታጋይን ከልቡ የሚወድና የሚያከብር
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ይታየዋል

ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2007
Posts: 355

PostPosted: Fri Feb 12, 2010 1:15 pm    Post subject: Re: የኔልሰን ማንዴላ 91ንደኛ አመትቱን አከበረ Reply with quote

ሾተል እንደጻፈ(ች)ው:
ክቡር ታላቁ ኒልሰን ማንዴላ መልካም ልደት እመኝልዎታለሁ ::አምላክ ከዛ የእስር ረመጥ አውጥቶ በዛሬዋ እለት 90 የልደት በአልዎን አምላክ እንድታከብሩ ስላደረገዎ አምላክን ከልቤ አመሰግንልዎታለሁ ::አሁንም ሌላ 100 ዘጠና አመቶችን በህይወት አኑሮ ልደትዎን ያስከብርዎ ዘንድ አምላክን እለምንልዎታለሁ ::

በህይወት እያለሁ አንድ ታላቅ የነጻነትና ፍትህ ታጋይ በህይወት ኖሮ አብሬ ከዚች ምድር ጋር በመኖሬ ደስተኛ ነኝ ::ከማንዴላ ብዙ ተምሬያለሁ ...ተግስትን ,ለተነሱለት አላማ መጽናትን ወዘተ ....ማንዴላ የትእግስት ምሳሌ ነው ...የነጻነት ,,,የትግል አባትና ምሳሌ ነው ....ማንዴላ ሁሉንም ነው ::ማንዴላ አንድነት ነው ....ማንዴላ በብቀላ አያምንም ....ማንዴላ ይቅርባይነትን ያምላክ ፈቃድን የጠበቀ ታላቅ አስተማሪና ምሳሌ አባት ነው ::ማንዴላ ሁሉንም ነው ::ጀግናው ማንዴላ ...

መልካም ልደት ለክቡር የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ይሁን ::

አሜን

ሾተል ...........የማንዴላ ልጅ

እንዲያው ትንሽ አታፍርም በአንተ አይነት ውሻ አፍና የወያኔ ቡችላ ታላቁ እና ነጻነትን ለጥቁር ህዝብ ያመጡት
ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ሲጠሩ ? ትንሽ አይሰቀጥጥህም እንደደሀና ሰው ከከለሰ ዜማዊ ባሪያዎች እና ፍርፍር ለቃሚዎች ጋር ስለታላቁ የነጻነት ሰው ስትደሰኩር ?
ውሻ መጀመሪያ ሂድና ነጻናት የሚለውን ቃል ምን እንደሆነ አንብብና ተረዳ አንተ ግን ለድራኩላው እና ስለአፍሪካው ሞሶሎኒው ስለሂትለር አምላክህም ስለመለሰ ሸናዊት አውራ ? Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed Embarassed
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ስሙ ይናገር

ዋና ኮትኳች

Joined: 14 Mar 2008
Posts: 692

PostPosted: Fri Feb 12, 2010 8:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሾተል እንደጻፈ(ች)ው:
http://www.youtube.com/watch?v=GzUB2Vag8UI&feature=related

የዛሬ አስር አመት ለተፈታው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላ ይሁንልኝ ::

ሾተል ነን ....ጀግናን የነጻነት ታጋይን ከልቡ የሚወድና የሚያከብር

ሾተል ስላስነበብከን የማንዴላ ታሪክ አመሰግናለሁ ምንም እንኳ ታሪኩን ብናውቅም ደጋግመን ብንሰማው የማይሰለቸን ታሪክ ነው ያለው ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ማንዴላን እንዴት አድርገህ ነው ከመለስ ጋር የምታስታርቀው ?? መለስን እንደምትደግፍ ስለማውቅ ነው ከምሬ ነው ሾተል ሌላው የዚህ ሰው ታሪክ ከብርቲካን ሚደቅሳ ጋር የሚመሳሰል ነው የሚመሳሰሉትም
. ሁለቱም የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው
. ሁለቱም ያጠኑት ህግ ትምህርትን ነው
. ሁለቱም የነጻነት ታጋዮች ናቸው
. በሁለቱም ላይ የእድሜ ልክ ፍርድ ነው የተሰጠው አይገርምም
_________________
God is Great
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Fri Feb 12, 2010 9:49 pm    Post subject: Reply with quote

ስሙ ይናገር
Quote:
ሾተል ስላስነበብከን የማንዴላ ታሪክ አመሰግናለሁ ምንም እንኳ ታሪኩን ብናውቅም ደጋግመን ብንሰማው የማይሰለቸን ታሪክ ነው ያለው ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ማንዴላን እንዴት አድርገህ ነው ከመለስ ጋር የምታስታርቀው ?? መለስን እንደምትደግፍ ስለማውቅ ነው ከምሬ ነው ሾተል ሌላው የዚህ ሰው ታሪክ ከብርቲካን ሚደቅሳ ጋር የሚመሳሰል ነው የሚመሳሰሉትም
. ሁለቱም የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው
. ሁለቱም ያጠኑት ህግ ትምህርትን ነው
. ሁለቱም የነጻነት ታጋዮች ናቸው
. በሁለቱም ላይ የእድሜ ልክ ፍርድ ነው የተሰጠው አይገርምም

እናንተ ያዳምና የሄዋን ወይም የአርዲና የሉሲ ዝርያዎች እረ ባካችሁ ሰውን ታውቁት ይመስል አንጎላችሁን አሳምናችሁ ወደስኽተት አትሂዱ ?
ስሙ ይናገር ደግሜ ደጋግሜ ብየዋለሁ አሁንም ይገባኽ ከሆነ ደግሜ እልሀለሁ ::እኔ እውነትን እንጂ የምደግፈው የማንንም ድርጅትና ፖለቲከኛ አልደግፍም ::እኔ ኢትዮዽያ ተወልጄ ኬንያ በልጅነቴ ተሰድጄ አፈር ከድሜ በልቼ ከወባ ጋር የሞት ድነት ትንቅንቅ አድርጌ እንደማንኛውም ኬንያ በረኻ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተርቦ ተጠምቶ እንዳለና እንደነበረ እንዲሁም የሚወዳቸውን የስደት ወንድሞቹን በቀን ሁለትም አንድም እንደቀበረና እየቀበረ እንዳለ ስደተኛ ያንን ሁሉ መከራ አይቼ ከእግዚአብሄር ጋር በራሴ ላብና ጥረት ያለማንም ስፖንሰር አውሮፓ ገብቼ ለድጋሚ ስደት የበቃሁ አንድ ተራ የአፍሪካ ስደተኛ ነኝ ::ታድያ አፈር ከድሜ ስበላ ወላ ወያኔ በለው መለስ ዜናዊ ወይም ቅንጅት በለው ብርሀኑ ነጋ ወይም ወላጆቼ ሆኑ አገሬ አልደረሰችልኝም ::እንዲደርሱልኝም አልተማጸንኩም አልለመንኩምም ::በራሴ ጥረት ነው አሁን ላለሁበት የተሻለ ስደት የበቃሁት ::ስለዚህ ለማንም መሆንና ማንንም መደገፍ አያስፈልገኝም ::እድሜ እከኬን ላራገፈልኝ የኦስትሪያ መንግስት ::አክብሮ አንቀባሮ ስራዬን አመስግኖ ሙከራዬን አድንቆና በየለቱ ለጥረቴ ምስክርነት ሲሻው በጋዜጣ ሲሻው በመጽሄት ሲሻው በመጽሀፍ አውጥቶ ስታመም በነጻ አክሞ መብቴን ስፈልግ ጠይቄ እምቢ ብባል በድፍረት እንድቃወመው ፈቅዶ እያኖረኝ ነው ::ስራ ሰጥቶኝ ደጎስ ያለ ገንዘብ እየከፈለኝ ይገኛል ::

እና ማንም ዝተታም ሲንበራጨቅ እውነቱን ስለተነገረው ወያኔ ነኽ ኢሀዴግ ነኽ ምናምን ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም ::አይደለሁም ልሆንም አልችልምም ::እኔ ከማንም ጋር ሳልነካካ ቀሪ ጊዜዬን በሰላም መኖር የምፈልግና በነጻነት እያሰብኩ መኖር የምፈልግ ሰው ነኝ ::ሰው ነኝና የወደፊቱም መናገር ባልችልም ያሁኑ አቁዋሜ ግን ነው ::ግን በየትኛውም መድረክ እንደማንኛውም ሰው እድሉ ከተሰጠኝ በነጻነት አስቤ በነጻነት መጻፌንና መናገሬን አላቆምም ::የትግራይን ህዝብ ሲሰድቡ ስላጋለጥኩ ክቡር ጀግና የኛ መኩሪያና መከበርያ አትሌቶቻችንን ሲሰድቡ ድምጻቸውን ቀድቼ ለህዝብ ስላሰማሁ እልክ ይዞዋቸው ወያኔ ወያኔ ቢሉ እንዴው እውነት መሰላችሁ ?ብሆን ማናባቱ ይከለክለኛል ::ወያኔ አይደለም የፈለኩትን ብሆን መብቴ መሰለኝ ::ልቤንና ድፍረቴን አቁዋሜን እግዚአብሄር ሆናችሁ ልብና ኩላሊቴን ማወቅ አትችሉም እንጂ ብትችሉ ኖሮ ምንኛ ባወቃችሁኝ ነበር ::እኔ ምቾት የማልፈልግ ሲምፕል ህይወት የምኖር ነኝ ::የአለም ነገር እየገባኝ ያለ ....በራሴ አንጎል ማሰብ የጀመርኩ በተጨበጨበበት ማጨብጨብ ያቆምኩ ነኝ ::

ወያኔ ብሆን ኖሮ ይኼኔ በዚህ ብርድ ጊዜ እዚህ አታገኘኝም ነበር ::ምን አልባት ሱሉልታ ተራራ ላይ በቀን 40 እስከ 50 ኪሎሜትር ለመሸፈን ረጅም እርቀት ስሮጥ ታገኘኝ ነበር ::ነገረ አለሙን ሁሉ ትቼ እሩጫ እሩጫ እሩጫ ስል ታየኝ ነበር ::አንተና መሰሎችኽ ሰው ባልዋለበት ዋለ ከሚሉ ጋር ውዬ አታየኝም ነበር ::ምን ያደርጋል ልቤ ትልቅ ሳለ የያዘኝ ይዞኝ ኦሎምፒክን በቲቪ እያየሁ አለሁ ::እንደኔ በአብድ ጎኑ የተዘጋጋ እድል አዳሜ አያጋጥምሽ ....እራሴን በፈለኩት አገኛለሁ ስል ባልፈለኩት አግኝቼው በእስቲ ይሁን ኑሮ እንደምኖር ማን ባወቀልኝ ::ከምድረ አህያና ከብት ከማይበስልና ከማይሰለጥን ህዝብ ጋር መች መዋል ያስፈልገኝ ነበር .....የሚያስፈልገኝ መሮጥ መሮጥ መሮጥ ...ያቺ ኦሎምፒክ የሚሉዋትን ነገር መንካት ....ምን ያደርጋል ደርሼባት ነበር ....ግን ህግ አልባ የሆነ አለም ውስጥ እየኖርን ስለሆነ ያንን መቀበል የግድ ነውና ይሁን እስቲ ::አሁንም አልመሸም ::

እና ልል የፈለኩት ወደዳችሁም ጠላችሁም እንኩዋን መለስ ዜናዊ ወይም ወያኔ አይደለም ቭየና ያለው የኢትዮዽያ ኤምባሲ አያውቀኝም ::ነገር ግን ኢትዮዽያ ታውቀኛለች ::እኔም እምዬ ኢትዮዽያን አውቃታለሁ ::ኢትዮዽያ ደግሞ መሬትዋ ብቻ ሳይሆን ህዝቦችዋ ብሄር ብሄረሰቦችዋ ናቸው :: ማለት 90 በላይ ያሉት ብሄሮችዋንና ቋንቋዎችዋን ይጨምራል ....ታድያ ከብሄሮችዋ አንዱ ሲሰደብብኝ ሲንቋሸሽብኝ ያመኛል ::በዛ ህመም የተነሳ እውነት ውስጥ ስለገባሁ እምሰለኝ ተቃዋሚ ተብዬ ምድረ ሰነቻ የክትፎ ቀን ጅሎች አይን ውስጥ ያስገባኝ ::

ወንድ የሆንሽ ያልሆነ ቦታ ከታችሁ እራሳችሁን በቢሆን አለም ከምታስደስቱ የትግራይ ህዝብ ሲሰደብ ለምን ሰደባችሁ ብዬ የሰደባችሁበትን አውዲዮ ቀርጬ በማሰማቴ ይሄ አውዲዮ የኛ አይደለም ወይም እኛ አልተሳደብንም ብላችሁ ሞግቱኝ ::ስትዋሹ ማስረጃ አምጡ ይሄ ይሄ ውሸት ነው ስላልኩኝ ያንን ትክክል ነው ስትሉ ሞግቱኝ ....ግን አንዴ ወያኔ አንዴ ምናምን ብትሉኝ የምታመጡት ነገር አይኖርም ::እንደፎከራችሁ ስታገኙን እንደምትገሉን እንዳቀዳችሁ ትኖራላችሁ ::ምንም አላችሁኝ ምን እኔን አታቆሙኝም ::

ለእውነት ስል የማደርገው ነገር በእግዚአብሄር ዘንድ ንጹህና ቅዱስ ስለሆነና ከየትም በኩል ምክርና ጥቅም አግኝቼ የማደርገው ስላልሆነ እግዚአብሄር ይጠብቀኛል ....እንደገና ጠላቶቼ እኔ ደርስ ሲደርሱ እንድቀድማቸው ሀይልና ጉልበት ከጥበብ ጋር ይሰጠኛል ::ወሬ ወይም ቱልቱላ አይደለም እየጻፍኩ ያለሁት ::እንኩዋን እርስ በራሳችሁ ካልተደራጃችሁት አንድ ላይ ውላችሁ ዞር ስትሉ ከምትተማሙና ከምትመቀኛኙ ዘመነኛ ታጋይ አይደለም እግዚአብሄር በአቁዋም በሀይልና ጉልበት ከጥበብ ጋር ተደራጅተው ሲነድፉኝና ሲላቸው ኮማ ውስጥ ከተው ሲያሰቃዩኝ ከነበሩትም ቢጫ የበረኻ ወባዎች እግዚአብሄር ጠብቆኛል ::

ስለዚህ ሾተል ወይም አምባቸው አባተ ደጀኔ የማንም አይደለም የማንም ሊሆን አይችልም ::ግን የእውነትና የህሊናው ነው ::

ጨረስኩ ::

ሾተል ነን ....የራሳችን የህሊናችንና የእግዚአብሄር አምላካችን ነን
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Fri Feb 12, 2010 10:03 pm    Post subject: Reply with quote

ውይ ይቅርታ ይኸንን የት ሆኜ እንደጻፍኩት ሳልነግራችሁ ::ላፕቶፔን ይዤ ሽንት ቤት ሆኜ አይነምድር እየወጣሁ ሳለ ነው ::ወይም በሌላ አማርኛ ወገቤን እየሞከርኩ በነበረ ሰአት ነው ::አንዲት ጉዋደኛዬ የሴት ነገር ሆነና የተለያየ ሾፕ ላትገዛ ልትለካ ወስዳ ስታንገላታኝ ውላ እቤትዋ ወስዳ ሀይክላስ ምግብ አብልታ ሸኝታኝ አሁን ገና እቤቴ መግባቴ ነው ::እኔ ጋር ነው ያደረችው ::ጥሩ ጉዋደኛዬ ስትሆን የብድ አይደለችም ::እንደእህትና ወንድም የሚሉት አይነት ::በዚህ ብርድ ይታያችሁ ከቺኮች ጋር ወጥታችሁ አንዴ ባርኔጣ ሲለኩ እንደገና ሌላ ሱቅ ቀይረው አንዴ ቦላሌ ሲለኩ እንደገና ሌላ ሱቅ ሄደው አንዴ የጆሮ ጌጥ ሲለኩ ሲውሉና እናንተን አስከትለው በዚህ ብርድ ሲያፈጉ ቅር አይላቸውም ::አቤት የእቅዳቸው ብዛት ...አቤት ስመታዊነት ::ብዙዎቹ የሚሉዋቸውን አይሰሙም ታድያ በራሳቸው በተሳሳተ መንገድ ጭረው በሁዋላ ሉዘር ሲሆኑ መጥተው ያለቃቅሳሉ ::ጥሩነቱ የሰውን ልጅ ሰው ከተረዳው ጥሩ ስለሆነ ክብርነታችንን ጠቅሞታል ::

1 ሰአት በሁዋላ ሀይ ክላስ ቦታ ሳንጭር አንቀርም ::እስቲ ከራሳችን ጋር እንደምንሄድና እንደማንሄድ እንሙዋገት ::

ሾተል ነን
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፍሉሀ 40

አዲስ

Joined: 09 Jan 2010
Posts: 17

PostPosted: Sun Feb 14, 2010 11:29 pm    Post subject: Reply with quote

የማንዴላን ታሪክ ብናውቀውም ባናውቀም ስሙን በማየቴ ገባሁ ነገሩ የወፌ ቆመች አይነት ነው ያደረከው አባባሌ ጥሩ ሄደህ እያለህ ዱቅ አረከው ወደ ልቁ አፍህ ስድብህን ምስህን ረጨህ አበለሻሽህው የፈለገ ቢሆን ቤቱን ለማክበር ዝም ብለህ መቀጥል ነበረብህ የዚህን ታላቅ ሰው ስም አጎደፍከው ለመሆኑ ከዛስ በሀላ የሚያነብ ኢትዮፕያዊ ይኖራል ብዮ አልገምትም እንደው ደከምክ መጀመሪያ ራስህን አጥዳ የሰውን አባትና እናት የሚሳደብ ሰው የራሱን ቤተሰብ የጠላ ነው :: ባለ ብዙ ስም መሆን አያዋጣም ዞሮ ዞሮ የተለመደ ቃል እኮ ነው የምታፈልቀው ባሻ , ቬኑስ , ጅብ , ... እስቲ ዋንስ ፎር ኦል ተለወጥ !!! እዚህ ዋርካ ውስጥ ሰው ያንተን ባለጌ አጠያፈ ቃላት ማየት ሰልችቶታል :: እኛ ባህላችንም አይደለም :: ደግሞ የእግዚሀርን ስም ማስቀመጥህ ???? ጉድ እኮ ነው ጃል ::
_________________
Never exaggerate your faults; your friends will attend to that.
Robert c.edward phd
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Mon Feb 15, 2010 12:48 am    Post subject: Reply with quote

ፍሉሀ 40 እንደጻፈ(ች)ው:
የማንዴላን ታሪክ ብናውቀውም ባናውቀም ስሙን በማየቴ ገባሁ ነገሩ የወፌ ቆመች አይነት ነው ያደረከው አባባሌ ጥሩ ሄደህ እያለህ ዱቅ አረከው ወደ ልቁ አፍህ ስድብህን ምስህን ረጨህ አበለሻሽህው የፈለገ ቢሆን ቤቱን ለማክበር ዝም ብለህ መቀጥል ነበረብህ የዚህን ታላቅ ሰው ስም አጎደፍከው ለመሆኑ ከዛስ በሀላ የሚያነብ ኢትዮፕያዊ ይኖራል ብዮ አልገምትም እንደው ደከምክ መጀመሪያ ራስህን አጥዳ የሰውን አባትና እናት የሚሳደብ ሰው የራሱን ቤተሰብ የጠላ ነው :: ባለ ብዙ ስም መሆን አያዋጣም ዞሮ ዞሮ የተለመደ ቃል እኮ ነው የምታፈልቀው ባሻ , ቬኑስ , ጅብ , ... እስቲ ዋንስ ፎር ኦል ተለወጥ !!! እዚህ ዋርካ ውስጥ ሰው ያንተን ባለጌ አጠያፈ ቃላት ማየት ሰልችቶታል :: እኛ ባህላችንም አይደለም :: ደግሞ የእግዚሀርን ስም ማስቀመጥህ ???? ጉድ እኮ ነው ጃል ::

ፍሉሀ 40....በመጀመርያ በአሁኑ ሰአት 7695 ጊዜ ይኼ ክፍል ተከፍቷል ::ከዚህ በሁዋላ ላንተ የተዋቡ ሳር መሰል ግጦሾችን ሳበላኽ ይኼ ክፍል 7695 በላይ ሊከፈት ካልቻለ እኔ ከዋርካ ልታገድ ....እንደገና እንዳንተ ያለን ንገሩኝ ባይ ስለተናገርኩ ማንዴላ ክብሩን ካጣ እስኪ እንይና እናትኽን ፍል ውሀ ውስጥ ዘፍዝፌ ላንተ ላስነጫት ::ታድያ እናትህን ስትነጫት ፍል ውሀው ትን ብሎኽ እላይዋ ላይ አስታውከኽ ሞተኽባት ለቅሶ ትቀመጥ ...አመሰግናለሁ

ሾተል ነን .....ንገሩን ያሉትን እንነግራቸዋለን
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Sun Jul 18, 2010 8:35 am    Post subject: Reply with quote

የነጻነት አባታችን የኔልሰን ማንዴላ 92ተኛ የልደት በአል ዛሬ በመላው አለም ተከብሮ ይውላል ::

አምላክ ሆይ ለኔልሰን ማንዴላ እድሜና ጤና ስለሰጠኸው እናመሰግንሀለን ::

አባታችን ኔልሰን ማንዴላ እንኩዋን 92 አመት የልደት በአልኽ አደረሰኽ ::

ሾተል ነን ....ሀፒ በርዝ ደይ ማንዴላ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
agrani

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2006
Posts: 116

PostPosted: Sun Jul 18, 2010 6:33 pm    Post subject: Reply with quote

የነጻነት አባታችን መልካም ልደት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማሉሜ

አዲስ

Joined: 28 Jan 2010
Posts: 19
Location: ZULU LAND

PostPosted: Sun Jul 18, 2010 9:04 pm    Post subject: Reply with quote

S.A ሲታገሉ ሁሉም አፍሪካዊ አብሩአቸው ነበር ዛሬግን ያን የረሱት ይመስላል ...ለማንኛውም
http://www.news24.com/SouthAfrica/News/Two-killed-in-PE-spaza-shop-20100718

ቸር እንሰንብት !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Sun Jul 18, 2010 9:19 pm    Post subject: Reply with quote

ማሉሜ እንደጻፈ(ች)ው:
S.A ሲታገሉ ሁሉም አፍሪካዊ አብሩአቸው ነበር ዛሬግን ያን የረሱት ይመስላል ...ለማንኛውም
http://www.news24.com/SouthAfrica/News/Two-killed-in-PE-spaza-shop-20100718

ቸር እንሰንብት !!

በጣም የሚያሳዝን ዜና .....የሚገርመው የአለም ዋንጫው ይጠናቀቅ እንጂ ምድረ ስደተኛና የውጭ አገር ሰዎችን ከደቡብ አፍሪካ ምድር እናጠፋለን ብለው ዝተው ነበር ....ይኼው ጀመሩ ...ቃላቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ቀደሱ ...

የሚገርመኝ የስደተኞች ኮሚሽነር ዛቻውንና ስደተኞቹን ችላ ማለቱ ነው ...

እንግዲህ ለወንድም እህቶቻችን መጸለይና የሚቻል ከሆነ ለአለም ህዝብ መጮኽ ነው

የሞቱትን ነፍስ ይማር

ሾተል ነን
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6865
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Mon Jul 18, 2011 6:00 pm    Post subject: Reply with quote

መልካም ልደት ለአባታችን ኔልሰን ማንዴላ ይሁን ::ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር ይስጥልን ::

ሾተል ነን ....ሐፕይ በርዝ ደይ ማንዴላ ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
Page 3 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia