WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
መድበለ እቴ ...
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Wed Apr 16, 2008 1:31 am    Post subject: መድበለ እቴ ... Reply with quote

የዛሬና የትናንት እሰጥ -አገባ

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ ......
አለም ቢታሰስ -ታሪክ ቢጠና
ሕዝብ ቢመዘን -ቢፈለግ ጀግና
የታሪክ ቀደምት -የሰው መገኛ
ከሁሉ የላቀ -ማን አለ እንደእኛ ?
እኮ ማን ?............እኮ በለኛ
ንገረኛ !!!

አየ ዘራፍ ...አየ ዘራፍ
አየ አካኪ ዘራፍ
አሁን የኛ ኩራት -የኛ ኩፈሳ
ታሪክ ስንዘክር -ወግ ስናወሳ
በትናንት ስኖር - ዛሬን ሳንሰራ
በባዶ ኩራት - ስንንጠራራ
የእጅ ግዞተኛ - በዕርጥባ ኗሪ
የጠኔ አብነት - በራብ ተጠሪ
በወሲብ ቅስፈት - አትራፊ ዝና
እንዲም አርጎ የለ - አንደኛ ጀግና
አይ ጀግና
አይ ጀግና ......

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ቤልጂግ ሳይኖረው -ባሩድ ሳይሰራ
መድፍ ሳይተኩስ -ሳያይ ጢያራ
ሰናድር ይዞ - ወጨፎ አንግቶ
ፈንጁን አክሽፎ -ጥይት መክቶ
ነጣ ባወጣን -በአያቴ ሥራ
አንዴት አልፎክር - አንዴት አልኮራ
እንዴት አልዘክር -ገድሉን አላውራ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ ..አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
የዛሬ ትውልድ -ሰቆቃ አፍጦ
በረሀብ ሰሎ -ውስጡ ተረግጦ
የአባቱ ገድል - የአያቱ ሥራ
ሲዘከር ቢኖር -ዓመት ቢወራ
ለተደቆሰው -ሰብዓዊነቱ
ጠኔ ላጣጋው -ለዛሬ አንጀቱ
ምኑ ላይ ይሆን -መፍትሄነቱ ?

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ጊዜ ተጣሞ -ቀን ተወላግዶ
ሥልጣኔያችን -ቁልቁል ተሰዶ
ዛሬን ብንደኸይ -ረሀብ ቢመጣ
ታሪካችንን -ኩራታችንን -እንዴት እንጣ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ -አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
ትናንት ከዛሬ -ካልተቆራኘ
ትውልድ ከትውልድ -ካልተገናኘ
የጊዜ ብልሀት -መሽቶ የመንጋቱ
ታሪክ በታሪክ -የመተካቱ
የቀናት መንጎድ - ትርጉሙ ጠፍቶ
ህዝብ ዛሬን ክዶ - ሰው ዛሬን ጠልቶ
ከትናንት ጓዳ -መሽጎ ገብቶ
እንዴት ይኖራል -አሁንን ጠልቶ ?

Last edited by እቴጌይት on Mon Apr 01, 2013 1:05 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Wed Apr 16, 2008 1:35 am    Post subject: Reply with quote

ማን ይሆን አሸናፊው ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብርቄነህ

ኮትኳች

Joined: 22 Jan 2009
Posts: 429

PostPosted: Wed Sep 23, 2009 7:09 pm    Post subject: Reply with quote

ይህን የመሰለ ቁምነገር አደባባይ ላይ ነው መዋል ያለበት ::

በእተጌይቱ :-
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ ......
አለም ቢታሰስ -ታሪክ ቢጠና
ሕዝብ ቢመዘን -ቢፈለግ ጀግና
የታሪክ ቀደምት -የሰው መገኛ
ከሁሉ የላቀ -ማን አለ እንደእኛ ?
እኮ ማን ?............እኮ በለኛ
ንገረኛ !!!

አየ ዘራፍ ...አየ ዘራፍ
አየ አካኪ ዘራፍ
አሁን የኛ ኩራት -የኛ ኩፈሳ
ታሪክ ስንዘክር -ወግ ስናወሳ
በትናንት ስኖር - ዛሬን ሳንሰራ
በባዶ ኩራት - ስንንጠራራ
የእጅ ግዞተኛ - በዕርጥባ ኗሪ
የጠኔ አብነት - በራብ ተጠሪ
በወሲብ ቅስፈት - አትራፊ ዝና
እንዲም አርጎ የለ - አንደኛ ጀግና
አይ ጀግና
አይ ጀግና ......

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ቤልጂግ ሳይኖረው -ባሩድ ሳይሰራ
መድፍ ሳይተኩስ -ሳያይ ጢያራ
ሰናድር ይዞ - ወጨፎ አንግቶ
ፈንጁን አክሽፎ -ጥይት መክቶ
ነጣ ባወጣን -በአያቴ ሥራ
አንዴት አልፎክር - አንዴት አልኮራ
እንዴት አልዘክር -ገድሉን አላውራ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ ..አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
የዛሬ ትውልድ -ሰቆቃ አፍጦ
በረሀብ ሰሎ -ውስጡ ተረግጦ
የአባቱ ገድል - የአያቱ ሥራ
ሲዘከር ቢኖር -ዓመት ቢወራ
ለተደቆሰው -ሰብዓዊነቱ
ጠኔ ላጣጋው -ለዛሬ አንጀቱ
ምኑ ላይ ይሆን -መፍትሄነቱ ?

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ጊዜ ተጣሞ -ቀን ተወላግዶ
ሥልጣኔያችን -ቁልቁል ተሰዶ
ዛሬን ብንደኸይ -ረሀብ ቢመጣ
ታሪካችንን -ኩራታችንን -እንዴት እንጣ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ -አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
ትናንት ከዛሬ -ካልተቆራኘ
ትውልድ ከትውልድ -ካልተገናኘ
የጊዜ ብልሀት -መሽቶ የመንጋቱ
ታሪክ በታሪክ -የመተካቱ
የቀናት መንጎድ - ትርጉሙ ጠፍቶ
ህዝብ ዛሬን ክዶ - ሰው ዛሬን ጠልቶ
ከትናንት ጓዳ -መሽጎ ገብቶ
እንዴት ይኖራል -አሁንን ጠልቶ ?

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Mon Apr 01, 2013 2:11 am    Post subject: Reply with quote

ምላስ

ኤሊ ጥንቸል ቀድሞ ካሰበው ደረሰ
ኤሊ ጥንቸል ቀድሞ - ካሰበወ ደረሰ
አንበሳ ሳር ሲግጥ - በበግ ተነከሰ
አህያ ተንጋሎ - ጅብ ጦሙን አደረ
ወፍ መሬት ስትሳብ - እባብ ላይ በረረ
በሬ ጥጃ ወልዶ - ባኮሌ ታለበ
እይጥ ተሞሽሮ - በድመት ታጀበ
ድንጋይ ቅመም ሆኖ - በጨው ተደቆሰ
ማኛው ነጭ ጤፉ - በወንፊት ታፈሰ .....
.......
ጮማው ተትረፍርፎ - ሳይጠፋ ከመንደር
ጎድንና ባቱ - ሳይታጣ ካገር
የዘመኑ ነገር - ጠፍቶት መላ ቅጡ
እኔን ግራ ገባኝ - ምላስ መመረጡ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Ahmed-1

ኮትኳች

Joined: 19 Mar 2007
Posts: 150

PostPosted: Mon Apr 01, 2013 8:39 am    Post subject: Re: መድበለ እቴ ... Reply with quote

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
የዛሬና የትናንት እሰጥ -አገባ

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ ......
አለም ቢታሰስ -ታሪክ ቢጠና
ሕዝብ ቢመዘን -ቢፈለግ ጀግና
የታሪክ ቀደምት -የሰው መገኛ
ከሁሉ የላቀ -ማን አለ እንደእኛ ?
እኮ ማን ?............እኮ በለኛ
ንገረኛ !!!

አየ ዘራፍ ...አየ ዘራፍ
አየ አካኪ ዘራፍ
አሁን የኛ ኩራት -የኛ ኩፈሳ
ታሪክ ስንዘክር -ወግ ስናወሳ
በትናንት ስኖር - ዛሬን ሳንሰራ
በባዶ ኩራት - ስንንጠራራ
የእጅ ግዞተኛ - በዕርጥባ ኗሪ
የጠኔ አብነት - በራብ ተጠሪ
በወሲብ ቅስፈት - አትራፊ ዝና
እንዲም አርጎ የለ - አንደኛ ጀግና
አይ ጀግና
አይ ጀግና ......

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ቤልጂግ ሳይኖረው -ባሩድ ሳይሰራ
መድፍ ሳይተኩስ -ሳያይ ጢያራ
ሰናድር ይዞ - ወጨፎ አንግቶ
ፈንጁን አክሽፎ -ጥይት መክቶ
ነጣ ባወጣን -በአያቴ ሥራ
አንዴት አልፎክር - አንዴት አልኮራ
እንዴት አልዘክር -ገድሉን አላውራ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ ..አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
የዛሬ ትውልድ -ሰቆቃ አፍጦ
በረሀብ ሰሎ -ውስጡ ተረግጦ
የአባቱ ገድል - የአያቱ ሥራ
ሲዘከር ቢኖር -ዓመት ቢወራ
ለተደቆሰው -ሰብዓዊነቱ
ጠኔ ላጣጋው -ለዛሬ አንጀቱ
ምኑ ላይ ይሆን -መፍትሄነቱ ?

ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ጊዜ ተጣሞ -ቀን ተወላግዶ
ሥልጣኔያችን -ቁልቁል ተሰዶ
ዛሬን ብንደኸይ -ረሀብ ቢመጣ
ታሪካችንን -ኩራታችንን -እንዴት እንጣ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ

አይ ዘራፍ -አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
ትናንት ከዛሬ -ካልተቆራኘ
ትውልድ ከትውልድ -ካልተገናኘ
የጊዜ ብልሀት -መሽቶ የመንጋቱ
ታሪክ በታሪክ -የመተካቱ
የቀናት መንጎድ - ትርጉሙ ጠፍቶ
ህዝብ ዛሬን ክዶ - ሰው ዛሬን ጠልቶ
ከትናንት ጓዳ -መሽጎ ገብቶ
እንዴት ይኖራል -አሁንን ጠልቶ ?

ድንቅንቅታ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Sun Apr 07, 2013 6:21 pm    Post subject: Reply with quote

አልሞተም ይሁዳ

የክህደቱ - ግዝፈት መጠን - ብርሀነ ውስጡን -አክስሎ
የበደሉ -ጸጸት ሸክም - ሕሊናውን አቁስሎ
መኖር ታክቶት - በጸለመ -እሱነቱ
መስሎኝ ነበር -አኮ ይሁዳ - የታነቀ - በኅጢአቱ

ግና ዛሬ - የዘመን ጉድ - ጉድ አሳየ
ከአንበብነው - ከመጣፉ - የተለየ

ትውፊት ንግርት - ትንቢቱ ሁሉ - ተለዋውጦ
ሀዲስ ብሉይ - ኦሪት ራዕይ - ተገላብጦ
የከሃዲው - መታነቁ -ሞቱ ቀርቶ
ማቅ መልብሱ -ምልጃው ጠፍቶ
በአደባባይ - እንደጻዲቅ - መድረክ ወጥቶ
ክህደት ግብሩን -ገድሉን ሲያውጅ - አፉን ሞልቶ

እውነት ታስሮ - ለስቅላት - ፍርድ ሲነዳ
ብዙ አሳየን - ገና አልሞተም -የኛ ይሁዳ !

Last edited by እቴጌይት on Mon Apr 08, 2013 4:17 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
TABI

ኮትኳች

Joined: 22 Dec 2008
Posts: 124

PostPosted: Mon Apr 08, 2013 12:37 pm    Post subject: Reply with quote

እቴጌይት .

ግጥሞችሽ በጣም ምርጥ ናቸው ፕሮፌሽናል ግጥሞች ናቸው ፉል ታይም ገጣሚ ብትሆኚ ሳያዋጣሽ አይቀርም Very Happy

የፖለቲካ ምልከታሽንም አድናቂ ነበርኩ አሁንስ ከአሰስ ገሰሱ መነታረኩ አስጠላሽ መሰለኝ እዛ ቦታም ጠፋሽ

አክባሪሽ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Mon Apr 08, 2013 10:57 pm    Post subject: Reply with quote

TABI እንደጻፈ(ች)ው:
እቴጌይት .

ግጥሞችሽ በጣም ምርጥ ናቸው ፕሮፌሽናል ግጥሞች ናቸው ፉል ታይም ገጣሚ ብትሆኚ ሳያዋጣሽ አይቀርም Very Happy

የፖለቲካ ምልከታሽንም አድናቂ ነበርኩ አሁንስ ከአሰስ ገሰሱ መነታረኩ አስጠላሽ መሰለኝ እዛ ቦታም ጠፋሽ

አክባሪሽ

ሠላም TAB
ለመልካም አስተያየትህ አመሰግናለሁ ! ያክብርልኝ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Tue Apr 09, 2013 3:57 am    Post subject: Reply with quote

ወለል ወይስ ጣሪያ

ምናቤ ሳይከለል -በገሀዱ ዓለም እውነታ
በዕለት ተለት ኑሮ ሀቅ - ተሸቦ ሳይገታ
የተስፋዬን ጉልላት - የነግ ሕልሜን አግዝፎት
የኔነቴ ራዕዬን - እላይ አብርሮ አክንፎት
የሀሳቤ መጥለቂያ -የምኞቴ ጀምበሩን
- የተስፋዬ ድነበሩን
በሀሳብ ሞገድ አቃንቶት - ጣራዬን ብመለከት
-የሁለንተናው ርቀት
ብቧጥጥ ብንጠራራ - ብዘል የማልደርስበት ....
ለእኔ ሩቅ ሆኖ የታየኝ -ከታች ቤት ሆኜ ሳየው
ለካስ ከላይ ቤት ላለው - መራመጃ ወለሉ ነው !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Fri Apr 26, 2013 10:47 pm    Post subject: Reply with quote

አርባ ቀን

ቀን ከሌሊት ሳንተኛ
ብንሮጥ ብንማስን እኛ
በያሕዌ ጥንተ ዕቅድ - በእሳቤው ታሽጎ
የሕወታችን መንገዱ -ቅድመ ዓለም ተደንግጎ
ካበቃለት ይህ ኑሮ
በአርባ ቀናት ተሰፍሮ ...

ላንዳንዱ መሸከሚያ
ለሌላው ደሞ ማሰቢያ
ለምን ጭንቅላት ሰጠ - እጅ እግርስ ለምን ሰራ ?
መክሊት ለምን አደለ - ለምን ንግድ አሰማራ ?
ደግሞስ የምጻቱ ፍርድ - እንዴት ፍርድ ተብሎ ይጠራ ?

Last edited by እቴጌይት on Sat Apr 27, 2013 12:44 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደመላሽ

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2010
Posts: 363

PostPosted: Fri Apr 26, 2013 11:35 pm    Post subject: Reply with quote

በዚ መልኩ አስተካክሎ ወንድማለማውዬ .

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:

አርባ ቀን

ቀን ከሌሊት ሳንተኛ
ብንሮጥ ብንማስን እኛ

በያሕዌ ቅድመ ዕቅድ - በእሳቤው ታሽጎ
የሕወታችን መንገዱ -ቅድመ ዓለም ተደንግጎ
ካበቃለት ይህ ኑሮ
በአርባ ቀናት ተሰፍሮ ...

ላንዳንዱ መሸከሚያ
ለሌላው ደሞ ማሰቢያ
ለምን ጭንቅላት ሰጠ - እጅ እግርስ ለምን ሰራ ?
መክሊት ለምን አደለ - ለምን ንግድ አሰማራ ?
ደግሞስ የምጻቱ ፍርድ - እንዴት ፍርድ ተብሎ ይጠራ ?

_________________
History teachs us that we DON'T learn from History
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
TABI

ኮትኳች

Joined: 22 Dec 2008
Posts: 124

PostPosted: Sat Apr 27, 2013 8:54 am    Post subject: Reply with quote

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
አርባ ቀን

ቀን ከሌሊት ሳንተኛ
ብንሮጥ ብንማስን እኛ
በያሕዌ ጥንተ ዕቅድ - በእሳቤው ታሽጎ
የሕወታችን መንገዱ -ቅድመ ዓለም ተደንግጎ
ካበቃለት ይህ ኑሮ
በአርባ ቀናት ተሰፍሮ ...

ላንዳንዱ መሸከሚያ
ለሌላው ደሞ ማሰቢያ
ለምን ጭንቅላት ሰጠ - እጅ እግርስ ለምን ሰራ ?
መክሊት ለምን አደለ - ለምን ንግድ አሰማራ ?
ደግሞስ የምጻቱ ፍርድ - እንዴት ፍርድ ተብሎ ይጠራ ?

እቱዬ ከግጥሞችሽ ጋር ፍቅር ያዘኝ መሰል Very Happy

ባላገባ ኖሮ ካንቺ ጋርም ሳይዘኝ አይቀርም ነበር Laughing

ግጥምሽ ጠንካራ ነች ጠንካራ ጥያቄንም አዝላለች ምላሽን ትጠይቃለች ከሀይማኖት አዋቂዎች :: የአርባ ቀን እድል ምንድነው ?

ዲጎኔ ለምን በግጥም አይሞክራትም ?

አንቺ እንድታስቢበት ደምሎ እንዲሸከምበት እኩል ጭንቅላትን የለገሰ አምላክ ክብሩ ይስፋ ! አንዱ ሊያስብ አንዱ ሊሸከም ግድ ነውና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እቴጌይት

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Sep 2007
Posts: 547

PostPosted: Sat Apr 27, 2013 9:09 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም TABI
በድጋሚ ለመልካም አስተያየትህ አመሰግናለሁ :: አስቲ አንድ ጥያቄ አዘል ግጥም ልመርቅ ደሞ ::

ቧልት ወይስ ባልትና

ባህር ላይ አዝንባ - ሜዳውን አድርቃ
ባለው ላይ ትሩፋት - ከሌለው መርቃ
ብዙውን አክስላ -ጥቂቱን አፍክታ
አንዱን ማቱሳላ -አንዱን በእንጭጭ ቀጭታ
ተፈጥሮ ቀመሯ
አካሄድ ነገሯ
ውጥንቅጥ ውጥኗ
ቧልት ነው ባልትና ?

Last edited by እቴጌይት on Tue Apr 30, 2013 3:13 am; edited 8 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
TABI

ኮትኳች

Joined: 22 Dec 2008
Posts: 124

PostPosted: Sat Apr 27, 2013 10:11 am    Post subject: Reply with quote

እቴጌይት እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም TABI
በድጋሚ ለመልካም አስተያየትህ አመሰግናለሁ :: አስቲ አንድ ጥያቄ አዘል ግጥም ልመርቅ ደሞ ::

ቧልት ወይስ ባልትና

ባህር ላይ አዝንባ - ሜዳውን አድርቃ
ባለው ላይ ትሩፋት - ከሌለው መርቃ
ብዙውን አክስላ -ጥቂቱን አፍክታ
አንዱን ማቱሳላ -አንዱን በእንጭጭ ቀጭታ
ተፈጥሮ ቀመሯ
አካሄድ ነገሯ
ውጥንቅጥ ውጥኗ
ቧልት ነው ባልትና ?

ዋው በድጋሚ !! የታላቹህ ዲጎኔ እናመሰግንሀለን ሳምራዊ አህመድ ወዘተ ...ቻሌንጅ ነው መልሱ እስቲ

እኔ ሀሳቤን በግጥም መግለጽ አልችልም

ነገር ግን I believe God is Fair and everything happens for a reason

ስለዚህ ተፈጥሮ ቧልት ሳትሆን ባልትና ነች የሚለውን ይበልጥ እወስደዋለው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደመላሽ

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2010
Posts: 363

PostPosted: Sat Apr 27, 2013 1:43 pm    Post subject: Reply with quote

ግዴለም እኔ ላንቴ ገጥማሎ ::

ኢቱዬ ናይለቲ
ባይቺሊም ላንቺ መቀኘቲ
TABI ፍቅሪ አለበቲ
የሚያስተነፍሶ ነቅሎ በመሰካቲ Laughing

ጊና ኢቱዬ ?
ባማረው የስንኚ ቁዋጠሮሽ
ካካጃለ ሊተኛ አብሮሽ (ሊጫወቲ አባሮሽ )
በቃሎቺሽ ውበቲ ላንቺ ካታመኘ
በምናቡ ሲሎሽ ባሳቢ ከናኘ
ማሰቢያኖ መሸከሚያ ታዛቢውስ ያገኘ ? Laughing Laughing

ደምሎ ስንታዮ
የገጣሚ አስገጣሚና አጋጣሚ አገናኝ Laughing Laughing

TABI እንደጻፈ(ች)ው:

እኔ ሀሳቤን በግጥም መግለጽ አልችልም

_________________
History teachs us that we DON'T learn from History
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia