WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች ...
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5 ... 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Jun 14, 2011 6:14 pm    Post subject: Reply with quote

ኢትዮጵያዊ ማነው ..? ኢትዮጵያዊነትስ ምንድነው ??
ካንድ 15 ቀን በፊት በእለተ ቅድሱ አርብ እለት ባንድ ሬስቶራንት ውስጥ ቁጭ ብዬ እራት በልቼ ከመድረክ የሚወጣውን የዘፋኙን ጣእመ ዜማ እየሰማሁ በሀሳብ ውስጥ ሆኜ ተጫዋቹን አስተውለው ነበር :: ዘፋኝ ሲጫወት አይኑን ጭፍኖ በስሜት ሆኖ ነው ... የታዳሚዎቹ የአድናቆት ጭብጨባና ሙገሳ ወይም የባለጌዎች ዘለፋና ሽሙጥ ለሱ ምኑን አይደለም :: ደስ ብሎት ኪይ ቦርዱን እየመታ እጆቹን ወደ ላይ እየሰቀለ በግሮቹ ቲዊስት ግራና ቀኝ እያለ ይጫወታል ;; ካንዱ ሙዚቃ ወደ ሌላው ሲሄድ እንኴን ተጨበጨብልኝ ብሎም ታዳሚውን ቀና ብሎ ሳያይ እንደ ንስር ክንፍ ሀይሉን እያደስ የሚቀጥለውን ሙዚቃውን ይሞዝቀዋል :: ፍቅርን ይቃኛል ...ኢትዮጵያን ያሞግሳል ...ትዝታን ከስፒክሩ በላይ ተፈጥሮ በሰጠችው ድምጽ ላቡን እያንጠፈጠፈ ይጫወታታል :: የአማርኛ የትግሪኛ የኦሮሞኛ የቆቱኛ ...ሁሉንም ያለ ችግር ይላቸዋል :: በስሜት : : የቤቱ ባለቤት ባይከፍለውም መጫወቱ እርካታ እንደሰጠው መቶ በመቶ እርግጠኛ ነበርኩ :: ሌላው ነገር ሁሉ ለርሱ ትርፍ ነው :: መጣሁ :: የመድረክ ሰው ሲጫወታቸው ከነበሩት ሙዚቃዎች አንዱ ይሄ ነበር ...ቀበጥባጣ ወጣት ...

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Jun 28, 2011 5:35 pm    Post subject: Reply with quote

ማነው ኢትዮጵያዊ ? ብዬ እቺን ርእስ ጀምሬ ኢትዮጵያዊ ፍለጋ ስኴትን ደከሜ ተመለስኩ :: እንደምናሉ የተከበሩ አንባቢ :: ደሞ ወጌን ወጋ ወጋ ላድርገው :: መቼም ሳመር ስልሆነ የሳምንቱ መጨረሻ ሲሆን አመሻሹ ላይ ሌላ ማህበራዊ ግዴታ ከሌለብኝ ወደ አራዳው ሰፈር ብቅ እላለሁ :: የአራዳ ልጆች ዜማ ይናፍቀኛል :: "ሰላም ነው ..? እንዴት ነው ... ሁሉ ነገር አማን ነው ?" መባባሉ ይናፍቀኛል :: ለመብላት የመጣውም እየተወዋቀ "ነፍሴ እንብላ .. ታዲያ እረ አንድ ጉረስ " መባባሉ ባያጎርስም ያጠግባል :: ህይወት በራዳው ሰፈር በአበሾች ጎዳና አርብ ምሽት ትደምቃለች :: የፍቅር ችቦ ይበራል :: ያለውም የተከዘውም የተረፈውም በድምቀቱ ዙሪያ እየዞረ በረከተ አርብን ይካፈላል :: ቅዳሜንም ይጨምራል :: ተረፈረፍ ያለ ጊዜ ያለው ደሞ ሰንብትንም በነ ማሪቱ ሙዚቃ እየተከዘ ያሳልፋል :: በነገራችን ላይ ይርዳው ጤናን በቀደም አየሁት :: ማሪቱ ለገሰ የምታጨወትበት ቤት ይርዳው ዘመነኛውን ዘፈን ይዘፍናል :: የማይቀረው ዘፈን የለም :: የጥንቶቹን ዘፋኞች ዘፈን አስተካክሎ በመጫወት ይታወቃል :: እዚህኛው ሬስቶራንት ከጔደኛዬ ጋር ነበር የሄድነው :: እስክስታ እንደሷ ጎበዝ ባልሆንም ለክፉ አልሰጥም :: እሷ ግን መቃ አንገት ናት ባንገቷና ባይኗ ትሰብቃለች :: አንድ ጊዜ ወሎዬ ነኝ ብላኝ ነበር .. ዘፈን ስትሰማ ያነዝራታል :: ሌላ ጊዜ ደሞ ስለ ጎንደር ስናወራ ሳላእቀው አንዱን የጎንደር ተወላጅ ሳማ እንዴ ጎንደሬ መሆኔን አታውቅም እንዴ ..? ቀስ እያልክ ... ብላ አስጠንቅቃኛለች ...ያህያ አደም አንድ ቀን ኦሮምኛ ሲጫወት ትርጉሙን ነገረችኝ ...ከዛ በኌላ ዘሯን መጠየቅ አቆምኩ :: አንዱ ልጅ ታዲያ ተቀምጠን ስናወራ ፍቃድህ ቢሆን አብረን ከሷ ጋር እንጫወት ብሎ ጠየቀኝ ""ምንም ችግር የለውም ተጫወት "" አልኩት :: ልጅ ኪነት ነበር መሰለኝ ያንዘፈዝፈው ጀመር :: ደረቱን እንደዛ እያንቀጠቀጠ ሲጫወት በልቤ ትንሽ መቅናቴ አልቀረም ...:: Very Happy እኔ ምለው ግን እስክስታ ማለት ትከሻ መምታት አይደለም እንዴ ? ምንድነው እሱ ደረትን እንደ ሴት ልጅ ማርገፍገፍ ..? ከምር እውነቴን ነው :: ...አለማየሁ እሸቴ እንኴን ብሎታል " ትከሻ ወይንዬ ወይን አለም ...ትከሻ ..ትከሻ ....ትከሻ የወይን ሀረጊቱ ነይልኝ በሞቴ ..." ዜማውን ፈልጉና አግኙት ::
እስክስታ ....
በትክሻ ነው የሚመታ ::
Cool እናማ ይሀውላችሁ ይሄ በዚህ እንዳለ ባንድ ወገን ደሞ እስክስታ የሚለማደዱ የሚመስሉ የዘፋኙን ሪትም እየጠበቁ ሊጫወቱ የሚሞክሩ እንደገባኝ ህንድያውያን አሉ :: ሴቷ ሌሎችን እያየች መጫወት ፈልጋለች ..ወንዶቹ ራሳቸውን ላለማስፎገር እያሉ ቀስ አያሉ እስክስታ መስል እስክስታ ይሞካክራሉ ...አንድ ልጅ ደምቆ መጣ :: ደመቀ :: ( አንድ ሰው ሞቅ ብሎት ሲገባ ደመቀ ይላሉ የአራዳ ልጆች :: ) ደሜ የስፖርት ቱታ አድርጎ ነው የመጣው በዚህ ሌላ ዝም ብዬ ሳጠናት ለመሬት በጣም ቅርብ ሆነችብኝ :: ወንበር ስቦ ሳይቀመጥ ሰርግ ቤት የገባ ይመስል በስክስታ ህንዳውያኑን ተቀላቀላቸው :: ሞቅ ያላት ህንዷ ልጅ እንቅስቃሴውና ድፍረቱ ደስ አሰናት መሰለኝ ያገሯን ልጆች ትታ ከሰ ጋር መጫወት ጀመረች :: ደሜም አልተሸነፈም :: እንደ መንበርከክ እያለ ዝቅ ምናምን እያለ ምንሽር ተኴሽ ነኝ አይነትም አያሳየ ( እየተነበረከከ ) ደስ ደስ አሰኛት :: ከልጅቷ ጋር ጥሩ ኬሚስትሪ ያለው ዳንስ ደነሱና ሲጨርሱ ደመቀ ፊቱ ላይ ያለውን ቸብ ያለ ልብ እየጠረገ ወደ ተቀመጥነው አያየ ...ንግግር አይነት ዘለፋ ጀመረ .." ወይ ጉድ ይገርማል ...ሸፋፋ ሁላ አሁን አንቺም ኢትዮጵያዊ ነኝ ትያለሽ ...ድንቄም ኢትዮጵያዊነት ኪስ ማይ አስ ከፈለክ እያንዳንድህ ( ደመቀ ያለውን ነው ..) የውጭ አገር ሰው እዚህ ተነስታ ይሀው የኢትዮጵያ ዘፈን ሲዘፈን ትጨፍራለች እኛ ግን ቁጭ ብለን እንደ መጫወቻ እናያታለን አሰዳቢ ሁሉ ...እዼያ "
...ደሜ ኢትዮጵያዊንትቷ ብልጭ አለባት :: እንግዲህ የደሜ የኢትዮጵያዊነት ትርጉም የኢትዮጵያ ዘፈን ሲዘፈን አብሮ መዝፈን ነው ቁጭ ብለህ ዘፈኑን የምታጣጥም ከሆንክ በሚዘፈነው ዘፈን ትዝታ ውስጥ ገብተህ ከሆንክ አንተ ኢትዮጵያዊ አየደለህም :: ደሜ በሞቅታ ፈረስ እየጋለበ ተናገረው እንጂ ቡዙዎች ኢትዮጵያዊነታችን የሚትናነቀን ስሜታችንን የሚቀሰቅስ ነገር ስናገኝ ነው :: የስፖርት በአል ስናይና ስንሰበሰብ ኢትዮጵያዊነታችን ይመጣል ግን ያንን ለማለትም እርግጠኛም አይደለሁም :: ያሰባብሰበን ማህበራዊ ግዴታችን ነው ? ስለተጋበዝን ነው ? የመግቢያ ትኬት ቀድመን ስለገዛን ነው ? ሚስት ወይ ባል ፍለጋ ነው I am not sure..ለመሆኑ ኢትዮጵያዊ ማነው ኢትዮጵያዊነትስ ምንድነው ? ካአንድ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ጋር ባለፈው ጊዜ ቃለ ምልልስ አደረኩ :: አማራጭ ስለሌለኝ እኔ በኢትዮጵያዊ እምጊሊዝኛ እሱ ደሞ ባሜሪካ እንጊሊዝኛ ውይይቱን አካሄድነው " የስ የስ በለው ነገሩ ግልጽ ነው እየተባባልን ...ያንን ውይይት ጨርስን :: ቶማስ ይባላል " ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኢትዮፕያዊነት አዳኑኝ "" አለኝ : "ለኔ ኢትዮጵያዊነት የሞትና የመኖር ጥያቄ ነበር :: አሜሪካዊ ሆኜ ተወልጄ አሜሪካዊ ሆኔ መኖሬ ወደ ሞት ነበር እየመራኝ የነበረው ::ማህበራዊ ህይወት ያሳዩኝ ኢትዮጵያውያኖች ከነበረብኝ የብቸኝነትና የግለኝነት , የራስ መውደድና የራስ ማምለክ ኢጎ ፈወሱኝ እነሱ ባይደርሱልኝ ኖሮ ራሴን እገድል ነበር " አለኝ :: ቶማስ ይሄን ሲለኝ እንባ አይኖቹ ላይ ሲያቀሩ ባይኔ አይቸዋለሁ :: ምንም ያጣው ነገር የለም :: እዙህ አገር ተወልደው ሱሪያቸውን ወደ ታች ዝቅ አድርገው የውስጥ ፓንታቸውን እያሳዩ በሚሄዱ ወጣቶች በጣም ይቆጫል :: ያዝናል ...ቡዙዎቹን ኮንፎሮንት አድርጎአቸዋል :: "የኢትዮጵያዊነት እሴት አልገባቸውም " ይላል አምርሮ :: አንድ ጊዜ ባሜሪካን ኮርፕ ሁለት ጊዜ ደሞ በራሱ ወጭ ኢትዪጵያ ሄዷል :: እንጊሊዝኛም ያስተምር ነበር :: ኢትዮጵያ ቤቴ እናቴ ናት ይላል :: መቀበሪያዬም ናት ብሎኛል :: በመግቢያዬ ላይ ማነው ኢትዮጵያ ብዬ ነበር :: ቶማስን አገኘሁ :: ከቶማስ ጋር ያደረኩትን ዉይይት እስከማቀርበው ይታገሱኝ የተከበሩ አንባቢዬ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com

Last edited by ክቡራን on Wed Jun 29, 2011 5:35 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገነትናሰሎሞን

ኮትኳች

Joined: 07 Jul 2009
Posts: 245

PostPosted: Tue Jun 28, 2011 8:08 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ .... ወያኔ ሚሊሻውን አዳራሽ ሞልቶ : የሚያወራውና ግጥም መደርደር ስለዚህ የውሽት ህዳሴ መተርተር ዋጋ ቢስ ነው :: ያለፉትን ሥርአቶች ህጸጽ እያነሱ መተችት : የሕዝቡ ከርሀብ ገደል ላይ የሚያድነው የለም ::
http://www.ethiomedia.com/andnen/2640.html
_________________
PROPONENTS OF THE ETHIOPIAN PATRIOTIC ARM STRUGGLE AGAINST WEYANE !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2955

PostPosted: Tue Jun 28, 2011 9:24 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ገነትናሰሎሞን

ዋርካ የህፃናት መዋያ እኮ አይደለም Laughing Laughing ማንንም መሸወድ አይቻልም

1. የቪዲዮው ርእስ ራሱ "ደናን :ያኔና አሁን " የሚል ነው ....የያኔውን ብቻ ቆርጦ ለማቅረብ አያመችም Wink Laughing

2. ቪዲዮው የተቀረፀው ቢያንስ 8 ዓመታት በፊት ነው

4. አካባቢው በድርቅ የሚጠቃና እናንተ የምትደግፏቸው ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱበት ቦታ ነበር

4. ደናን ፕሮጀክት የሚባል ግብረስናይ ድርጅት ተቋቁሞ የኦጋዴን ተራድኦና ልማት ማህበር ከሚባል ሀገር በቀል ድርጅት ; ከግብርና ሚኒስቴር ; ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ; ከሱማሌ ክልል ጤና ቢሮ ....ውሀ ቢሮ ;ከሱማሌ ክልል ፕሬዚደንት ; ዩኒሴፍ ወዘተ ጋር በመተባበር ሁኔታዎቹ ተለውጠዋል

አይደለም አሁን የዛሬ ሁለት አመት የነበረውን ለውጥ ተመልከቱት Wink

Denan:Then and Now...Part-2

የአዞ እንባ ምን ያደርጋል Laughing ......ለወገኖቻቹ አስባቹ ቢሆን ኖሮ ሁለተኛውን ክፍል ታቀርቡ ነበር ....ምንም እንኳን ባትረዷቸውም Razz

ሠላም

ገነትናሰሎሞን እንደጻፈ(ች)ው:
እስኪ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ .... ወያኔ ሚሊሻውን አዳራሽ ሞልቶ : የሚያወራውና ግጥም መደርደር ስለዚህ የውሽት ህዳሴ መተርተር ዋጋ ቢስ ነው :: ያለፉትን ሥርአቶች ህጸጽ እያነሱ መተችት : የሕዝቡ ከርሀብ ገደል ላይ የሚያድነው የለም ::
http://www.ethiomedia.com/andnen/2640.html

_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገነትናሰሎሞን

ኮትኳች

Joined: 07 Jul 2009
Posts: 245

PostPosted: Wed Jun 29, 2011 10:17 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን !
ዳግማዊ :
አዎን ... ቪዲዮው ሁለት ክፍል ነው - የድሮውንና የአሁኑን :: እና አሁን የምትሞግተኝ : ዛሬ የድናንም , የምስራቅ -ኢትዮጵያ ሕዝብ : የእርጎ ባሕር ሆኖለታል ነው የምትለው ?? የትናንት የቢቢሲ ዜናን ሁላችንም ስምተናል :: የምስራቅ አፍሪካ ሕዝብ : ወደ 13 ሚሊዮን የሚሆነው ለከፍተኛ ርሃብ እንደተጋለጠ !! እንዲያውም ቃለ -ምልልስ ሲያደርጉ : 1984 የኢትዮጵያ ርሃብ ሲያዳድር ነበር :: እንዲያው የአንተ ሥራ በዛብህ እንጂ :: የወያኔን ፓሊሲ ትከላክለህ ትዘልቀዋለህ ??
_________________
PROPONENTS OF THE ETHIOPIAN PATRIOTIC ARM STRUGGLE AGAINST WEYANE !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sun Jul 03, 2011 9:48 pm    Post subject: Reply with quote

ማነው ኢትዮጵያዊ ...?

......ካአንድ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ጋር ባለፈው ጊዜ ቃለ ምልልስ አደረኩ :: አማራጭ ስለሌለኝ እኔ በኢትዮጵያዊ እምጊሊዝኛ እሱ ደሞ ባሜሪካ እንጊሊዝኛ ውይይቱን አካሄድነው " የስ የስ በለው ነገሩ ግልጽ ነው እየተባባልን ...ያንን ውይይት ጨርስን :: ቶማስ ይባላል " ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አዳኑኝ "" አለኝ : "ለኔ ኢትዮጵያዊነት የሞትና የመኖር ጥያቄ ነበር :: አሜሪካዊ ሆኜ ተወልጄ አሜሪካዊ ሆኜ መኖሬ ወደ ሞት ነበር እየመራኝ የነበረው ::ማህበራዊ ህይወት ያሳዩኝ ኢትዮጵያውያኖች ከነበረብኝ የብቸኝነት , የግለኝነት , የራስ መውደድና የራስ ማምለክ "ኢጎ " ፈወሱኝ .. እኔነትን አስቀምጨ ለኛን መኖርን አስተማሩኝ ... እነሱ ባይደርሱልኝ ኖሮ ራሴን እገድል ነበር " አለኝ :: ቶማስ ይሄን ሲለኝ እንባ አይኖቹ ላይ ሲያቀሩ ባይኔ በብረቱ አይቸዋለሁ :: እዚህ አገር የተለያዩ ባህላዊ የዳንስ ውዝዋዜዎች ሲዘጋጁ ከፊት መሪ ዳንሰኞች አንዱ ቶማስ ነው :: እንደ ኦሮሞውች ይዘላል ዱላ ይዞ ...አደይ ኢትዮጵያ እያለ ይሸከረከራል እንደ ትግሬዎች ..አንገቱን እየሰበቀ እስክስታ ይመታል እንደ ጎንደሬዎች ....ባይኑ ይሰርቃል እንደ ወለዬዎች ....ያዩት ሁሉ እትፍ እትፍ ካይን ያውጣህ ሲሉት ታዝቤአለሁ :: መድረክ ላይ ቶማስን ያየው ሰው አሜሪካዊ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግረዋል :: ቶማስ ኢትዮጵያዊነትን ሙጥኝ ያለ ጎረምሳ ነው :: ምንም ያጣው ነገር የለም :: እዚህ አገር ተወልደው ሱሪያቸውን ወደ ታች ዝቅ አድርገው የውስጥ ፓንታቸውን እያሳዩ በሚሄዱ ወጣቶች በጣም ይቆጫል :: ይናደዳል :: ያዝናል ...ቡዙዎቹን ፊት ለፊት ኮንፎሮንት አድርጎአቸዋል :: አንድ ጊዜ ታክሲ ውስጥ ጎረምሶች የአሜሪካ ራፕ ሙዚቃ እየሰሙ ሆይ ሆይ ሲሉ ባለ ታክሲውን ሙዚቃውን እንዲያስቆም ነግሮት ልጆቹን ለመሆኑ ትርጉሙ ይገባችኌል ብሎ አፋጧቸዋል :: ቶማስ እንደነገረኝ ሙዚቃው እርግማንና ስድብ የተቀላቀለበት ነበር :: "የኢትዮጵያዊነት እሴት አልገባቸውም " አለኝ አምርሮ :: ባሜሪካን ኮርፕ ፕሮግራም አንድ ጊዜ ሌላ ጊዜ ደሞ በራሱ ወጭ ኢትዪጵያ ሄዷል :: እንጊሊዝኛም ያስተምር ነበር :: ኢትዮጵያ ቤቴ እናቴ ናት ይላል :: መቀበሪያዬም ናት ብሎኛል :: በርእሴ ላይ ማነው ኢትዮጵያዊ ብዬ ነበር :: ቶማስን አገኘሁ :: ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያን ወዳጆች ከያሉበት ሌት ተቀን እያፈላለገ ለአየር የሚያበቃው የታወቀው የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ድህረ ገጽ ቶማስ ያንግን የዚህ ሳምንት እንግዳ አድሮ ጋብዞታል :: ውይይቱን ለመከታተል እቺን ይጫኑ ::
http://etwnews.ethiopian-this-week.com/guest-of-the-week

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Jul 05, 2011 5:54 pm    Post subject: Reply with quote

እዚ ነገር እዚ ...(እቺ ነገር .,..እቺ ) Laughing ከነከንችኛ ላዋይዎ ብዬ እዚ አመጣሁልዎ የተከበሩ አንባቢ ሆይ በነገራችን ላይ ከነከንኝ የሚለውን አባባል አንድ የታወቀ በላ ድርብ ጾታ "ሸከከኝ " ሲል ሰማሁት ምን ማለት እንደሆነ እሱና ታናሹ ብቻ ናቸው የሚያውቁት :: ምንድነው ሸከከኝ ማለት ..? Very Happy መቼም ዋርካዋ ጸሀይ መጥቶን ልናርፍባት ስንመጣ የማታሰማን ጉድ የለም :: እስኪ ይሁና ይግበሮ ዝይገብሮ ... አለ ዲነካ እኮ ነው ::
እንደው እስኪ አንድ ነገር ላዋይዎ ....ደሞ እዚህ መጥቼ ካልጻፍኩት ሌላ ነገር መጦ ያሰርሳናል ብዬ ነው ...ከዛም በተጨማሪ ይሄንን በልቤ ይዜ የምብክነክንበት ምክንያት የለም :: ቢያንስ ሌላም ቦታ ባይሄድ ለርሶ ለተከበሩ አንባቢዬ ባዋይዎ ይቀለኛል :: ይሀውልዎ እንግዲህ የምሰራበት መስሪያ ቤት ኔሽን ዋይድ የሆነ የፉል ታይም ስራ አውጥቶ በኢንተርኔቱ ላይ ለቆአል :: አፒልኬሽን ከግራም ከቀኝም ከሌላ ስቴትም ምናልባት ከሀገር ውጭ ( ህንዶች ይሄንን ያደርጋሉ ) እየመጡ ነው :: ሰርች ኮሚቴ ውስጥ ከተመደቡት ሰዎች አንዱ እኔ ወንድምዎ ነኝ :: እዛ ውስጥ ስሜ አለ :: ከኔ ሙያ ጋር የሚያገናኝ ጉዳይ ስላለ የኔም ኢንፑት አሰፈላጊ እንደሆነ ታምኖበት ገብቻለሁ :: አሁን እኔ የማውቃቸው ልጆች የኛ ልጆች ( ኢትዮጵያውያን ) እዛ ውስጥ እንደገቡ አውቃለሁ :: እንደውም አንዳንዶቹ ማመልከት እንደሚፈልጉ ተነጋግረን ከቨር ሌተር ሁሉ አብረን ሰርተናል :: በኮሚቴ የሚሰራ ስራ ስለሆነ እግዜር ይርዳ እኔም የምችለውን አደርጋለሁ አልኩኝ :: የኮሚቴአችን ሰብሳቢ አሜሪካዊት ናት :: ሌሎችም በሙሉ ከኔና አንድ ህንድ በስተቀር ሁሉም አሜሪካዉያን ናቸው :: አሁን አንድ መሰሪ ፔንጤ ልጅ አለ :; ይሄ ልጅ ሌላ ዲፓርተመንት ነው የሚሰራው :: ከፔንጤነቱ ይልቅ ፖሎቲካዊ ስብእናው እጅግ ያየለ ነው :: ከየት እንደተማረው አላውቅም .ተንኮለኛም ነው :: ሰላምታ እንለዋወጣለን አንዳንዴ ስብሰባ ላይ ስንገናኝ በብሬክ ላይ አብረን እናወራለን ምሳም እንበላለን :: ፔንጤነቱን ለከቨር ይጠቀምበት እንጂ የለየለት ሰላይ መሆኑን እኔ ክቡራን አረጋጭአለሁ :: ይሁን ግደለም ያንን ጌታ በክብሩ ሲመጣ ለማን የክብር አክሊል እንደሚሰጥ እሱ ራሱ ያሳውቀናል :: That is not my subject... አሁን ይሄ ልጅ በዚች የቫኬሽን ጊዜ ( July 4 ) በመጠቀም ከኔ የበላይ አለቃ ጋር ( እሱም ኢትዮጵያዊ ነው ) በስልክ ግኑኝነት ያደርጋል :: ምናልባት መንፈስ ቅዱስ አለበት ብሎ የጠራ የፈረንሳይ ቢኖ አጠጥቶ ይሆናል እኔ አላውቅም :: እና እኔ ስልክ ይደውልና ምን ይለኛል (ማለት ይሄ አለቃዬ ) አንድ ሰው ከሰርች ኮሚቴ ውስጥ አስወጥተን ከሌላ ዲፓርትርመንት ሰው ማስገባት ይኖርብናል :: ሁላችሁም የሳይንስ ፋኩልቲ ሰዎች ናችሁ ከእንጊሊሽ ወይም ከሳይኮሎጂ ዲፓርተመንት ሰው መመጣት አለበት ይለኛል :: ማን እንዲወጣ ትፈለጋለህ ? የሚል ጥያቀ አቀረብኩ :: የኔ ጔደኛ የሆነውን አሜሪካዊ እሱ መውጣት አለብት ምክንያቱም አንተ የሱን ቦታ most likely cover ታደርጋለህ እና በሱ ቦታ ይሄ የኛ ልጅ (ስሙን ጠቅሶ ) ይገባል አለኝ :: ወዲያውኑ እሱ ለምን እዛ ቦታ እንዲገባም እንዳሰፈለገ ነገረኝ :: እከሌ የተባለው ሰው ( እሱም ዋና ፔንጤ ቆስጤ ነው ግን መሰሪ አይደለም ጥሩ ጸባይ ያለው ሰው ነው ) አመልክቷልና እኔ በተጸኖ ምክንያት ችሎታ ያላቸው ያገራችን ልጆች እንዲቀሩ ስለማልፈልግ ሰርች ኮሚቴው ላይ የሁለታችሁ ድምጽ ወሳኝነት ይኖረዋል ብዬ ስለማምን ነው አለኝና አረፈው :: እኔ ዶክተር ይወልህ ...እሱ አፕላይ ማድረጉን አልጠላም I don't have any problem with that ማንም ይሁን ማን ግን በሚያቀርበው ፕሬዜንቴሽን እኛን ኢምፕሬስ ማድረግ አለበት :: ካልሆነ እኔ የስራ ጔደኞቼም ይታዘቡኛል ኢምፕሬስ ላላደረገኝ ነገር ድምጸን መስጠት አልፈልግም አልኩትና አቆአሜን አቆቆአሜን ግልጽ አደረኩ :: እንዴት አታውቀም እንዴ ? አለኝ አውቀዋለሁ ግን እሱ ብቻ አይደለም አፕላይ ያደረገው እነ እከሌም እነ እከሌም ( በስም እየጠራሁ አፕላይ አድርገዋል ) እና እኔ እዚህ ውስጥ ሳንዲዊች ነው የምሆነው ስለዚህ እሱ የነሱ ቤተ ክርስቲያን አባል ስለሆነ ብቻ ሌሎቹን ኢግኖር አድርጌ ድምጽ አልሰጥም አልኩት :: ሁኔታው ግራ የገባው አለቃዬ እሺ እንጊዲያው ችሎታ ያላቸው የኛ ልጆች ( ኢትዮጵያውያኖችን ማለቱ ነው ) እንዳይቀሩ በርታ እኔ ምናልባት እሱን ሰርች ኮሚቴ ላላስገባው እችል ይሆናል ብሎኝ ስልኩን ዘጋው :: ይሄ ከሆነ በኈላ ሳስብ ነበር ...የዚህን ልጅ እንጀራ ዘጋሁበት ወይስ ለሌሎች እድል ከፈትኩ ...?? ምንድነው ያደረኩት ነገር እያልኩ ማሰቤ አልቀረም :: ያመለከቱት ልጆች በሙሉ በጊዜያዊነት እኛ ጋር የሚሰሩ በመሆናቸው ጔደኞቼ ናቸው ካንድንዶቹ ጋርም የትምህርት ቤት ጔደኞች ነን :: ታዲያ በዚህ ሽሩድ ፔንጤ አማካይነት የመጣውን ኦፈር እንዴት ልቀበል ...?? እሱ ብቻ አይደለም :: ጌታ የሱስ ክርስቶስን ራሱን ሊሽወዱት ሲሉ እንደያዝኴቸው ነው የምቆጥረው :: እንዴት ማለት ጥሩ ነገር ነው :: ይሄ ሰው የእግዚአብሄር ሰው ከሆነ በእግዚአብሄር ታላቅና ድንቅ ስራ የሚያምን ቢሆን በሀይሉ የሚታመን ከሆነ እንደዚህ ዐይነት ዘመዳዊ አሰራር ውስጥ ባልገባ ነበር :: ይሄ ለሚያምንበት እምነትና ላምላኩ ታማኝ አለመሆኑን አመላካች ነው :: ይሄ ልጅ ቀንቶት ስራውን ቢያገኝ እኮ ጌታ በድንቅ ጥበቡ ከመቶ አፕሌኬሽን ውስጥ መንፈስ ቅዱሱን ልኮ ነጥቆ ( ራፕቸር ) አወጣው እያሉ መድረክ ላይ እንደ ዶርዜ ጭፈራ እየዘለሉ ሀሌሉያቸውን ሊያቀልጡት እኮ ነው :: ይቺ ታዲያ የጌታ እጅ ናት ወይ ? እኔ ክቡራን አይደለም እላለሁ !! እርሶ ምን ይላሉ ? የተከበሩ እንባቢዬ :: ሰላም ቀን ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Wed Jul 06, 2011 9:58 pm    Post subject: Reply with quote

እንደው ወገኖቼ ይሄ ጌታ ሰጠው ጌታ ባረከው የሚባለው ነገር አሁንስ ቀልድ እየሆነ መጥቷል :: ከምር :: ይሄን አባባል የሚያበዙት ደሞ የፕሮትስታንት ተከታይ ወንድሞቼና እህቶቼ መሆናቸው ቀልዱን የባሰ ያደርገዋል :: ምንድነው ጌታ የሰጠህ ? ወይም የሰጠሽ ሲባሉ የሚመልሱት ሰማያዊን ተስፋና ህይወት ሳይሆን ምድራዊ አሰስ ገበስ ላይ መሆኑ ደሞ ያስተዛዝባል :: በክሬዲት ካርድ ማርሰዲስ ጭሮ ያወጣ አንዱ የፕርቶቴስታንት ዘፋኝ ለምሳሌ ምን አለ ...ጌታ በዋሽንገትን ዲሲ በማርሴዲስ ትሄዳለህ ብሎ ተናግሮኛል አለውና አረፈው :: ማርሰዲስ የሱ ፍላጎት የልቡ መሻት እንጂ የጌታ ፍቃድ እንዳልሆነ እንኵን ጌታ አይደልም ፎርሳው ራሱ በሚገባ ያውቀዋል :: ፎርሳው የምላችሁ ይሔ ዘማሪ ግሬደር ነገር ነው ;; ሲሄድ ራሱ የሚረግጠው መሬት ድም ድም የሚል ይመስላል :: ግድንግድ ነው :: In the name of jesus ስለሚል እንጂ ሬስሊንግ ቢጅምር እንጀራ ባነባበሮ አድርጎ የሚበላ ይመስለኛል :: ታዲያ አዘማመሩም እንደ ሰውነቱ ነው :: መድረክ ላይ ሲወጣ ምን እንደሚል ታውቃላችሁ ? ካጠገባችሁ ያለውን ሰው ፍሬን ልቀቅ በሉት ይላል :: ፍሬን ልቀቅ ..? የትኛውን ይዤ ነው የትኛውን የምለቀው ..? ከዛ ህዝበ ክርስቲያን እየተቀባበለ ከመድረክ የመጣውን ትእዛዝ ያስተላፋል :: ፍሬን በጥስ ተብለሀል ይላል አንዱ ለሌላው ከዛማ አለቀ ... በቃ መዝለል ትጀምራለህ
እምበር ተጋዳላይ
ከመስፍን ኡፋ ጋር ወደላይ እያልክ :: Very Happy
ይሄ ፓርት እዚ ላይ አያቆምም ይቀጥላል እናንተም እስኪ የታዘባችሁትን ጻፉ እኔ ብቻዬን እኮ ዛር የለብኝም ... Very Happy እስኪ ጨማምሩበት ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Thu Jul 07, 2011 3:58 pm    Post subject: Reply with quote

ይሄ ይሁኔ በላይ የሚባል ሰው አበዛው አሁንስ ... ወገኛ ነው :: ወጉ ይሙት እውነቴን ነው :: ጊሸን ማርያም መጫወቻ ናት እንዴ ? ባለፈው ከጔደኞቼ ጋር ሆነን እሱ ቤት ሄደን ነበር :: በርግጥ ባህላዊ የሆነ ስርአት የሚታይበት አስተናጋጆቹ እንደ ሌላው ሬስቶራንት የፈለጉትን የፈረንጅ ልብስ ሳይሆን የሚለብሱት ( BTW ጂንሲና ቲሸርት የፈረንጅ ልብስ ናቸው Very Happy) ባህላዊ ባለ ጥልፍ ቀሚስ አድርገው የሚያስተናጉዱበት ትእዛዝ ከመጣ ደሞ በሙቀጫ ይሁን በማድቀቂያ ቡና ተወቅጦ አቦል የሚጠጣበት ቤት አለው :: ዘፈኑም ባህላዊ ነው :: የማሲንቆና ክራር ቦታ በኪይ ቦርድ ቢነጠቅም :: ከዛም በተጨማሪ ሌላ ሬስቶራንት የማያዩት ነገር ይሁኔ ሊትል ሬስቶራንት ውስጥ አለ :: ምግብ ከመብላትዎ በፊት የእጅ ውሀ አንዲቷ አስተናጋጅ ከፎጣ ጋር ይዛልዎ ትመጣለች :: መቼም መግደርደሩ የጉድ ነው :: የእጅ መታጠቢያ ክፍል መታጠብ የለመድ ተስተናጋጅ ( ኢትዮጵያዊ ሁሉ ) እንደ አዲስ ክስተት ይደነግጣል :: ቁጭ ይበሉ የምትለዋ የአስተናጋጁዋ ልመና የተስተናጋጁ ደሞ መግደደር ምኑ ቅጡ .. ቅጽበታዊ ግርግርን ይፈጥራል :: ጊርጊሮ :: እነዚህ ሁሉ እሴቶቹ መልካም ቢሆኑም የይሁኔ በላይን በጊሸን ማርያም ስም መነገድን አልወደድኩትም :: አንዱን ዘፈን ከዘፈነ በኌላ ወደ ሚቀጥለው ዘፈኑ ሲሄድ "አሁን ደሞ በህዝብ ዘንድ ያስተዋወቀችኝና የቡዙዎችን አድናቆት ያተረፈችልኝ የጊሸን ማርያም ዘፈኔን ላሰማችሁ " አለን :: በጊሸን ማርያም ዘፈን ደረቱ እስኪደቃ እስክስታውን አስነካው :: እዛ ነው ፓራዶክስነቱ የታየኝ :: እሷን ከማክበርና ከማወደስ በላይ ገኖ የወጣው እስክስታውና ጭፈራው ነው :: ወደ ላይ ሁሉ እየዘለለ እግሮቹን በርከክ እያደረገ እንደውም ከፍት እድርጎ ጔንዴ ፍለጋ ወደ ታች ዝቅ እያለ እየተንጔደደ እስክስታውን አስኬደው :: እዚህ ላይ ማርያም መንፈሳዊነቷ ጸጋዋ ሳይሆን ጊሸን ተወልዳ እንዳደገች ኮረዳ ነው የተዘፈነላት :: አግባብ አይደለም እላለሁ :: ይስተካከል :: የቅዱሳን ስም ይከበር :: ተወዶልኛል ብሎ የእጊዝአብሄርን ቅዱሳን ስም በየመሸታው ቤት መድረክ ላይ እያነሱ ወደ ላይ መዝለልና እምቡር እምቡር ማለት ይቅር :: ጊሸን ማርያም እያልክ ወደ ታች ዝቅ ዝቅ የምትለው ምን ማየት ፈልገህ ነው አቶ ይሁኔ ? ነውር አይደለም እንዴ ? የስጋ የሆነውና የመንፈስ የሆነውን እንለይ እንጂ :: እንደው ግን ዘፋኝ ዘፈን ወዳጆች መንገዳቸው ወደ መንግስተ ሰማያት ሳይሆን ወደ ታችኛው ቤት ነው ነው የሚባለው ... ታዲያ ይሄ ዘፈን በስምሽ ዘፍኛለሁ ብሎ ለመከራከር እንዲመቸው ነው ወይስ እንዴት ቢያየው ነው ? በዘፈን ጉዳይ ላይ ካነሳን እኔም ላቤ ጠብ እስኪል የምወደው ዘፈን ሲዘፈን እወጣለሁ :: በጊሸን ማርያም ዘፈን ግን ተክዣለሁ እንጂ አልዘፈንኩም እዚህ ነጥብ ይያዝልኝ :: በተረፈ ይሁኔ መልካም ጸባይ ያለው ዲስሊንድ የሆነ ቤተሰቡን አክባሪ መሆኑን ባውቅም : በማርያም ስም መነገዱን እንዲያቆም ግን በአጋጣሚው እጠይቃለሁ ::
ክቡራን ነን ስንሆን ዝም ብለን አይደለም :: በሄድንበት ቦታ ብእራችንን ስለያዝንም ጭምር ነው ::
ተጕዥ ብእራችን የት ይሆን መድረሳሽ ..
እመር እመር አትበይ እያየሽ እርገጪ ..
ቀና መሬት መስሎሽ ጨለንቆ እንዳትሰምጪ ? አለ አለሙ እኮ ነው :: Laughing

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sat Jul 09, 2011 1:46 am    Post subject: Reply with quote

እሩምባ .. Cool
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sat Jul 16, 2011 11:04 pm    Post subject: Reply with quote

ለወ /ሪት ወይም / እክሊት እንደምናለሽልኝ ...አሁንማ የወ /ሪትና የወ / ልዩነት ከህብረተሰባችን ውስጥ ቀስ እያለ እየጠፋ ነው ::በላጲስ :: እኔ በሀገሬ ሳውቅ /ሪት ማለት ትዳር የሌላት ያላገባች ሴት የምትጠራበት የማእረግ ስሟ ነው :: ዛሬ ዛሬ ግን አግብታ ፈቷም በትዳር ይሁን ያለትዳር ሁለት ልጅ የታቀፈቸውም ወይዘርት ትባላለች :: እናም በየትኛው እንደምጠራሽ ግራ ገባኝ :: ይሄን መልክት እዚህ መጻፌ ለምክንያት ነው :: ዋርካ ውስጥ የሚመጡ ከተለያየት የህብረተሰብ ክፍልና አህጉራት የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን አሉ :: ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ እንደዚህ አይነት ገጠመኝ አሳልፈው ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :: ባለፈው ካንቺ ጋር በስልክ ሳወራ ስሜቴን አልተረዳሸም .... ያም ማለት ልልው የፈለኩት ነገር ወይ አልገባሽም ወይ ገብቶሽ እንዳልገባው በመምስል ራስሽን በግራም በቀኝም እንዳገረገረ በሬ ስትከላከዩ ነበረ :: የኌለኛው ይዞልሻል :: እኔም የስልኩ ውይይታችን መልክቱን እንዳልመታ ስለገባኝ በጽሁፍ የህሊናዬን ጨሀት ልገልጽልሽ ፈለኩ ::አንድ ቀን ስናወራ እንደ ቀልድ ጠይቄሽ እኔም ዋርካ እገባለሁ ስትዪ ሰምቻለሁና የሰከነ ቡና ይዘሽ አንቢው :: አሁን አሁን ቡዙ አድናቂዎች ረዳቶችና አለንልሽ የሚሉ ደጋፊዎች በዙሪያሽ በማሰለፍሽ ቡዙ እንደማላስፈልግሽ ተክለ ሰውነትሽ ነገረኝ :: አንዳንድ ሰው እኮ አፉ ባይናገር ሁለንተናው ያወራል ሲል አጫውቶኛል እዝራ ጔደኛዬ :: :: ይሄ እዝራ ጉደኛ ልጅ ነው ::እንደ ሰው ጮክ እያለ አያወራም :: ዝም ይላል :: ዝምታው ያስፈራል :: ጔደኛሞች በመሆናችን እንጂ ዝም ማለቱ እኔንም እኔንም ያስፈራኛል :: አንድ ቀን ትስማለህ ክቡራን ይህ ትውልድ በራሱ ጩሀት ደንቁሯል አለኝ :: እስከዛሬ ድረስ ምን ማለቱ ነው እያልኩ አብሰለስላለሁ :: እዝራ ጔደኛዬ እውነቱን ነው :: ሁላችንም እንጮሀላን :: አንቺም ትጮሂያለሽ ... ሲልሽ በስልክ ሲልሽ የሬድዮ ማይክራፎን ይዘሽ :: ጠጅ ቤት ጎራ ብቱዪ አግዳሚ ወንበር ላይ ያሉት በሙሉ ይጫሀሉ :: ሁሉም የውስጣቸውን መቃተትና ዋይታ ጭንቀትና ብሶት ብሎ ፈንድቶ እንዳይገድላቸው በመፍራት ይመስለኛል ይጫሀሉ :: ጎርፍ ሆኖ እንዳይወስዳቸው የተጨነቁ ይመስላል :: ችግሩ እዚህ ይጀምራል :: እነሱ የሚያዩት ጮሀው ራሳቸውን ተንፈስ ማድረጋቸውን እንጂ እሪታቸው ትክክል ይሁን አይሁን ምንም የሚያውቁት ነገር የላቸውም :: እንደ ገደል ማሚቶ ግን ያንን ጨሀታቸውን መልሰው ለራሳቸው ይሰሙታል :: ዝምተኛው ወዳጄ እዝራ ይህን አይቶ ይመስለኛል ትውልዱ በራሱ ጨሀት ደነቆረ ያለው :: ብሂሉን አልሳተም :: እናቴ ትሙት እንዳልልሽ አንዱ የታክሲ ጠራ አስጠባቂ ባለፈው በናትህ እንዳትምል ብሎ አስጠንቆቃኛል እና ተውኩት :: እዚህ ዋርካ ውስጥ ቡዙ ሰዎችን አውቃለሁ :: የሚወዱኝም የሚጠሉኝም አሉ :: እኔም ወንድምሽ መልአክ አይደለሁም :: ለሚወዱኝ ማር የላሰ ጠጅ ከወገቤ ዝቅ ብዬ አቀርባለሁ :: ለጠሉኝ ሳይናይድ መርዝ በብርጭቆ አለኝ ለማጋት ወደኌላ አልልም :: የራሴን እዚህ ላቁምና ወዳንቺና ወደኔ ጉዳይ እንምጣ :: ከቡዙ ጊዜ መጠፋፋት በኌላ ደወልሽልኝ ::እውነቱን ልንገርሽና ቁጥርሽን ሳየው ወዲያው ማንሳት እችል ነበር :: ግን አልፈለኩም ::ከራሴ ጋር መወያየት ጀመርኩ :: ቡዙ ጊዜ ደጋግሜ ብደውልም ለጥሪዬ ምላሽ አላገነሁም ካንቺም አብረውሽ ከሚሰሩ ፓርተኖሮሽም ጋር :: በዚህ ቂም የማይደፍረው ልቤ ቂም ይዞባችሁ ነበር :: ሜይል ልኬ ነበር :: በፌስ ቡክ ሞክሬ ነበር :: እንጊሊዝኛዬ እንደ ወይዘሮ አስኩ የጉሽ ጠላ አልወርድ ብሎ አስቸግሯችሁ እንደሆን ብዬ ባማርኛ አሟሽቼ በፒዲኤፍ ስካን አስክኜ ባማርኛ ፎንት መልክቴን ልኬ ነበር :: ግን ጥረቴ አልተሳካምና አዘንኩ :: አዘንኩ እንደውም አድማ የመታችሁብኝ መሰለኝ :: ታሳታውሺያልሽ ...አንድ ጊዜ የመጽሀፍ ግምገማ አለና የእክሌን መጽሀፍ አንብበህ አስተያየት እንድትሰጥ እፈልጋለሁ ስትዩኝ ...አላመነታሁም :: የዛኑ ምሽት ብእሬን ከወረቀት ጋር አገናኙሁት :: ዝግጅቱ ላይ ቡዙ ትልልቅ ሰዎች ይገኛሉ ብዬ አልጠበኩም ነበር በስም የማውቃቸውን ሰዎች ባካል በማየቴ አንዱ ገምጋሚ መሆኔ ፍርሀት ቢያሳድርብንኝም ማስታወሻዬን ይዤ ወደ መናገሪያው ሄድኩ :: ገና ስጠጋው ስፒከሩ ከኔ ይልቅ እሱ እሪ አለ :: መጛኛ !! በኌላ ተረጋግቼ ንግግሬን ስጀምር "ስፒክሩ ሲጮህ ፈርቼ ልወረውረው .. ነበር " ስል አብዛኛው ሰው አነጋገሬ ሳቀው :: ያኔ ፍርሀቴ ለቀቀኝ :: ምን እንዳልኩ አላውቅም : ብቻ ሳላነብ ያወራሆአቸው ቡዙ ነገሮች አንዳሉ ግን አስታውሳለሁ :: የአንድ ዶክተር ባለቤት መጨረሻ ላይ ለምን ካበሌቤቴ ጋር አትተዋወቁም ብቸኛ ነው ...የስን ጽሁፍ ሰዎችን ይወዳል ስትለኝ አንዳንድ ሰዎች ልብ ውስጥ መቅረዜን እንዳስቀመጥኩ አወኩኝ :: ዛሬ መጽሀፉን የገመኩለት ባደባባይ አድናቆቴን የቸርኩት ሰውዬ ሁለት ገጽ የማይሞላ የትዝብት አትርክል ሌኬልት እንዲገመግምልኝና ስህተቴን እንዲያሳየኝ ብጠይቀው መልስ ነፈገኝ ::ላንቺም CC ደግሜ ላኩኝ :: መልሲን ጊን ኢንጂሩ ሆነ ጉዳዩ :: የኔ ችግር ጽሁፌ ላየር ይብቃ አይብቃ አይደለም :: ጽሁፌ ላለመነበቡ ቡዙ ምክንያቶች አሉ :: አንድ የፕሮግራም አዘጋጅ ለፕሮግራሙ የሚሆኑትን ጽሁፎች የመመረጥና የማስተላለፍ ሀላፊነት እንዳለብት እገነዘባለሁ :: ችግሬ ግን ስህተቱ ይነገረኝና ልማርበት የሚል ነው :: ስለ ስነ ጽሁፍ አምላክ ስትል አንተ የተባና ቅቤ የሆነ ብእር ያለህ ሰው ነህና ስህተቴን ጠቁመኝ ለሚለው ልመናዬ መልስ አለማግኘቴ ነበር ውስጤን ያቆሶለው :: እንግዲህ በዛ ሁኔታ እያለሁ ነበር አንቺ ስልክ የመታሽው ...የጠፋሁበትን ምክንያት አስረዳሁኝ :: መልስ አለማግኔቴ ትክክል እንዳልነበረ እንደ መጀመሪያ ጔደኝነታችን በሀሜት መልክ ሳይሆን ብግልጽ በፊት ለፊት ነገርኩሽ :: እነድውም ስነ ጽሁፋዊ በደል እንደሆነ በንጹህ ህሊና አስረዳሁሽ :: አንቺ ይባስ ብለሽ እኔን ጥፋተኛ ለማድረግ ሞከርሽ :: የማይነካ ሰው አትንካ አይነት ተከላካይ ሆነሽ ቀረብሽ :: ሳቅሽ ለውነት የቆምሽ ትመሲዪኝ ነበር :: እውነትን ሳይሆን ሰዎችን የያዥሽ መሆንሽን ግን ከንግግርሽ ተረዳሁ :: የቆምሽው ራቁቷን ላለች እውነት ( Naked Truth) ሳይሆን እኛ አለንልሽ ላሉሽ ሰዎች መሆኑ ገባኝ :: አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ጽሁፎችኝ ጊዜ ሳገኝ ባየር ላይ አዳምጣለሁ :: ስለ እውነት ስለ ፍቅር ስለ መቻቻል አንዱ ስለ ሌላው ሲል ስለመኖር የየምታነቡያቸውን ልብ የሚያኖህልሉ ትምህርት ሰጪ ወጎች አዳመጥኩ :: አንዳንዴ ተጽፎ ተሰጥቷት ነው ውይስ ራሷ ናት የጻፈቸው እላለሁ :: የማንኖርበትን ነገር ለሌሎች አንስበክ :: እዝራ እንዳለኝ ትውልዱ የደነቆረው የማይኖርበትን እውነት በየለቱ ስለሚጩህ ነው :: አሁን እፎይ አልኩ :: ብታነቢው ግድ የለኝም ....ባታነቢውም ግድ የለኝም ....እኔ ግን ዛሬ ምሽት የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ :: ሰላማት ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Jul 19, 2011 1:47 am    Post subject: Reply with quote

ባለፈው ሳምንት አንድ ስብሰባ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሂዶ ነበር :: ስብሰባው የተዘጋጀው በሶስት ድርጅቶች ትብብር ነው :: ድርጅቶቹ በእግረ መድረካቸው ጥምረት የሚባል ፓርቲ ወይም ጥምር ድርጅት እንደመሰረቱም በለሆሳስ ይፋ አድርገዋል :: ጸሀፊው አቶ ነአምን ዘለቀ ሲያስተዋውቅ ሰምቼው ነው :: ቪዲዮውን ካላዩ የተከበሩ አንባቢዬ ሆይ ፈልገው ፈላገው ይስሙት ...
ፈልጌ አስፈልጌ ያን ሰሞን ያጣኌት ...
አወይ አጋጣሚ ድንገት ዛሬ አየኌት ... አለ ድንቅ የሙዚቃ ሌጀንድ :: አንዱ የኦነግ ተወካይ ዶክተር አማርኛቸውን "ዌል " እየወለወሉ ንግግራቸውን ጨረሱ ኦነግ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ :: እየሰባበረም ቢሆን አማርኛ መናገር ጀመረ :: ቀጥሎ ውይይቱን የመሩት ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ናቸው :: አስተዋዋቂው እንዳለው ዶክተሩ ቅድም ያልኴችሁ ጥምረት የሚባለው ድርጅት /መንበርና እንዲሁም ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት /መንበር ናቸው :: ታዲያ ዶክተር የተሰጣቸው ርእስ ስለማንነት ( አይደነቲቲ ) ጉዳይ ነበር ገለጻ የሚያደርጉት :: ርእስ ኦነጎችን ደስ ያሰኘ እንደሆነ አልጠራጥርም :: ስገምት :: አንድ ቀን አንድ ኦነግን የሚደግፍ የወለጋ ልጅ የስራ ባልደረባዬ "እኛ ኦሮሞዎች አይደንቲያችን ተሰርቆአል ብሎኛል :: የትኛው መንታፊ ሌባ አይደንቲቲውን መቼና የት እንደሰረቀው ግን አልገለጸልኝም :: ወደሳቸው ልመልሳችሁ ማለቴ ወደ ዶክተሩ :: ዶክተር እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ አይደንቲቲ አለው አሉ :: ቀጠሉ "" ያለ አይደንቲቲ የተፈጠረ ሰው የለም :: ያንድ ሰው መለያው አይደንቲቲው ነው እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ዩኒክነስ አለው ራሱን በራሱ ዲፋይን የሚያደርግበት የራሱ ማንነት መገለጫ አይደንቲትው ነው :: መቼም ዶክተር ከሚናገሩት ውስጥ 75% እንጊሊዝኛ ነው 25% ብቻ ናት ተጣርታ የወጣች አማርኛ ! እንጊሊዝኛ ኔፓ የሆነ ሰው የሳቸውን ንግግር ሰምቶ ገብቶት ሳይሆን ደንዞንዝና ተክዞ ይወጣል :: ትካዜ የሚመጣው እኮ አንድ ነገር ሳይገባን ሲቀር ነው :: እና ዶክተር ብሬ ስለሳቸው መናገር ጀመሩ ቅድም እንዳልኴችሁ ውይይቱ ስለ አይደንቲቲ ( የማንነት መገለጫ ጉዳይ ነው :Smile "እኔን ውሰዱኝ አሉ ብሬ ..እኔ ኢኮኖሚስት ነኝ ወሮልድ ክላስ ኢኮኖሚስቶች ጋር ስሆን እይደንቲትዬ ኢኮኖሚስት ነው :: ሙዚቃ ነፍሴ ነው ሙዚቃ እወዳለሁ ....እዚህ ያላችሁ አንዳዶች ታውቃላችሁ ...(ባይናቸው የሆኑ ሰዎችን መፈላለግ ጀመሩ ) ጉራጌ ነኝ ደሞ እይደንቲትዬ ነው :: ከናንተ ለየት ባለ ሁኔታ ክትፎና ቆጮ እወዳለሁ :: (ሁለት ጣታቸውን እንደ ባላ አድርገው ለተሰብሳቢዎቹ አሳዩ ) ክትፎ እግዜር አወጣት ...እንደ ቁርጥ ስጋ ሊበልቷት ነበር :: Very Happy ሌላ አይደንቱትዬ ደሞ የፍላዲሌግፊያ ኢግል ክለብ ዋና ደጋፊ ነኝ :: እኔ ያንን ክለብ ሰምቼው ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም :: ምናልባት በሳቸው ስቴት የሚኖሩ የአሜሪካን ፉት ቦል ተጫዋቾች ይሆኑ ይሆናል :: ስለ እግር ኴስ ቢያወሩ ወይም የማንቼን ስም ቢጠሩ .. ብሬ እላቸው ነበር :: ጎዖዖዖዖዖል ....:: Very Happy እንደው የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ብዬ ነው :: በቸር ያገናኘን ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Tue Jul 19, 2011 3:01 pm    Post subject: Reply with quote

ትንሽ እንሳቅ :: Very Happy
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Jul 19, 2011 3:30 pm    Post subject: Reply with quote

እረ በፈጠረህ ሀሳብህን በአንቀጽ ከፋፍለህ መጻፍ ተማር አንተ ጋዜጠኛ Laughing Razz ካሁን በፊት እንዲሁ አትከምር አላኩህም ....ድሮ የማትወደውን አማርኛ Wink ስትማር መልመጃ ሶስትን ዘለህ ዘለህ አሁን እንዲሁ ትደርተዋለህ ይሄን እጅ እጅ የሚል ሀሳብህን Laughing Razz

ለማንኛውም ሌላው ቢቀር ቀላል የሆነውን የስነ ጽሁፍ ህግጋትና የስርአተ ነጥብን ትክክለኛ አገባብ ለማወቅ ሞክር ለማለት ነው ....ራስህን ጋዜጠኛ ነኝ ብለህ ከማስብህ በፊት Rolling Eyes

ሞንሟናው ዘብሔረ -ጎዣም

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ለወ /ሪት ወይም / እክሊት እንደምናለሽልኝ ...አሁንማ የወ /ሪትና የወ / ልዩነት ከህብረተሰባችን ውስጥ ቀስ እያለ እየጠፋ ነው ::በላጲስ :: እኔ በሀገሬ ሳውቅ /ሪት ማለት ትዳር የሌላት ያላገባች ሴት የምትጠራበት የማእረግ ስሟ ነው :: ዛሬ ዛሬ ግን አግብታ ፈቷም በትዳር ይሁን ያለትዳር ሁለት ልጅ የታቀፈቸውም ወይዘርት ትባላለች :: እናም በየትኛው እንደምጠራሽ ግራ ገባኝ :: ይሄን መልክት እዚህ መጻፌ ለምክንያት ነው :: ዋርካ ውስጥ የሚመጡ ከተለያየት የህብረተሰብ ክፍልና አህጉራት የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን አሉ :: ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ እንደዚህ አይነት ገጠመኝ አሳልፈው ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :: ባለፈው ካንቺ ጋር በስልክ ሳወራ ስሜቴን አልተረዳሸም .... ያም ማለት ልልው የፈለኩት ነገር ወይ አልገባሽም ወይ ገብቶሽ እንዳልገባው በመምስል ራስሽን በግራም በቀኝም እንዳገረገረ በሬ ስትከላከዩ ነበረ :: የኌለኛው ይዞልሻል :: እኔም የስልኩ ውይይታችን መልክቱን እንዳልመታ ስለገባኝ በጽሁፍ የህሊናዬን ጨሀት ልገልጽልሽ ፈለኩ ::አንድ ቀን ስናወራ እንደ ቀልድ ጠይቄሽ እኔም ዋርካ እገባለሁ ስትዪ ሰምቻለሁና የሰከነ ቡና ይዘሽ አንቢው :: አሁን አሁን ቡዙ አድናቂዎች ረዳቶችና አለንልሽ የሚሉ ደጋፊዎች በዙሪያሽ በማሰለፍሽ ቡዙ እንደማላስፈልግሽ ተክለ ሰውነትሽ ነገረኝ :: አንዳንድ ሰው እኮ አፉ ባይናገር ሁለንተናው ያወራል ሲል አጫውቶኛል እዝራ ጔደኛዬ :: :: ይሄ እዝራ ጉደኛ ልጅ ነው ::እንደ ሰው ጮክ እያለ አያወራም :: ዝም ይላል :: ዝምታው ያስፈራል :: ጔደኛሞች በመሆናችን እንጂ ዝም ማለቱ እኔንም እኔንም ያስፈራኛል :: አንድ ቀን ትስማለህ ክቡራን ይህ ትውልድ በራሱ ጩሀት ደንቁሯል አለኝ :: እስከዛሬ ድረስ ምን ማለቱ ነው እያልኩ አብሰለስላለሁ :: እዝራ ጔደኛዬ እውነቱን ነው :: ሁላችንም እንጮሀላን :: አንቺም ትጮሂያለሽ ... ሲልሽ በስልክ ሲልሽ የሬድዮ ማይክራፎን ይዘሽ :: ጠጅ ቤት ጎራ ብቱዪ አግዳሚ ወንበር ላይ ያሉት በሙሉ ይጫሀሉ :: ሁሉም የውስጣቸውን መቃተትና ዋይታ ጭንቀትና ብሶት ብሎ ፈንድቶ እንዳይገድላቸው በመፍራት ይመስለኛል ይጫሀሉ :: ጎርፍ ሆኖ እንዳይወስዳቸው የተጨነቁ ይመስላል :: ችግሩ እዚህ ይጀምራል :: እነሱ የሚያዩት ጮሀው ራሳቸውን ተንፈስ ማድረጋቸውን እንጂ እሪታቸው ትክክል ይሁን አይሁን ምንም የሚያውቁት ነገር የላቸውም :: እንደ ገደል ማሚቶ ግን ያንን ጨሀታቸውን መልሰው ለራሳቸው ይሰሙታል :: ዝምተኛው ወዳጄ እዝራ ይህን አይቶ ይመስለኛል ትውልዱ በራሱ ጨሀት ደነቆረ ያለው :: ብሂሉን አልሳተም :: እናቴ ትሙት እንዳልልሽ አንዱ የታክሲ ጠራ አስጠባቂ ባለፈው በናትህ እንዳትምል ብሎ አስጠንቆቃኛል እና ተውኩት :: እዚህ ዋርካ ውስጥ ቡዙ ሰዎችን አውቃለሁ :: የሚወዱኝም የሚጠሉኝም አሉ :: እኔም ወንድምሽ መልአክ አይደለሁም :: ለሚወዱኝ ማር የላሰ ጠጅ ከወገቤ ዝቅ ብዬ አቀርባለሁ :: ለጠሉኝ ሳይናይድ መርዝ በብርጭቆ አለኝ ለማጋት ወደኌላ አልልም :: የራሴን እዚህ ላቁምና ወዳንቺና ወደኔ ጉዳይ እንምጣ :: ከቡዙ ጊዜ መጠፋፋት በኌላ ደወልሽልኝ ::እውነቱን ልንገርሽና ቁጥርሽን ሳየው ወዲያው ማንሳት እችል ነበር :: ግን አልፈለኩም ::ከራሴ ጋር መወያየት ጀመርኩ :: ቡዙ ጊዜ ደጋግሜ ብደውልም ለጥሪዬ ምላሽ አላገነሁም ካንቺም አብረውሽ ከሚሰሩ ፓርተኖሮሽም ጋር :: በዚህ ቂም የማይደፍረው ልቤ ቂም ይዞባችሁ ነበር :: ሜይል ልኬ ነበር :: በፌስ ቡክ ሞክሬ ነበር :: እንጊሊዝኛዬ እንደ ወይዘሮ አስኩ የጉሽ ጠላ አልወርድ ብሎ አስቸግሯችሁ እንደሆን ብዬ ባማርኛ አሟሽቼ በፒዲኤፍ ስካን አስክኜ ባማርኛ ፎንት መልክቴን ልኬ ነበር :: ግን ጥረቴ አልተሳካምና አዘንኩ :: አዘንኩ እንደውም አድማ የመታችሁብኝ መሰለኝ :: ታሳታውሺያልሽ ...አንድ ጊዜ የመጽሀፍ ግምገማ አለና የእክሌን መጽሀፍ አንብበህ አስተያየት እንድትሰጥ እፈልጋለሁ ስትዩኝ ...አላመነታሁም :: የዛኑ ምሽት ብእሬን ከወረቀት ጋር አገናኙሁት :: ዝግጅቱ ላይ ቡዙ ትልልቅ ሰዎች ይገኛሉ ብዬ አልጠበኩም ነበር በስም የማውቃቸውን ሰዎች ባካል በማየቴ አንዱ ገምጋሚ መሆኔ ፍርሀት ቢያሳድርብንኝም ማስታወሻዬን ይዤ ወደ መናገሪያው ሄድኩ :: ገና ስጠጋው ስፒከሩ ከኔ ይልቅ እሱ እሪ አለ :: መጛኛ !! በኌላ ተረጋግቼ ንግግሬን ስጀምር "ስፒክሩ ሲጮህ ፈርቼ ልወረውረው .. ነበር " ስል አብዛኛው ሰው አነጋገሬ ሳቀው :: ያኔ ፍርሀቴ ለቀቀኝ :: ምን እንዳልኩ አላውቅም : ብቻ ሳላነብ ያወራሆአቸው ቡዙ ነገሮች አንዳሉ ግን አስታውሳለሁ :: የአንድ ዶክተር ባለቤት መጨረሻ ላይ ለምን ካበሌቤቴ ጋር አትተዋወቁም ብቸኛ ነው ...የስን ጽሁፍ ሰዎችን ይወዳል ስትለኝ አንዳንድ ሰዎች ልብ ውስጥ መቅረዜን እንዳስቀመጥኩ አወኩኝ :: ዛሬ መጽሀፉን የገመኩለት ባደባባይ አድናቆቴን የቸርኩት ሰውዬ ሁለት ገጽ የማይሞላ የትዝብት አትርክል ሌኬልት እንዲገመግምልኝና ስህተቴን እንዲያሳየኝ ብጠይቀው መልስ ነፈገኝ ::ላንቺም CC ደግሜ ላኩኝ :: መልሲን ጊን ኢንጂሩ ሆነ ጉዳዩ :: የኔ ችግር ጽሁፌ ላየር ይብቃ አይብቃ አይደለም :: ጽሁፌ ላለመነበቡ ቡዙ ምክንያቶች አሉ :: አንድ የፕሮግራም አዘጋጅ ለፕሮግራሙ የሚሆኑትን ጽሁፎች የመመረጥና የማስተላለፍ ሀላፊነት እንዳለብት እገነዘባለሁ :: ችግሬ ግን ስህተቱ ይነገረኝና ልማርበት የሚል ነው :: ስለ ስነ ጽሁፍ አምላክ ስትል አንተ የተባና ቅቤ የሆነ ብእር ያለህ ሰው ነህና ስህተቴን ጠቁመኝ ለሚለው ልመናዬ መልስ አለማግኘቴ ነበር ውስጤን ያቆሶለው :: እንግዲህ በዛ ሁኔታ እያለሁ ነበር አንቺ ስልክ የመታሽው ...የጠፋሁበትን ምክንያት አስረዳሁኝ :: መልስ አለማግኔቴ ትክክል እንዳልነበረ እንደ መጀመሪያ ጔደኝነታችን በሀሜት መልክ ሳይሆን ብግልጽ በፊት ለፊት ነገርኩሽ :: እነድውም ስነ ጽሁፋዊ በደል እንደሆነ በንጹህ ህሊና አስረዳሁሽ :: አንቺ ይባስ ብለሽ እኔን ጥፋተኛ ለማድረግ ሞከርሽ :: የማይነካ ሰው አትንካ አይነት ተከላካይ ሆነሽ ቀረብሽ :: ሳቅሽ ለውነት የቆምሽ ትመሲዪኝ ነበር :: እውነትን ሳይሆን ሰዎችን የያዥሽ መሆንሽን ግን ከንግግርሽ ተረዳሁ :: የቆምሽው ራቁቷን ላለች እውነት ( Naked Truth) ሳይሆን እኛ አለንልሽ ላሉሽ ሰዎች መሆኑ ገባኝ :: አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ጽሁፎችኝ ጊዜ ሳገኝ ባየር ላይ አዳምጣለሁ :: ስለ እውነት ስለ ፍቅር ስለ መቻቻል አንዱ ስለ ሌላው ሲል ስለመኖር የየምታነቡያቸውን ልብ የሚያኖህልሉ ትምህርት ሰጪ ወጎች አዳመጥኩ :: አንዳንዴ ተጽፎ ተሰጥቷት ነው ውይስ ራሷ ናት የጻፈቸው እላለሁ :: የማንኖርበትን ነገር ለሌሎች አንስበክ :: እዝራ እንዳለኝ ትውልዱ የደነቆረው የማይኖርበትን እውነት በየለቱ ስለሚጩህ ነው :: አሁን እፎይ አልኩ :: ብታነቢው ግድ የለኝም ....ባታነቢውም ግድ የለኝም ....እኔ ግን ዛሬ ምሽት የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ :: ሰላማት ::

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2955

PostPosted: Tue Jul 19, 2011 7:36 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ክቡራን

በጣም ያዝናናኝ ፅሁፍ ነው ....እግዜር ይስጥህ Very Happy ቪዲዮውን በደንብ ማፈላለግ አለብኝ Laughing

ኢትዮጵያን ነፃ አውጪው "ዎርልድ ክላስ ኢኮኖሚስት " አይደንቲቲዎች መካከል

1. ለአማርኛ ተናጋሪዎች በኢንግሊሽ ማውራት

2. ፊላዴልፊያ ኢግልስ

3. ጉራጌነት

Wink Laughing Laughing Laughingቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

/ ወይ በዝግታ ልብ እየገዙ ነው ወይም አንደኛውኑ ሊለይላቸው ነው Laughing Laughing

በነገራችን ላይ "ለየለት " የሚለው ቃል መነሻው ምን ይሆን Question ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሠላም

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ባለፈው ሳምንት አንድ ስብሰባ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሂዶ ነበር :: ስብሰባው የተዘጋጀው በሶስት ድርጅቶች ትብብር ነው :: ድርጅቶቹ በእግረ መድረካቸው ጥምረት የሚባል ፓርቲ ወይም ጥምር ድርጅት እንደመሰረቱም በለሆሳስ ይፋ አድርገዋል :: ጸሀፊው አቶ ነአምን ዘለቀ ሲያስተዋውቅ ሰምቼው ነው :: ቪዲዮውን ካላዩ የተከበሩ አንባቢዬ ሆይ ፈልገው ፈላገው ይስሙት ...
ፈልጌ አስፈልጌ ያን ሰሞን ያጣኌት ...
አወይ አጋጣሚ ድንገት ዛሬ አየኌት ... አለ ድንቅ የሙዚቃ ሌጀንድ :: አንዱ የኦነግ ተወካይ ዶክተር አማርኛቸውን "ዌል " እየወለወሉ ንግግራቸውን ጨረሱ ኦነግ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ :: እየሰባበረም ቢሆን አማርኛ መናገር ጀመረ :: ቀጥሎ ውይይቱን የመሩት ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ናቸው :: አስተዋዋቂው እንዳለው ዶክተሩ ቅድም ያልኴችሁ ጥምረት የሚባለው ድርጅት /መንበርና እንዲሁም ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት /መንበር ናቸው :: ታዲያ ዶክተር የተሰጣቸው ርእስ ስለማንነት ( አይደነቲቲ ) ጉዳይ ነበር ገለጻ የሚያደርጉት :: ርእስ ኦነጎችን ደስ ያሰኘ እንደሆነ አልጠራጥርም :: ስገምት :: አንድ ቀን አንድ ኦነግን የሚደግፍ የወለጋ ልጅ የስራ ባልደረባዬ "እኛ ኦሮሞዎች አይደንቲያችን ተሰርቆአል ብሎኛል :: የትኛው መንታፊ ሌባ አይደንቲቲውን መቼና የት እንደሰረቀው ግን አልገለጸልኝም :: ወደሳቸው ልመልሳችሁ ማለቴ ወደ ዶክተሩ :: ዶክተር እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ አይደንቲቲ አለው አሉ :: ቀጠሉ "" ያለ አይደንቲቲ የተፈጠረ ሰው የለም :: ያንድ ሰው መለያው አይደንቲቲው ነው እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ዩኒክነስ አለው ራሱን በራሱ ዲፋይን የሚያደርግበት የራሱ ማንነት መገለጫ አይደንቲትው ነው :: መቼም ዶክተር ከሚናገሩት ውስጥ 75% እንጊሊዝኛ ነው 25% ብቻ ናት ተጣርታ የወጣች አማርኛ ! እንጊሊዝኛ ኔፓ የሆነ ሰው የሳቸውን ንግግር ሰምቶ ገብቶት ሳይሆን ደንዞንዝና ተክዞ ይወጣል :: ትካዜ የሚመጣው እኮ አንድ ነገር ሳይገባን ሲቀር ነው :: እና ዶክተር ብሬ ስለሳቸው መናገር ጀመሩ ቅድም እንዳልኴችሁ ውይይቱ ስለ አይደንቲቲ ( የማንነት መገለጫ ጉዳይ ነው :Smile "እኔን ውሰዱኝ አሉ ብሬ ..እኔ ኢኮኖሚስት ነኝ ወሮልድ ክላስ ኢኮኖሚስቶች ጋር ስሆን እይደንቲትዬ ኢኮኖሚስት ነው :: ሙዚቃ ነፍሴ ነው ሙዚቃ እወዳለሁ ....እዚህ ያላችሁ አንዳዶች ታውቃላችሁ ...(ባይናቸው የሆኑ ሰዎችን መፈላለግ ጀመሩ ) ጉራጌ ነኝ ደሞ እይደንቲትዬ ነው :: ከናንተ ለየት ባለ ሁኔታ ክትፎና ቆጮ እወዳለሁ :: (ሁለት ጣታቸውን እንደ ባላ አድርገው ለተሰብሳቢዎቹ አሳዩ ) ክትፎ እግዜር አወጣት ...እንደ ቁርጥ ስጋ ሊበልቷት ነበር :: Very Happy ሌላ አይደንቱትዬ ደሞ የፍላዲሌግፊያ ኢግል ክለብ ዋና ደጋፊ ነኝ :: እኔ ያንን ክለብ ሰምቼው ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም :: ምናልባት በሳቸው ስቴት የሚኖሩ የአሜሪካን ፉት ቦል ተጫዋቾች ይሆኑ ይሆናል :: ስለ እግር ኴስ ቢያወሩ ወይም የማንቼን ስም ቢጠሩ .. ብሬ እላቸው ነበር :: ጎዖዖዖዖዖል ....:: Very Happy እንደው የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ብዬ ነው :: በቸር ያገናኘን ::

_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5 ... 12, 13, 14  Next
Page 4 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia