WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
Ethiopian Origin-African American Greeks
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዮፍታሄ

ኮትኳች

Joined: 17 Jul 2007
Posts: 112

PostPosted: Thu May 14, 2009 5:39 pm    Post subject: Reply with quote

የሴታሴቶቹ ሮሃንያ መናፍስት ስም ዝርዝር ከብዙ በጥቂቱ :-

  በቅደም ተከተል : በሱባ በግዕዝና በአማረኛ :

  አቲት = አቲትዮን = አቴቴ ዱላ

  ሩህ = ራሄሎ = ሰይፈ አጥራ

  ዲላ = ሙላድ = አድይ ክምር ደማሚት

  ፍቲ = ፍታሉ = ፍትፍቴ

  ሸምሸል = ነገርጋር = ወርቂት

  ሰረቲን = አርሴማ = ዘማሪት

  ጭጫያ = ጸጌ ወርቅ = እንቁላል ነጪት

  ጀርጀርቲ = ዋካይ = ዳንዲት ሻንቂት

  አዶሌ = ወለተ ወርቅ = አዶሌ አዶሊት

  ትእያ = ንዝኅወርቅ = ቅርንጭፍት

  አድያ = ፍሬወርቅ = አደደ ክምር

  አሪቴ = ህሪት = ጫንጫ

  ኦርያ = አረቲ = አረርቲ

  ደቤ = ዓይነ ወርቅ = ዱፍቲ (በኦሮሞ )

  ርሂያ = ርህት = ራራሂት

  ጥእያ = እግዚእክብራ = ነገርጋር - ገርጋሪት

  አፍሊስ = እሌኒ = አልቴ - አልያ ፍላሊት

  ቤርቤር = ርብቃ = በቃባንቺ

  እትየኤል = እግዚእ -ባረካ = በአንቹ ይሁን ጫጫቴ

  ማቲያ = ዓይነ መብረቅ = ጫጫታ ጭልጥ ብላ

  ሶፍፍያኤ = ንግሥትለአቡሃ = ሶፎንያ ሶፊ

  ማማኤል = መውዴር = ማሚቴ -ማማዬ

  እንስጥጥያ = እግዚኃይላ = ነጭት እቼቴ

  ሜሪቶቤር = ሜሪ = ማርብላ

  ቡቲ = አልቡት = አልባባት ገለባት

  አንጥያ = ሠናይት = ዲራባልቲሃት - ባልቴት

  አሜር = መንበረ ፀሐይ = ጀንበሪቱ ጀርጀርቲ

  ሙጀጂ = አልበምህረት = መቅርጭት

  ሸምሸም = ሰፎረ ወርቅ = ቀራሚድ

ዋናዎቹ የሴት መናፍስት በነዚህ ስም የተጠቀሱት ናቸው ::

እንግዲህ ከላይ በተደርደሩት ስሞች በመጠቀም ምንያህሎቹን ስማቸው ሲጠራ የምናስታሰው ይሆን ?

ለማንኛውም አልፎ አልፎ ከስማቸው በመነሳት : በታሪክ በጽሑፍ የምናውቃቸውን ለማገናዘብ እሞክራለሁ ::
ሌሎቻችሁም የምታውቁትን በታሰሙን ጥሩ ነው ::

ለአሁኑ Easter Island እና Mexico Olmec heads የሚባሉትን ከዚህ በታች ባለው ፎቶው ተመልከቷቸው !

በእውነት እነዚህ ታላላቅ በድንጋይ የተቀረጹ የሰው ምስሎች .....could we say such huge monumental structures were built by the local population who never possessed iron instrument, who never had writing, without the help of some "advanced" entities?

http://img58.imageshack.us/img58/9681/sa8500541.jpg

http://img18.imageshack.us/img18/7237/museo321.jpg

እመለሳልሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዮፍታሄ

ኮትኳች

Joined: 17 Jul 2007
Posts: 112

PostPosted: Thu May 14, 2009 6:50 pm    Post subject: Reply with quote

ብርኃናዊት መጣሁ : ለብዙ ደቂቃዎች አንዳለ ትራክቱ /ዓምዱ ከዋርካ እልም ብሎ ጠፍቶብኝ ነው Surprised

አሁን ደሞ መጣ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Thu May 14, 2009 8:02 pm    Post subject: Reply with quote

ዮፍታሔ :

ቤቱ ለእኔም --! ብሎብኝ ነበር :: አሁን ነው ያየሁት ::

የሴታሴቶቹን መናፍስት ስም ዝርዝር ደጋግሜ አነበብኩት :: አንዳንዱ የሚገርም ነው - እሌኒ ? ርብቃ ? ወለተወርቅ ? አርሴማ ?.... በቃ ሰይጣን ከቅዱሳን ጋር መፎካከር ልማዱ ነው አይደል ?

አቴቴን እንኳ በደንብ እናውቃታለን :: እመሙላድንም እንዲሁ :: የወላዶችን ጽንስ የምታበላሽ ናት የሚል ነገር አንብቤያለሁ ::

በእርግዝና ጊዜ በጣም ጥሩ አቋም ላይ ሴቲቱ እንድትገኝ ... የሚታዘዙና የሚደረጉ ነገሮች ነበሩ መሰለኝ .. በባህላችን (ሳይንሱ የሚያዝዘው እንዳለ ሆኖ .. በሃይማኖቱ ደግሞ : ጾምና ጸሎትን አብዝታ እንድታደርግ ይመከራል .. ቅዱስ ቁርባንም እንዲሁ )...

እና ከዚያ ጋር የተያያዘ አንዳንድ የባሕል ህክምና ሰምቼ ነበር :: አሜሪካ ውስጥ እንኳ : ለመጽነስ ፕሮግራም የያዙ ሴቶች ... በፍራፍሬና ቅጠላቅጠል የሚጾሙ አሉ ... juice feast ይሉታል መሰለኝ :: በዚያን ወቅት : ብዙ ስሜታዊና አካላዊ የሆኑ ጥገኛ ነገሮች (emotional and physical parasites) ወደ ጽንሱ እንዳይተላለፍ በሚል ነው ይህን የሚያደርጉት ::

የእኛም ልማድ ጥሩ ነበረ - በእርግዝና ጊዜ የጾሙ ብዙ ቅዱሳን ታሪክን እናውቃለን :: ከእመቤታችን ጀምሮ :: ፍልሚያው ከነዚህ ጋር ነው ለካ !
(ድንግልስ ምንም አይነት ሕጸጽና ስሜታዊ መረበሽ ባይኖርባት : ቢያንስ ጾሟን እንደመባ አድርጋ ልጇን ተቀብላበታለች :: )

የወንዶችንም ባሕርይ በጣም የሚለውጡና ሴታ ሴት የሚያደርጉ መናፍስት እንዲሁ አስተዋጾኦዋቸው ቀላል አይደለም :: ትዳር ከመጥላት : ሴትን ከመጥላትና ከመደብደብ ጀምሮ : ራስም ሴታሴት እና ሉጢ እስከመሆን ድረስ የሚያደርሳቸው ነው ይሄ ::

... ይህን የመሳሰለ እውቀት ዛሬ ከኋላቀርነትና ከጥንቆላ ጋር በጭፍን አብሮ ተቆጥሮ .. ትውልዱ የመናፍስት መጫወቻ ሆኗል :: ሰይጣን ስትራተጂ ሲቀይር : እኛ አንነቃም :: እነ አቴቴ : የብሪትኒን ሱሪ ለብሰው ከች ሲሉ ... ምስኪን እህቶቻችን ከአገርልብሱ አቴቴ .. ወደ ጅንሱ አቴቴ በመሻገር አስደናቂ አረማመድ አሳይተዋል ....

ቀባጠርኩ !

እመለሳለሁ

ብርኃናዊት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዮፍታሄ

ኮትኳች

Joined: 17 Jul 2007
Posts: 112

PostPosted: Thu May 14, 2009 9:53 pm    Post subject: Reply with quote

እንደመሰልኝ የስሞቹ ነገር የራሱ ትርጉም ያለው ነው : በተለይ በግዕዙ ::

ለምሳሌ : ወለተ ወርቅ የሚባለው መናፍስት : በሳባ ስሙ አዶሌ ሲሆን በአማርኛ አዶሌ -አዶሊት ተብሎ ተጽፎ እናገኘዋለን :: እንግዲህ ይህ ለኔ ምን ያስታውሰኛል መሰለሽ ? አዶላ የሚባለውን ወርቅ የሚወጣበትን የሃገራችን ክፍል ነው ! አዶሊ በግዕዙ ወለተ ወርቅ የተባለችው በቀጥታ ትርጉሙ : የወርቅ ልጂት : ስለሆነ ከወርቅ ማአድን ጋር የተያያዘ ባህርያዊ ትስስር ሊኖር እንደሚችል ይጠቁመናል ::
እንዳነበብኩት ብዙዎች መናፍስቶች : የራሳቸው እንደ መለዮ የሆነ ከምድር የሚወጣ ንጥረነገር ወይም ማአድን በተለይም የከበረ ድንጋይ ጋር ልዩ የሆነ ስበት አላቸው :: ምክንያቱን ባላውቀውም : ለኛ ምግብና መጠጥ እንደሚያስፈልገን ለነሱ ምድራዊ ......elements.....እና አንዳንድ የአታክልት ሥራስሮች እንደ ምግብ ያስፈልጋቸው ይሆን ? እኔንጃ ብቻ ልብ ብሎ ለተመለከተው ብዙ ማገናዘብ የሚቻል ይመስለኛል ::

አሪቲ ; አረርቲ የተባለችውን ብንወስድ : አሪቲ የተባለ መልካም መዓዛ ያለው ተክል አገር ቤት እያለሁ አስታውሳለሁ :: አረርቲ የሚባል ወረዳ /አውራጃ ?: ባልሳሳት በአርሲ ወይንም ሰሜን ሸዋ አካባቢ እንደነበር አውቃለሁ ::

አሁን ትዝ ሲለኝ አንዳንድ ዛር አለባቸው የሚባሉ ሰዎች ልጅ ሆኜ ሳስታውስ : የዛሩን ግብር በሚያወጡበት ዕለት : ቤቱን በቃጤማ ሳር አሪቲ በመሳሰሉት እጽዋት ከሞሉ በህዋላ ; የሆነ ሽቶ ያርከፍርክፉበት ነበር :: በህዋላ ባለዛሩ ሰውዬ ወይንም ሴትየዋ አጓርተው አጓርተው ሲያበቁ በከሰሉ ፍም ላይ ያለምንም መቃጠል ባዶ እግራቸውን እየትረማመዱ ሰዎች በብልቃጥ የሚሰጥዋቸውን ሽቶ ጭልጥ አድረገው ሲጠጡት በቤቱ ቀዳዳ ተደብቀን እየተመለክትን አቤት ጉድ ጉድ እንል ነበር ::
ይሄ በልጅነቴ ሐረር ፈርስ መጋላ አካባቢ የአደሬ ጎረቤቶቻን ቤት ወስጥ ሲደረግ የተመለከቱት ነው ::

ለማንኛውም : ቆስጤ ብኤል ዘቡል (አዶየ አዶከበሬ ); ቃፍያ -አጵሎን (አባ ቆፍድድ ) እና ዳጎን አደን (አባጉንጉን ) እነዚህ መናፍስት /አማልክት በመጽሐፍ ቅዱስም በታሪክ ስነጽሑፍም የበደምብ የታወቁ ስለሆነ : ስለነዚህ ሮሐኒያን ስነጽሑፍ እና ......mythology/legend.....ምን እንደሚል ያነበብኩትን ይዤ እመጣለሁ ::

አሁን ወጣ ልበል ::

p.s. I am watching the video(Neqa) you suggested......ብዙ ነው Smile እያለፍኩ እያለፍኩ እመለከተዋለሁ በውነት ግን ይደንቃል አንዳንዱም ትያትር እየመሰለኝ ነው : ብቻ እኔ ምን አውቃለሁ ብለሽ ነው ? ግን የገረመኝ የሄ ሁሉ ወጣት በነዚህ ዛር መናፍስት ተጥለቅልቋል ማለት ነው : ደሮ እንደዚህ በማሕበረ ሰቡ የዚህን ያህል የተንሰራፉ አልመስለኝም ነበር ; አሁን ምን ተገኝቶ ይሆን ሰው ሁሉ : አዳል ሞቴ ; ጠቋር ; ብር አለንጋ አያለ የሚቀባጥረው ?

I am extremely perplexed by the familiarity of the youth with these unclean spirits Exclamation what gives?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀረር 700

መንገደኛ

Joined: 11 May 2009
Posts: 6

PostPosted: Fri May 15, 2009 8:55 pm    Post subject: Thanks for sharing what you know Reply with quote

ዮፍታሄ

ይቅርታ በአማርኛ ታይፕ ለማድረግ ፍጥነት የለኝም .

Thank you for sharing what you know. I am so amazed by the things that you have posted. As you know we hear many things about witches, demons, buda etc. in our country. But I have never heard of such detail information about these things. And I have never believed that they exist. By the way I am from Adre Tiko---when you mention your experience in Ferse MegalaIn my thoughts went back to my home town hehheh.

When I was a kid, I heard a story while neighbors drinking Buna. The story goes like this: There was one family living in Jegole whose daughter was so sick and expected to die. There was a man who came from Lilabela who heard about the sick girl and approached her father. The man told the father that he has the ability to talk to the dead and the demons and he can save his daughter, if he let him marry her after he cures her. The father agreed and the man did his thing and sure enough he cured her. As per their deal, the father let him marry the girl. I also heard that the girl was so beautiful but the man who said he can talk to the demons and evil sprits were so ugly and poor. After that, people afraid of him thinking he might hurt them and kept distance from him.

Do you know about this story? How do some people talk to demons and evil spirits? What power or knowledge they have to do this? And what circumstance led them to be in this kind of work?
_________________
Be Nice to other ppl!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዮፍታሄ

ኮትኳች

Joined: 17 Jul 2007
Posts: 112

PostPosted: Tue May 19, 2009 7:11 pm    Post subject: Reply with quote

እንደምነህ የአደሬ ጢቆው ልጅ Very Happy

እነዚህን ጽሑፎች ያገኘሁት ከቀድሞ መጽሐፍት ነው : ሆነ ብዬ የጥንት ኢትዮጵያዊያንን ድርሰቶች ስለምከታተል : የነርሱን ቃል ነው የማስተላልፈው : እንጂ በራሴ የተለየ መረጃ ኖሮኝ አይደለም ::
ዋናው ዓላማዬም : እነዚህን የግዕዝ ጽሑፎች : ካለን : የመጽሐፍ ቅዱስ : የታሪክና የሚቶሎጂ ዘርዝሮች ጋር በማነጻጸር አንባቢው የራሱን የተሻለ ግንዛቤ እንዲወስድ ማድረግ ነው :: በተለይም በዓለም ታሪክ አንዳንድ ዕንቆቅልሽ የነበሩና አሁንም የሚመስሉ ትዕይንቶች በጠራ መልኩ ልንመለከትበት የሚያስችል መነጽር ይሰጠናል በሚል ነው ::

ለምሣሌ : በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ <<...... የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ : ከመረጥዋቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ .........>>

የሚለው ጽሑፍ በታሪክ : ብዙ ጥያቄዎችን ያሰነሳ ነበር አሁንም ነው :: እነዚህ ወደ ምድር የወረዱት "የእግዚአብሔር ልጆች " እነማን ናቸው ? ከሴቶች ጋር ተዋለዱ ሲልስ : እንደ ሰው ልጅ በግብረ ሥጋ ነወይ ? የተወለዱት ልጆቻቸውስ ወዴት ገቡ ? በጥፋት ውኃ : ከኖሕና ቤተሰቦቹ በስተቀር ሌላው ሲደመሰስ : አብረው ጠፉ ወይ ? ወይንስ ወደቀድሞው ተፍጥሯቸው ተመለሱ ? ይህንንና የመሳሰሉት ጥያቄውች ይነሳሉ :: መጽሐፈ ሄኖክ የተባለው መጽሕፍ : ለነዚህ ጥያቄውች : በከፊሉ መልስ ስጥቶበታል : በከፊል ግን ጥያቄውቹ እንዳሉ ነው ::
ከላይ የቀረበው መጽሐፍ ደግሞ : ከሥረ መሠረቱ ሄዶ የነዚህን ዕንቆቅልሽ ነገሮች : ከሞላ ጎደል የመለሰው ይመስላል :: ስለዚህ የሰው ልጅ ዓለምን የሚቃኝባት መነጽር በተሻለ መልኩ እየጠራና ለዘመናት የተሸፈነውም እየተገለጠ የመጣ ይመስላል ::

ስላለከው ታሪክ በግሌ የማስታውሰው ነገር የለም : ነገር ግን ተመሳሳይ ታሪኮች በየመጽሐፍቱ ይገኛል : በተለይ በተረትና ምሥሌ መልኩ (እንደ ደረባ ደረብራባ ) በምትሐት ታሪኮች በዓለም ስነ ጽሕፉ ውስጥ የሚገኙ ብዙ አሉ :: ስለዚህ እውነት ይሁን ውሸት ባይታውቅም : እንዲህ ያሉ ነገሮች በየቦታው የሰማሉ ::

ችሎታው ያላቸው ሰዎች : ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩት "በድግምት " ነው ይባላል :: የሚነጋገሩትም በተለያዩ ለዚህ ተግባር በሚውሉ "ቃላት " ድግግሞሽ በመጠቀም ተጠሪውን ....specific entity....ካለበት በመቀስቀስ ወይም በማዘዝ : ድግምት በመሥራት ነው ለምሣሌ ...........ጨጨጨጨ .... ቀቀቀቀቀቀ ........ጃጃጃጃጃ .........ራራራራራራ .....ወዘተ ... በዚህ መልኩ "የደገማል " ይባላል ::
እንግዲህ በዚህ መልኩ : በደጋሚውና በሚጠራው መናፍስት ያለው ግንኙነት ይካሄዳል ሆኖም በዚህ .............transaction, which party has the upper hand, the human or the alien entity........የሚለው ጥያቄ እንደ ደጋሚው .....extent of knowledge.......የሚወሰን ሳይሆን አይቀርም ::
የጥንቱ የዕስራኤሉ ንጉሥ ሰለሞን : መናፍስት በእግሩ ስር እንደተገዙለት ለብዙ ነገሮችም በውድም በግድም ያገለግሉት እንደነበር በርካታ መጽሐፍት ተጽፏል :: እና : ሰዎች : ገንዘብ ለማግኘትም ለዕውቀትም ወይም ለቂምበቀልም ቢሆን እንዲህ አይነት ስራዎች በታሪክ ሲያደርጉ አልፈዋል : አሁንም በዚሁ መልኩ የሚጠነቁሉ በመላው ዓለም ሞልተዋል ::

.....................................................................................................................

ብርኃናዊት : .....Credo Mutwa.... ቃለምልልስ ሰማሁት : የሚገርም ነው :: ራሱ ሰውየው ግን በዚሁ ህይወትና እምነት የተጠመደ ይመስላል ::
.....Reptilian blood line......ስለሚባለው እዚህም እዚያም አይቻለሁ : ይህንን ነገር የጀምሩት : ዴቪድ አይክና ዘካርያ ሲቺን ; ትሑፍቻቸውን ተመልክቼው : ለኔ : ብዙም ተአማኒነት ያገኘሁባቸው አይደለም : በተለይ ዴቪድ ክርስትናንም : ከነዚሁ የእባብ ዘረማንዘሮች ጋር ለመደመር ያደረው ሙከራ የሚረባ ሆኖ አላገኘሁትም : አብዛኛው እንደ ዳቪንቺ ኮድ .....sensationalism.....ላይ የተመርኮዘ ተራ ፈጠራ መስሎ ነው የታየኝ በኔ በኩል !

ስለ ፒራሚዶቹ ያልሽውን ብታቀርቢው መልካም ነበር ::

ሰላም ሁኑ

.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Tue May 19, 2009 10:19 pm    Post subject: Reply with quote

ዮፍታሔ እንደምነህ !

ክሬዶ ሙትዋ ያያቸውን ነገሮች የሚተረጉምበት መልኩ ሳይሆን : እርሱ ከገጠሙት ነገሮች እኛ የምንረዳው ነገር ምንድነው በሚል መልኩ ነበር እኔ ያየሁት :: ሰፊ የአፍሪካ ባሕላዊ አስተሳሰቦች እውቀት አለው :: ለምሳሌ "በአፍሪካ አምላክ የሚባል ነገር ካለ : እርሱ ሊበላ የሚገባው ነገር ነው " የሚል የቆየ አባባል አለ ያለው ነገር ገርሞኝ ነበር :: ስለ ሥጋና ደሙ ትንቢት በሕገ ልቦና ሲነገር የነበረውን ይዘው ይሆን ? ብዬ አሰብሁ ::

ስለ reptalian ደግሞ - ክሬዶ ሙትዋ እና ዴቪድ አይክ ከሁለት የተለያዩ ዓለማት የተገኙ ሰዎች ናቸውና - በየመልካቸው ሊታይ ይገባል ብዬ አስባለሁ ::

እኔ በግሌ - ሰይጣን የሚጫወተውን ጨዋታ ነው እነዚህ ሰዎች በአንድም በሌላም መልኩ ያዩት ብዬ እገምታለሁ :: ከዚያ ውጪ ሊሆን አይችልም :: የሳበኝ ነጥብ ግን : ሰይጣን እንዴት አድርጎ ነው በፖለቲካችን ውስጥ : በኢኮኖሚያችን ውስጥ : በማኅበረሰባችን ውስጥ : .. የሚጫወተው የሚለውን ነገር የነዚህ ሰዎች ጥናትና ትዝብታቸው : በደንብ የሚገልጽ ስለሆነ ነው :: የዲክታተሮች ፖለቲካ ሰይጣን የሚቆጣጠረው ነገር ከሆነ (በርግጥም ነው ): በትምህርትና በመሣርያ ልንመክተው አንችልምና : አእምሮና መንፈሳችንን የተቆጣጠረውን ነገር : በግልና በማኅበረሰብ ደረጃ : እንዴት አድርገን መመከት እንዳለብን ነው ማወቅ ያለብን ብዬ ነው የማስበው :: ለችግር የምንጋለጠው : መንፈሳዊውን ዓለም : ዝም ብለን በፋንታሲ የምንጫወተው አስተሳሰብ አድርገን ቆጥረነው : በማኅበረሰብና በሥነ -መንግሥት ውስጥ ተጨባጭ የሆነ አስደንጋጭ ቦታ ያለው መሆኑን ሳንረዳ ስንቀር ነው ብዬ አምናለሁ :: እንዲያ ባይሆን ኖሮ : ዮሓንስ ራዕይ ስለሰይጣን ሲያወራ : በተለየ ሁኔታ የዓለም መንግሥታትንና : እነርሱ የሚያካሂዷቸውን ሕዝባዊ ነገሮችን (መሸጥ መለወጥ : ጎሳ ነገድ ቋንቋ : የሚባሉትን ነገሮች ..) በአትኩሮት አይጠቅስልንም ነበር ::

ከዚያ አንጻር : ዴቪድ አይክም ሆነ ክሬዶ ሙትዋ : እንዲሁም ሌሎች መንፈሳዊውን ዓለም ለማየት የሚሞክሩ ሰዎች የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ በመከታተል : የግል አስተያየታቸውን ከላዩ ላይ 'እፍፍ ... እፍፍ !' ብዬ አራግፌ : ፋክቱን ብቻ ለማየት እሞክራለሁ :: እንዲያ ሳደርግ ብዙ ጊዜ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር የሚጋጭ ነገር አላይበትም :: (እንዳልኩህ የግል አስተያየታቸውንና their way of connecting the dots .. አልቀበልም :: ግን ዶቶቹን ብቻ እንዲያሳዩኝ እጠቀምባቸዋለሁ :: )

ይህን ያህል ስለነሱ ካልሁ ዘንዳ ....

ወደ ፒራሚዶቼ ልግባ :-

መጣሁ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Tue May 19, 2009 10:39 pm    Post subject: Reply with quote

"ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው : የተዋሕዶ አንበሳም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው " ይላል የመጽሐፉ ርዕስ ::

በአባ ተስፋ ሥላሴ 1988 ተጻፈ :: በአዲስ አበባ ታተመ ::

አለፍ አለፍ እያልሁ : ስለፒራሚዶቹ ያነሱበትን ቦታ ልጻፈው :-

ኪሩቤልና ሱራፌል

ዘለዓለማዊ ቅዱስ የሆነ መንበር የተሸከሙ የጥበብ ኃይሎች : ኪሩቤልና ሱራፌል ሙሉ ለሙሉ በዓይን የማይታይ : ኅብሩ የማይታወቅ በአንድነትና በሦስትነት የሚጠራና የሚመሰገን : ለዘለዓለም የማይጠፋ የእሳት ብርሃን የሆነ ዙፋን ወይም መንበር የተሸከሙና የያዙ : ወይም እርሱ የተሸከማቸው አራቱ እንሰሳት የሚባሉት ሲሆኑ : እነርሱም በአራቱ ክፍለ ዘመናትና በአራቱ ወንጌላውያን የተመሰሉ ናቸው ::

1. ኪሩቤል የሚባሉት ኃይሎች - በሰው የተመሰለ ማቴዎስና በአንበሳ የተመሰለ ማርቆስ ሲሆኑ :

2. ሱራፌል የሚባሉት ኃይሎች ደግሞ - በላም የተመሰለ ሉቃስና በአሞራ የተመሰለ ዮሓንስ ናቸው ::

.....

በታማኝነት የቆሙ አለቆች

ሚካኤል
ገብርኤል
ሩፋኤል

እነዚህ ሦስቱ ሊቃነ መላእክት ለእያንዳንዳቸው 6 የብርሃን ክንፍ ያላቸው ሲሆኑ : የኃይል ሁሉ መገኛና ምንጭ የሆነ የብርሃኖች ብርሃን : የኮከቦች ኮከብ : የፀሓዮች ፀሓይ ከሆነ ከእውነተኛው ፀሓየ አፍ በየቀኑ የሚወጣውን 2 ስለት ያለውን የሰይፍ ትእዛዝ በመቀበል በተጠንቀቅ የሚጠባበቁ ናቸው :: ...

በአይን ሲታዩ የሚያስደንቁ ኃይሎች

1. የሰው መልክ
2. የበግ መልክ
3. የአሞራ መልክ
4. የአንበሳ መልክ
5. የተኩላ መልክ

Arrow የሰው መልክ የሚመስለው ኃይል : እግሩ እንደአንበሳ እግር ሆኖ : እጅና ፊቱ እንደሰው የሆነ : የስንዴ ዘለላና የፀሓይ ምልክት ያለበት ሞላላ ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ነው ::

Arrow የበግ መልክ የተባለው ኃይል ደግሞ : እጅና እግሩ ሰውነቱ በሙሉ እንደሰው መልክ ሆኖ : ከአንገቱ በላይ ግን አራት ቀንድ ያለው በግ የሆነ : የዘንባባና የፀሓይ ምልክት ያለበት ደፍጣጣ የሆነ ሰውድ በራሱ ላይ የደፋ ነው ::

Arrow የአሞራና መልክ የሚመስል የተባለው ኃይል ደግሞ : እጅና እግሩ ሰውነቱ በሙሉ ልክ እንደ ሰው አካል ሆኖ : ከአንገቱ በላይ ብቻ የአሞራ ፊት የሆነ የዘንዶና የፀሓይ ጨረር ያለበት ክብ የሆነ ዘውድ የሆነ ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ነው ::

Arrow የአንበሳ መልክ የተባለው ኃይል ደግሞ እጁና እግሩ : ሌላው ሰውነቱ በሙሉ እንደሰው አካል ሆኖ : ከአንገቱ በላይ ብቻ ጆሮው ወደኋላ የተኛ አንበሳ የሚመስል ነው ::

Arrow የተኩላ መልክ የሚመስል የተባለው ኃይል : በእጁና ደረቱ እስከወገቡ ድረስ እንደሰው አካል የሆነ : እግሩ ደግሞ የፈረስ ኮቴ ሲሆን : ከአንገቱ በላይ ግን ጆሮው ወደ ላይ ቀጥ ብሎ የቆመ : ሲያዩት የሚያስፈራ የተኩላ ገጽ ነው ::

እንደነዚህ ዓይነቱ ፍጥረታት ከሚደነቁ በስተቀር : በሰው አእምሮ የሚመረመሩ አይደለም :: ቢሆንም : ለእያንዳንዳቸው 4 ሰማያዊ ክንፍ ያላቸው የተደበቁ ልዩ ልዩ የሆኑ ምስጢሮችንና የጥበብ ሥራዎችን ለሰው ልጆች እንደሚገልጹ ይነገርላቸዋል ::

ወደ ኋላ ሄደት ብዬ ከዚህ የጀመርኩበት ምክንያት አለኝ ::

እመለሳለሁ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Tue May 19, 2009 10:56 pm    Post subject: Reply with quote

የቀጠለ ...

..እነዚህ ኃይሎች : በዓለም ውስጥ በጣም አስደናቂ የሆኑ ሥራዎችንና ሥነ -ጥበቦችን የሚሠሩና የሚያሠሩ እነርሱ መሆናቸውን የሥነከዋክብትና የሥነፍጥረት ተመራማሪዎች የሆኑ የጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጽፈዋል ::

በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ : በመሬትና በባሕር ውስጥ የተደበቁ ወይም የተቀበሩ ልዩ ልዩ ሕንጻዎችና : የፒራሚድ ባለ ሶስት ማዕዘን ከተሞች መኖራቸውን : እንዲሁም የተለያየ ቅርጽ ያላቸው ሃውልቶችም ጭምር እንደሚገኙ አስረድተዋል ::

1. አሐሜነስ መዝገበ ሰማያትና አውደ ከዋክብት በሚል ርዕስ - 1900 ከክ / በፊት የተጻፈ

2. ሄኖክ አዶናይ - የፍጥረት ሁሉ ምንጭ የሆነ የፀሓዮች ፀሓይና ሥራዎቹ በሚል ርዕስ 800 ከክ //በፊት የተጻፈ ::

ሁለቱም መጻሕፍት እስካሁን አሉ ብለው ጽፈዋል አባ ተስፋ ሥላሴ ::

በኢትዮጵያ ውስጥ ፒራሚዶቹና ሌሎች የተቀበሩ ከተሞች እንዴትና በማን እጅ ተሠሩ ?

በቅድሚያ ትንሽ ስለግብጽ ፒራሚዶች ልግለጽ ይላሉ አባ ተስፋ ...

..... ከየሃገሩ : የተለያዩ ተወላጆች የተስሳተ የቃል መረጃ በመቀበል : ራሳቸው ተመራምረው እንዳገኙ በማስመሰል ያቀረቡት ጽሑፍና ጥናት ሁሉ ሐሰት ነው ይላሉ ...

ከግብጽ ፒራሚዶች በፊት : እነርሱ የማያውቋቸው 9 የፒራሚድ ከተሞችና እንዲሁም የአክሱምና የላሊበላ አይነት 17 ከተሞች ይገኛሉ :: የአክሱም አይነት 7 ሲሆኑ : የላሊበላ አይነት ደግሞ 10 ናቸው ::

ማን እንደሰራቸውና በምን ኃይል እንደተሰሩ አብዛኛው በምሥጢር እንደተጠበቀ ሆኖ ... ባጭሩ የሚከተለውን ላስረዳ ይላሉ .. አባ ተስፋ ...

Arrow በሩፋኤል እጅ የተሰሩ :-

... በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ፒራሚዶችና በጣም አስደናቂ ከተሞች የተሠሩት በሩፋኤል ትእዛዝ ሲሆን : በተለይ ደግሞ በጥንት ኢትዮጵያ ወደብ በነበረው በአዱሊስ ወደብ የቀይ ባሕር አካባቢ የተሰሩት የፒራሚድ ከተሞች የኃይሉ ማረፊያ እንዲሆኑት የተሠሩት በራሱ በሩፋኤል እጅ ነው ::

የፒራሚዶቹ ሥራ ባለ ሦስት ማዕዘን ወይም ትራያንግል ሲሆን : ቁጥራቸውም 3 ናቸው :: የተሠሩትም መበላለጥ ሳይኖርባቸው እኩል ሆነው እንደሥላሴዎች ሥዕል ሲሆኑ : 100,000 ሜትር ርቀት ላይ በአስደናቂ ሁኔታ ቁመው ይታያሉ ::

ሥራቸውም ዓይነቱ የማይታወቅ ድንጋይ የሚመስል ሆኖ : ቅጥልጥል የሌለበት አንድ ወጥ ነው :: ሦስቱም ፒራሚዶች በጣም የሚያምር የራሳቸው የሆነ ሦስት ቀለም አላቸው :: ይኸውም : ከአዱሊስ ፊትን ወደምሥራቅ አዙሮ : በተለየ ዓይን ሲመለከቷቸው :-

Arrow ከመሐል ወደቀኝ ያለው ፒራሚድ ቀለሙ ፍጹም አረንጓዴ ነው ::

Arrow መሐለኛው ቢጫ ቀለም ያለው ሲሆን :

Arrow በግራ በኩል ያለው ደግሞ ቀለሙ ፍጹም ቀይ ነው ::

ማለትም እንደዛሬዋ እናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ -ብጫ -ቀይ ነው ::

ቢሆንም : የፒራሚዶቹ ውስጠኛ አካል ይህን ይመስላል ተብሎ በሰው አንደበት ሊነገር አይቻልም ይላል - መጽሐፈ ምስጢር ዘአዶናይ ራፋኤል ::

በሱራፌልና በኪሩቤል እጅ የተሠሩ

ይቀጥላል !

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Tue May 19, 2009 11:12 pm    Post subject: Reply with quote

በኪሩቤልና በሱራፌል እጅ የተሠሩ (9600 ከክ //በፊት )

.. በራፋኤል ፈቃድ : በኪሩቤልና በሱራፌል እጅ የተሠሩ የፒራሚድ ከተሞች ደግሞ : ከዞብል ራማ በሐር : በአሰብ አፋር : እስከ ጅቡቲ ድረስ የሚገኙ ሲሆኑ : ቁጥራቸውም ሦስት ናቸው :: እነዚህ ፒራሚዶች ቅጥልጥል የሌለባቸው : ሥራቸው አንድ ወጥ የሆነ ዕብነ በረድ የሚመስል ሲሆን : በጣም ሰፋፊ ናቸው :: ቀለማቸው የወይን ጠጅ : ውኃ ሰማያዊ : ጥቁር ሲሆኑ L ኪሩቤልና ሱራፌል የሚታዘዙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነገደ መላእክት : በገዛ ኃይላቸው እንዳይቃጠሉ : የመሬት ስበት የሚያገኙባቸው ከተሞች ናቸው :: ... መላእክት ለዘላለእም መኖር እንዲችሉ ስበት ያስፈልጋቸዋል : ማለትም : ቅዱሳን የሆኑ መላእክት ወደተቀደሰ ሰው እና ሥፍራ በከፍተኛ ፍጥነት ወርደው : በዚህ ዓለም የሚገኙ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን : እንዲሁም ክፋትና ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች በመጎብኘት ከፍተኛ የሆነ የድጋፍ ኃይል ያገኛሉ :: ለቦታውም ለሰዉም የበለጠ ቅድስናን ይሰጡታል ::

በአንጻሩ ደግሞ : ርኩሳን የሆኑ መናፍስትና ኃይላትም ወደዚህ ዓለም ወርደው : የረከሰ ሥፍራና የረከሱ ሰዎችን በመገናኘት ኃይላቸውን ያድሳሉ :: የረከሱ ሰዎችና የረከሰ ሥፍራ ማለትም : ያለማቅዋረጥ አመጽና ግድያን የሚፈጽሙ : በውሸት ሰውን የሚያጣሉና የሚያጋድሉ ሲሆኑ : የረከሰ ሥፍራ ሃያ አራት ሰአት ሙሉ ጭፈራና ዝሙት የሚፈጸምበት ዝሙት ወይም ዳንስ ቤት ነው :: ርኩሳን መናፍስቱም : ከበፊቱ የበለጠ ርክስናን ለሥፍራውና ለሰዎቹ ይሰጧቸዋል ይላል መጽሐፈ ምሥጢር ::

በሣጥናኤል እጅ የተሠሩ

መጣሁ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
yodit

ኮትኳች

Joined: 25 Oct 2003
Posts: 301

PostPosted: Wed May 20, 2009 7:09 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዋርካ ብርሀን
ኮንጆ እንደው ከራርሜ ብቅ ሰል ያንቺን ስም ካየሁ ጠቅ አድርጌ እገባለሁ ቅቅቅቅ አንቺ ስው ያማትገቢበት የለ ደሞ ዛሬ ሰለ መናፍስት ስም ዝርዝር ተያይዛችሁታል አንቺ ልጅ እውቀት በዛብሽ ቅቅቅ በይ በርቺ ቅቅቅቅ
መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዮፍታሄ

ኮትኳች

Joined: 17 Jul 2007
Posts: 112

PostPosted: Wed May 20, 2009 11:08 pm    Post subject: Reply with quote

ብርኃናዊት እንደጻፈ(ች)ው:

ከዚያ አንጻር : ዴቪድ አይክም ሆነ ክሬዶ ሙትዋ : እንዲሁም ሌሎች መንፈሳዊውን ዓለም ለማየት የሚሞክሩ ሰዎች የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ በመከታተል : የግል አስተያየታቸውን ከላዩ ላይ 'እፍፍ ... እፍፍ !' ብዬ አራግፌ : ፋክቱን ብቻ ለማየት እሞክራለሁ :: እንዲያ ሳደርግ ብዙ ጊዜ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር የሚጋጭ ነገር አላይበትም :: (እንዳልኩህ የግል አስተያየታቸውንና their way of connecting the dots .. አልቀበልም :: ግን ዶቶቹን ብቻ እንዲያሳዩኝ እጠቀምባቸዋለሁ :: )

ልክ ነሽ : አስተያየታቸውን በዚህ መልኩ ካየንው በርከት ያሉ እውነተኛ ነገሮች ሳይጠቁሙን አልቀሩም ::
ነገር ግን እያንዳንዷ የነዚህ መሰል ሰዎች አስተያየት በጠቅላላ ዕውቀት በቅድሚያ መፈተሽ የሚገባው ይመስለኛል ::

መቼም ይገርመኛል የነዚህ ፒራሞዶች ነገር : ለምን እስከዛሬ በሚስጥር እንደተያዘ ዕንቆቅልሽ ቢሆንብኝም (ምናልባት ለሁሉም ነገር ግዜና ሰዓት አለው በሚለው ብሂል ይሆን ?) ተስፋዬ በሕይወት እያለን ሃገራችን ሰላምና መልካም መንፈስ ወርዶ : እንዚህን ዕጹብ ድንቅ የሆኑ የጥንተ ዓለም ሥራዎችን ከተሰወሩበት ቆፍረንም ይሁን ፈልገን መርምረን ለእይታና ለዓለም ሕዝብ መማርያ መተዛዘቢያ የምናቀርብበት ዘመን ነው የናፈቀኝ !

አባ ተስፋ :-

  'መላዕክት ለዘላለም ለመኖር እንዲችሉ ስበት ያስፈልጋቸዋል '

  ብለዋል :: ይህች አባባል ትኩረቴን ስባዋለች !
  ለምን ብትይ ?

  በፊዚክስ አገላለጽ : ስበት .........

  Gravity:
  1) The natural force of attraction exerted by a celestial body, such as Earth, upon objects at or near its surface, tending to draw them toward the center of the body.
  2) The natural force of attraction between any two massive bodies, which is directly proportional to the product of their masses and inversely proportional to the square of the distance between them.
  3) Gravity is a force of attraction that exists between any two masses any two bodies, any two particles.

  የሚል ትርጉም ነው የምናገኘው :: በዚህ መሠረት ......

  If we have two massive objects A and B,

  if m= mass, f= force of gravitation and g=universal gravitational coefficient.

  m(A) x m(B) = m(AB)g
  the higher the mass of the objects, the higher their gravitational pool towards each other, since their relationship directly proportional.

  However, their relationship based on distance is inversely proportional.

  Here, we will have, if r= being square of the distance between the masses

  (A)r x (B)r = AB/r^2

  If we combine the two eqautions 1&2 we will have,

  f= gm(A)m(B)/r^2

  Modern scientists think gravity is made up of particles called gravitons which travel at the speed of light. However, most physcists if they were to be honest, will admit that they do not know what gravity "is" in any fundamental way - only know how it behaves.

በዚህ ባለን [ዘመናዊ ዕውቀት ]: "መላዕክቶች ለዘላለም መኖር እንዲችሉ ስብት ያስፈልጋቸዋል " የሚለውን የአባ ተስፋን አስተያየት ብንመለከተው ምን እንረዳለን ?

በኔ አስተያየት : ስበት : ምንም እንኳን "ምንነቱን " በቅጡ ባናውቅም : በዓይን ባናየውም መኖሩን በተጨባጭ ማወቅ የምንችለው ክስተት ስለሆነ : መላዕክት ምንም መንፈሳዊያን (እንደ የጥንት ኢትዮጵያዊያን አረዳድ : ከእሳትና ከንፋስ የተፈጠሩ ) ፍጥረጣት ቢሆኑም ኃይልን ለመቀበል /ለህያወታቸው : ስበት : እንደሚያስፈልጋቸው ነው ::

ይህንን "በኢትዮጵያውኛ " ብንመለከተው :-

ቅዱስን መላዕክት : የቅዱሳን መካናትና የቅዱሳን ሰዎች "ስበት " ይሻሉ :: በአንጻሩም : ክፉ መናፍስት የረከሱ ቦታዎችና የክፉ ሰዎች : ስበት : ያስፈልጋቸውል ማለት ነው ......at least......ወደዚህ ዓለማችን በሚመጡበት ጊዜ ::

ይሄ ለኔ ምን ያመለክተኛል መሰለሽ : ብዙ ጊዜ በሃገራችን : ሰዎች ቤተክርስቲያን ; ደብር በዚህ ቦታ ወይ እግሌ ቅዱስ ያረፈበት ቦታ : ቤቴን እንድትሰራ ተብዬ በህልምም ሆነ በራዕይ ታዝዣልሁ ብለው ቤተክርስትያን ቤተመቅድስ የሚተክሉት : በትክክል : እንዚህ ቅዱሳን አካላት : መልካሙን ስብት : ፍለጋ : የቦታው ወይም የጉባኤው ቅድስና : ኃይልም እንዲሆናቸው ስለሚሹ መሆኑ አይመስልሽም ?

ስለዚህ : ሁለት : የስብት ባህሪዎች የምናገኝ መሰለኝ : መልካሙን የሚያበርታታ የሚያጎለብት : ስብትና : ክፉውንም እንዲሁ ኃይል የሚሰጥ ስበት ነው ::
አሁን የራሳችንን "ኢትዮጵያዊ " አመክሮ ብንጠቀም :-

In the intrinsic property of gravitation, there has to be included a positive and a negative gravitational force; just as we have positive and negative integers. ምናልባት ....matter/anti-matter....እንደሚባለው ....gravity/anti-gravity.......ያሉ የሚኖሩ ክስተታት ይሆኑ ይሆናል ::

እነዚህ መላዕክታት ጥንተ ዓለም ሰሩዋቸው የተባሉት ፒራሚዶችም ማንልባት ይህንን የሚፈልጉትን ......................gravitational force........channel.........የሚደርጉባቸው ......geometrical structures......ይሆኑ ይሆን ? ምናልባትስ የፒራሚዶች የሦስት ማዕዘናዊ ሹል ቅርጽና ግዙፍነቱ ለዚሁ አኗኗቸው እንዲረዳ የተቀረጸ .......perfect design......ይሆንን ?

እንዳው ልፈላሰፍ ብዬ ያቀርብኩት አስታያየት መሆኑ ይታውቅልኝ Wink ሆኖም .......it makes you think, doesn't it?

ሰላም ሁኚ

ጽሑፍሽ ይቀጥል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘላለማዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Aug 2004
Posts: 680
Location: ethiopia

PostPosted: Thu May 21, 2009 12:12 am    Post subject: ብርኃናዊት ለቀቀች ! Reply with quote

ይቺናት ጨዋታ ! እንደ ብርኃናዊት መቼ ነው የለቀቀችው ? አሃ… ይቅርታ «ማርያምን ምልዓልተ ፍጡራን፤ በአምላክና በሰው መካከል ያለች» ያለች ጊዜ ጨርቋን አልጣለችን እንጂ መልቀቋን አስመስክራ ንሯል። እንዲህ ብሶባት ግን አልተከታተልኩም ነበር። አሁን ይሄ ምን ይባላል፦
ብርኃናዊት እንደጻፈ(ች)ው:
በኪሩቤልና በሱራፌል እጅ የተሠሩ የፒራሚድ ከተሞች ደግሞ : ከዞብል ራማ በሐር : በአሰብ አፋር : እስከ ጅቡቲ ድረስ የሚገኙ ሲሆኑ : ቁጥራቸውም ሦስት ናቸው

በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ይህ የተተረከው ? ኦሆሆ ! ኪሩቤልና ሱራፌል የተሰሩ ከተሞች ! ድንቅ አይደለምን ? ከአሰብ እስከ ጀምሮ እስከ ጁቡቲ ድረስ የሚዘልቀው የአፋር በረሃ እንደጋለ ብረት የሚፋጅ ምድር ነው። እንግዲህ እስከዛሬ ድረስ የማውቃቸው የአርኪዮሎጂና የጥንት ታሪክ ዘገባዎች አንድም ቦታ ላይ «የብርኃናዊትን፦ በኪሩቤልና ሱራፌል የተሰሩ ፒራሚዶች» የሚተርክ ነገር አላየሁም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነት ቅዠት እንደሌለው መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። ምናልባት አርኪዎሎጂውን የጥንተ -ታሪክ ምርምሮች በቅርቡ የገለጡት ምስጢር ካለ ብዬም የማውቃቸውን የሙያው ዌብሳይቶች ባበሳቅላቸው ምንም የለም።

ስለዚህ ነው ብርኃናዊት፦ ለቀቀች ያልኩት ! ጥሩ ቱሪናፋ ወጥቷት የለም እንደ ! አይ አለመታደል በክርስትና ስም የምትቀድደው ውሸት አነሳትና ደግሞ ወደ ከርሰ -ምድርና፣ የጥንተ -ታሪክ ምርምር ውስጥ ገብታ መዘባረቅ ጀመረች። «አሁን የባሏን መጽሐፍ አጠበች»፤ አበስኩ ገበርኩ እንዲች አይነቷን ወንፊት ያገባት ! ይወለዳትማ ይድራትና ይገላገላል - ያገባት ግን በምን ይገላገላታል !
_________________
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Fri May 22, 2009 4:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላምታ ዮፍታሔ :

ስበትን አስመልክቶ የተመለከትክበት መንገድ : ልክ እኔ እንደታሰበኝ ዓይነት ነው :: እግዚአብሔር በፍጡራኑ መሐል ህብረትና ፍቅርን ስለሚፈልግ አስተሳስሮ ፈጠረን :: ሌላው ቀርቶ - ከዝህች ከኃላፊዋ መሬት ተፈጥሮ ጋር እንኳ እንዴት አድርጎ እንድንጠቀምበትና እንድንንከባከበው አድርጎ እንደሰራን ሳስብ በጣም ይገርመኛል :: ተፈጥሮን ልንኖራት እንጂ ልንቆጣጠራትና አቢዩዝ ልናደርጋት አልፈጠረንም ::

መላእክት ደግሞ ይህን ያህል ጥልቅ ፍቅርና ትስስር ከሰው ልጅ ጋር እንዲኖራቸው መደረጉ የሚገርም ነው :: በርግጥም it makes sense. ያለማንም ረዳት ሁሉን ማድረግ የሚችለው ጌታ : መላእክትን የሥራው ማስፈጸሚያ መሳሪያ አድርጎ ከሰው ጋር ማገናኘቱ ይህን ያስገነዝበናል :: ድንግል ማርያምን እናቱ እንድትሆን ብሥራት ሲያበስራት : እግዚአብሔር ራሱ በራዕይ ለነብያት እንደተገለጠው አድርጎ ሊያበሥራት ይችል ነበር - ያውም የገዛ እናቱን :: ግን መልአክ ላከ :: መልአኩ ከርሷ ቅድስናን ተጋርቶ : እርሷን ደስ አሰኝቶ : ሁለቱም ልዩ መንፈሳዊ ኃይል ተለዋውጠውና በፍቅር ተነጋግረው ነው የተለያዩት :: ይህ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው :: ይህ ነው እግዚአብሔርን ፍቅር የሚያስብለው አንዱ ዋና ገጽታ ::

ልቀጥል !

_______________________________

በሣጥናኤል እጅ የተሠሩ (8300 ከክ //በፊት

ከምሌ ዱፍቲ አንስቶ : የአዋሽ ወንዝ መጨረሻ : ከፑንቲ በርበራ እስከ ሕንድ ባሕር ድረስ የሚገኙ 3 የፒራሚድ ከተሞች የተሠሩት : በራፋኤል ትእዛዝ በሣጥናኤል እጅ ሲሆን : 3ሺህ ሜትር ርቀት የሚገኙ ናቸው :: ሥራቸውም እንደሌሎቹ ፒራሚዶች እኩል የሆነ ባለ 3 መአዘን ወይም ትራያንግል ሆኖ : በጣም ሰፋፊ ሆነው : ጥቁር ድንጋይ በሚመስል ቅጥልጥል በሌለበት ሥራ የታነጹ ናቸው :: በወንዝ የጠጠር ድንጋይ ፈርጥ ወይም ሞዛይክ የተለበጡ ናቸው ::

ይኸውም ከቁንድዶ ተራራ ሆኖ ፊትን ወደ ምሥራቅ አዙሮ ሲመለከቱ (የሁሉም ዓይን ሳይሆን : የተለየ ዓይን ማለቴ ነው ) በቀኝ ያለው ፒራሚድ ከተማ : ቀለሙ እንደበረዶ ነጭ ነው :: በመሐል ያለው ደግሞ በጣም ጥቁር ሲሆን : በግራ ያለው ግን ቡናማ ነው :: ቢሆንም እነዚህ የፒራሚድ ከተሞች የጥበብ ከተሞች ሲሆኑ : ለሰው ልጆችና ለሌላው ፍጥረት ሁሉ ልዩ ልዩ የሆነ ጥበብን የሚያስተምሩና የሚሰጡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቅዱሳን የሆኑ መላእክትና እንዲሁ ሥጋ የለበሱ ርኩሳን የሆኑ መናፍስት የሚኖሩባቸው ከተሞች ናቸው ::

... መላእክት 35 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆናቸውን ሰዎች እየመረጡ ወደከተማቸው በመውሰድ : ለሰው ልጆችና ለፍጥረቱ ሁሉ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ልዩ ልዩ የሥነ -ጥበብ ሥራዎችን መሥራት እንዲችሉ አዕምሯቸው ውስጥ የሚስሉና በቀዶ ጥገና የሚያስተካክሉ የጥበብ ኃይሎች ሲሆኑ : የሚያስገርመው ግን ለዚሁ ፈጠራ የሚመርጧቸው ሰዎች ከማንኛውም እምነት የማይወግኑትን ሰዎች ብቻ መሆኑ ነው :: ይህም የሚሆነው : በጥቁር የፒራሚድ ከተማ ሲሆን : በነጩ የፒራሚድ ከተማ ተወስደው አመጽና ግፍን : ማንኛውንም የርኩሰትን ሥራ ሁሉ እንዲፈጽሙ በቀዶ ጥገና አእምሯቸው ውስጥ የሚቀረጽላቸው ሰዎች ደግሞ : ከአይሁድና ከክርስትና እምነት ጀምሮ : የማንኛውም ሃይማኦት እምነት ተከታዮች ብቻ ናቸው ::

Credo Mutwa በኢንተርቪዉ ላይ ያነሳው exactly ይህን ነገር ነው :: እኔ በበኩሌ : ከአንድ የኢትዮጵያ ገዳም የተገኘ የጥንት ጽሑፍ እና : የአንድ ደቡብ አፍሪካዊ ሽማግሌ ገጠመኝ መገጣጠሙ ገርሞኛል ::

ስለ መንፈሳውያን የጥበብ መማርያ የፒራሚድ ከተሞች ደግሞ ይቀጥላል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርኃናዊት

አለቃ

Joined: 27 Oct 2007
Posts: 2182

PostPosted: Fri May 22, 2009 5:06 pm    Post subject: Reply with quote

አባ ተስፋ : ከላይ ለጭካኔ ሥራ ክርስቲያኖችን ርኩሳን መናፍት እየወሰዱ የሚያስተምሩበት መሆኑን ሲናገሩ : በምሳሌነት : በኢትዮጵያ ሳይቀር : አውሮፓና አሜሪካ : በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተነሱ ዲክታተሮችን ጭካኔ እንደምሳሌነት ይዘረዝራሉ ::

በመቀጠል :-

ቀለሙ ቡናማ የሆነው የፒራሚድ ከተማ ሥራው እንደሌሎቹ የፒራሚድ ከተሞች ባለ ሦስት ማዕዘን ወይም ትራያንግል ሲሆን : ወደዚህ የጥበብ ከተማ ተወስደው እንዲሰለጥኑ የሚደረጉት ደግሞ ከክርስቲያኖች ጀምሮ ማንኛውም ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑትን ሲሆን : ሰልጥነው ሲወጡ : ፍጹም መንፈሳውያን ሆነው ልዩ ልዩ የሃይማኖት መጻሕፍትን የሚጽፉና ልዩ ልዩ የሆኑ የሃይማኖት ተቋሞችን የሚሠሩና የሚመሠርቱ እንዲሁም በየቋንቋቸው ልዩ ልዩ በጣም የሚያስደስቱ መንፈሳዉና ሥጋዊ የሆኑ መዝሙሮችንና ጨዋታዎችን የሚደርሱና የሚያዘጋጁ የጥበብ ኃይሎች ይሆናሉ ::..... ይላል መጽሐፈ ምስጢር ::

በዓይን ሲታዩ በሚያስደንቁ ኃይሎች እጅ የተሠሩ 4300: 3112: 2780: 2100: እና 1510 ክክ // የተሠሩ

የምሥር ዓይነት የፒራሚድ ከተሞች ደግሞ የሚገኙት በላዕላይ ግብጽ በኑብያ : ናፓታ : መርዌ : እንዲሁም በታሕታይ ግብጽ በስፊኒክስ ሲሆኑ : ሥራቸውም ባለሦስት ማዕዘን ወይም ትራያንግል ሆኖ : ያለሲሚንቶ ጭቃ ሰው ሊሸከመው በማይችል ትላልቅ ደንጊያ ተቀጣጥሎና ተነባብሮ በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሠራ ነው :: ነገር ግን .... ተመራማሪዎች ... በሰው ኃይል ተሠራ ብለው እንደሚያነበንቡት አይደለም :: 5 ኃይሎች ተሠሩ እንጂ ::

... ይሁን እንጂ ፒራሚዶቹ እንዴት እንደተሠሩና ማን እንደአነጻቸው የሚገልጸው ማስረጃ በያንዳንዱ ፒራሚድ ውስጥና በሐውልቶቹ ላይ በጥንት ኢትዮጵያ የምሥር ጽሑፍ ወይም ሂሮግሊፊክስ ተቀርጾ ይገኛል :: ቢሆንም በምሥር የነበሩ አብዛኞቹ ሐውልቶች ወደ ባዕድ ሀገር የተወሰዱ ሲሆን : 27 በሮም ይገኛሉ :: .....እንዲሁም ሌሎች በፈረንሳይ : በጀርመን : በአሜሪካ : ... መኖራቸው ባይካድም : የሚያስደንቁት 5 ኃይሎች በሰው የሬሳ ሽታ ስለሚታደሱና ከወርቅ ከዕንቁ ከአልማዝ የተሠራ ልዩ ልዩ የሆነ ቅርጻ ቅርጽንና በሐውልቶች የተቀረጸ ልዩ ልዩ ሥዕልን ማየት ስለሚወድዱ : የኃይላቸው ማረፊያ እንዲሆናቸው ነው ያሰሯቸው እንጂ በሰው ኃይል የተሰሩ አይደሉም ::5 ሊቃነ መላዕክት በአራቱ መአዘነ አለም ሹሞች የተሰሩ 3000: 2000 1000 ከክ //

...የአክሱም አይነት የሕንጻ ሥራ ትናንሹን ለይቼ ትላልቁን ብቻ እጠቅሳለሁ :- ይኸውም በሽሬ : በዋልድባ : በጎንደር : በጣና : በጎዛም : በወለጋ : በመቀደሻ (መቃድሾ ) ድረስ ያሉ 7 ሲሆንኑ : የሠሩትም የኃልያቸው ማረፊያ እንዲሆናቸው : በሱርያል : በሰዳካኤል : በሰላታኤል : እና በአናንያኤል ነው ::

የሥራቸውም ዓይነቱ ከአንድ ደንጊያ ወጥ ሆኖ : በአስደናቂ ሁኔታ የጻነጸ ሲሆን : ባለ 8 ማዕዘን ባለ 6 ማዕዘንና ባለ 4 ማዕዘን ነው :: ጣራቸውና ግድግዳቸውም ሕብሩ የማይታወቅ ሐረግና ልዩ ልዩ ሥዕል ያሸበረቀና ያጌጠ ነው ::

በታማኝነት በቆሙ አለቆች እጅ የተሠሩ 2900: 1800: 1400: 900 600 እና 300 ከክ //

ይቀጥላል !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 4 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia