WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ወዲ ትግራይ እራሰህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ !!
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
Hagoss

አዲስ


Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 3:42 am    Post subject: Reply with quote

ከመይ ወዲ ትግራይ !! እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በሙሉ !!

ጉድ መጣ ጉድ መጣ
ገንፎ ዛፍ ላይ ወጣ
ይላል አምሓራ ሲተርት

የሻቢያ ሰርጎገቦች ወደ 11ኛው ሰኣት ላይ ደርሰዋል ::
አሁን በዚህ እድሜው ይህ ነፍሰገዳይ እንዲህ ማበድ ኣለበት ?

Code:
ስብሃት ነጋ - ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተጣላ ሰው ::

ከኢትዮሚድያ - ስብሃት ነጋ የጫካው የወያኔ አመራር ቁንጮ አባል እያለ “የሥለላ እና ባዶ ስድስት” ተብሎ የሚታወቀው የቶርቸር እና ግድያ ክፍል ኃላፊ ነበር። የብዙ እስር ቤቶች ኃላፊ ! ስብሃት ሌሊት ከመጣ፣ ለሞት ተዘጋጅተን እንጠብቃለን። ብዙ እስረኞች ተጠርተው ይወጡና በዛው ይቀራሉ” ያለን አንድ የቀድሞ 06 ታሳሪ ነው   አንድ ጊዜ ስብሃት ወጣት ታጋዮችን “ቤተሰብ የናፈቃችሁ መሄድ ስለሚፈቀድላችሁ እጃችሁን አውጡ ! ይላቸዋል በጊዜው የበረሃ ኑሮ፤ ውጣ ውረዱ፣ ረሀቡ   ጥማቱ እና የእናት ናፍቆት ያልቻሉ ለጋ ወጣቶች ጥያቄውን ተቀብለው ቤተሰብ ጠይቀው ለመመለስ ዕድል አገኘን ብለው ከየምድባቸው ፈቃደኛ ሁነው ይቀርባሉ። 15 እና 16 አመት ለጋ ወጣቶች የሚገኙባቸው 60 በላይ ተሰበሰቡ። ስብሃት ነጋ የ“እናቴ ናፈቅሽኝ” ጉጅሌ ይህ ነው ብሎ ሳቀ። የሞት ፍርድ መሆኑ ነው። ሌሊቱም ሁሉንም በልቷቸው አደረ ! (ዋቢ - /መድህን አርአያ እና ተስፋይ አፅብሃ በቃልና በፅሁፍ እንደገለፁት ) ስብሃት ነጋ የፈጸማቸው ወንጀሎች ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። በሀገራችን “አቦይ   የሚል ቃል በጣም ክቡር ቃል ነው። አንቱታን ላተረፉ፣ ከቤተሰብ እስከ ህብረተሰብ በቅንነት ላገለገሉ አዛውንቶች የሚሰጥ ልማዳዊ ማእረግ ነው። ሰዎችን እንደከብት ሲያርድ ለኖረ ጭራቅ አይገባም። ስብሃት ነጋን “አቦይ ስብሃት” ተብሎ ሲጠራ ስንሰማ ይሰቀጥጠናል። ሰይጣን ሰውን ያሳስታል፣ ስብሃት ነጋ ደግሞ ስይጣንም ሳይቀር ያሳስታል ያሉት ማን ነበሩ ? እናም “አቦይ” የምትለውን ክቡር ቃል ከዚህ በታች ከሰፈረው ድንቅ ፅሁፍ አውጥተናታል። መልካም ንባብ !
*****************
ባሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ማለትም በትግርኛው ክፍል [በጥር 272012 [አርብ ]] በቀረበው ያቶ ብስራት አማረ መጽሃፍ ውይይት / አረጋዊ የህወሓት መስራችና አቶ ስብሃት ነጋ በሰጡት አስተያየት የሚመለክት
ነው። በጸሃፊው እምነት በዚሁ ውይይት የአቶ ስብሃት አስተያየት በጣም አደገኛና ከፋፋይ መልእክት ላድማጭ አስተላልፈዋል የሚል እምነት አለው። በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አነሰና በትግራይም ያንን የመከፋፈል ስሜት እንዲያብብ /እንዲሰፍን ሆን ተብሎ የተተፋ መርዝ ስለሆነ ከታሪክና ከሰውየው ባህርይ ምን ማለት እንደሆነ እንደሚከተለው ላንባቢ አቅርበነዋል። የከፋፋይነትን ቆፍጣና ባህርይ የተላበሱ አቶ ስብሃት ያሉትን ቃል በቃል በትግርኛ አስቀምጠን ወደ አማርኛ መልሰነዋል።
አቶ ስብሃት የሚከተለው በትግርኛ ብለዋል፡
[ሕዚ ምስቲ መጽሃፍ ዝጸሃፎ አታአሳሲርካ ድዩ ዝሬኤ፤ ዝገደፎ ነገር ክህሉ እዩ። ነቲ ፅሁፍ ግን ከም ባክግራውንድ [background] መጠን ማለት ካብ ትግራይ ወፃኢ ካብ ኤርትራ ወፃኢ ንኻልእ ከምዘልአልካዮ፤ ንጋምቤላ፣ ንኻልዕ ዝሓውስ አይኮነን አክሱም። ትግራይ እውን ሙሉእ ትግራይ ዝሓውስ አይመስለንን። ተምብየን አካል ናይ አክሱማይት ኢምፓየር ነይሩ ዝብል ሕቶ አለኒ። ኢቨን [even] ዓጋመ ነይሩ ? አብ ሓደ አጋጣሚ ፐረፕለስ ኦፍ ኤረትርያን ዝብል ናይ ዓጋመ ስያሞ ዝብል አብኡ ሪኤ፤ ስያሞ አበይ እዩ እንተበልኩ ዓጋመ እዩ ኢሎምዎ በቲ ናይ ቀደም አፀዋውዓ ንሱውን ፓርት ኦፍ አክሱማይት ከምዘይነበረ እየ ተረዲአ፤ ዘርፎር [therefore] ለጀንድ [legend][ፅውፅዋይ ] እንተዘይኮይኑ ኮንክሪት [concrete] ዝተቀመጠ ታሪኽ ስለዘይፈልጥ ነታ መጽሃፍ ግን አይ ቲንክ [I think]ረለቫንት [relevant] መእተዊ ዝብል አለኒ፤
ናይ ኢትዮጵያ ታሪኽ እንደገና ክጸሓፍ ከምዘሎ እየ ዝአምን። ሓቀኛ ናይ ኢትይጵያ ታሪኽ ንኽፀሓፍ በሪ ትኸፍት ]
አቶ ስብሃት ያሉት ወደ አማርኛ ሲመለስ፡ -
[አሁን ይህ የሚታየው ክፃፈው መፅሃፍ ተዛምዶ ነው። የተወው ነገር ሊኖር ይችላል። ይህ ጽሁፍ እንደ መነሻ መጠን ማለትም ከትግራይና ኤርትራ ውጭ ልክ አንተም እንዳነሳኸው ጋምቤላና ሌላም የሚጨምር አይደለም አክሱም። ወደ ትግራይም ስንመጣ አሁን ያለው ትግራይን የሚጨምር አይመስለኝም። ተምቤን የአክሱማይት ኢምፓየር አካል ነበር ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ። እንዲያውም አጋሜስ [አውራጃ ] ነበር ወይ ? ባንድ አጋጣሚ በፐረፕለስ ኦፍ ኤርትራ የአጋሜ ስያሞ የሚል አየሁ። ስያሞ ማለት ደግሞ ብድሮ ኣጠራር አጋሜ ነው ብለውታል።እና የአክሱም አካል እንዳልሆነ ተገነዘብኩኝ። እና አፈታሪክ ካልሆነ የተጨበጠ ታሪክ ስልማላውቅ ስለ መፅሃፍዋ ግን እንደማስበው ተገቢ መንደርደርያ ነው እላለለሁ። የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መጻፍ አለበት ብዬ ነው የማምነው። እውነተኛ ታሪክ እንዲፃፍ [መፅሃፍዋ ] በር ትከፍታለች። ]
የአቶ ስብሃት አስተያየት የመጣው በመጀመርያ / አረጋዊ ያክሱም መንግስት [ኢምፓየር ] ታሪክ ሰፊ ግዛት የሚያጠቃልል እንደነበረና [ሲዳሞን ሜጫንና እናርያ በደቡብ በሰሜን ደግሞ ሜሮዌን [ ከሱዳን ዋና ከተማ በሰሜናዊ ምስራቅ 135 ማይልስ ርቃ የምትገኝ ያክሱም አካል የነበረ ታሪካዊ ቦታ ] እንዲሁም እስከ ቀይ ባህር ጠረፍ ድረስ እንደነበረ ከገለጹ በኋላ ነው። ታሪክም / አረጋዊን ያሉትን ይላል፤ ይደግፋችዋልም።
ስብሃት ነጋ
2
ስብሃት ግን ያክሱም መንግስት በዶ / አረጋዊ ከተባለው በተቃራኒ በመቆም እንድያውም ትግራይን በሙሉ ማካተቱ እንደሚጠራጠሩ ነግረውናል። ለጥርጣርያቸው መንስኤ የሆነውም እንደ ማስረጃ የጠቀሱት ቢኖር Periplus of the Erythraean Sea [ፐሪፕለስ ኦፍ ኤርትርያን ] የሚል ግሪኮች ድሮ ስለ ጉዞና የንግድ ሁኔታ የሚተርክ ጽሁፍ ጠቅሰዋል። ይህ ጽሁፍ እሳቸው ላሉት በትኛው ገጽ እንደሚገኝ ግን አልተናገሩም።
ባቶ ስብሃት የተጠቀሰው የታሪክ አስረጅ ግን ስለ አክሱም ሲናገር እንደ ሚከተለው ይላል፡
[The first mention of Aksum was in a Greek guidebook written around A.D.
100, Periplus of the Erythraean Sea. It describes Zoskales (ZAHSkuhleez),
thought to be the first king of Aksum. He was a stickler about his possessions
and always [greedy] for getting more, but in other respects a fine person and well
versed in reading and writing Greek. Under Zoskales and other rulers, Aksum
seized areas along the Red Sea and the Blue Nile in Africa. The rulers also crossed the Red Sea and took control of lands on the southwestern Arabian Peninsula.]
[ http://sharepoint.chiles.leon.k12.fl.us/mcneilt/Textbook%20for%20World%20History/Chapter%2008/Ch%208%20Sec%203.pdf
ትርጉሙ፡
[ስለ አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ተጽፎ የተገኘው 100 .. አካባቢ በፐሪፕለስ ኦፍ ኤርትርያ የተባለ መጽሃፍ ነው። የሚገልጸውም ስለ ዘስካለስ የተባለው የመጀመርያው ያክሱም ንጉስ ነው። ንጉሱ በንብረቱ በጣም ጠንቃቃና ለመጨመርም ከፍ ያለ ፍላጎት የነበረው ንጉስ ነው። በሌላ ጎኑ ደግሞ ጥሩ ሰውና እንዲሁም የግሪክ ቛንቛ አቀላጥፎ የሚናገርና የሚጽፍ ነበር። አክሱም በዘስካለስና ሌሎች ገዢዎች በነበሩበት ሰዓት ቀይ ባህርና የጥቁር አባይ አካባቢ ግዛትዋ ነበር። ገዢዎቹ ወደ ደቡብ አረብያ [የመን ] በመሻገርም የተወሰኑ መሬቶች በቁጥጥራቸው አርገው ነበር። ]
ቁም ነገሩ በግልጽና በማያሻማ መንገድ ያክሱም ስልጣኔ ጥቁር አባይንም ጭምር እንደሚጠቀልል ይገልጻል። እና የአቶ ስብሃት አባባል ከየት እንዳመጡት ግልጽ አይደለም ሙግታቸውም ውሃ አያቛጥርም እንላለን።
እስኪ ደግሞ ያገራችን ምሁራንና ትላልቅ ሰዎች ስለ አክሱም ያሉትን እንመልከት፡
/ ተወልደ ትኩእ ባዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር አባል እንዲሁም የታሪክ ተማራማሪ የሆኑት መጽሃፋቸው ከዶ / አረጋዊ አባባል ጋር ይስማማል። አብነቶችን ብናስቀምጥ ለተባለው እንደ ማስረጃ ያገለግላል። የኢትዮጵያ አንድነት እና ኢጣልያ በሚለው መጽሃፋቸው [/ ተወልደ ትኩእ የታሪክ ምሁር ] ስለ አክሱም ያሉትን እንይ፡
“የአክሱም ታሪክ የምናውቀው ከመጀምርያ ሲቛቛም አይደለም። በጠፋው የአዱሊስ ሓወልት የምናገኘው ጽሁፍ ያንድ አዲስ መንግስት ሳይሆን የአንድ ረጅም ታሪክ ያሳለፈ የብዙ የሚቆጠሩ አመታት የተደራጀ የምድር ጦርና የባህር ሃይል ያለው ከታላቁ የሮማ መንግስት በጦር ሜዳ የሚፋለም መንግስት ነው። ንጉሱ የሚተርከው [በሃወልቱ ያለው ጽሁፍ ማለት ነው ] በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ስላደረጋቸው ዘመቻዎች ነው” [ገጽ 38] ይላል
በመቀጠለም የታሪክ ምሁሩ ስለ አክሱም ታላቅነትና ገናናት እንዲሁም ወደ የመን የተደረገው ዘመቻ ሲገልጹ፡
“ዘመቻው ግዙፍ ነበር። የኢትዮጵያ ወታደሮች ቀይ ባህርን ሲያቋርጡ 191 በቢዛንታይን የንግድ መርከቦችና 170 አጼ ካሌብ ባሰራቸው ተሳፍረው ነበር። የመን የደረሱትንና አጼ ካሌብ ያካሄደው ዘመቻ በሁለት ዙር ነበር” [ገጽ .47]
ግሪካዊ የታሪክ ተማራማሪ ሄሮዶቶስም ያክሱም [ኢትዮጵያ ] ስልጣኔ ክነሮማና ፐርስያ እንዲሁም ቻይና ጋር የሚወዳደር ትልቅ ግዛት ያጠቃለለ እንደነበር ይገልጻል።
ንቡረዕድ ገብረመስቀል ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ስትዋሃድ አፄ /ስላሴ ክኤርትራ ሲመለሱ እግረ መንገዳቸው ወደ አክሱም ብቅ ብለው በነበሩበት ሰአት ንቡረዕዱ ከንጉሱ ፊት ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ ባክሱም ዘመነ መንግስት አብርሃ ትግራይን ሲገዛ ታናሽ ወንድሙ አፅብሃ ደግሞ ሸዋን ይገዛ እንደነበረና ይህ ማለት ደግሞ የትግራይና የሸዋን ትሥሥር የሚያመልክት እንደሆነ የገለጹበት ሁኔታ በዘውዴ ረታ ስለ ኤርትራ ችግር ባቀለሙት መጽሃፋቸው ተዘግቦ ይገኛል። ይህ ታሪካዊ ትስስር ሸዋ ያሉት አዛውንቶችና ትግራይ ያሉት ሽማግሌዎች አሳምረው ያውቃሉ እኛ ልጆቻቸውም ያሉትን እናምናለን።
በመጨረሻም የማያዳግም ማስረጃ የሚጠቀሰ ቢኖር ስለ ቅዱስ ያሬድ ነው። የነበረበት ጊዜ ባጼ ገብረ መስቀል 6ኛው /ዘመን ነው። ያሬድ ያክሱም ተወላጅ ይሁን እንጂ መጨርሻ አካባቢ ወደ ጎንደር አካባቢ በመሄድ ነው መንፈሳዊ ጊዜው
3
ያሳለፈው። ጸናጽልና መቆምያው በጣና ጭርቆስ ቤተ ክርስትያን [በጎጃም ] እስከ አሁን ድረስ እንዳሉ ይነገራል። ታድያ አቶ ስብሃት የአክሱም ‘ኢምፓየር’ መላ ትግራይን ማካለሉ እንጃ ማለታቸው ከምን የመነጨ ነው ትላለህ /ትያለሽ አንባቢ ?
በታሪክ ታላላቅ መንግስታት [ኢምፓየር ] የምንላቸው ትልቅ የሆኑበት ምክንያትና ባህርይ [ክራተርያ ] መሰረቱ ሰፊ ግዛትና ሃብት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ብዙ ህዝብና ሪሶርስ በጃቸው ካስገቡ በሃላ ነው ማለት ነው። የአክሱም ስልጣኔም ይህንኑ መስፈርት ይጋራል /ያሟላል። ከዚሁ ባህርይ ውጭ ሊሆንም አይችልም።
እንግዲህ አንባቢ /አንባቢት ያገርና የውጭ የታሪክ ምሁራን ስለ አክሱም ከላይ የተጠቀሰውን ይላሉ፤ አቶ ስብሃት ግን የፖለቲካ እንጂ የታሪክ ምሁር ያልሆኑ አዛውንት ያክሱም ስልስጣኔ ላለው ኢትዮጵያስ ይቅርና መላ ትግራይን ማዳረሱ እጠራጠራለሁ ብለው መናገራቸው ምን ለማለት ፈልገው ነው ? ነገሩ አስገራሚ ወይስ አሳዛኝ ?
ያቶ ስብሃት መልእክት ትግራይን ለሁለት የሚከፍል ንግግር ነው ካንደበታቸው ሲነገሩን የሰማነው። ይህ አስተያየት በተራ ሰው አንደበት የተነገረ ሳይሆን ካንድ ቱባ የህወሓት መሪ ነው። እና ለዚሁ ሃሳብ ምን ለማለት እየተፈለገ እንደሆነ የሚሰማንን እናስቀምጥና አንባቢ ደግሞ የራሱ /የራስዋ ግንዛቤ ይወስዳል።
ስብሃት ነጋ በመጀምርያ በመምህርነት ቀጥለውም ወደ ትግል አለም ገብተው እስከ አሁን ከፖለቲካ አለም ያልተለዩ ሰው ናቸው። በትግራይ ሰው ህሊናና በታሪክ የሌለ ነገር በመገናኛ ብዙሃን ቀርበው ያክሱም ስልጣኔ ለኢትዮጵያ ታላቅዋ አገር ይቅርና ለሁሉም የትግራይ አውራጃዎች እንኳ የሚመለከት አልነበረም [አጋሜና ተምብየን እንደማያካትት ] ወይም ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልጹ የሰማናቸው በሃዘን /በቁጭት ነው ! ያሉበትን ድርጅት በባህላችንና ሃይማኖታችን ያሳደረው አሉታዊ ተጽእኖ አነሰና ነው አሁን በቀረችው አንድነታችን የመጡብን ? ያስብላል።
አቶ ስብሃት ! ለመሆኑ ምን ያህል ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ የተጻፉ መጻህፍቶች አንብበው ነው አሁን ወደአሉን ጥርጣሬ ሊገቡ የቻሉት ? ቁንጽል ስለ ፐረፕለስ ኦፍ ኢርትራን የሚል ዋቢ ብቻ በማስቀመጥ ስለ አጋሜ አውራጃ ያክሱም ስልጣኔ አካል እንዳልነበረ ሊነግሩን ሞክረዋል። ታድያ ለታሪክ ሰዎችና ለኛ እስከ አሁን ያልተገለጸልን ምስጢር ለርስዎ እንዴት እንደበራላቸው ለወደፊት ዘርዝረው ቢነግሩን መልካም ነበር። ያወቅነው ነገር ቢኖር ግን የታሪክ እውቀትዎ አንሶ ሳይሆን ሆን ብለው ታሪካችንን እየበለዙ ነው የሚለው ላሉት ነውረኛ አባባል ይገልጸዋል።ጉዳዩ ቅድም እንደጠቀስነው ተራ ንግግር /አስተያየት አይደለም፡፡ እስኪ ስለ አቶ ስብሃት ጸባይና ተግባር የሚነገሩትን [ከዚሁ በታች ያሉትን ] አንባቢ /አንባቢት ልብ እንዲለውና አሁን ሰውየው ካሉት አያይዞ እንዲመዝነው በትህትና እንጠይቃለን።
ሰውየው ካውራጃ አልፈው ወደ ስጋ ዝምድና ወርደው የማዳላት ስራ ይተገብራሉ። የስራ ዕድልና ሹመት ሲሰጡ ባቶ ስብሃት ቤት ዋና መለኪያው እውቀትና ችሎታ ሳይሆን እሳቸው ከተወለዱበት /ከተማሩበት አካባብን መሰረት አድረገው እንደሚሰሩ ነው።
እንግዲህ ትክክለኛውን ታሪካችንን ባልሆነ ይትበሃል [ተረት ተረት ] ነገር ለመተካት የቃጡ ደፋር አዛውንት ከላይ የተጠቀሰውን የማይደገፍ ባህርይና ተግባር ባለቤት ለመሆን ምን ሊያግዳቸው ይችላል ?
በትንሽ ግዛት የተከለለ ህብረተሰብ ማለትም ባቶ ስብሃት አባባል ባክሱም ባድዋና በደቡብ ኤርትራ [አከለጉዛይና ሰራዬ ] በነበሩት ህዝቦችና ሃብት ብቻ ያክሱምን ስልጣኔ የሚያክል ታሪክና መንግስት ሊፈጥሩ ከቶ አይቻላቸውም። ከሎጂክም ውጭ ነው። ማለትም ኢምፓየር ከሚለው ባህርይ ራሱ የሚጋጭ አስተሳሰብ ነው።በቅርቡ ታሪክ እንኳ ስንመለከት እንግሊዝ ትልቅ የሆነችበት ምክንያት ያለምን ሩብ አካል ስለገዛችና የተገዢዎቹ ሃብት በመበዝበዝዋ ነው። አሜርካን ብንመለከት ሰፊ ግዛትና ሃብት ነው ትልቅ ያደረጋት እንጅ ሌላ ምስጢር አይደለም።አክሱም በራሱ ትልቅ ስልጣኔ የነበረና ግዛቱም ሰፊ እንደነበረ ካለው ቅርስና ከተጻፈው ታሪክ መናገር ይቻላል። የቆሙት ሃወልቶችና የተሰሩት ጥበቦች እንዲሁም የወረስነው ፊደል በቁጥር አነስተኛ ህዝቦችና በጠባብ ግዛት በሰፈሩ ህዝቦች የተገነቡ ሳይሆኑ የብዙ ህዝብ ጉልበትና ሃብት ውጤት መሆናቸው ግልፅ ነው።
ከላይ የተገለጸው ሃይለ ሃሳብ የሚደግፍ አስረጅ ደግሞ እስኪ እንይ፡
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻው፥ ጒዞውና መድረሻው በሚል ርዕስ የተከተበው ጽሁፍ በታሪክ ምሁር የሆኑ ኢትዮጵያዊ / ጌታቸው ኃይሌ እንደሚከተለው ይላል፡
“የዓባይን ግልገልነትና ዓቢይነት ያነሣሁት ለሥልጣኔያችን ልደትና እድገት ምሳሌ እንዲሆነኝ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ይዞት የሚጓዘው ሥልጣኔ የተወለደው የኢትዮጵያ መንግሥት እተወለደበት ቦታ
ነው፤ ጽራዕ ወይም ትግራይ ውስጥ ማለቴ ነው። ሥልጣኔው በዚያና በዚህ ተጒዞ፥ ተጒዞ እየዳበረ
መንግሥታዊ ማእከላችንን አዲስ አበባ ላይ ካደረግነው ከእኛ ዘመን ደርሷል። የዓባይ ወንዝ ሲጓዝ ከየቦታው
የሌላ ወንዞች ውኻ እየተመገበ እንደገዘፈ ሁሉ፥ የኢትዮጵያ ሥልጣኔም መንግሥት እጁን ከዘረጋበትና
ማእከሉ ካደረገበት ቦታ ሁሉ ምግብ እያገኘ ገዝፏል። መግዘፍ ብቻ ሳይሆን መልኩም በመጠኑም ቢሆን
ተለውጧል።” http://ethiomedia.com/broad/ethiopian_civilization.pdf
4
እና እነ ካሌብ እስከ የመን ድረስ ዘምተዋል ተብሎ የተጻፈው ታሪክና ያቶ ስብሃት ነጋ ደግሞ አጋሜና ተምብየን ያክሱም አካል ነበሩ ለማለት ያስቸግራል የሚለው መሰርይ አስተሳሰብ በራሱ አይጋጭም ወይ ? በዚሁ ያልገባን ቢኖርና የምንጠይቀው በወቅቱ በአጋሜና በተምብየን አካባቢ ሰው አልነበረም ነው ? ወይስ ነበሩ ግን ለብቻቸው መንግስትና ታሪክ ነበራቸው ለማለት ነው የተሞኮረው ? ለመሆኑ አክሱም ወደቡ አዱሊስ አልነበረም ወይ ? ወይስ እንደአሁኑ አክሱማውያን ወደቡ ተከራይተው ነው ሲወጡና ሲገቡ የነበሩት ? አጋሜ ያለው ጉሎ መከዳስ የሳባ ታሪክና ያክሱም አካል አይደለምን ? ባለስላጣን ሁነው በድርጅታቸው የታቀፉትን አባላት አንዱን ከፍ ሌላው ደግሞ ዝቅ የማድረግ ችሎታ ባንድ ወቅት እንደነበራቸው ይታወቃል አቶ ስብሃት። ያች የተለመደች አመልም እንግዲህ በታሪካችን ለመድገም የፈለጉ ይመስላሉ። በዚሁ ግን አዳልጦዋቸው ሲወድቁ አይተናልና፤ ለወደፊቱ ባይሞክር መልካም ነው።
ያክሱም ስልጣኔ መላ ትግራይን እንደሚጠቀልል የተጨበጠ ታሪክ የለም ብለዋል አቶ ስብሃት። ምን ያህል መጻህፍት ቢፈትሹ ነው ይህ ለማለት የደፈሩት ? የተጨበጠ የለም የሚል ሰው እኮ ብዙ አንብቦና ተመራምሮ ነው እንጂ ከሜዳ ተነስቶ በስሜት የሚባል ነገር ለትዝብት ይዳርጋል። ማስረጃ የለም ማለት ጉዳይ አልነበረም ማለት አይደለም። ወደ ገለጹት ጉዳይ ስንመለስ ደግሞ እኛ በምናውቀው መንገድ ያገርና የውጭ ታሪክ ፀሃፊዎች ያሉትን የሚደግፍ በብዛት ሞልተዋል። እና ምን ለማለት እንደፈለጉ እንቆቅልሽ ሳይሆን ያው ያች መርዘኛ የመከፋፈል ስራ ህይወት እንድትዘራ ስለፈለጉ እንጂ።
ስለ አክሱም ታሪክ ሲገልጹ ኣቶ ስብሃት አንድ ነገር ረስተዋል። ማለትም ባህር የሆነውን ታሪካችን እንኳንስ በፖለቲከኛ ይህ ነው ነው ሊባል ይቅርና ለታሪክ ባለሞያዎችም እስከ ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ ነው። በዚህ እድሜዎ ያንድ እናት ልጆች ለሁለት ለመክፈል የቃጡና በዚሁ አድራጎታቸው የሚታዘንባቸው ስብሃት ናቸው እንላለን። ሰው የድሜ ባለጸጋ ሲሆን ያምላክ ትዕዛዛት ያከብራል፤ ከዚያም አልፎ ለሰውም ፍቅር ይለግሳል። እርስዎ ግን የታጠቁትን ጎራዴ ካፎቱ አውጥተው በታሪካችንና በክብራችን አንገት ላይ ለማዋል ሙከራ አድርገዋል።ማውቅ ያለብዎትን ግን እኛ የትግራይ ሰዎች /ልጆች ያንድ እናትና አባት መሆናችንና አውራጃ አጥር ሁኖ እሳቸው ወደ አዘጋጁልን አደገኛ ወጥመድ እንደማንወድቅ አሳምረን ልንነግርዎት እንፈልጋለን ! ! !
ማሳሰብ የምንፈልገው አዳንድ የትግራይ ማህበር ነን ወይም የትግራይ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ማህበራትና ግለሰቦች እኛና እነሱ ወይም ትግራይን ለሁለት የሚከፍል አባባል ካቶ ስብሃት ሰምተዋል። እና ምን ይላሉ ? በዚሁ ዙርያ የተሰማቸውን ቢገልጹልን መልካም ነው።
አቶ ስብሃት ነጋ የታሪክ ምሁር አይደሉም ግን የፖለቲካ ምንዝርና ሲፈለጉ ጎራ እንደሚልዋት አይተናል፤ ለወደፊትም ስብሃት የሚለው ስምም ፍቺው ከፋፋይና ያክሱምን ታሪክ ለማሳነስ የሞከረ ተብለው ታሪክ ሲያወሳቸው ይኖራል።
/
ዋቢ ፅሁፎች
1. የኢትዮጵያ አንድነት እና ኢጣልያ። / ተወልደ ትኩእ .ሚያዝያ 1990
2. ማስታወሻ [ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ] ከዘነበ ወላ የካቲት 1993 ገጽ 296
3. http://sharepoint.chiles.leon.k12.fl.us/mcneilt/Textbook%20for%20World%20History/Chapter%2008/Ch%208%20Sec%203.pdf
4. http://ethiomedia.com/broad/ethiopian_civilization.pdf
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
February 11, 2012


ሀጎስ
ደቂ መቕለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ


Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 4:05 am    Post subject: Reply with quote

የሚገርመውስ የስብሀት ታሪካዊ ትንታኔ ሳይሆን የሱን ታሪካዊ ትንታኔ ከቁም ነገር ጽፈው መልስ በሚሆን መልኩ ታሪካዊ ትንትና ለመስጠት የተነሱት ናቸው :: መለስም እንዲህ ሳይቸግረው በባንዳ አቅሙ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ትንተና እሰጣለሁ ብሎ ጀምሮ በየት በየት በኩል እንደሆነ ሳያውቀው ""የህዳሴው "" ግድብ ላይ ደርሶ በሳቅ ጨረሰን ::

አኒ ዌይስ የህወሀቶችን በታሪክ ላይ ያላቸውን አቋም ፕሮፌሰር ጨርሰውታል ---ታሪክ በጥይት አይጻፍም ! ይልቅ ለማወቅ ፈልጌ የነበረው ... አጋሜ ምን አለ በስብሀት እጂ እና እግር በሌለው ታሪክ ? ተምቤንስ ምን አለ ??

ከወደትግራይ ዳር መጣ ሄደት እያለ ...ህወሀትን የሚተገትግ ቡድን ተነስቷል ይባላል ...መቼስ ወሬ አይደበቅ ! አጋሜ መሆኑ ነው ?!

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Hagoss

አዲስ


Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 5:53 pm    Post subject: Reply with quote

ስለም ወገኖች !!
በትግራይ ህዝብ ስም በተሰየመው ሕወሓት ድርጅት ውስጥ ገና ከመነሻው በስልጣን ውስጥ የተሰገሰጉት እንደነ መለስ ዜናውና ስብሓት ነጋ የመሳሰሉት የሻቢያ ሰርጎ ገቦች የትግራይ ወጣቶችን ለኤርትራ ነጻነት ውድ ሕይወታቸውን እንዲሰው ከማድረጋቸውም በላይ የተረፉትን ማለትም የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያላቸውን የትግራይ ወጣቶችን እንዴት ሲስተማቲካሊ እደሚያስፈጇቸው ከወዲ ገብረመድህን ኣራያ እንደገና በጥሞና ያዳምጡት ::


http://www.youtube.com/watch?v=tvKAr6Dy5Oo&feature=player_embedded#!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Abba Tobia

ዋና ኮትኳች


Joined: 02 Nov 2011
Posts: 833
Location: asia

PostPosted: Tue Feb 21, 2012 1:15 am    Post subject: Re: ወዲ ትግራይ እራሰህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ !! Reply with quote

Hagoss እንደጻፈ(ች)ው:
ተወላጅነታቸው ኤርትራዊ የሆኑት
ማለትም እንደ :
1.መለስ ዜናዊ ,
2.ሰብሀት ነጋ ,
3.በረኸት ሰሞኦን ,
4.ሳሙራ የኑስ .
5. አባይ ጸሀዬ -
6.ተከለወይኒ አሰፋ
7. ቅዱሳን ነጋ

በትግራ ነጻ አውጭነት ስም ሕወሀት ውስጥ ተሰግስገው ውስጥ ለውስጥ ለሻቢያ በመስራትና በመመሳጠር በትግርይ ሕዝብና በትግራይ ተወላጆች ላይ የፈጽሙትን ደባ እንደሚከተለው እንመልከት ::

በተለያየ ወቅት ስለ ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልና ሻቢያን ስለተቃወሙ ብቻ ከሕወሀት የተባረሩ የትግራይ ተወላጆች

1. ዾክተር ሀረጋዊ በርሄ

2. ዶክተር ግደይ ዘርዓጽዮን

3. አቶ ገብረ መድህን አርዓያ

4./ አረጋሽ አዳነ

5.አቶ አለምሰገድ ገብረዓምላክ

6. አቶ ስዬ አብረሀ
ይቀጥላል

ሀጎስ
ደቂ መቕለ


ስለ ትግራይ ከትግሬ በስተቀር ማን ያገባዋል ብለህ ነው እዚህ ኢትዮጵያ መድረክ ላይ የምትንጫጫው ? ትግራይ በነመለስ ብቻ ሳይሆን ከዛም በፊት የመቶ ዐመታት የአማርኛ ተናጋሪ ጠላት እንደሆነ ጥቂትና አንጡራ ኢትዮጵያዊያን የሆንን እናውቀዋለን .

ትግራይ /አገር ከኢትዮጵያ ተቆርጦ መጣል አለበት .
_________________
i oppose woyane because i disagree forever about ethnic federalism and article 39, the right to secede.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዶሮ IQ

ኮትኳች


Joined: 23 Jun 2010
Posts: 214
Location: ye Doro Qot

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 4:05 pm    Post subject: Reply with quote

http://www.youtube.com/watch?v=sOG4awko0qw&feature=related

የወዲ /መድሕን ኣርዓያ ሁለተኛው ክፍል :
የሻቢያ ተወካዎች መለስና ስብሐት ለተራበው የትግራይ ህዝብ የሚሰጠውን ገንዘብ እንዴት እንድሚነጥቁ ያዳምጡ ::

የመቀሌ ዶሮ
ቅቅቅቅቅ
_________________
Doro´s IQ is Better than Weyane Cadre´s IQ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Hagoss

አዲስ


Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 9:11 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዶሮ መዘግየቴን ተመልክተህ ቀጥዩን የኣቶ ገብረመድህን ኣርኣያን ኢንተርቪው በማቅረብህ በጣም አመሰግናለሁ ::

ለዛሬው ኤኔ ይዠ የቀረብኩት ታዋቂውና ሀገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ( የዓደዋ ተወላጅ ) የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን ነው :: ኣቶ ጌታቸው ረዳ የሻቢያ ሰርጎ ገቦችና አሽከሮቻቸው ለኢትዮጵያና ለትግራይ ህዝብ የቀመሙትን መርዝ የሚያረክስ መጽሀፍ ከማቅረባቸውም በላይ ከነጻነት ለኢትዮጵያ ራዲዮ ጋር ውይይት አድርገዋል ::
ይንንም ውይይት ከዚህ በታች ባለው ሊንክ አብረን እንስማቸው ::

http://www.youtube.com/watch?v=qeG7Aizjei0&feature=related
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
Page 4 of 4

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia