WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
%@#$?&
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 47, 48, 49  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Sun Feb 01, 2009 11:47 am    Post subject: Reply with quote

~~~~~~~~~~~~~~~~ሞት አዲሱ ~~~~~~~~~~~~~

ረጅም ጊዜ ሆኖታል :: አገሩን አላስታውስም :: የአንድ አገር ጎሳ ተወላጆች አዲስ ልጅ ሲወለድ እሪ ብለው እያለቀሱ ሲሆን የሚቀበሉት : ሰው ሲሞት ግን በእልልታና በጭፈራ እንደሚሸኙት ሰምቻለሁ ወይም አንብቤያለሁ :: ዛሬ ቀናሁባቸው ::

ባለፈው ሰሞን ወንድማችን ኩዛ በኢትዮጵያ ስለሚደርሱት አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች የለጠፈውን አሳዛኝ ትእይንት ማየት ፈርቼ ኮምፒውተሬን አጥፍቼ ተነሳሁ ...የራሴውን ጉድ ሳላውቅ :: ድሮ ድሮ ከስሬ ሽጉጥ የሚለውን : ሳጠና እንኩዋን ወይ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ወይ እግሬን ተደግፎ የሚተኛውን ትንሹን ወንድሜን በዚሁ አደጋ ማጣቴን መቼ ሰማሁና ::

መርዶው ሲመጣልኝ ከአምላክ ጋር ሙግት ገጠምኩ :: ከስንት መንከራተት በሁዋላ ኑሮው ሲሳካለት ለምን ወንድሜን ወሰድከው ብዬ ...አባቴም ደግ ሰው ነውና ይህ አይገባውም ብዬ ...እንደው ቆሽቴ አርሮ ነው እንጂ ልጅ የሚሞትበት ሰው ሁሉ ክፉ ነው ያለው ማነው ? ከዛ ደግሞ ራሴን በፀፀት ልጠቀጥቅ ሞከርኩ ... እንዲህ ባደረኩለት ኖሮ : ይህን ደግሞ ባላደረኩለት ኖሮ ...ከሞት አድነው ይመስል :: የወንድሜን ድምጽ መጨረሻ የሰማሁት ያሰበው ተሳክቶለት ተደስቶ ሳለ ነበር ...ይዞት ሊጉዋዘው ::

"ለካስ ሞት እንዲህ ነው ?" አባቴ ሲለኝ አጠገቤ የሚሩዋሩዋጡትን ልጆቼን እያየሁ አንጀቴ ተላወሰ :: ሞት ለሱ አዲስ አይደለም ...እንደው የልጅ ሞት ሆኖበት ነው እንጂ :: "አይዞህ አባዬ " ከማለት ሌላ ምን ልለው እችላለሁ ? ስልኩን ዘግቼ ህይወትን ያዝኩዋት ሲል ለተቀጠፈው ወንድሜ አለቀስኩ : ልጁን ከስሩ ለተነጠቀው ምስኪን አባቴ አለቀስኩ : እዚህ ለብቻዬ አንጀቴ ለተከነው ለራሴይቱ አለቀስኩ : "ልጆቼን ባጣ ምን ይውጠኛል " ብዬ አጠገቤ ላሉትም ህጻናት በስጋት አለቀስኩ : "አስቀድመህ እኔን አስሬ ግደለኝ " ብዬም አምላኬን ለመንኩት ...አንዴ እንኩዋን ሞቶ መነሳት ያለ ይመስል :: ሲነጋ ልጆቼን ወደ ትምህርት ቤት ሸኝቼ እኔም ወደእለቱ ጉዳዬ ነጎድኩ ...የፈረንጅ አገር ለቅሶ ! ምድርም ተሽከረከረች : ጨረቃዋም ደበዘዘች : ፀሀይዋም ወጣች : ህይወትም ቀጠለች ...ይብላኝ እንጂ ለሞተው :: ወይስ የሞት አለም በጣም የተሻለ ሆኖ እሱ "ይብላኝ ለምትኖሪው " እያለኝ ይሆን ? ማን ያውቃል Idea

ሞት በረከሰበት ዘመን ታዲያ ምን አዲስ ነገር ሆኖ ነው ትሉኝ ይሆን ? አዎን ልክ ናችሁ :: እንደው ሞት አዲሱ አናውዞኝ ነው እንጂ ...ጽፌው ቢወጣልኝ : ተንፍሼው ቢቀለኝ :: እንግዲህ ከአገር ማዶ ሆነን ለምናነባው መጽጽናናትን ይላክልን : የተለዩንንም እናቶች : አባቶች : እህቶች : ወንድሞች : ዘመዶችና ጉዋደኞችም ቸሩ አምላካችን ነፍሳቸውን ይማርልን ...እኛም ኮንትራታችን ተሙዋጦ እስክንቀላቀላቸው ድረስ :: እስቲ የነገ ሰው ብሎን በቸር ያገናኘን ::

መልክሻና Tጂዬ መልእክታችሁ ደርሶኛል ...እግዜር ያክብርልኝ :: ሳይታማ ...ለጥቆማው አመሰግናለሁ :: ቢልሻ ጣዝማዬና ባሻ እጅ ነስቻለሁ :: ሙዝነቴ አቶ ተንኮሉ Laughing ከረጅም ጊዜ በሁዋላ እንዴት አሳከኝ ...የውሀ እናቱ በጣም ሰርቶዋል Wink : የሻማው ግን እንዳልከው አንድ ሳይሆን ሁለት ፋብሪካ ከሌለህ በቀር ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ሀይት 2000

አዲስ

Joined: 09 Apr 2008
Posts: 26
Location: UAS

PostPosted: Sun Feb 01, 2009 7:55 pm    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ ቁስልሽ ተስማኝ አመመኝ በእኔ የደረስ ደረስብሽ እግዝያቤህር ጽናቱን ይስጥሽ ምን ይባላል ሌላ ለቤተስብሽ መጽናናት ይስጥኣችው የእኔ እመቤት
_________________
START
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
password

ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2008
Posts: 197
Location: Scandic

PostPosted: Mon Feb 02, 2009 12:51 am    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ፣ ስለተነጠቅሽው ውድ ወንድምሽ የጻፍሽውን አንብቤ የተሰማኝን ሀዘን እንዴት እንደምገልጽ አላውቅም። የሞትን ምትና ህመሙን ብዙዎቻችን እናውቀዋለን ብዬ አምናለው። ድንገተኛው ሲሆን ግን ከበድ ይላል። እግዚአብሄር መፅናናትን ሰለሚሰጥሽ እንደምትወጭው አልጠራጠርም።

በአገራችን ያለው የመኪና አደጋ ችግር ብዙ መንስኤዎች ይኖሩታል። ጭቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

መኪና የማሽከርከር ችሎታ ሳይኖር መንዳት
ተክኒካዊ ብልሽት ያለው መኪና መንዳት
ጠጥቶ መንዳት
ከባድ መድሀኒት ወስዶ መንዳት
የመንገዱ ስፋት ከሚፈቅደው ፍጥነት በላይ መንዳት
የእግረኛውና የኣካባቢው ሁኔታ ከሚፈቅደው ፍጥነት በላይ መንዳት
እይታ የሚከልል ነገር ባለበት ሁኔታ በፍጥነት መንዳት

የመንገድ መጥበብ
የአደጋ ማስጠንቃቂያ ምልክቶች በሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች አለመኖር
ፍጥነት የሚያስቀንሱ ጉብታዎች በሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች አለመኖር
የትራፊክ መብራቶች በሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች አለመኖር
የትራፊክ ፖሊሶች በሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች አለመኖር
የትራፊክ ፖሊሶች ጥብቅ አለመሆን
የትራፊክ ህግ ጥብቅ አለመሆን
የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ጥብቅ አለመሆን
ህብረተሰቡ ስለታራፊክ ህግና ደንብ ያለው ግንዛቤ ማነስ ወዘተ።

ዝርዝሩ ቀጣይ ነው።

ትርንጎ፣ ካንቺ አውቄ ሳይሆን ... በውጩ አለም ውዶቻቸውን በተመሳሰይ አደጋ ያጡ ሰዎች ሲያደርጉ ያየሁትን፣ (አንቺም ሳታዪ አትቀሪም፣ ) ነው ማንሳት የፈለግሁት። እንዲህ አይነት ከፉ አጋጣሚ የደረሰባቸው ሰዎች ወይም ቤቴሰቦች፣ አደጋ ያስከተለውን ችግር በሚቻላቸው በመቅረፍ ለሌላ ህይወት መትረፍ ምክንያት ከመሆናቸው ባሻገር ... በመካያው ለራሳቸውም መጽናናትን ያገኙበታል። የወንድምሽ ሞት ለሌላ ሰው ህይወት መትረፍ ምክንያት ይሆን ዘንድ አቅምሽ፣ ጊዜሽና ችሎታሽ በፈቀደው መጠን ከላይ ከተዘረዘሩትን ችግሮች ጥቂቱን ለመቅረፍ የበኩልሽን አስተዋጽኦ ብታደርጊ ለማለት ነው ያሰብኩት ግን አባባሉን የቻልኩበት፣ የሚባልበትንም ጊዜ የጠበቅሁ አልመሰለኝም። የስነ ጽሁፍ ችሎታሽን በማስታወስ የመጣልኝ ሀሳብ ስለሆነ ነው የጫጫርኩት። እና በጋዜጣና በመጽሄቶች ችግሮቹን የሚጠቅሱና መፍትሄ የሚጠቁሙ መጣጥፎች አልፎ እልፎ ብታበረከቺ የመንግስት አካላትና ህብረተሰቡ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማደረግ ይቻል ይሆናል ... ብሎም በዚህ ክፉ አጣፈንታ የምትቀጭን ሌላ ነፍስ መታደግ ..... እስኪ ወደፊት ብዙ ዋርካዊያን ባሳተፈ መልኩ እንዳስሰዋለን .

ብርታትና መጽናናትን እየተመኘሁልሽ

ፓስ
_________________
http://babile.webs.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Report post
ifa

ኮትኳች

Joined: 09 Jul 2007
Posts: 115

PostPosted: Mon Feb 02, 2009 7:26 am    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ እኔ ስውር አድናቂሽ ነበርኩ ...ሁሌም ጽሁፍሽን እያነበብኩ እድሜ ይጨምርልች ብየ ነበር ቤትሽን የምለቀው ዛሬ ግን ስለወንድምሽ ያልሽው አንጀቴን አላውሶ አይኔን እንባ አስቀርሮ ከባህር ማዶ ስላሉ ወገኖቼ በፍርሀት እንዳስብ አደረገን ...አይዞሽ እህቴ ብርታቱን / ይስጥሽ ...የተሰማሽን ሁሉ መጥተሽ ጫር ጫር አድርጊ ቀለል እንዲልሽ .....
ዩር ሲክሬት አድማየረር አይፋ
_________________
Ethiopians are: " THE BLAMELESS RACE "

Homer (Greek poet of the 8th century B.C.)
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Mon Feb 02, 2009 8:48 am    Post subject: Reply with quote

ሀይቴ የኔ እመቤት አይዞን ነው እንግዲህ :: ፓስሻ ጥቆማህን ወድጄዋለሁ ...ግን ለእኛ አገር እንዴት የሚሰራ ይመስልሀል ? ማለቴ ሰሚ አለ ወይ ? ifa እጅ ነስቻለሁ :: ሁላችሁንም እግዜር ያክብርልኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2669

PostPosted: Mon Feb 02, 2009 1:59 pm    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ * እንደጻፈ(ች)ው:
~~~~~~~~~~~~~~~~ሞት አዲሱ ~~~~~~~~~~~~~

ነባሩና ሁሌም ነዋሪዉ ሞት !!!
Quote:

ረጅም ጊዜ ሆኖታል :: አገሩን አላስታውስም :: የአንድ አገር ጎሳ ተወላጆች አዲስ ልጅ ሲወለድ እሪ ብለው እያለቀሱ ሲሆን የሚቀበሉት : ሰው ሲሞት ግን በእልልታና በጭፈራ እንደሚሸኙት ሰምቻለሁ ወይም አንብቤያለሁ :: ዛሬ ቀናሁባቸው :: .

ሀዘንም ደስታም ስሜት የሚሰጡን ማህበረሰባችን ባወረሰን የአኗኗር ኢትባህልና እሴት ነዉ :: የሞትን አስደሳችነት በሚሰብክ ማህበረሰብና ሞትን እንደ ቅጣት በሚያይ ማህበረሰብ መካከል ያደገ ሰዉ ነገርዬ የተፈጥሮ ክስተት መሆኑን ሁሉም ቢረዱትም አቀባበሉ ላይ ግን ይለያያል ::

ምንም ይሁን ምን ... በአበሻ ማህበረሰብ ለተወለደችዉ ትርንጎ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አብዛኞቻችን ስሜትሽ ይጋባብናል :: በተለይም ..እንደ ባህላችን በሟቹ የቀብር ስነስርዐት ላይ ተገኝተሽ አፈር በትነሽ አለመሰናበትሽ ጸጸቱን ከፍ ያደርገዋል ::

ለመጎረር ወይንም ለመፈላሰፍ መሞከሬ አይደለም .... ሞት ይዞት ወደማናዉቀዉ አለም በሚሄደዉ ሰዉ አልከፋም .... ለምን እንዲህ ደረሰበትም ብዬ አላዝንም ... ......... አላዝንም ስል ለወሬ ያክል አለማዛን አይደለም ... ከልቤ አላዝንም :: በህይወቴ በሚያጋጥሙኝ ማንኛዉንም አይነት ክስተቶች ልቀለብሳቸዉ የምችላቸዉ ነገሮች አሉ :: በጭራሽ ለመቀልበስ የማልሞክራቸዉ ነገሮች አሉ ::የማልሞክራቸዉን ነገሮች ደግሞ አምኜ በጸጋ መቀበል የግድ ነዉ :: ይህንን ስል ሀይማኖታዊ በመሆን የሰዉ ልጅ መሞት የሽግግር ወቅት ነዉ .... ሽግግሩም ከስጋዊ ህይወት ወደ ነፍሳዊ ዘላለማዊ ህይወት ... አልያም ከሰዋዊ ተፈጥሮ ወደሌላ ተፈጥሮ የለዉጥ ሂደት ነዉ የሚል ሜታፊዚካል እምነትም የለኝም :: ወደየትም እንሂድ ወደየት .... ከተወለድንበት ቀን ጀምሮ የምንጠብቀዉ የህይወት ክስተት ነዉ :: ወይንም የህይወቴ አንዱ አካል ነዉ :: አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ጉዞዬ ወደዚህ ወደማይቀረዉ ሞት ነዉ :: አበበም :: ከበደም :: አድሪያኖም :: ሙዜቪችም :: ..........

የመጀመሪያዉ መላ ምቴ ከላይ ያለዉ ሲሆን .... ዋናዉና ሞትን እንዳልፈራ የማያደርገኝ ነገር ደግሞ .... ..... ወደዚህ ምድር ከመምጣቴ በፊት ያለዉን ነገር ለማስታወስ እሞክራለሁ .... ምንም :: ምንም ::ምንም :: ስሞትም ወደየት እንደምሄድ አላዉቀዉም :: ምንም ::ምንም ::ምንም :: ሰላም :: ጸጥ ረጭ ያለ ሰላም :: በምንም በማንም የማይረበሽ ሰላም :: ታዲያ እንደ ሞት ምን ጣፋጭ ነገር አለ ? .... .... እንደቀለድ ጣል ያረግሻት ቁም ነገር አለች ? "እሱ ስለኔ ያዝን ይሆን ?" ብለሻል .... ..... እንደዛ ነዉ ሚሰማኝ :: ሰዉ ሁነሽ በመፈጠርሽ ለራስሽ የምትሰጭዉ የህይወት የቤት ስራ አለ :: መቸዉንም ተሰርቶ የማያልቅ የቤት ስራ ::ይህ የቤት ስራ አስቀያሚ የሚያደርገዉ አለማለቁ ብቻ አይደለም :: እንድትሰሪዉ የሌሎችንም ኢንፑት መፈለጉ ላይ ነዉ :: ማህበራዊ እንስሳ እስከሆንን ድረስ ስንኖር ከእምነታችን ባለፈ በሰዎች እምነት .... ማህበረሰቡ በማህበራዊ የኮንትራቱ ዉሉ የፈጠረብሽ መስተጋብር አለ :: አሰልች :: አስቀያሚ :: የነጻነት ጸር :: ኡፍፍፍፍ :: ታዲያ ከዚህ ሁሉ የአለም ኮተት ተለይቶ እፎይ ነጻነቴ !!! ማለት ያሳዝን ይሆን ?

ይህንንን ያክል ስቀባዥር ... ሱሳይድን አጥብቀዉ ከሚጠሉ .... ከሚኮንኑ ሰዎች አንዱ ነኝ ::ሽንፈትን ስለማልወድ ::
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዱዲ

ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2004
Posts: 291
Location: united states

PostPosted: Mon Feb 02, 2009 6:40 pm    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ !
አዝናለሁ እህትዬ ...የሚገርምና አሳዛኝ አጋጣሚ ነው :: እግዚአብሄር ያጥናሽ ..ወንድምን ማጣት ቀላል አይደለም ያውም ታናሽና ወጣት ወንድም ....እግዚብሄር ነፍሱን ከጻድቃኖች መሀል ያኑርልን ::
ሀዘንሽን ለዋርካ ታዳሚዎች ብታካፍይ ንጹሁና ሰው ወዳድ ልብሽን አሳየኝ :: ተባረኪ !
አምላክ በቸርነቱ አንቺንና ልጆችሽን ይጠብቅልን ::
የልጅሽ ታሪክ ድንቅ ነው :: ትርንጎዬ አንቺ በኛ ሀገር ባህል ባል ካገቡ በሁዋላ ትምህርት የለም ብለሽ አስበሽ ነው እስዋ ግን ባሉን ይዛ ዶክትሬቱንም አፈፍ ታረርጋለችና አታስቢ ..ቂቂቂቂቂቂ
የዘወትር አድናቂሽ ዱዲ ነኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲዱ

ዋና ኮትኳች

Joined: 13 Jul 2007
Posts: 593
Location: Here

PostPosted: Tue Feb 03, 2009 12:09 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ትርንጎ

የወንድም ማጣት ዜና -- በተለይም ደግሞ ወደታች አሽቆልቁለሽ እያየሽው ያሳደግሽው ............... በጣም ኃይለኛ በትር ነው :: ................. በተለይ እዚህ በስደት እየተኖረ እንዲህ አይነት ነገር መስማት ምን ያህል እንደሚከብድ ማናችንም እናውቀዋለን ::

ሆኖም ፈጣሪ ያመጣውን ነገር ኃዘኑን በልክ አድርጎ ታግሶ ኑሮን እንደገና መጀመር ነው ::

ከላይ ሙዝ ያለው ነገርም የሆነ እውነታ አለበትና ምናልባትም ቅፅበታዊ መርዶ ስንሰማ ብንደነግጥም በኔ አስተሳሰብ መታዘን ያለበት እዚህች የተግማማች አለም ውስጥ ለቀረነው ለኛ ነውና አንቺም አይዞሽ በርቺ ::

ነፍሱን ይማረው ::

ሀዲዱ
_________________
የሰቆቃውና የመከራው ማለቂያ ፤ ማብቂያ በእግዚአብሄርና በእኛ አንድነት ይሆናል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራያራዩማ

አዲስ

Joined: 18 Jul 2008
Posts: 16

PostPosted: Tue Feb 03, 2009 5:04 pm    Post subject: ራያራዩማ Reply with quote

ውድ ትርንጎ :

በጣም የሚያሳዝን አጋጣሚ ........ቸሩ እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጥሽ :: እግዚአብሄር ነፍሱን በመንግስቱ ያስባት :: መፈጠር ካለ .........ሞት መች ይቀራል ..... የእያንዳንዳችን በዚህ አለም ላይ መኖር ሌሎች ሰዎች (ቢያንስ ወላጆቻችን ወይም ልጆቻችን ) ስለሚፈልጉት ጭምር እንጂ :: ምክንያቱም : የነዚህ ህይወትም ምንልባት 'ኗሪው ' depend ሊሆን ስለሚችል ::

ራያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Truth...

ኮትኳች

Joined: 22 Dec 2008
Posts: 154

PostPosted: Tue Feb 03, 2009 6:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ትርንጎ

እንዴት የሚያሳዝን አጋጣሚ ነው የደረሰብሽ… በጣም ያሳዝናል። እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጥሽ ከማለት በቀር ምን ይባላል። …እንግዲህ ይሄ የህይወት አንዱ ገጽታ ነው። ምን ማድረግ ይቻላይ።

እኔም የፓስን ሃሳብ እጋራለሁ… እንዴት መተግበር እንዲቻል ግን ጥቂት ጊዜ ወስደሽ መላ ሊፈይዱ ከሚችሉ ዕውቀቱና አቅሙ ካላቸው መልካም ሰወች ጋር አብር መምከሩ በበለጠ ውጤታማ ያደርግሽል።

በቀረው ቸር ሰንብቺ

ትሩዝ
_________________
Yes
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Wed Feb 04, 2009 4:02 pm    Post subject: Reply with quote

ሙዝሻ ዱዲነት ሀዲዱዬ ራያዬና ትሩዝሻ እንዲሁም ከነሱ በላይ ለፃፋችሁና በጉዋሮ ብቅ ላላችሁት ሁሉ እግዜር ይስጥልኝ : ያክብርልኝ :: ይገርማል ...እዚህ የፃፍኩት እንደው ልተንፍሰው ብዬ ነበር :: ግን የናንተ አይዞሽ ማለትና የራሳችሁንም ታሪክ ማካፈል እንዴት ያጽናናል መሰላችሁ :: ውድድድድድ አደርጋችሁዋለሁ ::

ሁሌም አክባሪያችሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Fri Feb 06, 2009 12:19 am    Post subject: Reply with quote

እዝጋቤር ሐዘንሽን ያቅልለው :: በርታ : በርታ በይ : እህቴ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2669

PostPosted: Fri Feb 06, 2009 3:35 pm    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
እዝጋቤር ሐዘንሽን ያቅልለው :: በርታ : በርታ በይ : እህቴ ::

አንተን መስማትስ አይሰማህም .... እንዴዉ ለወጉ ያክል ምናለ በሙሉ ስሙ ብትጠራዉ ?

ትርንጎሻ ቀጣዩ ጽሁፍሽ ደግሞ ምን ይሆን ? Wink
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኤልሳ *

ኮትኳች

Joined: 27 Jul 2006
Posts: 191

PostPosted: Sat Feb 07, 2009 12:53 am    Post subject: Reply with quote

አይዞሽ እህቴ እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጥሽ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Sat Feb 07, 2009 3:34 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ትርንጎ : እንደምን አለሽ ? እግዚአብሄር ያጥናሽ !!! በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው ያጋጠመሽ .......በተለይ ደሞ ሳይታሰብ እንደዚህ በአደጋ ሲሆን የበለጠ ስሜት ይጎዳል :: ቢሆንም ሞት ለሁላችንም ነው እና ተጽናኝ :: እግዚአብሄር ላንች እና ለመላው ቤተሰብሽ ጽናትን ይስጣችሁ !!! የወንድምሽን ነፍስም በገነት ያኑራት !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 47, 48, 49  Next
Page 2 of 49

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia