WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው !
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጣዕም

ኮትኳች

Joined: 01 May 2004
Posts: 265
Location: canada

PostPosted: Sat Aug 15, 2009 6:45 pm    Post subject: ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው ! Reply with quote

የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ :: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ .. http://www.haddisnigat.org
_________________
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Aug 17, 2009 2:24 pm    Post subject: Reply with quote

Code:
የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ :: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ

ያስቀመጥከውን ዌብ ሳይት ክሊክ ከማድረጌ በፊት -- እናንተው እራሳችሁ ያላችሁበት ዝግጅት መስሎኝ - አንተን በመድረክ የማይበት አጋጣሚ ተፈጠረ ብዬ በደስታ ፈገግ ብዬ ነበር ::
ከምር ግን ክርስትያንም ይኖርበት ይሆን ብዬም ልጠይቅህ ነበር -- ቢሆንም ግን እስቲ እንሞክረዋለን -- ሳቅ በሳቅ ለመሆን ::

ምነው ግን ሁላችሁም አንድ ላይ ተግተለተላችሁ ?
ታምራት ዘፋኙ , እነሻምበል በላይ ሌሎችም ሰሞኑን ቶሮንቶን ሊያጣብቧት ነው :: ሁሉንም የምንገባ ከሆነ ግን ከሰርን ማለት ነው Laughing Laughing

ጣዕሙ -- በስፖንሰርነቱ ውስጥ ካለህበት ግን በናንተም እንዳይደገም አንድ ቅሬታ ላስመዝግብ ::
ባለፈው እነቢኒያም -- ሸምሱን ያመጡ ጊዜ የተካሄደው ትኬት ሽያጭም ሆነ በሩ ላይ የሰዉ አገባብ ሁኔታ እጅግ አሳፋሪ ነበር ::
በስርዓት ሰልፍ መያዝ ከምር ሞኝነት ይመስላል :: ሰልፉ በብሉር ስትሪት ኖርዝ በኩል ባለች ትንሽ ስትሪት ኮርነር ላይ ሁሉ ታጥፎ የሄደና የረዘመ ነበር :: ሰዉ የተሰለፈው አንድ ሰዓት ቀድሞ መጥቶ ነበር : በብዛት ቀድሞ የገባው ግን በኋላ የመጣውና ቀጥታ በትኬት መቁረጫው በፊት ከሰልፍ ውጭ የቆመውና በትውውቅ የሚተማመነው ብቻ ነው :: እናም ያሰጠላ ነበር ግርግሩ :: ፕሊስ ይህ እንዳይደገም - የሰዉ ቁጥር እንደዛ የሚበዛላችሁ ከሆነ :: "የአበሻ ቀጠሮ " ጋር የሚመሳሰሉ መጥፎ ባህሪዎቻችንን እንድናስወግድ እስቲ እናንተ መሪ ሁኑ ::

ታምራትንና ላንተ ስል ደግሞ Laughing Laughing ይህንን ኮሜዲ ለማየት ሞክራለሁ :: እንደተለመደው አንተንና ክርስትያንን በዐይን አያችሁ ይሆን እንዴ ብዬ ልመኝ :: እስቲ የዛ ሰው ይበለን -- መቀነቱ አሁንም ካልጠለፈን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1568
Location: Mars

PostPosted: Mon Aug 17, 2009 4:24 pm    Post subject: ጉድ ነው Reply with quote

ሄሎ ዉዶች የጥንቶቹ

ጣዕም ታዲያስ ! እናንተ ሥራችሁን አልፈታችሁም ጎበዞች ናችሁ !! በርቱ !

ብሩክ ! አንተ ብቻም አይደለህ በቦታዉ የምትገኘው "ተጋባዥ " እንግዳም ሁሉ አለ !! ቅቅቅ ከመጣሕ ጉድህ ነው ! መቼም !! ተጋባዥ እንግዳው ጣዕምና አንተን ማየት ይፈልጋል !!

ዳሞት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Aug 17, 2009 5:07 pm    Post subject: Reply with quote

ዋኖሴው የዳሞት ልጅ - የጥንቱ የጧቱ
አሁኑኑ ሳቅ በሳቅ ሆንኩልህ --- ጉድህ ፈላ ስትለኝ :: ምን የኔ ብቻ የጣዕሙም ሊፈላ ነው -- የክርስትያንንስ ድምጹንም ሰምቻለሁ - አልያዝ ያለው ጣዕሙ ነበር -- ራሱን ሊደብቅ ቢሞክርም ትኬቱን ሲያሻሽጥ ጋማውን እለዋለሁ ::

"ተጋባዥ " እንግዳው አንተ እንዳትሆንና ከነጥምጥምህ እንዳላይህ :: እኛስ እኛ ነን - ምን እንዳይቀርብን :: ሚስት የለንም ብለን አልዋሸን :: ይብላኝ ለናንተ አይነቱ -- አንዴ ተማሪ አንዴ ወያኔ ሲገባ የናቴን ጡት የቦንቡ ፍንዳታ አስጣለኝ ብላችሁ ለዋሻችሁት Laughing

"ምጣና " እንይህ እስቲ
ዋኖሴ ያንን የጥንቱን -- እንደልባችን እንጣጥ እንጣጥ ያልንበትን ጊዜ በማስታወስ እጅ ነስቻለሁ -- አይጥፉ እባክዎትን -- እኔን ክርስትያኖና ብርሀናዊት ከሚላፉበት ቦታ አያጡኝም Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጣዕም

ኮትኳች

Joined: 01 May 2004
Posts: 265
Location: canada

PostPosted: Mon Aug 17, 2009 10:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ብሩኬ ወዳጄ
ደህና ነህ ወይ ? በጣም ደስ አለኝ ጎራ በማለትህ :: ምነው ግን የቅርብ ሩቅ ሆንክ ? ባለፈው ዓመት ለምልክት ቅጠልያ ቀለም ጨርቅ አንጠልጥየ በር ላይ ብጠብቅህ የውሀ ሽታ ሆንክብኝ :: እንደው የመተያያችን ጊዜ እራቀብኝ :: መጪው ዕሁድ ግን ሳንተያይ አንቀርም ቀልቤ ነግሮኛል : ቅቅቅ ክርስቲያንም በቃ ሁሌ እንደፎከረ ነው ;;
እንልከው የሁላችን መግተልተል የኮሚኒቲ አባላትን ከማሰልቸት አልፎ ኪስን ያራቁታል :: መቸም የመጀመሪያ አዘጋጆቹ እኛ ነበርን ሆኖም ሌሎችም በግላቸው ከእኛ በኍላ እንሞክር በማለት እንዳየህው የተለያየ ዝግጅት ሊያደርጉ ደፋ ቀና ይላሉ :: ብቻ ሁላችንም ይቅናን :: ሌላ ምን ይባላል ወገን ::

ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በመጣ ወቅት የነበረዉን የትኬት ሽያጭና የበር ላይ ችግር አይነት በእኛ በኩል እንዳይደገም በማሰብ አንድ ሰው ትኬት ከሁለት ሰው በላይ መግዛት እንደማይችል በቅድሚያ በዕለቱ ለማሳሰብ እንጥራለን :: ዝግጅቱም በስዓቱ እንደሚጀመር ስፖንሰር ካደርጓቸው ድርጅቶች ማረጋገጫ አግኝቻለሁ :: አይዞንን ብቻ አንተ ገተልተል አድርገህ አምጣቸው ውዶችህን ; ቅቅቅ

እስቲ እባክህ አሁን እንኳን እንገናኝ :; እኔን አታጣኝም
ቸር እንሰንብት
_________________
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ጣዕም

ኮትኳች

Joined: 01 May 2004
Posts: 265
Location: canada

PostPosted: Mon Aug 17, 2009 10:25 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ዋኖሴ
እንዴት ነህ ወገን ደህና ነህ ወይ ? የሳይቨር ልጆች የጥንቶቹ ትናፈቃላችሁ :: እንጀራ ፍለጋ ደፋ ቀና ስንል የስንት ወዳጆች ትውውቅ ተዘነጋ :: ዋኖሴ ; ዋርካ ስል ስራዎችህን አነባለሁ በርታልኝ ::

መቸም እንዳቅማችን እንሞክራልን :: ምንም እንኳን ጊዜና አጋጣሚው እየጠፋ እንደምንፈልገው ባይሆንም በየወሩ ወቅት እየጠበቅን እርስ በእርሳችን እንሳሳቃለን እንማማራለን :: አልፎ አልፎም ይህን የመሰለ ዝግጅት በማቅረብ ወገኖቻችን ጋር እንዝናናለን :: መቸስ የጣይቱ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ምስጋና ይግባቸው ወደፊትም የእኛንም ጭምር ደብለቅ እያደርግን እንቀጥላለን :: ቅቅቅ

እንግዶቻችንን በናፍቆት እንጠብቃለን :: ቅቅቅቅ ጠርቀምቀም ብላችሁ ! ከመግቢያው በር ላይ ደግሞ ምልክት ይዠ እጠብቃችኍለሁ ::

እስከዛው ቸር ይግጠመን
_________________
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1568
Location: Mars

PostPosted: Wed Aug 19, 2009 12:54 am    Post subject: Reply with quote

አመሰግናለሁ ! ጣዕም ! ተጋባዥ እንግዳዉ ቤትህ ሊመጣ ይችላል ተዘጋጂ ! ቅቅቅ ብሩክ ግን ካለ አይመጣም ! ቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 782
Location: united states

PostPosted: Wed Aug 19, 2009 3:35 am    Post subject: Re: ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው ! Reply with quote

ጣዕም እንደጻፈ(ች)ው:
የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ :: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ .. http://www.haddisnigat.org

*************************************************

ስላም ጣእምዩ እንዴት ነህልኝ ብሮ Question
እነ አለምፅሀይን (ጣይቱ መአከልን ) ስላም በልልኝ መቼም የቅርብ እሩቅ ከሆንኩኝ ስነበትኩኝ ከነሱም ጋር አይገርምህም ...............ምንለበት እኔም እንደ ብሩክ መገኝት ብቸል ሀሪፈ ነበር ........................

ዋኖስቻን እንዴት ነህልኝ ብሮ Question ሁሉም አማን አገሩ ስፈሩ መንደሩ አረ ሁሉም ቅቅቅቅቅቅቅቅ ስላም ነው ያቺን ቤት ከዘጉብን ቦሀላ መተያየት ጠፋ ይገርማል

ከብዙ መውድድድ ጋር
የግልልልልልልል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Aug 19, 2009 1:57 pm    Post subject: Reply with quote

Code:
ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በመጣ ወቅት የነበረዉን የትኬት ሽያጭና የበር ላይ ችግር አይነት በእኛ በኩል እንዳይደገም በማሰብ አንድ ሰው ትኬት ከሁለት ሰው በላይ መግዛት እንደማይችል በቅድሚያ በዕለቱ ለማሳሰብ እንጥራለን :: ዝግጅቱም በስዓቱ እንደሚጀመር ስፖንሰር ካደርጓቸው ድርጅቶች ማረጋገጫ አግኝቻለሁ :: አይዞንን ብቻ አንተ ገተልተል አድርገህ አምጣቸው ውዶችህን ; ቅቅቅ

ክበበው የሚለው ስሙ አስቸግሮኝ ነበር ሸምሱ ያልኩት :: ክበበው በመጠኑ አስደሰተን -- በመጠኑ ! አጠረ ዝግጅቱ :: ለዕረፍት የሚሄድበትም ጊዜ በዛ --- ቢሆንም ግን በመጠኑ ዴስ ብሎን አመሸን --- Laughing Laughing የትኬት አሻሻጩንና የስፖንሰሮቹን ብቃት ሳስበው ግን --- አልፎ አልፎ -- "ዘፋኝ አመጣን " ምናምን ብለው ሲያስተዋውቁ ባልሄድስ የሚል ሀሳብ ብልጭ ይልብኛል :: መቼ ይሆን "እኛ " --- "እኛ " ለሆነው ነገር ክብርና ስርዐትን ምንሰጠው ?
ለመሆኑ ሙቪ ወይም ሬስቶራንት ስንሄድ ከምንይዘው ሰልፍ (ከሌሎች ጋር ) ንቅንቅ እንላለን ? ሰውነታችን ሳይሆን ዓይናችን ከመስመር ዝንፍ የሚልብን ስንቶቻችን ነን ::
አወኩሽ ናኩሽ --- ድክመታችን !

ጣዕሙ ምናልባት ከስፖንሰሮቹ መሀል አንዱ አንተ ከሆንክ (እንደሌለህበት ፍንጭ ብትሰጥም ) እድሉ አላችሁና እስቲም እኛም እንደ "ሌሎቹ " በስርዐት እንድንገባ አድርጉ ::

ዋኖስ -- አንተ እንግዳ ይኑርህ እንጂ -- አይዞን ዕንግዳህን ቀና ብለን አናይም --- ከምር ግን -- ምናልባት የሚለውን ሀሳብ ትቼ የግድ መሄድ አለብኝ ብዬ ወስኛለሁ Laughing Laughing ከመጣህ ቅዳሜ ጧት ማርያም ቤተክርስትያን ቼክ አድርገኝ ቅቅቅ እሁድማ አልቀርም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Wed Aug 19, 2009 4:19 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ሁላችሁም :

ደስ የሚል ዜና ነው ... ዘንድሮስ አያመልጠኝም ብዬ ለራሴ ምያለሁ ..... ሰንኮፍ ካላገጠመኝ ....ጣዕማችን ....እንግዲህ አንተን ፍለጋ አይኔን በራፍይ ላይ ማጎረጥረጤ አይቀርም ::

ብሩኬ አንተንስ ማወቅ አያቅተኝም .. በአካል ባላይህም ከሰው መሀል ለይቼ የማውቅህ ይመስለኛል ... ስማ ደግሞ እንዳለፈው እንዳትጠፋ አደራ .. Sad

ዋኖሴ እንግዳችን ስለሆንክ በቀይ ስጋጃ ምንጣፍ እንቀበላለን አንተ ብቻ ምጣ ::

በሉ እንግዲህ እዚያው እንገናኝ ..

ብሩኬ ስትደርስ ስልክ ምታልኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Aug 24, 2009 2:22 pm    Post subject: Reply with quote

"ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው "

3:00 pm ዝግጅቱ የሚጀመር ሲሆን 2:30 pm በሩ ይከፈታል ይላል ማስታወቅያው ::
አረፈድን ብለን ተጣደፍን --- 2:55 ደረስን ትኬታችንን ቆርጠን --- ቦታ መምረጥ ሳንቸገር የሚመቸን ቦታ ተቀመጥን ::
------
ደከም ያለ ጭብጨባ ተሰማ ----- ለማንኛውም ዝግጅቱ ተጀመረ ::
በአበሻ ምድር እንመራሀለን ብለው የተቀመጡ ጥቂቶች በወጣቱ ትውልድ ላይ ያደረሱት በደል 1 -- ስደት -- ሽሽት ትውስታ ..... ሩጫ ,
አዎ ሽሽት የችግራችን ሁሉ መፍትሄ መሆኑን ያስታወሰ መልዕክት በዝግታ በአዕምሯችን ተሰራጨ -- አለምጸሀይ ወዳጆ የወጣቱን ትውልድ መከራ ከቤተሰቧ ታሪክ ጋር , ሳይጠገብ ያጣችውን የወላጆቿን ፍቅርና --- በድንገት ህይወታቸው ይቺን ምድር ለአንዴና ለመጨረሻው ሳይሰናበተው ያስረከቧትን የወንድሞቿን አደራ -- ልጅ መውለድ አምሯት -- በሀላፊነቷ ምክንያት አምልጧት የሚሰማትን ስሜት በዕንባ ታጅባ ስታሰማን ተመልካቹ አብሯት በጸጥታ ያነባ ጀመር --- ጌትሽ ወንድሟ በለጋ እድሜው ብሄራዊ ውትድርና ሸሽቶ አሜሪካ ከመድረሱ በፊት በሱዳን በረሀ ያጋጠመው ችግርና የልጅነት ፍቅሩን አንስቶ ከህመም ስሜቱ ታግሎ ሲያወራ ሳየውና በአካባቢዬ የተቀመጡት ሰዎች ፍጹም በስሜት የተሞላ ለቅሶ ስመለከት ---- የዝግጅቱን ርዕስ እንደገና ለማየት ተገደድኩ ---

ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው ---- ወይ አለመገጣጠም አልኩ ---- በርግጥም ውነተኛ ታሪካችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ዝግጅት ነው ---- "ወንዶች " አሉ ጠንካሮች ናቸው : ለቅሶን ይታገሉታል ---- ድሮ ቀረ --- ወንዶቹም አለቀሱ --- በዝግጅቱ ተመሰጥኩ - በታሪኩም ከልብ አዘንኩ --- እንባን ግን ተቆጣጠርኩት -- ድሮ የተወራላቸው "ወንዶች " ውስጥ እራሴን አገኘሁት Laughing
የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ---- ሐዲስ ንጋት የቶሮንቶውም ምንኛ ድንቆች ናችሁ :: የምታፈሱትን ጊዜና ጉልበት -- ካለው የሰሜን አሜሪካ ኑሮ ጋር ሳስበውና የሌሎችንም የአገሬ ሰዎች እገዛ ደረጃ ስገምተው በእጅጉ አከበርኳችሁ :: ቀናሁባችሁም ::
በርቱ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሊስትሮው

ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2004
Posts: 278

PostPosted: Mon Aug 24, 2009 5:40 pm    Post subject: Reply with quote

brookk እንደጻፈ(ች)ው:
"ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው "

---- በርግጥም ውነተኛ ታሪካችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ዝግጅት ነው ---- "ወንዶች " አሉ ጠንካሮች ናቸው : ለቅሶን ይታገሉታል ---- ድሮ ቀረ --- ወንዶቹም አለቀሱ --- በዝግጅቱ ተመሰጥኩ - በታሪኩም ከልብ አዘንኩ --- እንባን ግን ተቆጣጠርኩት -- ድሮ የተወራላቸው "ወንዶች " ውስጥ እራሴን አገኘሁት Laughing

.................... ደረቅ ............ Crying or Very sad
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Aug 24, 2009 8:45 pm    Post subject: Reply with quote

ሊስትሮው እንደጻፈ(ች)ው:

.................... ደረቅ ............ Crying or Very sad

ታድያ በየሜዳው ዝም ብለን እንልቀቀው ? Shocked
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሊስትሮው

ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2004
Posts: 278

PostPosted: Tue Aug 25, 2009 3:27 pm    Post subject: Reply with quote

brookk እንደጻፈ(ች)ው:
ሊስትሮው እንደጻፈ(ች)ው:

.................... ደረቅ ............ Crying or Very sad

ታድያ በየሜዳው ዝም ብለን እንልቀቀው ? Shocked

ኡፕስ ለካ ሜዳ ላይ ነበራቹ ደሞ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ መስላቹኝ Smile ......ቢሆንም ቢሆንም ግን ምን አለህ ቢደማህ Razz ......አረ ባክ ያቺ በረሮ የሆነበት ስሟን ያየሁ መስሎኝ Question መቸም ስራዋ ገነት አያስገባት ንዳው ትለፋለች ንጂ Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 286
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Aug 25, 2009 4:22 pm    Post subject: Reply with quote

ሊስትሮው
ምናለ ቢደማህ ? ትቀልዳለህ
ሜዳና አዳራሽ አሁን ምን ልዩነት አላቸው ? አዳራሹም ሰፊ --- ሜዳውም ልቅ
እኛ የለመድነው --- ሰው ሳያየን -- ሳይታዘበን ወደውስጥ ገባ ብለን --- ጠበብ ያለውጋ ነው --- ስቅስቅ ብለን ምናፈሰው አባ ! ዕንባችንን

በረሮማ ደከመች -- አረጀች እሷም --- ሄዶ ሄዶ መቼም ማርጀት አይቀር Laughing Laughing ተለወጠች እንደድሮም መዝለል ተወች
ቢሆንም በጣሙን ናፍቃሀለች --- እራስህን በራስህ በሷ ስም እንድትስምም ጋብዛሀለች
በል ኢንጆይ ዩርሰልፍ

በነገራችን ላይ ሰሞኑን በጣም ተከስተናል -- አትጥፋ
አርዕስቱን ግን አትርሳ --- ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው - ነው የሚለው :: ከለቅሶው በኋላ ሳቅ በሳቅ ሆነን ነበር --- ጣዕሙንም በአካል አየሁት --- ማለፊያ ልጅ ነው ቅቅቅ ክርስትያኖ ድምጡ አልተሰማም :: እኔም ስልክ አልመታሁም --- ግን አዳራሹ ውስጥ ስጣራ ነበር -- ብቅ ብለው አስተያየት ቢሰጡ ብዬ ነበር --- እነሱ እንደኔ ስራ የፈቱ አይመስልም Laughing
ድራማው የተጀመረበት ሰዐት ግን በአበሻው አቆጣጠር ነበር Laughing Laughing ግን በዝግጅቱ ተካስን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia