View previous topic :: View next topic
Author
Message
መላ -ምት Joined: 25 Apr 2009 Posts: 848
Posted: Tue Jul 19, 2011 8:28 pm Post subject:
ሰላም ወንድም ክቡራን !
እኔም በጥሞና እና እየጣመኝ የተከታተልኩት ንግግር ነው :: ልቅም ያለ እውነታ ነው (በኔ ስታንድ ):: የታዘብከውን ማካፈልህ ድግ ነው :: ሞያህን ግን ተጠቅመህ አልተቸህም :: ታድያ አንኳር አንኳሩን እያንገዋለልክ በሞያህ መነጽር እንዴት እንዳየኸው አሳያንን እንጂ ::
ባለፈው አንተ እራስህ ልዩነታችን ውበታችን እንደሆነ አይነት ነገር ጽፈህ ማለፍያ ነው ብለን ነበረ :: ታድያ ከዚህ አንጻር ምሁሩ የገደፍት ነገር ያለ ይመስኻል ?
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ባለፈው ሳምንት አንድ ስብሰባ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሂዶ ነበር :: ስብሰባው የተዘጋጀው በሶስት ድርጅቶች ትብብር ነው :: ድርጅቶቹ በእግረ መድረካቸው ጥምረት የሚባል ፓርቲ ወይም ጥምር ድርጅት እንደመሰረቱም በለሆሳስ ይፋ አድርገዋል :: ጸሀፊው አቶ ነአምን ዘለቀ ሲያስተዋውቅ ሰምቼው ነው :: ቪዲዮውን ካላዩ የተከበሩ አንባቢዬ ሆይ ፈልገው ፈላገው ይስሙት ...
ፈልጌ አስፈልጌ ያን ሰሞን ያጣኌት ...
አወይ አጋጣሚ ድንገት ዛሬ አየኌት ... አለ ያ ድንቅ የሙዚቃ ሌጀንድ :: አንዱ የኦነግ ተወካይ ዶክተር አማርኛቸውን በ "ዌል " እየወለወሉ ንግግራቸውን ጨረሱ ኦነግ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ :: እየሰባበረም ቢሆን አማርኛ መናገር ጀመረ :: ቀጥሎ ውይይቱን የመሩት ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ናቸው :: አስተዋዋቂው እንዳለው ዶክተሩ ቅድም ያልኴችሁ ጥምረት የሚባለው ድርጅት ሊ /መንበርና እንዲሁም ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት ሊ /መንበር ናቸው :: ታዲያ ዶክተር የተሰጣቸው ርእስ ስለማንነት ( አይደነቲቲ ) ጉዳይ ነበር ገለጻ የሚያደርጉት :: ያ ርእስ ኦነጎችን ደስ ያሰኘ እንደሆነ አልጠራጥርም :: ስገምት :: አንድ ቀን አንድ ኦነግን የሚደግፍ የወለጋ ልጅ የስራ ባልደረባዬ "እኛ ኦሮሞዎች አይደንቲያችን ተሰርቆአል ብሎኛል :: የትኛው መንታፊ ሌባ አይደንቲቲውን መቼና የት እንደሰረቀው ግን አልገለጸልኝም :: ወደሳቸው ልመልሳችሁ ማለቴ ወደ ዶክተሩ :: ዶክተር እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ አይደንቲቲ አለው አሉ :: ቀጠሉ "" ያለ አይደንቲቲ የተፈጠረ ሰው የለም :: ያንድ ሰው መለያው አይደንቲቲው ነው እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ዩኒክነስ አለው ራሱን በራሱ ዲፋይን የሚያደርግበት የራሱ ማንነት መገለጫ አይደንቲትው ነው :: መቼም ዶክተር ከሚናገሩት ውስጥ 75% እንጊሊዝኛ ነው 25% ብቻ ናት ተጣርታ የወጣች አማርኛ ! እንጊሊዝኛ ኔፓ የሆነ ሰው የሳቸውን ንግግር ሰምቶ ገብቶት ሳይሆን ደንዞንዝና ተክዞ ይወጣል :: ትካዜ የሚመጣው እኮ አንድ ነገር ሳይገባን ሲቀር ነው :: እና ዶክተር ብሬ ስለሳቸው መናገር ጀመሩ ቅድም እንዳልኴችሁ ውይይቱ ስለ አይደንቲቲ ( የማንነት መገለጫ ጉዳይ ነው : "እኔን ውሰዱኝ አሉ ብሬ ..እኔ ኢኮኖሚስት ነኝ ወሮልድ ክላስ ኢኮኖሚስቶች ጋር ስሆን እይደንቲትዬ ኢኮኖሚስት ነው :: ሙዚቃ ነፍሴ ነው ሙዚቃ እወዳለሁ ....እዚህ ያላችሁ አንዳዶች ታውቃላችሁ ...(ባይናቸው የሆኑ ሰዎችን መፈላለግ ጀመሩ ) ጉራጌ ነኝ ያ ደሞ እይደንቲትዬ ነው :: ከናንተ ለየት ባለ ሁኔታ ክትፎና ቆጮ እወዳለሁ :: (ሁለት ጣታቸውን እንደ ባላ አድርገው ለተሰብሳቢዎቹ አሳዩ ) ክትፎ እግዜር አወጣት ...እንደ ቁርጥ ስጋ ሊበልቷት ነበር :: ሌላ አይደንቱትዬ ደሞ የፍላዲሌግፊያ ኢግል ክለብ ዋና ደጋፊ ነኝ :: እኔ ያንን ክለብ ሰምቼው ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም :: ምናልባት በሳቸው ስቴት የሚኖሩ የአሜሪካን ፉት ቦል ተጫዋቾች ይሆኑ ይሆናል :: ስለ እግር ኴስ ቢያወሩ ወይም የማንቼን ስም ቢጠሩ ጎ ..ጎ ብሬ እላቸው ነበር :: ጎዖዖዖዖዖል ....:: እንደው የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ብዬ ነው :: በቸር ያገናኘን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Tue Jul 19, 2011 9:39 pm Post subject:
ለዳግማዊና መላምት ሰላምታዬ አክብሮቴ ይድረስ :: እናንተ የጽሁፉን ሀሳብ ይዛችሁ ምስጋናችሁንም ችትቻሁንም አቀረባችሁልኝ :: ቴንኩዩ :: ( እንጊሊዝኛ መቀላቀል የምሁር ምልክት ነው :: ማን እንጊሊዝኛ ተናግሮ ማን ይቀራል ..? ማን ከማን ያንሳል ? ) የዶክተርን ብሬንም የዶክተር ድሮ ድፎንም የነአምንንም ቪዲዮ ይሀው በግላጭ አምጥቸዋለሁና ኑና እንዋቀስ :: ሀጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ አለላ ትነጣለች :: እንደ ጀበና ብትጠቁር እንደ ባዘቶ ትነጣለች ተብሏልና ( ትንቢተ ኢሳያስ ላይ ) ፈረሱም ሜዳውም ይሀውና እንግዲህ ኑና እንቧቀስ :: ቁረጽ በሎ ... ቁረጽ በሎ .... ቁረጽ በሎ ...ግፋ በሎ ...በሎ በሎ በሎ ...በሎ ..... Just kidding!! እናንተ በጻፍኩት ጭብጥ ላይ አስተያየት ስትሰጡ በቀደመው ዘመን ፍርፍር በመባል የሚታወቀው ሙና ደሞ በቅርጹና በፊደላት አጣጣል ላይ አስተያት ሰጠ :: ትልልቅ ጭንቅላቶች ሀሳብን ትንንሽ ጭንቅራቶች ደሞ ...ምንን ልበል .. እንግዲህ ይሄ የሚያሳየን ዋርካዋ ውስጥ ራሺናል ቲንከርስ ያሉትን ያህል የፌስ ቡክ ሙክት የሆኑ ኢራሽናል ቲንከርስም እንዳሉ ነው :: አስተማሪ ነበርኩም ብሎኛል አንዷን ልጅ አሳዝናኝም ከ ሲ ወደ ኤ አመጣሆአት ብሏል :: እንግዲህ የኢትዮጵያ የትምርት ጥራት ስለመወደቁ አንዱ ተጠያቂ እሱ ስለመሆኑ አልገባውም :: እዚህ ዋርካ ላይ ኢትዮፒያንስ ስኩል ኦፍ ቶውት እንክፈት የሚል አንዱ ድሩዬ ለምሳሌ በጽሁፉ መጨረሻ ህወአት መታነቅ አለበት እያለ ከሚዘጋ ሙናን እንደ በሬ ጠልፎ ቢጥለው ፌይር ኢትዮጵያዊ ባልኩት ነበር :: ዳሩ ጉዳዩ የፌይረነስ ጉዳይ አይደለም :: ጉዳዩ ወዲህ ነው :: ይሁን እስኪ :: ለማንኛውም ውይይቱን ስሙትና አስተያየት እንድትሰጡበት ይሀው እዚህ አለ :: መላ ምት ዶክተሩ ምንም የረባ ነገር አልተናገሩም ለማለት አልደፍርም :: አንዳንድ ጥሩ ነገር አሁን ሰማሁ :: የኢትዮጵያ ፖሎቲካ ችግር ሁልጊዜ የኌላችንን ስለምናይ ወይም ያለፍንበትን ስለምናይ ነው :: የኌላችን ሳይሆን የፊታችን ማየት መጀመር አለብን አሉ :: መልካም ነው ::
መጣነ :: http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=CmFwi1BM55o _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የተሞናሞነው Joined: 11 May 2011 Posts: 1126
Posted: Wed Jul 20, 2011 2:17 am Post subject:
አይ አንተ ጂሉ ወያኔ ...የቋንቋውን ህግ ተከትለህ ፍሬፈርስኪ ወያኔያዊ ዜናህን ዘብዝብ ብሎ መምከር ቁም ነገር አይደለምን አንዳች ቁምጥና ይያዝህና ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለውን 'የሚገርሙህን አንዳንድ ነገሮች ላነበበ ሰው አንድ ነገር ይረዳል ....አንተን የሚገርሙህ ...የሚጨንቁህ ... የሚጠዘጥዙህ ...የሚከነክኑህ ...የሚያንቁህ ...አንቆ ይጣልህና ....በሙሉ ከዘረኛው ህዋሃት ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰቦች ናቸው ...ሁሉም እንደናንተ ከዘረኛው አይኔን ግንባር ያርገው ወያኔ ፋብሪካ ተፈብርካችሁ እንደወጣችሁት አይነት እንዲያስብ ትፈልጋላችሁ ....አንተም አንዱ ሳሙና (ከህዋሃት ዘረኛ ላቦራቶሪ የተፈጠርህ አይጥ ማለት ይሻላል መሰል ) ነህና የተለየ ሃሳብ ያለው ወይም ካንተ ጎራ ውጭ ያልተሰለፈ ሰው የሚያደርገው ሁሉ ያንቅሃል እና እዚህ መጥተህ የሚያስገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች እያልክ ትለፋደዳለህ ....ይሄ ነው ፍሬ ፈርስኪ ማለትስ ለፍዳዳው ....ባለፈው ለበአል ቤቱ ተጠርተህ ሄደህ እንኳን ገና ለገና ሰውየው ያንተ ፖለቲካ አስተሳሰብ ወገን ስላልሆነ የሚስቱን ዶሮ በልተህ ቡናውን ጠጥተህ እዚህ መጠህ ስትለፋደድ አንብቤ ግን ያው ከህዋሃት የላቦራቶሪ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው አይጦች የሚጠበቅ ስለሆነ እንዳንተ ሳይገርመኝ አንብቤህ አልፌያለሁ ....ስለዚህ ፍሬ ፈርስኪ ማለት አንተ እንጂ ሞንሟናው አይደለም
ወይ ጋዜጠኛ ነኝ አትበለን ....አንዱም ባለፈው ሲነግርህ ነበር ...ቋንቋውን አስተካክል ብሎ ...አማርኛችን እትለፋደድበት ግድ ይለናልና ዝም አንልህም ...ቋንቋውን ሳትችል አንተም ነገ ወያኔ ብድግ አድርጎ የበረከትን ቦታ ሰጥቶህ አማራ ክልል ጉብ ትላለህ ...ከዚያ እንደበረከት ( መርገሙ ) የአማርኛ ቪኦኤ ለቃለ መጠይቅ ሲጋብዝህ በአማርኛ ቃለ ምልልስ አልሰጥም ብለህ በትግርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ትሰጣለህ (በርግጥ ከህዝቡ ስላልሆነና ስለማይወደው እንጂ ቋንቋው ጠፍቶትስ አይደለም )....ይሄስ ግን እንዴው ከሚገርሙህ አንዳንድ ነገሮች ውስጥ አይጨመርም ...የብአዴኑ (የህዋሃት አሽከር ) የአማራው ድርጂት ትልቅ ሰው በረከተ መርገሙ በአማርኛ ቃለ ምልልስ አልሰጥም ብሎ በትግርኛና በእንግሊዝኛ ሲሰጥ ....ሳሙና አለ ፕሮፌሰር መስፍን ...እኔ ደግሞ አይጥ ብያችኋለሁ ...በላቦራቶሪ አንድ አይነት እንድትሆኑ ተፈጥራችሁ ጦቢያን እንድታጠፉ የተበተናችሁ አጥፊ አይጦች
ሞንሟናው ዘብሔረ -ጎዣም
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ለዳግማዊና መላምት ሰላምታዬ አክብሮቴ ይድረስ :: እናንተ የጽሁፉን ሀሳብ ይዛችሁ ምስጋናችሁንም ችትቻሁንም አቀረባችሁልኝ :: ቴንኩዩ :: ( እንጊሊዝኛ መቀላቀል የምሁር ምልክት ነው :: ማን እንጊሊዝኛ ተናግሮ ማን ይቀራል ..? ማን ከማን ያንሳል ? ) የዶክተርን ብሬንም የዶክተር ድሮ ድፎንም የነአምንንም ቪዲዮ ይሀው በግላጭ አምጥቸዋለሁና ኑና እንዋቀስ :: ሀጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ አለላ ትነጣለች :: እንደ ጀበና ብትጠቁር እንደ ባዘቶ ትነጣለች ተብሏልና ( ትንቢተ ኢሳያስ ላይ ) ፈረሱም ሜዳውም ይሀውና እንግዲህ ኑና እንቧቀስ :: ቁረጽ በሎ ... ቁረጽ በሎ .... ቁረጽ በሎ ...ግፋ በሎ ...በሎ በሎ በሎ ...በሎ ..... Just kidding!! እናንተ በጻፍኩት ጭብጥ ላይ አስተያየት ስትሰጡ በቀደመው ዘመን ፍርፍር በመባል የሚታወቀው ሙና ደሞ በቅርጹና በፊደላት አጣጣል ላይ አስተያት ሰጠ :: ትልልቅ ጭንቅላቶች ሀሳብን ትንንሽ ጭንቅራቶች ደሞ ...ምንን ልበል .. እንግዲህ ይሄ የሚያሳየን ዋርካዋ ውስጥ ራሺናል ቲንከርስ ያሉትን ያህል የፌስ ቡክ ሙክት የሆኑ ኢራሽናል ቲንከርስም እንዳሉ ነው :: አስተማሪ ነበርኩም ብሎኛል አንዷን ልጅ አሳዝናኝም ከ ሲ ወደ ኤ አመጣሆአት ብሏል :: እንግዲህ የኢትዮጵያ የትምርት ጥራት ስለመወደቁ አንዱ ተጠያቂ እሱ ስለመሆኑ አልገባውም :: እዚህ ዋርካ ላይ ኢትዮፒያንስ ስኩል ኦፍ ቶውት እንክፈት የሚል አንዱ ድሩዬ ለምሳሌ በጽሁፉ መጨረሻ ህወአት መታነቅ አለበት እያለ ከሚዘጋ ሙናን እንደ በሬ ጠልፎ ቢጥለው ፌይር ኢትዮጵያዊ ባልኩት ነበር :: ዳሩ ጉዳዩ የፌይረነስ ጉዳይ አይደለም :: ጉዳዩ ወዲህ ነው :: ይሁን እስኪ :: ለማንኛውም ውይይቱን ስሙትና አስተያየት እንድትሰጡበት ይሀው እዚህ አለ :: መላ ምት ዶክተሩ ምንም የረባ ነገር አልተናገሩም ለማለት አልደፍርም :: አንዳንድ ጥሩ ነገር አሁን ሰማሁ :: የኢትዮጵያ ፖሎቲካ ችግር ሁልጊዜ የኌላችንን ስለምናይ ወይም ያለፍንበትን ስለምናይ ነው :: የኌላችን ሳይሆን የፊታችን ማየት መጀመር አለብን አሉ :: መልካም ነው ::
መጣነ :: http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=CmFwi1BM55o
_________________http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Sun Aug 28, 2011 3:14 am Post subject:
ገመቹ ኢታና በ 43 አመቱ ትግሬ ነህ ተባለ :: ነገሩ ቀልድ እይደለም :: መራራ እውነት ናት ለገሜ ገመቺሳ :: የሆሩግድሩው ገመቹ በኦርሞነቱና በወለጋ ተወላጅነቱ ሲያወራ ኮራ እያለ ነው :: አንዳንዴ ጀርመኖች ሌሎች ጀርመን ተናጋሪ የሆኑትን የድንበር አካላዮቻቸውን እንደሚያዩት ገሜም እኮ ከማን አንሸ ነው መስል ከባሌና ከርሲ የመጡ ኦሮሞውችን አይኑን ገርበብ አድርጎ ያያቸዋል :: እንግዲህ የማወራው ስለዚህ እኔ ስላወኩት ገመቹ ነው :: ሁሉም ወለጌዎች እንደሱ ያያሉ እንደሱ ያስባሉ ማለት አይደለም :: ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ ግን የገመቹ ኦሮሚፋነት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ተገኘ :: ኢታና ቶላ የገመቹ አባት ገመቹን ከ 9 ከልጆቻቸው ሳይለዩ እንደ ልጆቻቸው ቢያሳድጉትም ለመፈጠሩ የስነ ህይወት ጠበልን ያቀበሉት ግን ኢታና ራሳቸው አይደሉም :: ታዲያ ማን ነው ? እኔንጃ ...! ገመቹ እናቱ አያንቱን በባዝኛው ይምሰል እንጂ በመልክ ካባቱ ጋር ቡዙ አይመሳሰልም :: የልጅ በረከት የበዛላቸው ኢታና አንዱ ልጃቸው ከሌሎች ተለይቶ እሱን ባለመምሰሉ ቅንጣት ታክል አላሳሰባቸውም :: እናቱን ከመሰለ ይበቃል ...ብለው ትተውታል :: እሱም እንደ አባት ታዞ ሲገረፍ አንገቱን ደፍቶ ባብቱ ስር ከብት እየጠበቀ ወተት እየጠጣ ልጅነቱን አሳልፏል :: ሲያድግ ደሞ ሻሂ ቤት በመሄድ የጉርምስናውን ልክ አሳይቶ አድጎአል :: ግንባሩ ሰፋ ብሎ አይኖቹ ጠለቅ ከማለታቸው ሌላ የከንፈሩ ሰብሰብ ማለት ግና ካባቱ ቶላ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው :: ይሄንን ጎፍታኮ ጎፍታኪያ ላረቄ ሙሉልኝ እያለ የሚለው መኮና ኡድሮ እንኴን ተገንዝቧል :: ይሄ በዚህ አንዳለ ዛሬ ለዩናይትድ ኔሽን ተቀጥሮ ወፍራም እንጀራ ከሸኖ ቅቤ ጋር የሚያስበላውን ደሞዝ የሚያገኝው ገመቹ አንድ ቀን ቁርጥ እሱን ከሚመሰል ሰው ጋር ተዋወቀ :: በራሱ ሚስት በኩል :: ነገሩ እንዲህ ነው የሚስቱ የአክስት ልጅ ከአንድ መልከ መልካም ጎረምሳ ጋር ትተዋወቃለች .. ጎረምሳው ባጭር ጊዜ ውስጥ ከልጅቷ ቤተ ዘመዶች ጋር ይተዋወቃል :: ከተዋወቃቸው ሰዎች አንዱ የገመቹ ሚስት ትርሲት ትገኛለች :: ትሪስት ይሄን ያክስቷን ልጅ መጀመሪያ እንዳየችው በመርፌ ከኌላ ጠቅ የተደረገች ያህል ተሰማት :: እፏን ከፍታ እንደ መጮህ አለችና ተወችው .. ሰው አጠገቧ ባይኖር ኖሮ ግን እሪ ማለት ፈልጋ ነበር :: ከፈለጉ እንወራረድ የተከበሩ አንባቢ ሆይ !! ጎረምሳው መደንገጧን ሲያይ እንደ መቀለድ እያለ " የሰራሽው ሀጢአት ካለ ተሰርዮልሻል ..ዳግም ህጢአት እንዳትሰሪ .." አላት :: አነጋገሩና የቃላት አሰባበሩ የባሰ አስደነገጣት :: ሳቅ ሲል ጉንጩ ሰርጎድ ይላል :: ባሏም እንደዚህ አይነት አሳሳቅ እንደሚስቅ ስታውቅ የባሰ ግራ ተጋባች :: ሰው ሳይሆን የባሏን አነጋገር የወሰደ አንድ ወጣት መንፈስ ፊቷ ላይ ቆሞ የሚቀልድባት መሰላት :: ለሰላምታ የዘረጋላትን እጅ ፈራ ተባ እያለች ጨበጠችውና ወደ መኪናዋ ስትገባ አማተበች :: ጎረምሳው ግን ፈገግ እያለ ግን ደሞ የጔደኛው አክስት የፊቷ ገጽታ መለዋወጥ እየገረመው የግቢውን በር በቀስታ ዘግቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ :: አንዳንዴ እኮ ዘርህ የምርጫ ጉዳይ ነው ኢትዮጵያዊዕነትህ ብቻ ነው ምርጫና ድርድር ውስጥ የማይገባው :: ይቀጥላል እንደ ሁኔታው :: ቃሮዬ .. ቃሮዬ ቃሮዬ ... _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዞብል 2 Joined: 30 Jan 2004 Posts: 1987
Posted: Tue Aug 30, 2011 6:59 pm Post subject:
ክብሮም እኔን ግርም የሚለኝ ሆድህን ሳየው ቤቢ ፊያት የታቀፍክ ነው የሚመስለኝ
ዞብል ከአራዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Fri Sep 09, 2011 11:30 pm Post subject:
እንደው የሚገርሙኝን ነገሮች እስኪ አልፎ አልፎ ለመጻፍ እየፈለኩ ጊዜ ውድ ሆነና ቶሎ ቶሎ መምጣት ጠፋ :: እዚህ ዋርካ ውስጥ አንዳንዱ በግድ የምየ ኢትዮጵያ ልጅ ሆነ :: ይገርማል ሌሎችም ደሞ ከዛ ጽበል ጽዲቅ እንደርሳቸው በዋርካው እነሱነታቸው ብቻ እኛም ካነተ ጋር ነን የማለት ይመስላል እንኰን አደረሰህ የእምየ ልጅ ይሉታል :: ሌሎቻንማ ለኢትዮጵያ የእንጀራ ልጆቿ ነን ማለት ነው :: የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ በቀለ ስጋ ቤት ተገኘ አሉ .....ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ ሲቸከቸክ የነበረ የሽንት ቤት ወታደር ዋርካ ፖሎቲካ ክፍል ተገኘ አሉ :: እማ ዘቢደር እኮ ናቸው :: ወይ እንኴን አደረሳችሁ ....ኢትዮጵያዊነትን እኮ የሚገመጥ ሽልጦ አደረጉት ...! እስኪ መጣን በቤቴ የተሰማኝን የታዘብኩትን የገረመኝን እጽፋለሁ :: አግራሞት የያዘላቸው እንደኔ ቤት ከፍተው ይጻፉ ትንታግ እሳት የሚተፋ ብእር ካላቸው :: መልካም በአል ይሁንላችሁ ውድ የአገሬ የኢትዮጵያ ልጆች ::
የጠላሽ አይኑ ይጥፋ ..
የማንነቴ ምንጭ ኢትዮጵያ እገሬ የሚለውን ዘፈን እጋብዛለሁ :: አንቀውታ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዳግማዊ ዋለልኝ Joined: 20 Oct 2010 Posts: 2372
Posted: Sat Sep 10, 2011 12:09 am Post subject:
ሠላም ክቡራን
እንኳን አደረሰህ
Quote: ኢትዮጵያዊነትን እኮ የሚገመጥ ሽልጦ አደረጉት
ኢትዮጵያዊነትንም እንደግንቦት 7 የአርበኝነት ሰርቲፊኬት ሜርዮት ሆቴል አሰልፈው ማደል እንዳይጀምሩ ያሰጋል
ዞብል 2...ለአንተም መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ
ሠላም
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : እንደው የሚገርሙኝን ነገሮች እስኪ አልፎ አልፎ ለመጻፍ እየፈለኩ ጊዜ ውድ ሆነና ቶሎ ቶሎ መምጣት ጠፋ :: እዚህ ዋርካ ውስጥ አንዳንዱ በግድ የምየ ኢትዮጵያ ልጅ ሆነ :: ይገርማል ሌሎችም ደሞ ከዛ ጽበል ጽዲቅ እንደርሳቸው በዋርካው እነሱነታቸው ብቻ እኛም ካነተ ጋር ነን የማለት ይመስላል እንኰን አደረሰህ የእምየ ልጅ ይሉታል :: ሌሎቻንማ ለኢትዮጵያ የእንጀራ ልጆቿ ነን ማለት ነው :: የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ በቀለ ስጋ ቤት ተገኘ አሉ .....ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ ሲቸከቸክ የነበረ የሽንት ቤት ወታደር ዋርካ ፖሎቲካ ክፍል ተገኘ አሉ :: እማ ዘቢደር እኮ ናቸው :: ወይ እንኴን አደረሳችሁ ....ኢትዮጵያዊነትን እኮ የሚገመጥ ሽልጦ አደረጉት ...! እስኪ መጣን በቤቴ የተሰማኝን የታዘብኩትን የገረመኝን እጽፋለሁ :: አግራሞት የያዘላቸው እንደኔ ቤት ከፍተው ይጻፉ ትንታግ እሳት የሚተፋ ብእር ካላቸው :: መልካም በአል ይሁንላችሁ ውድ የአገሬ የኢትዮጵያ ልጆች ::
የጠላሽ አይኑ ይጥፋ ..
የማንነቴ ምንጭ ኢትዮጵያ እገሬ የሚለውን ዘፈን እጋብዛለሁ :: አንቀውታ ::
_________________“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Sat Sep 10, 2011 4:00 pm Post subject:
ላንተም መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ ዳግማዊ ወንድሜ :: በዚህ አመት ቡዙ መስቀለኛ ጥያቄ እያቀረብክ ቡዙዎችን መስቀለኛ መንገድ ላይ አስቀርተሀቸዋል ... አንዳንዶችም ታመው አልጋ ይዘዋልና ጥያቄህን እንድትቀንስ ይሁን የሚል አቤቱታ ቀርቦብሀል መልካም በአል ለሁላችሁም እንዲሁም ለከረከሮው ዞብልም ጭምር :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Sun Sep 25, 2011 7:23 pm Post subject:
ትናንት ማታ የሴት ጔደኛዬ በራሷ ምርጫ መታጠቢያ ቤት ውስጥ የሚሰቀሉ ፎጣዎችን ገዝታ አየሁ :: የቤት እቃ መግዛት ስትፈልግ ከኔ ጋር አትማከርም :: በከለር ወይም በሞዴል አመራረጥ አንገናኝም :: እኔ ባህላዊ ወይም ካዥዋላዊ የሚባሉት አይነት ነኝ :: ፎጣው ከቻይና ይሁን ካዘርባጂያን ወይም ካሩሻ ይሁን ካዲስ አለም እኔን አይመለከትም :: ብቻ ስፈልገው እንደ ፎጣ ሆኖ ይገኝልኝ በቃ .........ጋዬ :: እሷ ግን ኬጂቢ ይመስል ስም አይታ አጣርታ የተሰራበትን ቦታ ና ቢቻል ቢቻል የታዋቂ ሰው ስም አርፎበት እንደሆነ ተመራምራ ካላወቀችም ጠይቃና አስጠይቃ ነው የምትገዛው ...:: ታዲያ ዛሬ እስኪ እንደው ለነገሩ ብዬ ከፎጣው ስር የተጻፈውን ለማየት አብሯት የተሰፋችውን ነጭ ልጣፍ ማንበብ ጀመርኩ :: አይኔን ማመን አልቻልኩም :: ደግሜ አየሁና ብቻዬን እንደ እብድ ሳኩ :: ያለምንም ማጋነን እንዲህ የሚል ጽሁፍ አየሁ ::
kasshun Fina Collection , ይላል :: ከዛ ደሞ ወረድ ብሎ Made in China ይላል :: እንደ ቨርሳቺ ኮሌክሽን , ክርስቲያን ዲዎር ኮሌክሽን , ኤሊዛቤት አርደን ኮሌክሺን የኛው ካሳሁን ፊኛም ኮሌክሺን እንዳለው እኔ አላቅም ነበር ... ጔደኛዬ ለምን እንደሳኩ ብታውቅ ምርጫዋን ያጣጣልኩባት መስሎ ሊሰማት ይችላል ..ያ ከሆነ ደሞ የተጠመደ ፈንጂ እንዳይፈነዳ ስለፈራሁ መሳቄን እንድታውቅብኝ ፊቴን በውሀ ቸብ ቸብ አድርጌ ወጣሁ :: ምሽቱ የሰላም እንዲሆን ... _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ኮ ር ማ ው Joined: 17 Oct 2010 Posts: 312
Posted: Mon Sep 26, 2011 12:34 pm Post subject:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ትናንት ማታ የሴት ጔደኛዬ በራሷ ምርጫ መታጠቢያ ቤት ውስጥ የሚሰቀሉ ፎጣዎችን ገዝታ አየሁ :: የቤት እቃ መግዛት ስትፈልግ ከኔ ጋር አትማከርም :: በከለር ወይም በሞዴል አመራረጥ አንገናኝም :: እኔ ባህላዊ ወይም ካዥዋላዊ የሚባሉት አይነት ነኝ :: ፎጣው ከቻይና ይሁን ካዘርባጂያን ወይም ካሩሻ ይሁን ካዲስ አለም እኔን አይመለከትም :: ብቻ ስፈልገው እንደ ፎጣ ሆኖ ይገኝልኝ በቃ .........ጋዬ :: እሷ ግን ኬጂቢ ይመስል ስም አይታ አጣርታ የተሰራበትን ቦታ
ና ቢቻል ቢቻል የታዋቂ ሰው ስም አርፎበት እንደሆነ ተመራምራ ካላወቀችም ጠይቃና አስጠይቃ ነው የምትገዛው ...:: ታዲያ ዛሬ እስኪ እንደው ለነገሩ ብዬ ከፎጣው ስር የተጻፈውን ለማየት አብሯት የተሰፋችውን ነጭ ልጣፍ ማንበብ ጀመርኩ :: አይኔን ማመን አልቻልኩም :: ደግሜ አየሁና ብቻዬን እንደ እብድ ሳኩ :: ያለምንም ማጋነን እንዲህ የሚል ጽሁፍ አየሁ ::
kasshun Fina Collection , ይላል :: ከዛ ደሞ ወረድ ብሎ Made in China ይላል :: እንደ ቨርሳቺ ኮሌክሽን , ክርስቲያን ዲዎር ኮሌክሽን , ኤሊዛቤት አርደን ኮሌክሺን የኛው ካሳሁን ፊኛም ኮሌክሺን እንዳለው እኔ አላቅም ነበር ... ጔደኛዬ ለምን እንደሳኩ ብታውቅ ምርጫዋን ያጣጣልኩባት መስሎ ሊሰማት ይችላል ..ያ ከሆነ ደሞ የተጠመደ ፈንጂ እንዳይፈነዳ ስለፈራሁ መሳቄን እንድታውቅብኝ ፊቴን በውሀ ቸብ ቸብ አድርጌ ወጣሁ :: ምሽቱ የሰላም እንዲሆን ...
ርካሽ ቢራ ጠጥተህ ነው ማንበብ የተሳነህ ...ለስሙ ሰው ሲሳሳት አርማለሁ ትል ነበር ..እኔም ላርምህ እስኪ በል ተቀበል መቼም አይዋጥልህ
ካሳሁን ፈኛ ( kassahun figna ) ተብሎ ነው የሚነበበው
ያንተ ግን
ካሱን ፊና ( kasshun fina ) ነው እናም የምልክ ካሱን እና ካሳሁንን ምን አገናኝው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Mon Sep 26, 2011 4:29 pm Post subject:
ኮርማው ( በሰላም ነው ግን ይሄ ስም ) እረ እታረማለሁ ...መቼ እኔ ና አንተ ተነጋግረን እናውቅና ነው ሀሳብ አልቀበልም ያልኩት ...ነው ወይስ እንደ ታሜ ገለታ አራት አይነት ማሊያ ለብሰሽ ዋርካ ውስጥ ትፋለሚያለሽ ...? በሌላ ስም ምናልባት ተገናኝተን እንዳይሆን ብዬ ነው :: ያንተው እንዳለ ሆኖ ጥዋት ከቤት ስወጣ እስኪ ላጣራ ብዬ መልሼ ፎጣውን አየሁት :: ትክክለኛውን አሁን ነው ያገኘሁት :: ካሳ ፊኛ ይላል :: (Kasa Fina collection ) ይሄ ነገር ግራ አጋብቶኛል :: ካሳ ፊኛ ማነው ቻይናዊ ነው ...ኢትዮጵያዊ ነው ...? ከሆነ ደሞ ይሄ ስም እንዴት አይታወቅም ...ወይ ደሞ በቻይኝና ሌላ ትርጉም ይኖረው ይሆን .. ይሄ ካሳ ፊኛ ማለት ? ....እስኪ አጣራልኝ ኮርማው ...እኔም የማገኘውን ይዥ ብቅ እስክል ድረስ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ኮ ር ማ ው Joined: 17 Oct 2010 Posts: 312
Posted: Mon Sep 26, 2011 5:48 pm Post subject:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ኮርማው ( በሰላም ነው ግን ይሄ ስም ) እረ እታረማለሁ ...መቼ እኔ ና አንተ ተነጋግረን እናውቅና ነው ሀሳብ አልቀበልም ያልኩት ...ነው ወይስ እንደ ታሜ ገለታ አራት አይነት ማሊያ ለብሰሽ ዋርካ ውስጥ ትፋለሚያለሽ ...? በሌላ ስም ምናልባት ተገናኝተን እንዳይሆን ብዬ ነው :: ያንተው እንዳለ ሆኖ ጥዋት ከቤት ስወጣ እስኪ ላጣራ ብዬ መልሼ ፎጣውን አየሁት :: ትክክለኛውን አሁን ነው ያገኘሁት :: ካሳ ፊኛ ይላል :: (Kasa Fina collection ) ይሄ ነገር ግራ አጋብቶኛል :: ካሳ ፊኛ ማነው ቻይናዊ ነው ...ኢትዮጵያዊ ነው ...? ከሆነ ደሞ ይሄ ስም እንዴት አይታወቅም ...ወይ ደሞ በቻይኝና ሌላ ትርጉም ይኖረው ይሆን .. ይሄ ካሳ ፊኛ ማለት ? ....እስኪ አጣራልኝ ኮርማው ...እኔም የማገኘውን ይዥ ብቅ እስክል ድረስ ::
አሁንም ተሳስተሀል ..እኔማ እጸድቅ ብዬ እንጂ ፖለቲካ እንጀራየ አይደለም እናም አሁንም ላርምህ
ካሳ / kassa ) ሲሆን ፊኛ ደግሞ (figna )
ያንተ ሚስት የገዛችው ፋይናል ሴል እሲኪወጣ ጠብቃ ማለት ነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4280
Posted: Sat Oct 01, 2011 2:58 am Post subject:
አቤት አቤት ስንት ተመጻዳቂ አለ ....ጃል ...!! "Oops" አለች ፋንታዬ እኮ ናት ...በንጊሊዝኛ ልተርት ብላ ... :: "ማን ከማን ያንሳል ....ሁ ማይነስ ሁ .....? " ተብሏል እኮ :: ለዛም ነው ፋንታዬ መላኩ በእንጊሊዝኛ ተረት መተረት የጀመረችው :: እንደምናሉልኝ የተከበሩ ወዳጄ :: በ 7 አመቷ ታላቅ ወንድሟን ከቤት ወጥቶ ሳይመለስ ቀርቶ ናፍቆት አላስችል ብሏት ወጥቶ የቀረውን ወንድሜን እፈልጋለሁ ብላ ስለ ወንድሟ ደህንነት መልክት ይዘው የመጡ ነጋዴዎችን ከኌላ ከኍላ እየተከተለች በዛው በረሀ የቀረች ጔደኛ አለችኝ :: የሀገረ - አሜሪካን ኑሮን ለማሸነፍ ዛሬ አብረን ደፋ ቀና እንላለን :: የትናቱን የበረህ - ህይወት በነጋ በጠባው ትመግበኛለች :: ከድሜዋ ልጅነት አንጻር ተጋዳላይ መሆኗን ከኔና ከጔዶቿ በስተቀር ቡዙ ሰው አያቅም :: እሷም የዋዛ አይደለችም :: ስለማንነቷ አንድም ፍንጭ አትሰጥም :: አንድ ቀን በወሬ በወሬ አንስተን የመለስ ዜናዊ ሚስት እኮ የሚሊዮን ዩሮ ልብስ ገዛች ተብሎ አነበብኩ አልኴት :: ሳቆዋን ለቀቀችው :: እንደዛ ስቃ አታቅም :: "መለስ ሌላ ሚስት አገባ እንዴ ...ወይስ ጔል ጎላን ነው የምትለኝ ....?" አለችኝ ..."
እረ የበረሀ ሚስቱን ነው አልፈታም " አልኮአት ::
"ጔል ጎላ ( የሷ አጠራር ነው አዜብ ጎላን ማለቷ ነው ) እዚህ ግቢ እኮ የምንላት አይደለችም ... አብረን ነው በረሀ ያደግነው ... አጋጣሚ ሆኖ እንጂ ከመለስ ጋር በፐርሰናሊቲ በጣም ይለያያሉ .. እሱ የሁላችንም አስተማሪ ነበር .. ከመጫወት ከመሳቅ በስተቀር ብር ራሱ ምን መልክ እንዳለው የምታቅ አይደለችም አለችኝ ጨዋታ ልፊያ ቀልድ የምትወድ ነበረች ጔል ጎላ ..." እያለች ትዝታዋን አጫወተችኝ :: የጔደኛዬን ትዝታ አንድ ቀን ሰብስቤ አቀርበዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :: :: ታሪክ በታሪክ ነቱ ይቀመጣል :: ትናንት ምን ነበርን ዛሬስ ምንድነን ነገ ወዴት ነን እነዚህ ነገሮች ናቸው ሁሌም ባምሮዬ የሚመላለሱት :: ...ስለ ወያነ ሳስብ ሁሌም የማስበው እቺን ጕደኛዬን ነው :: ወያኔነት ገብቷት ይሁን ወይም የታላቅ ወንድሟ ናፍቆት አላስችል ብሏት በረሀ ገባች :: የህወአት ሰራዊት መቀሌ ሲገባ መቀሌን ከያዙት ጋንታዎች የሷ ጋንታ አንዱ ነበር :: ታዲያ ያኔ የነበረውን ስሜቷን ስታጫውተኝ .. " ከቡዙ አመት በኌላ ወደ መቀሌ ስንገባ ትልቅ ውቅያኖስ ውስጥ የገባሁ አይነት ሆኖ ነበር የተሰማኝ .." ብላኛለች :: የሰው ኑሮ ንግግርና ህይወት ጨዋታና የማህበራዊ ህይወት ብሂል ተደማምረው አፈዘዙኝ ... አደነዘዙኝ ... እንኴን አዲስ አበባ ይቅርና ከመቀሌ ሰው ጋር አንድ አይነት ቌንቌ እየተነጋገርን መግባባት አልቻልንም ነበር .." ብላ አጫውታኛለች :: ኒውዮርክ ወይም ሆንክ ኮንግ የሆነባት ያህል ነበር የተሰማት ...ያኔ :: እንዳልኩት የወያኔዋን ጔደኛዬን ትዝታዎች አለፍ አለፍ እያልኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ :: እለተ አረብ ነውና ትንሽ ፈግግ የሚያደርግ ነገር ስፈልግ ፍልፍሉን አገኘሁ ..( በረከት በቀለን ):: በረከት በቅርብ ቀን የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት እንግዳችን ይሆናል :: እስከዛው ለቅምሻ ያህል ከተጫወታቸው ቡዙ ኮሞዲዎች አንዱን ልጋብዝዎና ልሰናበት ::የነገ ሰው ይበለን :: እቺን ይጫኑ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com