WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እንዴት ነው ነገሩ ? የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Thu May 19, 2011 8:49 pm    Post subject: እንዴት ነው ነገሩ ? የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ Reply with quote

በሃገራችን በየሳምንቱና በየወሩ እንደ ፊኛ እየተለጠጠ የመጣው የዋጋ ግሽበትና የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅሙ በየግዜው እየተዳከመ መምጣት ከተጠናከረ ይኸው አስር ዓመታት በላይ አሳልፎ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ::
በዘመናችን የኢኮኖሚክስ ቲዎሪ አስተምሮ የዋጋ ግሽበት የሚከሰትበት ዋናው ምክንያት የሸቀጥ አቅርቦትና (goods) አገልግሎት (services) እንዳሉ ሆነው የገንዘብ ቁጥር (ስርጭት ) (money supply) በየግዜው እየጨመረ ሲመጣ ነው ::
inflation is a situation where money supply increases without the required increase in the supply of goods and services.
Economists say inflation is a fiscal phenomenon in which a government with a budget deficit can finance itself either by printing money or by issuing public debt.
A highly developed country such as USA can issue public debt(ious) because it has readily available array of buyers such as China.
An underdeveloped/developing country such as Ethiopia can not! for the simple fact it is not trust worthy thus, does not have buyers.

በሃገራች የዋጋ ግሸበት እየተስፋፋ መሄድ ከአስር ዓመታት በላይ ያሳለፈ ሲሆን እንደሚባለው ከዓለም 2008 ዓም ጀምሮ ከተከሰተው የምግብና የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም :: (በርግጥ አባብሶታል )
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ (ዚምባብዌን ከውድድር ካወጣናት ) በዋጋ ግሽበት (41%) ከዓለም አንደኛ ደረጃውን ተረክባ ይዛ ትገኛለች ! እንኳን ደስ ያለን Embarassed
የኢትዮጵያ .....CSA..... እንኳን ቁጥሩን 30% አርጎ ባለፈው አቀርቦታል ::
http://www.aneki.com/inflation.html

ዚምባብዌን ያወጣሁት ቁጥሩ በሂሳብ ለማስቀመጥ እንኳን የማይመች [11,200,000% inflation rate] በማስቆጥር የሙጋቤ የግል መፈንጫ የሆነችው ሃገር ገንዘብ እንደ እንደ ሞኖፖሊ ጨዋታ ወረቀት የአንድ ሚሊዮን የአስር ሚሊዮን የብር ኖት የሚታተምባት በአሁኑ ሰዓት ከዓለም መሰረታዊ የፋይናንስ ግንኙነት ጨዋታ ውጪ የሆነች ሃገር ስለሆነ ነው ::

የሃገራችን ግን አካሄዱ በጣም የሚያሳስብና የሚያስደነግጥ እንደሆነ ነው የምናየው :: ወደ ዚምባብዌ መንገድ እያመራን ይሆን ወገኖቼ ?
ዞሮ ዞሮ የኢንፍሌሽኑ ዋናው ምክንያት ከሚገባው በላይ ገንዘብ እያየተመ እንደሆነ በግልጽ ልናውቀው የሚገባ ነው ::
የወያኔ መንግሥት ዓመታዊ ባጀቱን ለማብቃቃት ተጨማሪ ገንዘብ እያተመ የዋጋ ግሽብቱን ራሱ እያባባሰ ሕዝቡን የስውር (inflation tax) እንዲከፍል እያደረገው ነው ::
የቀድሞው አሜሪካን ፕሬዝደንት ሬገን እንዲህ የሚል ንግግር ተናግረው ነበር :-
  Inflation is as violent as a mugger, as frightening as an armed robber and as deadly as a hit man.

ትክክል ናቸው !
የኢትዮጵያ ሕዝብ .....is getting mugged by a violent and deadly assassin!
ይህ በንዲህ እያለ ግን ወያኔዎች እንደሚሉት በስግብግብ ነጋዴዎችና .......increased demand..... ምክንያት ነው የዋጋ ግሽበቱ የተከሰተው ::
በዚህም ሰበብ በመላ አገሪቱ ድንገተኛ የሸቀጦች ዋጋ ተመን ይፋ ካደረገ በኋላ በተለይ የምግብ ዓይነቶች ከገበያ አንዲጠፉ አሊያም አለቅጥ እንዲወደዱ ምክንያት ሆነዋል ::
በመላ አገሪቱ ስኳር ብርቅ ሸቀጥ ኾኗል ዘይት በጥቂት አስመጭዎች እጅ ላይ በመውደቁ ከተተመነለት ዋጋ በላይ ተሽጧል በስተኋላ ላይም መንግስት ስግብግብ ነጋዴዎች የሚላቸውን ኅብረተሰቡን እንዳይጎዱት ሲል ከማሌዚያ በአንጻራዊ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ (Palm Oil) ዘይትን በየቀበሌው እያሰለፈ በመሸጥ ላይ ይገኝ ነበር ::
NOTE
[አሁን ኢትዮጵያን የምታክል ለእርሻ ሰብልና ለዘይት ምርት የተመቸች ሃገር ሌላው ቢቀር ስኳርና ዘይት አምርታ ለሕዝቦቿ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅርብ ያቅታት ነበር ? shame!
ይታያቹህ ግን ለዓለም በተለይ ለአውሮፓ ምርጥ ምርጡን የዘይት ፍሬዎች (oilseeds and pulses) አሁንም ዋና አቅራቢ ሃገር ኢትዮጵያ !......Enigma of Enigmas.]

የሆኖ ሆኖ በሃገራችን አሁን ያለው በጀት አመዳደብና ባጠቃላይ ...resource allocation.....ከኢኮኖሚያዊ እውነታ ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ባብዛኛው ፖለቲካ እምነት ብቻ በማናለብኝነት የተጸነሱ ....fantasy project......ላይ የሚያተኩሩ ስለሆነ የፖለቲካው አመለካከት እስካለተቀየረ ደርስ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ቀውስ ትዕይንት በዚሁ እየቀጠለ እንደሚሄድ ለመተንበይ አያዳግትም ፊኛምውም ተለጥጦ ተለጥጦ የሚፈንዳበትም ቀን ይደርሳል ::

ቸርነቱ የማያልቅበት አግዚአብሔር አምላክ የኢትዮጵያን ሕዝብ በረድኤቱ እየመገበ ከዚህ ሁሉ ቀውስ እንደሚያወጣው የማይጠራጠረው .......

ዛህኑ ይመኔ
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Thu May 19, 2011 10:32 pm    Post subject: Reply with quote

ካላያችሁት የዚምባብዌ 50,000,000 ብር ኖትና ሌሎችም
እዚህ ታች ወረድ ብላቹህ በከረንሲው ላይ ክሊክ እያደረጋቹህ ተመለከቱ :-
There was also a special 100,000,000,000,000(መቶ ትሪሊዮን ኖት !!!) issued by the bank of Zimbabwe Shocked
http://en.nkfu.com/zimbabwe-currency/

አንድ ቢራ የሚሸጥበት የዚም ዶላር ክምር አያችሁት ? ዚምባብዌ ከረንሲ 5 የሚለውን ታች ያለውን ፎቶ ክሊክ አርጉት ::
አሁን የዚምባብዌን ከረንሲ ማንም የሚቀበለው የለም እነሱም 2009 ጀምሮ ማስገደድ ትተአል ሙጋቤና ክሮኒዎቹ የሚጠቀሙት በሀርድ ከረንሲ ነው ደሃው ህዝቡ አፈር እየላሰ የድንጋይ ዘመን ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ህይወት እየተወዛወዘ ይኖራል ይባላል ::

ያሳዝናል አንድ ሕዝብ በአንድ በአምባገነን መዳፍ ስር እንዲህ ሲወድቅና ስብእናው ሲገፈፍ !
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተውማነው

ኮትኳች

Joined: 16 Apr 2011
Posts: 129
Location: mexico city

PostPosted: Thu May 19, 2011 11:38 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድም ዛህኑ በጣም ጥሩ ትንታኔ ነው !! ፊኛው ከሚገባው በላይ ተለጥጦ ሊፈነዳ እኮ ትንሽ ቀርቶታል !!
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችገር ከቀን ወደቀን እየባሰበት እንጂ ምንም የሚለወጥ ነገር የለም የወያኔው ቡደን ግን ትንሽ ሰው በተሰበሰበበት ቡና ቤት እየገቡ ስለ አባይ ግንባታ ሰዉን እያደናቁሩት ነው ትንንሽ የኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች ንግድ ፈቃዳቸውን እየመለሱ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ ነው ነጋዴዎን ህብረተሰብ ህዝቡ ጋር ለማቃቃር ዘውትእር እየሰሩ ነው አሁን ደግሞ ባለታክሲውን እና ተጠቃሚውን ለማጋጨት የሞከሩት ሳይሳካ ቀርትዋል ይሄ ሁሉ ትብትብ እራሳቸውን አንቆ እንደሚገድላቸው አለማወቃቸው ነው !! እንደው በምን ቀን ብቻ አስደግመው አገራችንን የሙጥኝ እንዳሉ ነው ዘውትር የሚደንቀኝ
ብቻ 2011 አብዮት ዘመን ነውና ወደዱም ጠሉም አብዮቱ መፈንዳቱ የማይቀር ነው !!! ድል ለጭቁን ወገኔ !!!!!
_________________
LONG LIVE TO ETHIOPIA !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Mon May 30, 2011 6:32 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት እንዲሁም ለተውማነው

የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር ወደ አዲስ አበባ ዎክ እያደረጉ የገቡበትን ግምቦት 20 የሚሉትን ቀን ፌሽታቸውን እምበር ተጋዳላይ እየዘለሉ በመስቀል አደባባይ ባከበሩበት ማግስት ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊያን ሽሮ እንኳን አሮባቸው በጠኔ ተይዘው እንሚገኙ አዲስ ፎርቹን የተባለው ጋዜጣ ዋቢ በማድረግ ይህንን ዘግቧል ::

  The retail prices of pulses such as chickpeas, and cereals such as teff are increasing, making shiro wot with injera, the staple food of low-income households, more expensive to the point of becoming unaffordable to some who have begun replacing teff with maize to make injera. They are also skipping meals, writes EDEN SAHLE, FORTUNE STAFF WRITER.
  http://www.addisfortune.com/agenda.htm

አንድ ኪሎ ነጭ ሽሮ 26 ብር
አንድ ኩንታል አተርና ሽምብራ 1850 ብር 2002 ሚያዚያ 1050 ብር 76% የዋጋ ጭማሪ Exclamation
ባቄላ 1450 ብር 2002 ሚያዚያ 950 ብር 53% የዋጋ ጭማሪ !
ምሥር ክክ 2000 ብር
ድፍን ምስር 1850 ብር
በቆሎ 21% የዋጋ ጭማሪ በአንድ ዓመት ወስጥ
ማሽላ 18% >>>>>>
ስንዴ 14% >>>>>>>
ጤፍ 10% >>>>>>>
ባለፈው ሕዝቡ የዓብይ ጾምን ለመፍታት አንዲት ዶሮ ለመግዛት እንኳን አሮበት ነበር ዶር ባማካይ 140 ብር ሲሸጥ አንድ ኪሎ የወጥ ሥጋ 52 እስከ 60 ብር ነበር ::
በነገራችን ላይ ቅቤና ወተት ተረስቷል ዘይትና ስኳር በሌሊት ቀበሌ ካልተሰለፈ የሚያገኘውም የለም ::

እስቲ ተመለከቱት ብቻ በተለይ የምሥርና የአተር የባቄላ ዘር እንደዚህ ከልክ ያለፈ መናሩ የሚያስገርመው ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ለሳውዲ አረቢያ ወዘተ ... ከዋናዎቹ Oil seeds and Pulses exporters አንዷ መሆኗ ነው ::

ሰላም
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Mon May 30, 2011 11:08 pm    Post subject: Reply with quote

Oilseeds and Pulses የሚባሉት ሰብሎች እነማን ናቸው ?
  Sesame seed = ሰሊጥ
  Niger seed = ኑግ
  Sunflower seed = ሱፍ
  Pumpkin seed = የዱባ ፍሬ
  Ground Nuts = ለውዝ
  Linseed = ተልባ
  Horse Beans = ባቄላ
  Peas = አተር
  Chick peas = ሽምብራ
  Lentil = ምሥር

እነዚህ በጣም High protein and very high calorie የሆኑት polyunsaturated fatty acids የታመቁ ሰብሎች ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ (በድህነትም ቢኖር ስጋ እንክዋን መብላት አቅም ባይኖረው ) አስፈላጊውን ተመጣጣኝ Protein caloric intake ለሰውነቱ የሚያቀርቡ የኑሮ መሰረት የነበሩ ስብሎች ነበሩ ::
በቄላ ለምሳሌ በሽሮ ወጥነት የደሃውን ወስፋት እየዘጋ በጾም ግዜም በእልበትነት በስልጆነት በንፍሮነት እንዲሁም በጸሎት ሐሙስም ወቅት በጉልባንነት ባጥቃላይ ከኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ከዋናዎቹ የኢትዮጵያን ምርት እሴቶች አንዱ ነበር ::
አሁንስ ? አሁንማ ሽሮ እንኳን ብርቅ ሆኖ በኪሎ 26 ብር እየተሸጠ ነው ::
ሁሉ የሃገራችን የሁመራው ሰሊጥ የጎንደር የጎጃም የሸዋ የወሎ የወለጋ የሲዳሞ ወዘተ ገበሬዎች ምርቶች ምሥር ባቄላ ሽምብራ ተልባው ኑጉ አተሩ ሁሉ የት ገባ ?
ወደ ሳውድ አረቢያ የገልፍ ኤሚሬትስና ወደ አውሮፓ ኤክስፖርት እየተደረገ ነው !
ይህንን ኤክስፕርት ቢዝነስ በዋናነት እየመራ ዶላር በውጪ ሃገር የባንክ ቤርሙዳዎች አያካባተ የሚገኘው ማነው ብለን ብንጠይቅ የኢትዮጵያ መሪ ነኝ የሚለው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በዘረፈው የኢትዮጵያ ሃብት ካቋቋማቸው 13 "ኤፈርት " ድርጆቶች (10 ተላጣፊዎቻቸው ጋር ) ዋነኛው ጉና ተብሎ የሚታወቀው አዲት የማይነካው ከሕግ በላይ የሆነው ድርጅት ነው ::
http://www.ethiomarket.com/effort/effort_companies.htm

አሁንም በቅርቡ የኢትዮጵያ ብር officially devalue መደረጉ ስለማይቀር ይህንን ዓይን ያወጣ የዘረፋ ኤክስፓርት እነሚያጠናክረው ግልጽ ሰልሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ሽሮና ዘይት አሮበት በጠኔ ሆዱ ሲነፋ ታዳጊ ሕጻናቱ malnutrition ሲረግፉ እነ የጉናና የሌሎቹ 'share holders" በሆንግ ኮንግ በማሌሲያ በካይማን ደሴቶች ያካበቱትን ገንዘብ እጥፍ እጥፍ እየጨመረላቸው ወተቷ የማያልቅባትን ያቺን ኢትዮጵያዊቱን ላም የዳማ ማለባቸውን ይቀጥላሉ ::
ጠቅላይ ሚኒስትራቸውም ....... Birr devaluation is essential to promote our export commodities and earn hard currency......እያለ ሲመጻደቅ ታዩታላቹህ ::

ብቻ ሁላችንም ግልጽ እንሁን (the time demands it) ሁሉንንም እንመርምር መጨረሻውም ማየታችን አይቀር !

ሰላም ለሁሉም
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
AddisMeraf

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 01 Nov 2009
Posts: 1576

PostPosted: Tue May 31, 2011 4:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዛህኑ

ይሄ እየተለጠጠ የሄደውን የኑሮ ውድነት በጭፍን ፍልስፍና የሚመሩት ወያኔዎች እናስቆማለን ብለው በድንባሬ ያወጡት "መፍትሄ " መልሶ ሁኔታውን እያባባሰው ነው :: ሳያደርጉትም ተው ተብለው ነበረ ግን በወትሮ ማን አለብኝነታቸው ተግብረውታል :: ግን ችግሩ ባሰ እንጂ አልተሻሻለም :: ይሄንኑ ተጨማሪ ችግር አስመልክቶ ብሉምበርግ የዘገበውን እዚህ ተጭናችሁ አንብቡ ::
_________________
Remembering Meles Zenawi's Era! >> http://www.youtube.com/watch?v=uK1oi0-8uyQ&feature=youtu.be
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፋኖፋኖ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Nov 2006
Posts: 805

PostPosted: Tue May 31, 2011 5:28 pm    Post subject: Reply with quote

ዛህኑ እንደጻፈ(ች)ው:
በሃገራችን በየሳምንቱና በየወሩ እንደ ፊኛ እየተለጠጠ የመጣው የዋጋ ግሽበትና የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅሙ በየግዜው እየተዳከመ መምጣት ከተጠናከረ ይኸው አስር ዓመታት በላይ አሳልፎ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ::
በዘመናችን የኢኮኖሚክስ ቲዎሪ አስተምሮ የዋጋ ግሽበት የሚከሰትበት ዋናው ምክንያት የሸቀጥ አቅርቦትና (goods) አገልግሎት (services) እንዳሉ ሆነው የገንዘብ ቁጥር (ስርጭት ) (money supply) በየግዜው እየጨመረ ሲመጣ ነው ::
inflation is a situation where money supply increases without the required increase in the supply of goods and services.
Economists say inflation is a fiscal phenomenon in which a government with a budget deficit can finance itself either by printing money or by issuing public debt.
A highly developed country such as USA can issue public debt(ious) because it has readily available array of buyers such as China.
An underdeveloped/developing country such as Ethiopia can not! for the simple fact it is not trust worthy thus, does not have buyers.

በሃገራች የዋጋ ግሸበት እየተስፋፋ መሄድ ከአስር ዓመታት በላይ ያሳለፈ ሲሆን እንደሚባለው ከዓለም 2008 ዓም ጀምሮ ከተከሰተው የምግብና የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም :: (በርግጥ አባብሶታል )
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ (ዚምባብዌን ከውድድር ካወጣናት ) በዋጋ ግሽበት (41%) ከዓለም አንደኛ ደረጃውን ተረክባ ይዛ ትገኛለች ! እንኳን ደስ ያለን Embarassed
የኢትዮጵያ .....CSA..... እንኳን ቁጥሩን 30% አርጎ ባለፈው አቀርቦታል ::

ዛህኑ እነም ጥሩ ትንታኔ ነው እላለሁ ::

ወያኔ ብር እያተመ ይረጭ ይሆናል :: ወይም የወያኔ የጡት አባት ሻቢያ ብር እያተመ እየረጨ ይሆናል :: ምክንያቱም ትላንት ቺስታ የነበሩ የወያኔ ደጋፊ ቀልጣፎች በአመት ሁለት አመት ሚሊየነሮች ሆነው ቁጭ ይላሉ :: ህዝቡ ደሀ ነው : የመግዛት ሀይሉ በጣም ደካማ ነው ግን ሆኖም ነጋዴ ተብዬ ቀልጣፎች ለማን ሽጠው በማን አትረፈው ከመቅጽበት ሚሊየነሮች የሚሆኑበት ሁኔታና መንገድ አልገባኝም ::

ዛህኑ ሰለ instant millionaires እንዴትና ከየት አስረዳኝ እስኪ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በይሉል

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Sep 2004
Posts: 1115
Location: Beylul-60km North of Assab.

PostPosted: Tue May 31, 2011 6:04 pm    Post subject: Reply with quote

የሚገርመኝ :-
የህዝቡ ትእግስት
የገዢወች ትእቢት
የካድሬው ቅብጠት
የአስመሳዩ ብዛት
የመከራው ብዛት
የትእግስቱ ብዛት
የወጣቱ ዳተኝነት ::
_________________
*The hardest thing about any political campain is how to win without proving that you are unworthy of winning!! E.stevenson

*Even if you win the rat race,you are still a rat!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
TOKICHO

ኮትኳች

Joined: 02 Feb 2005
Posts: 143
Location: kenya

PostPosted: Tue May 31, 2011 8:28 pm    Post subject: Reply with quote

በይሉል እንደጻፈ(ች)ው:
የሚገርመኝ :-
የህዝቡ ትእግስት
የገዢወች ትእቢት
የካድሬው ቅብጠት
የአስመሳዩ ብዛት
የመከራው ብዛት
የትእግስቱ ብዛት
የወጣቱ ዳተኝነት ::

በይሉል ዋናውን ነጥብ ዘነጋህው እሳ .......

የሕዝቡ ፈሪ መሆን

ቶኪቾ
ወረ Crying or Very sad Crying or Very sad
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Thu Jun 02, 2011 12:52 am    Post subject: Reply with quote

ፋኖፋኖ እንደጻፈ(ች)ው:

ዛህኑ እነም ጥሩ ትንታኔ ነው እላለሁ ::

ወያኔ ብር እያተመ ይረጭ ይሆናል :: ወይም የወያኔ የጡት አባት ሻቢያ ብር እያተመ እየረጨ ይሆናል :: ምክንያቱም ትላንት ቺስታ የነበሩ የወያኔ ደጋፊ ቀልጣፎች በአመት ሁለት አመት ሚሊየነሮች ሆነው ቁጭ ይላሉ :: ህዝቡ ደሀ ነው : የመግዛት ሀይሉ በጣም ደካማ ነው ግን ሆኖም ነጋዴ ተብዬ ቀልጣፎች ለማን ሽጠው በማን አትረፈው ከመቅጽበት ሚሊየነሮች የሚሆኑበት ሁኔታና መንገድ አልገባኝም ::

ዛህኑ ሰለ instant millionaires እንዴትና ከየት አስረዳኝ እስኪ ::

ሰላም ፋኖፋኖ

ወያኔ ብር የሚያትመው ፈልጎ ሳይሆን ግድ ስለሆነበት ነው ::
አስተዳደሩ በጀት አለመብቃቃት ውስጥ ከገባ ዓመታት አስቆጥሯል ::
The simplest thing to do when you are in a deficit is to print more money .
የሰጎኗን ተረት ታውቀዋለህ አይደል ?
ጠላት ሊበላት ሲመጣ አንገቷን አሸዋ ወስጥ ቀብራ እስካላየችው ደርስ መጥቶ የማይዘነጥላት የሚመስላት አይነት ነው ::
የወያኔ ስትራቴጂስቶች ፓለቲካዊ /ኢኮኖምያዊ መስመሩን ከማስተካከል ይልቅ ለግዜው መድሃኒት ይሆናል ብለው በድንቁርና ገንዘብ ማተሙን መርጠዋል ::
አሁን የዓመታት abuse cumulative effect ነው ወያኔን ቁርጠት ውስጥ የከተተው !
ዛሬ "The chickens come home to roost' እንደሚባለው ነው ::
የሁኔታው መባባስ ያላማራቸው ከባሕር ማዶ የመጡ ከወያኔ አሳዳሪዎች አንዱ የሆነው ድርጅት IMF ኢኮኖሚስቶች ሰሞኑን ተልከው ብሔራዊ ባንክ ድንኳን ሰርተው ከወያኔ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ይገኛሉ ::
IMF worried about broad money growth and budget deficit in Ethiopia
በመሰረቱ የአንድ ሃገር የገንዘብ ክምችት ማለት ለገበያ ልውውጥ በመላው ሃገሪቷ ተሰራጭቶ የሚገኘው የገንዘብ ኖትና በባንኮች ተቀምጦ የሚገኘው ሕዝብና ድርጆቶች እንደልብ የሚያወጡት የሚያስገቡት ሂሳብ ነው ::
Money Supply = Currency in circulation + Demand deposits.
Demand deposit is merely depositors' easily accessed assets that are on the books of financial institutions.
ስለዚህ Wikipedia ላይ ጥሩ አርቲክል አለ Money Supply ብለህ ግባና ተመለከተው ::
ሻቢያ እያተመ ይረጭ ይሆናል ላልከው ምናልባት ሊሆን የሚችል ነገር ነው ::
ነግን ግን ብሩ ያው "counterfeit" ነው የሚሆነው እንደዚህ ያለውን ገንዘብ መለየት ብዙም አስቸጋሪ አይመስለኝም የሆኖ ሆኖ የወያኔና የሻቢያን የቆየ የተቆራኘ unhealthy ግንኙነት የምናውቀው ስለሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የብር ኅትመት ማሺን ናቅፋ ቢገኝ እኔ ብዙም አይደንቀኝም :: Wink
ኤርትራም ቢሆን በአሁኑ ሰዓት ሃይለኛ inflation ላይ ትገኛለች (23 rank).

ስለ ኢትዮጵያ "Instant millionaires" የጠየከው ግለሰቦችን የሚመለከት ቢሆንም በትክክል እንደነዚህ ያሉ ሰዎች በሃገራችን በማያናቅ ቁጥር እንደሚገኙ ሁላችንም የምናውቀው ይመስለኛል ሆኖም ሃብቱ ያካበቱበት ዘዴ ለየቅሉ ይመስለኛል ::
ባብዛኛው ግን ከቁልፍ ወያኔ ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር ለምሳሌ ያለ "collateral" ከባንክ ታላላቅ የገንዘብ ብድር በማግኘት ; ጉምሩክ አካባቢ የሚደረጉ አየር ባየር transactions; አንዳንድ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ለምሳሌ የህንጻ ስራ የመንገድ ወዘተ ለመሳሰሉት በተለይ ማሺነሪዎች (ቡል ዶዘር , ግሬደረ ወዘተ ......) አቅርቦ በከፍተኛ ዋጋ በማከራየት overnignt millionares የሆኑ ሰዎች አውቃለሁ ::
ሌሎችም ብዙ የሌብነት ሃብት ማካበቻ መንገዶች ይኖራሉ ሁሉም ግን አንድ common denominator አቸው ካለው አስተዳደር ባለስልጣኖች ጋር በዘር ወይም በጥቅም መቆራኘታቸው ነው !
ለማንኛውም ጳውሎስ ሚልኪያስ ስለ ኢትዮጵያ ከጻፈው ጽሑፍ ውስጥ ገጽ 204 አንብበው ::
The New Class Post-1991
የሚለው የበለጠ ለጥያቄህ መልስ የሚሰጥ ይመሰለኛል ::

መልካም ምሽት
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዛህኑ

ኮትኳች

Joined: 06 Jun 2009
Posts: 230

PostPosted: Tue Jun 14, 2011 10:43 pm    Post subject: Reply with quote

  "Price increases in Ethiopia result from imported inflation, not domestic driven inflation."

  Hailemariam Desalegn, deputy prime minister and foreign minister, said this about the rising cost of living, as reported by Bloomberg on Thursday, June 9, 2011. Global food and fuel prices, and not domestic fiscal and monetary policies, were the causes of inflation, he said.[Emphasis mine]
  http://www.addisfortune.com/

የወያኔ ውጭ ጉዳይ / አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጠኔ እያማቀቀ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት በተመለከተ የሰጠው አስተያየት ነው ::
አለቃው አቶ መለስ የተናገረውን እንደ በቀቀን ከመድገም በሰተቀር አዲስ ነገር የለም ::
ሰሞኑን የአይ ኤም ኤፍ ኢኮኖሚስቶች ፓሊሲያቸውን እንዲያስተካክሉ ያቀረቡላቸውን ምክር እንኳን አሻፈረኝ እንዳሉ ይገኛሉ ::
የሚቀጥለውን ዓመት በጀት 22 ቢሊዮን ብር እንደሚጨመር ተናግርዋል ::
ብሩ ከየት መጥቶ ?
ይታተማላ ምን ችግር አለው ወረቀት እስካለ ድረስ Smile
Politics Trump Common Sense to Determine Economic Policy
የሰጎኗን ተረት .....in broad day light....እየተመለከትነው ነው ::

ሰላም ለቤቱ
_________________
ዛህኑ ይመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Wed Jun 15, 2011 2:35 am    Post subject: Reply with quote

ተኮቻ በቀጥታም ባይሆ በይሉል ደጋግሞ "የህዝቡ ትእግስት " በማለት ለመግለጽ የሞከረው አንተ ዋናው ነጥብ ያልከው ነው :: እኔስ ምን ያድርግ ህዝብ ባይ ነኝ :: የጠገበ ጅብ አውርዶ የባሰ የተራበ እኔ ልብላ ብቻ የሚል ጅብ ሲመጣበት ምን ያድርግ :: በተቋዋሚዎች መካከል ቅንጅትን ጨምሮ የምናየው የእርስ በእርስ ጦርነት ሲታይ ከወያኔ የተሻሉ ናቸው የሚለው በጣም ያጠራጥራል :: በአሁኑ ወቅት በአቅምም በልምድም በችሎታም in job training ያገኙት ቢሆንም ወያኔ ሀገር ለመምራት በየትኛውም መመዘኛ የተሻለ አቅም ያለው መስሎ ይታያል :: በዚህ አመት ኢትዮጵያ ሄጄ ያየሁት ስራ የሚመርጥ ጉረኛ ካልሆነ በስተቀር ገጠርም ሆነ ከተማ ሄዶ ለመስራት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው የስራ እድል ድሮ ከማቀው የተሻለ እንዳለ ነው ያየሁት :: ምንም ኑሮ ቢወደድም ህዝቡን ወደ አመጽ የማይወስደው ዋናው ምክንያት ሰርቶ መግባት መቻሉ ይመስለኛል :: የወያኔ ከኮሚንዝም የወረሰው ፖሊስዎቹ ሀገሪቷ አሁን ካለው በበለጠ ፍጥነት እንዳታድግ እንቅፋት ቢሆንም የተወሰነ የኢኮኖሚ እድገት እንዳለ ግን የሚገነቡትን ህንጻዎች በመመልከት ሳይሆን በጠቅላላው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በአካል በመመልከት መገመት ይቻላል :: ወያኔ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠርና IT በኩል ብዙ መስራት እንዳለበት ግን ለመገንዘብ በቀላሉ ይቻላል ::

ለወያኔ ከላይ የጻፍኩትን ባልጽፍ ደስ ባለኝ ግን የተሻለ ልምድ ያለው አማራጭ አለ ብዬ ስለማልገምት ወያኔ የሚለውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ እስኪጨርስ እድል ቢሰጠው ከሀገር ጥቅም አንጻር የተሻለ ይመስለኛል ::

TOKICHO እንደጻፈ(ች)ው:
በይሉል እንደጻፈ(ች)ው:
የሚገርመኝ :-
የህዝቡ ትእግስት
የገዢወች ትእቢት
የካድሬው ቅብጠት
የአስመሳዩ ብዛት
የመከራው ብዛት
የትእግስቱ ብዛት
የወጣቱ ዳተኝነት ::

በይሉል ዋናውን ነጥብ ዘነጋህው እሳ .......

የሕዝቡ ፈሪ መሆን

ቶኪቾ
ወረ Crying or Very sad Crying or Very sad
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jun 15, 2011 2:50 am    Post subject: Reply with quote

የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው:
ተኮቻ በቀጥታም ባይሆ በይሉል ደጋግሞ "የህዝቡ ትእግስት " በማለት ለመግለጽ የሞከረው አንተ ዋናው ነጥብ ያልከው ነው :: እኔስ ምን ያድርግ ህዝብ ባይ ነኝ :: የጠገበ ጅብ አውርዶ የባሰ የተራበ እኔ ልብላ ብቻ የሚል ጅብ ሲመጣበት ምን ያድርግ :: በተቋዋሚዎች መካከል ቅንጅትን ጨምሮ የምናየው የእርስ በእርስ ጦርነት ሲታይ ከወያኔ የተሻሉ ናቸው የሚለው በጣም ያጠራጥራል :: በአሁኑ ወቅት በአቅምም በልምድም በችሎታም in job training ያገኙት ቢሆንም ወያኔ ሀገር ለመምራት በየትኛውም መመዘኛ የተሻለ አቅም ያለው መስሎ ይታያል :: በዚህ አመት ኢትዮጵያ ሄጄ ያየሁት ስራ የሚመርጥ ጉረኛ ካልሆነ በስተቀር ገጠርም ሆነ ከተማ ሄዶ ለመስራት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው የስራ እድል ድሮ ከማቀው የተሻለ እንዳለ ነው ያየሁት :: ምንም ኑሮ ቢወደድም ህዝቡን ወደ አመጽ የማይወስደው ዋናው ምክንያት ሰርቶ መግባት መቻሉ ይመስለኛል :: የወያኔ ከኮሚንዝም የወረሰው ፖሊስዎቹ ሀገሪቷ አሁን ካለው በበለጠ ፍጥነት እንዳታድግ እንቅፋት ቢሆንም የተወሰነ የኢኮኖሚ እድገት እንዳለ ግን የሚገነቡትን ህንጻዎች በመመልከት ሳይሆን በጠቅላላው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በአካል በመመልከት መገመት ይቻላል :: ወያኔ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠርና IT በኩል ብዙ መስራት እንዳለበት ግን ለመገንዘብ በቀላሉ ይቻላል ::

ለወያኔ ከላይ የጻፍኩትን ባልጽፍ ደስ ባለኝ ግን የተሻለ ልምድ ያለው አማራጭ አለ ብዬ ስለማልገምት ወያኔ የሚለውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ እስኪጨርስ እድል ቢሰጠው ከሀገር ጥቅም አንጻር የተሻለ ይመስለኛል ::

TOKICHO እንደጻፈ(ች)ው:
በይሉል እንደጻፈ(ች)ው:
የሚገርመኝ :-
የህዝቡ ትእግስት
የገዢወች ትእቢት
የካድሬው ቅብጠት
የአስመሳዩ ብዛት
የመከራው ብዛት
የትእግስቱ ብዛት
የወጣቱ ዳተኝነት ::

በይሉል ዋናውን ነጥብ ዘነጋህው እሳ .......

የሕዝቡ ፈሪ መሆን

ቶኪቾ
ወረ Crying or Very sad Crying or Very sad

የዘመኑ :-

ከወያኔ 20 የአገዛዝ ዓመታት ሠፋ ያለ የግንባታ ሥራ የታየው ባለፉት 5 ዓመታት ነው :: እናም ባለፉት 5 ዓመታት በወያኔ አገዛዝ የተገነቡት ግንባታዎች በአብዛኛው ለወደፊቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት የማያስችሉ (እንዲያውም ዕንቅፋት የሚሆኑ ) ናቸው :: ሩቅ ሣትሄድ በሼሁ የተገነባውን ናኒ ሕንጻ ውሠድ :- ይህ ሕንፃ እስካሁን ሥራ መጀመሩን እጠራጠራለሁ :: እንደዚያም ሆነ ሕንፃው የተገነባበት ሥፍራ ዋና የመሬት ነውጥ የሚያሠጋበት ቦታ ላይ ነው ያለው :: ሌሎቹም ሕንፃዎችና ግንባታዎች ለከተሞች ዕድገት በወጣው ማስተር ፕላን እና በተገቢው የጥንቃቄ መሥፈርት መሠረት ያልተገነቡ በመሆናቸው ዕድሜያቸው አጭር ነው :: አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በአፄ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን የተሠሩት የበድሉ ሕንፃን ዓይነቶች ምንም የረባ ጥገና ሣይደረግላቸው በጥሩ ሁኔታ ሲገኙ ትላንት የተገነቡ ሕንፃዎች ወይ ጣሪያቸው ሲያፈስ : አልፎ ተርፎም ምሦሦዎቻቸው ሲሠነጣጠቁ ይታያል :: መንገዶቹም ቢሆን አሥፋልት ለብሠው ዓመት ሣያገለግሉ ወደ ኮረኮንችነት ይቀየራሉ :: የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት የአገር ሃብት መባከን : በግንባታ ሥራ የሚሠማሩ ኩባንያዎችና አስፈፃሚ ባለሥልጣኖች ያለአግባብ መበልፀግ : በአጠቃላይ አገሪቱ በሙስና የሚያምን ትውልድ መነኻሪያ እንድትሆን የሚያደርግ ነው ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፋኖፋኖ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Nov 2006
Posts: 805

PostPosted: Wed Jun 15, 2011 3:14 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
Nani Building, the tallest high-rise in Addis Ababa, is to become home to what may be the largest supermarket in the country on the first floor with a furniture store and stationery on the second, while the rest is largely to be occupied by MIDROC.

እንዴ ባለ 22 ፎቅ ናኒ ሕንጻ ነው እንዴ THE TALLEST BUILDING in Addis ? አዲሳበባ ሕንጻ በሕንጻ ሆኗል የሚባለው ባለ ስንት ፎቅ ሕንጻ እየሰሩ ነው ? ሲያትል ስልኪ የሚኖርበት አፓርትሜንት 25 ፎቅ ነው :: ድንቄም ሕንጻ በሕንጻ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2955

PostPosted: Wed Jun 15, 2011 4:04 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ለሁሉም

የተድላ ሀይሉና የፋኖፍኖ አስተያየት ለጨለምተኝነት ጥሩ ምሳሌ ይሆናሉ Laughing

የዘመኑ ልሳን ስለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጠቅሶ ሲፅፍ (ለዛውም የሚገነቡትን ህንፃዎች ግምት ውስጥ ሳያስገባ ) ተድላ ሀይሉና ፋኖፋኖ ስለናኒ ህንፃ ያወራሉ Wink Laughing ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ልብ አርጉ ....የህንፃዎች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የሚገነቡት በግለሰቦች ነው

ለተድላ ሀይሉ

Quote:
ሩቅ ሣትሄድ በሼሁ የተገነባውን ናኒ ሕንጻ ውሠድ :- ይህ ሕንፃ እስካሁን ሥራ መጀመሩን እጠራጠራለሁ :: እንደዚያም ሆነ ሕንፃው የተገነባበት ሥፍራ ዋና የመሬት ነውጥ የሚያሠጋበት ቦታ ላይ ነው ያለው ::

1. የምን የመሬት ነውጥ ነው የምታወራው Question

2. ለሼሁ አዝነህ ነው Question Wink Laughing

ለፋኖፋኖ

Quote:
እንዴ ባለ 22 ፎቅ ናኒ ሕንጻ ነው እንዴ THE TALLEST BUILDING in Addis ? አዲሳበባ ሕንጻ በሕንጻ ሆኗል የሚባለው ባለ ስንት ፎቅ ሕንጻ እየሰሩ ነው ? ሲያትል ስልኪ የሚኖርበት አፓርትሜንት 25 ፎቅ ነው :: ድንቄም ሕንጻ በሕንጻ

አባባልህ ትንሽ .....እንትን አያስመስልብህም Wink Laughing

አንድ ከተማ በህንጣ ላይ ህንጣ እንድትሆን ህንፃዎቹ ባለስንት ፎቅ መሆን አለባቸው Question Rolling Eyes

ለዘመኑ ልሳን አስተያየት አድናቆቴን እገልፃለሁ

ሠላም
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
Page 1 of 10

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia