WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች ...
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Sat Apr 23, 2011 6:52 am    Post subject: Reply with quote

ሮብ እለት ጥዋት 10.30 AM

ኤስቴር ገርበብ ያለውን በር ሳታንኴኴ ገፋ አድርጋው ገባች :: ለወትሮው የሚታየው የፊቷ ብርሀን ደብዝዟል :: ከጥቁር ፊቷ ጋር የምትቀባው ቅባት ብርሀን ሲያርፍባቸው በስሱ እንደታሸ ኑግ ያብረቀርቁ ነበር :: ዛሬ ግን እነዛ ድምቀቶቿ የሉም :: ቦግ ያሉት አይኖቿ ግን አሁንም ጨረራቸውን ይፈነጥቃሉ :: አይኖቿ ክፍሉን መቃኘት ያቆመው የኔን አይኖች ሲያዩ ሆነ :: ዝም ብላ አየችኝ :: እውነት ለመናገር ይሄ ዐስተያየትቷ ያስፈራኛል :: ትክ ብላ ስትመለከት እንዳች ጥንቆላ ለመስራት ያሰበች ያስመስላታል :: ደግሞ በተፈጥሮዋ ቸኩላ ስለማትናገር በውስጧ ምን እንዳለ ለማወቅ ያስቸግራል :: ይቺ ልጅ እኔ ሳላያት ጥንቆላ ሳትሞክር አትቀርም አልኩ በልቤ :: አዳል ሞቲ ... አዳል ኮቲ ..ሻላላሚዶ . .:: Very Happy
በደከመና በተሰላቸ ሁኔታ ወንበሩን ወደ ኌላ ስባ ወደ ኌላዋ ጋለል እንደማለት አለች :: "Bouchron " የፈረንሳይ ሽቶ ከላይዋ ላይ እየተነሳ ወደኔ መጣ :: የት ላይ ይሆን ሽቶዋን የተቀባችው ? ክንዶቿ ስር ነው ....አንገቷ ላይ ነው ጡቶቿ መካከል ነው ..? yes I got it!! ጡቶቿ መህል ነው ያርከፈከፈችው :: ያለ ይሉኝታ አፈጠጥኩባቸው ያደረገችው የጡት መያዣ ከስር ወደ ላይ ቀና አድርጎ ጡቷን ክስር ከመደገፍ ውጭ ሌላ ስራ የለውም :: ይሄን የሰራው ዲዛይን እጁ ብርክ ይበል .. ያለ ይሉኝታ አፈጠጥኩበት :: ይሄ ሁሉ ሲሆን እነዛ ጠንቌይ አይኖቿ ለካ ያዩኛል አሁንም አልለቀሉኝም ... በድንጋጤ አይኖቼን ወደ ቦታው መለስኩት ::
ምቀኛ ::
ዝምታውን ለመስበር ወሬ አመጣሁ ...

" ዛሬ የደካከመሽ ትመስያለሽ ..."

" አዎ ደክሞኛል በደንብ አልተኛሁም ..."

" ምነው በደህና ?"

" ባንተ የተነሳ "

" በኔ የተነሳ ምን ? "

" ባንተ የተነሳ በቁ እንቅልፍ አልተኛሁም "

" አልገባኝም ...ጨዋታውን ልቀይርባት አሰብኩ ...ፈተናሽ እንዴት ሆነ ? "

ፈገግ እንደማለት ብላ መልስ ሰጠችኝ :: ለፈተናው እያጠናሁ ነው ግን ጤንነት አይሰማኝም ጉሮሮዬን ሁሉ ያመኛል ..
"አዎ ድምጽሽም እንደ በፊቱ አይደለም " " ሆስፒታል ሄደሻል ? "

" አሁን መሄድ አልፈልግም ...ፈተናዬን ልጨርስ ! "

" ጥሩ አስበሻል .."

" ጔደኛህ እንዴት ናት .."

" ደህና ናት .."

" ግን በጣም ልጅ ትመስላለች .."

" አዎ እኔ በድሜ እበልጣታለሁ .."

ባይኗ ንቅንቄ መስማማቷን ገለጸችልኝ ::

ትንሽ ዝምታ ::

"መቼ ነው ልደትህ ? "

"የማን ?

የማን ..? ( የኔን ጥያቄ ደገመችው ) ያንተ ነዋ ከኔና ካንተ ሌላ ሰው እዚህ አለ እንዴ ? "

"መስከረም 10 .."

" ሌቪ ነህ ማለት ነው ?"

" ይሆናል እኔ ግን ይገርምሻል በዚህ አይነት እገር አላምንም "

" እኔም ሌቪ እነደሆንኩ ታውቃለህ ? "

" አላቅም ነበር ያንቺም በርዝ ደይ መስከረም ነው ማለት ነው ? "

እኅኅ ... አሁንም ባይኖቿ አዎንታዋን ነገረችኝ ::

አይኖቿ አሁን ህይወት አላቸው ያወራሉ ::

" ለዚህ ይሆናል የምንግባባው .."

"ምን አልሽኝ . እንደ መባነን አልኩ ::

ባንድ ወር የመወለዳችን ምክንያቱ ይመስለኛል የሚያግባባን አይመስልህም ? :

አረ ይመስለኛል ...ይመስለኛል ሳላውቀው ቃሉን ጠበቅ አድርጌ ደገምኩት :: ለካ እንደዚህ ደድበሀል ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Sun Apr 24, 2011 6:38 pm    Post subject: Reply with quote

ክላራይሶ ክላራይሶ ...

አምላክ ክርስቶስ ...
ያድነነ ከመአቱ ይሰውርነ

በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲ ...

ስማነ አምላክነ ...--መድሀኒነ ...( *3)

እነሆ ክላራይሶ አልን ... ክላራይሶ ለምድራችን ክላራይሶ ላገራችን ክላራይሶ ለኢትዮጵያ ...አገራችንን ከጠላቶቿ እንዲጠብቅልን ......ክላራይሶ እያልን አነባን ሙሉውን ሌሊት :: አምላካችን ለመሪዎቻችን ማስተዋልና ጥበብን እንዲሰጥ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ህዝብን የሚበድሉትን ግፍ የሚፈጽሙትን በዘመድ በጉቦ ሀላፊነታቸውን የሸቀሉትን በመዋእለ - ንዋይ ፍቅር የሰከሩትን ከመንገዳቸው እንዲመለሱ ሳይሆን ቅዱስ ሚካኤል አንገታቸውን በሲባጎ ሲጥ እንዲያደርግልን አምርረን አልቀስን :: ባንጻሩም ለውነት የቆሙትን የሀገራቸውን እድገትና ልማት ለማየት ቀን ከሌት የሚለፉትን ወንጀለቾችን አራሙቻዎችን እያሳደዱ የሌባ እጃቸውን የሚቆርጡትን ለነዛ የውነት አርበኞች አለቀስን :: ቅዱስ ሚካኤል በቸርነቱ እንዲጠበቅቻው ክላራይሶ አልን :: ክላራይሶ አልን ... በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ስለሰራነው ሀጢአታችን ..እጆቻችን ወደ ሰማይ አቅንተን ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Fri Apr 29, 2011 1:34 am    Post subject: Reply with quote

" The age of privacy is over.." ይሄን ያለው ወጣቱ የፌስ ቡክ ፈጣሪና ባለቤት እንዲሁም ዲታው ማርክ ዙከርበርግ ነው :: ሰዎች ሌላ ሰው እንዲያውቅባቸው የሚፈልጉት ውስጣቸው ተደብቆ የሚቀር ሚስጥር ይኖራቸው ይሆናል :: ባገራችንም አባባል ተመሳሳይ እገላለጽ አለ :: " ሁሉንም ካወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል "" ፌስ ቡክ ያንን የማህበራዊ ህይወት ተውፊት ( ሶሺያል ኖርም ) አፍርሶታል :: አንድ ነገር ፌስ ቡክ ላይ ከሰፈረ በቃ ሚስጥርነቱ አበቃ :: ለዚህም ነው ማርክ ፌስ ቡክ የህበረተሰቡን የኑሮ ፈሊጥ ስራት ለወጥቷል ብሎ በድፍረት የሚገልጸው :: 672 ሚሊዮን 949 850 የአለም ህዝብ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ( አዲክትድ ) ወይም ሱሰኛ እንደሆነ ያውቃሉ ? አሜሪካ , ኢንዶኖሽያ , ዩናይትድ ኪንግደም , ተርኪና ህንድ እንደ ቀደም ተከተላቸው ፌስ ቡክን በማዘውተር ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ቦታ ይዘዋል :: ካፍሪካ ግብጽ በተጠቃሚነት አንደኛ ናት :: ፌስ ቡክ ለግብጽ መጣላት ወይስ መጣባት ይላሉ የተከበሩ አንባቢ ? መልሱ እንደመላሾቹ ይለያይ ይሆናል :: ግብጽ ሙባረክን አጣች ... አባይንም ሳታጣው አትቀርም ( በሹክሽኩታ !!) :: ወዳገራችን ጉዳይ ጠጋ ስንል ፌስ ቡክን የሚጠቀሙ 277, 720 ተጠቃሚዎች አሉ :: ከነዚህ ውስጥ 41% 25-34 እድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሲሆኑ 69% ተጠቃሚዎች ወንዶች 31% ደግሞ ሴቶች ናቸው :: ሬሾ ብንጥል 2:1 ነን :: ጥሩ ወይስ መጥፎ ? Very Happy አንዱ እዚህ ዋርካ ላይ
በፌስ ቡክ ፍቅር ተነድፌ ...
ተነዳድፌ ....
ንብ በልታኝ ....
ተርብ አቂላኝ .... እያለ የሳድስ ግጥም ሲደረድር አስተዋልኩ :: እኔን የገረመኝ እንዲህ የነሆለለው የፌስ ቡክ አዲክትድ በመሆኑ ነው ወይስ የውነት የምታፈቅረው ልጅ አግኝቶ ነው ? ፍቅር እኮ እንደ ታንጎ አይነት ዳንስ ነው መተሻሸት መተያየት ጠረን ለጠረን መፈላለግን ግድ ይላል :: ጠንቀቅ በል ወገኔ አሞሌ ጨው ሲያሳዩህ ጭብጦህን የምታስረክብ ስለመሆንክ ውሎህን ያየ ይረዳል :: ምክር ነው :: በሉ እስኪ ሰላም ያገናኘን :: ቻው ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ፍርንትት

ኮትኳች

Joined: 06 Dec 2010
Posts: 457

PostPosted: Fri Apr 29, 2011 1:52 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
" አንዱ እዚህ ዋርካ ላይ
በፌስ ቡክ ፍቅር ተነድፌ ...
ተነዳድፌ ....
ንብ በልታኝ ....
ተርብ አቂላኝ .... እያለ የሳድስ ግጥም ሲደረድር አስተዋልኩ ::
ቻው ::

እረ ክቡራን አንተም ? እስኪ የሳድስ ግጥም የሆኑትን ግጥሞቸን አሳየኝ Rolling Eyes ተው እንጅ ትልቅ ሰው ነኝ ስትል አልነበረም : የጎዤውን ግጥምማ የሳድስ አትላቸውም እስኪ አንድ አምጣ አሁን ?? አንተና ሾተል ግን የሳድስም ብትሞክሩ እኔ አበረታታችኍለሁ Laughing

እረ ክቡራን እንዴት ነህ ግን ተጠፋፋን እኮ ባክህ : ዛሬ ሾተልህን ሳለቃልቀው : ስቀጠቅጠው ; ሳንቀጠቅጠውና ሳሰቃጥጠው ዋልኩኝ እልሀለሁ Laughing

ደህና እደር በል

ጎዤው ነኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 7076
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Fri Apr 29, 2011 2:11 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
" Very Happy አንዱ እዚህ ዋርካ ላይ
በፌስ ቡክ ፍቅር ተነድፌ ...
ተነዳድፌ ....
ንብ በልታኝ ....
ተርብ አቂላኝ .... እያለ የሳድስ ግጥም ሲደረድር አስተዋልኩ :: እኔን የገረመኝ እንዲህ የነሆለለው የፌስ ቡክ አዲክትድ በመሆኑ ነው ወይስ የውነት የምታፈቅረው ልጅ አግኝቶ ነው ? ፍቅር እኮ እንደ ታንጎ አይነት ዳንስ ነው መተሻሸት መተያየት ጠረን ለጠረን መፈላለግን ግድ ይላል :: ጠንቀቅ በል ወገኔ አሞሌ ጨው ሲያሳዩህ ጭብጦህን የምታስረክብ ስለመሆንክ ውሎህን ያየ ይረዳል :: ምክር ነው :: በሉ እስኪ ሰላም ያገናኘን :: ቻው ::

ለራሴ ስዞር ውዬና ከጉዋደኞቼ ጋር ያገር ባህል ሙዚቃን ከፍተን ስንውረገረግ አምሽተን ድክም ብሎኝ እቤቴ ሳይክሌን እየነዳሁ የገባሁት አሁን በቅርብ ጊዜ ቢሆንም ደክሞኝ ልተኛ ስል ነበር ወንድማችን ክቡራን የጻፍከውን እንደ ሞኝ ሳላስበው በሳቅ የፈረስኩበትን ጽሁፍህን ያነበብኩት ::

ዋው ትናገረዋለኽ ነው የሚባለው ::ለሊቴን ለሊት አደረከው ::

ይኼንን ፍናፍንት የሚሉትን ከብት ሳጫውተው ነበር የዋልኩት አንተም ልክ ልኩን ነገርከው ::እስቲ ይታይኽ ስሙን ሳትጽፍ ስለ ከብትነቱ ብትጽፍም ከብት በአሽሙርም ይሁን በቅኔ ስለከብትነቱ ሲናገሩ ከሰማ ዘሎ እኔን ነው ብሎ ስለእሱ መጻፉን ስለሚያውቅ ይኼ ከብት ዘሎ ገብቶ መልስ መለሰ ::ስራውን ያውቃታላ ::

ደግሞ በእውቀቱ ስለማይተማመንና ደደብነቱን ስለሚያውቅ ሞቶ ተቀብሮ ሳለ ልጋደል ብሎ በጣረሞቱ ይንበጫረቃል ::

እኔ እንደ ፍናፍንት ግጥም ያለ ደካማ ግጥም ተብዬ በህይወቴ አንብቤ አላውቅም ::ግን የሚገርመኝ ኮንፊደንሱ ::የሆነ የሌባ ልጅ ሌባ ስለሆነ ድርቅ ሲል ደግሞ አይጣል ነው ::

እና በሰአት እንደ ተጠመደ ፈንጂ ቀስ እያንል ልንፈነዳዳለት ነው ::

ሶርይ ካላለ ፍናፍንት አለቀለት ::ሳንደርስበት ደርሶብን የለ አንጎሉን እንደ ሀዲስ 1 ከጥቅም ውጭ እናደርገዋለን ::

ሾተል ነን .......በፌስ ቡክ ቺክ ጠብሼ ጠብሼ ....ጡት መስያዣ ከሚኒስከርት ተላብሼ ተላብሼ ብሎ ፍናፍንት ገጠመ ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Sun May 01, 2011 12:35 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም የተከበሩ አንባቢ እንደው የግብዝ ሰዎች ጉዳይ ነገር አሳስቦኝ እርሶም አልጻፉት ይሆናል እንጂ እንደኔ አሳስቦዎት ወይም አጋጥሞዎት ይሆናል ብዬ ላዋይዎት መጣሁ :: በውነት ነው የምልዎት ከሚያውቁት አምስት ሰዎች አንዱ ግብዝና ራሱን ከፍ አድርጎ ማየት ወይም ማሳየት የሚወድ ነው :; የኔ የግኑኝነት ስታቲክስ ያንን ይላል :: አንድ ጔደኛ አለኝ ስልክ እያወራ ባጋጣሚ ስልኩ ቢቌረጥ ...ጥፋቱ ከኔ ነው አይልም ...."ምን የማይረባ ስልክ ትገዙና በየቦታው የሰው ጭወታ ታቆረፍዳላችሁ እያለ ይነጫነጫል :: ኢሊቬተር ውስጥ ሆኖም ስልኩ ቢቌረጥ የሚኮነነው የርሶ ስልክ ነው :: እርሱ ኤየር ፖርት ሆኖ ስልክ ቢቌረጥ ጥፋቱ የርሶ ነው :: የርሱ ስልክ ሁሌም እንደበሸረች ነው ( አብሽሮን ልብ ይሏል ) :: በዚህ የፋሲካ ሰሞን የታዘብኩትን አንድ አንድ ገጠመኜን ላዋይዎ :: የፋሲካ እለት አንድ ቤት እጋበዝና ወደ ከሰአቱ አካባቢ እደርሳለሁ :: መቼም ፋሲካ ነው ሁሉም በቤቱ እንደ አቅሙ ደግሷል የፋሲካ እለት ደግ የማይሆን ማን አለ ? በቤቱ ውስጥ አንድ 10 የምንሆን ሰዎች አለን : ካንድ ሶስት ሰዎች በስተቀር (እኔን ጨምሮ ) ቀሪዎቹ በሙሉ ዘመዳሞች ናቸው :: እኔን የጋበዘችኝ የባለቤቱ ሚስት እህት ናት :: ትውውቃችን የቆየ ነው :: የቤቱን አባወራ በዝና እንጂ ባይን አይቼው አላውቅም :: በተዋወቅን ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጅንን መሆኑ ገባኝ :: አውቃለሁ ባይ ነው :: እህትየው ( እቺ የኔ ጔደኛ ) ዝናውን ሁሌም ከፍ አድርጋ ነው የምታወራው ) አገር ቤት ትልቅ ቦታ እንደነበረው የተማረ እንደመነበር መንግስት ሙያውን ስለሚፈልገው ትልቅ ቦታ ላይ እንዳሰቅመጠውና በሺዎች የሚቆጠር ብር በወር ይከፍለው እንደነበር ደጋግማ አጫውታኛለች :: እኔማ አንዳንዴ ስለኔ ንገሪ ብሎ "ስፖክስ ውመን " አድርጔት ይሆን እንዴ ብዬ እስከመጠራጠር እደርሳለሁ :: ክፋቱ ደሞ እዚህ አገር መጥቶ የተቀጠረው ሆቴል ቤት ውስጥ ነው :: ጔደኛዬ እንደነገረችኝ ድሮም የፋብሪካ ማናጀር ነበር አሁን ደሞ ማርየት ሆቴል ውስጥ ማናጀር ነው ብላኛለች ( ፍሮንት ደሥክ ነው የሚሰራው ልትለኝ ግን አልፈለገችም ) :: ያም ሆነ ይህ ግን ቡዙ የተባለለትን ሰውዬ ዛሬ ባይነ ስጋ አየሁት :: ከሚናግርበት የማይናገርበት ይበልጣል :: ሁሉም ሰው ስቆ ሲጨርስ እሱ ይስቃል :: ተወርቶ ያለቀለትን ጨዋታ መልሶ ያመጣና እንደ አዲስ እንዲወራ ያደርጋል :: የቤቱ አባወራ የመሆኑን ያህል የጨዋታው መዘውርም በሱ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ፊር ፊር ስል በስል አይኖቼ ወጋሁት :: ለሎች ፈታ ብዬ የምጫወተውን ያህል እሱ በሚጠይቃቸው ወይም በሚያነሳቸው ሀሳቦች ላይ "ቦይኮት " አደረኩኝ :: እግዚአብኄር ምስክሬ ነው እጥ ክፍሌ ሆኖ ትእቢተኛ ሰው አልወድም :: ብሞትም የሚገድሉኝ የትእቢተኛ እጆች ናቸው :: ሩህሩህና ሀምብል ሰው እኔን ለመግደል እጁ አይታዘዝለትም :: ይሄን በኮንፊደስ እነግርዎታለሁ የተከበሩ አንባቢ :: ጨዋታው ሞቅ ደመቅ እያለ ሴቶቹ ምግብ ሲያቀራርቡ የጔደኛዬ እህት ደሞ ቡናውን ማንከሸከሽ ጀመረች :: የአእውደ አመት ሙዚቃ ተክፈተ :: ቤቱ ባውዳ ዐመት አድባር ተሞላ :: " በሉ እንግዲህ የምትችሉትን ያዙ " ተብለን የቤቱ ባለቤት እየመራችን ምግብ ማንሳት ተጀመረ :: በኌላ ዘመድ አዝማዱ አይ መጀመሪያ ስሙን ጠርተው አባወራው ( ጅንኑ ሰውዬ ) ያንሳ አሉ :: እሱ ሳያነሳ እኛ አናነሳም አሉ :: ሁላችንም ተስማማን " ግርማ አንሳ ... ግርማ አንተ ጀምርልን .." አሉ ሌሎችም እየተቀባበሉ ..." ግርምዬ አንሳ እንጂ " አለች ባገር ልብስ ያሸበረቀችው ባለቤቱ ..." ግርማ ሆዬ በላሁ ብሎ እምቢኝ አለ :: " የለም መጀመሪያ እንግዳ ያንሳ እንግዳ ይከበራል ." ..አለ እንደ መፈላሰፍ እየቃጣው :: ሌሎች ደሞ አንተ ቅደም አንተ አንሳ አሉ እየተቀባበሉ >>> አንዷ እንደ ዶልፊን የሞጠመጠች ሹል አፍ ደሞ እንደውም በጸሎት አንተ ባርክልን አለችው :: ሳቄ መጥቶ ትን ሲለኝ ግርማ በጭረፍታ አይቶ ክፉኛ ገላመጠኝ :: መጀመሪያም አልጣምኩትም ንበር አሁን ግን ለየለት :: Very Happy Very Happy " እረ ግርምየ " ብላ እየተባለ ሲለምንና እኛም ያለቤታችን በምንተ - እፍረት ስንጋብዘው አጅሬ በመለመኑ ብቻ መንፈሱ ሀሴት ያገኘችዋና የካንጊሀም ክብርን ያጎናጭፈችው ውስጥዊ ክብሩን እሺ ማሰኝት አቅቶት አሁን በልቻለሁ በሚለው አቌሙ ጸና :: ሌሎቻችችን ቀልጠፍ አያለን ከወጡም ከዶሮውም ከእንቁላሉም መቌደሻውን ሁሉ ሳይቀር ጨለፍነው :: ግርማ መቌደሻውን የወሰደውን ሳህን ሲሰልል በጥንቃቄ አየሁት :: ደግነቱ እኔ አይደለሁም :: ወላዲት አምላክን አሁን አይለቀኝም ነበር :: Very Happy ያታያችሁ እስኪ ..እንግዳ እቤት ጋብዛችሁ ያውም በፋሲካ ምድር አልበላም ማለት ምን አይነት ፈሊጥ ነው ?? ምግብ አንሷል እንዳይባል ያለው ምግብ ..ለሌላ ሁለተኛ ዙር ይበቃል :: የቻልነውን ያህል በልተን አመስግነን ገበታ ከፍ ማለት ሲጀምርና የተቆላው ቡና ሊቀራረብ ዝግጅቱ ቡና ለመጠጣት ስንዘገጃጅ ሲጀምር አልበላም ያለው አባ ወራ ግርማ ትሪ ይዞ ከወጡቹ አይነት እየጨለፈ ማውጣት ጀመረ ...ከዛ ግርምዬ ምነው ብላ እንጂ እያለች ስትለምነው የነበረችዋን ባለቤቱን ባለሙያ የሆነውን አቦል ቡና አፍልታ እንዳታጠጣን በጥቅሻ ጠራትና አጠገቡ እንድትቀመጥ ምልክት ሰጣት :: በንግዳ ፊት ልታሳፍረው ስላልፈለገች እንጂ ሁኔታው ደስ ያላት አይመስለኝም :: እኛ አጃችን ተጣጥበን ቡና ስንጠብቅ ክላሲካል የመሰለ ሙዚቃ ተከፈተና የሮሚዮና ጁሊየት የፍቅር ታሪክ በሁለቱ ባልና ሚስቶች መሰራት ተጀመረ :: አባ ወራ ግርማ በእጅሽ እንዳትጎርሺ አይነት ትእዛዝ ቀስ ብሎ ሹክ አላት መሰለኝ እጇን ወደ ኈላ አድርጋ ግርምዬ አንድ ለሱ እየጎረስ አንድ ለሷ ደግሞ ያጎርሳት ጀመር :: የፈረድብን እኛ እነሱ ተጎራሰው እስኪጨርሱ ሳንወድ በግድ የከፈቱልንን የራሳቸውን ቪዲዮ መክስከስ ጀመርን :: የእኔ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ታዳሚዎችም የግብዣ ሙድ ሳይተን አልቀረም :: እንደገባኝ ሊያስተላልፍልን የነበረው አንድ መልክት ነበር :: ለቤቱም ለላውደ አመቱም ሊሚስቱም ቢቻል ደሞ ለትንሳኤውም ዛሬ "አውራው ዶሮው እኔ ነኝ የሚል :: እርግጠኛ ነኝ ብቻችውን ሲሆኑ እንዲህ እሷ እጇን ወደ ኌሊት የታሰረች መስላ እየቀረበች አይጎራረሱም :: አረ ለመሆኑ መቼ ተገናኝተውስ ? አንዳንዱ እኮ ሚስት ጥዋት ለስራ ወጥታ ማታ ስትገባ ባል ደሞ ለምሽት ስራ ሻንጣውን ከሽፎ ይወጣል :: ምናልባት የሚገናኙት መኪናቸውን የሚያቆሙበት ፓርኪንግ ቦታ ላይ ይሆናል :: ለማንኛውም ግን ላመት በአሉ ቤታቸውን ብቻ ሳይሆን ልባቸውንም መንፈሳቸውን ከፍተው ቁጭ ብድግ ብለው ብሉልኝ ጠጡልኝ እያሉ ከልባቸው ጠብ እርገፍ እያሉ የሚያስተናግዱ ቡዙ ጔደኞችንም አፍርቻለሁ :: ሸማ በየፈርጁ እንደሚለበስ ጔደኝነትም በየፈርጁ አለን ለማለት ነው :: መልካም የበአል ሰሞነኛ ይሁንልዎት ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Thu May 12, 2011 7:39 pm    Post subject: Reply with quote

ከጅብ ጅማት ክራር አሰርቼ ...
ባቲና አምባሰል ልጫወት ጔጉቼ ...
ቅኝት ብቅያይር ...ብውጥር ባላላ ...
የሚወጣው ሁሉ እንብላ ....እንብላ .....

ጠይና ይስጥልኝ የተከበሩ አንባቢዬ ....እቺን ከላይ ያነብብዋትን ስንኝ ያገኘሁት ከማስታወሻ ደብተሬ ላይ ነው :: ማን እንደጻፈውና ከየት እንዳገኘኌት እስካሁን አላወኩም :: ደብተሬ ላይ ግን አስፍሬታለሁ :: ምናልባት እኮ የጻፍኩት እኔም ልሆን እችላለሁ ....አንዳንዼ በኔና በርሶ መሀል ይቅር እንጂ ከሰማይ ይሁን ከተራራ የሚወርዱ መገለጾች አሉኝ :: Very Happy ዳሩ ምን ያደርጋል ነቢይ ባገሩ አልተከበረ ሆኖ እንጂ ... ብቻ ግጥሙ ግጥም ነው :: የገጠመ :: ስለገረመችኝ እዚ አመጣኌት :: ጸሀፊውን ካወኩት .. የተከበሩ አንባቢ አንድ ይበሉኝ :: አለበለዛ የኔ ነው ልበል መሰለኘ .... Cool ሰላም ይሁኑ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sat May 14, 2011 2:55 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ከጅብ ጅማት ክራር አሰርቼ ...
ባቲና አምባሰል ልጫወት ጔጉቼ ...
ቅኝት ብቅያይር ...ብውጥር ባላላ ...
የሚወጣው ሁሉ እንብላ ....እንብላ .....

ጠይና ይስጥልኝ የተከበሩ አንባቢዬ ....እቺን ከላይ ያነብብዋትን ስንኝ ያገኘሁት ከማስታወሻ ደብተሬ ላይ ነው :: ማን እንደጻፈውና ከየት እንዳገኘኌት እስካሁን አላወኩም :: ደብተሬ ላይ ግን አስፍሬታለሁ :: ምናልባት እኮ የጻፍኩት እኔም ልሆን እችላለሁ ....አንዳንዼ በኔና በርሶ መሀል ይቅር እንጂ ከሰማይ ይሁን ከተራራ የሚወርዱ መገለጾች አሉኝ :: Very Happy ዳሩ ምን ያደርጋል ነቢይ ባገሩ አልተከበረ ሆኖ እንጂ ... ብቻ ግጥሙ ግጥም ነው :: የገጠመ :: ስለገረመችኝ እዚ አመጣኌት :: ጸሀፊውን ካወኩት .. የተከበሩ አንባቢ አንድ ይበሉኝ :: አለበለዛ የኔ ነው ልበል መሰለኘ .... Cool ሰላም ይሁኑ ::ይሁን ግድ የለም ከየትም ጂማቱ

ከጂብ ወይ ከአህያ ቆዳ መሰራቱ

አይደለም ክፋቱ :

እኔስ ያስገረመኝ ...

ጂብም ዘፈን ለምዶ ክራር መቃኘቱ

አምባሰል ትዝታን ባቲን መጫወቱ ::
ሞንሟናው ነኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Mon May 16, 2011 12:48 pm    Post subject: Reply with quote

እንደምናሉ የተከበሩ አንባቢ እቺን ነገር ካገር ቤት ዜና ከሚያስተላልፍ ጋዜጠኛ ነው የሰማሁት ...አባይን ለመገደብ ምን ያህል ሲሚንቶ እንደሚያስፈልግ ያውቃሉ ...? 100 ሚሊዮን ኩንታል ሲሚንቶ Exclamation ( መቶ ሚሊዮን ኩንታል ሲል ..ስንዴ መሰለው እንዴ ..ልል ነበር ይቅርታ . Very Happy ) ያስፈልጋል :: ዘርዘር ያለ ነገር ሳገኝ ይዤልዎት እመጣለሁ :: Cool
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Mon May 16, 2011 1:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሞንማናው እንደገጠመው ::

Quote:
ይሁን ግድ የለም ከየትም ጂማቱ

ከጂብ ወይ ከአህያ ቆዳ መሰራቱ

አይደለም ክፋቱ :

እኔስ ያስገረመኝ ...

ጂብም ዘፈን ለምዶ ክራር መቃኘቱ

አምባሰል ትዝታን ባቲን መጫወቱ ::

ሸጋ ግጥም ናት ይልመድብህ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Tue May 24, 2011 7:11 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተከበሩ አንባብዬ አንዳንድ ቁርጭራጭ ገጠመኝቼን በቁርጥራጭ ወረቅት ላይ ጫረ ጫር አደርግና እዚህ መጥቼ ካላሳፈርኩት ገጠመኞች በዛው እየተነኑ ይጠፋሉ :: ጥሩ ጥሩ ሀሳብ ማፍለቂያ የሆኑ እውነተኛ ገጠመኞችን ዳኪሜንትድ አድርጎ ማስቀመጥ አይከፋም ስል እመክርዎታለሁ :: ማን ያውቃል አንድ ቀን እኮ ተሰባስበው ድንክዬ መድብል ይወጣቸው ይሆናል ::

እነሆ በረከት ....
የስልክ መልክት ማዳመጫዬን ቁጥር ስመታ ድምጿን አንጂ አይቻት የማላውቃት ኦፕሬተር ፈጥና መጣች ::
You have 7 unheard massages. Main menu, to hear your massage click one to save it press 7, to discard it press 4, to hear this menu again press 9 to end this call press #, አንድ ቁጥርን ተጫንኩ :: አይናፋርዋና ተሽኮርኮማሚዋ ኢቫንጂለን ናት :: ከሰውነቷ መፈርጠምና ትውልዷ ናይጄሪያ ኢቡ ስቴት መሆኑን ኮርታ ባትናገር ኖሮ ከኢሊባቦር ቴፒ ነው የመጣችው የአገሬ ልጅ ብዬ ባስተዋቀኴችሁ ነበር ... ኢቫንጀሊን ግን ናይጄሪያዊ አንጂ ሌላ ልትሆን አትችልም መሆንም አትፈልግም ;: ለጭዋታ ብዬ እንኴን ኢሩባ ወይም አውሳ ነሽ ስላት አትወድም ፈጥና መልስ ትሰጣለች ..I am from Ibu state...ኢቡነት ከናይጀሪያውነቷ በላይ ያኮራታል :: ግን ህይወት አገጣጠማችና ጔደኛሞች ሆንን :: አንዳንዼ ስልክ ትደውልልኛለች :: ስታጣኝ አትበሳጭም ሁሌ ቀና መልስ ትተዋለች ...ስልክህን ያላነሳሀው ስራ እየሰራህ ይሆናል ...መንገድ ላይ መሆን አለብህ ...ወይም ስብሰባ ላይ ነህ ...ወይም ጥናት ላይ ነህ ....በቃ ይሄ ነው መልክቷ :: ይሄ ጉዳይ በራሱ ይገርመኛል ...በውነት ሁሌ እንደዚህ ነው የምታስበው ማለት ነው ?? በጣም እየተቀራረብን ስንመጣ ኢትዮጵያዊት ጔደኛ እንዳለኝ ነግሬአታለሁ :: ግን ያንን በመልክቷ ላይ አታነሳም :: እነደ መሽኮርመም አለችና ሳቀች :: ምንም አላለችም :: ትቧጭረኝ ይሆን ብዬ ነበር አላደረግችውም :.. ወይስ ቀጠሮ አለኝ ብላ ትሄድ ይሆን .. ብዬ ገመትኩ ...እሱንም አላደረገቸውም :: ቀና ብላ አለችና አየችኝ ...ምን ልትለኝ ይሆን ..?
I wanted to be your freind...that is all.. ደስ አለኝ :: እኔም እንድዛው አልኴት ...likewise...
ከዛም ፍሬንዲሺፓችን ህይወትንና ውበትን እየተበላሰ ቀጠለ :: አንድ ቀን ሲያቀብጠኝ ፉፉ እንደምወድ ተናገርኩ :: "ፉፉ እኮ ባገራችን ገንፎ ነው ገንፎ ሁሌም አይሰራም :: ሴቶች ሲወልዱ ብቻ ካልሆነ አይገኝም ውድ ነው አልኩና የፉፉን ታላቅነት ከገንፎ ጋር እያመሳከርኩ አስረድኍት :: ኢቫንጀሊን በገለጽኩላት ታሪክ ልቧ ክፉኛ አዘነ :: ለካ ሰውነቴ ( ከሷ ግዙፍ አካል ጋር ሲተያይ ) እሳት የየለበለበው ግንድ የመሰለው ማግኘት ያለበትን ፉፉ ባለማግኘትቱ ነው ብላ ክፉኛ አዘነችልኝ :: ሰከንድ ሳትቆይ ስልኴን አወጣችና ቁጥር መምታት ጀመረች ::
የት እየደውልሽ ነው ?
አንድ የማውቀው የናይጀሪያንስ ሬስቶራንት አለ ...በስንት ሰአት እንደሚዘጉ ቼክ ላደርግ ነው ...?"

..በስንት ሰአት ..." ተናግሬ ሳልጭረስ አቌረጠችኝ ::

"አዎ 6.00 PM ነው የሚዘጉት .. እንሂድ የምተወደው ፉፉ እዛ አለ :: "
መቼም ለሞራልም ብዬ ለጨዋታም ማጣፈጫም ብዬ ንግግር ባደርግ እቺ ኢቫንጀሊን አይገባትም :: ባመጣሁት ቀልድ ተበሳጨሁ :: አቦ አፍሪካውያን አራድነት የሚባል ነገር የለባቸውም መግደርደርም አያውቁም ደሞም አያስገደረድሩም :: ባፋንኩሎ ::
"ሬስቶራንት ገብተን ከፉፉ ጋር በጎድጔዳ ሳህን ሙቅ ውሀ አብሮ ቀረበልን ::
"ምንድነው ይሄ ኢቫንጀሊን ? "
ሳቀች :: ጥያቄዬ ሁሉ ያስቃታል ::
" ጣቶችህን የምትነክረበት ነው " አለችኝ በባህላችን ፉፉ በጅ ነው የሚበላው አንዴ ከተባለ በኈላ ጣቶችህን በሙቅ ውሀ ነከር ታደርጋለህ :: ከዛ ትበላለህ " ስታደርግ አየሁ ::
ፉፉ በፍየል ስጋ አጣጥሜ በልቼ ጠገብኩ :: እሷ ስለወሰደችኝና ሀሳቡንም ስላመጣች ግብዣውም የሷ ይሆናል ብዬ ተስፋ እድርጌ ነበር ..ሂሳቡን አሳላፊው ሲያመጣ ኢትዮጵያዊ ባህሌ አስገድድኝ ..
"እኔ ነኝ የምክፈለው ...አይሆንም ኢቫጅሊን " አልኩ :: የጠበኩት "" አይ እንተ ለዚህ ቤት እንግዳ ነህ ደሞ እኔ ነኝ ሀሳቡን ያመጣሁት ትለኝ ይሆናል ብዬ ነበር ..." ኢቫንጀሊን ግን ሳቅ ብላ ቢሉን አቀበለችኝ :: ይድፋሽ :: Very Happy
ወደ መኪናችን ስንመለስ የከፈልኩት 60 ዶላር ውስጤን አንዝሮት ነበር :: ንዝረት :: ኢቫንጀሊን ግን የበላነው ፉፉ ሀይ ክላስ ነው እያለች ደስ ይላት ጀምሯል ::
ቆይ ጠብቂ ... ( ይቀጥላል ) ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Tue May 24, 2011 1:57 pm    Post subject: Reply with quote

አምባሰል ሙዚቃና መርአዊ ስጦት :: እቺን ጠቅ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue May 24, 2011 2:43 pm    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
አምባሰል ሙዚቃና መርአዊ ስጦት :: እቺን ጠቅ ::

አቶ ክቡራን እንዴት ነው ነገሩ ወያኔወች ስትባሉ ህግና ደንብም አክብራችሁስ አትውቁም ...ይሄ እኮ የፖለቲካ መድረክ ነው ...ዋርካ ስነ -ጽሁፍ ወይም ከኔዋ እስካገኝሽ ድረስ አጠገብ ወስደህ አትለጥፍም ....በዚያውም ስለ ፍቅርና እንዴት ቺክ እንደሚጠበስ ብታነብ ይሻላል ብዬ ነው ....እዚያች ሬስቶራንት አርብ አርብ እየሄዱ ድድ ቢያሰጡ እኮ አጠባበሱን ካላወቁበት አይሆንም Wink Laughing

ለአስተያየት ያህል ነው Rolling Eyes

የተሞናሞነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Tue May 24, 2011 5:57 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅ ...ሲሉ ሰምታ የፈረጃ ዶሮ ሱሳይድ አደረገች አለ አንዱ :: ወገኛ ::

ሙና እንደጻፈ(ች)ው:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
አምባሰል ሙዚቃና መርአዊ ስጦት :: እቺን ጠቅ ::

አቶ ክቡራን እንዴት ነው ነገሩ ወያኔወች ስትባሉ ህግና ደንብም አክብራችሁስ አትውቁም ...ይሄ እኮ የፖለቲካ መድረክ ነው ...ዋርካ ስነ -ጽሁፍ ወይም ከኔዋ እስካገኝሽ ድረስ አጠገብ ወስደህ አትለጥፍም ....በዚያውም ስለ ፍቅርና እንዴት ቺክ እንደሚጠበስ ብታነብ ይሻላል ብዬ ነው ....እዚያች ሬስቶራንት አርብ አርብ እየሄዱ ድድ ቢያሰጡ እኮ አጠባበሱን ካላወቁበት አይሆንም Wink Laughing

ለአስተያየት ያህል ነው Rolling Eyes

የተሞናሞነው

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Sat May 28, 2011 2:32 am    Post subject: Reply with quote

ኴሷ ኴሳ ....ኢቫንጀሊን ኢጉዋ ዛሬ ልትደንስ ነው :: በስልክ የተወችልኝን መልክት ሰማሁት ቢኢቡኛ የተቃኘ እንጊሊዝኛ ....በፉፉ ቅባት ከወዛ ከንፈር በግድ እየተላቀቀ የሚወረውር የሆሄዎች እንክብል ... ወረድ ቀጠን ወፈር ጎረነን ደሞ ሳሳ እያለ ከጥጥ ባዘቶ እየተፈለቀቀ የሚወጣ አይነት የንጊሊዝኛ ስዋሰው በኢቡአዊ ዝማሬ መወረድ ጀመረ :: "Hallo , on July 4 there is a dance program in my church , I am going to present my country dance I will be dancing ( ኴሳ ..ኳሳ እሪ እሪ ሪሪሪሪሪ ..ኢቫንጀሊን ዛሬ ልትደንስ ነው :Smile ሰማያዊ ዝማሬ በሚዘመርበት መንፈሳዊ ውዳሴ በሚወደስበት ስብከት በሰንበት ከበሚሰበክበት የቤተክርሲቲያን መድረክ የኢቡዋ ወይዘሮ ኢቫንጀሊን ኡግዋ በናይጀሪያንኛ ሪትም አሻም አሻም ልትልበት ነው :: መልክቱ አላቆመም ... " I want you to be there for me.. ," ( ይሄኛው ትእዛዝ ነው ..እንደ ሰውነቷ ፍርጥም ያለ :: ከዚህ በፊት አፈረጣጠሟን አይቼ ኢቫንጀሊንን በፍቅር ሀይል እንጂ በጠብ እንደማላሸንፋት ለራሴ ቃል ገብቻለሁ :: ጡቶቿ ግን እንደ ራሺያ ሚሳይል የቆሙ እንደ ሜሎን የተለቁ ናቸው :: አናዳንዴ እንዴት ብትይዛቸው ነው እነዚህ መንትዮቿ እንደዚህ የደደሩት እላለሁ :: ትልቁ ማሸነፍያዋ እሱ ነው :: መልክቱ አላበቃም :: " please mark your calander . The internace is 60us"" ምን ?? በለው በለው , 60 ዶላር ? የመግቢያውን ዋጋ ስሰማ እጢዬ ዱብ አለ :: ለመግቢያ 60 ብር ...ቀልዱ አልበዛም እንዴ ኢቫንጀሊን ..? ነፍሱን ይማረውና ያገሬ ምርጥ ዘፋኝ ጥላሁን ገሰሰ ኮንሰርት ሲያሳይ 30 ዶላር ብቻ እኮ ነው ያስከፈለኝ :: ያንቺው በዛ የኛ ቡዙነሽ .... እንዴት ነው የመንግሰተ ሰማያት ትኬትም አብሮ ይሰጣል እንደ ..? እቺ ልጅ እኮ 60 ብርን መቀለጃ አደረገችው አሁንስ :: ባለፈው እንደ ቀልድ ፉፉ የምርጦች ምርጥ ምግብ ነው ብዬ ሲያቀብጠኝ ተናግሬ 60 ብሬን እየተቃጠልኩ አስቀምጭ ወጣሁ :: ለዛውም እኮ እሱ አልበቃ ብሏት እንደት ነው ግራትቱይድ ላስተናጋጁ ሰጠሀው ወይ ብላኛለች ...." አይ እኛ ባገራችን ግራቲቱዩድ ለወንዶች አንሰጥም ለሴት አስተናጋጅ ካልሆነ ብዬ አፏን አሼብብኣአት እንጂ በዋሌቴ ላይ ቆርጣ እንደተነሳች ደረሸባታለሁ :: ሞኝሺን ፈልጊ ብቻሽን ብተፈልጊ ተሽከርከሪበት እንጂ ይሄን ያህል ብር ከፍዬስ አልመጣም :: የገንዘቡን ልክ ካወኩ በኌላ መልክት ቴክስት ማድረግ ጀመርኩ :: በልቤ ግን ፕላን B እያወጠነጠንኩ ነው :: ( የሚቀጥል )
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 12, 13, 14  Next
Page 3 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia