WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች :- ሙላቱ አስታጥቄ እና ....
Goto page Previous  1, 2, 3 ... , 11, 12, 13  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jan 28, 2012 2:35 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሙዚቃ አፍቃሪዎች :-

መሐሙድ አህመድ በችሎታው በነገሠበት ዘመን በስድሣዎቹ አጋማሽ የተጫወታቸውን ዜማዎች በዩ -ቲዩብ ላይ ተለጥፈው አገኘኋቸውና ከእናንተ ጋር ለምን አብረን አናዳምጣቸውም የሚል ኃሣብ መጣብኝ ::

ምንጮች :-
1 ..... መሐሙድ አህመድ : የሺ ሀረጊቱ
የሺ የሺ የሺ የሺ የሺ ሀረጊቱ :
የክቲቱ :
ሥንቱን ሥንቱን ሥንቱን ደጅ ልጥና ልማለድ ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ ::

የሺ ሀረጊቱ :
የክቲቱ :
የእኔ ዘረ -ብዙ :
ሥንቱን ደጅ ልጥና ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ (2 ጊዜ )

የሺ ሀረጊቱ ሥሚኝ ፍቅሬ : የእኔ ዘረ ብዙ :
በጨረቃ ይዤሽ እንዳልጠፋ : ብዙ ነው መዘዙ ::
እናትሽን ባስጠይቅ ስለፍቅር : አይገባኝም አሉ :
ለአባትሽ ሰው ባስልክ እንደገና : በእኔ ያሾፋሉ ::

የሺ ሀረጊቱ :
የክቲቱ :
የእኔ ዘረ -ብዙ :
ሥንቱን ደጅ ልጥና : ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ (2 ጊዜ )

የሺ ሀረጊቱ :
የእኔ የክቲቱ :
ሥንቱን ደጅ ልጥና : ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ ::

የሺ ሀረጊቱ :
የክቲቱ :
የእኔ ዘረ -ብዙ :
ሥንቱን ደጅ ልጥና : ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ (2 ጊዜ )

አማርኛ እንዳለሽ አስረጃቸው : ውስጡን ዘርዝረሽ :
ፍቅሩ አሸንፎኛል መሄዴ ነው : እረፉት ብለሽ ::
አምናለሁ በእናትሽ : በአባትሽ ቤት ጮማ ሠልችቶሻል :
አትስጊ ከእኔ ዘንድ አይገድሽም : ልብ ይቀርብልሻል ::

የሺ ሀረጊቱ :
የክቲቱ :
የእኔ ዘረ -ብዙ :
ሥንቱን ደጅ ልጥና : ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ (3 ጊዜ )
ሥንቱን ደጅ ልጥና : ልማለድ :
ይዤሽ እስክነጉድ ::

2 ..... መሐሙድ አህመድ : ሁሉም በጊዜው ነው ::

ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል :
በማለት --- ቀድሞ ተናግሮታል ::
ሣትደፈር ኖራ : ጨረቃም ርቃ :
በሰው ተፈተነች : ጊዜዋን ጠብቃ ::

ሽምብራ ሲዘራ : ሌላው ይታጨዳል :
አንዱ ሞቶ ሲያድር : አንዱ ይወለዳል ::
ቆንጆዋ እያለች : የምታምር ሸጋ :
አጋጣሚ ሆኖ : ይወደዳል ፉንጋ ::

ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል :
በማለት --- ቀድሞ ተናግሮታል ::
ሣትደፈር ኖራ : ጨረቃም ርቃ :
በሰው ተፈተነች : ጊዜዋን ጠብቃ ::

የተደነቀው : ተብሎ በራሪ :
ገጠር ተሠደደ : አሁን የታል ጋሪ ::
ዕውነቱን ልናገር : ባይመሥል ዘለፋ :
ያን -ጊዜ በጋሪም : ያገባም አይጠፋ ::

ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል :
በማለት --- ቀድሞ ተናግሮታል ::
ሣትደፈር ኖራ : ጨረቃም ርቃ :
በሰው ተፈተነች : ጊዜዋን ጠብቃ :: (2 ጊዜ )

ኩር -ኩር ተቆጥራ ያን -ጊዜ እንደ ታኖስ :
ምርጥ እኮ ነበረች : ሰው ስታመላልስ ::
ሁሉ ሁካታ : አሁን ተቀንሶ :
ማርቸዲስ ይዞታል : ድምፁን አለስልሦ ::

ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል :
በማለት --- ቀድሞ ተናግሮታል ::
ሣትደፈር ኖራ : ጨረቃም ርቃ :
በሰው ተፈተነች : ጊዜዋን ጠብቃ ::

በሰው ተፈተነች ጊዜዋን ጠብቃ :: (2ጊዜ )

3 ..... መሐሙድ አህመድ : ችላ አትበይ

የኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
አይ ... ቶሎ ነይ ::
የእኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
እባክሽን ቶሎ ነይ ::

ነገር ወዲያ ወዲህ : ሆነና ቸገረኝ :
ከአንቺ የተለየ : ምን ኃሣብ ነበረኝ ::
ፍፁም ጥሩ አይደለም : የሰው ወሬ አትሥሚ :
ስለ እግዚአብሔር ብለሽ : በፍቅር አትለግሚ ::

የኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
አይ ... ቶሎ ነይ ::
የእኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
እባክሽን ቶሎ ነይ ::

ስወድሽ : ሣፈቅርሽ : እንደዚያ እያየሽኝ :
በሰው ወሬ ናዳ : ምነው በረገግሽ ::
በጆሮሽ ብትሰሚው : ፊቴን ሣላጠቁረው :
ፍቅራችንን በአጭር ለምን እናስቀረው ::

የኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
አይ ... ቶሎ ነይ ::
የእኔ ኃሣብ : ችላ አትበይ :
እባክሽን ቶሎ ነይ ::

4 ..... መሐሙድ አህመድ : እንቁ መሣይ ::

እንዳንቺ አላየሁም እስካሁን :
ተፈጥሮሽ በዓለም ላይ ምን ይሆን :
አልማዝ ዕንቁ መሣይ : ወርቅ ሥራ :
ውበትሽ ፀሐይ ነው የሚያበራ ::

ከጨረቃ ድምቀት :
ከፀሐይ ሙቀት :
ከአበቦች መዓዛ : ከአትክልቶች ውበት :
ቀምሞ ሠርቶሻል ከሁሉም ዓይነት :
ወደ ዓለም ሥትመጪ : በሥነ -ፍጥረት ::

እንዳንቺ አላየሁም እስካሁን :
ተፈጥሮሽ በዓለም ላይ ምን ይሆን :
አልማዝ ዕንቁ መሣይ : ወርቅ ሥራ :
ውበትሽ ፀሐይ ነው የሚያበራ ::

በዓለም ላይ ተፈጥረው : በዓለም የሚውሉ :
በተፈጥሮ ውበት የሚደነቁ አሉ ::
እኔም በበኩሌ እንደመረጥኩሽ :
አልማዝ ዕንቁ መሣይ በዕውነት አንቺ ነሽ ::

እንዳንቺ አላየሁም እስካሁን :
ተፈጥሮሽ በዓለም ላይ ምን ይሆን :
አልማዝ ዕንቁ መሣይ : ወርቅ ሥራ :
ውበትሽ ፀሐይ ነው የሚያበራ :: (2 ጊዜ )

ለዛና ፈገግታሽ : የደስታ ምንጭ :
ከፊትሽ አይጠፋም : ምንም ብትቆጪ ::
ደግሞም በአለባበስ : ምን ይወጣልሻል :
አዋቂ የሠራው : ሁሉም ያምርብሻል ::

እንዳንቺ አላየሁም እስካሁን :
ተፈጥሮሽ በዓለም ላይ ምን ይሆን :
አልማዝ ዕንቁ መሣይ : ወርቅ ሥራ :
ውበትሽ ፀሐይ ነው የሚያበራ :: (2 ጊዜ )

ውበትሽ ፀሐይ ነው የሚያበራ :Sad7 ጊዜ )

5 ..... መሐሙድ አህመድ : ትዝታ ::

ትዝታሽ ዘወትር ወደ እኔ እየመጣ : (2 ጊዜ )
እፎይ የምልበት ሕይወቴ ጊዜ አጣ :Sad2 ጊዜ )

እህህ በማለት ዕድሜየን ልጨርሠው : (2 ጊዜ )
በዐይኔ እያየሁሽ ነው ሆዴን የሚብሠው :: (2 ጊዜ )

እህህ ማለትን ማንም አያውቀው : (2 ጊዜ )
ከልብ ውስጥ ገብቶ ካላጨነቀው :: (2 ጊዜ )

ሁልጊዜ ከላይ -ታች እኔ እምባዝነው : (2 ጊዜ )
የጎደለው ሞልቶ ይሆናል ብዬ ነው :: (2 ጊዜ )

ላላለልኝ ነገር አጉል ከመልፋቱ : (2 ጊዜ )
ይሻለኝ ይሆናል አንገቴን መድፋቱ :: (2 ጊዜ )

ጀማምራኝ ነበረ እንደመናፈቅ : (2 ጊዜ )
ፍቅር የማይገባት መሆኗን ሣላውቅ :: (2 ጊዜ )

በተልባ እየበላሁ ጮማ እየተመኘሁ :
በተልባ እየበላሁ ቅቤ እየተመኘሁ :
በሽታ ሆንሽብኝ ጤናም አላገኘሁ :: (2 ጊዜ )

ስትበይም አብይው :ስትጠጪ አጠጪው : (2 ጊዜ )
ልቤ ካንቺ ጋር ነው እንዳታስርቢው :: (3 ጊዜ )

ነይ ነይ ጎፈሬ :
ነይ ነይ ሹሩባ :
የብረት አልጋ ያረገርጋል :
የሰው ሆንሽና : ምን ይደረጋል (2 ጊዜ )

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jan 30, 2012 6:22 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የጥንት ሙዚቃ አፍቃሪዎች :--

ግርማ ነጋሽ ዘመኑን በማላስታውሰው ዓመት "ምነው ተለየሽኝ " የምትለዋን ድንቅ ዜማ ተጫውቷል :: ከድምፁ በማይተናነስ ፉጨቱ ለዚያን ዘመን ጎረምሶች የማይረሣ ትዝታ እንደሚኖረው እገምታለሁ ::

ግርማ ነጋሽ : ምነው ተለየሽኝ ::

ምነው ተለየሽኝ : መሥከረም ሣይጠባ :
እንቁጣጣሽ እያልን : ሣናጌጥ በአበባ ::
.....

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢጥቅ

ኮትኳች

Joined: 12 Sep 2009
Posts: 443

PostPosted: Thu Feb 16, 2012 5:14 pm    Post subject: Reply with quote

እስቲ እኔ ደግሞ ይሄን ዘፈን ላቅር ለድሮ ዘፈን ወዳጆ ምርጥ ዘፈን !!!
http://www.youtube.com/watch?v=tEQu5iEOzeY&feature=player_detailpage
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 16, 2012 8:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሙዚቃ አፍቃሪዎች :-

እሣቱ ተሰማ ድምጻቸው እየተሥረቀረቀ አድማጭን ከሚመስጡ የጥንት ድምጻውያን ውስጥ የሚመደብ ነው :: በተለይ ስለአገራችን ያዜማቸው ዜማዎች ከራስ ማንነት ጋር ተዋህደው ሁሌም ከኅሊና የማይጠፉ ናቸው ::

እሣቱ ተሰማ
ግሩም ናት ድንቅ ናት ለምለሟ ሀገሬ :
በጣም ደስ ይለኛል ከእርሷ መፈጠሬ ::

እሣቱ ተሰማ
አያ ማሩ እሸቴ :
ሸዋ ነው ቤቴ :
ማሚቴ ::

እሣቱ ተሰማ :
ድማማ : ድማማ : ድማሜ :
አንቺ ነሽ ሕመሜ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
MeronZG

አዲስ

Joined: 12 Nov 2011
Posts: 35
Location: Seattle

PostPosted: Fri Feb 17, 2012 3:30 am    Post subject: Reply with quote

ሩቅ ምስራቅ ያለች
ጃፓኖን ወድጄ
ትዝ ትለጘለች
በፍቅር ነድጄ

http://www.hubesha.com/audio.php?arid=81&abid=199&aid=2837

በጣም የምወደው ዘፈን የጥላሁን ነው
_________________
Ethiopian Music (7000+) http://www.hubesha.com/audio.php
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Feb 17, 2012 4:46 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የሙዚቃ አፍቃሪዎች :-

ዋርካ እንደገና ጽዳቷ መጠበቅ ስለጀመረ እስኪ ከድሮ ሙዚቃዎች ልጋብዛችሁ ::

ሙሉቀን መለሰ : እናቴ ስትወልደኝ ::

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::
ሣቅሁኝ በልጅነት : አለቀስሁ አድጌ :
የትላንቱ ለጋ : ዛሬ ግን ጠውልጌ ::

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::
በምጥ መጠበቧ እምዬ ስትወልደኝ :
ማስተማሯ ኖሯል ኖሮ እንደሚጨንቀኝ ::

አሃሃሃ .. ኦሆሆሆ ..

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::
ሣቅሁኝ በልጅነት : አለቀስሁ አድጌ :
የትላንቱ ለጋ : ዛሬ ግን ጠውልጌ ::
አልፎ ልጅነቴ : ጎፍላነቴን አይተው :
ጥረህ ግረህ ብላ : አሉኝ ተሠብሥበው ::
የለም ሕያውነት : ዘለዓለም መደሠት :
ከሞት ተከልሎ : እንዳማሩ መቅረት ::

እህህ ...

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::
ሣቅሁኝ በልጅነት : አለቀስሁ አድጌ :
የትላንቱ ለጋ : ዛሬ ግን ጠውልጌ ::
ዓለምን ለማዬት ትላንትና መጥቶ :
ዛሬ ሆኖ መሄድ በሣጥን ተከትቶ ::
የዓለም መሸ አዳሪ : ኃላፊ ሲነጋ :
ሣያውቀው ይሸኛል በተኛበት አልጋ ::

እህህ ...

እናቴ ስትወልደኝ :
መቼ አማከረችኝ :
የፊት ጉዴን ትታ : እደግ ማሞ አለችኝ ::
ሣቅሁኝ በልጅነት : አለቀስሁ አድጌ :
የትላንቱ ለጋ : ዛሬ ግን ጠውልጌ :: (4 ጊዜ )

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 397

PostPosted: Fri Feb 17, 2012 7:21 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ዱሮ የታወቀ የባህል ዘፋኝ የሚዘፍነው እረብ እረብ የሚያስደርግ ድል ያለ ዘፈን ነበር :: ስሙን አላውቀውም ...እንዲህ ይሄዳል

ጎበዜ ጎበዜ
አሆ
ጎበዜ
-------------

በምንሽር
እህም ነው
አርገው ሽርሽር
እህም ነው
በዲሞትፈር
እህም ነው
አርገው ፍርፍር .......እያለ ይሄዳል

ሰውየው በኦሮምኛ ሲዘፍንም ጥርት ያለ ኦሮሞ ይመስል ነበር :: ካሴቱ ነበረኝ ጠፋብኝ

በል አፈላልገህ ጠቁመኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Feb 17, 2012 9:21 pm    Post subject: Reply with quote

-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ ዱሮ የታወቀ የባህል ዘፋኝ የሚዘፍነው እረብ እረብ የሚያስደርግ ድል ያለ ዘፈን ነበር :: ስሙን አላውቀውም ...እንዲህ ይሄዳል

ጎበዜ ጎበዜ
አሆ
ጎበዜ
-------------

በምንሽር
እህም ነው
አርገው ሽርሽር
እህም ነው
በዲሞትፈር
እህም ነው
አርገው ፍርፍር .......እያለ ይሄዳል

ሰውየው በኦሮምኛ ሲዘፍንም ጥርት ያለ ኦሮሞ ይመስል ነበር :: ካሴቱ ነበረኝ ጠፋብኝ

በል አፈላልገህ ጠቁመኝ

ሰላም '-...-' :-

ጥያቄህ በትክክል ገብቶኝ ከሆነ ድምጻዊው 'ሟቹ አበበ ተሰማ ' ሣይሆን አይቀርም :: ከእርሱ ዜማዎች መካከል በአማርኛ የዘፈነውን 'የአብዮት ዘመን ማለዳ ማለዳ ' የሚለውን ዘፈን : የኦሮምኛ ዘፈኖች እንዲሁም ድሮ የተጫወተውን 'ወለሌ ' የሚለውን እንደገና ተከልሶ የዘፈናቸው እነሆ :-

ምንጮች :-
አበበ ተሰማ : ማለዳ : ማለዳ ::

አበበ ተሰማ : የኦሮምኛ ዘፈኖች ::

አበበ ተሰማ : ወለሌ : የአባይ ዳር ጉማሬ ::

ተድላ

_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 397

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 3:23 am    Post subject: Reply with quote

ልክ ነህ ተድላ እሱ ነው

ካልኩት ጎበዜ ጎበዜ ከሚለው ዘፈን ጋር ሀሪመሩመሩ ሸዋዬ ሀሪመሩመሩ .....የሚል ዘፈን በዛው ካሰት አብሮ ነበር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 10:39 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የቆዩ ሙዚቃዎች አፍቃሪዎች :-

ከመሐሙድ አህመድ የቆዩ ዜማዎች 1966 .. የተጫወተው "ዓለም ... ዓለም " በሚለው ተዝናኑ ::

መሐሙድ አህመድ : 1966 .. (... 1974)

ዓለም ... ዓለም
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ሥመ -ጠቅላላዋ : ዓለም መልከ -ብዙ :
ሁሉም ተሸከመሽ : ኑሮም ከእነ ጓዙ ::
ከወዲያ ከወዲህ : ስትመላለሺ :
ስንቱ - ብሎ : ስንቱ አዘነብሽ ::
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
.....
ዓለም ነጋዴ ነሽ : ሻጭ ነሽ ለሚገዛ :
ያውም ባለ ወረት : ሸቀጥሽ የበዛ ::
አንዱ ሲያመሠግን : አንዱ ሲጠላሽ :
ያዳላል እያሉ : ኑሮ ሚዛንሽ ::
ዓለምዬ ... ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
...........
..........
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ዓለም መንገደኛ : ነሽና ኃላፊ :
ታዲያ ምናለበት : ሰውን ባትገፊ ::
ሩጫሽ ወደፊት : ነወይ ወደላይ :
እስኪ ወደኋላም : ወደፊትም እይ ::
.....
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ሁሉጊዜ አትጠፊም : ከሰው አንደበት ::
ዓለም የሁሉም ነሽ : ወይንስ የጥቂት ::
ኧረ ማን ይኖራል : ዓለም ካንቺ ጋራ :
ሁሉም ዐይቶሽ ያልፋል : እንደ ሕልም እንጀራ ::
ዓለምዬ ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat May 26, 2012 5:31 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የቆዩ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች አፍቃሪዎች :-

ዛሬ የማቀርብላችሁ የሙዚቃ ምርጫ ሣይሆን የድምፃውያንን ሙዚቃ በሸክላ ቀርፆ ለአድማጮች በማቅረብ ሥራ ከኢትዮጵያውያን መካከል ቀዳሚ የሚባለውን የሙዚቃ አስተዋዋቂ ሰው ነው :: አምኃ እሸቴን በሥም ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ያውቁታል ? 'Amha Records' የሚለውን የሙዚቃ አሣታሚ መለያ ግን ድሮ ሙዚቃ በሸክላ ማጫዎቻ ያዳምጡ የነበሩት አይስቱትም :: እኔ ሙዚቃ ማዳመጥ የጀመርኩት በካሤት ዘመን ስለሆነ 'አምኃ የሙዚቃ አሣታሚ ' የሚባል አላስታውስም :- ባይሆን እነ 'አምባሠል ' : 'ማራቶን ' : 'ኤሌክትራ ' : 'ታንጎ ' የመሣሠሉትን አስታውሣለሁ :: አምኃ እሸቴ ከኒውዮርክ የሚለቀቀው 'Tadias' ድረ -ገፅ ጋር ያደረገው ቃለ -መጠይቅ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መቅረጽና ለገበያ ማቅረብ ሥራ እንዴት እያደገ እንደመጣ መጠነኛ ግንዛቤ ይሠጠናል ብዬ አስባለሁ : ተከታተሉት :-

ምንጭ :- Tadias Staff Reporter, Tadias, May 25, 2012. Amha Eshete & Contribution of Amha Records to Modern Ethiopian Music.

Quote:
New York (TADIAS) Five decades ago, when the Italian owner of the only record store in Addis Ababa could not keep up with growing local demand for more music variety, an Ethiopian music enthusiast named Amha Eshete opened his own shop. I ended up opening the first music shop owned by a native Ethiopian, diversified the import and started buying directly from New York, India, Kenya, and West Africa, Amha recalled in a recent interview with Tadias Magazine. But there was one very important ingredient missing I was selling foreign music labels, all kinds of music except Ethiopian records, which was absurd, he added.

Amha Eshete is the Founder of Amha Records the pioneering record company whose work from the golden era of Ethiopian music is now enshrined in the world-famous é thiopiques CD series.

There was a government decree that granted music publishing monopoly to the national association Hager Fikir Maheber, but they did not produce a single record of modern Ethiopian music. He continued: After many sleepless nights I was determined to take a risk of probable imprisonment and decided to ignore the decree to start producing modern Ethiopian music.

Referring to his first client on the Amha Records label Amha said, Alemayehu Eshete was willing to take that risk with me.

Amha describes the music scene in Ethiopia then as almost similar to that of today buzzing with the mixture of international sounds, Ethio-jazz, and traditional music. During the 1960s and 70s modern Ethiopian music was emerging at an incredible pace even though there was an extensive government control and censorship every step of the way, he said. It was the first time that new and modern night clubs were being opened, records players were being installed in cars, and enjoying music was the spirit of the time.

Professionally, Amha said he had no role models and that he learned through trial and error, often making business decisions based on just gut feeling.

I had no experience, for example, on how to negotiate with the artists, he said. I did what I thought was right and fair to me and all the others involved at the time. He added: It was a lifetime experience and believe you me it worked because I was able to produce one hundred and three 45s and a dozen LPs in a few years.

Amha leased the distribution rights of his originals to the French label Buda Musique in the 90s. My work is not owned by Buda Musique but it is definitely pressed and distributed under an exclusive license by them, he noted. The main credit should be given to Mr. Francis Falceto to bring about this re-birth of the golden age of Ethiopian music into reality in the form of the é thiopiques series. He continued: Mr. Francis was the one who was adamantly determined to reproduce this music and introduce it to the outside world. He should get all the credit because this music would have been buried and stayed buried somewhere in the suburbs of Athens, Greece where all the masters were stored until then.

For Amha, the most dramatic recent change in the Ethiopian music industry has been the size of compensation packages for singers. The Ethiopian superstar Tilahun Gessesse used to be paid about 200 birr per month, he said. I paid Alemayehu Eshete and Mahmoud Ahmed 2,000 birr for a single recording of an album. He added: This was all unheard of at the time, and in fact I can say it was the talk of the town.

Things have very much changed now, Amha noted. Payment of one million birr is no more a topic of conversation. The recent sales and revenue from Teddy Afros recording might gross millions of dollars. he added: This is definitely progress in the right direction and it is the beginning of good things to come.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Sat May 26, 2012 7:11 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የቆዩ ሙዚቃዎች አፍቃሪዎች :-

ከመሐሙድ አህመድ የቆዩ ዜማዎች 1966 .. የተጫወተው "ዓለም ... ዓለም " በሚለው ተዝናኑ ::

መሐሙድ አህመድ : 1966 .. (... 1974)

ዓለም ... ዓለም
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ሥመ -ጠቅላላዋ : ዓለም መልከ -ብዙ :
ሁሉም ተሸከመሽ : ኑሮም ከእነ ጓዙ ::
ከወዲያ ከወዲህ : ስትመላለሺ :
ስንቱ - ብሎ : ስንቱ አዘነብሽ ::
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
.....
ዓለም ነጋዴ ነሽ : ሻጭ ነሽ ለሚገዛ :
ያውም ባለ ወረት : ሸቀጥሽ የበዛ ::
አንዱ ሲያመሠግን : አንዱ ሲጠላሽ :
ያዳላል እያሉ : ኑሮ ሚዛንሽ ::
ዓለምዬ ... ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
...........
..........
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ዓለም መንገደኛ : ነሽና ኃላፊ :
ታዲያ ምናለበት : ሰውን ባትገፊ ::
ሩጫሽ ወደፊት : ነወይ ወደላይ :
እስኪ ወደኋላም : ወደፊትም እይ ::
.....
ዓለም : ዓለም : ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::
ሁሉጊዜ አትጠፊም : ከሰው አንደበት ::
ዓለም የሁሉም ነሽ : ወይንስ የጥቂት ::
ኧረ ማን ይኖራል : ዓለም ካንቺ ጋራ :
ሁሉም ዐይቶሽ ያልፋል : እንደ ሕልም እንጀራ ::
ዓለምዬ ምን ይመስልሻል :
ሰው ሁሉ ታዝቦሻል ::

ተድላ

መሀሙድ ማለት እልም ያለ አለቅላቂ ወያኔና ልክስክስ ሰው ነው :: ይሄንን ቆሻሻ ሰው ነው ብለህ እዚህ ማምጣትህ ገርሞኛል :: የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አንቅሮ ከተፋው ዘመናት አስቆጥረዋል :: ኢትዮጵያዊነት ሲመች የሚደርቡት ሲቸግር የሚጥሉት ካባ አይደለም :: ወያኔ የገባ ግዜ በሬዲዮ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት የተናገረውን ይልቅ አምጣና አሰማን ከሌለህ እኔ በካሴት ስላለኝ ገልብጨም ቢሆን እለጥፈዋለው ::
_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun May 27, 2012 12:41 am    Post subject: Reply with quote

የመረረው . እንደጻፈ(ች)ው:
መሀሙድ ማለት እልም ያለ አለቅላቂ ወያኔና ልክስክስ ሰው ነው :: ይሄንን ቆሻሻ ሰው ነው ብለህ እዚህ ማምጣትህ ገርሞኛል :: የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አንቅሮ ከተፋው ዘመናት አስቆጥረዋል :: ኢትዮጵያዊነት ሲመች የሚደርቡት ሲቸግር የሚጥሉት ካባ አይደለም :: ወያኔ የገባ ግዜ በሬዲዮ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት የተናገረውን ይልቅ አምጣና አሰማን ከሌለህ እኔ በካሴት ስላለኝ ገልብጨም ቢሆን እለጥፈዋለው ::

በመርሆህ እስማማለሁ :: ነገር ግን ከኢትዮጵያ አዝማሪዎች አሁን ለወያኔም ሆነ ለዚያ አረብ ያላፈነደደ አዝማሪ እስኪ ጥራልኝ ? ለመሆኑ ከእነሙሉ ስብዕናቸው : ክብራቸውን እንዳስጠበቁ የዘለቁ ኢትዮጵያውያን አዝማሪዎች በቁጥር ከእጃችን ጣቶች ይበልጣሉ ? እኔም ቢቸግረኝ እንጂ ማህሙድ አሁን ለዘቀጠበት ስብዕና ዋጋ ሰጥቼ አይደለም :: ባይሆን እኒያ የቆዩ የማህሙድ ዜማዎች አንድን የኢትዮጵያ ወርቃማ የሙዚቃ ዕድገት ዘመን ያስታውሱናል : አይመስልህም ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Sun May 27, 2012 11:27 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
የመረረው . እንደጻፈ(ች)ው:
መሀሙድ ማለት እልም ያለ አለቅላቂ ወያኔና ልክስክስ ሰው ነው :: ይሄንን ቆሻሻ ሰው ነው ብለህ እዚህ ማምጣትህ ገርሞኛል :: የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አንቅሮ ከተፋው ዘመናት አስቆጥረዋል :: ኢትዮጵያዊነት ሲመች የሚደርቡት ሲቸግር የሚጥሉት ካባ አይደለም :: ወያኔ የገባ ግዜ በሬዲዮ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት የተናገረውን ይልቅ አምጣና አሰማን ከሌለህ እኔ በካሴት ስላለኝ ገልብጨም ቢሆን እለጥፈዋለው ::

በመርሆህ እስማማለሁ :: ነገር ግን ከኢትዮጵያ አዝማሪዎች አሁን ለወያኔም ሆነ ለዚያ አረብ ያላፈነደደ አዝማሪ እስኪ ጥራልኝ ? ለመሆኑ ከእነሙሉ ስብዕናቸው : ክብራቸውን እንዳስጠበቁ የዘለቁ ኢትዮጵያውያን አዝማሪዎች በቁጥር ከእጃችን ጣቶች ይበልጣሉ ? እኔም ቢቸግረኝ እንጂ ማህሙድ አሁን ለዘቀጠበት ስብዕና ዋጋ ሰጥቼ አይደለም :: ባይሆን እኒያ የቆዩ የማህሙድ ዜማዎች አንድን የኢትዮጵያ ወርቃማ የሙዚቃ ዕድገት ዘመን ያስታውሱናል : አይመስልህም ?

ተድላ

እሱስ እውነትህን ነው የዚህ ሰውዬ ለየት የሚያደርገው ግን የገቡ ሰሞን ህፃናትና ሴቶች ጨለንቆ ገደል ውስጥ እየታረዱ በሚጣሉበት ወቅት እናንተ ጀግኖች ምናምን እያለ ሲያሞጋግሳቸው ነበር :: ጭቁኑን የደሃ ልጅ እንጂ ወራሪ አሸንፈው የመጡ ይመስል :: ለምሳሌ ጥልዬ ምንም እንኩዋን ከሼሁ ድጎማ ቢደረግለትም ይሄንን ያህል አልዘገጠም :: ኢትዮጵያዊነቱ ክብሩን አልረሳም :: መሀሙድ ግን ፍየል ከመድረሷ እንዲሉ ካድሬ አግብቶ ደንበኛ ወያኔ ሆኖ ነበር ::

ለሙዚቃው እድገት ብዙ አስተዋፆ አድርጔል እኔ ይሄንን አልክድም ይሁን እንጂ እንድጠላው ያደረገኝ ዋናው ምክንያት ቢኖር ኢትዮጵያ በምጥ ተይዛ ልጆቿ ሲያለቅሱ እሱ ከጠላታችን ጋር አብሮ በኛ ስቃይ ማላገጡ ነበር ::

http://www.youtube.com/watch?v=_fEKDvBRql8
_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed May 30, 2012 7:58 pm    Post subject: Reply with quote

ዜና ዕረፍት

ታዋቂው የባሕል ሙዚቃ ተጫዋችና ድምፃዊ ቻላቸው አሸናፊ በተወለደ 47 ዓመቱ አረፈ ::

ዜናውን ያገኘሁት ከሚከተለው ድረ -ገፅ ነው ::

ምንጭ :- Bawza Staff, Tuesday May 29, 2012. ኢትዮጵያዊው የባህል ዘፋኝ ቻላቸው አሸናፊ በተወለደ 47 ዓመቱ አረፈ ::

በጥረቱ ከፍተኛ የኪነት ሰው መሆን የቻለው ቻላቸው አሸናፊ ገና ብዙ በሚሠራበት ዘመን ማረፉ ያሣዝናል :: እግዚአብሔር ነፍሱን ይቀበላት : ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ይሥጣቸው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... , 11, 12, 13  Next
Page 12 of 13

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia