|
|
|
| View previous topic :: View next topic |
| Author |
Message |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sat Dec 19, 2009 6:58 pm Post subject: እምዬ ምኒልክ |
|
|
በዚህ አምድ የጥቁር ህዝቦች ባለውለታና የኢትዩጵያ አባት የእምዬ ምኒልክ ታሪክ ይዘከራል :: የሚከፋው ይክፋው : ደስ የሚለውም ደስ ይበለው : የሚያስነፀውም ያስነጥሰው (ቀድመን ግን ይማርዎት ብለናል )::
"ወደ ጋላ አገር ከመሄድና ወደ አጼ ቴዎድሮስ ከመግባት ማናቸውን ይመርጣሉ " ብለው ሲጠይቁዋቸው ወደ ጋላ አገር ይዛችሁኝ ብትሸሹ ይሻለኛል ብለው ተናገሩ "
ከመቅደላ ማምለጥ
ምኒልክ ከመቅደላ የወጡበትን ዘመን አንዳንዶች 1858 አ .ም . ሲያደርጉት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ግን 1857 አ .ም . ነው ይላሉ ::
ሰኔ 24 ቀን መቅደላ ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ ነበር :: የመቅደላን በር የሚጠብቁ ዘበኞች ከዝናቡ ለመሸሽ ወደየጎጇቸው ገቡ :: ዘቦቹ በየጎጇቸው ውስጥ ተጠልለው ሳለ አንድ አንበሳ ከዱር ውስጥ መጣባቸው :: ወታደሮቹም አንበሳውን አይተው ሲጫጫሁና ሲተራመሱ አንበሳው ወደዱር ሄደ :: ወታደሮቹም በፈረስ እየሆኑ አንበሳውን ተከትለው ሄዱ :: ወታደሮቹ አንበሳውን ተከታትለው ፈልገው አጥተው ወደሰፈራቸው ሲመለሱ ቆቂት በር ክፍት ሆኖ አገኙት ::
በዚያ አንበሳ ግርግር መሀል ቆቂት በርን ማን እንደከፈተው አልታወቀም :: ቆቂት በር የተከፈተው ምኒልክ ከሀያ ተከታዩቻቸው ጋር ሲያመልጡ ነበር :: ምኒልክን ያስመለጡ የሸዋ ሰዎች ባቀዱት ፕላን መሰረት አብዛኛው ምኒልክን ይዞ ሲሄድ : ጥቂት ሰዎች ወደ ሌላ አቅጣጫ ተልከው በዚያም ምኒልክ ባልሄዱበት በሌላ አቅጣጫ በኩል ብዙ ጥይት ተኩሰው ተመልሰው ከምኒልክ ጋር ተገናኝተው ጉዟቸውን ቀጠሉ ::
ይሄም ታሪክ ይቀጥላል  _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
እዮባ

Joined: 20 Jun 2009 Posts: 670 Location: In the state of peace
|
Posted: Sat Dec 19, 2009 7:18 pm Post subject: |
|
|
በአሁኑ ሰአት የኛ ትልቁ መርህ ኢትዮጵያን ለዘመኑ ኢትዮጵያውያን ልቀቁልን የሚል ነው :: የድሮዎቹ መሪዎች ቢሞቱም መንፈሳቸው ግን እስካሁን እየገዛን ይገኛል ::
አዲሲቷ ኢትዮጵያ እንደ ውሀና ዘይት ሳይሆን እንደ ማክያቶ ደባልቀን በአዲሱ ትውልድ የምትመራ ተወዳጅ አገር እንድትሆን እንዲሁም ያለፉትን ስራቶች ለታሪክ ትተን ከፖለቲካችን አውጥተን እንድንኖር ነው :: _________________ A+T ርኛ
MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC. |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sat Dec 19, 2009 7:42 pm Post subject: |
|
|
ታሪክና ፓለቲካ ወንድማማቾች ናቸው ይላል ትንሹ ወቸውጉድ :: እንዲያውም መንታዎች ናቸው :
ዛሬ ለኢትዩጵያውያን የአጼ ምኒልክን ታሪክ ደግመን ደጋግመን መናገር አለብን :: የሳቸው የፓለቲካ ስልትም ሆነ ለሀገር እድገት የሰሩት ታላላቅ ስራዎች : ለዛሬው ትውልድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል :: ከበፊት ጀምሮ አምባገነን በመሆን ህዝብ ሲጨፈጭፉ የነበሩትንም መሪዎች ማንነት ለኢትዩጵያውያን የማሳወቅ ግዴታ አለብን :: ጥሩውንም መጥፎውንም በመናገር ህዝባችንን መማር ያለበትን ነገር ማስተማር ግድ ነው ::
ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
ሞንዶን ስለደብዳቤዎቹ ሲጽፍ ".....አንዳንዶቹም መልስ እንዲጻፍላቸውና በፓስታ ቤት የኢትዩጵያ ቴምብር ተለጥፎ እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ነበሩ :: ምክንያቱም ቴምብሩ ላይ የምኒልክን መልክ ለማየት እያሉ ነው :: ከአውስትራሊያና ከቤኑዜላ የተጻፉት ደግሞ የእርስዎ ወታደሮች መሆን እንፈልጋለን የሚሉ ናቸው ....."
"የአድዋው ጦርነት ኢትዩጵያን በዘመናዊው የአለም ካርታ ውስጥ ስሟን አስገባት ::" ማርጀሪ ፐርሀም
ይቀጥላል  _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
እዮባ

Joined: 20 Jun 2009 Posts: 670 Location: In the state of peace
|
Posted: Sat Dec 19, 2009 8:14 pm Post subject: |
|
|
"Change in all things is sweet. " ይላል እውቁ ፈላስፋ አርስቶትል ::
ያንተ አንዱ ትልቁ ችግርህ ሚኒሊክን የወደድካቸው ዘረኛ ስለሆንክ ነው :: የትግራይ ወይም የኤርትራ እንዲሁም የደቡብ ተወላጅ ብትሆን ኖሮ አትወዳቸውም ነበር :: ይህ ደሞ Logical fact ነው :: በጣም የሚያሳዝነው ደሞ ይህንን ከወደፊቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካና ራዕይ ጋር ልታስተሳስረው ትፈልጋለህ :: ሚኒሊክ በአድዋ ጦርነት ጊዜ ከትግራይ ቦርደር ተመልሷል ይህንንም ያደረገው ኤርትራን እንደአገሩ ስላልቆጠራት ነበር :: ሌላው ችግርህ ደግሞ ሚኒሊክን ምን በጊዜው እንኳን ማን እንደነበረ ሳታውቀው ማምለክህ ነው ይህ ደግሞ የልጅ ልጆችህ ስለ መንግስቱ ውስጣዊ ጥልቅ ማንነት እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ እንደማየት ያክል ያስቃል :: ""Everyone should be respected as an individual but not idiolized"" ይላል ሌላው እውቁ ፈላስፋ አልበርት አይነስታይን ::
ፖለቲካና ታሪክ መንትዮች የሚሆኑት እንደ ፖለቲካ አራማጁ የህሊና ክብደትና ቅለት ነው :: ጥሩ አስተሳሰብ ያለው ሀቀኛ ፖለቲከኛ በታሪክ ጥሩ ስራ ሰርተው ያለፉትን ትቀብሎ ከፖለቲካው ጎን ያራምዳል :: ዘረኛ የሆነና ስለሌላው የማይጨነቅ እንደ አክሱም ሀውልት ከአንድ ጥርብ ድንጋይ ብቻ ተፈልፍሎ የተሰራ ደግሞ ልክ የራሱን መሰል ባለ ታሪክ ሰው የሰራውን ስራ ይከተላል ::
ወደ አገራችን ፖለቲካ ስንመጣ ሚኒሊክ ለሸዋ ህዝብ ጥሩ አድርጎ ለትግራይና ለጎንደር መጥፎ ሰርቶ አልፎ ሊሆን ይችላል :: ስለዚህም ወቅታዊውን ፖለቲካ ከታሪክ ጋር ስናቆራኝ ትልቅ መከፋፈልን ያመጣል ምክንያቱም ግማሹ ሚኒሊክን ያመልካል ግማሹ ደግሞ አጥብቆ ይጠላል  _________________ A+T ርኛ
MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC. |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ባክቡክ

Joined: 20 Nov 2009 Posts: 326
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 1:04 am Post subject: |
|
|
ወቸጉድ - በዚህ ባቀረብከው አስተያየት ላይ እንደምረዳው ምን ያክል የወያኔወቹን የፖለቲካ ስርአት አራማጅ እና አቀንቃኝ መሆንህን ነው :  _________________ why html is off ? |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ጨምጫሚ

Joined: 20 Sep 2009 Posts: 950
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 1:27 am Post subject: |
|
|
| ጋላ አገር ?.... በል በል ስነስርአት ኦሮሚያ ነው ሚባለው :: |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 4:13 am Post subject: |
|
|
| ጨምጫሚ እንደጻፈ(ች)ው: | | ጋላ አገር ?.... በል በል ስነስርአት ኦሮሚያ ነው ሚባለው :: | ሰላም ጨምጫሚ ! እኔ የጻፍኩት ከመጽሀፉ ቃል በቃል ወስጄ ነው እንጂ የኦሮሞን ህዝብ አገር የጋላ አገር ለማለት አይደለም :: ጋላም ተባለ ኦሮሞ ብዙሀኑ የኢትዩጵያ ህዝብ የኦሮሞ ዘር እንዳለበት ደግሞ የ DNA ምርመራ አያስፈልገውም ::
ትንሹ ወቸውጉድ ዘብሄረ ሰላሌ _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 4:29 am Post subject: |
|
|
| ባክቡክ እንደጻፈ(ች)ው: | ወቸጉድ - በዚህ ባቀረብከው አስተያየት ላይ እንደምረዳው ምን ያክል የወያኔወቹን የፖለቲካ ስርአት አራማጅ እና አቀንቃኝ መሆንህን ነው :  | ሰላም ባክቡክ ! እስቲ ንገረኝ የወያኔ ፓለቲካ አቀንቃኝ መሆኔን የሚያሳየው የቱ ነው ? ወይስ የታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን መጻፌ ነውር ነው ? እኔ የማደንቃቸው መሪዎች አጼ ምኒልክና አጼ ሀይለስላሴ ናቸው :: ስለእነርሱ የታሪክ ባለሙያዎች የጻፉትን መጻፌ ደግሞ ምንም ከዘረኝነት ጋርም ሆነ ከወያኔነት ጋር አይገናኝም ::
| እዩባ እንደጻፈ(ች)ው: | | ያንተ አንዱ ትልቁ ችግርህ ሚኒሊክን የወደድካቸው ዘረኛ ስለሆንክ ነው | እረ በእናትህ የማይሆን ነገር አትናገር :: አጼ ምኒልክን መውደድ ከዘረኝነት ጋር ምን ያገናኘዋል ? ንጉሱ የሰሩትን ታሪክ አንብቤ : ለሀገራቸው ያደረጉትን ታላላቅ ስራዎች በአይኔ አይቼ ነው የወደድኳቸው :: እሳቸው የሰሩት ታላቅ ድልና ለሀገራቸው ያደረጉት ስራዎች እኮ ዛሬም በኢትዩጵያ ምድርና በአለም ታሪክ ህያው ናቸው :: ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የምናያቸው ብዙዎቹ ነገሮች እኮ የእምዬ ምኒልክ ውጤቶች ናቸው :: ዘረኝነቴን በትክክል ንገረኝና መታረም ካለብኝ ልታረም :: ምናልባት ሳላውቀው ዘረኛ ሆኜ ከሆነ ማለት ነው :: ዘረኝነትን ግን አልደግፍም ::
| Quote: | | የትግራይ ወይም የኤርትራ እንዲሁም የደቡብ ተወላጅ ብትሆን ኖሮ አትወዳቸውም ነበር | የትግራይ ተወላጅ ስትል ተኩላ ሀጎስን ማለትህ ነው ? ወይስ ገብረኪዳን ደስታን ? እውር እውርን ቢመራው ተያይዞ ገደል ይባላል :: ኢትዩጵያዊነቱን የሚወድና ከሀዲ ያልሆነ የትግራይ ተወላጅ ግን እምዬ ምኒልክን አይጠላም :: እንዲያውም ይወዳቸዋል :: የኤርትራ ተወላጅ ላልከው እንኳ ነው መልሴ :: በመጀመሪያ ኤርትራውያን ማንን ይወዳሉ ብለህ ነው ? ሙሉ ትግራይንና ብዙውን ኢትዩጵያዊ ይጠላሉ :: በፊትም ለጣሊያኖች ተቀጥረው ኢትዩጵያን የወጉ ነበሩ :: ባንድስታሮች ናቸው የደቡቡን ግን ተወው :: ያይጥ ምስክር ድንቢጥ ይባላልና ::
| Quote: | | ሚኒሊክ በአድዋ ጦርነት ጊዜ ከትግራይ ቦርደር ተመልሷል ይህንንም ያደረገው ኤርትራን እንደአገሩ ስላልቆጠራት ነበር | የዚህን ምክንያት ከዚህ በፊት የታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን ጠቅሼ ተናግሬአለሁ :: የሚገርመው ግን ኤርትራውያን አሁንም ኢትዩጵያዊ አይደለንም ብለው ማመናቸው ነው :: አሁን በዘመናችን የካዱንን ላለፈው ግዜ ልንከራከርላቸው ስንጥር ማየት ራሱ ያሳፍራል :: እነርሱ ለጣሊያን ተቀጥረው ሳይቀር ወግተውናል ::
| Quote: | | ወደ አገራችን ፖለቲካ ስንመጣ ሚኒሊክ ለሸዋ ህዝብ ጥሩ አድርጎ ለትግራይና ለጎንደር መጥፎ ሰርቶ አልፎ ሊሆን ይችላል :: | ምኒልክ ለትግራይና ለጎንደር ምንም መጥፎ ነገር አልሰራም :: በጣሊያን ከመገዛት እነርሱንም ይሁን ሌላውን ኢትዩጵያዊ ያዳነ የጥቁር ህዝቦች ባለውለታቸው ነው ::
FYI እኔ ሰው አላመልክም :: የማመልከው አንድና አንድ ነው እሱም የሰማይና የምድሩን ፈጣሪ :: ሰውን እወዳለሁ : የማደንቀውን አደንቃለሁ :: _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ባክቡክ

Joined: 20 Nov 2009 Posts: 326
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 2:51 pm Post subject: |
|
|
ወቸውጉድ : እንደምታውቀው ወያኔወቹ በጠመንጃ አፈሙዝ ሀገራችንን መግዛት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ድረስ የሚያራምዱት የፖለቲካ ስርእት በታትነህ ወይም አፋጅተህ ግዛው በመሆኑ አንዱን ብሄረሰብ ከሌላው ይህ የሀገር መሪ ወይም ንጉስ እንዲህ ብሎሀል ይሄን ስም ሰጥቶሀል አዋርዶሀል ንቆሀል በሚል ሽፋን የብዙ ወገኖች ህይወት እንዳለፈ ግልጽ ነው ከዚያ አኩአያ ነው ምንም እምዬ ምኒሊክ ለሀገራችን ካጠፉት ይልቅ ያለሙት ቢበልጥም በአሁኑ ሰአት እርሳቸው ያደረጉአቸውን ደካማ ጎኖች መጠቆሙ በይበልጥ የዚህ ታሪክ ተጠቃሚ የሚሆኑት ወያኔወች ናቸው ብዬ ስለማስብ ነው እንጂ አንተን በእንደዚህ መልኩ ልተች የቻልኩት ካስቀየምኩ ይቅርታ እጠይቃለሁ ! _________________ why html is off ? |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
እዮባ

Joined: 20 Jun 2009 Posts: 670 Location: In the state of peace
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 4:53 pm Post subject: |
|
|
| ወቸውጉድ እንደጻፈ(ች)ው: |
እረ በእናትህ የማይሆን ነገር አትናገር :: አጼ ምኒልክን መውደድ ከዘረኝነት ጋር ምን ያገናኘዋል ? ንጉሱ የሰሩትን ታሪክ አንብቤ : ለሀገራቸው ያደረጉትን ታላላቅ ስራዎች በአይኔ አይቼ ነው የወደድኳቸው :: እሳቸው የሰሩት ታላቅ ድልና ለሀገራቸው ያደረጉት ስራዎች እኮ ዛሬም በኢትዩጵያ ምድርና በአለም ታሪክ ህያው ናቸው :: ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የምናያቸው ብዙዎቹ ነገሮች እኮ የእምዬ ምኒልክ ውጤቶች ናቸው :: ዘረኝነቴን በትክክል ንገረኝና መታረም ካለብኝ ልታረም :: ምናልባት ሳላውቀው ዘረኛ ሆኜ ከሆነ ማለት ነው :: ዘረኝነትን ግን አልደግፍም ::
|
ያኔ ያቀረብከው ምክንያት ""ወታደሮች ስለተዳከሙ ...ሰለከሱ ....
ተመልሰን እንመጣለን ብለው አጼ ሚኒሊክ ተመለሱ "" የሚል ምናምን ነበር :: ታድያ አመታት ሙሉ ጣልያን ኤርትራን ሲገዛ ለምን ተመልሰው ሄደው አልወጉትም ነበር ? ወታደሩን በነበረው ቁጥር ለመተካት እኮ ከ 2 አመት በላይ አያስፈልግም ነበር :: ይቅርታ አርግልኝና ባለፈው ያቀረብከው ምክንያት ምንም ስሜት የማይሰጥ ሆኖ በማግኘቴ ትንሽ ስቄ ነበር :: የሚገርመው እኮ ደግሞ ኤርትራን አሳልፈው ከመስጠታቸው በላይ የውጫሌው ጣልያን ኤርትራን በህጋዊ መልክ በደንብ አርጎ እንዲገዛ የሚፈቅደው ስምምነት ላይ መፈረማቸው ነው :: እስኪ ለዚህ ምክንያቱን ስጤኝ ?? ሌላው ደግሞ ዘረኝነትህን የነገርኩህ ከዚህ በፊት የጻፍካቸውን ጽሁፎች በተለይም ስለ አጼ ቴዎድሮስ እና ስለ ጎንደር ህዝብ እንዲሁም ስለ ደቡብ መጥፎነት ይጻፍካቸው ያለህን ጥላቻ ያመለክታል :: እኔ ቁርጡን ንገረኝ ካልክ ደግሞ ኤርትራውያን ኢትዮጵያን ስለካዱ አልፈርድባቸውም ትክክል ነው ያደረጉት አሰብን ይዘው መሄዳቸው ብቻ ነው የቆጨኝ :: አሁን የምናያቸው አዲስ አበባ ውስጥ ያሉት ስልጣኔዎች በሚኒሊክ ጊዜ ነው የመጡት አልክ
መቼስ ምንም አይነት ጥላቻ ስለሌለኝ አዲስ አበባ ውስጥ በአይን የሚታየውነና የማይካዱትን ጥቂት ዘመናዊ ነገሮች አስገብተዋል ስለዚህም ሚኒሊክን አመሰግናቸዋለው :: _________________ A+T ርኛ
MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC. |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 6:34 pm Post subject: |
|
|
[quote="ባክቡክ "]ሰላም ባክቡክ ! ስለቀናው ምላሽህ አመሰግናለሁ :: እኛን ሊያፋጁን የተነሱት እኮ ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ : ኢትዩጵያን አንፈልግም : ነጻ መሆን እንፈልጋለን : ተውን ብለው የሄዱት ኤሪዎችም ጭምር ናቸው :: የስሙኒሎሚና የመሳሰሉት እዚህ ሲደነፉ የሚውሉት እኮ ለዚህ ርካሽ ስራቸው ነው :: መቼስ ግብረገብ የማያቅን ህብረተሰብ ግብረገብ ከማስተማር ሌላ ምን ታደርገዋለህ ? የደም ጉዳይ ይሆን ?
| እዮባ እንደጻፈ(ች)ው: | ያኔ ያቀረብከው ምክንያት ""ወታደሮች ስለተዳከሙ ...ሰለከሱ ....
ተመልሰን እንመጣለን ብለው አጼ ሚኒሊክ ተመለሱ "" የሚል ምናምን ነበር :: | እኔ ሳልሆን ያልኩት ራሳቸው ጀግናው ምኒልክ ያሉትን : የታሪክ ጸሀፊዎች የጻፉትን ነው ያቀረብኩት ::
| Quote: | | ታድያ አመታት ሙሉ ጣልያን ኤርትራን ሲገዛ ለምን ተመልሰው ሄደው አልወጉትም ነበር ? ወታደሩን በነበረው ቁጥር ለመተካት እኮ ከ 2 አመት በላይ አያስፈልግም ነበር :: | ኤርትራውያኖች እንደልማዳቸው ባንዳነታቸውን ቀጠሉ :: እምዬ ምኒልክም አገራቸውን መገንባቱን ተያያዙት :: ህዝባቸውን ከረሀብ ; ከመሀይምነት ...ወደ ስልጣኔ ለማሸጋገር ደፋ ቀና አሉ :: በጣም የሚገርመው ያንተ እንዲህ ለኤርትራውያን መከራከርህ : አንተ ራስህ ኤርትራዊ መሆንህን ፍንትው አድርጎ ያሳያል :: በተለይም በአሁኑ ሰአት ስለኤርትራ ጉዳይ የሚሰጠው ኢትዩጵያዊ የለም :: ለትግራይ ህዝብ ያላቸውን ጥላቻ በሌላው ኢትዩጵያዊ መሀል ሊያስፋፉ የሚጥሩ ዘባተሎዎች ናቸው :: ለኢትዩጵያ ውድቀት ቀን ከሌት ደፋ ቀና የሚሉ : ስልጣኔን ሳይሆን ምቀኝነትንና ተንኮልን : የተሞሉ : ናቸው :: Shewa.org በሚለው ዌብሳይታቸውም ይህንን ለትግራይ ህዝብ ያላቸውን ጥላቻ ሲለቀልቁ የሚውሉ : ስራን ሳይሆን ወሬን ተግባር ያደረጉ ናቸው ::
| Quote: | | ይቅርታ አርግልኝና ባለፈው ያቀረብከው ምክንያት ምንም ስሜት የማይሰጥ ሆኖ በማግኘቴ ትንሽ ስቄ ነበር :: | መሳቅ ጥሩ ነው : እድሜ ያረዝማል :: እስቲ እኔም ልሳቅ እድሜዬም ለማርዘም
| Quote: | | የሚገርመው እኮ ደግሞ ኤርትራን አሳልፈው ከመስጠታቸው በላይ የውጫሌው ጣልያን ኤርትራን በህጋዊ መልክ በደንብ አርጎ እንዲገዛ የሚፈቅደው ስምምነት ላይ መፈረማቸው ነው :: | እሳቸው ከመፈረማቸው በፊት እኮ ኤሪዎች ለጣሊያን ተንበርክከው : ግዛኝ እርገጠኝ : ለጣሊያን ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ሳይቀር ብለዋል ስንት ኤርትራዊ ነበር ኢትዩጵያን የወጋው ? ባንዳ ሁሌም ባንዳ ነው ::
| Quote: | | ሌላው ደግሞ ዘረኝነትህን የነገርኩህ ከዚህ በፊት የጻፍካቸውን ጽሁፎች በተለይም ስለ አጼ ቴዎድሮስ እና ስለ ጎንደር ህዝብ እንዲሁም ስለ ደቡብ መጥፎነት ይጻፍካቸው ያለህን ጥላቻ ያመለክታል :: | አንድ ቦታ ስለጎንደርና ስለደቡብ መጥፎነት የጻፍኩትን አሳየኝ ? ስለ አጼ ቴዎድሮስ የጻፍኩትን : አሁንም እጽፋለሁ :: አሁንም ቢሆን አጼ ቴዎድሮስ ጀግና አልነበሩም :: ያጠፋውንም ያላጠፋውንም : እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ ሲገሉና ሲቆርጡ የነበሩ አምባገነን ናቸው :: ይሄ እኮ የህሊና ጉዳይ ነው :: እስቲ የትኛው ህሊና ነው : ምንም የማያውቁ ህጻናትን በእሳት የሚያቃጥል : ገበሬውን : የቤ /ክ መሪዎችን : ሽማግሌዎችን ; አሮጊቶችን ....እጅ መቁረጥ ; በእሳት ማጋየት ; ገደል መጨመር : ይሄ ጤነኝነት ነው ብዬ ፈጽሞ አላስብም :: የፈለገ ሰው ለምን የፈለገውን አይልም : አጼ ቴዎድሮስ ለእኔ ጀግና ሳይሆኑ : የአእምሮ በሽተኛ ናቸው :: እውነታውም ያ ነው ::
| Quote: | | እኔ ቁርጡን ንገረኝ ካልክ ደግሞ ኤርትራውያን ኢትዮጵያን ስለካዱ አልፈርድባቸውም ትክክል ነው ያደረጉት አሰብን ይዘው መሄዳቸው ብቻ ነው የቆጨኝ :: | ለምን ሲከዱ አይከርሙም :: እኛ እኮ አሁን የምንለው አትምጡብን አንመጣባችሁም ነው :: ችጋር መከራውን ሲያበላው ይሄው በየኢትዩጵያ ዌብሳይቶች ውስጥ : እንደ ጉንዳን የሚርመሰመሱት እነሱ መስለውኝ :: እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ ነገር : ማንም ኢትዩጵያዊ ኤርትራውያንን አይፈልግም ካሁን በኅላ :: ይቅናችሁ ብለናል ::
| Quote: | አሁን የምናያቸው አዲስ አበባ ውስጥ ያሉት ስልጣኔዎች በሚኒሊክ ጊዜ ነው የመጡት አልክ | አዎ :: ገና እዚህ እያንዳንዱን ነገር እጽፋለሁ ::
| Quote: | | መቼስ ምንም አይነት ጥላቻ ስለሌለኝ | አንተ ነህ ለአድዋው ጀግና ለእምዬ ምኒልክ ጥላቻ የሌለህ ?
| Quote: | | አዲስ አበባ ውስጥ በአይን የሚታየውነና የማይካዱትን ጥቂት ዘመናዊ ነገሮች አስገብተዋል ስለዚህም ሚኒሊክን አመሰግናቸዋለው :: | ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
"ምኒልክ ዘመናዊ ኢትዩጵያን የመሰረተ ሰው ነው "
የእምዬ ምኒልክን ሰአት .......
http://www.eastafricaforum.net/2009/11/22/ethiopia-emperor-meneliks-watch-sold-for-52000-at-geneva-auction/comment-page-1/
http://nazret.com/blog/index.php?title=ethiopia_emperor_menelik_s_watch_sold_fo&more=1&c=1&tb=1&pb=1
ይቀጥላል  _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 8:35 pm Post subject: |
|
|
የኢትዩጵያ እድገት
አጼ ምኒልክ ከነገሱ በኅላ .....መሳፍንቱንም ሆነ ባላባቱን በወዳጅነትና በፍቅር ስለተቃረቡት አብዛኛው ያለምንም ደም መፋሰስ ሲገብርላቸው እምቢ ያለውንም በጦር ሀይል እያስገበሩ : የወጋቸውን መልሰው ስለሚሾሙ ፍቅር በዝቶ ከተበታተነችው ኢትዩጵያ ዛሬ ያለንባትን ኢትዩጵያን መሰረቱ ::
ዳግማዊ አጼ ምኒልክ እጅግ በጣም ስራ ወዳድ ሰው ነበሩ :: ስራ ወዳድ በመሆናቸውም ብዙው የስልጣኔ ስራ ወደ አገራችን የገባው በምኒልክ ዘመነ መንግስት ነው :: አጼ ምኒልክ በዘመናቸው በኤሮፓ የነበረ የስልጣኔ ስራ ሁሉ ወደ ኢትዩጵያ እንዲገባ አድርገዋል :: ማስገባት ብቻ ሳይሆንም ሌሎችን ለማበረታታት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገባውን አዲስ ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰሩት ወይም የሚጠቀሙት ምኒልክ ራሳቸው ነበሩ ::
በኢትዩጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጀመሪያዋን አውቶሞቢል የነዱ ምኒልክ ናቸው :: በኢትዩጵያ ሾፌሮች ታሪክ ውስጥ ፐርፌክት ድራይቨር የሚለውን የመጀመሪያውን የመንጃ ፈቃድ የተቀበሉ ምኒልክ ናቸው :: በመኪና የሚፈጨውን እህል የሚፈጨው ጋኔን ነው ተብሎ ይታመን በነበረበት ጊዜ ጋኔን ያለመሆኑን ለማሳወቅ የመጀመሪያውና የመጨረሻውም ኢትዩጵያዊ ዱቄት አስፈጭ ንጉስ ምኒልክ ናቸው :: የመጀመሪያውን ስልክ አስገብተው ጋኔኑ ከዙፋኑ አጠገብ ይውጣ ብለው የዘመኑ ጳጳስ ጭምር ከባድ ተቃውሞ ቢያነሱባቸው ታግለው ስልክን የመሰረቱ ምኒልክ ናቸው :: የመጀመሪያዋን ብስክሌት መንዳት ተምረው የነዱ ምኒልክ ናቸው :: ጣይቱን ብስክሌት መንዳት አስተምረው ሴቶች ከመሸፋፈንና ከማፈር እንዲወጡ የታገሉ ምኒልክ ናቸው :: ሆቴል መብላት ነውር ያለመሆኑን ለማስተማር በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ሆቴል ከፍተው ሚስታቸውን ጣይቱን ወጥቤት አድርገው በገንዘባቸው መኳንንት እየጋበዙ ሆቴል መብላትን ያስተማሩ ምኒልክ ናቸው :: የዛሬውን የኢትዩጵያ ሰንደቅ አላማ በ 1881 አ .ም . በአዋጅ አረንጎዴ ; ቢጫ ; ቀይ እንዲሆን ያደረጉ ምኒልክ ናቸው ::
http://www.africa.upenn.edu/Flags_GIFS/Ethiopia_Flag_11176.gif
የተለያዩ አበቦችና ጽጌረዳዎችን ከአውሮፓ እያስመጡ እስካሁን የምንጠቀምባቸውን ልዩ አበቦች ያራቡ ምኒልክ ናቸው :: የኮክ : የእንጆሪ : የወይን እና የመሳሰሉትን የአትክልት ልዩ ዘሮች እያስመጡ ያራቡ ምኒልክ ናቸው :: እስከዛሬ ለኢትዩጵያ ትልቅ ጥቅም የሚሰጠውን ባህር ዛፍን አስመጥተው የተከሉና ያባዙ ምኒልክ ናቸው ::
በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የውጭ አገር ትምህርት ቤት የከፈቱ : የመጀመሪያውን የሙዚቃ ትምህርት ቤት ያቋቋሙ ምኒልክ ናቸው :: ኤሌክትሪክና ባቡር ያስገቡ : ዘመናዊ የመንገድ ስራ ያስጀመሩ : ፓስታ ድርጅትን ያቋቋሙ ምኒልክ ናቸው :: ሰው ሲባል እኩል ነውና ማንም ሰው ሰውን ባሪያ እንዳይል ብለው የባሪያን ነጻነት ያወጁና ሰው እንደከብት እንዳይሸጥ የታገሉ ምኒልክ ናቸው :: ሴት ልጅ በወላጆቿ ምርጫ ሳይሆን በፈቃድዋ የመረጠችውን ባል እንድታገባ ያወጁና ለሴት ልጆች ነጻነት የታገሉ ምኒልክ ናቸው :: ሰራተኛ በስራው እንዳይበደል አዋጅ ያስነገሩ : ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ አስገዳጅ ህግ ያወጡ ምኒልክ ናቸው :: የተሰራ ጨርቅ ከማስመጣት ይልቅ ድር እያስመጡ ማሰራት እንደሚረክስ አውቀው ድር ማስመጣትን የጀመሩ ምኒልክ ናቸው :: ጥይት ፋብሪካን ሲያቋቁሙ "አፍሪካውያን ነጻ መውጣት አለባቸው : ኢትዩጵያም የጥንት ክብርዋን : ወሰንዋን በሙሉ ለማስከበር ትነሳለች " ብለው ለኤሮፓውያን ደብዳቤ የጻፉ ምኒልክ ናቸው ::
በ 1874 አ .ም . ከተማቸውን እንጦጦ ካደረጉ በኅላ በአምስተኛው አመት ቁልቁለቱን ወርደው ዋና ከተማቸው አዲስ አበባ እንዲሆን የወሰኑ ምኒልክ ናቸው :: ስለምኒልክ እጅግ ብዙ ታሪክ አለ ::
በመላው አለም ዝናቸው የታወቀው ታላቁ ምኒልክ ዝናቸውን ያገነኑት በስራቸው እንጂ በዘራቸው አልነበረም :: ሹመት በዘር እንጂ በስራ ባልነበረበት ዘመን የተገኙት ምኒልክ የሚሾሙት የተገላቢጦሽ ነበር :: ሹመት በስራም ብለው ያወጁ ምኒልክ ናቸው ::
አቤቱ አምላካችን ሆይ በዚህ ዘመን ለስራ የተነሳሳ : አንድነትን አላማው ያደረገ : በዘር የማይከፋፍለን : ምኒልክ IIIን አምጣልን :: አሜን ::
ይቀጥላል  _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ጌዴዎን

Joined: 26 Sep 2004 Posts: 94 Location: united states
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 9:13 pm Post subject: |
|
|
የዛሬው ደግሞ አወደ ነገስት ላይ እንኳን ያልሰፈረ አፈታሪክ ነው ቂቂቂቂቂቂቂ
ኢትዮጵያው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አቶሞቢል የገባው በምኒልክ ዘመን ቢሆንም የመጀመሪያው ድራይቨር ( አውቶሞቢል አሽከርካሪ ) ምኒልክ ሳይሆኑ የይድነቃቸው አባት አቶ ተሰማ እሸቴ ነበሩ ::
ስለአንድ ነገር ስትጽፍ ተጨባጭ ማስረጃ ጋር ቢሆን ጥሩ ነበር :: |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Sun Dec 20, 2009 9:29 pm Post subject: |
|
|
የውሾቹን ጩኅት ሰምተው አንባቢዎች እንዳይደናበሩ : ማስረጃ እናቀርባለን ::
ጽሁፉ የተወሰደው አጤ ምኒልክ : ከጳውሎስ ኞኞ : የመጀመሪያው መጽሀፍ ገጽ 236-237 ነው ::
ውሾቹም ጮሀሉ : የጀግናው የእምዬ ምኒልክ ታላቅ ታሪክም ይቀጥላል  _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |
|
|
|
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
|
| Back to top |
|
|
|
|
 |
ወቸውጉድ

Joined: 11 Mar 2006 Posts: 1766
|
Posted: Mon Dec 21, 2009 7:11 am Post subject: |
|
|
At the news of the victory at Adowa black people all over the world rejoiced. Ethiopia became a symbol of the struggle for freedom and black intellectuals and religious leaders made pilgrimages to the country. The battle of Adowa not only saved Ethiopia from colonization by Rome but raised the status of an African country to an equal partner in the world community.
When the Italians under Mussolini again invaded the country 40 years later, black people worldwide supported Haile Selassie's efforts to regain freedom for Ethiopia and celebrated on May 5th 1941 when the Emperor returned in triumph to Addis Abeba. _________________ "REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw- |