WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እንቁዎቹ አርቲስቶቻችንና እጣ ፈንታቸው ..
Goto page 1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Thu Sep 08, 2011 5:34 pm    Post subject: እንቁዎቹ አርቲስቶቻችንና እጣ ፈንታቸው .. Reply with quote

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን , የስፖርት ሰዎችን ., ደራሲያንና ባጠቃላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ያላቸውን ገጸ -በረከት እነሆ ያሉትንና አሁንም የሚሉትን ውድ ኢትዮጵያንን ከያሉበት እየፈለገና እያፈላለገ የሚያቀርበው እንደው ባጠቃላይ ለተረሱ ድምጾች ድምጽ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ወይንም Ethiopian This week በሚል ስም የሚታወቀው የቅርስ ድህረ ገጽ ( እቺን ይጫኑ ) የተለያዩ የመድረክ ሰዎችን ማቅረቡ ይታወቃል :: ለዚህም ስራው እንደ አርቲስት ዶክሌ እንበልና እዝጋቤር ታመስገን እንላለን :: Very Happy ነገር ግን ደሞ በመረት ላይ ያለውን እውነታ ስንመለከት ትናንት የመድረክ እንቁዎች የነበሩ አርቲስቶቻቸን ትናንት በዜማቸው ሲያሆነሉልልን የነበሩ ኪነ ጥበባውያን እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣ አያዞህ ባይ በማጣት ከመድረክም ከዚች ምድርም ቀስ በወስ እየተገፉ የሄዱበትን ሁኔታ እያስተዋልን ነው :: አድናቂዎቻቸውም ሆኑ የሚመለከተው የመንግስት አካል ( በጡረታ ከተገለሉት ውጭ ) የሚደርግላቸው ምንም ድጋፍ የለም :: የኪነ ጥበብ ሰው ለመሆን ተፈጥሮዊ ስጦታ ግድ ይላል :: ክርሀርቫርድ ወይም የል ወይም ከጆን ሀፕኪኒስ ዩኒቨርስቲ ወይም ከፓትሪስ ሉሙምባ የኪነ ጥበብ /ቤት የታወቀ ድግሪ ብንይዝም ጥበቡ በውስጣችን ከሌለ እንደሚጮህ ጽናጽል ነን :: የጥበብ መንፈስ ቅዱስ ይወርድብን ዘንድ ግድ ይላል :: እነዚህ ኪነ ጥበባውያን ከጊዜ ወደ ግዜ እየተረሱ አንዳንዶችም በሞት እየተለዩ ሌሎችም አስታዋሽ አጥተው ያልጋ ቁራኛ እየሆኑ ነው :: በተለያየ ጊዜ ካርቲስቶች ጋር ያደርገነውን ውይይት ለሰማ አንዳች ፍንጭ ያገኛል ብለን እናምናለን :: እቺን ደግመው ይጫኑ :: ባገር ውስጥ የአርቲስቶች ማህበር ቢኖርም መሳርቾቹና አባላቱም ቡዙ ባለመጠናከራቸው የትናንቶቹ እጹብ አርቲስቶቻችን እጣ ፋንታ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነው :: በዚህ ሳምንት የዝግጅት ክፍላችን ከሶስት ድንቅ ባለሙያዎች ጋር ለሰአታት የቆየ ውይይት አድርጎአል :: በመድረክ ላይ የምንወዳቸውንና የደስታችንን ምንጭ የሆኑትን ያህል የግል ህይወታቸውን ስንሰማና ያሉበትን ኑሮ ከነሱ ስንረዳ ምን ያህል አሳዛኝ ፈተና ላይ እነደሆኑ መረዳት ይቻላል :: አርቲስት ዶክሌን ( የወንድወሰን ብርሀኑን ) እንውሰድ .. ድንቅና ጎበዝ ወጣት ( ጎልማሳ ) አርቲስት ነው :: አርቲስቱ የእለት እንጀራውን ለመብላት መኪና ይቀጠቅጣል :: በሙያዊ አጠራር ባትላሜራ ነው :: በዚህ ስራው በደረሰበት ጉዳት አንድ አይኑ አያይለትም :: እርዳታ ባገር ውስጥ ጠይቆ እስካሁን የረባ ነገር አላገኘም :: ይህ አርቲስት እስካሁን ካቀረባቸው ስራዎች ሌላ ገና ለመድረክ ያልወጡ ያልተሰሩና ሊሰራቸው የሚፈልጋቸው 60 በላይ የሚሆኑ ቀልዶችና ጭውውቶች አሉት :: በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ እንኴን አሁንም ቁጭ አላለም :: ውይይታችን ስናደርግ በቅርብ ቀን በሚወጣ አንድ ፊልም ውስጥ ይሳተፍ ነበር :: የዶክሌ ( ወንድወሰን ) መጻዊ እድል ግን አደገኛ ነው :: አርቲስቱ እርዳታ ካላገኘና ወደ ውጭ ሄዶ መታከም ካልቻለ ሁለተኛውንም አይኑን በመጀመሪያው አይኑ ኢንፌክሽን ምክንያት ሊያጣው እንደሚችል ዶክተሮች ነግረውታል :: ( አርደተውታል ማለት ይሻላል መሰለኝ ) ..ሳይመሽ የምንችለውን ካልረዳናቸው እነዚህን ባለሙያዎች እስከ ወዲያኛው አናያቸውም :: በውይይታችን ላይ እንዴት አርቲስቱን ማግኘት እንደሚቻል ተወያይተናል :: መርዳት የምትፈልጉም ካላችሁ እሱ የሚገኝበትን ቀጥታ የእጁን ቁጥር ልንሰጣችሁ ሙሉ ፍቃደኞች ነን :: ሌላው ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ ነው :: ስለዚህ እውቅ ጋዜጠኛ ሁኔታ ማወቅ የቻልነው ካርቲስት ግርማ ነጋሽ ጋር ባደርግነው ውይይት ላይ ነው :: አርቲስት ግርማ ነጋሽ በነገራችን ላይ ( የኔ ሀሳብ , እንገናኛለን ...አልረሳሽም ...የሸማኔ ፍቅር ..... ዘፋኝና ለተወሰነ ወቅት የስፖርት ጋዜጠኛ የነበረ ነው ) ንጉሴ አክሊሉ ተፈጥሮ የጋዜጠኝነት ዝናብ ያዘነበችለት ድንቅ ሰው ነው :: ግርማ ነጋሽና ጔደኞቹ ንጉሴን ለመርዳት ታች ላይ እያሉ ነው :; ግን ባገር ውስጥም ሆኑ በውጭ ያሉት አድናቂዎቹን ድጋፍና እርዳታ ይፈለጋሉ :: ወገን ለወገን ደራሽ ይሁን :: የእምዬ ኢትዮጵያ ልጅ ወድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ...ኢትዮጵያ እናቴ , እትዮጵያ ኩራቴ ..ኢትዮጵያ አክስቴ . ...እያሉ ከስማችን በታች መደርደር ብቻውን ኢትዮጵያዊነት አይደለም :: ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያውያንን መርዳትና በችግራቸው መድረስ ነው :: በኢትዮጵያ ስም ለለመኑና ለተቸገሩ አንድ ጣሳ ጠላና አንድ ሳህን ንፍሮ ማቀበል ባህላችን እኮ ነው :: ባገር ውጭ ያለን አንድ ብር ሆነ 5 ብር 10 ብርም ሆነ መቶ ብር የምንችለውን እንርዳቸው .. አሉሁልህ አይዞህ ብለን ወገኝተኝነታችን እናሳይ :: ገንዘብ ባይኖረንም እንኴን ደውለን እናጽናናቸው :: በቅርብ ጊዜ ሁሉም ቃለ ምልልሶች ስለሚለቀቁ ከራሳቸው አንደበት ሁሉንም ትሰሙታላችሁ :: ሰላም ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Thu Sep 08, 2011 7:32 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ ከዶክሌ ( የወንድወስን ብርሀኑ ) ከራሱ ስራዎች አንዳንዶቹን ልጋብዛችሁ ::
አይ እድል ... http://www.youtube.com/watch?v=ayi6CN0LJvM&feature=related

ፕሮፊሰር ዶክሌ :- http://www.youtube.com/watch?v=rMWbtN00EvA&feature=related

ዋንጫው :- http://www.youtube.com/watch?v=E117eWv7D6k&feature=related

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1631

PostPosted: Thu Sep 08, 2011 8:57 pm    Post subject: Re: እንቁዎቹ አርቲስቶቻችንና እጣ ፈንታቸው .. Reply with quote

ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ ምን ሆነ ደግሞ ????

እስኪ አብራራልን ::

ሀዲስክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን , የስፖርት ሰዎችን ., ደራሲያንና ባጠቃላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ያላቸውን ገጸ -በረከት እነሆ ያሉትንና አሁንም የሚሉትን ውድ ኢትዮጵያንን ከያሉበት እየፈለገና እያፈላለገ የሚያቀርበው እንደው ባጠቃላይ ለተረሱ ድምጾች ድምጽ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ወይንም Ethiopian This week በሚል ስም የሚታወቀው የቅርስ ድህረ ገጽ ( እቺን ይጫኑ ) የተለያዩ የመድረክ ሰዎችን ማቅረቡ ይታወቃል :: ለዚህም ስራው እንደ አርቲስት ዶክሌ እንበልና እዝጋቤር ታመስገን እንላለን :: Very Happy ነገር ግን ደሞ በመረት ላይ ያለውን እውነታ ስንመለከት ትናንት የመድረክ እንቁዎች የነበሩ አርቲስቶቻቸን ትናንት በዜማቸው ሲያሆነሉልልን የነበሩ ኪነ ጥበባውያን እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣ አያዞህ ባይ በማጣት ከመድረክም ከዚች ምድርም ቀስ በወስ እየተገፉ የሄዱበትን ሁኔታ እያስተዋልን ነው :: አድናቂዎቻቸውም ሆኑ የሚመለከተው የመንግስት አካል ( በጡረታ ከተገለሉት ውጭ ) የሚደርግላቸው ምንም ድጋፍ የለም :: የኪነ ጥበብ ሰው ለመሆን ተፈጥሮዊ ስጦታ ግድ ይላል :: ክርሀርቫርድ ወይም የል ወይም ከጆን ሀፕኪኒስ ዩኒቨርስቲ ወይም ከፓትሪስ ሉሙምባ የኪነ ጥበብ /ቤት የታወቀ ድግሪ ብንይዝም ጥበቡ በውስጣችን ከሌለ እንደሚጮህ ጽናጽል ነን :: የጥበብ መንፈስ ቅዱስ ይወርድብን ዘንድ ግድ ይላል :: እነዚህ ኪነ ጥበባውያን ከጊዜ ወደ ግዜ እየተረሱ አንዳንዶችም በሞት እየተለዩ ሌሎችም አስታዋሽ አጥተው ያልጋ ቁራኛ እየሆኑ ነው :: በተለያየ ጊዜ ካርቲስቶች ጋር ያደርገነውን ውይይት ለሰማ አንዳች ፍንጭ ያገኛል ብለን እናምናለን :: እቺን ደግመው ይጫኑ :: ባገር ውስጥ የአርቲስቶች ማህበር ቢኖርም መሳርቾቹና አባላቱም ቡዙ ባለመጠናከራቸው የትናንቶቹ እጹብ አርቲስቶቻችን እጣ ፋንታ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነው :: በዚህ ሳምንት የዝግጅት ክፍላችን ከሶስት ድንቅ ባለሙያዎች ጋር ለሰአታት የቆየ ውይይት አድርጎአል :: በመድረክ ላይ የምንወዳቸውንና የደስታችንን ምንጭ የሆኑትን ያህል የግል ህይወታቸውን ስንሰማና ያሉበትን ኑሮ ከነሱ ስንረዳ ምን ያህል አሳዛኝ ፈተና ላይ እነደሆኑ መረዳት ይቻላል :: አርቲስት ዶክሌን ( የወንድወሰን ብርሀኑን ) እንውሰድ .. ድንቅና ጎበዝ ወጣት ( ጎልማሳ ) አርቲስት ነው :: አርቲስቱ የእለት እንጀራውን ለመብላት መኪና ይቀጠቅጣል :: በሙያዊ አጠራር ባትላሜራ ነው :: በዚህ ስራው በደረሰበት ጉዳት አንድ አይኑ አያይለትም :: እርዳታ ባገር ውስጥ ጠይቆ እስካሁን የረባ ነገር አላገኘም :: ይህ አርቲስት እስካሁን ካቀረባቸው ስራዎች ሌላ ገና ለመድረክ ያልወጡ ያልተሰሩና ሊሰራቸው የሚፈልጋቸው 60 በላይ የሚሆኑ ቀልዶችና ጭውውቶች አሉት :: በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ እንኴን አሁንም ቁጭ አላለም :: ውይይታችን ስናደርግ በቅርብ ቀን በሚወጣ አንድ ፊልም ውስጥ ይሳተፍ ነበር :: የዶክሌ ( ወንድወሰን ) መጻዊ እድል ግን አደገኛ ነው :: አርቲስቱ እርዳታ ካላገኘና ወደ ውጭ ሄዶ መታከም ካልቻለ ሁለተኛውንም አይኑን በመጀመሪያው አይኑ ኢንፌክሽን ምክንያት ሊያጣው እንደሚችል ዶክተሮች ነግረውታል :: ( አርደተውታል ማለት ይሻላል መሰለኝ ) ..ሳይመሽ የምንችለውን ካልረዳናቸው እነዚህን ባለሙያዎች እስከ ወዲያኛው አናያቸውም :: በውይይታችን ላይ እንዴት አርቲስቱን ማግኘት እንደሚቻል ተወያይተናል :: መርዳት የምትፈልጉም ካላችሁ እሱ የሚገኝበትን ቀጥታ የእጁን ቁጥር ልንሰጣችሁ ሙሉ ፍቃደኞች ነን :: ሌላው ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ ነው :: ስለዚህ እውቅ ጋዜጠኛ ሁኔታ ማወቅ የቻልነው ካርቲስት ግርማ ነጋሽ ጋር ባደርግነው ውይይት ላይ ነው :: አርቲስት ግርማ ነጋሽ በነገራችን ላይ ( የኔ ሀሳብ , እንገናኛለን ...አልረሳሽም ...የሸማኔ ፍቅር ..... ዘፋኝና ለተወሰነ ወቅት የስፖርት ጋዜጠኛ የነበረ ነው ) ንጉሴ አክሊሉ ተፈጥሮ የጋዜጠኝነት ዝናብ ያዘነበችለት ድንቅ ሰው ነው :: ግርማ ነጋሽና ጔደኞቹ ንጉሴን ለመርዳት ታች ላይ እያሉ ነው :; ግን ባገር ውስጥም ሆኑ በውጭ ያሉት አድናቂዎቹን ድጋፍና እርዳታ ይፈለጋሉ :: ወገን ለወገን ደራሽ ይሁን :: የእምዬ ኢትዮጵያ ልጅ ወድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ...ኢትዮጵያ እናቴ , እትዮጵያ ኩራቴ ..ኢትዮጵያ አክስቴ . ...እያሉ ከስማችን በታች መደርደር ብቻውን ኢትዮጵያዊነት አይደለም :: ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያውያንን መርዳትና በችግራቸው መድረስ ነው :: በኢትዮጵያ ስም ለለመኑና ለተቸገሩ አንድ ጣሳ ጠላና አንድ ሳህን ንፍሮ ማቀበል ባህላችን እኮ ነው :: ባገር ውጭ ያለን አንድ ብር ሆነ 5 ብር 10 ብርም ሆነ መቶ ብር የምንችለውን እንርዳቸው .. አሉሁልህ አይዞህ ብለን ወገኝተኝነታችን እናሳይ :: ገንዘብ ባይኖረንም እንኴን ደውለን እናጽናናቸው :: በቅርብ ጊዜ ሁሉም ቃለ ምልልሶች ስለሚለቀቁ ከራሳቸው አንደበት ሁሉንም ትሰሙታላችሁ :: ሰላም ::

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቤንዚን

ዋና ኮትኳች

Joined: 30 Jun 2008
Posts: 835

PostPosted: Thu Sep 08, 2011 10:10 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ ክቡራን ለምታደርገው መልካም ስራ እግዚአብሄር ይባርክ h:: ንጉሴ አክሊሉ ያልካቸው ጋዜጠኛ voa ላይ ይቀርቡ የነበሩት ናቸው ? አስታውሳለሁ በዚያ ውብ ዜማቸው ሲዘምሩና የቃላት አጠቃቀማቸውንና ገጠመኞቻቸውን አደንቅ ነበር :: ምን እርዳታ ይፈልጋሉ ?:: ከቻልክ እስቲ ዘርዘር አድርገው የእርዳታውን አይነት i sure would like to help.
thanks bro.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Fri Sep 09, 2011 12:30 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ቤንዚን ወንድሜ ::
አዎ ንጉሴ አክሊሉ በቪኦኤ ላይ አልፎ አልፎ ይቀርብ የነበረ ሲሆን በይበልጥ ግን የሚታወቀው በእሁድ ፕሮግራም ዝግጅት ላይ ነው :: ንጉሴ ተሰጥኦ ያለው ጋዜጠኛ ነው :: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ንጉሴ የአይኖቹ ብርሀን እየደከሙ እቤት መዋል ጀምሯል :: ይሄ አሳዛኝ ዜና ነው :: ከተነገረኝ መረጃ ባስቸኴይ ህክምና ካገኘ የአይኖቹ ብርሀን ይመለሳሉ :: ለንጉሴ አክሊሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሚቴ አቌቁመው ወደ ላይ ወደ ታች ከሚሉት ሰዎች አንዱ አርቲስት ግርማ ነጋሽ ነው :: ግርማ ሁሉንም ነገር ይገልጽላችኌል :: አዎን ንጉሴ እርዳታ ያስፈልገዋል :: ኢንተርቪውን በጣም በቅርብ ጊዜ ልለቀው እሞክራለሁ :: በኔ ከሚነገር በራሱ በግርማ ቢነገር ይሻላል ብዬ ነው :: ግን ወንድሜ ቤንዚን አንተና አንተን መሰል ቅንና መልካም ሰዎች አይጠፉምና ስለ ሁኔታው በቀጥታ እንድታውቁ የግርማንም የንጉሴንም ቁጥር እተወልሀለሁ :: ግርማ ነጋሽ 0911411508 ይገኛል :: ራሱ ንጉሴ አክሊሉን ደሞ 0911212429 ደውሎ ማግኘት ይቻላል :: የንጉሴ ጔደኞች ለሱ እርዳታ ማሰባሰቢያ በስሙ የከፈቱለት አካውንት ደሞ አለ ::
ይሀውም አዋሽ ኢንተርናሺናል ባንክ ካሳንቺስ ብራንች ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥር 79 ነው :: በዚሁም አጋጣሚ የኔንም ጔደኛ ወንዴን ( ዶክሌን ) አትርሱት :: የእሱም የእጅ ስልክ 0913029833 ነው :: በባንክ ትንሽ ገንዘብም ከላካችሁለት ዳሽን ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ ሲሆን የባንክ አካውንት ቁጥሩ 5027524105015 ነው :: አስባችሁ ሁለቱንም የረዳችሁትንም ደውላችሁም የምታጽኗቸውም እግዚአብሄር አምላክ እናንተንም ቤተ ሰባችሁንም ይባርክ :: በቅርብ ጊዜ ሁሉም ኢንተርቪዎች ይለቀቃሉና ከፈረሱ አፍ ሁሉንም ትሰሙታላችሁ :: ሰላም ::

ቤንዚን እንደጻፈ(ች)ው:
ወንድሜ ክቡራን ለምታደርገው መልካም ስራ እግዚአብሄ ይባርክ h:: ንጉሴ አክሊሉ ያልካቸው ጋዜጠኛ voa ላይ ይቀርቡ የነበሩት ናቸው ? አስታውሳለሁ በዚያ ውብ ዜማቸው ሲዘምሩና የቃላት አጠቃቀማቸውንና ገጠመኞቻቸውን አደንቅ ነበር :: ምን እርዳታ ይፈልጋሉ ?:: ከቻልክ እስቲ ዘርዘር አድርገው የእርዳታውን አይነት i sure would like to help.
thanks bro.

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተውማነው

ኮትኳች

Joined: 16 Apr 2011
Posts: 129
Location: mexico city

PostPosted: Fri Sep 09, 2011 1:04 am    Post subject: Reply with quote

የታመመውን ወንድማችን ኑግሴን እግዚአብሄር ብርሀኑን ይግለጥለት አዎ አርቲስቶቻችን ህብረተሰቡ እንዳገለገሉ ህሉ እኛም ልንረዳቸው ግድ ነው ሀምሳ ሎም I አንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው ይላል ያገሬ ሰው እና እንተባበር የበኩሌን ከማድረግ ወደሁዋላ አልልም ;; አቶክብራን እንዲህ ለበጎ ተግባር መነሳሳትህ ያስመሰግንካል ግን አርቲስት ደበበ እሸቱ በዛሬው እለት በዘረኛው ወያኔ መታሰሩንስ ምን ትላለህ ?Artiste Debebe Eshetu arrested, charged with terrorism
_________________
LONG LIVE TO ETHIOPIA !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Mon Oct 24, 2011 12:05 pm    Post subject: Reply with quote

የሙዚቃ አሬንጀር ( ቅንብር ) የዜማ ደራሲ ተሾመ ሲሳይ ማነው ?
በያኔው የምድር ጦር ኦርኬስትራ ውስጥ በዜማና በግጥም ደራሲነት እንዲሁም አቀነባባሪነት ቡዙ ድንቅ ስራዎች አሉት :: ባንድ ወቅት የአምባሰል ተጫዋች ካሳ ተሰማ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በዛን ምሽት "ትንፋሼ ተቀርጾ " የሚለውን ዜማ ከሌላ ጔደኛው ጋር ( ሲራክ ታደሰ ) ጋር አብሮ የደረሰው ይሄው አርቲስት ነው :: በዘመነ ደርግ የመጀመሪያዎቹ ወራት የወጡ ዜማዎች " ያለምንም ደም እንከኗ ይወደም ...በቀና መንፈስ ኢትዮጵያ ትቅደም ....ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ . ..የሚባሉትን ያብዮት ዘፈኖች ዜማ ያቀናበረ እሱ ነው :: ዛሬም በሙያው አገሩን እያገለገለ ይገኛል :: አሁን በሚዘመረው በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ላይ የሱ አስተዋጾችም እሉበት :: የምድር ጦር ኦርኬስትራ ታሪክና አመሰራረት የሚዳስስ አንድ የጽሁፍ መድብል ከጔደኞቹ ጋር በማዘጋጀት ስራ ተጠምዷል :: ይሄ አርቲስት የሳምንቱ የድህረ ገጻችን እንግዳ ሆኗል :: ከንግዳችን ጋር ያደርገነውን ውይይት ለመስማት እቺን ይጫኑ ::
http://etwnews.ethiopian-this-week.com/guest-of-the-week
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Fri Oct 28, 2011 1:25 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚች ቤት ወዳጆች ,
የታወቀው ድምጸ መረዋው ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት እንግዳችን ይሆናል :: ቢንጎ ! Very Happy ከንጉሴ ጋር ስለ ጤንነቱ ሁኔታ , ከቤተ ክህነት ወደ ጋዜጠኝነት እንዴት እንደተዛወረ ባንድ ወቅት ( በደረግ ዘመን ) የእሁድ ፕሮግራም ላይ ድፍረት ያለው ነገር በማቅረቡ ወደ ፕሬስ እንዲዛወር እንጂ እሁድ ፕሮግራምን እንዳያዘጋጅ ስለመክለክሉ በወቅቱ ከሌሎች ሁሉ ( የሙያ አጋርቹ የሚመሰክሩት ነው ) ደፋር ስለ መሆኑ ስለ ሌሎችም እናወጋለን ...ስለ ንጉሴ ማወቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ በጥያቔ መልክ እናነሳዋልና ሀሳባችሁን ወዲህ በሉኝ :: እስከዛው አንድ ለመንገድ እዚች ! ባይ :: Very Happy

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sun Nov 06, 2011 2:28 am    Post subject: Reply with quote

በመድረክ ስሙ ሳጂን ዶክሌ በመባል ይታወቃል :: ኮሜዲያን ነው :: በጣም ቡዙ በሆኑ አስቂኝ ጭውውቶች ውስጥ ተሳትፏል እንዲሁም ደርሷል :: ዶክሌ ወይም በውነተኛው ስሙ ወንዶሰን ብርሀኑ የኪነ ጥበብ ፍቅር ይኑረው እንጂ ዋና መተዳደሪያው የመኪና ከፈን ጠጋኝ ( ወይም ባትላሜራ ነው ) ስራው በፈጠረበት ችግር ምክንያት የዶክሌ አንድ አይኑ አያይለትም :: ህክምና ባስቸኴይ ካላገኘ ኢንፌክሽኑ ወደ ሁለተኛ አይኑ ሊሄድ እንደሚችል ሀኪሙ ነግሮታል ::አርቲስቶችን ከየቦታው እየፈለገ እንግዶቹ የሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ድህረ ገጽ ( http://www.ethiopianthisweek.com ) ዶክሌን የሳምንቱ እንግዳ ሲያደርግ ደሰታ ይሰማዋል :: ውይይቱን ለመከታተል እቺን ይጫኑ ::
http://etwnews.ethiopian-this-week.com/guest-of-the-week

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sun Nov 06, 2011 4:31 am    Post subject: Reply with quote

እስኪ ከዶክሌ ( ወንድወሰን ) ስራዎች "ፕሮፊሰር " የተባለውን ባለ ሁለት ክፍል አስቂኝ ቀልድ እንመልከት ::

ክፍል 1

ክፍል 2

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 4:01 am    Post subject: Reply with quote

ኢትዮጵያዊነት ክብር ነው :: ኢትዮጵያዊ መሆን እኮ መዋረድ ራስን ዝቅ ማድረግ አይደለም ::ኢትዮጵያዊነት እየተቸገሩና እየተራቡም እንኴን አይ ደህና ነኝ እግዚአብሄር ይመስገን ማለት ነው ኢትዮጵያዊነት ትሁትና ይሉኝታነት ነው :: የዚህ ሁሉ ድምር ነው ኢትዮጵያዊነት :: ኢትዮጵያዊነት እኮ አጋስስነት አይደለም ;; መጀመሪያ ነገር (ሀሌፍ ) እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ነን ... "ሪጋድርለስ ኦፍ አወር ፖሎዪካል ዲፊረንስስ ..." እኔ ኢትዮጵያዊነትን በዛ ዲፋይን አደርጋለሁ :: ፈረንጆች የሚተርቱት አንድ ተረት አላቸው ምን ይላሉ ..you reap what you sow ይላሉ ምን ማለት ነው ..ይሄ ?? የዘራሀውን ታጭዳለህ ማለት ነው በንጥር አማርኛ !! ያልዘራነውን ለማጨድ አንሞክር ...ክፋት እየሰራን ደግነትን ለማጨድ እንሞክር !! ወደ ቤተ ክርስቲያንም አንሂድ ለኮንጊሬግሽኑ መርገምት እንሆናለን :: እውነቴን ነው :: ዛሬ ድንቅ ወጣትና ቡዙ ሊሰሩ የሚችሉ የኪነ ጥበብ ወንድሞቻችንን ካልረዳን ነገ አናያቸውም :: ኢትዮጱያ አገራችን የኪነ ጥበባውያን ድሀ ናት !! ልጆቿን መደገፍና መርዳት አልቻለችም :: ቡዙ በአሉ ግርማዎች , ቡዙ ብርሀኑ ዘሪሁኖች , ቡዙ የፍታሂ ንጉሴዎች , ቡዙ ስብሀት /እግዚአብሄሮች በኖሩን ነበር :: ግን በችግራቸውና በውድቀታቸው አልደረሰልንላቸም አልደገፍንላቸውም ...እነ አላሙዲን የሚረዱት ስም ያለውን ሰው ነው ...( ይቅርታ ይደረገልኝ ! መርዳታቸውን አክብራለሁ ...ሁሉንም መርዳትና መድረስ አይችሉም ይሆናል ...) ግን ሁሌም ለምን ከአላሙዲን እንጠብቃለን ...ለምን ወንድሞቻችንን ራሳችንን አንታደጋቸውም ? 10 ዶላር ወይም 10 ዩሮ ወይንም 10 ፓውንድ ማንን ገደለ ?? እኔ ይሄንን የምለው ራሴን አግልሌ አይደለም ...የምችለውን ለዚህ ወንድሜ ልኬለታለሁ :: እግዚአብሄር ምስክሬ ነው :: እኛም የምንችለውን እናድርግ እየወጡ የሚመጡ ታላላቅ አርቲስቶችን ቆመው እንድናይ ከፈለግን ዛሬ በችግራቸው እንድረስላቸው :: ቅድም እንዳልኩት ነው , ""ያልተዘራ አይታጨድም ::"" እስኪ እቺን ቪዲዮ ልጋብዝ ::
http://www.youtube.com/watch?v=MvrxozUk7Cg&feature=related

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Wed Nov 09, 2011 2:15 pm    Post subject: Reply with quote

የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ድህረ ገጽ ( http://www.ethiopianthisweek.com) ዋና አዘጋጅ አንድ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ከታዋቂው የእሁድ ፕሮጋራም አዘጋጅ ከከተማ ነዋሪዎች ፕሮግራም አዘጋጅ , ከቴሊቪዥን የስፖርት ዜናዎች አዘጋጅና አርታዒ እንዲሁም በቤት ክህነት ትምህርቱና በዜማ አወራረዱ ድንቅ ከሆነው ንጉሴ አክሊሉ ጋር ለሰአታት የቆየ ውይይት አድርጔል :: በዚህ ውይይት ላይ ቡዙ ጉዳዮች ተነስተዋል :: ንጉሴ ለምን ከእሁድ ፕሮግራም እንደለቀቀ እንደውም ከሚወደው የሬድዮ ፕሮግራም እስከ መጨረሻው የለቀቀበትን ዝርዝር ጉዳይ ተወያይትናል :: ከዚህም በተጨማሪ ስለ ንጉሴ የአይን ህመም መንስኤና አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከራሱ አንደበት እንሰማለን :: ሙሉው ቃለ ምልልስ በድህረ ገጻችን ላይ በቅርብ ይለቀቃል :: ለቅምሻ ያህል እቺን ልናካፍል ወደድን :: Stay tuned...
http://ia600702.us.archive.org/27/items/Nakillu1/Naklilupiece1.mp3

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
menzewu

ኮትኳች

Joined: 25 Dec 2009
Posts: 368

PostPosted: Wed Nov 09, 2011 10:45 pm    Post subject: Reply with quote

ክቡራን ....መቸም ሁሉ ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ ....ንጉሴ አክሊሉን በማስታወስህ ....እንዲታወስ በማድረግህ ...ድምጹ በሳይበር አለም እንዲሰማ በማድረግህ እጅግ በጣም ትመሰገናለህ . ንጉሴ እጅግ በጣም ልዪ የሆነ የተፈጥሮና በትምህርት የዳበረ ችሎታ ያለው ሰው ነው . ከሱ ጋር ትንሽ ጊዜ አግኝቶ ረጋ ብሎ ለተጫወተ ሰው መንፈሱ በጣም እንደሚታደስ አያጠራጥርም .

የአይኑ ህመም ትራኮማ ነው . እስራኤል ሄዶ በህክምና ተሞክሮ ነበር . አልሆነም .. ምን ያህል የህክምና ተስፋ እንዳለው እንጃ . ሆኖም ግን መረዳት የሚገባው እንቁ የሆነ ሰው ነው .

ንጉሴ የታዋቂው የኢትዮጵያ / ምሁር የአፈ ሊቅ አክሊሉ ገብረ ኪሮስ ሊጅ ነው . በቅርቡ የሊቁን መጽሀፍ አሳትሟል . መንፈሳዊ ትምህርት የቀሰመው ...ቅዳሴ ...ዜማ ..ቅኔ .. በታእካ ነገስት በአታ ለማርያም ገዳም ነው . በንጉሱ ዘመን በበአታ ቤክ ድምጸ መረዋና ተወዳጅ ዲያቆን እንደነበረ አስታውሳለሁ ..

በእኢንተርቪው ላይ ያሰማው የደብተራ የተረብ ዜማ ወደሁዋላ በትዝታ ወስዶ ሳቅም እንባም አመጣብኝ ..

አረቄ ከመወይን ጣእሙ
እስኩ ድግሙ ድግሙ
እንዳለ ወንድሙ !!!!!

ተባረክ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Thu Nov 10, 2011 3:56 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
Code:
በእኢንተርቪው ላይ ያሰማው የደብተራ የተረብ ዜማ ወደሁዋላ በትዝታ ወስዶ ሳቅም እንባም አመጣብኝ ..

አረቄ ከመወይን ጣእሙ
 
እስኩ ድግሙ ድግሙ
እንዳለ ወንድሙ !!!!!

ተባረክ

አዎን መንዜው እንዳልከው ንጉሴ ቢጨለፍ ቢጪለፍ የማያልቅ ቡዙ ታሪክ አለው : በጣም የገረመኝ ነገር የሰራቸውን ፕሮግራሞች ጭውውታቸውን ሁሉ ያስታውሳቸዋል :: አንዱ ውይይታችን እንዴት ከእሁድ ጥዋት ፕሮግራም እንደተባረረ የሚገልጽ ነበር :: የመባረሩ ምክንያት አሸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ ለእኁድ ዝግጅት የሚሆን አንድ ጭውወት አዘጋጅቶ ንጉሴ ያን አቀናብሮ በማቅረቡ እንደሆነ ገልጾልኝ ጭወውቱን እንዳለ ገጽ ባህሪያቱን ሁሉ ሳይቀር ሲነግረኝ ተዘጋጅቶበት የሚያነብ እንጂ እያስተወሰው አይመስልም :; ይህ እንግዲህ ከዛሬ 27 አመት በፊት የነበረ ባንድ ወቅት የተላለፈ ፕሮግራም መሆኑን ልብ ይሏል :; አብረን እንሰማዋለን መንዜው :: ሰላም ቀን :
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Sun Nov 13, 2011 1:15 am    Post subject: Reply with quote

ከወጣትና ካንጋፋ አርቲስቶቻችን ጋር የጀመርነውን ውይይት እንቀጥላለን :: በኢትዮጵያ የዘህ ሳምንት የሳምንቱ እንግዳ ክፍለ -ጊዜ ዝግጅት ( እቺን ይጫኑ ) ቀጣይ እንግዶቻችን የሚሆኑት አርቲስት በረከት በቀለ ( ፍልፍሉ ) , ምትኩ ፈንቴ (ማይ ክርስቶስና ) አሰፋ ተገኝ ( ዘገየ ) ናቸው :: ስለነዚህ አርቲስቶች ማወቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ በጥያቄ መልክ እናነሣቸዋለንና ሀሳባችሁን አስቀምጡ :: ላሁኑ ግን ፍልፍሉና ምትኩ የሰሩትን ሀኪም አድነው የሚለውን ጭውውት ተጋበዙ :: ግሩም አርት ነው ::
ክፍል 1

ክፍል 2

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3  Next
Page 1 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia