WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እንዴት ነው ነገሩ ? የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጎማ እግሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Jun 2007
Posts: 716

PostPosted: Sun May 27, 2012 3:30 am    Post subject: Reply with quote

አይ እነ ተላ በቃ እናንተ Post Modern Public Policy and Economics theory እክታጠኑ አገር ቆማ ትጠብቅ !!
እርስ በርሳችሁ ስትሞከሻሹ ደግሞ እንዴት እንደምታሳዝኑ ስድብ + ስድብ = ስድብ በሆነ ማቲማቲካል ሎጂክ የምትኖሩ ግዑዛን !!

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ዛህኑ :-

ለተብራራው መልስህ ላመሠግንህ እወዳለሁ :: አየህ 'ውሸት ሲደጋገም ዕውነት ይመሥላል ::' ብለው የተነሡ ቀጣፊዎችን እርቃናቸውን ማስቀረት የሚቻለው እንዲህ አንተ እንደምታደርገው ያለመታከት ዕውነትን ደጋግሞ በመናገርና በመጻፍ ስለ ሃቅ ብሎም በመመሥከር ነው :: ስለዚህም እኔ በግሌ በዚህ ምግባርህ ከሚያደንቁህ እና ከሚያመሠግኑህ ወገኖችህ አንዱ እንደሆንኩ ለማመላከትም ያህል ነው :: ከወራት በፊት አንተ ያንን ዓይነት የሠላ ትንታኔ ስታቀርብ 'ይሆን ይሆን ?' ብለው የተጠራጠሩ አይጠፉም :: ማረጋገጫው አሁን በተግባር የምናየው ሃቅ ነው ::

ለወደፊቱም እንዲህ ዓይነት የውይይት መጫሪያ ሃሣቦች ሣገኝ ጎራ እያልኩ መጎትጎቴ አይቀርም ::

መልካሙን ሁሉ የምመኝልህ ወንድምህ ::

ተድላ

_________________
Rights go hand in hand with responsibility, with dignity, with respect for oneself and for the other.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
6 ኪሎ

ኮትኳች

Joined: 06 Jan 2004
Posts: 233

PostPosted: Sun May 27, 2012 4:38 am    Post subject: Reply with quote

ሬሳው ገማ እግሩ (ዳግማዊ ግብስብሱ ) ቂቂቂቂቂቂ

ባይሳ አጋድሞህ አልነበረም እንዴ ለካ እስካሁን እየተፈራገጥክ ነው
ነፍስ ካለ መፍራገጥ አይቀርም ይሉ ንበር ጋሼ ጉደታ መሬት ይቅለላቸውና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጎማ እግሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Jun 2007
Posts: 716

PostPosted: Sun May 27, 2012 7:18 am    Post subject: Reply with quote

ነገር አለሙ የተዛነፈባችሁ መላቅጡ የጠፋችሁ መሆኑን የምናውቀው እኮ እንዲህ ስትዘላብዱ ነው :: እከሌ ነህ አንተ እከሌ ነህ ብላችሁ የመላ ምት ንግግራችሁ የሚያሳብቅባችሁ እኮ በተለያየ ስም የምትገቡ ደነዞች መሆናችሁን ነው :: እናንተን ፈርቶ ስም ይቀያይራል ??? እስኪ አስበው ታንክና መትረየስ ታጥቃችሁ እንኳን የፈራችሁ የለም እንኳንስ እዚህ ከድኅረ ገፅ በስተጀርባ ሽንታም የበሬ ፈስ ሁሉ ::

6 ኪሎ እንደጻፈ(ች)ው:
ሬሳው ገማ እግሩ (ዳግማዊ ግብስብሱ ) ቂቂቂቂቂቂ

ባይሳ አጋድሞህ አልነበረም እንዴ ለካ እስካሁን እየተፈራገጥክ ነው
ነፍስ ካለ መፍራገጥ አይቀርም ይሉ ንበር ጋሼ ጉደታ መሬት ይቅለላቸውና

_________________
Rights go hand in hand with responsibility, with dignity, with respect for oneself and for the other.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun May 27, 2012 9:18 am    Post subject: Reply with quote

ጎማ እግሩ እንደጻፈ(ች)ው:
ነገር አለሙ የተዛነፈባችሁ መላቅጡ የጠፋችሁ መሆኑን የምናውቀው እኮ እንዲህ ስትዘላብዱ ነው :: እከሌ ነህ አንተ እከሌ ነህ ብላችሁ የመላ ምት ንግግራችሁ የሚያሳብቅባችሁ እኮ በተለያየ ስም የምትገቡ ደነዞች መሆናችሁን ነው :: እናንተን ፈርቶ ስም ይቀያይራል ??? እስኪ አስበው ታንክና መትረየስ ታጥቃችሁ እንኳን የፈራችሁ የለም እንኳንስ እዚህ ከድኅረ ገፅ በስተጀርባ ሽንታም የበሬ ፈስ ሁሉ ::

6 ኪሎ እንደጻፈ(ች)ው:
ሬሳው ገማ እግሩ (ዳግማዊ ግብስብሱ ) ቂቂቂቂቂቂ

ባይሳ አጋድሞህ አልነበረም እንዴ ለካ እስካሁን እየተፈራገጥክ ነው
ነፍስ ካለ መፍራገጥ አይቀርም ይሉ ንበር ጋሼ ጉደታ መሬት ይቅለላቸውና

ታንኩንም : መድፉንም : ወዘተርፈ ... ለእነ ስልኪ አስረክበህ (ምናልባትም ያልተሠለበ የሽንት መሽኛ ካለህ እሱንም ጨምረህ አስረክበህ ) የእነ ስልኪ የጋማ ከብት (ጎማ እግር ) ሆነህ አዲስ አበባ የገባህ አንተው ኃፍረተ -ቢሱ የወያኔ ሎሌ ነህ Razz Razz Razz Razz Razz Razz Razz

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jun 13, 2012 1:25 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖቼ :-

ወንድማችን ዛህኑ እንደገና ብቅ ብሎ ተጨማሪ አስተያዬቶቹን እስኪያካፍለን ድረስ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የሆነው 'ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ ' "ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የዋጋ ግሽበት መንስዔዋች " ባቀረበው ትንታኔ እናዝግም :: ኃይለመስቀል የለገሠን (መለስን ) የኢኮኖሚ አመራር "መለኖሚክስ " በሚል ቃል ገልፆታል :: ምክንያቱን እና የቃሉን ምንጭ ከጽሑፉ ውስጥ ታገኙታላችሁ ::

ምንጭ :- ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ : ፍትህ ጋዜጣ : አርብ ሰኔ 1 ቀን 2004 ..:: የዋጋ ግሽበቱ እና የ‹‹መለኖሚክስ›› ክስረት ::

Quote:
በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ለምግብ ፍጆታ በሚል የሚያወጡት ወጪ ረሀብን ከማስታገስ የዘለለ ጠቀሜታ እንደማይኖረው በተለይ በከተማ ላይ የተሰሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በቀን አንድ ሰው ያስፈልገዋል የሚባለው የካሎሪ መጠን ለማሟላት መወሰድ ይኖርባቸዋል የሚባሉት የተለያዩ አይነት ምግቦች በድህነት ውስጥ ለሚኖሩት ዜጎች የማይቻሉ ሆነዋል፡፡

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ዋጋ ከሌሎቹ አገራት ጋር ሊነፃፀር በማይችል መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ያለ የዋጋ ግሽበት እያሳየ መጥቷል። ለዚህ የዋጋ መናር ከሌሎቹ አገራት ጋር በንፅፅር ለማቅረብ አዳጋች እንደሆነ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ የተለየ ለመሆኑ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ያወሳሉ።

የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ የአብዛኛው ድሃ የአገሪቷ ነዋሪን ኑሮ እያቃወሰ ነው፡፡ በተለይ የዚህ ችግር ቀጥተኛ ሰለባ የሆኑት በገጠርና በከተማ የሚገኙ በፍጥነት የማይቀያየር ቋሚ ገቢ ላይ የተመሰረቱ ቤተሰቦች ናቸው። በንፅፅር ሲታይ ደግሞ በከተማ የሚገኘው ደሃው ማህበረሰብ ለችግሩ እጅግ ተጋላጭ መሆኑን ጥናቶቹ ይጠቁማሉ።

/ ያሬድ አማረ ‹‹ Urban food Insecurity and coping mechanisms›› በሚል ርዕስ በሰሩት ጥናት በምግብ ዋጋ ግሽበት የተነሳ ስለሚሰቃዩ አዲስ አበቤዎች ይተርካሉ፡፡ አጥኚው እንደሚሉት ለቁርስ ተሳክቶላቸው ከሚበሉ ደሃ ቤተሰቦች መካከል ለልጆቻቸውና ለራሳቸው አንድ አንባሻ ከተገኘ ከሻይ ጋር ካልተገኘም በውሃ አጣጥመው መመገብ ከቻሉ በኑሯቸው ትልቅ ስኬት እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ያልሆነላቸው፡ - ከተገኘ አንድን ዳቦ ወይም አንባሻ ለሁለት ተቋድሰው ከሌለም ፆም መዋል የየዕለት ተግባራቸው መሆኑን ፀሐፊው ይገልፃሉ።

በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱት ቤተሰቦች መካከል ከግማሽ የሚበልጡት ቤተሰቦች ቁርስ የሚባል እንደማያውቁ ተጠቁሟል። ህፃናት በአፋቸው ምንም ሳይቀምሱ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይሄዳሉ። በጥናቱ ከተጠቀሱት መካከል አንዲት እናት፡ -

‹‹በየሶስት አልያም አራት ቀናት ውስጥ አንዱን ቀን ምንም ምግብ እቤት ውስጥ የማይኖርበት ጊዜ የተለመደ ነው። እንዲህ አይነት ችግር ሲገጥመኝ ለልጆቼ ምንም የሚበላ ነገር እንደሌለ እነግራቸዋለሁ። አጋጣሚ ሆኖ የተገኘ ጊዜ ደግሞ አንዷን እንጀራ አራት ቦታ ቆርሼ፣ ትንሽ ሽሮ ፈሰስ አደርግና እንዲቃመሱ አደርጋቸዋለሁ። አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ህፃናቱ ያለውን ችግር እየተረዱ መጥተዋል። እንደከዚህ ቀደሙ ምግብ አምጪ እያሉ አያስቸግሩኝም›› ስትል ስለቤተሰቧ ያሰፈረችው ቃል የድህነቱ አስከፊ ገፅታ ምን ያህል ደረጃ እንደደረሰ የሚያመለክት ይመስላል።

ተጠያቂው ማን ነው ?
እስከዚህ ወቅት ድረስ የወጡትን መንግስታዊ መረጃዎች ስንመለከት የዋጋ ንረቱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚስተዋልባቸው በሀገር ውስጥ ተመርተው ለፍጆታ የሚውሉ ምርቶች ላይ ነው። የእነዚህ ምርቶች የግሽበት መጠን እንደ ንዑስ የፍጆታ ምርት ስብስብ /Commodity/ እስከ 50% ሲደርስ፤ ጤፍ፣ ስንዴና ሌሎች ጥራጥሬ እህሎች እጅግ እያሻቀበ ያለ የዋጋ መጠን ይታይባቸዋል። ለብዙ ኢኮኖሚስቶች እነዚህ ምርቶች ላይ የሚስተዋሉት ቁጥራዊ መገለጫዎች የሚያስረዱት ከአጠቃላይ ሀገራዊ የዋጋ ግሽበቱ አንፃር ግፊታቸው ጠንካራ መሆኑ የዋጋ ንረቱን መነሾ ውጪያዊ ከማድረግ ይልቅ በአቅርቦትና ፍላጐት ጥምረት ላይ የሚንተራሱ ከውስጣዊ ኢኮኖሚያዊ ጉድለቶች እንዲነሱ ያደርጋቸዋል። ይህንን መከራከሪያ ለማለዘብ መንግስት የሚጠቅሳቸው ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ቢሆንም ክርክሩ ብዙ የሚያስኬድ አይመስልም። ምክንያቱም ቡና እና ሌሎች የፍራፍሬና አትክልት ምርቶች ከአጠቃላዩ የፍጆታ ዋጋ ጥምር አመልካች /Consumer price index/ ውስጥ ያላቸው ድርሻ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፣ ምንም እንኳን ምርቶቹ በአለም አቀፍ የዋጋ አለመረጋጋት የሚነኩ ቢሆንም፤ በዋጋቸው ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ለማሻገር የሚኖራቸው እድል እጅግ አነስተኛ ነው። አክሰስ ካፒታል Ethiopia: macroeconomic Handbook 2011/12 በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ በተነፃፃሪ ዝግ ሊባል የሚችለውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ስርዓት ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር በማወዳደር የዋጋ ንረቱ ምንጭ ውጫዊ ነው የሚለውን መከራከሪያ ‹‹ስሁት አረዳድ›› ይለዋል። ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባው የምርት መጠን ከአጠቃላዩ ሀገራዊ ምርቷ /GDP/ እስከ 26% ብቻ ከመሆኑ አንፃር፣ ከሀገሪቱ ጋር ተቀራራቢ ሊባል የሚችል ኢኮኖሚያዊ ክፍተት የሚያሳዩ ሌሎች ሀገራት ከተመዘገበው የዋጋ ንረት የኢትዮጵያ እስከ አራት እጥፍ መሄዱ፣ የዋጋ ንረቱ ‹‹ከውጪ የገባ ነው›› የሚለውን ሙግት ጎደሎ ያደርገዋል።

የኢትዮጵያን ማክሮ -ኢኮኖሚ ያጠኑ ምሁራንም ሆኑ ተቋማት የዋጋ ንረቱን አስመልክቶ አንድ ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ። እስከ 1995 .. አጋማሽ ድረስ የዋጋ ንረቱ የኢኮኖሚው መሰረታዊ መለያ የመሆን አቅም አልነበረውም። 1995 .. ወዲህ ፀሐፊዎቹ ‹‹እንግዳ›› ብለው እስከመጥራት ባደረሳቸው መልኩ ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። / አለማየሁ ገዳ ለዚህ ሁኔታ የስርዓቱን የማክሮ -ኢኮኖሚ አስተዳደር ዘዬ ተጠያቂ ያደርጋሉ። / ‹‹ Readings on the Ethiopian Economy›› ብለው በሰየሙት መድብል ውስጥ ባካተቱት Inflation, Development finance and monetary policy Issues በሚለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው እስከ 1990ዎቹ መጀመሪያ ድረስ ኢህአዴግ ተቋማዊ በሆነ መንገድ ከደርግ የወረሳቸውን ጥብቅ የፊስካልና ሞኒተሪ ፖሊሲዎች መጠቀሙ ለታየው ዝቅተኛ የዋጋ ንረት አነስተኝነት አስተዋፅኦ ሲኖረው፤ ከዚህ በግልባጩ ከተጠቀሰው ጊዜ ወዲህ ስርዓቱ የእኒህን ሁለት ፖሊሲዎች የአፈፃፀም ጥብቀት በማላላቱ የዋጋ ንረቱ መናር እንደጀመረ ያወሳሉ። እንደ ኢኮኖሚክስ መምህሩ ሙግት ለዚህ የፖሊሲ ልልነትም ልማታዊ መንግስት ነኝ የሚለው የገዢው ፓርቲ እምነት ገበያ ውስጥ የሚኖረውን ጣልቃ ገብነት እንዲያስፋፉ ማስቻሉ የዋጋ ግሽበቱን አባብሶታል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተለምዷዊ ባህርይ ከእርሻ ምርቶች ከፍና ዝቅ ማለት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ መሆኑ ነው። የአየር ሁኔታውን መዛባት ተከትሎ ዝቅ እያለ የሚሄደው የእርሻው ክፍለ - ኢኮኖሚ የምርት ውጤት፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱንም በዛው ልክ ይጫነዋል። የዚህ ግፊት ሀገራዊ የምርቶች ዋጋን በማወክ የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል። እስከ 1990ዎቹ መጀመሪያ ድረስ የዋጋ ግሽበቱ እና የእርሻ ምርት ውጤቶች ቀጥተኛ ተዛምዶ እንደነበራቸው ብዙዎቹ ኢኮኖሚስቶች ይስማማሉ። በኢኮኖሚው ታሪክ እስከወቅቱ ድረስ ከፍተኛ ሊባሉ የሚችሉ የዋጋ ግሽበቶች የተከሰቱት ድርቅና ጦርነት በነበረባቸው ሶስት ወቅቶች እንደነበረ ዲክ ዱሪቫል፣ ጆሴፍ ሎኒንግ እና ዮሐንስ አያሌው የተባሉ አጥኚዎች ይናገራሉ። 1977. ከባድ ድርቅ ሲከሰት፣ በኢትዮ - ኤርትራ ጦርነት ወቅት እና እንደገና 1995 .. የተስተዋለው ድርቅ፤ ከፍተኛ የተባሉትን 16%- 21% የዋጋ ግሽበት ተመዝግቦባቸዋል። ሶስቱ ኢኮኖሚስቶች Inflation dynamics, food prices in Ethiopia በሚል ርዕስ በሰሩት ጥናት ለድህረ 95 የዋጋ ግሽበት እየናረ መምጣት ኢህአዴግ በምክንያትነት የሚያስቀምጠውን በግብርናው ሴክተር ላይ የሚካሄድ የመዋቅራዊ ለውጥ ጉዳይ በማንሳት፣ ‹‹መዋቅራዊ ለውጡ ለምግብ ዋጋ መናር አስተዋፅኦ እንዳለው የሚያሳይ መረጃ ማግኘት አልቻልንም›› ሲሉ ተከራክረዋል። ከተጠቀሰው ዓመት ወደዚህ ያለው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጠኑ እንደሚጠቅሱት በተለያዩ ክፍለ ኢኮኖሚዎች ላይ በተለይም የግብርናው ምርቶች ከፍተኛ እድገት እያሳዩ ቢመጡም፣ ተፃራሪ በሆነ መንገድ የምርቶች ዋጋ ሽቅብ መናሩን ቀጥሏል። ‹‹በዋጋ መናር እና በምርቶቹ እድገት መሀከል የተፈጠረው ተጣሮሻዊ ዝምድና ብዙዎችን በፍጥነት እያደገ ነው የሚባለውን የኢኮኖሚ እድገት እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል›› ይላሉ / አለማየሁ ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፋቸው። እርሳቸው የሚሉት ዓይነት ጥርጣሬ በሌሎች ተቋማትም በኩል ይሰማል።

ጄሮ ሆንዳ፣ ዛያጀን ዛህናንድ እና አሏን ቶማስ .. 2008 .. ለአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት /IMF/ በሰሩት ጥናት የቅርብ ጊዜው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሶስት የተለያዩ መልኮች እንዳሉት ተንትነዋል። የመጀመሪያው በዕድገቱ መጠን ላይ ስምምነት ባይኖርም ግሽበቱ አለ ከሚባለው የኢኮኖሚ እድገት ጋር አብሮ ማሻቀቡ ነው። በተለይም የጥራጥሬ ምርቶች አቅርቦት ከፍላጎት ጋር አለመጣጣሙ እርዳታ ሰጪ ሀገራት ከምግብ እርዳታ ወደ ገንዘብ -ነክ ድጎማ ማዘንበላቸውን በምክንያትነት የሚያነሱት እነ ጄሮ ሆንዳ፤ መንግስታዊው የኢትዮጵያ የልማት ምርምር ተቋምም /..አር .አይ / ‹‹ይህን የዋጋ ግሽበት እንቆቅልሽ የሚያደርገው ባለፉት አራት ተከታታይ አመታት የተሻለ የምርት ስብሰባ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡ ነው›› ማለቱን በፅሁፋቸው ህዳግ ላይ ያስነብባሉ። በአጥኚዎቹ የተነሳው ሁለተኛው ነጥብ የዋጋ ግሽበቱ ከጎረቤት ሀገራት አንፃር እጅግ ከፍተኛ ሊባል በሚችል መልኩ የሚያሳየው ዓመታዊ እድገት ሲሆን ይህንን ያባባሰው ሶስተኛው እንግዳ ጉዳይ ከተመለደው ውጪ ምግብ ነክ ያልሆኑት ምርቶች ዋጋ ከፍ እያለ መምጣት ነው።

የግሽበቱ ከየት መጤነት
የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እያንገዳገደው ባለው የዋጋ ግሽበት ጉዳይ የተሰሩ ጥናቶች በቁጥር አነስተኛ ሊባሉ የሚችሉ ሆነውም አጥኚዎቹ የሚነሱባቸው የዲስፕሊኑ አስተምህሮቶች መለያየት፣ የመረጃ አጠነቃቀር ጉድለት እና የመተንተኛ ሞዴሎቹ የፖለቲካል -ኢኮኖሚ ተለዋጮችን በምልዕት አለማካተታቸው ጥናቶቹን አልፎ አልፎ ለሚስተዋለው ተጣራሽ ድምዳሜዎች ዳርጓቸዋል። አንዳንዶቹ አጥኚዎች አጠቃላይ ሀገራዊ ፍላጐቱ መገራት እንዳለበት ሲከራከሩ፣ ሌሎቹ በዋናነት በግብርና ምርቶች ላይ ለሚስተዋለው የአቅርቦት መቀዛቀዝ ቅድሚያ ይሰጣሉ። ከዚህ ውጪም ከገንዘብ አቅርቦት እስከ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የነዳጅ ዋጋ መናርንም በምክንያትነት ያስቀምጣሉ።

ባለፉት አስርት አመታት ያለው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መለያ ባህርይ ሆኖ የወጣው ከፍተኛ የመንግስት የባጀት ጉድለት ነው። ከሀገሪቱ ጠቅላላ ምርት ድርሻ እስከ 10% የሚደርሰው የባጀት ጉድለት ማዕከላዊ መንግስቱን ብድር ፍለጋ እንዲንከራተት አድርጎታል። ጉድለቱንም ለመሙላት የወሰዳቸው አማራጮች ከሀገር ውስጥና ውጪ መበደርን እንዲሁም ህዝባዊ ተቋማትን ወደ ግል ማዛወር ነው። ክብሮም ተፈራ የተባሉ ኢኮኖሚስት እንደሚጠቅሱት እስከ 1990ዎቹ አጋማሽ ስርዓቱ ከተከተለው ጥብቅ ሞኒተሪ ፖሊሲ የተነሳ በባጀት ጉድለቱ እና የዋጋ ግሽበት መካከል ይሄ ነው የሚባል ተዛምዶ አልተከሰተም። ‹‹ከዚህ ወቅት በኋላ›› ይላሉ አጥኚው The sources of the recent inflationary experience in Ethiopia በሚለው ጥናታዊ ስራቸው ‹‹የባጀት ጉድለቱ እያደገ ለመጣው የዋጋ ግሽበት አስተዋፅኦ አድርጓል።›› ይህን መሰሉ የአጥኚዎቹ ድምዳሜ መንግስት የባጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ሲል በዋናነት ከሀገር ውስጥ መበደሩ፣ ኢኮኖሚስ ‹‹ሞኒታይዜሽን›› የሚሉትን መፍጠሩ፣ ይህም አጠቃላይ የገንዘብ አቅርቦቱን ስለሚጨምረው የዋጋ ግሽበቱን እያናረው ይመጣል። መንግስት ከሀገር ውስጥ የሚወስደው የብድር መጠን ከሀገር ውጪ ከሚቀበለው ያለው ልዩነት እጅግ አነስተኛ የነበረ ቢሆንም 1995 .. ወዲህ ከሀገር ውስጥ የሚበደረው የብድር መጠን በአማካይ 50% እየጨመረ መጥቷል። እንደ ብዙዎቹ አጥኚዎች መከራከሪያ መንግስት በዚህ መልኩ ከሀገር ውስጥ በብዛት በመበደር የባጀት ጉድለቱን ለመሙላት እየተሞከረ ያለበት ምክንያት ለመበደር በሚከፈለው የወለድ መጠን እና በዋጋ ግሽበቱ መካከል በሁለት ዲጂት የሚለካ ልዩነት መኖሩ የሀገር ውስጥ ብድሩን የቀለለ ያደረግልታል። ገዢው ፓርቲ በስፋት እየሰራባቸው ያሉት የተቋማት ማስፋፋትና የመሰረተ ልማት ግንባታ መንግስታዊ ወጪውን መጨመራቸው ለባጀት ጉድለቱ መባባስ ቀዳሚው ምክንያት ነው። ኢህአዴግ በነዚህ መንግስታዊ ወጪዎች የተነሳ የሚከሰተውን የባጀት ጉድለት ለመሙላት የሀገር ውስጥ ብድር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መንተራሱ በተራዛሚው በገበያ ውስጥ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ከፍ ያደርገዋል።

የነገሩ አጥኚዎች እንደሚሉት ለሀገራዊ የኢኮኖሚ መረጋጋት በጠቅላላው የኢኮኖሚ እድገት እና በገንዘብ አቅርቦት መጠን መሀከል ተቀራራቢ ዕድገት መኖር እንዳለበት ይመክራሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት የወጡት የብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚያሳዩት በኢኮኖሚው ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን ዓመታዊ እድገት ከአጠቃላዩ ኢኮኖሚያዊ እድገት አንፃር በአማካይ እጥፍ በሆነ መልኩ መጨመሩን ነው። እንደ ጉዳዩ ተከታታዮች ከዚህ በተፃራሪ ለመንግስታዊ ወጪዎቹ ሲል ፌዴራል መንግስቱ ገንዘብ እስከማተም ድረስ መሄዱ ከሀገር ውስጥ ብድር መብዛቱ ጋር ሲተሳሰር የምርቶቹን ዋጋ እየገፋቸው ይሄዳል።

/ አለማየሁ ገዳና ክብሮም ታፈረ ጥብቀት ያላቸውን የኢኮኖሚ ሞዴሎችን በመጠቀም እንደሚደመድሙት የገንዘብ አቅርቦት በአንድ በመቶ ቢያድግ የምግብ ዋጋ 1.49 በመቶ ሲጨምር፣ ምግብ ነክ ያልሆነው የዋጋ ንረት ደግሞ 0.94 በመቶ ያድጋል። ሀገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱን እስከ 40% ከፍ እንዲል ያደረገው በዋናነት የምግብ ዋጋ መናር ከመሆኑ አንፃር ከገንዘብ አቅርቦት ጋር ያለው ዝምድና በዚህ ደረጃ መሆኑ ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል። በላይ ጌታቸው የተባሉ አጥኚ ይህን አውድ በመንተራስ Economic Analysis of inflation from the short-run and longrun perspectives በሚል ርዕስ በፃፉት ጥናት ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት መንግስት የገንዘብ አቅርቦቱን መግራት እንዳለበት አሳስበዋል። የምግብ ዋጋን እያናሩ ከሚገኙ ተለዋጮች መሀከል ሌላኛው በገበያ ውስጥ ያለው የምግብ አቅርቦት ማነስ ነው። እነ አለማየሁ ገዳ The galloping inflation in Ethiopia: A Cautionary tale for aspiring Developmental state in Africa በሚለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ዋስትና አልባ የመሬት ስሪት እና የአየር ፀባይ ለውጥ የሀገሪቱን የምግብ አቅርቦት የሚፈታተኑ ጉዳዮች ናቸው። በነዚህ ተዛማጅ ምክንያቶች የምግብ አቅርቦቱ የገበያውን ፍላጐት ያህል ማደግ ያለመቻሉ የዋጋ ንረቱን እንዲባባስ እንዳደረገው ፅፈዋል።

በሌላ ጫፍ የዋጋ ግሽበት ከፍ እያለ መምጣት ሲጀምር ዜጐች ገንዘባቸውን በባንኮች ለማስቀመጥ የሚኖራቸውን ፍላጐት እየቀነሰ ይመጣል። በጊዜ ርዝመት ያከማቹት ገንዘብ የመግዛት አቅሙ እያሽቆለቆለ መምጣቱ የመቆጠብ ፍላጎታቸውን መቀዝቀዙን ተከትሎ በባንኮች ከማከማቸት ይልቅ ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን መሰብሰብ ላይ ስለሚያውሉት በገበያ ውስጥ የሚኖረው የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ ይመጣል። እንደእነ / አለማየሁ ሙግት ይህ ተሳሳሪ ጉዞ የምግብ ዋጋን ለማናር በቂ ምክንያት ይሆናል።

አክሰስ ካፒታል የስታስቲክስ ባለስልጣንን ይፋዊ የዋጋ ግሽበት መረጃን ተንተርሶ በስራው ጥናታዊ ዘገባ የዋጋ ግሽበቱ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ ሲያደርጋት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ከቤላሩስ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ተቋሙ ከላይ በተጠቀሰው እትሙ እንደሚለው ወደ 40% እየተጠጋ ያለው የዋጋ ግሽበት ከገዢው ፓርቲ የትራንስፎርሜሽን እና የእድገት እቅድ ጋር ይላተማል። 2003 .. እስከ 2007 .. ድረስ በሚዘልቀው የትራንስፎርሜሽኑ የጊዜ ገደብ ኢህአዴግ የግሽበት መጠኑን ወደ ነጠላ ዲጂት ለማድረግ ያለመ ቢሆንም የቀደመው ዓመት የፍጆታ ዋጋ ጥምር አመልካች /CPI/ 38% መሆኑ እና በተቋሙ መደምደሚያ የዚህ ዓመቱም ወደ 48% መጠጋቱ፤ ስርዓቱ እጅግ መልካም ሊባሉ የሚችሉ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ቢተገበር እንኳን የትራንስፎርሜሽኑ ዓመታት አማካይ የዋጋ ንረት 15% ያነሰ አይሆንም።

‹መለኖሚክስ› ከስሯል ?
በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆሚያ የሚገኝለት የማይመስለውን የዋጋ ግሽበት መንስኤዎች በተመለከተ አቶ መለስ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚያነሱት በዋናነት ፈጣን ያሉትን የኢኮኖሚ እድገት፣ የአርሶ አደሮችን የገቢ መሻሻል እና ‹‹ስግብግብ›› ያሏቸውን ነጋዴዎችን ቢሆንም ክርክራቸው ብዙም የሚያስኬድ አይመስልም። ብዙ ኢኮኖሚስቶች እንደሚስማሙት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ሁልጊዜና በግድ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አይታጀብም። ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ነው የሚባሉት ሀገራት አማካይ የዋጋ ግሽበት መጠን የኢትዮጵያን አንድ አራተኛ (8%) ከመሆኑ በዘለለ ከዚህ መሰል ሀገራት መሀል ከፍተኛ የሚባለውን የግሽበት መጠን ያስተናገደችው ምንጎሊያ ስትሆን፣ የሞንጎሊያ የዋጋ ግሽበት መጠን ከኢትዮጵያ በግማሽ ያነሰ መሆኑ ክርክራቸውን የሚያጎድልባቸው ይመስላል።

ሌላው የአቶ መለስ መከራከሪያ አርሶ አደሩ ገቢው በማደጉ ከዚህ ቀደም በነበረበት ከ‹‹አጣብቂኝ የሽያጭ አማራጭ›› /distress sales/ በመላቀቁ ተደራድሮ የመሸጥ አቅሙ ጎልብቷል የሚል ነው። በጉዳዩ ላይ የፃፉት / ሰይድ ሃሰን መከራከሪያውን ‹‹ጎደሎ›› ሲሉ ያጣጥሉታል። The causes of the current Ethiopian soaring inflation rate በሚለው ፅሁፋቸው / ሰይድ እንደሚጠቅሱት በትክክልም አርሶ አደሩ ለምርቶቹ የተሻለ ዋጋ ከጠየቀ እና በፈለገው ዋጋ መሸጥ ከቻለ፣ አርሶ አደሩ በዚህ የገበያ ባህርይ የተሻለ በመነቃቃት አመራረቱን በማሳለጥ ምርቶቹን ስለሚጨምር፤ አሁን የሚታየው የግብርና አቅርቦት እጥረት አይከሰትም። በውጤቱም የምግብ ዋጋ ግሽበት እየቀነሰ ይመጣል።

የጅምላ እና የችርቻሮ ገበያው የማይገባውን ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ምርቶችን በመደበቅ ገበያውን መረበሹ ለግሽበቱ ምክንያት ሆኗል የሚለው የስርዓቱ ልሂቃን ሌላኛው ነጥብ ነው። እንደ አንዳንድ ተንታኞች ሙግት ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት እነዚህ የገበያ ክፍሎች ለዋጋ ንረቱ አሉታዊ ድርሻ ሳይኖራቸው፤ ኢህአዴግ በልማታዊ መንግስት ኀልዮት ሽፋን መንግስታዊ ጫናውን በገበያው ላይ ማጠናከር በጀመረበት ወቅት (1995. ወዲህ ) ለተከሰተው ከፍተኛ ግሽበት እነርሱን ተጠያቂ ማድረግ የፖሊሲ ስህተት መሸፈኛ ከመሆን አይዘልም። አቶ መለስ በፓርላማ ቆይታዎቻቸው የስርዓታቸውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ክሽፈት ለመሻገር የሚያቀርቡአቸው ደብዛዛ መከራከሪያዎች ‹‹መለኖሚክስ›› /የመለስ ኢኮኖሚክስ / ብለው የሚጠሯቸው የነገሩ ተከታታዮች፤ የቀደመውን ዓመት ጨምሮ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ ወደነጠላ ዲጂት /10% ያነሰ / ማውረድ ግባቸው እንደሆነ አቶ መለስ በተደጋጋሚ ቢናገሩም፣ የተከሰቱት ሁነቶች ግን የሰውየውን የፖሊሲ ክስረት ጮኸው ይናገራሉ፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
baysa

ኮትኳች

Joined: 31 Mar 2006
Posts: 178

PostPosted: Wed Jun 13, 2012 3:37 am    Post subject: Reply with quote

እንደ እንደ አንተ ካህያ ተወልደህ አባትህን የማታውቅ የሸሌው ልጅ ገማ እግሩ ኦነግ ነኝ ቢለህ ስታጭበረብር ወያነነትሽ ሲነቃ ማስክሽን አውልቀሽ ከች አልሽ እንዸ ያቺ ከየትኛው አህያ አርግዛ እንዳራችህ የማታውቅ ሽሌው እናትህስ ደህና ነች ቂቂቂቂቂ ያንሻፈፈቺህን የሙጃሌህንስ ነገር ከምን አደረስክ ? ጥንብ ወያኔ

ጎማ እግሩ እንደጻፈ(ች)ው:
ነገር አለሙ የተዛነፈባችሁ መላቅጡ የጠፋችሁ መሆኑን የምናውቀው እኮ እንዲህ ስትዘላብዱ ነው :: እከሌ ነህ አንተ እከሌ ነህ ብላችሁ የመላ ምት ንግግራችሁ የሚያሳብቅባችሁ እኮ በተለያየ ስም የምትገቡ ደነዞች መሆናችሁን ነው :: እናንተን ፈርቶ ስም ይቀያይራል ??? እስኪ አስበው ታንክና መትረየስ ታጥቃችሁ እንኳን የፈራችሁ የለም እንኳንስ እዚህ ከድኅረ ገፅ በስተጀርባ ሽንታም የበሬ ፈስ ሁሉ ::

6 ኪሎ እንደጻፈ(ች)ው:
ሬሳው ገማ እግሩ (ዳግማዊ ግብስብሱ ) ቂቂቂቂቂቂ

ባይሳ አጋድሞህ አልነበረም እንዴ ለካ እስካሁን እየተፈራገጥክ ነው
ነፍስ ካለ መፍራገጥ አይቀርም ይሉ ንበር ጋሼ ጉደታ መሬት ይቅለላቸውና

_________________
proud to be Ethiopian
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 07, 2012 5:40 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዛህኑ :-

ሁለት ተደጋጋፊ የሆኑ ዜናዎች አንበብኩና እስኪ ለሁላችንም ላካፍል ብዬ አሠብኩ :: ሠሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ይበልጥ እያሻቀበ እንደሄደ እንዲሁም የአገሪቱ ባንኮች የውጪ ምንዛሪ ዕጥረት እያጋጠማቸውና በዚህም ምክንያት የአስመጭና ላኪ ነጋዴዎች የቅድሚያ ክፍያ መጠየቂያ (Letter of Credit) ለመክፈት ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ 'ካፒታል ' የሚባለው ጋዜጣ ዘግቧል ::

ምንጮች :-
1 ..... Solomon Bekele, Capital, Monday, 06 August 2012 11:59. Despite contrary data food prices continue climb.

2 ..... Pawlos Belete, Capital, Monday, 06 August 2012 12:11. Hard currency shortage resurfaces.

ለገሠ [መለስ ] ዜናዊ ከሞተ ወር እንኳን ሣይደፍን ይህን ያህል የኢኮኖሚ ቀውሡ ከተባባሠ በመንፈቁ ምን ሊከሠት ይሆን ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Tue Aug 07, 2012 7:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ :-

የአሁኗ ኢትዮጵያ እኮ አንድ እግር በቆሎ እሸት 4.00 ብር የሚሸጥባት ሃገር ናት Exclamation
አንድ ኩንታል ጠፍ 1850 ብር አንድ ኪሎ ሽንኩርት 13 ብር አንድ ሊትሮ ዘይት 40 ብር ምኑ ቅጡ ; ነገሩ ሁሉ የተደበላለቀበት ሆኗል እኮ !
የወያኔው "ልማታዊ አስተዳደር " የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው እኮ ለዚህ ሁሉ "ድል Shocked' ያበቃን ::
የብላኔ ኢኮኖሚ እደገት ወሬና ፉከራ ለሕዝቡ ምግብ አይሆነው !
አሁን CSA አንደ ተፈለገውን ቁጥሮች የሚያገላብጥለት የኢትዮጵያ ብቸኛኛው ቺፍ ኢኮሚስት AWOL ስለሆነ ምናልባት ትክክለኛውን የሕዝቡን ሰቆቃ reflect የሚያደርገውን statistical data ያለፍርሃት ሊያቀርቡ ይችሉ ይሆናል እንጂ የዋጋው ግሽበት እያደገ የገንዘባችንም መደከም እየቀጠለ የሚሄድ ነው ::
በዚህ የበከተ የነለገሠ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ የሚቀጠል ከሆነ ያለው ችግር እየተባባሰ እንጂ ምንም የሚቀርፍበት መንገድ የለውም ............ከሃገራዊ መጎሳቆልና ከውርደት በስተቀር ሌላ ምንም አይነት የሚጓዝበት አቅጣጫ የለውም !
የወያኔን ባሕሪ ታውቀዋለህና መሻሻል ትምሕርት መውሰድና መታረምን ምን ያህል የሚጸየፉ የወገንተኛ ግትር ፋሺስቶች ስብስብ ስለሆነ ጣዖታቸውም እንዲህ ጉድ አድርጓቸው ቢጠፋም በቅርቡ የሚታረሙ አይመስለኝም ከነአካቴው የሕዝቡ የስቃይ ጽዋ ሞልቶ ፈሰሶ ይበቃል እምቢ ብሎ ካላቸው ይዞታ አስካላስወገዳቸው ድርስ !
የውጭ ምንዛሪ reserve በተመለከተ የአሜሪካ መንግሥት IMF በኩል ለአንድ ሁለት ወራት የሚሆን ዶላር ይሰጣቸው ይሆናል ......provided that .....አዲስ ከመለስ በኋላ የሚመጣውን አስተዳደር በተመለከተ ዩናትድ ስቴትስ መንግስት የሚያስቀምጥላቸውን precondition እስከ ተቀበሉ ደርስ ......very interesting times indeed.............በሃገራችን ያለው ::
በኔአስተያየት ግን ከሁን በህዋላ ያለውን የኢትዮጵያ አስተዳደርና ሁኔታ የሚወስነው ወያኔ ሆነ ዩኤስ አይመስለኝም ::
የሚወስነው ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የሚሆነው ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ሁኔታ እየጠራ እየመጣ እንደሆነ የሚሰማኝ ::
የደፈረሰው እስኪጠራ ግን ጥቂት ዓመታት የሚፈልግ ይመስለኛል ::
ለማንኛውም እግዚአብሔር ሃገራችንን ከክፉ ይጠብቅለን የሚያለቅሱትን እናቶች አባቶቻችን በስደት የሚሰቃዩ እህትና ወንድሞቻችንን እንደ ራሄል እምባ ይመከትልንና ፍርዱን ይስጥ !
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 07, 2012 8:24 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዛህኑ :-

እግዚአብሔር የኢትዮጵያን እናቶች ዋይታ የአባቶችን ለቅሶ : ወደፈጣሪው የተመለሠውን ወጣት ልመና ሠምቷል :: አልሠማ ያለው ከፈጣሪው ጋር እንደተጣላ ዕለተ -ሞቱን የሚጠብቀው የአብዮታዊው ትውልድ ብቻ ነው :: እነርሱም ቀኑ እየጨለመባቸው መጥቷል :: ስለዚህ ምሥጋና ለፈጣሪያችን አሁን ትንሽ የብርሃን ፍንጣቂ እያየን ነው : እየቆየ ጊዜው ይበልጥ ብሩኅ ይሆንልናል ::

****************

ስለ ውጭ ምንዛሪ ዕጥረት የበለጠ ታብራራልናለህ ብዬ ጠብቄ ነበር :: አሁን ባለው የተተረማመሠ የወያኔ የውስጥ ሁኔታ ትልልቆቹ ማፊያዎች ብቻ ሣይሆኑ ተራው የወያኔ አባል ሣይቀር በአገሪቱ ባንኮችና በግለሠቦችም ካዝና የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በተገኘው የሥርቆት መንገድ ወደውጪ ለማሸሽ ከበቂ በላይ ምክንያት አላቸው :: ስለዚህ ከስድስት ሣምንት ባልበለጠ ጊዜ ነዳጅ መግዢያ ዶላር ሊያጡና ትርምሱ ሊባባስ ይችላል የሚል ግምት አለኝ :: አንተስ እንዴት ታየዋለህ ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Wed Aug 08, 2012 3:09 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

****************

ስለ ውጭ ምንዛሪ ዕጥረት የበለጠ ታብራራልናለህ ብዬ ጠብቄ ነበር :: አሁን ባለው የተተረማመሠ የወያኔ የውስጥ ሁኔታ ትልልቆቹ ማፊያዎች ብቻ ሣይሆኑ ተራው የወያኔ አባል ሣይቀር በአገሪቱ ባንኮችና በግለሠቦችም ካዝና የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በተገኘው የሥርቆት መንገድ ወደውጪ ለማሸሽ ከበቂ በላይ ምክንያት አላቸው :: ስለዚህ ከስድስት ሣምንት ባልበለጠ ጊዜ ነዳጅ መግዢያ ዶላር ሊያጡና ትርምሱ ሊባባስ ይችላል የሚል ግምት አለኝ :: አንተስ እንዴት ታየዋለህ ?
ተድላ

ወንድሜ ተድላ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ እኮ አነሰም በዛም ሁሌ ያለ ነው ምክንያቱም ሃገራችን demand and supply imbalance የቆየብን ስለሆነ ነው ::
በዛም ላይ ላለፉት ሃያ ስላሳ ዓመታት budget deficit የወጣንበት ግዜ የለም በተለያ ባለፉት አስር ዓመታት የበጀቱ አለመብቃቃት ከልክ በላይ እየተባባሰ መጥቶ negative balance መንቀሳቀስ እንደ ፋሽን ሆኗል ::
የዚህም ወጤት የብር መንግዛት አቅም መድከም የዋጋ ግሽበትን እንዳስከተለ በዚህ ዓመድ ስለዚህ በሰፊው ስለተወያየንበት ተመልሶ ወደዛ መግባቱ አስፈላጊነቱ አልታየኝም ::
በብሔራዊ ባንክ የተያዘ /የተቀመጠ የውጭ ምንዛሪ (የዶላር የዩሮም ሊሆን ይችላል ) የኢትዮጵያ ብርን ይዞታውን (ወደላይ ወደታች ሳይል ) ጠብቆ እንዲቀመጥ የሚረዳው safe guard ነው :: እንዲሁም እንዳሁኑ ሰዓት የአስተዳደር uncertainity በሃገራችን ሲታይ ሊከሰት የሚችለውን economic shocks መከላከያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ::
አንግዲህ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ያለውን የብር /ዶላር መመንዘርያ (exchange rate) እንዳለ ጠብቆ እንዲሄድ ከተፈለገ ብሄራዊ ባንኩ ተጨማሪ ብር ማተም አትሞ የውጭ ምንዛሪ (Forex market) መግዛት አለበት ማለት ነው Exclamation
ይህ እንግዲህ እንደምናውቀው ብር ሲታተምና ሲሰራጭ (money supply increase) የማይቀረውን የዋጋ ግሽበት ይዞ ይመጣል ማለት ነው ማለትም ከላው inflation ተጨማሪ ድርብ inflation ጎትቶ ይመጣል ማለት ነው ::
ከላይ እንዳልኩት እንግዲህ IMF ከጸደቀባቸው ለዚህ የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ሟሟያ የተወሰኑ ሚሊዮን ዶላሮች (external remedy) ያበድራቸው ይሆናል (ግምት ነው ) ::
ይሄን እንግዲህ በሂደት የምናየው ይሆናል በስድስት ሳምንት ውስጥ የሚሆነውን ለመተንበይ በቂ መረጃ የለኝምና እጥረቱም ምን ያህል እንደሆነም ግልጽ አይደለምና አሁን ያለው ...wait and see approach.......ነው በኔ በኩል ::
አስታውሳለሁ በደርግ ግዜ እንዲሁ የምንዛሪ አጥረት ተከስቶ ነዳጅ ለተወሰነ ግዜ በዱቤ ከሶቪየት ሕብረት ይገባ እንደነበረ ::
ያሁኑኑም ህኔታ ለመመዘን ሂደት ያስፈለገዋል ነው የምል ::

ሰላም
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2739
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Thu Aug 09, 2012 10:24 pm    Post subject: Reply with quote

ዛህኑ እንደጻፈ(ች)ው:

አንግዲህ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ያለውን የብር /ዶላር መመንዘርያ (exchange rate) እንዳለ ጠብቆ እንዲሄድ ከተፈለገ ብሄራዊ ባንኩ ተጨማሪ ብር ማተም አትሞ የውጭ ምንዛሪ (Forex market) መግዛት አለበት ማለት ነው Exclamation

Question Question Question
እጥረት አጋጠመ እየተባለ ያለው የዶላር እንጂ የብር አይደለም : ... ታድያ ዶላር ሲያጥር ... ብር ማተም መፍትሄ ሊሆን ይችላል እንዴ ዛህኑ ? ...
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Sat Aug 11, 2012 2:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሓየት 11 እንደጻፈ(ች)ው:

Question Question Question
እጥረት አጋጠመ እየተባለ ያለው የዶላር እንጂ የብር አይደለም : ... ታድያ ዶላር ሲያጥር ... ብር ማተም መፍትሄ ሊሆን ይችላል እንዴ ዛህኑ ? ...

አዎ (ጤናማ ) ባይሆንም አንዱ መፍትሄ ነው ::
ምናልባት ይህንን ዓመድ ከዚህ ቀደም ተከታተልህው ከሆነ ያነሳህውን ጥያቄ የሚዳስስ ውይይት አድርገን ነበር ::
ዋናው ነጥብ ይሄ ነበር :-
በዓለም በለንደን ከተማ የሚከናወን በየቀኑ ሦስት ትሪሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚሸጥ የሚለውጥ
Forex/FX market ተብሎ የሚጠራ ማዕከል አለ ::
በዚህ ማዕከል ውስጥ ኢትዮጵያም እንደ ሌሎች ዓለም ሃገሮች ትሳተፋለች ::
ይሄ ገበያ የያንዳዱን ዓለም የሚጠቀማበቸውን ከረንሲዎች ዋጋ (relative value) የሚተምን ነው ተብሎ ዓለም ይሰራበታል ::
በዚህ ገበያ ውስጥ ደካማ (weak) እና ጠንካራ የሚባሉትም ከረንሲዎች በዶላር አሻሻጭነት ይሳተፋሉ ::
እንደ ኢትዮጵያ ያለች Fixed exchange rate መዋቅር የምትጠቀም ሃገር in order to maintain the local exchange rate ብሔራዊ ባንኩ buys and sells its own currency on the foreign exchange market in return for the currency to which it is pegged.
ለምሳሌ if, it is determined a single unit of a local currency is equal to US $1.00 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ will have to ensure that it can supply the market with those dollars.
ይህንን exhange rate ይዞ ለመቀጠል ብሄራዊ ባንኩ በቂ ነው ተብሎ የሚገመት foreign reserves ያስቀምጣል ማለት ነው ::
When foreign exchange gets too depleted ለምሳሌ 2005 ጀምሮ በኢትዮጵያ እንደሆነው ሃገሪቷ ገንዘቧን devalue እንድታደርግ ትገደዳለች በተለይ IMF እዚህ ላይ ከፍ ያለ ጫና ያደርጋል ::
በሃገር ቤት ለነጋዴው የሚፈቀደው የዶላር አቅርቦት ከገበያው ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ከሆነ (increased demand) ካለ (አሁን ነጋዴዎች LC ማግኘት አልቻሉም እንደተባለው ) ጥያቄያቸውን ለሟሟላት ያለውንም (exchange rate) ይዞ ለመቀጠል ብሔራዊ ባንኩ will have to issue more of the domestic currency and purchase the foreign currency, which will increase the amount foreign reserves.
ይሄ ማለት ደግሞ money is being 'printed' ማለት ነው ::
ይሄ የሃገር ውስጥ ዋጋ ግሽበትን ያመጣል በተጓዳኝም የብር ዋጋ እንደገና እንዲከስር (devalue) እንዲያደርግ ያስገድደዋል ማለት ነው ::

ሌላው አማራጭ ሃገሪቷ ያካበተችው የወርቅ ክምችት ካለ ይህንን ወርቅ በረሰርቭ ከርስንሲው ለውጠው ችግሩን ለግዜው ለማስታመም ይቻል ይሆናል ::
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2739
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Sat Aug 11, 2012 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዛህኑ

አሁንም ያልገባኝ ነጥብ አለ :: ... ይሄ ነገር ሁሌም እንደተምታታብኝ ነውና ... በትዕግስት እንደምታስተናግደኝ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ሎንዶን ከሚገኘው የፎሬክስ ማርኬት ... ብር ፕሪንት አድርጎ ዶላር መግዛት የሚቻል ከሆነ ... የዶላር እጥረት ከመነሻው እንዴት ሊያጋጥም ይችላል :: ... ለንደኖችን አዳዲስ የታተሙ ብሮችን እያስታቀፉ ... ዶላር በዶላር መሆን ይቻላል ... ማለት እኮ ነው :: ... ይህ ማለት ደግሞ የሚከስሩት ... ዶላርን በብር የሚሸጡት ... የለንደን ፎሬክስ ገበያተኞች እንጂ ... ብር ያተመው መንግስትም ይሁን አገሪቱ አይደሉም ማለት ነው :: ...

እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ... በለንደን ፎሬክስ ማርኬት ... ሲጀመር ዶላርን በብር ለመሸጥ ፈቃደኛ የሚሆን ነጋዴ አይኖርም ::... ሲምፕሊ ... የኢትዮጵያን ብር የሚፈልግ ነጋዴ ... በጣም ውስን በመሆኑ ::

... ምናልባት የራሳቸውን ሎካል ከረንሲ አትመው ... በፎሬክስ ማርኬት ዶላር የመግዛት ፖሲቢሊቲ ያላቸው አገሮች ... ሎካል ከረንሲያቸው ጠንካራና ... ከአገራቸው ውጪ ሌላ ቦታ ላይም ተፈላጊነት ሲኖረው ይመስለኛል :: ... ለምሳሌ የቻይና , የዩሮ , የጃፓን ወዘተ :: ... የእነዚህ ገንዘብ በእርግጥም ሌላም አገር ላይ ገንዘቡ ተፈላጊ ስለሚሆንና የአገራቱ ኢኮኖሚም አስተማማኝ ስለሚሆን ... ነጋዴው ዶላርን ለመሸጥ ፈቃደኛ ይሆናል :: ... ዶላር ለመግዛት ፕሪንት የሚደረግ ገንዘብ ካለም ... በአለም አቀፍ ገበያ በኩል ሰርኩሌት ሲያደርግ ጀምሮ ... እስከ አገርቤት ድረስ ... የሚታይ ግሽበት ይኖራልና ... አታሚዎቹ መንግስታት ይህንን አማራጭ አይፈልጉትም :: ...

የኢትዮጵያን ከወሰድን ግን ... መንግስት ገንዘብ አትሞ ዶላር ቢገዛ ... ኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ካላቸው ነጋዴዎች ውጪ ... ሻጩ ብሩን የሚገዛለት ብዙም አይኖርምና ...... ከስሮ ሲሸጠው ብቻ ነው ... አገሪቱ ግሽበት ሊያጋጥማት የሚችለው :: ... ኪሳራውን የሚፈልግ ነጋዴ ደግሞ አይኖርምና ... ሲጀርም ዶላሩን ለብር ደፍሮ አይሸጥም :: ... ለዚህም መሰለኝ መንግስት ከዶላር ውጪ ... ሌሎች ሀርድ ከረንሲስ በጣም የሚፈልጋቸው ... ጀስት ባይ ዶላር ::

አንተ ያነሳኸው ሀሳብ ... መንግስት ብር አትሞ ዶላር የመግዛት ፖሲቢሊቲው ያለው ... አገር ቤት ዶላር የሚያቀርብ ሰው ሲኖርና መንግስት በቂ ብር ሳይኖረው ሲቀር ይመስለኛል :: ... አሁን እየተባለ ያለው ግን ... ሪሰርቩ ብቻ ሳይሆን ... ዶላር በአገሪቱ እጥረት አጋጥሟል ነው :: ... የብር ችግር አይደለም :: ... ይህ ደግሞ አሁን ባለንበት ሁኔታ የሚጠበቅ ነው :: ... ሁሉም ባላሀብት (ዘራፊ ባለስልጣንም ጭምር ) ... ሀብቱን ማሸሽ ጀምሯል ... ማለት ነው :: ... ለዚህ አንድ አማራጭ ሊሆን የሚችለው ,,, መጨረሻ ላይ ያቀረብከው ,,, የወርቅ ወይም የመሳሰሉት ሪሰርቭ ማቅረብ ከተቻለ ... ወይም ብድር /ችሮታ /ረሚታንስ ከተገኘ ይሆናል ማለት ነው ::

የምትለውን ልስማ ::

ዛህኑ እንደጻፈ(ች)ው:
ሓየት 11 እንደጻፈ(ች)ው:

Question Question Question
እጥረት አጋጠመ እየተባለ ያለው የዶላር እንጂ የብር አይደለም : ... ታድያ ዶላር ሲያጥር ... ብር ማተም መፍትሄ ሊሆን ይችላል እንዴ ዛህኑ ? ...

አዎ (ጤናማ ) ባይሆንም አንዱ መፍትሄ ነው ::
ምናልባት ይህንን ዓመድ ከዚህ ቀደም ተከታተልህው ከሆነ ያነሳህውን ጥያቄ የሚዳስስ ውይይት አድርገን ነበር ::
ዋናው ነጥብ ይሄ ነበር :-
በዓለም በለንደን ከተማ የሚከናወን በየቀኑ ሦስት ትሪሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚሸጥ የሚለውጥ
Forex/FX market ተብሎ የሚጠራ ማዕከል አለ ::
በዚህ ማዕከል ውስጥ ኢትዮጵያም እንደ ሌሎች ዓለም ሃገሮች ትሳተፋለች ::
ይሄ ገበያ የያንዳዱን ዓለም የሚጠቀማበቸውን ከረንሲዎች ዋጋ (relative value) የሚተምን ነው ተብሎ ዓለም ይሰራበታል ::
በዚህ ገበያ ውስጥ ደካማ (weak) እና ጠንካራ የሚባሉትም ከረንሲዎች በዶላር አሻሻጭነት ይሳተፋሉ ::
እንደ ኢትዮጵያ ያለች Fixed exchange rate መዋቅር የምትጠቀም ሃገር in order to maintain the local exchange rate ብሔራዊ ባንኩ buys and sells its own currency on the foreign exchange market in return for the currency to which it is pegged.
ለምሳሌ if, it is determined a single unit of a local currency is equal to US $1.00 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ will have to ensure that it can supply the market with those dollars.
ይህንን exhange rate ይዞ ለመቀጠል ብሄራዊ ባንኩ በቂ ነው ተብሎ የሚገመት foreign reserves ያስቀምጣል ማለት ነው ::
When foreign exchange gets too depleted ለምሳሌ 2005 ጀምሮ በኢትዮጵያ እንደሆነው ሃገሪቷ ገንዘቧን devalue እንድታደርግ ትገደዳለች በተለይ IMF እዚህ ላይ ከፍ ያለ ጫና ያደርጋል ::
በሃገር ቤት ለነጋዴው የሚፈቀደው የዶላር አቅርቦት ከገበያው ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ከሆነ (increased demand) ካለ (አሁን ነጋዴዎች LC ማግኘት አልቻሉም እንደተባለው ) ጥያቄያቸውን ለሟሟላት ያለውንም (exchange rate) ይዞ ለመቀጠል ብሔራዊ ባንኩ will have to issue more of the domestic currency and purchase the foreign currency, which will increase the amount foreign reserves.
ይሄ ማለት ደግሞ money is being 'printed' ማለት ነው ::
ይሄ የሃገር ውስጥ ዋጋ ግሽበትን ያመጣል በተጓዳኝም የብር ዋጋ እንደገና እንዲከስር (devalue) እንዲያደርግ ያስገድደዋል ማለት ነው ::

ሌላው አማራጭ ሃገሪቷ ያካበተችው የወርቅ ክምችት ካለ ይህንን ወርቅ በረሰርቭ ከርስንሲው ለውጠው ችግሩን ለግዜው ለማስታመም ይቻል ይሆናል ::

_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 14, 2012 5:28 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

ሰላም ዛህኑ :-

ላለፉት 21 ዓመታት የወያኔ የወጪና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ ባልተመጣጠነና እጅግ በተዛባ ያጋደለ ሚዛን ሲመራ ኖረ :: እስካለፉት 2 ወራት ድረስ ወያኔዎች በልመናም : በብድርም ይህንን የወጪና ገቢ የንግድ ሚዛን ልዩነት ለማጥበብ ቢሞክሩም ካሠፈኑት የተዛባ የንግድ ሥርዓትና በሙሥና በተዘፈቁት ሹሞቻቸው በሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ዝርፊያ ምክንያት አልተሣካም :: ይባስ ብሎ የአገዛዝ ሥርዓቱ ዋናው አምበል የዛሬ ወር አካባቢ ለዘለዓለም በማሸለቡ የልመና ቋቱን ቋጥሮ የሚለምንላቸው ሁነኛ ለማኛቸውን አጥተዋል :: እንግዲህ እኒህ ችግሮች ጥርሥ አውጥተው አደባባይ ላይ ወጥተዋል :: ያለፈው ሣምንት በባንክ አዲስ የቅድሚያ ክፍያ መተማመኛ ቅፅ (Letter of Credit) መክፈትን ከለከሉ :: ከዚያ ተከትሎ በጥቁር ገበያ የዶላርና ሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች የምንዛሪ ዋጋ በባንክ ከሚለወጠው ዋጋ ልዩነቱ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ ይበልጥ እንዳሻቀበ እዚያው አገር ቤት የሚታተመው ካፒታል ጋዜጣ ትላንት ሰኞ ዘግቧል :: ይህ አዝማሚያ ወዴት ያመራል ?

ምንጭ :- Pawlos Belete, Monday, 13 August 2012 11:01. Black market re-flourishes.

Quote:
The gap between official exchange rate and that of black market is widening. Banks are buying one USD for 17.85 birr while selling it for 18.21 birr as of the official rate published by the National Bank of Ethiopia on Friday August 10. The parallel market is buying one dollar for 18.5 birr surpassing Fridays official selling rate. Such a trend is observed for the first time since the country depreciated the birr against major foreign currencies two years ago.The observed difference in the value of exchange rate is diverting hard currency bearers from using formal exchange channels to the informal one creating room for the underground business to re-flourish.

The gap between official exchange rate and that of black market remained close to one percent for almost two years after the government depreciated the exchange rate of the birr against major foreign currencies on average by 20 percent. However, this gap widening in the past two weeks has reached close to five percent as of last Friday.

The expanding difference shows the imbalance between demand and supply of foreign currency according to experts.

The observed difference in exchange rate has already triggered speculation about possible price hikes in the near future, at least, for imported goods in the business circle of the country. If this speculation materializes, the situation will accelerate inflation which was rather decelerating during the past few months.

We are processing letters of credit for selected sectors of the economy on a priority basis since there is a foreign currency shortage. There is not as such directive that bans processing it, said an executive in the banking sector on condition of anonymity a week ago.

Though the inflow of hard currency to the country from remittances, tourism and other sources has not been made public so far, it is reported that the country earned USD 3.1 billion from exports last fiscal year.

The government of Ethiopia envisions single digit inflation and five percent depreciation of the birr against major foreign currencies in this Ethiopian fiscal year.

In what was termed as massive government crackdown, the government confiscated close to USD 6 million from black market dealers in Addis Ababa in March 2008. Since then, the city has not observed such a major move despite fragmented efforts to discourage it. At that time the nation was facing a critical shortage of foreign currency.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Oct 02, 2012 4:59 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዛህኑ :-

ሁላችንም እንደምናውቀው በዓለም የገንዘብ ድርጅት (International Monetary Fund - IMF) እና በዓለም ባንክ ጉሉኮስ ተውተርትሮ የቆመው የትግሬ -ወያኔዎች አገዛዝ ከእኒህ የኅልውናው መሠረት ከሆኑት ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር ዘወትር 'በቅጥፈት የኢኮኖሚ ዕድገት ስታትስቲክስ ' እንደተወዛገቡ ይገኛሉ :: ከሁለቱ ወገኖች 'ማን ትክክል ነው ?' ከማለት ይልቅ የትኛው 'ወገን ውሸቱን ያሣንሣል ?' ማለቱ ተገቢ ነው :: ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2005 .. የዓለም የገንዘብ ድርጅት ያወጣውን መግለጫ ተመልክተኸው ይሆናል ብዬ አምናለሁ :: እናም እስኪ አንዳንድ ማብራሪያዎችን አካፍለን ::

ምንጭ :- IMF, October 1, 2012. IMF Executive Board Concludes 2012 Article IV Consultation with Ethiopia, Public Information Notice (PIN) No. 12/117.

Quote:
On September 12, 2012, the Executive Board of the International Monetary Fund (IMF) concluded the Article IV consultation with Ethiopia.1

Background

Ethiopias macroeconomic performance in 2011/12 has been mixed. Strong, broad-based growth continues at a pace of about 7 percent and poverty reduction measured by poverty head count declined from 38.7 to 29.6 percent during the six years to 2010/11. However, inflation surged to 40 percent in August 2011, largely reflecting a combination of factors including loose monetary policy, and high global food prices but has eased to about 21 percent in June 2012 supported by a slowdown in global food and fuel price inflation and the implementation of the base money nominal anchor. Despite the continued robust increases in goods exports and remittances, the current account deteriorated in the first half of 2011/12 contrasting the surplus recorded in 2010/11 attributed to a frontloading of import of capital goods the previous year. The developments in 2011/12 largely reflect a recovery of imports of capital goods, an increase in consumer goods imports, and a weakening of the services balance due to a surge in service imports.

The federal government budget execution in 2011/12 has been tight based on a strong tax revenue increase when compared to the previous fiscal year, and a slower-than-budgeted execution of recurrent expenditure. However, the public sector (including state-owned enterprises) as a whole has been providing strong fiscal impulse given the state-owned enterprise substantial capital expenditures financed by borrowing from external sources and the Commercial Bank of Ethiopia (CBE). A rise in regional government deposits at CBE contributed to the funding. The 2012/13 budget focuses on sustaining growth, lowering inflation further, mobilizing revenue, and spending on pro-poor projects. The revenue target is within reach with the continuation of administrative efforts. Total expenditure is projected to grow slower than nominal GDP, but poverty-related spending as a share of GDP will be maintained.

Monetary policy in 2011/12 has largely been geared toward lowering inflation with the implementation of the base money nominal anchor. Base money at end-May 2012 declined by 0.9 percent year-on-year as the central bank has ceased providing new direct credit to the government since July 2011 and has been selling foreign reserves in recent months to achieve a base money contraction target of 4 percent for the fiscal year. However, the lowering of the reserve requirement ratio in early January from 15 percent to 10 percent weakens the tightening effect of the base money contraction. Broad money at end-May 2012 grew by 29 percent year-on-year on account of strong credit growth to public enterprises. Despite the planned National Bank of Ethiopia (NBE) financing of the 2012/13 budget, which could affect inflation expectations, the 2012/13 monetary targets focus on lowering inflation.

The NBE directive that requires commercial banks (excluding CBE) to hold bills issued by NBE is impeding financial intermediation. By creating a significant maturity mismatch in the private banks balance sheets, it has a considerable negative impact on their capacity to play their conventional intermediation role. Financial sector soundness indicators do not point to immediate concerns. However, recent developments such as the increasingly dominant market share of CBE and its growing exposure to large public enterprises, and the adverse impact of NBE directive on private banks suggest a need for a closer scrutiny of the banking system.

Absent increased role of the private sector to leverage the large public infrastructure investment and efforts to improve the doing business conditions, IMF staff project that real GDP growth will slow down to 6.5 percent in 2012/13 and over the medium term. However, the authorities project the economy to grow at double digit rates.

Executive Board Assessment

Executive Directors welcomed Ethiopias strong economic growth and continued progress in poverty reduction. However, Directors noted that the authorities public sector-led development strategy is contributing to macroeconomic imbalances. To sustain robust growth and address the emerging risks, policies for the period ahead should focus on promoting disinflation, achieving an appropriate pace of public investment, reconstituting official reserves, and promoting greater financial sector stability.

Directors welcomed the authorities goal of reducing inflation. In this context, they urged the central bank to pursue a tighter monetary stance and avoid further deficit financing. Directors also underscored the importance of broadening the toolkit of monetary policy instruments, including by revamping the market for government securities, which could foster private saving and investment. Greater exchange rate flexibility would safeguard foreign exchange reserves, strengthen external competitiveness, and mitigate external vulnerabilities.

Directors encouraged the authorities to persevere with their fiscal reforms. In particular, they saw scope for further improvements in tax administration and revenue mobilization. Additional public financial management reforms and development of a medium-term debt management strategy encompassing both domestic and external debt would help achieve the fiscal objectives under the Growth and Transformation Plan and maintain fiscal sustainability. Any non-concessional borrowing should be consistent with maintaining a low risk of debt distress.

Directors stressed that effective financial sector supervision and regulation remain crucial for macroeconomic stability. In this regard they advised the authorities to consider participation in the Financial Sector Assessment Program which would help identify vulnerabilities in the financial system and suggest corrective actions as appropriate. Directors encouraged the authorities to address the remaining deficiencies in Ethiopias AML/CFT regime.

Directors agreed that deeper structural reforms are essential for promoting growth. Accordingly, they underscored the importance of creating a more favorable business environment and enhancing the role of private sector in the economy. Directors also called for further efforts to improve data quality and supported Fund technical assistance in this area.

አክባሪህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
Page 9 of 10

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia