WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 6:38 am    Post subject: ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ Reply with quote

መቸም እዚህ አካባቢ የሚርመሰመሱ ትኍኖች (ተባዮች ) ይሄንን ቅዱስ ስም እንዲህ ተደጋግሞ በርዕስ ሲያዩት 'ዋይ ....በስመ - መለስ በታላቋ ትግራይ ... ምናምን ' Razz ብለው እንደሚያማትቡ የኒህን ትኍኖች ጸባይ የሚያውቅ ሁሉ ይገባዋል Laughing

ንጉስና ካህን ከሆነው ከመልከ ጼዴቅ ልጅ ኢት ኤል በኍላ ኢትዮጵ ከተባለው የመጀመሪያ ንጉስ ስሟን ወስዳ ገናናና ቅዱስ ታሪኳ ከጥንት የሚጀምረው ታላቋ ኢትዮጵያችን በተለያዩ ገዳማት ውስጥ 'ይህችን ሃገር ጠብቃት ' እያሉ በጾም በጸሎት በሚጨነቁላት በሚለምኑላት እንዲሁም በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠብቃ ራዕየ ሰፊወች እጅ ስትገባ እየሰፋች እንደ ወያኔ ራዕየ -ቢስና ጠባብ ጎጠኛ ሲያጋጥማትም ግዛቷ እየጠበበ እዚህ ደርሳለች ::

ታዲያ ምንም እንኳን እኒህ ትኍኖች እየተርመሰመሱ ይህንን ቅዱስና ገናና ስሟን ሊያቆሽሹ ቢሞክሩም ኢትዮጵያችን ግን የቃል ኪዳኑን ታቦት የጠበቀች የያዘችም የቅዱሳን ሃገር ናትና አለች ወደ ፊትም ትኖራለች :: ትኍኖቿም ለጊዜው እንጂ እንደተኆኑ አይኖሩም ይጠፋሉ ...ትኍን በዲዲቲ ይጠፋልና Laughing

ለማንኛውም ኢሳት ቴሌቪዥን ከዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ቃለ -ምልልስ አዳምጡ ::

http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=RBaFyQh1-K0

ኢሳትም እንዲህ ታሪካዊ ሃገራዊና ህዝባዊ ፋይዳ ያላቸውን ቃለ ምልልሶች በማድረጉ ታላቅ አድናቆትና ምስጋና ሊሰጠው ይገባል ...የኢትዮጵያ ጉዳይ ግድ የሚለን ወገኖች እንረዳቸው ዘንድምበዚሁ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ::ሞንሟናው ኢትዮጵያዊ ከጊዮን ምንጭ -ጎዣም
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/

Last edited by የተሞናሞነው on Fri Mar 02, 2012 1:17 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 7:41 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገን ኢት -ዮጵያዊያን Very Happy

ስለ ኢትዮጵያ ታላቅና ገናና ታሪክ ስናወሳ በቅድመ -ታሪክ የነበራትና ከዚያም በኋላ በቅርቡ የምናውቀው እጂጉን ብዙ እንደሆነና በአለም ዘንድ ያላት ግን ሆን ተብሎ በሃገር በቀል ባንዳወችና በፈረንጅና በአረብ ጭን ከፋቾች እንዲጠፋ እየተደረገ ያለው ...እውነታው ግን ትልቅና ብዙ እንዲሁም ገና ብዙ ያልታወቀ ነው ::

ለዛሬ እዚህ ላይ ላወሳው የፈለግሁት ስለ ታቦተ -ጺዮን (ጽላተ -ሙሴ ) እና ስለ አክሱም ሃውልት ነው :: አባቶቻችን እንደነገሩን እንደ ግርሃም ሃንኩክና የመሳሰሉ የተለያዩ የውጭ ተመራማሪወችም ደርሰውበት እንደመሰከሩት ጽላተ -ሙሴ 6ኛው ምዕተ አለም (መሰለኝ ) ከኢየሩሳሌም በግብጽ (ግብጽ ላይ ቆይታለች ) ወደ ኢትዮጵያ ገብታ ጣና ገዳም ላይ ለብዙ መቶ አመታት ቆይታ ነበር እንደገና ወደ አክሱም የተዛወረችው :: እንግዲህ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሚነግረንም የአክሱም ሃውልቶች የቆሙት ታቦተ -ጺዮን ወደ እዚያ ከተዛወረች በኋላ ሳይሆን አይቀርም :: ነገር ግን የአርኪዮሎጂና የታሪክ ጸሃፍት ጊዜውን ይገምቱ እንጂ እንዴት እንደተሰራና እንደቆመ ለምን አላማም እንደቆመ የሚሰጡት መላ ምት ተአማኒነቱ እጂግ ደካማ ነው :: የነገስታት መቃብር ነው ቢባልም ግን አሳማኝ አይደለም (ልክ የግብጽን ፒራሚዶች አንዳንዶቹ ለመቃብር ነው እንዳሉት ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንዳልሆነና ከዚያ ውጭ ለሆነ ብዙም ግልጽ ላልሆነ ወይም ሆን ተብሎ ግልጽ እንዳይሆን ለተደረገ አላማ ነው ::

በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እንዳሉት እንደ ግብጽ ፒራሚዶች ...ደቡብ አሜሪካ ውስጥ እንዳሉት ሚስጥራዊ ፒራሚዶችና ቅርጻ ቅርጾች ...በጃፓን በህንድና በሌሎቹም እስያ ሃገሮች እንዳሉት ጥንታዊ ስልጣኔወች የአክሱም ሃውልቶችም እስካሁን ሚስጥር ናቸው :: በነገራችን ላይ ወድቆና ምናልባትም በዮዲት ጉዲት ዘመን ነው የወደቀውና የተሰበረው የሚባለው 33 ሜትር የሚደርሰው ሃውልት በአለም ላይ ካሉት ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው ከተሰሩት ሃውልቶች በርዝማኔው ተወዳዳሪ የለውም :: እና እኒህን የሚያካክሉ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ በዚያን ጊዜ በነበረው ወይም ሊኖር በሚችለው የቴክኖሎጂ ውጤት ሊሰሩ ይችላሉ ማለትም ካላቸው ግዙፍነትና ካንድ ወጥ ድንጋይ ከመሰራታቸው አንጻር ምራቅ የሚያስውጥ ማሳመኛ አይሆንም ::

የኔን መላ ምት ላስቀምጥና እናንተ የምትሉትን ትቀጥሉልኛላችሁ :: ከላይ እንዳልኩት ጽላተ -ሙሴ በአክሱም ትገኛለች :: እንግዲህ መጽሃፍ ቅዱስ እንደሚገልጸውም ጽላቱ ልዩ የሆነ ሃይል ያለው ነገር ነው (በርግጥ ሳይንቲስቶች እጂግ የመጠቀ የቴክኖሎጂ ውጤት ነበር እያሉ መላምታቸውን ያስቀምጣሉ ):: እና አሁንም እንደ እኔ መላ ምት የአክሱም ሃውልቶች የተሰሩት በዚሁ ጽላት ሃይል እንጂ በጊዜው በነበረው የአክሱማዊያን ሰዋዊ ጥበብ ብቻ አይመስለኝም :: በታቦቱ ሃይል እየተረዱ የቆሙ ሃውልቶች ሊሆኑ ይችላሉ ::

ሃውልቶቹን ጥንት አባቶቻችን ለምን ማቆም አስፈለጋቸው ብየም ብዙ ጊዜ አስቤ መረጃም ለማገላበጥ ሞክሬ አጥጋቢ መልስ ላገኝ አልቻልሁም :: ደግሞ ሃውልቶቹ በር ወይም መስኮት መሰል አላቸው ...ምናልባት ወደ ሌላኛው አለም ወይም ሰማይ (ከሞት በኋላ ወዳለው ዳያሜንሽን ) መግቢያ በር ምሳሌወች ይሆኑ ይሆን ? ምን እናውቃለን :: ምናልባትም ከስነ -ከዋክብት ጋር ልክ እንደ ግብጽ ፒራሚዶች የራሳቸው ውስብስብ ግንኙነት ሊኖራቸውም ይችላል ...ጥናት አልተደረገምና አናውቅም እንጅ ::

እዚያው አክባቢ ያሉ አክሱማዊያንስ ምን ይላሉ ?...ምናልባት ስለ ሃውልቶቹ አሰራርና ለምን እንደ ተሰሩ ሲወርድ ሲዋረድ በአፈ -ታሪክ የደረሰ ግን ችላ የተባለ ሊኖር ይችላልና አክሱምን በቅርብ የምታውቁ ወዲህ በሉኝ :: ይህ የኔና የኢትዮጵያ ጉዳይ እንጂ የወያኔ ወይም የመለስ ጉዳይ አይደለምና በቅን ልቡና ታወሩ ዘንድ እጠይቃችኍለሁ እናንተ ብጣሻሞች Laughing Laughingሞንሟናው ኢት -ዮጵያዊ
ስፈልግ ጣና ስፈልግ አክሱም ጺዮን -ሁሉም የራሴ Very Happy
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2961

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 8:50 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም የተሞናሞነው

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:

ለዛሬ እዚህ ላይ ላወሳው የፈለግሁት ስለ ታቦተ -ጺዮን (ጽላተ -ሙሴ ) እና ስለ አክሱም ሃውልት ነው :: አባቶቻችን እንደነገሩን እንደ ግርሃም ሃንኩክና የመሳሰሉ የተለያዩ የውጭ ተመራማሪወችም ደርሰውበት እንደመሰከሩት ጽላተ -ሙሴ 6ኛው ምዕተ አለም (መሰለኝ ) ከኢየሩሳሌም በግብጽ (ግብጽ ላይ ቆይታለች ) ወደ ኢትዮጵያ ገብታ ጣና ገዳም ላይ ለብዙ መቶ አመታት ቆይታ ነበር እንደገና ወደ አክሱም የተዛወረችው ::

የእምነቱን እና የአባቶቻችንን ጨዋታ ለጊዜው ተወውና እነግራሀም ሀንኩክ እና የተለያዩ የውጭ ተመራማሪዎች ደርሰውበት የመሰከሩትን አሳየኝ እስቲ Wink Laughing Laughing Laughing

ዘንድሮ የጤና ያድርግልህ Rolling Eyes

ሠላም
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3360
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 3:17 pm    Post subject: Reply with quote

ሞንሟናው

ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ለፀረ -ኢትዮጵያውያን መስቀል እንዳየ ሴጣን ያንዘፈዝፋቸዋል ..........ቂቂቂቂ

ዋርካን ኢትዮጵያ በሚል ፀበል ስለረጨሃት እግዜር ይስጥህ ::

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 5:22 pm    Post subject: Reply with quote

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ቅደሚ
በህብረተስባዊነት አብቢ ለምልሚ
ቃልኪደን ገብተዋል ጀግኖሽ ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት ለነጻነትሽ
.
.
.
.
.
.
.
.
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
አንድ ሀገር አንድ ህዝብ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3360
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 5:58 pm    Post subject: Reply with quote

እንደጻፈ(ች)ው:
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ቅደሚ
በህብረተስባዊነት አብቢ ለምልሚ
ቃልኪደን ገብተዋል ጀግኖሽ ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት ለነጻነትሽ
መስዋዕት ሊሆኑ ለክብር ለዝናሽ
ተራመጅ ወደፊት በጥበብ ጎዳና
..................................... ብልፅግና
የጀግኖች እናት ነሽ ................
ጠላቶችሽ ይጥፉ ለዘላለም ኑሪሪሪሪሪ
.
.
.
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
አንድ ሀገር አንድ ህዝብ

_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 9:18 pm    Post subject: Reply with quote

ተነሱ እናንተ ፍትህ ፈላጊወች
ተነሱ እናንተ የፍትህ ምርከኞች
ፍትህ በሚገባ ይበየናል
ሻል ያላለ ምን ይታያል
ከንግዲህ ባለፈው ይብቃን
ኢምንት ነን እልፍ እንሁን
..
.
.
.
.
.
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር "!!!!
አንድ ሀገር አንድ ህዝብ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ደም

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2011
Posts: 292

PostPosted: Mon Nov 07, 2011 9:25 pm    Post subject: Reply with quote

who said we don't like ethiopia you fuking moron i love ethiopia but i hate you since you are banda thats all Wink
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Nov 08, 2011 8:47 am    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ ሰላምታየን በማስቀደም ወንድም ጌታንና ኮርማውን ይህንን ዘፈን ጋበዝኍችሁ ...እንደተቀመጣችሁም ቢሆን እስክስ በሉልኝ እስኪ Very Happy

http://www.youtube.com/watch?v=Dz0OK7O-G2U

በኢትዮጵያችን ስም በተከፈተው በዚህ ቤት ቀስ እያልን እናወጋለን ቅዳሴም መዝሙርም መንዙማም እንሰማበታለን እንዘፍንበታለን እንፎክርበታለንም Smileኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር Exclamationሞንሟናው ኢትዮጵያዊ - ከጊዮን
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Tue Nov 08, 2011 1:07 pm    Post subject: Reply with quote

ትክክል ብለሀል ጌታው ..አንተንም ...ሞንሟናውንም ..ኮርማውንም የኢትዮጲያ አምላክ ይጠብቃችሁ .
መቼም የኢትዮጲያ አምላክ ሲባል ማን ስቅ ..ስቅ ..እንደሚለው ስለማውውቅ ...እኔ ደግሞ አስቀድሜ .. ማን አነሳት ደግሞ ማለቴ አልቀረም Very Happy

እስቲ .. ይችን ግጥም ተጋበዙልኝ .
http://www.dailymotion.com/video/x7g99t_i-love-ethiopia-poetry_creation

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
ሞንሟናው

ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ለፀረ -ኢትዮጵያውያን መስቀል እንዳየ ሴጣን ያንዘፈዝፋቸዋል ..........ቂቂቂቂ

ዋርካን ኢትዮጵያ በሚል ፀበል ስለረጨሃት እግዜር ይስጥህ ::

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ

_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኡቹሩ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Oct 2011
Posts: 96

PostPosted: Tue Nov 08, 2011 1:32 pm    Post subject: Reply with quote

እንደጻፈ(ች)ው:
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ቅደሚ
በህብረተስባዊነት አብቢ ለምልሚ
ቃልኪደን ገብተዋል ጀግኖሽ ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት ለነጻነትሽ
.
.
.
.
.
.
.
.
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
አንድ ሀገር አንድ ህዝብ

ኢትዮጵያች ትቅደም አቆርቅዋዥዋ ይወደም

እኔና አንተ እንሁን በርሀ ወረ
ብረት የሚቃማ ጀግና ተወለደ

ግራ የገባው ኡቹሩ ነን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2010
Posts: 312

PostPosted: Tue Nov 08, 2011 2:38 pm    Post subject: Reply with quote

አንዲት ኢትዮጵያ ወይም ሞት !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Nov 09, 2011 6:13 am    Post subject: Reply with quote

የባዕድ ቅጥረኛው በዘር ተኮለኮለው ወያኔ /ሻቢያ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ተቀን ቢማስንም በየገዳማቱ በየደብሩና በየቤተከርስቲያኑ የቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎትና ውዳሴ ይጠብቃታል Exclamation

http://www.youtube.com/watch?v=1P0AOV27Tqc

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

ሞንሟናው
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Wed Nov 09, 2011 7:22 am    Post subject: Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
ሞንሟናው

ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ለፀረ -ኢትዮጵያውያን መስቀል እንዳየ ሴጣን ያንዘፈዝፋቸዋል ..........ቂቂቂቂ

ዋርካን ኢትዮጵያ በሚል ፀበል ስለረጨሃት እግዜር ይስጥህ ::

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ

የኛ ጌታ ኢትዮጵያ አሁን እያለፈላት የመጣው ወያኔ ከመሰቀል እና ከፀበል ነጻ ካወጣት በህዋላ ነው Laughing መሰቀል አንጠልጥላማ የኖረችበት ጭለማ ዘመን የቅርቡ ትዝታችን ነው Laughing

የተሞናሞነው ... ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ትላለች ጀሚላ ከችርችል ጎዳና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Wed Nov 09, 2011 9:57 am    Post subject: Reply with quote

ወርቅነች እንደጻፈ(ች)ው:

የኛ ጌታ ኢትዮጵያ አሁን እያለፈላት የመጣው Question Question Question Question Question Question Question Question Question Question Question

አህለን ሳህለን ወርቅነች ! ኢትዮጵያ እያለፈላት ነው ለካ ! Confused አጀብ Exclamation አጀብ ነው Exclamation who knew Question ከተመቸሽ ወላሂ ቢላሂ ይመችሽ ብለናል :: ግን ያልገባኝ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለኢትዮጵያ ሰላም ..ለኢትዮጵያኖች ፍቅር ለኢትዮጵያ አንድነት መቆርቆር የጀመሩትና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት የፈለጉት ወያኔ ከመጣ ብህዋላ ነው እንዴ Question እነ ሸህ አባድር ሀረር ሆነው ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያኖች ፍቅርና ሰላም ሲጾሙ ሲጽልዩ እንደነበር እና እነ ሳይድ ኢብራሂም ያሲን (ሸህ አሊ ) ወሎ ሆነው ለኢትዮጵያ ስላም ለኢትዮጵያኖች ፍቅርና ደስታ መንዙማ ሲገጥሙ ..ሲያንጎራጉሩ .. እነደነበር .አልሰማሽም ማለት ነው Question እስቲ ወደ ደጋጎቹ መንደር ..ገር አገሩ ጎራ በይ እና የሀይማኖትሽንና የአገርሽን ታሪክ ተማሪ - ሀቁንም እወቂ :: ወያኔዎች ይዋሻሉና እነሱ የሚሉትን እንደ ቅዱስ ቆራን ቃል መቀበል አያስፈልግም :: ምናልባት ወያኔ ያመጣብን የሳላፊ /ዋሀቢ ጂሀዲስቶች ይሄንን ታሪክ ይክዳሉ ደሞም ይጠላሉ ይናደዳሉ :: በተለይ በቱርኮች ተሹመው ከሀረር ወደ ወሎ የገቡት ባንዳዎች እንደ ገራዶ አይነት ከተማዎች ቆርቁረው ከሌሎች ወሎዬዎች ተገልልው የሚኖሩት መጤዎቹ ይሄንን ታሪክ አያውቁትም ይሆናል ቢያውቁትም እነሱም እንደሰላፊዎቹ ይክዱታል :: ስለዚህ የኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክን ለማወቅ በቅጥታ ወደ ጥሩ ሲና ማምራት ነው :: አደራ ዋሀቢስቱ አላሙዲን ዋሽቶ ተወለድኩበት ከሚለው ቦታም ሆነ ገራዶ ጋር ያሉት ገደሎች ተሳስተሽ እንዳትገቢ ::
ወዲህ ወዲያ ሳትይ በወረ ባቡ በኩል ወደ ጥሩ ሲና አምሪ ...

http://www.kezira.de/wp-content/uploads/2011/08/Tiru_Sina_400X250.jpg
http://www.kezira.de/wp-content/uploads/2011/08/TiruSina_innen_400x300.jpg

እዛ ስትደርሺ እውነታውን ተረጅዋለሽ :: እውነታውም ባጭሩ ይሄ ነው Arrow የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለበዙ ዘበን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ብልዋል ትላንትም ብለዋል ዛሬም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ይላሉ ነገም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለታቸው አይቀርም :: እንዴት አይሉም . Question በቁራን የታዘዘውን Question የአደራ የውለታ ሀገር በነብይ መሀመድ የተባረከ የተቀደስ አገር ? For Thousands of years Ethiopia is the only place on the planet where Cross and Crescent co exist in comfort becaused Ethiopia is blessed and holy by both relgions and beloved by both its followers!!! And that is the truth Exclamation Exclamation

ከላይ የተጠቀሱት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ታላቅ ፍቅርና ክብር የሚገልጹ ታሪካዊ ሀይማኖታዊ ምሳሌዎች ማናልባት ከብዙ መቶ አመታት በፊት የሆኑ ስለሆነ ተረስቶሽ ሊሆን ይችላል :: እነ አሊ ቢራ ግን ኢትዮጵያ ብለው መዝፈናቸውና መሀመድ አህሙድ በደርግ ጊዜ
[color=red]እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም Exclamation
ማለቱ ለመሸምጠጥ የሚያስቸግር ይምስለኛል :: አስታወሽው ? ግን ... Question የእውነት ሙስሊም ብትሆኚማ ከወያኔ በላይ ምስጋናሽ ለደርግ ይሆን ነበር :: Idea ቢያንስ በደርግ ጊዜም አልፎልኛል ማለት ነበረብሽ አንቺ ውለታቢስ ወያኔ :: .. it was Dergue more than Woyane who did so much for Ethiopian Muslims including making Ethiopian Public holiday designated without religious bias in the Deruge proclamation of 21 D e c e m b e r 1974 Idea ምስጋና ቢስ ነሽ በእውነት :: ወያኔ መስጊድ እንክዋን ክልክሎሻል Exclamation የሼይጣን አርማ የሆነውን የሉሲፈር ኮከብን ያንጠለጠሉት ወያኔዎችማ ጠግበው ... እነ ሰኩቱሬ .. መካ መዲና ቤተስኪያን እንሰራለን እያሉሽ ነው !!! አስታፍሩላህ በይ Exclamation ህዋሀት ሀራም ነው :: አላህ አያድነውም ::
Laughing Laughing Laughing በነገራችን ላይ ወርቅነች አንተም እንደ አላህ በዋርካ 99 የተልያዩ ስሞች ያሉህ ትመስላለህ ሳልልህ አላልፍም Laughing Laughing Laughing
ማአሰላማ ..
_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg

Last edited by ዓለማየሁ on Wed Nov 09, 2011 12:38 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 1 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia