View previous topic :: View next topic
Author
Message
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Tue Jan 10, 2012 3:43 pm Post subject:
ስርርር እንደጻፈ(ች)ው : የአንተ ጠባብ ጭንቅላት ብላ ብላ የኦርቶዶክስ መፅሀፍትን (ምርጦቹን ---በአምላክ እጅ የተፃፉትን ) መተቸት ጀመረች ??? የማታድግ ጥጃ አሻቅባ ትሸናለች አሉ ....
Dude, you got such a clumsy dickhead
በአምላክ እጅ የተጻፉትን
ይመችሽ አቦ ስርርር ጭሱ
@ ሚስተር ሲሊ -ማን
አይዞአችን : በስድብ ውስጥ ራሳችንን መወሸቅ ከቻልን እንታገል እንዳልኩት እናንተም ቀጥሉ እኔም እቀጥላለሁ :: የናንተ ስድብ የተክለዬን ገድል ነፍስ ይዘራበት እንደሆን እናያለን
ሠላም ! _________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ቆቁ Joined: 21 Sep 2003 Posts: 4466 Location: united states
Posted: Tue Jan 10, 2012 6:29 pm Post subject:
ወዳጄ ጸዋር አሁን ደግሞ
ገድለ www.youtube. ጀመርክ ከዛ በሁዋላ ደግሞ ስለ አለቃ ኪዳነ ወልድ መዘብዘብ ጀመርክ
አንድ ባለ ቅኔ ደብተራ ነው አንድ ደብተራ ባለ ቅኔ ሊሆን ይችላል የሚል ነገር ግልጽ ይሆንልህ ይሆን ?
አንድ ደብተራ ደብተራ ሊባል የሚያስችለው መስፈርት ምንድነው ?
አንድ ባለቅኔስ ባለቅኔ ሊያሰኘው የሚችለው መስፈርት ምንድነው
ገድለ ዩ - ቲውብ : ገድለ በዓሉ ግርማ :. ገድለ ዲያቆኔ ሉሌ እያነበብክ እባክህ አትንበዝበዝ
ማንበብ ትችላለህ ነገር ግን አይገባህም እኮ ነው የምልህ
አለቃ ኪዳነ ወልድ የጻፉት ገብቷህል
ፕሮፌሰር ጌታቸው ሐይሌ የጻፍፉትስ ገብቷህል
አለቃ ኪዳነ ወልድ የጻፉት ስለዚህ አንተ ከላይ ስለጻፍከው ገድል ነው
ኦሪጂናሉ ገድለ ተክለ ሐይማኖት የት ገባ የሚል ጥያቄ በዚህ በሚጢጢዋ ጭንቅላትህ አንኩዋክቶብህ ይሆን
ከ 254 አመታት በሁዋላ ተበላሸ ነው ያሉት ብለሀል ::
ከ 254 አመታት በፊት ግን አልተበላሸም ነበር ማለታቸውስ አልገባህ ይሆን ?
ታነባለህ ነገር አይገባህም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ስርርር Joined: 05 Mar 2010 Posts: 731
Posted: Tue Jan 10, 2012 8:06 pm Post subject:
ስምህን ቄስ ይጥራውና ፀዋር ! በተንቦረቀቀው ቂጥህ ማሰብ ጀመርክ አይደል ? ለማንም ጥቁር ቂጥህን እያስወቃህ ....ይህንን የ getto/vulgar እንግሊዝኛ አስለመዱህና ሲሊ ማን ....ዱድ ዲክ ሄድ .....ምናምን ትላለህ :: የእንግዴ ልጅ ... ዝምብ ! እንዳንተ አይነቱ ነው ለሃገርም ለወገን አሳፋሪ ሆኖ በየሔድንበት ሁሉ መሰደቢያ የሆንነው :: ላንተን ብሎ ኦርቶዶክስ .....ሂድና ለፓስተርህ አፈንድድለት ....በቂጥህ ይከትልሃል !!!!!!!!! ፍግም ያድርግህና ! ድሮም ከፍናፍንት ወንዳገረድ ምን ይጠበቃል ??
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Tue Jan 10, 2012 10:51 pm Post subject:
ቆቁ እንደጻፈ(ች)ው : ከ 254 አመታት በሁዋላ ተበላሸ ነው ያሉት ብለሀል ::
ታነባለህ ነገር አይገባህም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
ቆቅነት አድርቅ ነህ ለካ
ያልተጻፈ አንብበህ ስታበቃ : እኔን አይገባህም ትለኛለህ እንዴ
ግድየለህም በወዳጅነታችን ይዤሀለሁ : ታናሽህ ብሆንም ምክሬን ስማና ሙሉውን መጽሀፍ ወደ emailህ የምልክልህን ሁኔታ እናመቻች :: ከዛ ለክርክር ሳይሆን ለራስህ ግንዛቤ ጊዜ ሰጥተህ በደንብ ታነበዋለህ ::
በሆነ ምክንያት ያልተጻፈ ስላነበብክ አሳጥሬ የጽሁፉን ጭብጥ ላስቀምጥልህ ::
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሶስት ተክለሀይማኖታዊያን ነበሩ ይላሉ አለቃ ኪዳነ ወልድ :: የመጀመሪያው ተከለዬ ሀዋሪያዊ ገድሉን የፈጸመ እንደነበረ ያወራሉ :: ሁለተኛው ተክልዬ በወጉ አይታወቅም :: ሶስተኛው ተክለዬ ደግሞ አጭቤው ባለክንፍ ናቸው :: አጭቤ የተባሉበት ምክንያት እንደ አባ ዲያብሎስ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግስት ቅርብ የነበሩ አፈ ጮሌ በመሆናቸው ነው :: ሀዋሪያዊ ገድላቸውን የተወጡ ስላልነበሩም ነው :: በአፈ ጮሌነታቸው ለይኩኖ አምላክ በዋሉለት ውለታ : ያለሆኑትንና ያልሰሩትን እንደሰሩ ተደርጎ መቀርቡን ነው አለቃ ኪዳነ ወልድ የሚናገሩት ::
በይኩኖ አምላክ ጊዜ በውሸት ከፍከፍ ያሉት አንሶ እሳቸው ከሞቱ ከ 254 አመታት ብኋላ ደግሞ ዮሐንስ ከማ የተባለ አንድ የአእምሮ ስንኩል (የስርርር አምላክ ) ሌላ ስህተት ሰራና የቀዳሚው ተክልዬ ታሪክና የአጭቤው ተክልዬ ታሪክ እንደ አንድ ሰው ታሪክ ጨፍልቆ : ከስንኩል አእምሮው የፈለቀ ውሸት ጨማምሮበት (ክንፎችን ጭምሮ ቸሮአቸው ) አሁን አንተ ሳታነብ የምታምንበትንና የምትከራከርለትን ገድል ጻፈ ያ ገድል ማለትም አንተ የምታምንበት ገድል የአጭቤው ማለትም የዕጬጌው ተክለሀይማኖት ገድል እንደሆነ ነው በቤተ ክርስቲያኒቱና በምእመናኑ በስፋት የሚታወቀው ::
ይህን ይመስላል ወዳጄ ቆቁ :: መቼስ እምነትህን ካንተ በላይ እኔ ማወቅ አልነበረብኝም :: ስምንተኛው ሺ ይሏል ይህ ነው
ሠላም _________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ቆቁ Joined: 21 Sep 2003 Posts: 4466 Location: united states
Posted: Wed Jan 11, 2012 8:24 pm Post subject:
Quote:
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሶስት ተክለሀይማኖታዊያን ነበሩ ይላሉ አለቃ ኪዳነ ወልድ :: የመጀመሪያው ተከለዬ ሀዋሪያዊ ገድሉን የፈጸመ እንደነበረ ያወራሉ :: ሁለተኛው ተክልዬ በወጉ አይታወቅም :: ሶስተኛው ተክለዬ ደግሞ አጭቤው ባለክንፍ ናቸው :: አጭቤ የተባሉበት ምክንያት እንደ አባ ዲያብሎስ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግስት ቅርብ የነበሩ አፈ ጮሌ በመሆናቸው ነው :: ሀዋሪያዊ ገድላቸውን የተወጡ ስላልነበሩም ነው :: በአፈ ጮሌነታቸው ለይኩኖ አምላክ በዋሉለት ውለታ : ያለሆኑትንና ያልሰሩትን እንደሰሩ ተደርጎ መቀርቡን ነው አለቃ ኪዳነ ወልድ የሚናገሩት ::
በይኩኖ አምላክ ጊዜ በውሸት ከፍከፍ ያሉት አንሶ እሳቸው ከሞቱ ከ 254 አመታት ብኋላ ደግሞ ዮሐንስ ከማ የተባለ አንድ የአእምሮ ስንኩል (የስርርር አምላክ ) ሌላ ስህተት ሰራና የቀዳሚው ተክልዬ ታሪክና የአጭቤው ተክልዬ ታሪክ እንደ አንድ ሰው ታሪክ ጨፍልቆ : ከስንኩል አእምሮው የፈለቀ ውሸት ጨማምሮበት (ክንፎችን ጭምሮ ቸሮአቸው ) አሁን አንተ ሳታነብ የምታምንበትንና የምትከራከርለትን ገድል ጻፈ ያ ገድል ማለትም አንተ የምታምንበት ገድል የአጭቤው ማለትም የዕጬጌው ተክለሀይማኖት ገድል እንደሆነ ነው በቤተ ክርስቲያኒቱና በምእመናኑ በስፋት የሚታወቀው ::
እዚህ ላይ እኮ ነው አንበህ አይገባህም ያልኩህ
ታነባለህ ነገር ግን ያነበብከው አይገባህም እኮ ነው የምልህ
ሶስት ተክለ ሐይማኖት የሚባሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ ::
ሶስት በቀለ ወይም አራት በቀለ የሚባሉ ነበሩ እንደ ማለት ነው ::
ሲወርድ ሲዋረድ የነዚህ ሶስት ተክለ ሐይማኖቶች ታሪክ ተጨፍልቆ አንድ ሆነና አሁን የሚነበበውን ገድለ ተክለ ሐይማኖት ሆነ ነው የምትለው ::
1. ተክለ ሐይማኖት ገድሉን የፈጸመው
2. በወጉ የማይታወቀው ተክልዬ
3. ባለክንፍ ተክልዬ
እዚህ ላይ ስታነብ አንድ ሐዋርያ ተክለ ሐይማኖት የሚባል ኢትዮጵያዊ እንደነበረ ግን አትክድም ::
ስለሆነም እኛ ኦርቶዶክሶች የምንቀበለው ይህንን ሐዋርያ ተክለ ሓይማኖት ነው ::
የገብረ መንፈስ ቅዱስም ታሪክ እንደዚሁ ነው
በመጀመሪያ ጽሁፌ ያልኩህ ይሄንን እኮ ነው
ገድሉ ተፈጽሟል ሐዋርያቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ : ሶርያኖችም ነበሩ
ለምን እንደዚህ ያለ ገድል ተጻፈ ብለህ ብትጠይቅስ ምን ይመስልሀል ?
ለመሆኑ ኦሪጂናል የሆነው ገድለ ተክለ ሐይማኖት እና ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድለ ሰምራ ክርስቶስ በመቃጠሉና የእምነት እና የአምልኮ መናጋት በኢትዮጵያ ስለተጀመረ ይሆን ?
ይህ የአምልኮ መናጋት ይሆን ለሐገራችን ትልቅ እዳ ሆኖ የቀረው ብለህ ጤይቀህ ይሆን ?
ማነው የዚህ ገድል ጸሓፊ ?
ከአጼ ዘርዓ ያቆብ በፊት ስለ ነበረው ሁኔታ እኮ ማውራት አልቻልንም ታሪካችን እምነታችን በጠቅላላው በመውደሙ :: በመተረማመሱ
ክርስቲያኑ ስለ ክርስትና ማውራት አይችልም
የጋዳው ማህበር ስለ ጋዳው ማህበር ማውራት አይችልም
የእስልምና ተከታዩ ስለ እስልምና ማውራት አይችልም
ሐገርህ ኢትዮጵያ ድብልቅልቅ ያለ ታሪክ እና እምነት አደበላልቃ መጉዋዝ ጀመረች
ስለዚህም ነው የአቡነ ተክለ ሐይማኖት እናት በንጉስ ጦና ይሁን በሌላ ተማርከው መሄዳቸው
አቡነ ተክለ ሐይማኖት ከቲሳ የተወለዱ መሆናቸው
እያለ እያለ ይቀጥላል ታሪካችን መደበላለቃችን
በነገራችን 254 አመት ማለት 253 ሰከንድ ማለት እኮ አይደለም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Wed Jan 11, 2012 10:13 pm Post subject:
ቆቅነት እንደተገነዘብኩት ከሆነ በራስህ አለም የምትኖር ፈላስፋ ነህ :: ይቺን አለምህን ክፉኛ እንደበጠበጥኩብህ ይሰማኛል :: ከዚህ ብኋላ አለምህን እንደለመድከው እንትቀጭ : እንድትፈስበት : እንድትሆንበት ብቻህን እተውሀለሁ የመጨረሻ አስተያየት ሰስጥህ ግን ደፈርከኝ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ ::
ቆቅነት ያንተ ችግር ሳታነብ መከራከርህ ብቻ አይደለም :: የምታነባቸውንም በአግባቡ እንደማትረዳቸው ነው የኔ ግንዛቤ :: ወይም ደግሞ ትኩረትህ ክርክር ስለሆነ የምታነበውን አጣመህ ነው የምትረዳው :: ከዚህም በተጨማሪም ማንበብ የማያስፈልገው ስለ እምነትህ ያለህ አጠቃላይ ግንዛቤም ዝቅተኛ እንደሆነ ነው የተረዳሁት :: አንድ ምሳሌ ብጠቅስልህ : ቤተ ክርስቲያን የምታምንበት ተክለሀይማኖት ሀዋሪያውን እንደሆነ ለመመስከር ሞክረሀል :: ነገር ግን በስዕል የምታውቀው ተክለሀይማኖት ቆራጣ እግርና ባለክንፈ መሆኑን ልብ ማለት አልቻልክም :: እንዳልኩህ አለምህን አልበጥብጥብህና ሠላሙን ተመኝቼልህ ልሰናበትህ ::
አክባሪህ !
ቆቁ እንደጻፈ(ች)ው : Quote:
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሶስት ተክለሀይማኖታዊያን ነበሩ ይላሉ አለቃ ኪዳነ ወልድ :: የመጀመሪያው ተከለዬ ሀዋሪያዊ ገድሉን የፈጸመ እንደነበረ ያወራሉ :: ሁለተኛው ተክልዬ በወጉ አይታወቅም :: ሶስተኛው ተክለዬ ደግሞ አጭቤው ባለክንፍ ናቸው :: አጭቤ የተባሉበት ምክንያት እንደ አባ ዲያብሎስ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግስት ቅርብ የነበሩ አፈ ጮሌ በመሆናቸው ነው :: ሀዋሪያዊ ገድላቸውን የተወጡ ስላልነበሩም ነው :: በአፈ ጮሌነታቸው ለይኩኖ አምላክ በዋሉለት ውለታ : ያለሆኑትንና ያልሰሩትን እንደሰሩ ተደርጎ መቀርቡን ነው አለቃ ኪዳነ ወልድ የሚናገሩት ::
በይኩኖ አምላክ ጊዜ በውሸት ከፍከፍ ያሉት አንሶ እሳቸው ከሞቱ ከ 254 አመታት ብኋላ ደግሞ ዮሐንስ ከማ የተባለ አንድ የአእምሮ ስንኩል (የስርርር አምላክ ) ሌላ ስህተት ሰራና የቀዳሚው ተክልዬ ታሪክና የአጭቤው ተክልዬ ታሪክ እንደ አንድ ሰው ታሪክ ጨፍልቆ : ከስንኩል አእምሮው የፈለቀ ውሸት ጨማምሮበት (ክንፎችን ጭምሮ ቸሮአቸው ) አሁን አንተ ሳታነብ የምታምንበትንና የምትከራከርለትን ገድል ጻፈ ያ ገድል ማለትም አንተ የምታምንበት ገድል የአጭቤው ማለትም የዕጬጌው ተክለሀይማኖት ገድል እንደሆነ ነው በቤተ ክርስቲያኒቱና በምእመናኑ በስፋት የሚታወቀው ::
እዚህ ላይ እኮ ነው አንበህ አይገባህም ያልኩህ
ታነባለህ ነገር ግን ያነበብከው አይገባህም እኮ ነው የምልህ
ሶስት ተክለ ሐይማኖት የሚባሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ ::
ሶስት በቀለ ወይም አራት በቀለ የሚባሉ ነበሩ እንደ ማለት ነው ::
ሲወርድ ሲዋረድ የነዚህ ሶስት ተክለ ሐይማኖቶች ታሪክ ተጨፍልቆ አንድ ሆነና አሁን የሚነበበውን ገድለ ተክለ ሐይማኖት ሆነ ነው የምትለው ::
1. ተክለ ሐይማኖት ገድሉን የፈጸመው
2. በወጉ የማይታወቀው ተክልዬ
3. ባለክንፍ ተክልዬ
እዚህ ላይ ስታነብ አንድ ሐዋርያ ተክለ ሐይማኖት የሚባል ኢትዮጵያዊ እንደነበረ ግን አትክድም ::
ስለሆነም እኛ ኦርቶዶክሶች የምንቀበለው ይህንን ሐዋርያ ተክለ ሓይማኖት ነው ::
የገብረ መንፈስ ቅዱስም ታሪክ እንደዚሁ ነው
በመጀመሪያ ጽሁፌ ያልኩህ ይሄንን እኮ ነው
ገድሉ ተፈጽሟል ሐዋርያቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ : ሶርያኖችም ነበሩ
ለምን እንደዚህ ያለ ገድል ተጻፈ ብለህ ብትጠይቅስ ምን ይመስልሀል ?
ለመሆኑ ኦሪጂናል የሆነው ገድለ ተክለ ሐይማኖት እና ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድለ ሰምራ ክርስቶስ በመቃጠሉና የእምነት እና የአምልኮ መናጋት በኢትዮጵያ ስለተጀመረ ይሆን ?
ይህ የአምልኮ መናጋት ይሆን ለሐገራችን ትልቅ እዳ ሆኖ የቀረው ብለህ ጤይቀህ ይሆን ?
ማነው የዚህ ገድል ጸሓፊ ?
ከአጼ ዘርዓ ያቆብ በፊት ስለ ነበረው ሁኔታ እኮ ማውራት አልቻልንም ታሪካችን እምነታችን በጠቅላላው በመውደሙ :: በመተረማመሱ
ክርስቲያኑ ስለ ክርስትና ማውራት አይችልም
የጋዳው ማህበር ስለ ጋዳው ማህበር ማውራት አይችልም
የእስልምና ተከታዩ ስለ እስልምና ማውራት አይችልም
ሐገርህ ኢትዮጵያ ድብልቅልቅ ያለ ታሪክ እና እምነት አደበላልቃ መጉዋዝ ጀመረች
ስለዚህም ነው የአቡነ ተክለ ሐይማኖት እናት በንጉስ ጦና ይሁን በሌላ ተማርከው መሄዳቸው
አቡነ ተክለ ሐይማኖት ከቲሳ የተወለዱ መሆናቸው
እያለ እያለ ይቀጥላል ታሪካችን መደበላለቃችን
በነገራችን 254 አመት ማለት 253 ሰከንድ ማለት እኮ አይደለም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
ፈላስፋው ቆቁ ሳይካትሪስቱም
_________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ቆቁ Joined: 21 Sep 2003 Posts: 4466 Location: united states
Posted: Thu Jan 12, 2012 9:24 pm Post subject:
ጸዋር ትክክለኛው መንገድ እና ለውጥ ፍለጋው እንዳንተ በመሳለቅ እና በመዝለፍ አይደለም አኮ ነው የምልህ
ተክለ ሐይማኖት ሐዋርያው ::
ለምን ስለ ክንፍና ስለ አንድ እግር ትከራከራለህ ?
መዳረቅ መሳለቅ እኮ ነው የጀመርከው
ለለውጥ የምትጉዋዝ ከሆነ
የሐዋርያው ተክለ ሐይማኖትን ታሪክ ተከተል
የዚህ የሐዋርያው ተክለ ሐይማኖት ገድል ምንድነው የሚለው ?
እዚህ ላይ ነው ለውጡ : ማሻሻሉ ወዳጄ ጸዋር
ገብረ መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ
ከበስተሁዋላ የተጻፈውን በመመልከት አይደለም ዘለፋ እና መሳለቅ ማድረግ የሚገባህ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚባል የሶርያ ስደተኛ በባይዛንተን ኢምፓየር በኢትዮጵያ ነበር የሚለው ጉዳይ ነው ::
እነዚህ ሐዋርያት ከትክክለኛው የሐዋርያት ተግባርና የክርስትና እምንት የሚለዩ ስራዎች በምድረ ኢትዮጵያ ሰርተዋል የሚለው ጥያቄ ነው አንተን የሚያመራምርህ
ከነሱ ሞት በሁዋላ ለዛውም ከ 254 አመታት በሁዋላ እንደዚህ ተጻፈ እንደዛ ተጻፈ በማለት መሳለቁ የደካማዎች ነጥብ ነው ::
ከ 254 አመታት በሁዋላ መዓት የቅኔ ባለሙያዎች ተነስተዋል በኢትዮጵያ የተለያየ ባህል መሰረት እንደ አሸን የፈሉ ደብተራዎች እና ባለቅኔዎች ተነስተዋል : ተፈልፍለዋል ::
ከራሳቸው ባህልና ተለምዶ በመነሳት ብዙ ቅኔዎችና ገድሎች ለመጻፍ የበቁ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ነበሩ አሉ ::
ይህንን እና የመሳሰለውን በመመልከት ብስለትህን ጠለቅ ለማድረግ ሞክርና ለመወያየት ተዘጋጅ
ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Mon Jan 16, 2012 3:18 pm Post subject: በዛብህ : ልማድና ፈጣሪ
ሠላም እንደምን ቆያችሁ
ለዛሬ ደግሞ ጋሽ ሀዲስ አለማየሁ ከተዉልን ዕንቁ ድርሰት ቀንጨብ አድርጌ ለዚህ ቤት የሚመጥነውን አስነብባችኋለሁኝ :: በድጋሚ መልካም ቆይታ ::
አንዳንድ ጊዜ ሽምብራ ብቻ እየቆረጠመ ውሀ እየጠጣ ሶስትም ሰባትም ቀን እየጾመ ሲጸልይ እንኩዋ እንደ ድሮው እልም አያይም :: የሚያየውም ያክል የሚያስፈራራና ቅዠት እንጂ የሚያጽናና ተስፋ የሚሰጥ አይደለም :: ስለዚህ ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ሰብለን የማግኘቱ ተስፋ እየተቀነሰ እያነሰ መሄድ ብቻ ሳይሆን ያ ብቅ ጥልቅ እያለ አብሮት የሚኖረው በሄደበት ሁሉ የሚከተለው ፍራት ባሳቡ ውስጥ እየጎላ ይታዬው ጀመር :: ገና ሲፈጠር ፈጣሪው የመደበለትን ህይወት በመሸሹ ወላጆቹንም እ /ርንም የበደለ መሆኑ ቅጣት የሚገባው ጥፋተኛ መሆኑ በጉልህ ድምጽ ራሱ ውስጥ ሲጮህ ይሰማው ጀመር :: ለመስዋትነት እንጂ ደስ ብሎት ኖሮ ለማለፍ ያልተፈጠረ መሆኑን ይጠረጥር ጀመር ::
'ብቻ ለምን ? ከተወለድሁ ጀምሮ እንዲህ ያለ ፍርድ ሊያስፈርድብኝ የሚችል በደል እ /ርን አልበደልሁም ! ሳልወለድም ልበድለው አልችልም : ታድያ ሳልበድል ለምን የግዞት ኑሮ እንድኖት ይፈረድብኛል ' ይላል በዛብህ ትክክለኛ ነው የሚባለው እ /ር ባልበደሉት ላይ የቅጣት ፍርድ የሚፈርድበት ምክንያት አልገባው ብሎ በራሱ ውስጥ ያለ ሰሚ ያለ ዳኛ እየተሙዋገተ ::
ከዚህ በሱ ላይ ከድረሰው ጋር ተያይዞ በጠቅላላው ሰው የሚኖርበት የማህበራዊ ኑሮ ስራት ይታየዋል :: በጌታና በባሪያ : በስጋዊም ሆነ በምንፈሳዊ ገዢዎችና በተገዢው ህዝብ መሀከል ያለው በግፍ ባድልዎና በጭካኔ ላይ የተመሰረተ ስራት ይታየዋል :: ከዚያ ደካማ ይደገፍበታል : የተበደለ ይካስበታል : የሰው መብትና ነጻነት ይከበርበታል ብሎ ይገምተው የነበረው የንጉሱ አደባባይ ደካማ በመደገፍ ፈንታ ተበደልሁ ብሎ ለማኩረፍ ነጻነት የማያገኝበት መሆኑን አንድ ቀን እግብር ላይ ያየው ትዝ ይለዋል :: ከዚያ የመንፈሳዊ መሪዎችና አስተማሪዎች ነን በሚሉት ዘንድ ያለ ስጋውያን ገዢዎች ከሚያደርጉት የማያንስ መገበያየት : ጉቦ : ግፍ : በደል : ተንኮል : ሁሉ ይታየዋል ::
'አዎ ! አለሙ እንደ ለማኝ እህል ድብልቅልቅ ያለ እንደ ባለጌዎች ሸንጎ ትልቅ ድምጽ ያላቸው ብቻ እንዲሰሙበት ብርቱ ጡንቻ ያላቸው ብቻ እንዲያሸንፉበት ሆኖ የተሰራ ነው ! እኔም ተሰሚ ድምጽና ብርቱ ጡንቻ ከሌላቸው አንዱ ነኝ :: ብቻ ይህን ሁሉ እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ማነው ? እ /ር ነው ? ወይስ ጉዱ ካሳ ሁል ጊዜ እንደሚለው ልማድ ነው ?' ይላል በዛብህ : የማያዩ አይኖቹን ፍጥጥ አድርጎ ፊት ለፊት ተክሎ :: 'ይህ ሁሉ አይንና ጆሮ በሌለው አድልዎ ላይ የተመሰረተ ስራት : እውነት አዋቂው , ትክክለኛው , ቸሩ , ትልቁ እ /ር የሰራው ነው ? እሱስ ባይሰራው የሰሩትንና ሲሰሩት የሚኖሩትን ለምን ዝም ይላቸዋል ? እንጃ ! የሱ ስራት አይደለም እንዳልል ጌታና ባሪያ , ገዢ ንጉስና ተገዢ ህዝብ , አባትና እናት ልጃቸውን እንደ ያእቆብ መስዋእት አድርገው ማቅረብ ሁሉ ከኦሪት ጀምሮ በመጽሀፍ ይገኛል ; እሱ የሰራው ስራት ነው እንዳልል ፍጥረቱን ያላንዳች ምክንያት በበዳይና በተበዳይ መሀከል እንዲከፋፈል ማድረግ : ያልበደለ ሁልጊዜ እንደ ተቀጣ የበደለ ሁል ጊዜ እንደበደለ እንዲኖር ማድረግ : እንኩዋንስ ያዋቂዎች ሁሉ አዋቂ የሆነው እ /ር , የመንደር ዳኛም የሚፈረደው አይደለ ! ታድያ እንዴት ነው ? እንጃ !'
ጋሽ ሀዲስ በበዛብህ በኩል ያስተላለፉት መልዕክት ለምድራዊ ችግሮቹ ሠማያዊ ጣልቃ ገብነትን (devine intervention) ሲጠብቅ እጅና እግሩን አቆላልፎ ሲቀመጥ ለኖረ ህዝብ ነበር :: የሚገርመው ግን ዛሬም ያ ህዝብ ምንም ያልተለወጠ መሆኑ ነው :: ይባስ ብሎም የለውጥ አቀንቃኝ ይሆናል የሚባለው ዘመናዊ ት /ትን የተቋደሰው የህብረተሰባችን ክፍል ካልተማረው የባሰ ደረቅና arrogant መሆኑ ነው :: የጋሽ ሀዲስ ትምህርት ዘመን የማይሽረው የሚያስብለውም ይህ የእኛ ባለንበት መቆም ነው ለዛሬው ትውልድ የሚመጥን ትምህርት እንደመሆኑ እንድናስብበት ነው ወደፊት ማምጣቴ :: በተለይም መጥፎ ልማዶችንና የውሸት ታሪኮችን ሳያነቡና ሳይመረምሩ አምነው ተቀብለው : በጨበጣ ይህን መጥፎ ልማድና ታሪክ ለመከላከል የሚንፈራገጡ አጉራ ዘለል ቄሶችና ተከታዮቻቸው በደንብ ሊያነቡት ይገባል ::
ሠላም _________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ቆቁ Joined: 21 Sep 2003 Posts: 4466 Location: united states
Posted: Mon Jan 16, 2012 8:08 pm Post subject:
ደግሞ ዛሬ ገድለ ፍቅር እስከ መቃብር ማንበብ ጀመርክ
ጸዋር ወዳጄ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሮ ግሮ ያስተማረው ልጁ እንዳንተ ያለው ማለት ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማ በመሆኑ
ብቻ ነው ለውጥና መሻሻል የቀረው ::
ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
ያለው ያልታወቀው የኢትዮጵያ ገበሬ ነበር እንዲህ ያለው ::
ይገባሀል ይህ አባባል
የአንተን ዝባዝንኬ በሁለት ስንኝ ብቻ ነው የአገሬ ገበሬ በጠቅላላው የዘጋው ::
ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Thu Feb 09, 2012 12:21 am Post subject: የፈላስፎች ንግግር
የሐሰት ወገኖች ተመቸን እያሉ
ብዙ ጊዜ አድመው እየተማማሉ
እውነትን ከዓለም ላይ ሊያጠፉዋት ተነሡ
እውነት ግን ሁል ጊዜ መከታ ለነሱ
ታግላ እያሸነፈች ስትኖር ረግታ
ጠላቶችዋ ሁሉ በሱዋ ጥፋት ፈንታ
አንድ ባንድ ወድቀው እየተሰበሩ
ከስማቸው ጋራ ሁሉም ጠፍተው ቀሩ ::
ከበደ ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ 1ኛ መጽሀፍ [color=indigo] _________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዲጎኔ Joined: 19 Aug 2005 Posts: 3881 Location: united states
Posted: Thu Feb 09, 2012 1:27 am Post subject:
ሰላም ለሁላችን ይሁን
ፕሮፌሰር ጌታቸው በደርግ ወታደሮች ሽባ ሆነው ይቅርታ ያደረጉላቸው ክርስቲያን ወንድም ናቸው ::በቅርቡም ያሳተሙት ይህ የነደቅ እስጢፎ መጽሀፍ ከፍቅር እስከመቃብር ቀጥሎ የዚያን ግፈኛ ስርአት በክርስትና ስም በህዝቦች ላይ ያደረሰውን መንፈሳዊና ስጋዊ ጭቆና የሚገልጽ ነው ::በትክክል ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት የእኛ ነገር በሁሉም አቅጣጫ ጥያቄ ያለበት እርም የተሞላበት ታሪክ ያለን ህዝቦች ነን ::አውሮፓን ለተሻለ ደረጃ ያበቃት የመንፈሳዊም ሆነ የኢንዱስትሪያል ተሀድሶ በእኛዋ ሀገር እንዳይኖር እነዘርያቆብ አጋንንታዊ መሪዎች ምንደኛ ቀሳውስቶቻቸው መሳሪያነት የፈጠሩት እንቅፋት አሁንም ድረስ ሰንኮፉ አልተነቀለም ::ከተሀድሶ ዘመን በሁዋላ ይህ እውነተ የተገለጸለት መለስተኛ እርምጃ የወሰደ መይሳው ካሳ ድንቅ የተሀድሶ ሚሽነሪዎችን ከኮሎኒያሊስም አራማጅ "ሚሲዮን 'ለይቶ የያዘ ሲሆን ዮሀንስ ቤል የተባለ ቅን ሚሲዮናዊም ከምይሳው ካሳ ጋር ሲፋለም ተሰውቷል ::ሆኖም ግን መይሳው ካሳ አለቃ ዘነብን በመሰሉ የተሀድሶ ሊቆች ድጋፍ ብዙ ራእዮቹ ቀጥሎ መጨረሻ ላይ ለወራሪ እጅ አልሰጥ ብሎ በራሱ ወገኖች ጠቁዋሚነት ሊይዙት የሞከሩትን ተፋልሞ ራሱን ሰውቷል ::ከዚያ በፊት ያለስራ ይቀለቡ የነበሩ ደብተራዎችን ስራ ስሩ በማለቱ ሆድ አምላኮቹ በቁርባን ውስጥ መርዝ ከተው ሊገድሉት የነበሩትን ራሳቸው በልተው እንዲንጨፈረሩ ሆኗል ::መይሳው ካሳን የተካው ሚኒሊክም ደቡብና ኦሮሚያ በጦር ያለህዝቦች ፈቃድ ቢጠቀልልም እንደ ካሳ በተሀድሶ ሚሲዮናዊያን በመጠኑ ተጠቅሟል የሀገር ተሀድሶዎችን እነሂካ ኦነሲሞስ ነሲብና አለቃ ታዬን ለሚኒስትርነት ቢያጭም እነርሱ ወንጌልን አብልጠውው ሹመቱን ባይቀበሉም በዘመናዊ ጥበብ ምክር ረድተዋል ::
እንግዲህ አሁን ለዚያች ሀገርና ህዝቦች ያለ ብቸኛ አማራጭ በመንፈሳዊም በስጋዊም ነገር መታደስ ብቻ ነው ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከቀዳማዊ ፋብሪካ ጋፋት ሰፈር ተሀድሶ ጸሎት ቤት
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው : ሠላም
HOW MANY OF YOU HAVE HAD THE CHANCE TO READ ደቂቀ እስጢፋኖስ , A BOOK TRANSLATED FROM GE'EZ BY GETACHEW HAILE
IF YOU HAVE NOT READ IT YET, I WOULD RECOMMEND YOU.
Quote: እውነት ተደብቃ አትቀርም፡፡ እንደ ወንጌሉ ቃልም "የማይገለጥ የተከደነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ የለም፡፡ " (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 26)፡፡ መነሻው እውነት፣ ከእውነትም የወንጌል እውነት የሆነው የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ገድልና የተጋድሎ ታሪክ በሰው ሐሳብ እንዳይነሣ ተደርጎ ከተገደለና ከተቀበረ ብዙ ምእት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንጻሩ የእነርሱ እውነተኛነት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና በተከታዮቹ ሐሰተኛ ምስክርነት ሲስተባበል ኖሯል፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እውነተኛ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ሐሰተኛ፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሃይማኖተኛ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ከሓድያን፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የማርያም ወዳጅ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ የማርያም ጠላት፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ክርስቲያን፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ደግሞ አይሁዳውያን፣ ሰው በላው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጻድቅ፣ ስለ ክርስቶስ ወንጌል የተገደሉና እንደሚታረዱ በጎች የተቆጠሩት አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ግን ኃጥኣን፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሃይማኖትን በካራ ለማስፋፋት ላወጀው ጭፍጨፋ ብርሃን የወረደለት የእግዚአብሔር ወዳጅ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ለማርያም ሥዕልና ለመስቀል አንሰግድም ስላሉ መቅሠፍት የወረደባቸው አፅራረ እግዚአብሔር መሆናቸው ሲተረክ ምእት ዓመታት ዐልፈዋል፡፡ http://www.abaselama.org/2011/12/blog-post_19.html#more
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሥለ መጽሀፉ ካወሩት ከመፅሀፉ ቀዳሚ ቃል የተወሰደ TO DOWNLOAD AND READ THE BOOK FOR FREE CLICK here )
Quote: ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ የተጻፈው ይህ መጽሀፍ የኢ /ያን ህዝብ ታሪክና ባህል በአዲስ መንፈስ እንደገና እንድንመረምር የሚጋብዘን ይመስለኛል :: ኢ /ያን የአይሁድ አገር ለማድረግ : የክርስቲያን አገር ለማድረግ : የእስላም አገር ለማድረግ የጠፋው የሰው ሕይወት : የፈሰሰው የሰው ደም : የወደመው ንብረት ለሕገ አራዊት እንደተገበረ መሥዋዕት ልንወስደው የምንችል ይመስለኛል :: የሚያሳዝነው ለሕገ አራዊት መገበሩ ገና ዛሬም አለማብቃቱ ነው :: ይህ ነው እያንዳንዳችን ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚያስገድደን : ምንድን ነው በእኛ ውስጥ ወይም በባህላችን ውስጥ ሐሳብን እንደጦር የሚፈሩ ሰዎች አናታችን ላይ እንዲወጡ የሚያደርጋቸው ? በተራው ኢትዮጵያዊም ዘንድ ቢሆን ይኸው ሓሳብን የመፍራት አዝማሚያ እንዴት ባህል ሆን ? ጭቆናን የኢ /ያን ባሕርይ ያደረገው ምንድን ነው ? ከማንም ህዝብ የተለየ የጭቆና ዝንባሌ የለንም የሚሉ ሰዎች አሉ :: ይህንን እውነት ለመካድ መሞከሩ አይረዳንም : መድሀኒት የሚሆነን መቀበሉና መመርመሩ ነው ::
ጌታቸው በመግቢያው ላይ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከማርቲን ሉተር ሠላሳ ዓመታት ቀድመው ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያመጡ ሰዎች ነበሩ ይላል :: ይህ ትልቅ ነጥብ ነው :: ... አእምሮ ከአፈና ሲወጣና ነጻነትን ሲያገኝ ከሰው ልጅ ውስጥ የእግዚአብሄር እስትንፋስ ይወጣል : ወሰኑ የማይታወቅ የመፍጠር ችሎታ በተጨባጭ ተግባር ይገለጣል ::
ከዕለት ተዕለት የኑሮ ትግል በቀር ማሰብን እንደሙያ የያዙ ሰዎች ከሃይማኖት ውጪ በኢ /ያ ነበሩ ለማለት ያስቸግራል : እነዚያውም በሃይማኖት አጥር ውስጥ ሆነው የማሰብ ችሎታቸውን ያሳዩ ሰዎች - እንደ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው : ከዚያም ብኋላ እንደፈላስፋው ዘርዓያዕቆብ ያሉት -- ለስደትና ለስቃይ መዳረጋቸው : በኢት /ያ ውስጥ ማሰብ የተከለከለ ተግባር መሆኑን ነው :: ት /ቱ በተራቀቀበት በሃይማኖቱ አጥር ውስጥ ማሰብ ከተከለከለ ትምህርት በሌለበት ከሃይማኖቱ አጥር ውጪ ማሰብ ጨንግፏል ማለት ሳይሆን አይቀርም ::
ጌታቸው ስለደቂቀ እስጢፋኖስ "እበባቸውን አረጋፉት : የእንቅስቃሴያቸውን ነበልባል ውሕእ ቸልሰውበት ሳይቀጣጠል ቀረ " ሲል የደቂቀ እስጢፋኖስን ሓሳብና እምነት መዳፈን በሚገባ ይገልጠዋል :: ውጤቱ ግን በደቂቀ እስጢፋኖስ የተወሰነ አልነበረም : በአጠቃላይ በኢ /ያ የአእምሮ ነጻነት ተዳፍኖ እንዲቀርና ኢ /ያ በልጆቿ የአእምሮ ኋይል እንዳትጠቀምበት ሆኗል :: ይኽም ድኻነታችንንና ኋላቀርነታችንን ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳን ይመስለኛል :: "
Quote: እስጢፋኖሳውያን የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ነበሩ የተባሉት፥ በገድላቸው ተጽፎ እንደ ተገኘው በልዩ ልዩ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው እውነት በማፈንገጥ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ በሆኑ ትምህርቶችና ልምምዶች ሥር የወደቁ መነኮሳትንና ምእመናንን በእግዚአብሔር ቃል ለማቃናትና ለማስተካከል፥ በቃልም በሥራም ካደረጉት የለውጥ እንቅስቃሴ አንጻር ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ እንዳሉት «እነ አባ እስጢፋኖስ መለወጥን ሳይሆን መተከልን፣ መሰረትን አለመልቀቅን ነበር የሰበኩ፡፡ መጽሐፍ 'ካብ የሚያፈርስ እባብ ይነክሰዋል ' ስለሚል 'አባቶችህ የሠሩትን ሥርዐት አታፍርስ '፤ የሐዋርያትና የነቢያት (የነቢያትና የሐዋርያት ቢል በቀና ነበር ) ሥርዐት ሙሉ ሆኖ ሳለ ውሃ በላዩ የምትጨምርበት ምንድን ነው ? ከሙሉው ጽዋ ላይ ውሃ ቢጨምሩበት ይፈሳል ነበር የሚሉ፡፡» ይህ በመርሕ ደረጃ ትክክል ነው፡፡ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ በተግባር የሚታየው ግን ከዚህ በተቃራኒ ስለ ነበረ፥ መሠረታችንን አንልቀቅ፤ የለቀቅንም ወደ መሠረታችን እንመለስ ነበር የእነርሱ ተጋድሎ፡፡ በትምህርታቸው መሳጭነት የተበሳጩትና በመንፈሳዊ ኑሯቸው ማራኪነት ውስጣዊ ሰብእናቸው የተከሰሰው መነኮሳት ግን ልዩ ልዩ ስም ሰጥተው አባ እስጢፋኖስን በመጤ ሃይማኖት አቀንቃኝነት እስከ መክሰስ ደርሰው ነበር፡፡ ...
እነአባ እስጢፋኖስ “የተሐድሶ አራማጆች” የሚል ስም ተሰጣቸው ያሉት ከግማሽ ምእት ዓመት ጀምሮ ነው፤ ይሁን እንጂ ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጊዜ አንሥቶ ከሃይማኖት ማፈንገጣቸውን በሚገልጹ ስሞች፥ ለምሳሌ፡ - ፀረ ማርያም፣ ፀረ መስቀል፣ መናፍቃን፣ ወዘተ . እየተባሉ ሲጠሩ እንደ ነበረ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ቢኖሩ ኖሮ ተረኛው ስም «ተሐድሶ» ይወጣላቸው እንደ ነበረም አያጠራጥርም፡፡
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Fri Mar 16, 2012 12:50 am Post subject:
የተክለ ሃይማኖት መቃብር አጥንት ለምን ይታጠናል ?
ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሕዝባችንን ያጠፋ፣ ወንጌልን የጋረደ ግርዶሽና በበሬው ወለደ ተረት የተሞላ ሆኖ ሳለ እርሱን የጻፈ ያጻፈና የተሳለመ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጻፍለት ይናገራል። በዚህ ሐሰተኛ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያናችን ምመናን ወንጌልን ትተው እርሱን በማሰራጨት ሥጋውና ደሙን በመቀበል ፋንታ የደብረ ሊባኖስን ፍርፋሪ በመብላት፤ ንስሐ በመግባት ፈንታ በደብረ ሊባኖስ በመቀበር ለመጽደቅ ከንቱ ተስፋ ይዘው ይገኛሉ። ስለዚህ መጽሐፉ የሐሰት አባት ዲያብሎስ የሸረበው ተንኮል መሆኑን ለሕዝባችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን። በጣም የሚያሳዝነው ግን በክርስቶስ ያመኑ ወንጌልን ተምረው ለሕዝባቸው ለማስተማር ደፋ ቀና የሚሉ መምህራን ይህን የሐሰት ድርሰት ባለመቀበላቸው በቤተ ክህነት አደገኛ ፖለቲከኞች መናፍቃን እየተባሉ መሰደዳቸው ነው። ክርስቲያን ለመባል የሚያበቃ የገድለ ተክለ ሃይማኖትን ተረት ማመን ወይስ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ማመንና በርሱ መኖር ? ይህ መጽሐፍ የወንጌልን ቦታ እስኪለቅ ድረስ በውስጡ የያየዘውን ባዶ ተረት እናሳያለን።
የተክለ ሃይማኖት መቃብር በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደሚገኝ ሁላችንም እናውቃለን። አንጥቱ ግን ግንቦት አሥራ ሁለት ቀን ካምሳ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ወጥቶ አምልኮ በሚደረግበት ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደተቀመጠ ይታወቃል። በየጊዜውም እጣን ይታጠናል። ለምን ይሆን ? በጸሎት ብዛት ተቆረጠች የተባለችው እግር ግን የግል ቤት ተሠርቶላት በዚያ ትኖርላች ይባላል። ሌላው ታሪክ ደግሞ ክንፍ አውጥታ አርጋለች ስለሚል ከተክለ ሃይማኖት ስእል ጋር ክንፍ ያወጣች እግር አብራ ተስላ ትታያለች። ተክልዬ ክንፍ ያላወጣ አካል ያላቸው አይመስለኝም። ሆኖም የተክለ ሃይማኖት እግር አለች በሚባለው ቤት የተክለ ሃይማኖት በዓል ሲሆን በሕዝብ ተጨናንቃ በዓይናችን አይተናል፤ እግሪቱን ለማየት ሞክረን ግን ሳናያት ቀረን።
ወደ ነገራችን እንመለስና የተክለ ሃይማኖት መቃብር የሚገኘው መንግሥተ ሰማያት ባለችበት አቅጣጫ ነው ተብሏል። ታሪኩ የሚጀምረው ሃምሳ ዘጠነኛው ምራፍ ላይ ነው። አምደ መስቀል የተባለ የተክለ ሃይማኖት የእሕት ልጅ በድንገት ሞተ ይለናል። መነኮሳቱ ፍታት ፈተው ሊቀብሩት ሲሞክሩ በድኑ ተንቀሳቀሰ መነኮሳቱ ምን ሆንክ ቢሉት እንደምታዩት ሞትኩ መላእክትም ወደ ተክለ ሃይሞት ቤት ወሰዱኝ፤ በዚያ ተክለ ሃይማኖትን አየሁት አክሊሉ ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበራል፤ ክብሩን ልናገረው አልችልም አላቸው ይላል። ተክለ ሃይምኖትም አምደ መስቀልን ከመንግሥተ ሰማያት ወደ ደብረ ሊባኖስ እንዲመለስ አዘዘው የሚከተለውንም መልእክት ነገረው «ኤልሳ ወደኔ ይምጣ ፊልጶስ በመንበሬ ይቀመጥ .. መታሰቢያየን እንዲያደርጉ ለሚመጣው ትውልድ ንገሩ ዳግመኛም ይህ የምታየው አዳራሽ በመቃብሬ ላይ ነው፤ ጌታየ እስኪመጣ ድረስ እንዲሁ ይኖራል ይህንንም ለሚመጣው ትውልድ ነገሩ» ገድለ ተ ሃይማኖት ምዕራፍ 59፤ 4-6።
ኤልሳእ ተክለ ሃይማኖት ሲሞቱ በርሳቸው የተተካው የገዳሙ አስተዳዳሪ ሲሆን ፊልጶስ የተባለው ደግሞ አባ ኤልሳን አስወግዶ እጨጌ የሆነው የተክለ ሃይማኖት ዘመድ ነው። የገዳም ስልጣንም አስገራሚ የፖለቲካ ድራማ ይታይባታል። ይህ አምደ መስቀል ሞቶ ተክለ ሃይማኖት ካለበት ከደረሰ በኋላ እንደገና በተክለ ሃይማኖት ታዝዞ ነው ከሞት ተነሥቶ ይህን መልክት ያደረሰው። ታሪኩን ስንመረምረው ከተክለ ሃይማኖት ጋር ሥጋዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዝምድና ያላቸው ሰዎች ማድረግ የሚፈልጉትን ለማድረግ ተክለ ሃይማኖት ነገረን ለማለት የፈጠሩት ዘዴ እንጂ የተክለ ሃይማኖት ነፍስ ሙታንን የምታስነሳ ሆና አይደለም። በመጀምሪያ ገድሉ ተክለ ሃይማኖት 25ኛ ኪሩብ ሆነው በጽርሃ አርያም የጌታን መንበር እያጠኑ ይኖራሉ ብሎን ነበር። አሁን ደግሞ በነፍሳቸው በመንግሥተ ሰማያት በደብረ ሊባኖስ መቃብራቸው አቅጣጫ እንደሚገኙ ይነግረናል። እኒህ ሰው በሁሉም ይገኛሉ ማለት ነው ?። አንድ የእግዚአብሔር ሰው «መታሰቢያየን አድርጉ ለሚመጣውም ትውልድ ንገሩ» ብሎ እንዴት ሊያስተምር ይችላል ? ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያቸው እንዲደረግላቸው ዝናቸው ለሚመጣው ትውልድ እንዲነግራላቸው የፈለጉት ለምን ይሆን ? መታሰቢያቸው ቢደረግስ ለምን ይጠቅማቸዋል ? መታሰቢያ ባማርኛ ሲሆን በግዝ ተዝካር ይባላል። ተዝካር ለሙታን የሚደረገው ነፍሳትን ለማጽደቅ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች የቅዱሳን እውነተኛ ታሪኮች ከማናውቃቸው መታሰቢያ እንዲደርግላቸው ታሪካቸው ለትውልድ እንዲነግርላቸው ያስተማሩ ቅዱሳን የሉም። የተክለየ አዋጅ ግን ጥያቄ ያስነሳል። አጥንታቸውና መቃብራቸው የሚታጠነው በዚህ አዋጅ ምክንያት ነው ብለን እንድናስብ ያደርገናል። ከሞት ከተነሳው ካምደ መስቀል መልክት በኋላ እጨጌ ፊልጶስ ስለ ተክለ ሃይማኖት መቃብር የሚከተለውን አሳፋሪ አዋጅ አወጁ
«ወበእንተዝ ተሠራ ከመ ይጥእኑ መቃብረ አቡሆሙ በበዕብሬቶሙ ወይግበሩ ተዝካሮ በፍቅር ተጋቢኦሙ እምበሐውርቲሆሙ»
ትርጉም «ስለዚህም በየተራቸው ያባታቸውን መቃብር እንዲያጥኑ ከየሀገራቸውም ተሰብስበው በፍቅር መታሰቢያውን እንዲያደርጉ ሥራት ተሠራ» ምዕራፍ 59፤ 10 ተክለ ሃይማኖትን ማምለክ የተጀመረው ከዚህ አሳዛኝና አሳፋሪ አዋጅ ጀምሮ ነው። አምደ መስቀል መታሰቢያየን አድርጉ ብለዋል ብሎ መልክት ሲያመጣ እነጨጌ ፊልጶስ የተረዱት አምልኮን ነው። የተከለ ሃይማኖት መቃብር በመንግሥተ ሰማያት ሥር ነው የተባለውም መቃብሩን ለማስመለክ ሆን ተብሎ የተሸረበ ተንኮል ነው።
እጣን በመጽሐፍ ቅዱስ በአምልኮ ጊዜ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ መስዋእት ነው ዘሌ 16፤ 13። እሥራኤላውያን የነቢያቶቻቸውን መቃብር ያስጌጡ ነበር ማቴ 23፤ 29። እጣን ለመቃብራቸው ያጥኑ እንደነበር ግን አልተጻፈም። ታዲያ የተክለ ሃይማኖት መቃብር ለምን ይታጠናል ? ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን ? ለስእል ማጠን የተጀመረውም መቃብርን ማጠን ከተጀመረ ጀምሮ ሳይሆን አይቀርም። በቤተ መቅደሳችን ውስጥ ያሉ ስእሎች ሁሉ በቅዳሴና በኪዳን ጊዜ ይታጠናሉ። የጌታ የመቤታችን የመላእክት የተክለ ሃይማኖት የገብረ ማንፈስ ቅዱስ ሰው ከመርካቶ ገዝቶ እያመጣ ያንጠለጠለው ስእል (የሰው እጅ ሥራ ) ሁሉ ይታጠናል። ስእል ለትምህርት የተሠራ እንጂ ለአምልኮ የተሠራ አይደለም ግን ለምን ይታጠናል ? እጣን ማጠን አምልኮ ከሆነ ስእሎችን ስናጥንስ እያመለክን አይደለምን ? የተክለ ሃይማኖት አጥንት ዛሬም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በየጊዜው ይታጠናል። ለምን ? እንዲህ ዓይነቱ ባዕድ ነገር በጌታችን በሐዋርያቱና በሊቃውንቱ ከተገለጠው እውነተኛ የክርስትና ሃይማኖት የወጣ ስለሆነ ሊወገድ ይገባዋል። የቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት መሪዎችስ ስላስተዳደር ስለገንዘብ ስለ ሹመት ስለፖለቲካ በመካሰስ ጊዜያቸውን ከማባከን እንደጥንቶቹ የእሥራኤል ነገሥታት ቤተ መቅደሱን ቢያጸዱ አይሻልም ? እንደዚህ ዓይነቱን ነውር ከመካከላችን ሳናስውግድ መግባባት እንችላለንን ? 2ኛ ዜና 29፤ 1-24።
ይድረስ ለሊቃውንት ጉባኤ
ሊቅነታችሁ ለማን ነው ? ለሕዝቡ ለእግዚአብሔር ወይስ ለኑራችሁ ? እኛና እናንተ ፊት ለፊት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረናል፤ እናንተም ይህ ከዚህ በላይ ያየነው ስሕተት መሆኑን ታውቃላችሁ። ሁሉም ጳጳሳት እንዲሁም ብዙ ካህናት ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያችንን እንደበከለና ለእርምጃዋ እንቅፋት እንደሆነ ያውቃሉ። የኛ ጥያቄ ሕዝቡ በስሕተት ትምህርት እንዲህ እየተጎዳ ለምን ዝም እንላለን ነው ? ለምን አይታረምም ? እኛ ይህን ጉዳይ ባደባባይ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ለመግለጥ የተገደድነው ሁላችሁም ስሕተት መሆኑን እያወቃችሁ ዝም በማለታችሁና እንዲያውም እኛን የተሳሳቱ ናቸው በማለት ክሳችሁን ባደባባይ በማቅረባችሁ ነው። እባካችሁ ወደ እውነት እንመለስ እውነቱን አስተምረን እንሰደድ ለሕዝባችን እንራራለት ምድራዊው ኑራችን የሰማይ መኖሪያችችንን የሚያዘጋጅ ነውና ለሰማዩ እንሥራ።
ተስፋ ነኝ _________________ I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የተሞናሞነው Joined: 11 May 2011 Posts: 1126
Posted: Fri Mar 16, 2012 1:03 am Post subject:
ከራስህ የሆነ ነገር የማታመነጨው በኮፒ ፔስት ዋርካን የሞላሀት ሉጢው ጠዋር ... ይህንን ኮፒ ፔስትህን ዋርካ ጄኔራል ላይ ለቅልቅ ይህ የፖለቲካ ቤት ነው ተባልክ እኮ ...አይገባህም እንዴ ድንጋይ ራስ ...ጉግል ስታደርግ ከምትውል ምናለ ከረከሰው አናትህ ውስጥስ የራስህ የሆነ ነገር ለማፍለቅ ብትሞክር ....ድንፈፍ ....እዚህ ደግመህ ኮፒ ፔስትህን እንዳላይ ...ሉጢ
ልጅ ሞንሟናው _________________http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሚስተር -x Joined: 02 Feb 2009 Posts: 1257
Posted: Fri Mar 16, 2012 3:18 am Post subject:
ከቁም ነገሩ ባሻገር
Historical timeline of the development of modern weapons starting at 1364 with the first recorded use of a firearm.
.በገጽ 24 ላይ አጼ ያግብአ ጽዮን በ 1278-1286 ለማርያምና ለመስቀል ያልሰገደ ... ከጠመንጃዬ አፎት ለምትወጣ እሳት እሳት ይዳረጋል ብሎ አስፈራራ ይለናል ::
??
የገባው ቢያስረዳኝ :: ኢትዮጵያ ውስጥ ጠብመንጃ ነበር በዚያ ዘመን ? _________________ እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፀዋር Joined: 16 Feb 2010 Posts: 488
Posted: Wed Mar 21, 2012 5:10 pm Post subject:
"እኔም ለሰዎች ክርስቲያን እመስላቸው ነበር :: ነገር ግን በልቤ እርሱ እንዳስታወቀን የሁሉ ፈጣሪና የሁሉ ጠባቂ በሆነ በእ /ር ካልሆነ በስተቀር በማንም አላምንም :: አማኝ ሳልሆን አማኝ እመስላለው :: በእ /ር ዘንድ ይህ ያስቀጣኝ ይሆን ?"
"ከሞቴ ብኋላ አዋቂና መርማሪ ሰው ቢገኝ ግን በሀሳቤ ላይ ሀሳቡን እንዲጨምርበት እለምነዋለሁ ::... የሀገራችን ሰዎች በእ /ር ረድኤት አዋቂዎች እንዲሆኑ : እውነትንም ወደ ማወቅ እንዲደርሱ : ሐሰትን እንዳይፈልጓትና አመጻንም ተስፋ አድርገው ዝም ብለው ከከንቱ ወደ ከንቱ እንዳይሄዱ : እውነትን እንዲያውቁና ወንድሞቻቸውን እንዲወዱ : እንግዲህ እስካሁን እንደሚያደርጉት በከንቱ በሀይማኖታቸው እንዳይጣሉ - እኔ የጀመርኩትን አንተ ጨርሰው ... :: "
ፈላስፋው ዘርዓያቆብ ... 1660 ዓ .ም .