WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ሡልጣን ውይይቱ ተጀምሯል !
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sun Apr 10, 2011 7:52 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ሡልጣን :-

አባባሉ ከተመቸህ Copyright ማዕቀብ የለም ::ባንተ በኩልም እንደዚያው እንደሚሆን እገምታለሁ ::ወደ ውይይታችን ስመለስ ደግሞ :-

1)ስለ አብና ወልድ 'ሥልጣን ' ልዩነት ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀሃል ::ባለፈው ያልኩት እንዳለ ሆኖ ወልድ ለአብ ይታዘዛል አብ ግን ማንንም አያዝም ::ወልድ የማያውቃቸው ነገሮች ሊኖሩ ሲችሉ ከአብ ግን የተሰወረ ምንም ነገር የለም :.:ሰውንም ሆነ ሌሎች ፍጥረታትን ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ፈጥረዋል ::የዕለት ሲሳያችንን የሚሰጠን አብ ሲሆን የምንሞተው ግን ከአዳም በወረስነው ኃጥያት ምክንያት ነው ::ከሙታን የሚያስነሳንም አብ ነው ::መነፈስ ቅዱስን በሚመለከት ከአብ የሰረጸ ሲሆን ለምሳሌ ኢየሱስ ሲጠመቅ በጴንጤ ቆስጤ ቀን ሐዋርያት ተአምራትን ሲሰሩ ወዘተ ...ኃይሉ ታይቷል ::ከአብና ወልድ ጋር ግን አናወዳድረውም ::

2)ቅዱስንና ጻድቃን እንደኛው የአዳምና የሔዋን ኃጥያት ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ ከተራው ሰው ግን በባህርያቸውና በሥራቸው ይለያሉ ::ለኃይማኖታቸው ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ከእግዚአብሔር የሆኑ ተአምራትን የሰሩም ሊሆኑ ይችላሉ ::ባለፈው ግልጽ አላደረግኩም ይሆናል እንጂ እነዚህ ሰዎች በራሳቸው የሚያደርጉት ምንም ነገር የለም ::በእግዚአብሔር ፈቃድ የሰው ልጆችን ሊረዱ ይችላሉ እንጂ ::

የጠየቅኩህን በሚግባ አብራርተኸዋል አመሰግናለሁ ::

Quote:
እኔ ደግሞ ልቀጥል

መርሀባ ጠይቀኝ ካላወቅኩ ጠይቄ እመጣለሁ

Quote:
11)በኢስላም ንስሐ አለ ወይ ?

አዎ !በሚገባ ንስሀ አለ ንስሀ ተቀባይነት እንዲኖረው 3 ቅድመ ሁኔታዎች አሉ
1 በሰራው ወንጀል መጸጸት 2 ከወንጀሉ በቅጽበት ማቆም 3 ወደ ወንጀሉ ላለመመለስበ እርግጠኝነት መወሰን ናቸው :;እነዚህ መስፈርቶችን ያሟላ ንስሀ በመግባት ወደ ፈጣሪው ብቻ ይቅርታ ይጠይቃል ::

Quote:
12)ዒሳ በመጨረሻው ቀን ይመጣል ብለህ ታምናለህ ?

አዎ በጣም ይመጣል ::እንወደዋለን እናከብረዋለን ::ቀሪ ህይወቱን በኢስላም እንደወትሮው ይመራል

Quote:
13)አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ምን ትሆናለች ?

የሰው ነፍስ እስከ ትንሳኤ ቀን በጊዜያውነት የምትቀመጥበት ቦታ አላት

Quote:
14)በኢስላምስ ጻድቃንና ቅዱሳን አሉ አይደለም ወይ ?

በኢስላም ጻድቃን ወይም ቅዱሳን ተብለው በካታጎሪ መከፈላቸውን ሳይሆን አላህን በጣም የሚፈራ እና ያዘዘውን ሁሉ የሚፈጽም ከተከለከለው መጥፎ ነገር የሚከለከል ሙእሚን ይባላል :: በህይወት እያለ በነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት ጀነት ከተመሰከረላቸው ሰዎች ውጭ እከሌ ጻዲቅ ነው ብለን መወሰን አንችልም :;
ነገር ግን ጥሩ አማኞች የተሻለ ደረጃ በገነት እንደሚተብቃቸው የታወቀ ነው ::እኔ በአላህ የታዘዝኩትን
እሰራለሁ እንጅ ጻድቃን ነኝ ብየ መናገር አልችልም ::

Quote:
15)ከመካና መዲና በተጨማሪ ሁሉም ሙስሊም የሚቀበላቸው የተቀደሱ ቦታዎች አሉ ?

በኢስላም የተቀደሱ ቦታዎች 3 ናቸው መካን መዲናን እና በይተል መቅዲስ (ቁድስ ) እነኝህ ናቸው :;

Quote:
በተረፈ ውይይቱ ሥርዓቱን እንደጠበቀ መሆኑ አስደስቶኛል ::So far so good! ማለት የሚወድ አንድ አስተማሪ ትዝ አለኝ ::

በውይይቱ ደስተና ነኝ
ዛሬ እረፍትህ ቀን ሲለሆነ እድሉን ለመጠቀም ነው ቶሎ የመለስኩ
Arrow እስኪ ወደ ጥያቄዎች ልሂድ Question
Arrow ስለ ገነት እና ገሀነም እምነታችሁ ምን ይላል ?
ሰው በገነት እንዴት ይኖራል ?በገሀነምስ ?
Arrow ክርስትና ታላቅ ወንጀል የሚባለው ምንድን ነው ?
Arrow እምነታችሁ አንድ ሰው ሌላ ሚስት ማግባት አይችልምን ?መፍታት ይፈቀዳል ?
Arrow በመጽሀፋችሁ ስለ ኢስላም ወይም ስለ ነብያችን የሚያወሳ አንቀጽ ይኖራል ብለህ ታምናለህ ?
Arrow መጽሀፍ ቅዱስ እስከ አሁን የጥንት ቅርጹን ይዞ ሳይበረዝ ቆይቷል ብለህ ታምናለህ ?
ከምስጋና ጋር
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Apr 16, 2011 12:31 pm    Post subject: Reply with quote

ሡልጣን :-አሁንም በድጋሚ ሰላምታዬን በማቅረብ ወደ ጥያቄዎችህ እመለሳለሁ :-

Arrow ገነትን በሚመለከት ምድራዊውን ነው ወይስ ሰማያዊውን ?ምክንያቱም አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እስካከበሩ ጊዜ ድረስ የኖሩበት ቦታ ምድራዊው ገነት ሲሆን ሰው ከሞተ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነፍሱ ልትኖርበት የምትችለው 'ቦታ ' ደግሞ ሰማያዊው ገነት ነው ::ገሃነም ግን ንስሐ ያልገባ ኃጢያተኛ ነፍስ የምትሠቃይበት ነው ::

Arrow ወንጀል ስትል ኃጢያት ማለት ፈልገህ ከሆነ በማያሻማ ሁኔታ ከኃጢያቶች ሁሉ የከፋው ዝሙት ነው ::

Arrow አንድ ክርስትያን ሚስቱን መፍታት የሚችለውና ሌላ ማግባት የሚችለው ሚስቱ ካመነዘረች ብቻ ነው ::::ከዚህ በቀር ሚስቱ የሞተችበት ሰው እንደገና ማግባት ይችላል ::
Arrow መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ በተለየ ሁኔታ ስለ ኢስላም ወይም ስለ ነቢያችሁ ተጠቅሷል የሚል እምነት የለኝም ::

Arrow ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከሆነ የምትለው አዎን ስህተት አለባቸው እላለሁ ::የመጀመርያው (Original) መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ምንም ዓይነት ስህተት የለም ::

እስቲ እንደተለመደው ደግሞ የእኔን ጥያቄዎች ላስከትል

16) ሱና ኢስላም ውጭ ያሉት ሙስሊሞች ሙናፊቓን ናቸው ብለህ ታምናለህ ?

17)ቑርኣንና ሐዲሶች የሚጋጩበት ቦታ ይኖራል ?

1Coolበአማርኛ ስንት ዓይነት የቑርኣን ትርጉሞች አሉ ?የትኛውስ ነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአብዛኛው የሚጠቀሙበት ?

19)በገነት (አኺራ ) ልዩነት አለ ወይስ ገነት (ጀነት ) የገባ ሁሉ እኩል ነው ?

20)የዓለም ፍፃሜ (የውመል ቒያማ ?) ሲደርስ የሚታዩ ምልክቶች አሉ ?

Happy weekend!
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sat Apr 16, 2011 3:36 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሡልጣን :-አሁንም በድጋሚ ሰላምታዬን በማቅረብ ወደ ጥያቄዎችህ እመለሳለሁ :-

እንደምን አለህ ? እየጠበቅኩህ ነው
[/quote]
Quote:
Arrow ገነትን በሚመለከት ምድራዊውን ነው ወይስ ሰማያዊውን ?ምክንያቱም አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እስካከበሩ ጊዜ ድረስ የኖሩበት ቦታ ምድራዊው ገነት ሲሆን ሰው ከሞተ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነፍሱ ልትኖርበት የምትችለው 'ቦታ ' ደግሞ ሰማያዊው ገነት ነው ::ገሃነም ግን ንስሐ ያልገባ ኃጢያተኛ ነፍስ የምትሠቃይበት ነው ::

Arrow ወንጀል ስትል ኃጢያት ማለት ፈልገህ ከሆነ በማያሻማ ሁኔታ ከኃጢያቶች ሁሉ የከፋው ዝሙት ነው ::

Arrow አንድ ክርስትያን ሚስቱን መፍታት የሚችለውና ሌላ ማግባት የሚችለው ሚስቱ ካመነዘረች ብቻ ነው ::::ከዚህ በቀር ሚስቱ የሞተችበት ሰው እንደገና ማግባት ይችላል ::
Arrow መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ በተለየ ሁኔታ ስለ ኢስላም ወይም ስለ ነቢያችሁ ተጠቅሷል የሚል እምነት የለኝም ::

Arrow ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከሆነ የምትለው አዎን ስህተት አለባቸው እላለሁ ::የመጀመርያው (Original) መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ምንም ዓይነት ስህተት የለም ::

አመሰግናለሁ

Quote:
እስቲ እንደተለመደው ደግሞ የእኔን ጥያቄዎች ላስከትል

ይቻላል

Quote:
16) ሱና ኢስላም ውጭ ያሉት ሙስሊሞች ሙናፊቓን ናቸው ብለህ ታምናለህ ?

በቅድሚያ የሙናፊቅ ትርጉም በመጠኑ ልጥቀስልህ
ሙናፊቅ ማለት ሙስሊም ሆኖ አስመሳይ ተራማጅ ማለት ነው
ይህም ማለት ለሰው ይምሰል እና ለይዩልኝ የሚሰግድ :ሰው በማያየው ሁኔታ የሚተው አላህን ብዙ የማያወሳ እምነቱ ከምላሱ እንጅ ከልቡ ውስጥ ያልሆነ ማለት ነው ::
ከሱኒ ሙስሊም ውጭ ያሉት በማወቅ እና ባለማወቅ ስህተት የሚፈጽሙ ሁሉም ስያሜያቸው አንድ አይደለም ::
ስለዚህ በማወቅ ልባቸው ሳያምን አስመሳይ ተራማጆች ሙናፊቅ ሲባሉ ባለማወቅ ከሱና ውጭ ያለ ነገር የሚሰሩ ደግሞ ጃሂል ይባላሉ (ጃሂል ማለት ማይም ወይም አላዋቂ ) ማለት ነው ከዚህም በላይ ከኢስላም ጓዝን ጠቅልሎ የሚያስወጣ ወንጀል ክህደት ላይ የሚያደርስ ይኖራል

Quote:
17)ቑርኣንና ሐዲሶች የሚጋጩበት ቦታ ይኖራል ?

በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ::ቁርአን ከሀዲስ ጋር ወይም ቁር አን ከቁ አን ጋር ሀዲስ ከሀዲስ ጋር ፈጽሞ አይጋጭም ::
ምናልባት እኛ የግንዛቤ ሁኔታ እና እውቀት ማነስ ካልሆነ በስተቀር ::የተጋጨ የሚመስለን ነገር ካለ እውቀት ማነስ ነው ::ለዚያም ነው 1432 አመት ያክል ቁር አን ሳይበረዝ ሳይከለስ እስከ አሁን የቆየበት ምክንያት ፈጣሪ አላህ እኔ እጠብቀዋለሁ ስላለ ሙስሊሞች ቁርአን ይበረዛል ይከለሳል ብለው አይሰጉም ::
ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ይህን በተመለከተ ለሚያቀርቡት
ስርአት ያለው ጥያቄ ኢስላም ከበቂ በላይ መልስ አለው ::
ነገር ግን የአንድን አንቀጽ ሙሉ መል እክት ሳይረዱ ከፊቱ ወይም ከኍላ ቃላትን ብቻ እየገነጠሉ ይጋጫል ወይም እንደዚህ ያለ ነገር አለ ማለቱ ከቅንነት ማነስ ነው ::የፈጣሪ ንግግር ፍጹም አይጋጭም ::

Quote:
1Coolበአማርኛ ስንት ዓይነት የቑርኣን ትርጉሞች አሉ ?የትኛውስ ነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአብዛኛው የሚጠቀሙበት ?

በቁጥር ይህን ያክል ብየ መግለጽ አልችልም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሀይለስላሴ ጊዜ የተተረጎመ አለ አሁን ደግሞ ሙስሊም ምሁራን መሰረታዊ ጭብጡን ሳይለቁ የተረጎሙበት ሁኔታ ይስተዋላል ::ኢትዮጵያውያን ሁሉንም እንደትርጉም እንጠቀምባቸዋለን ::ነገር ግን የአረበኛውን ቁር አን የመሰለ ነገር የለም እኛ አሁን አረበኛ ቋንቋ እየተረዳን ስንመጣ የቁር አን ትርጉም ራሱ ስለሚገባን አማርኛ ትርጉሙ ለጀማሪዎች እንዲረዱት ያክል ነው

ተአምረኛው ቁርአን በሰው ልጅ ጭንቅላት ውስጥ በቀላሉ ሴቭ የመሆን እና ቁር አንን በቃላቸው ያጠኑ ወጣቶች ፍጹም ሳይሳሳቱ እና ቁር አን ሳያዩ ማንበብ የመቻላቸው ሚስጥር ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ እውነቱን እስከፈለጉ ድረስ ቁር አንን ገር ማድረጉን ያመላክታል ::
ሌላው እርግጠኝነት የምነግርህ በኡቅር አን ውስጥ እንኳንስ አንድ ቃል እና ፊደል ይቅርና አንድ ነጥብ እንኳ ብትጨመር በቀላሉ ይታወቃል :;
ለዚህም ብሎ ፈጣሪያችን የቁር አንን ቢጤ አምሳያ ሰውም ሆነ አጋንንት ተሰባስቦ አንድ አንቀጽ ማምጣት እንደማይችል ተናግሯል ::
ስለ ቁር አን እና ሀዲስ ባወራ አልሰለችም ምክንያቱም የጥንት ሰዎች ታሪክ ያለበት የወደፊቱ ትንበያ የተተነበየበት እና አኡን እየደረሰ ያለበት ሁኔታ አለ ::
ማብራሪያውን ስላስረዘምኩት ይቅርታ

Quote:
19)በገነት (አኺራ ) ልዩነት አለ ወይስ ገነት (ጀነት ) የገባ ሁሉ እኩል ነው ?

በጀነት በደረጃ እጅግ በጣም መበላለጥ አለ ::ይህም መበላለጥ የሚሆነው በዚህ ምድር ባስቀደምከው መልካም ስራ እና ለፈጣሪህ እንደ ስግድተህ እና እንደጾምህ መጠን
በአጠቃላይ እንደመልካም ስራህ በጣም የደረጃ ልዩነት አለ ::

Quote:
20)የዓለም ፍፃሜ (የውመል ቒያማ ?) ሲደርስ የሚታዩ ምልክቶች አሉ ?

በጣም አሉ !ታናናሽ እና ታላላቅ በመባል ይታወቃሉ
አስፈላጊ ከሆነ እንደጉድ ይዘረዘራሉ ምክንያቱም አሁን እየታዩ ስለሆነ .....................::

እኔም ጥያቄየን ላስከትል ዊክ ኢንድ ሳያልፍ

1 በኦርጆናል ይዘቱ አይደለም ተበርዟል ብለህ የምትጠረጥረው የአማርኛውን ትርጉም ነው ወይስ የቱን ነው ?ኦርጂናሉ ባይብል የተጻፈበት ቋንቋው ምንድን ነበር ?
2 ጀነት ያልኩህ የምድሩን የነ አዳምን አይደለም ::ይህን ካልኩስ እስኪስለጀነት በመጽሀፋችሁ እንዴት እንደሚመስል አስረዳኝ ::ገሀነም ውስጥ ሰዎች እንዴት ይቀጣሉ ?በመንፈስ ወይስ በስጋ ?
4 መጽሀፍ ቅዱስ 50 ስህተት እንዳለው በሸህ አህመድ ዲዳት ቀርቧል ስህተቶችም ተገልጸዋል እንዴት ታየዋለህ ?
5 መጽሀፍ ቅዱስን ማን ጻፈው ? ጸሀፊው ከሀዋሪያዎች ውስጥ አንዱ ነበር ?
በል እንዳይበዛብህ
ቸር እንሰንብት
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቸርነቱ

ኮትኳች

Joined: 05 Sep 2010
Posts: 174

PostPosted: Sat Apr 16, 2011 3:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው:

ቸር እንሰንብት [/quote]

መላሹ ይህንንም ይመልሳሉ የሚል ተስፋ ለኝ

How many angels helped Muhammad at badr?
Three thousand

Remember thou saidst to the Faithful: "Is it not enough for you that Allah should help you with three thousand angels (Specially) sent down?

Qur'an 3:124
One thousand

Remember ye implored the assistance of your Lord, and He answered you: "I will assist you with a thousand of the angels, ranks on ranks."

Qur'an 8:9
But here Allah claims he doesn't even send angels near kaafirs.

We send not down the angels save with the Fact, and in that case (the disbelievers) would not be tolerated.

Qur'an 15:8

ሀዲት
How may wives did Solomon have?
One-hundred

Narrated Abu Huraira:"Tonight I will go round (i.e. have sexual relations with) one hundred women (my wives)

Sahih Bukhari 7:62:169
Ninety

Narrated Abu Huraira:Allah's Apostle said, "(The Prophet) Solomon once said, 'Tonight I will sleep with ninety women, each of whom will bring forth a (would-be) cavalier who will fight in Allah's Cause

Sahih Bukhari 8:78:634
Seventy

Narrated Abu Huraira Abu Huraira reported that Sulaiman b. Dawud said: I will certainly have intercourse with seventy wives during the night, and every wife amongst them will give birth to a child, who will fight in the cause of Allah. It was said to him: Say:" Insha' Allah" (God willing), but he did not say so and forgot it.

Sahih Muslim 15:4069
Sixty

Narrated Abu Huraira; Allah's Prophet Solomon who had sixty wives, once said, "Tonight I will have sexual relation (sleep) with all my wives so that each of them will become pregnant and bring forth (a boy who will grow into) a cavalier and will fight in Allah's Cause."

Sahih Bukhari 9:93:561

በግጭት ጉዳይ ባትወያዩ መልካም ነው እስልምና በእግጠኝነት ግጭት በግጭት ነው 100%
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 17, 2011 9:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላምታዬን በማስቀደም :-ስለ ሰጠኸኝ መልሶች እያመሰገንኩ

1)መፅሐፍ ቅዱስ መጀመርያ የተፃፈው በዕብራይስጥ በሱርስት (አራማይክ )(ብሉይ ኪዳን ) እና ግሪክ (አዲስ ኪዳን ) ቋንቋዎች ሲሆን እንደዚህ ሲባል ግን በአሁኑ ዘመን የሚነገሩት የእነዚህ ልሳናት መጠርያዎችን የያዙ ቋንቋዎች ማለት ግን አይደለም ::የትርጉም ስህተት ሊኖር ይችላል ያልኩት አማርኛው ላይ ብቻ ሳይሆን የትናውም ትርጉም የሰው ሥራ በመሆኑ መጠኑ ይነስም ይብዛ ሁሉም ላይ ሊኖር ይችላል ብዬ እገምታለሁ ::

2)ስለ ገነትና ገሃነም የምጨምረው ነገር ቢኖር ገነትም ሆነ ገሃነም የምትገባው ነፍሳችን ናት እንጂ ሥጋችን አይደለም ::ነፍሱ ገነት የገባች ሰው ለዘላለም ተደስቶ ሲኖር ነፍሱ ገሃነም የገባችበት ደግሞ ለዘላለም በእሳት እየተቃጠለ ይኖራል ማለት ነው ::

3)አሕመድ ዲዳት የትኛውን ትርጉም ወስዶ ስህተቶቹን እንደቆጠረ አላውቅም ::በተለያዩ ትርጉሞች ላይ ያሉትን ስህተቶች ደምሮ ከሆነ ግን በሺህ የሚቆጠሩ ስህተቶች ቢገኙ አይገርመኝም ::ምክንያቱም በዘመናችን ማንም እየተነሳ ለአመለካከቱ በሚመቸው መንገድ ሊተረጉም ስለሚችል ነው ::የቀድሞ ትርጉሞች ግን ግሪክኛ ዕብራይስጥ ግእዝ ላቲን አርመንኛ ወዘተ ብዙም ስህተት ይገኝባቸዋል ብዬ አልገምትም ::

4)መፅሐፍ ቅዱስን ለመፃፍ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታት የወሰደ ሲሆን ፀሀፊዎቹም ነቢያት ካህናት ሐዋርያት ወዘተ ናቸው

ደህና እንሰንብት
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Mon Apr 18, 2011 2:03 pm    Post subject: Reply with quote

አመሰግናለሁ
በአንተ ጥያቄዎች እስክንገናኝ
እስከ ሳምንት ......መልካም ሳምንት
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sat May 14, 2011 7:51 pm    Post subject: Reply with quote

ሡልጣን :-የከበረ ሰላምታዬ ይድረስህ እያልኩ :-

የተለመደው ሳምንታዊ ውይይታችን ከተቋረጠ ሶስት ሳምንታትን አስቆጥሯል ::በኔ በኩል ያሉትን ምክንያቶች መዘርዘር አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም ::በተረፈ ግን ቤታችን ተጠብቃ ስለቆየችን ደስ ብሎኛል ::

የኔን ጥያቄዎች እየጠበቅክ ነውና እነሆ :-

21)ሙስሊሞች ለቑርኣን (ለቃሉ ብቻ ሳይሆን ለተፃፈበትም ወረቀት ) የተለየ ክብር እንደሚሰጡት በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመረዳት ችያለሁ ::እስቲ አንድ ሙስሊም ቑርኣንን በምን ዓይነት ሁኔታ ማስቀመጥና ማንበብ እንዳለበት ብታብራራልኝ ::እነዚህ ሁኔታዎች ሙስሊም ላልሆነ ሰውስ ይሰራሉ ወይ ::የዓረብኛው ቑርኣንና በሌላ ቋንቋ የተተረጎመ ቑርኣን እኩል ክብር ሊሰጣቸው ይገባል ?

22)አንድ ሙስሊም ካፊር የሆነ ሰው ቤት ውስጥ ሆኖ የሶላት ሠዓት ቢደርስበት እዚያው መስገድ ይችላል ወይ ?

23)አንድ ሙስሊም ካፊር ማግባት ይችላል ወይ ? ሴቷስ ካፊር ወንድ ማግባት ትችላለች ?::ማለትም ካፊሮቹ ሳይሰልሙ ማለት ነው ::

24)የኢስላም ምልክት (ጨረቃን ከዋክብቱ ) መሠረታቸው ምንድነው ?

25)በአንድ ሙስሊም መቃብር ላይ ሐውልት ማቆም የሚፈቀድበት ሁኔታ አለ ?ለታዋቂ ሰዎችስ አደባባይ ላይ ሐውልት ማቆም ይፈቀዳል ?

26)አንድ ሙስሊም ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን የማግባት መብት አለው ?ግዴታስ አለበት ?

27)ለሙስሊም ወንዶች የተሰጠ የአለባበስ ሥርዓት አለ ?

2Coolአንድ ሙስሊም ባንክ (ኢስላማዊ ያልሆነ ) ገንዘብ ሲያስቀምጥ ወለዱን ምን ያደርገዋል ?

29)አንድ መስማትና መናገር የተሳነው ሰው መስለም ቢፈልግ እንዴት ነው የሚሆነው ?

30)በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያሉ ሱኒ ሙስሊሞች በሙሉ የሚመሩበት ሰው አለ ?

ዛሬ ጥያቄዎቹን በርከት ያደረግኳቸው ስለተጠፋፋን ነው ::መልካም ጊዜ !!
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sun May 15, 2011 7:16 am    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሡልጣን :-የከበረ ሰላምታዬ ይድረስህ እያልኩ :-

[/quote]
እንደምን አለህ ተጠፋፋን አይደል ?

Quote:
የተለመደው ሳምንታዊ ውይይታችን ከተቋረጠ ሶስት ሳምንታትን አስቆጥሯል ::በኔ በኩል ያሉትን ምክንያቶች መዘርዘር አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም ::በተረፈ ግን ቤታችን ተጠብቃ ስለቆየችን ደስ ብሎኛል ::

ወደ ሰላማዊ ውይይታችን እንኳን ደህና መጣህ

Quote:
21)ሙስሊሞች ለቁርኣን (ለቃሉ ብቻ ሳይሆን ለተፃፈበትም ወረቀት ) የተለየ ክብር እንደሚሰጡት በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመረዳት ችያለሁ ::እስቲ አንድ ሙስሊም ቑርኣንን በምን ዓይነት ሁኔታ ማስቀመጥና ማንበብ እንዳለበት ብታብራራልኝ ::እነዚህ ሁኔታዎች ሙስሊም ላልሆነ ሰውስ ይሰራሉ ወይ ::የዓረብኛው ቑርኣንና በሌላ ቋንቋ የተተረጎመ ቑርኣን እኩል ክብር ሊሰጣቸው ይገባል ?

ቁርአን የአላህ ቃል ስለሆነ እጅግ በጣም እናከብረዋለን ::
የአረበኛውን ቁርአን ለሰላት እንደምንዘጋጀው አይነት ውዱዕ (ትጥበት ሳይኖረን እጅ መንካት ክልክል ነው )ምክንያቱም ንጹህ ሆነን እንጅ እንዳንነካው ቁር አን ተገልጾልና !ቆሻሻ ቦታ ካልሆነ በስተቀር ካለ ውዱእ ግን በቃል ማንበብ እንችላለን
አረበኛ ያልሆነውን ቅዱስ ቁር አን ካለ ውዱ መንካት ይቻላል ::ሙስሊም ያልሆነ ሰው ቁር አንን መንካት ክልክል ነው :: ቁር አንን ከጠረፔዛ ወይም ከሸልፍ ላይ ማስቀመጥ ይቻላል መሬት ላይ ግን እንደማንኛውም መጽሀፍ ማስቀመጥ አይቻልም ::

Quote:
22)አንድ ሙስሊም ካፊር የሆነ ሰው ቤት ውስጥ ሆኖ የሶላት ሠዓት ቢደርስበት እዚያው መስገድ ይችላል ወይ ?

ባለቤቱ ከፈቀደለት እና ቦታው ወይም ንጹህ መስገጃ ካገኘ ይቻላል

Quote:
23)አንድ ሙስሊም ካፊር ማግባት ይችላል ወይ ? ሴቷስ ካፊር ወንድ ማግባት ትችላለች ?::ማለትም ካፊሮቹ ሳይሰልሙ ማለት ነው ::

ሙስሊም ወንድ ካፊር ሴት ሳትሰልም ማግባት ይችላል ሙስሊም ሴት ግን ካፊር ወንድ ካልሰለመ ማግባት አትችልም

Quote:
24)የኢስላም ምልክት (ጨረቃን ከዋክብቱ ) መሠረታቸው ምንድነው ?

ጨረቃ እና ኮከብ የኢስላም ምልክት ናቸው ማለት አይቻልም ነገር ግን የረመዳንን ጾም ለመጀመር እና ለመጨረስ እንደ ምልክት በጨረቃ እንጠቀማለን ምክንያቱም ጨረቃ ከመጀመሪያው ወር 1 ቀን ትንሽ ሆና 15 ቀን ላይ ትክክል ግማሽ 30 ቀን ሙሉ ትሆናለች ስለዚህ እሷን አይታችሁ ስተወጣ ጹሙ ከዚያ ወር ሲሞላ አፍጥሩ ተብለን ታዝዘናል ::ከዚህ ውጭ ከኢስላም ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ::

Quote:
25)በአንድ ሙስሊም መቃብር ላይ ሐውልት ማቆም የሚፈቀድበት ሁኔታ አለ ?ለታዋቂ ሰዎችስ አደባባይ ላይ ሐውልት ማቆም ይፈቀዳል ?

ለሙስሊም መቃብር ሀውልት ለምንም ለማንም የትም ቦታ መስራት ክልክል ነው እንደዚህ የሚያደርጉ ካሉ ሀይማኖታቸውን የማያውቁ ጃሂሎች (ማይሞች )ናቸው ::

Quote:
26)አንድ ሙስሊም ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን የማግባት መብት አለው ?ግዴታስ አለበት ?

መብትም የለው ግዴታም የለበትም !!!ነገር ግን የወንድሙ ሚስት ሌላ ባል ብታገባ የወንድሙ ልጆች ይበደላሉ ብለው ከሰጉ እና በሌላ ምክንያትም ሁለቱ ለትዳር ተፈላልገው ከተስማሙ ሊጋቡ ይችላሉ ::በግዴታ የወንድምን ሚስት መውረስ የማይምነት ስርአት ነው እንጅ በኢስላም የለም ::

Quote:
27)ለሙስሊም ወንዶች የተሰጠ የአለባበስ ሥርዓት አለ ?

ወንዶች በአለባበስም ይሁን በተለያዩ ሁኔታዎች ሴቶችን መመሳሰል ተከልክሏል ::ከዚህ ውጭ ግን ሱሪ ቁርጭምጭሚት በታች ማስረዘም ክልክል ነው :: እንብርት እስከ ጉልበት በታች ያለው የሰውነት ክፍል መሸፈን አለበት ::

Quote:
2Coolአንድ ሙስሊም ባንክ (ኢስላማዊ ያልሆነ ) ገንዘብ ሲያስቀምጥ ወለዱን ምን ያደርገዋል ?

ወለዱን እለት ጉርስ ለሌለው ምስኪን ይሰጠዋል ነገር ግን ...ነገር ግን ምንዳ አያገኝበትም ::ካልሆነ ደግሞ ሽንት ቤት ለመስራት ይጠቀምበታል ::

Quote:
29)አንድ መስማትና መናገር የተሳነው ሰው መስለም ቢፈልግ እንዴት ነው የሚሆነው ?

የዚህን መልስ አላውቀውም
አስፈላጊ ከሆነ ልጠይቅ እችላለሁ

[quote]30)በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያሉ ሱኒ ሙስሊሞች በሙሉ የሚመሩበት ሰው አለ ?/[quote]

የሙስሊሞች መሪ ወይም ኢማም ተብሎ የሚጠራ አንድ ግለሰብ የለም ምክንያቱም አለም በተለያዩ መሪዎች ስለምትተዳደር ነገር ግን የሙስሊሞች መመሪያ ቁር አን እና ሀዲስ ነው :;ነብዩ ሙሐመድ በህይወት ባይኖሩም የሳቸውን ፈለግ በመከተል በኢስላም ህይውታችንን እንመራለን እንጅ አንድን ግለሰብ አንከተልም ::
ነግር ግን በተለያዩ ሀገር ያሉ ሙስሊሞች በሀገራቸው ሀይማኖታዊ ጉዳይ ክርክር ከተነሳ እልባት የሚሰጥ ሙፍቲ የሚባል ሰው አለ ይህ ሀይማኖት እውቀቱ የተካነ ሰው በመካከል ለሚነሳ ጥያቄ የመጨረሻ ብይን ይሰጣል ይህ እንግዲህ በማህበራዊ ህይወት ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለሙፍቲ ሄደው በመናገር መልሱ ይሰጣቸዋል ::
ፈትዋ የሚባለው ነገር ታላቅ እውቀት ስለሚጠይቅ ሙፍቲ መሆነ ቀላል አይደለም :;
ምናልባትም ጥያቄህን የተረዳሁት ካልመስለህ አብራርተህ ጠይቀኝ ::

Quote:
ዛሬ ጥያቄዎቹን በርከት ያደረግኳቸው ስለተጠፋፋን ነው ::መልካም ጊዜ !!

ጥያቄዎች ብዙም አይባሉም አንድ ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ልንገርህ
መልሶችን እየመለስኩ ያለሁ ስለ ኢስላም ካነበብኩት ትንሽ እውቀቴ ነው በማንኛውም ጊዜ የኔ መልስ ከኢስላም ህግጋቶች ጋር ተጋጭቶ ካገኘኸው ስህተቱ ከኔ እንጅ ከኢስላም አይደለም ::በተለየ ሁኔታ በአጽንኦት በልዩ ትኩረት እንዲመለስልህ የምትፈልገውን ጥያቄ ካለ አሳውቀኝ እና ጠይቄ እመለሳለሁ

አሁንም ለመጠየቅ እድሉን ስጥቸሀለሁ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sun May 15, 2011 1:02 pm    Post subject: Reply with quote

በድጋሚ ሰላም :-

አንዳንድ መልሶችህ ላይ አሁንም ጥያቄዎች አሉኝ ::ሌላ ጊዜ ጠቅለል አድርጌ ለማቅረብ አስቤአለሁ ::በነገራችን ላይ ያንተም ሆኑ የኔ መልሶች የግላችን ብቻ መሆናቸው ግልጽ ነው ::እንዲያውም መልስ ላጣንላቸው ጥያቄዎች ሌላ ሰው ባንጠይቅ ወይም ሌሎች መፃሐፍትን ባናገለብጥ የተሻለ ይመስለኛል ::እንግዲህ በሰጠኸኝ ዕድል መሠረት ሌሎች ጥያቄዎቼን ላቅርብ ::ያለፈው አልበዛም ስላልክ አሁን በርከት አድርጌዋለሁ ::እንደተመቸህ ቀስ ብለህ መመለስ መብትህ ነው ::የሚያስቸኩል ነገር የለም ::

31)በኢስላም ግራኝ የሆነ ሰው እንዴት ይታያል ?

32)የነቢዩ ሙሐመድ ዝርያዎች በአሁኑ ዘመን በሱኒ ኢስላም ያላቸው ሚና ምንድንነው ?

33)የረመዳን ፆም በመላው ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ በአንድ ቀን የማይጀመረውና የማያልቀው ለምንደነው ?

34)አንድ ሙስሊም ለመስገድ ቢፈልግና የመካን አቅጣጫ ለማወቅ ካልቻለ ምን ያደርጋል ?

35)አንድ ካፊር የሙስሊም ሚዜ ሊሆን ይችላል /ትችላለች ?ሙስሊምስ የካፊር ሚዜ መሆን ይፈቀድለታል ?

36)በኢስላም ትዳር ሳይዙ መኖር (እድሜ ልክ ) የሚፈቀድበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ?

37)ሙስሊሞች መፅሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ይላሉ (አንተም ከላይ ጥይቀኸኝ ነበር ) ቑርኣንም ላይ አለ :::ያልተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ግን በአሁኑ ዘመን አለ ይላሉ ወይስ ምን ሆኗል ይላሉ ?

3Coolአንድን ሐጂ ያላደረገን ሰው ሐጂ ብሎ መጥራት (እንደ ቀልድም ቢሆን ) ችግር አለው ?

39)በኢስላም መከበር ያለባቸው በዓላት የትኞቹ ናቸው ?

40)አንድ ሙስሊም ሙስሊም አይደለሁም ብሎ ሃይማኖቱን እንዲክድ የሚፈቀድለት ሁኔታዎች ምን ዓይነት ናቸው ?
41)የሱኒ ኢስላም ሊቃውንት ሁሉ የሚስማሙባቸው ሐዲሶች የትኞቹ ናቸው ?

42)ኢስላም ስለ ሳይንስ ምን ይላል ?

43)መስጊድ ሄዶ የሚሰግድ እቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ከሚሰግድ ሰው የሚበልጥበት ሁኔታ አለ ?

44)በኢስላም ከአሳማ ሌላ እንዳይበሉ የተከለከሉ እንስስሳት አሉ ?

45)አንድ ሙስሊም ውሻ ለማሳደግ ወይም ለማሳደር የሚፈቀድለት ሁኔታዎች አሉ ?

46)ከቤተሰቡ ሙስሊም የሆነና ከካፊርነት ወደ ሙስሊምነት በተቀየረ ሰው መሐል ልዩነት አለ ?

47)ቑርኣን ላይ ማስታወሻ መፃፍ ወይም የሚፈለግ ቦታ ላይ ምልክት ማድረግ ይፈቀዳል ?

4Coolበኢስላም ነቢዩ ሙሐመድ በጀነት መርየምን (የዒሳን እናት ) ያገባሉ ተብሎ ይታመናል ?

49)አንድ ሙስሊም ካፊር ያረደውን መብላት የሚፈቀድለት ጊዜ አለ ?

50)ኢስላም ከመጣቱ በፊት የኖሩ ሰዎች በምን መመዘኛ ነው የሚፈረድባቸው ?

በል እንግዲህ መልካም ጊዜ እየተመኘሁልህ ለዛሬ በዚሁ እሰናበትሃለሁ ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sun May 15, 2011 2:42 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
በድጋሚ ሰላም :-

ሰላምህ ይብዛ

Quote:
አንዳንድ መልሶችህ ላይ አሁንም ጥያቄዎች አሉኝ ::ሌላ ጊዜ ጠቅለል አድርጌ ለማቅረብ አስቤአለሁ ::በነገራችን ላይ ያንተም ሆኑ የኔ መልሶች የግላችን ብቻ መሆናቸው ግልጽ ነው ::እንዲያውም መልስ ላጣንላቸው ጥያቄዎች ሌላ ሰው ባንጠይቅ ወይም ሌሎች መፃሐፍትን ባናገለብጥ የተሻለ ይመስለኛል ::እንግዲህ በሰጠኸኝ ዕድል መሠረት ሌሎች ጥያቄዎቼን ላቅርብ ::ያለፈው አልበዛም ስላልክ አሁን በርከት አድርጌዋለሁ ::እንደተመቸህ ቀስ ብለህ መመለስ መብትህ ነው ::የሚያስቸኩል ነገር የለም ::

ተስማምቻለሁ

Quote:
31)በኢስላም ግራኝ የሆነ ሰው እንዴት ይታያል ?

እኔ እስከማውቀው ምንም ችግር የለውም ከቻለ በቀኝ እጁ ቢበላ ይመረጣል ነገር ግን ግራኝ ሆኖ ካልቻለ አይገደድም
ከዚህ ውጭ የማውቀው ነገር የለም

Quote:
32)የነቢዩ ሙሐመድ ዝርያዎች በአሁኑ ዘመን በሱኒ ኢስላም ያላቸው ሚና ምንድንነው ?

የነብይ ዘር መሆን ምንም ጥቅም የለውም
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለልጃቸው ለፋጡማ ''አንች ፋጡማ ሆይ ነፍስሽን ከገሀነም እሳት ጠብቂ :የነብይ ልጅ መሆንሽ አይጠቅምሽም እንዳሉ ተዘግቧል ::
የኖህ ልጅ ከነአን ከሰማይ በወረደ ውሀ ተጥለቅልቆ ሲጠፋ ጌታየ ምነው ልጄን ብለው አምላካቸውን ሲማፀኑ እሱ ልጅህ አይደለም ስራው ትክክል አይደለም እና !ተብለው ተገሥጸዋል ::
እናም የነብይ ወገን ወይም ዘመድ መሆን ዋጋ የለውም
ለመሸረሻ አንድ የሚገርም :የሚያሳዝን ታሪክ ልንገርህ ::
ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁአለይሂ ወሰለም በሆነ አጋጣሚ ከባልደረቦቻቸው ጋር እያወሩ እያለ አንድ የገጸር ሰው መጣና ስለ ሞተው አባቱ የት እንደሆነ ጠየቀ እሳቸው አባትህ እሳት ውስጥ ነው አሉት በዚህ ጊዜ ሰውየው ቅር ማለቱን ስላዩ አባቴ እና አባትህ እሳት ውስጥ ናቸው አሉት ! ነብዩ ሙሐመድ እናታቸውን ቀብር ለመጎኘት አላህን አስፈቀዱ ፈቀደላቸው :; አንተ ትምራት ዘንድ ይቅርታ ልጠይቅላት ብለው ተማጸኑ አይቻልም ተባሉ ::
ተመልከት ይህ እናታቸው እና አባታቸው ነው ከዚህ በላይ ዝምድና አለ ?
ምክንያቱም በኢስላም ከላህ ውጭ ያለን ነገር እያመለከ የሞተ እሳት ነው እና :: ቁርአንም 'አላህ እሱ የስልጣን ተጋሪ አድርገው ሌሎችን የሚያመልኩ ሰዎችን (የሚያሻርኩትን ) አይምርም ከዚህ ውጭ ያለውን ወንጀል ግን ከፈለገ ይምራል ካልፈለገም ይቀጣል ::
ስለዚህ የነብይ ዘር መሆን ዋጋ የለውም መልካም ስራ ላይ መዘውተር እንጅ !!!

Quote:
33)የረመዳን ፆም በመላው ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ በአንድ ቀን የማይጀመረውና የማያልቀው ለምንደነው ?

ሙስሊሞች ጨረቃን አይተው ነው የሚጾሙ በዚህ መሰረት አሜሪካ እና ሳኡዲ ያለው ብዙ የሰአት ልዩነት አለ ሳኡዲ ዛሬ ማታ ከታየ አሜሪካ ነገ ጠዋት ይታያል እንደማለት ነው ::ስለዚህ ቢበዛ ራቅ ወዳሉት ሀገሮች የአንድ ቀል ልዩነት ይስተዋላል ::
አልፎ አልፎ ጨረቃ መታየቷን በተለያዩ ሚዲያዎች መስማት ያልቻለ ሰው ጾም በተጀመረበት ጊዜ ላይጀምር እና በተጨረሰበት ጊዜ ላይጨርስ ይችላል ::

Quote:
34)አንድ ሙስሊም ለመስገድ ቢፈልግና የመካን አቅጣጫ ለማወቅ ካልቻለ ምን ያደርጋል ?

በተቻለ መጠን ለማወቅ ይጥራል ሰዎችንም ጠይቆ !ከአቅሙ በላይ ከሆነ ግን ወደ ገመተው አቅጣጫ ቢሰግድ ችግር የለም ::በአሁኑ ጊዜ ግን አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ስላለ ይህን አይነት ችግር እምብዛም አይከሰትም

Quote:
35)አንድ ካፊር የሙስሊም ሚዜ ሊሆን ይችላል /ትችላለች ?ሙስሊምስ የካፊር ሚዜ መሆን ይፈቀድለታል ?

የዚህን መልስ አላውቀውም

Quote:
36)በኢስላም ትዳር ሳይዙ መኖር (እድሜ ልክ ) የሚፈቀድበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ?

በፍጹም የለም ::ከጤና ጋር የተገናኘ ችግር ከሌለ በስተቀር ........

Quote:
37)ሙስሊሞች መፅሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ይላሉ (አንተም ከላይ ጥይቀኸኝ ነበር ) ቑርኣንም ላይ አለ :::ያልተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ግን በአሁኑ ዘመን አለ ይላሉ ወይስ ምን ሆኗል ይላሉ ?

መጽሀፍ ቅዱስ የሰዎች ሀሳብ እንደተጨመረበት ቁር አን ገልጾልናል ያልተበረዘ አለ ወይም የለም ለማለት እውቀቱ የለኝም እርግጠኝነት መናገር የምችለው ቁር አን መቸውንም እንደማይበረዝ አላህ እንደሚጠብቀው ቃል የተገባለት መሆኑን ነው ::

Quote:
3Coolአንድን ሐጂ ያላደረገን ሰው ሐጂ ብሎ መጥራት (እንደ ቀልድም ቢሆን ) ችግር አለው ?

ሀጅ ያደረገ ሰውም ቢሆን ሀጅ ተብሎ አይጠራም ይህ በተለምዶ የሚታይ አላዋቂነት እንጅ ይህ ስያሜ አይሰጥም ስለዚህ ሀጅ ያላደረገ ሰው ሀጅ ብትለው ችግር የለውም ::
የሀጅን ስር አት ሀጅ እንዲባል ሳይሆን ወንጀሉን አላህ እንዲምረው ስር አቱ የፈጸመ ሰው እናቱ ማህጸን እንደተወለደ ህጻን ወንጀሉ ይማራል ::በኢስላም ይዩልኝ ለይስሙልኝ የሚሰራ ስራ ሁሉ ዋጋ የለውም :;ስለዚህ ሀጅ ያደረገን ሰው ሀጅ ብሎ መጥራት መሰረት ቢስ ወይም ተለምዶ ባህል ነው እንጅ ኢስላም ህግጋት አይደለም

Quote:
39)በኢስላም መከበር ያለባቸው በዓላት የትኞቹ ናቸው ?

በኢስላም መከበር ያለባቸው በአላት 2 ናቸው እነሱም ኢድ አልፈጥር እና ኢድ አል አድሀ (የአረፋ በአል ናቸው )
ነብዩ ሙሐመድ እና ተከታዮቻቸው ያከበሯቸው እና እንዲከበሩ ያዘዟቸው እነዚህን ሁለቱን ነው ::በተረፈ ጁምአ (አርብ ቀን ) ከሌሎች ቀን የበለጠ ክብር አለው ለዚህም ምክንያቶች አሉ ::ከዚህ ውጭ የሚከበሩ ነገሮች ባህል እንጅ ኢስላምን አይወክሉም

Quote:
40)አንድ ሙስሊም ሙስሊም አይደለሁም ብሎ ሃይማኖቱን እንዲክድ የሚፈቀድለት ሁኔታዎች ምን ዓይነት ናቸው ?

የዚህን መልስ ጠይቄ እመጣለሁ አላውቀውም ::

Quote:
41)የሱኒ ኢስላም ሊቃውንት ሁሉ የሚስማሙባቸው ሐዲሶች የትኞቹ ናቸው ?

ቡኻሪ እና ሙስሊም በመባል የታወቁት ሁለት ሲሆኑ ሌሎች ዘጋቢዎች እነ አቡዳውድ ኢብን ማጀህ ቲርሚዚ እና ሌሎችም አሉ ::ሸህ አልባኒ የሚባሉ ታላቅ አዋቂ (አሊም ) ብዙ ሊቃውንት የሚስማሙባቸውን ሀዲሶች ለይተው ታላቅ ስራ ሰርተዋል ::

Quote:
42)ኢስላም ስለ ሳይንስ ምን ይላል ?

ኢስላም ለሰው ልጅ ጥቂት እውቀት እንጅ ብዙ እንዳልተሰጠ ይናገራል ይጭ ጥቂት እውቀት ግን እስከ አሁን ሳይንስ የደረሰበትን ደረጃ ለማስገኘት ችላለች ::እናም ኢስላም ስለ ሳይንስ ከሚለው ይልቅ ሳይንስ ኢስላምን እውነታ እያረጋገጠ ያለበት ወቅት ነው ::ሳይንስ በጥቅሉ የሰው ልጅ አእምሮ ማለት ይመስለኛል
እናም ሳይንስ ኢስላምን ያረጋግጣል ::
ለምሳሌ ቁርአን ስለ ጉንዳን ባወሳበት ታሪክ ላይ የነብዩሏህ ዳዊት ወታደሮች ሲመጡ ጉንዳኖች የዳዊት ወታደር መጣላችሁ እንዳይሰባብራችሁ ማለታቸውን ነብዩሏህ ዳውድ (ዳዊት ) ሰሙ እንስሳን ቋንቋ የመስማት ችሎታ አላህ ሰጥ ቷቸው ነበር በዚህ ጊዜ ብዙ ሳይንቲስቶች እንዴት ጉንዳን ሰበራለች እያሉ ይሳለቁ ነበር አሁን ግን ከብዙ ጊዜ ምርምር በኍላ ጉንዳን የመስታወት ጸባይ እንዳላት እና እንደም ጸበር አረጋግጠዋል ::ለዚህም ነው ሳይንስ ቁር አንን እውነታ ያረጋግጣል ; ያልኩት ...ብዙ ምሳሌዎች አሉ ::

Quote:
43)መስጊድ ሄዶ የሚሰግድ እቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ከሚሰግድ ሰው የሚበልጥበት ሁኔታ አለ ?

አዎ !27 ደረጃ ይበልጣል ምክንያቱም መስጊድ ሙስሊም ወንድሞች የሚገናኙበት እና ስለ ጤንነታቸው ስለ ማህበራዊ ኑሯቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው ሰላት ሰግደው ከወጡ በኍላ ውጭ የሚወያዩበት አጋጣሚ ስላለ ማንኛውም አዛን የሚሰማ ሙስሊም መስጊድ ሄዶ የመስገድ ግዴታ አለበት ! በተለያየ ምክንያት ግን እቤቱ ሊሰግድ የሚፈቀድበት ሁኔታ አለ

Quote:
44)በኢስላም ከአሳማ ሌላ እንዳይበሉ የተከለከሉ እንስስሳት አሉ ?

አዎ !አሉ ::

Quote:
45)አንድ ሙስሊም ውሻ ለማሳደግ ወይም ለማሳደር የሚፈቀድለት ሁኔታዎች አሉ ?

ይኖራል ብየ እገምታለሁ ለምሳሌ ለአደን ..እርግጠኛ ግን አይደለሁም አስፈላጊ ከመሰለህ ጠይቄ እመልሳለሁ

Quote:
46)ከቤተሰቡ ሙስሊም የሆነና ከካፊርነት ወደ ሙስሊምነት በተቀየረ ሰው መሐል ልዩነት አለ ?

አዎ !ከካፊር ወደ ሙስሊም የተመለሰ ድሮ ይሰራ የነበረው ወንጀል ሁሉ ተሰርዞ ወደ መልካም ስራ ይጻፍለታል ይህ ታላቅ እድል ነው ከዚያ በኍላ ሰላት መስገድ መጾም የመሳሰሉትን ኢስላም መሰረቶች ያከናውናል ::ከዚህ በኍላ የሚሰራው ወንጀል ግን ይጻፍበታል ንስህ ገብቶ ተጸጽቶ እስካልተመለሰ ድረስ !!ከዚህ ውጭ ሁሉም አንድ ናቸው /ሙስሊም ሙስሊም ነው ::በነገራችን ላይ ማንኛውም ሰው ሲወለድ በተፈጥሮ ሙስሊም እንደሆነ ኢስላም ያስተምራል
ቤተሰቦቹ ናቸው ወደ ሌላ እምነት የሚቀይሩት !!

Quote:
47)ቑርኣን ላይ ማስታወሻ መፃፍ ወይም የሚፈለግ ቦታ ላይ ምልክት ማድረግ ይፈቀዳል ?

ቁር አንን ለመሀፈዝ (በቃል ለማጥናት )የጀመሩበትን ቦታ የጨረሱበትን ቦታ ምል ክት ማድረግ ችግር የለውም :;ነገር ግን በቁር አኑ ፊደሎች ላይ ተጽ እኖ በማያስድር መልኩ ነው ::በነገራችን ላይ ከሙሉ ቁርአን ውስጥ አንድ ቃል ይቅርና አንድ ነጥብ እንኳ ብትጨመር በቀላሉ ይታወቃል ::
ነገር ግን ሌላ ከጽሁፍ ውጭ ያለ ምልክት ማድረጉ ይመረጣል እንጅ ማስታሻ መያዝ አይፈቀድም ::

Quote:
4Coolበኢስላም ነቢዩ ሙሐመድ በጀነት መርየምን (የዒሳን እናት ) ያገባሉ ተብሎ ይታመናል ?

የዚህን መልስ አላውቀውም ጠይቄ እመጣለሁ

Quote:
49)አንድ ሙስሊም ካፊር ያረደውን መብላት የሚፈቀድለት ጊዜ አለ ?

አዎ !ምንም አይነት ፕሪኮንዲሽን የለም ! አህለል ኪታብ ተብለው የሚጠሩ አይሁድ እና ክርስቲያን ያረዱትን መመገብ ይችላል

Quote:
50)ኢስላም ከመጣቱ በፊት የኖሩ ሰዎች በምን መመዘኛ ነው የሚፈረድባቸው ?

ኢስላም የጥንት የጠዋት ነው ::ከአዳም ጀምሮ ያሉ ነብያቶች እና ሰዎች እምነታቸው ኢስላም ነበር !ለየዘመናቱ ሰዎች የተለያዩ መጽሀፍት ከፍጣሪ በነብያቶች አማካኝነት መምሪያ ተላልፎላቸዋል ስለዚህ በየወቅቱ ኢስላም ነበር የመተዳደሪያ ደንቡ እንደየሰዎች እና እንደየዘመናቱ ኦሪት
ወንጌል ዳዊት እንዲሁም ለመጨረሻ ጊዜ ቁር አን እስኪሰጠን ድረስ በወቅቱ የነበሩ መጽሀፎች ሁሉ የፈጣሪ አንድነትን አስተምረዋል ::ጥያቄዉም እና ፍርዳቸውም በዚያ መሰረት ይሆናል

Quote:
በል እንግዲህ መልካም ጊዜ እየተመኘሁልህ ለዛሬ በዚሁ እሰናበትሃለሁ ::

ዛሬ እረፍትህ ቀን ከአንተ ጋር ለመወያየት ካለኝ ታላቅ ፍላጎት አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን ዛሬም ቢሆን ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ
ማታ ላይ ይህን ገጽ እጎበኘዋሉ ::

ዘርአይ ደረስ እውነት በአጉል ለማመስገን እና ለመሸንገልም አይደለም የውይይት ስርአትህ ይመቻል :: እርግጥ ስርአት ያለው ሰው ነህ ::አንተም ይህንን አትክድም (አላስፈላጊ ነገር ውስጥ ልግባ ብትል እንኳ ስብእናህ የማይፈቅድልህ አይነት ሰው ሆነህ አግኝቸኻለሁ ::በዚህ ጸባይህ ቀጥልበት :: እድሜም ቢሆን ቢቻል አባቴ ካልሆነም ታላቅ ወንድሜ እንደምትሆን እገምታለሁ ::በጣም አከብርሀለሁ
ከልብም አመሰግንሀለሁ

ምንጊዜም አክባሪህ
ሱልጣን
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sun May 15, 2011 4:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ ሱልጣን :-

እኔ እንኳን ዛሬ ብዙ ጥያቄዎች ስለጠየቅኩህ ይበቃል ብዬ ነበር ::ተጨማሪ ጥያቀዎችን እንዳቀርብ በጋበዝከኝ መሠረት ልቀጥል ::በነገራችን ላይ የምትስማማ ከሆነ ከላይ እንዳልኩት አንተም ሆንክ እኔ መልስ ልንሰጥባቸው ያልቻሉ ጥያቄዎች ካሉ ለጊዜው ብናልፋቸውና ሌላ ሰው ከመጠየቅም ሆነ መፃህፍትን ከማገላበጥ ብንታቀብ ምን ይመስልሐል ?ባይሆን ወደፊት ጥያቄዎቻችንን የጨረስን መስሎ ከታየን ባጥጋቢ ሁኔታ ያልተብራሩ ጥያቄዎች ካሉ እንደገና እንመለስባቸዋለን ::

51)በመሠረቱ ጫትና ቡና እንዲሁም የመሳሰሉ አነቃቂዎች በኢስላም የተከለከሉ (ሐራም )ናቸው የሚሉ አሉ ::አንተስ ምን ትላለህ ?

52)የሸሪዓ ህግና መንግሥታዊ ህግ በሚጋጩበት አገር ላይ ሙስሊሞች ምንድነው የሚያደርጉት ?

53)ፎቶ መነሳት ክልክል ነው የሚሉ ሙስሊሞች አጋጥመውኛል ::አንተስ ምን ትላለህ ?

54)በኢስላም የቅርብ ዘመድ ማግባት እንደሚፈቀድ ይታወቃል ::አንድ ሙስሊም የአጎት ልጅ ማግባት ይፈቀዳል የአክስት ልጅ ግን አይፈቀድም ብሎኝ ነበር ::እስቲ ይህን አብራራልኝ ::የእህት ልጅ የወንድም ልጅ የመሳሰሉትስ ?

55)ሙስሊም ያልሆነ ሰውን አሰላም አሌይኩም ማለት ክልክል ነው የሚባለውስ ?

56)እስቲ ኢማም ,ዓሊም ,ሙላሕ ,ሼኽ ,ቓዲ ,ዑዣዝ ,ሙፍቲ ,አያቶላሕ ,የመሳሰሉትን የኢስላም የማዕረግ ስሞች የሥራ ድርሻቸውንና የማዕረግ ቅደም ተከተላቸውን አብራራልኝ ::

57)አንድ ሙስሊም የራሱንም ሆነ የልጆቹን ልደት ማክበር አይችልም ይባላል ::የልጆች ልደትም ማክበር አይፈቀድም የሚባለው እውነት ነው ?

5Coolሴቶች ለቀብር መሄድ አይፈቀድላቸውም ሲባልም ሰምቻለሁ :.እውነት ነው ?

59)ሚናራ (Minaret) የሌለው መስጊድ የተሟላ አይደለም ማለት ይቻላል ?

60)የኢብራሒም ልጅ ኢስማዔል ነቢይ ነበር ?ነቢዩ ሙሐመድስ የኢስማዔል ዝርያ አለው የሚባለው ?

61)በኢስላም አላህ አንተ ነው አንቱ የሚባለው ?

62)አንድ ሙስሊም ሃይማኖቱን ቀይሮ ከኖረ በኋላ ተጽጽቶ ቢመለስ እንዴት ነው የሚደረገው ?

63)አንድ ካፊርስ ከሰለመ በኋላ ለመተው ቢፈልግ ?

64)በኢስላም ዒሳ ከነቢያት ሁሉ የበላይ እንደሆነ ይታመናል ሲባል እሰማለሁ ::ከዒሳ ቀጥሎስ ማን ነው ?

65)የነቢዩ ሙሐመድ እናትና ሚስቶች በኢስላም የተለየ ቦታ አልቸው የሚባለው እውነት ነው ?

66)አንድ ሙስሊም ለልጁ ጨርሶ ሊያወጣ የማይችላቸው ሥሞች አሉ ?

67)በኢስላም ከቁጥሮች ውስጥ ልዩ ክብር ያለው ቁጥር ወይም የማይወደድ አለ ?

6Coolቴምር ወይም የቴምር ዛፍ የተለየ ክብር አለው ?

69)ከእንስሳትስ የተለየ ክብር ያለው እንስሳ አለ ?

70)በሬሳ ሳጥን መቅበር የተከለከለ ነው የሚባለውስ እውነት ነው ?

በል እንግዲህ ሱልጣን በጣም ካላመሸህ ዛሬውኑ መልስህን ላየው እችል ይሆናል ::ካልሆነም ሌላ ጊዜ ::በኔ በኩል ከአሁን በኋላ አንተ ተጨማሪ ጥያቄዎች ከሌሉህ ላልትወሰነ ጊዜ ሌሎች ትያቄዎችን የማቀርብ አይመስለኝም ::በተረፈ ያንተም የውይይት ባህል እስካሁን ድረስ ተስማምቶኛል ::ምንም ዓይነት ቅሬታ የለኝም ::በሰላም አስጀምሮ ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ በሰላም እንደሚያስጨርሰን ተስፋ አደርጋለሁ ::የሃይማኖት ጉዳይ የሚያልቅ ባይሆንም እንኳ ::እኛ ሰልችቶን ካልተውነው ማለት ነው ::

በቸር ይግጠመን
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sun May 15, 2011 8:53 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም በድጋሚ ሱልጣን :-

እኔ እንኳን ዛሬ ብዙ ጥያቄዎች ስለጠየቅኩህ ይበቃል ብዬ ነበር ::ተጨማሪ ጥያቀዎችን እንዳቀርብ በጋበዝከኝ መሠረት ልቀጥል ::በነገራችን ላይ የምትስማማ ከሆነ ከላይ እንዳልኩት አንተም ሆንክ እኔ መልስ ልንሰጥባቸው ያልቻሉ ጥያቄዎች ካሉ ለጊዜው ብናልፋቸውና ሌላ ሰው ከመጠየቅም ሆነ መፃህፍትን ከማገላበጥ ብንታቀብ ምን ይመስልሐል ?ባይሆን ወደፊት ጥያቄዎቻችንን የጨረስን መስሎ ከታየን ባጥጋቢ ሁኔታ ያልተብራሩ ጥያቄዎች ካሉ እንደገና እንመለስባቸዋለን ::

Quote:
51)በመሠረቱ ጫትና ቡና እንዲሁም የመሳሰሉ አነቃቂዎች በኢስላም የተከለከሉ (ሐራም )ናቸው የሚሉ አሉ ::አንተስ ምን ትላለህ ?

ጫት ሀራም ነው ቡና ግን ልክ እንደሻይ ተቆጥሮ ከተጠጣ እና ከአምልኮት ጋር ካልተያያዘ ችግር የለውም ::
ሌላ አነቃቂ ነግር አደንዛዥ እጽ ሀራም ነው ::

Quote:
52)የሸሪዓ ህግና መንግሥታዊ ህግ በሚጋጩበት አገር ላይ ሙስሊሞች ምንድነው የሚያደርጉት ?

የሸሪአን ህግ ይከተላሉ

Quote:
53)ፎቶ መነሳት ክልክል ነው የሚሉ ሙስሊሞች አጋጥመውኛል ::አንተስ ምን ትላለህ ?

ፎቶ መነሳት በምሁራን መካከል የተለያየ አስተያየት አለ የሰውም ሆነ እንስሳ ሰልበት ውስጥ መስቀል ክልክል ነው ሌላ የአበባ ይወንዝ እና ፏፏቴ የተራራ አይነት ነገር ማንሳትም ይሁን ከቤት ለዲኮር መጠቀም ይቻላል የሰው ምስል ግን አይቻልም ምክንያቱም ዘዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ያን ምስል ወደ ማምለክ ይደረሳል እና ነው :;
በተረፈ ለቁምነገር አስፈላጊ የሆነ መታወቂያም ይሁን ሌላ ፎቶ
ከሴቶች ጋር አላስፈላጊ ቅልቅል እና አስነዋሪ ነገር እስከለለበት ድረስ ችግር የለውም :: እጅ የተሰሩ የሰውም ይሁን እንስሳ ቅርሣ
ቅርጻ ቅርጽ ግን አይፈቀድም ::
Quote:
54)በኢስላም የቅርብ ዘመድ ማግባት እንደሚፈቀድ ይታወቃል ::አንድ ሙስሊም የአጎት ልጅ ማግባት ይፈቀዳል የአክስት ልጅ ግን አይፈቀድም ብሎኝ ነበር ::እስቲ ይህን አብራራልኝ ::የእህት ልጅ የወንድም ልጅ የመሳሰሉትስ ?

የአጎት ልጅ እና የአክስት ልጅ ማግባት ይፈቀዳል

Quote:
55)ሙስሊም ያልሆነ ሰውን አሰላም አሌይኩም ማለት ክልክል ነው የሚባለውስ ?

አሰላሙ አለይኩም የሚባለው የጀነት ሰዎች ሰላምታ ነው ስለዚህ ሙስሊሞች ለሙስሊሞች ብቻ ነው የተፈቀደ ::በነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጊዜ አይሁዶች እየመጡ ይህን ቃል በማመሳሰል ይራገሙ ነበር ነብዩም ወአለይኩም (በናንተ ላይ )ብለው ይመልሱላቸው ነበር ...ማብራራት ይቻላል ...

Quote:
56)እስቲ ኢማም ,ዓሊም ,ሙላሕ ,ሼኽ ,ቓዲ ,ዑዣዝ ,ሙፍቲ ,አያቶላሕ ,የመሳሰሉትን የኢስላም የማዕረግ ስሞች የሥራ ድርሻቸውንና የማዕረግ ቅደም ተከተላቸውን አብራራልኝ ::

ኢማም መሪ የሰላትም ይሁን የሙስሊሞች መሪ ቃዲ የሸሪአ ፍርድ ቤት ዳኛ ሙፍቲ በሀይማኖት ጉዳዮች ብይን የሚሰጥ ታላቅ አዋቂ ሲህን ሸህ 3 አይነት ትርጉም አለው 1 በሀይማኖት ጥሩ እውቀት ያለው 2 እድሜው 40 አመት የሆነ 3 በጣም ሀብታም የሆነ ሸኽ ተብሎ ይጠራል በኢስላም ግን ሸህ ማለት አዋቂ ወይም አሊም እንደማለት ነው :;

5
Quote:
7)አንድ ሙስሊም የራሱንም ሆነ የልጆቹን ልደት ማክበር አይችልም ይባላል ::የልጆች ልደትም ማክበር አይፈቀድም የሚባለው እውነት ነው ?

በኢስላም የማንንም ሰው ወይም ነብይ ልደት አይከበርም ::

[quote]5Coolሴቶች ለቀብር መሄድ አይፈቀድላቸውም ሲባልም ሰምቻለሁ :.እውነት ነው ?[quote]
አዎ እውነት ነው ምክንያት አለው ......ድሮ ይፈቀድላቸው ነበር እለታት አንድ ቀን ሟች በወንጀሉ ሲቀጣ ይሰማ ስለነበት አንጀታቸው አልችል ብለው ቆፍረው ሊወስዱት ፈለጉ በዚህ ምክንያት ተከለከሉ ::
በነገራችን ላይ ቀብር መጎብኘት ያስፈለገበት ምክንያት ሞትን ለማስታወስ እና Fእውታሪን በጥሩ ሁኔታ ለማምለክ እንዲቻል ነው ::

Quote:
59)ሚናራ (Minaret) የሌለው መስጊድ የተሟላ አይደለም ማለት ይቻላል ?

ይህን አልሰማሁም ነገር ግን መስጊድ መሆኑ ታውቆ ሰዎች ሄደው ይሰግዱበት ዘንድ ከሌላው በት ልዩነት መኖር አለበት ::የሌላ አካባቢ ሰዎችም ሚናራውን በማየት መስጊድ መኖሩን አይተው መስገድ ይችሉ ዘንድ ሚናራ ቢኖረው ጥሩ ነው

Quote:
60)የኢብራሒም ልጅ ኢስማዔል ነቢይ ነበር ?ነቢዩ ሙሐመድስ የኢስማዔል ዝርያ አለው የሚባለው ?

አዎ ነብይ ነበር ዝርያቸው አንድ ነው

Quote:
61)በኢስላም አላህ አንተ ነው አንቱ የሚባለው ?

አንተ ነው የሚባል

Quote:
62)አንድ ሙስሊም ሃይማኖቱን ቀይሮ ከኖረ በኋላ ተጽጽቶ ቢመለስ እንዴት ነው የሚደረገው ?

አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢለሏህ ዋነሙሀመደን ረሱሉሏህ ወአነ ኢሳ ብዱሁ ወረሱሉሁ ብሎ መመከር አለበት
ይህም ማለት ሰውነቱን ከታጠበ በኍላ እውነት የሚያመልኩ ጌታ ከላህ በስተቀር የለም ነብዩ ሙሀመድ ነብይ እና መላክተኛ ናእው ኢሳም ነብይ እና መላክተኛ ነው ብሎ ማለት ወደ ኢስላም ያስገባዋል ::ይህ እንግዲህ ጣእረሞት ላይ ሳይሆን ከተመለሰ ነው ::በጣእረሞት ላይ ሆነ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ እያለ እየታገለ የተደረገ ንስሀ ተቀባይነት የለውም ::

Quote:
63)አንድ ካፊርስ ከሰለመ በኋላ ለመተው ቢፈልግ ?

ከሰለመ በኍላ እምቢ ካለ የሞት ቅጣት ይፈጸምበታል ይህ የሚሆነው ግን በሸሪአ በሚተዳደሩ ሀገሮች ላይ ነው እንጅ ማንም ተነስቶ አይገድለውም

Quote:
64)በኢስላም ዒሳ ከነቢያት ሁሉ የበላይ እንደሆነ ይታመናል ሲባል እሰማለሁ ::ከዒሳ ቀጥሎስ ማን ነው ?

በኢስላም ከነብያት ሁሉ በላይ ነብዩ ሙሐመድ ናቸው ከአኢያ ሌሎች አራት ነብያት አሉ ኢሳ ኢብራሂም እና ሌሎችም

Quote:
65)የነቢዩ ሙሐመድ እናትና ሚስቶች በኢስላም የተለየ ቦታ አልቸው የሚባለው እውነት ነው ?

ሚስቶቻቸው የሙእሚኖች ወይም የአማኖች ሁሉ እናት በመባል ይታወቃሉ የተለየ ክብርም አላቸው ነገር ግን እናታቸው በክህደት ስለሞተች ክብር ይቅር እና የፈጣሪ ምህረት እንድታገኝ እንኳ እንዳይጠይቁ አላህ ከልክሏቸዋል ምክንያቱም ኢስላም ትልቁ ወንጀል ከላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ማምለክ ነና !

Quote:
66)አንድ ሙስሊም ለልጁ ጨርሶ ሊያወጣ የማይችላቸው ሥሞች አሉ ?

አዎ አሉ !

Quote:
67)በኢስላም ከቁጥሮች ውስጥ ልዩ ክብር ያለው ቁጥር ወይም የማይወደድ አለ ?

ነጠላ ቁጥሮች ይወደዳሉ ለምሳለ 1 ሶስት አምስት የመሳሰሉት ::

Quote:
6Coolቴምር ወይም የቴምር ዛፍ የተለየ ክብር አለው ?

ተምር የተለየ ክብር እንዳለው አላውቅም ነገር ግን ለብዙ ነገሮች መድሀኒት እንደሆነ አልውቃለሁ ልክ እንደማር ማለት ነው

Quote:
69)ከእንስሳትስ የተለየ ክብር ያለው እንስሳ አለ ?

ለጊዜው አላስታውስም

Quote:
70)በሬሳ ሳጥን መቅበር የተከለከለ ነው የሚባለውስ እውነት ነው ?

የሙስሊሞች የአቀባበር ስነ ራት ልዩ ውበት አለው
ሀብታም እና ደሀ እኩል በነጭ ጨርቅ (ከፈን ) ነው የሚቀበሩ
በሬሳ ሳጥን መቅበር እንደሚቻል ወይም እንደማይቻል አላውቅም

Quote:
በል እንግዲህ ሱልጣን በጣም ካላመሸህ ዛሬውኑ መልስህን ላየው እችል ይሆናል ::ካልሆነም ሌላ ጊዜ ::በኔ በኩል ከአሁን በኋላ አንተ ተጨማሪ ጥያቄዎች ከሌሉህ ላልትወሰነ ጊዜ ሌሎች ትያቄዎችን የማቀርብ አይመስለኝም ::በተረፈ ያንተም የውይይት ባህል እስካሁን ድረስ ተስማምቶኛል ::ምንም ዓይነት ቅሬታ የለኝም ::በሰላም አስጀምሮ ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ በሰላም እንደሚያስጨርሰን ተስፋ አደርጋለሁ ::የሃይማኖት ጉዳይ የሚያልቅ ባይሆንም እንኳ ::እኛ ሰልችቶን ካልተውነው ማለት ነው ::

በቸር ይግጠመን

አመሰግናለሁ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jun 15, 2012 7:56 pm    Post subject: Reply with quote

የአክብሮት ሰላምታ በማስቀደም :-

ሱልጣን ዋርካ ላይ ስምህ ስለማይታይ ወይ እንደኔ አልፎ ልፎ ለማንበብ ብቅ ትል ይሆናል ወይም ደግሞ ጨርሰህ ከዋርካ ርቀህ ይሆናል ::ለማንኛውም ይህን ከዓመት በፊት ያቆምነውን ውይይት መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ አሳውቀኝ ::ጊዜውን ግን እንዴት ይሮጣል !
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 463

PostPosted: Sun Jun 17, 2012 4:51 am    Post subject: Reply with quote

እንደምን አለህ ወዳጀ ? አዎ አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ ::
ውይይቱን ለመቀጠል ዝግጁ ነኝ
ለመልሱ በመዝግየቴ ይቅርታ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1081
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Jun 17, 2012 8:49 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ ሱልጣን :- ወደ ውይይታችን እንኳን በደህና መጣህ እያልኩ ለዛሬ መንደርደርያ እንዲሆን አንዳንድ ነጥቦችን አነሳለሁ ::

Arrow ይህን ርእስ ከዓመት በኋላ ተመልሼ ሳየው ያቋረጥኩት እኔ መሆኔን ተረድቻለሁና በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ ::በተረፈ ለመልሱ አልዘገየህም እንዲያውም እንዲህ ትፈጥናለህ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር ::

Arrow እኔ በበኩሌ በተለይ ባለፉት ወራት paltalk እከታተል ስለነበር የሃይማኖት ውይይቶችንም በሰፊው ተከታትያለሁ ::ካንተ ጋር የተነጋገርንባቸውም ጉዳዮች በሰፊው ሲብራሩ ሰምቻለሁ ::ሆኖም ግን የተለያዩ ሰዎች ሲያስተምሩ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እንደማይስማሙ ለመረዳት ችያለሁ ::

በነገራችን ላይ ያኔ የጠየቅሁህን ጥያቄዎች ሁሉንም ላላስታውስ ስለምችል ደግሜ ላለመጠየቅ ስል 70ውንም ጥያቄዎች እንደገና ማየት ስላለብኝ እስከዚያው ድረስ እንዳላነሳኋቸው እርግጠኛ የምላቸውን ጥያቄዎች ለዛሬ አቀርባለሁ ::

71)paltalk ውስጥ የሚያስተምሩ ሙስሊም ሴቶች አጋጥመውኛል ::ባንተ አመለካከትይህ አካሄድ ትክክል ነው ወይ ?

72)ኡስታዝ የሚባሉት አስተማሪዎች ለዚህ 'ሥልጣን ' ያበቃቸው መመዘኛ ምንድነው ?

73) መጅሊስ የሚባለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አመራር አካል የተቋቋመው በደርግ ዘመን ነው ሲባል ሰምቼአለሁ ::ይህ አባባል ትክክል ከሆነ ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዴት ነበር የሚተዳደሩት ?

74)ከወራት በፊት የተጀመረው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ሁሉንም ሙስሊም ያካትታል ወይስ እነ መለስ እንደሚሉት ጥቂቶች የሚያካሂዱት ነው ?

75)አል ሐባሾች ሙስሊሞች ናቸው ማለት ይቻላል ?

76)ራሱን ዋሃቢያ እያለ የሚጠራ ድርጅት በዓለም ላይም ሆነ በአገራችን አለ ?ካለስ የዋሃቢያና የሰለፊያ ልዩነት ምንድነው ?

77)የነቢያችሁ ሙሐመድ አሟሟት በሕመም ነው ወይስ የሰው እጅ አለበት ?

7Coolሙስሊሞች ከበሉ በኋላ ጣቶቻቸውን የሚልሱበት ምክንያት ሃይማኖታዊ መሠረት አለው ?

79)ክርስቲያን ዓረቦች አላህን እንደ አምላክ ሥም መጠቀማቸው በሙስሊሙ ላይ ቅሬታ አሳድሯል ?

80)ከመካና ከመዲና በክብር ማን ይበልጣል ?ወይስ በሙስሊሙ እኩል ነው የሚታዩት ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
Page 2 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia