WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ለውጥ ያስፈልጋል :?: ከለውጥ በፊት የለውጥ እንቅፋት የወገድ !!
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Thu Jan 05, 2012 9:07 pm    Post subject: Reply with quote

ነፍሱን ይማረውና የተስፋዬ ካሣን ቀልድ አስታወስከኝ :: ሴትዮዋ ገበያ ደርሰው ወደቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ መንገድ ላይ አንድ እብድ ይገጥማቸውና አንዳንድ ነገር ይቀልድባቸዋል :: የኑሮ ውድነቱ ሊያሳብዳቸው የደረሰ እናት : ቀልዱ ያለ ጊዜው የተቀለደ ነበርና : "አንተ ምን አለብህ ወዳጄ በደህና ጊዜ አብደሀል " Laughing

ወዳጄ ዘእግዚነም ጊዮርጊስ ፈረሰኛው የአድዋ ጦርነት ላይ ተካፍሎ ነበር የምትል ሰው ስለ ክርስቶስ ሠምራ ውሸት ምን እንድትለኝ እጠብቃለሁ ?

ህሊና ላለው ሰው ግን ይህ ገድል ለራሱ ይናገራል :: ምንም ትንታኔ አያስፈልገውም :: ተጨማሪ ካስፈለገህ ወደ ብኋላ ብቅ እላለሁ ::

ሠላም

ዘእግዚነ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ጸዋር :

ስላስነበብከን የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ታምር እናመሰግናለን ::

ሆኖም አንድ ነገር አልነገርከንም :: የቱ ስህተት የትኛው እውነት እንደሆነ አላሳየከንም :: ስህተትና እውነት ለማለት ደግሞ መመዘኛ ያሰፈልገዋል እና በምን መዘኛ መሰረት ስህተት እና እውነት ሊሆን እንደሚችል እስኪ በዚያው ንገረን ::

በነገራችን ላይ አንዳንድ ገድላት ችግር ሊኖርባቸው እንደሚችል ቢገመትም አንተም ሆነ አንተ መሰረት ያደረግሀቸው ሰዎች እንደሚሉት ግን አይደለም ::

እኔ የምጠይቅህ ጽንፈኛ ስለሆንሁ ወይም እንዳትጽፍ ስለፈለግሁ ሳይሆን በዚህ ዙሪያ ሌሎች የጻፉትን በማምጣት የገደል ማሚቶ ከመሆን ውጭ አንዳች የሚረባ ነገር እንደማትናገር /እንደማትጽፍ ስለማውቅ ነው :: እና ከቻልክ በሌላ ርእስ ብትጽፍ የተሻለ እንደሆነ እመክርሀለሁ ::

ሰላም ሁን !
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
እነ ቆቁ (ፈላስፋውና ሳይካትሪስቱ Laughing ) ጥብቅና ከቆሙላቸው ገድላት የክርስቶስ ሠምራ ገድል ምን እንደሚል እንመልከት :: ይህ ገድል እልም ባለ የደካሞች ፈጠራ በወሸት የታጨቀ ገድል ለመሆኑ የሚከራከር ካለ አንድ በአንድ ውሸቶቹን እየጻፍኩ እልሁን ለማስጨረስ ቃል እገባለሁ :: ለጊዜው ከመነሻው ለወርሀ መስከረም ታስቦ በተጻፈው ገድል እንጀምር ::"አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነን በወርሃ መስከረም የሚነበብ የሚጸለይ የእናታችን የብጽዕት ክርስቶስ ሠምራን ገድል ለመጻፍ እንጀምራለን :: በረከተ ጸሎቷ ወሀብተ ረድኤቷ ይሃሉ ምስሌነ ለዓለም ዓለም አሜን ::

ከዕለታት ከአንደኛይቱ ቀን ያደረገችውን ተአምር ልንገራችሁ ስሙ :: ከአገልጋዮቿ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች :: ከዕለታት በአንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት :: ያም የእሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉሮሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት :: በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደ ሌላ ክፍል ወሰዱት :: በፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ በክርስቲያንነቴ ላይ የካህን ሚስት ስሆን ነፍሰ ገዳይ ሆኛለሁና :: ሰውስ ምንይለኛል : ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ : ከእንግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሽጋት እችላለሁ : እያለች አለቀሰች :: ከዚህ ብኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር በፅዓት አደረገች : አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋሕደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ያለኝን ገንዘብና ሃብቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተልሃለሁ ::
አንተን ከመከተል ከቶ ወደ ኋላ አልልም :: ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም : ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም :: አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ :: እንግዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በሃዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች ብኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች :: ከዚህ ብኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ሓይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ አሏት :: በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና በሕይወት አገኘቻት : ከዚያም …”

ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ወርሃ መስከረም የሚነበብ 35-48.

"ዳግመኛ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሰምራን የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሰማይ አሳርጎ ከፈጣሪዋ ፊት አቆማት ጌታም በየዕለቱ 3 ነፍሳት ከሲኦል እንድታወጣ ስልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ገባላት :: በዚያን ጊዜ አቤቱ ጌታዬ የቅዱሳን ገድል ሲነበብ ሀሰት ነው በማለት የማያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን ትምራቸዋለህ ወይስ አትምራቸውም አለችው :: እሱም "በጥቡዕ " ልብ ሆነው ያለመጠራጠር የሚያምኑት ወደ መንግስቴ ይገባሉ የማያምኑ ቢኖሩ ግን ክፍላቸው ከነ አርዮስና ሰባልዮስ ጋር ነው አላት ::"
ይህ ደግሞ ጥቅምት ላይ ከሚነበበው ገድሏ የተወሰደ ነው ::

የዘመናችን ፈላስፋዎች "የክርስቶስን መንግስት " ለመወረስ "በጥቡዕ " ልብ ማመንን ተቀብለው ለውሸት ጥብቅና ይቆማሉ እንጂ ስለሚያመልኩት ለመመራመርም ሆነ በምክንያታዊ ትንታኔ ለማስረዳት አቅሙም ፍላጎቱም የላቸውም :: ታድያ ማን ይሆን ሳይካትሪስት የሚያስፈልገው Question

ሠላም

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 6:55 pm    Post subject: Reply with quote

ጸዋር እምነትህ ምንድነው ?

ፈላስፋው እና ሳይካትሪስቱ ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 7:37 pm    Post subject: Reply with quote

"የኔ ሀይማኖት ህይወት ነው ".... በዓሉ ግርማ (ኦሮማይ ) Cool Wink

ቆቁ እንደጻፈ(ች)ው:
ጸዋር እምነትህ ምንድነው ?

ፈላስፋው እና ሳይካትሪስቱ ቆቁ

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 7:54 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
"የኔ ሀይማኖት ህይወት ነው ".... በዓሉ ግርማ (ኦሮማይ ) Cool :win

ምነው እምነትህን ለመግለፅ ይህን ያህል ምጥ አስፈለገህ ? አሁንም ግልፅ አላደረክልንም በመፅሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር እንደማታምን ሌላ ማስረጃ እነሆ :-

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ ():

Quote:
እርስ በእርሱ የሚቃረነው ምንድነው ?ውጊያ ላይ የተሳተፉ ሁሉ ቅዱሳን አይደሉም ካልክ እግዚአብሄር ራሱ እነ ንጉሥ ዳዊትን እንዲዋጉ ያዝ አልነበረም ወይ ?ፀዋር እንደፃፈው :-

Quote:
ወንድሜ እኔ ሰውን ጻድቅ /ቅዱስ የማድረግ ስልጣን የለኝም :: ምናልባት አንተ የጦር ጄነራል ሁላ ጻድቅ የማድረግ ስልጣን ተሰጥቶህ ሊሆን ይችላል Laughing Laughing Laughing እኔ ጥያቄ ነው ያቀረብኩት :: ጻድቃን /ቅዱሳን እንዴት ጦርነት ላይ ይሳተፋሉ Question እንዴት እግዚአብሔር ቅዱሳንን እንዲዋጉ ያዛል Question

/ ዳዊትን እንዲዋጋ አዘዘው :: ከእስራኤል የተመረጠ ነገድ ቆሞ ሌላውን ጨፈጨፈው :: በውሀ በላቸው :: በእሳት ፈጃቸው :: አንቀጠቀጣቸው :: ዘላለማዊ ሞት ሞቱ :: የገሀነም እሳት ለበለባቸው :: ቅብጥርስ የሚለው እምነት እኮ ያንተ እምነት ነው :: የኔ አይደለም :: እኔ እየጠየቅኩህ ነው ያለሁት ::

ሁሉን ቻይ የፍቅር አምላክ እንዴት ጦረኛ ሊሆን ይችላል Question

ህይወትና ሞትን ; ጊዜና ቦታን ; አተምና ህዋን ; ነፍሳትና ከዋክብትን ; ህያውና ግዑዝ ነገርን ሁሉ የፈጠረ ተአምራዊው ሀይል ; እንዴት ሰዋዊ ባህሪ ተሰጥቶት ክገዛ ራሱ ፍጡራን ጋር ካንዱ ወግኖ አንዱን ወገን ሲወጋ ይኖራል Question

_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 8:08 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:

ወዳጄ ዘእግዚነም ጊዮርጊስ ፈረሰኛው የአድዋ ጦርነት ላይ ተካፍሎ ነበር የምትል ሰው ስለ ክርስቶስ ሠምራ ውሸት ምን እንድትለኝ እጠብቃለሁ ?
ዋርካ ጄኔራል ላይ የዛሬ 9 ወር ገደማ እኔ በከፈትኩት ርእስ ላይ ዘእግዚነ ያለው እንዲህ ነበር

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ ():

Quote:
ወደ አድዋ ጦርነትና የጊዮርጊስ ተሳትፎ ስንመለስም እኔ ይህን ጉዳይ ያነሳሁት የጣሊያን ወታደሮች ራሳቸው ምስክርነት ሰጥተዋል ሲባል ስለሰማሁ ምናልባት እዚህ ዋርካ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ የሚችል ሰው ሊኖር ይችላል በሚል ተስፋ ነው ::

ዘእግዚነ እንደፃፈው :-

Quote:
ሰላም ዘርአይ ደረስ :

በጊዜው ሊያወያይ የሚችል ጥያቄ ነው ያቀረብከው ሆኖም መልስ የሰጠ የለም እኔም አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ከመስማቴ ውጭ በቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ወይም ከታላላቅ አባቶች ሲነገር አልሰማሁም ለዚህ ነው አፌን ሞልቸ መናገር ያልቻልሁት ::

ከታች ያያዝሁት ሊንክ ስለዚህ በጥቂቱ ይናገራል ::

http://www.britishmuseum.org/explore/highlights/highlight_objects/aoa/b/the_battle_of_adwa,_painting.aspx
_________________

_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 9:16 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ዘርዐይ ደረስ

የምን ምጥ አመጣህ ወዳጄ :: አካሄዳችሁ ስለገባኝ በዚህ አምድ መናገር ስላልፈልግኩ እንጂ ስለማምንበት ለመናገር ምንም ምጥ የሚያስይዝ ነገር የለውም :: ሆኖም በዚህ አምድ ላይ የኔ ትኩረት በኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስር የሰደደውን ውሸት ማጋለጥ ነው :: ለዚህም የገፋፋችሁኝ ራሳችሁ ናችሁ :: አላስፈላጊ የሆኑትን ልማዶች : ትብታቦችና ትውፊቶችን ለማንሳት ሞክሩ : ሪፎርም ቢጤ ያስፈልጋችኋል እያልኩ በየአጋጣሚው ቅንነት የተሞላውን አስተያየቴን ስሰጥ : የናንተ መልስ የተለመደው ዘለፋ ነበር :: በሰለጠነ መንገድ የሰውን ሀሳብ ማስተናገድ እንኳን አልፈለጋችሁም ::ስለዚህ ለለየለየት ውሸት ራሱን የሚያስገዛና ለጣዖት ሲሰግድ የሚኖር ሰው : ቀና መንፈስ የተላበሰ ሀሳብን ከማስተናገድ ይልቅ በመናፍቅነት እየፈረጀ የሰውን ልብ ሲያደርቅ : ሀቁን ወደ አደባባይ አውጥቶ ማሳየት እንደሚገባ አምናለሁ :: ከዛ ብኋላ እምነቱን (ውሸትን ) መከላከል የሚችል ይከላከላል Laughing ሽምጥጥ አድርጎ የሚክድም ይክዳል Laughing አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ደግሞ ይወስዳል ማለት ነው ::

እናም ይህን ተረድተህ እምነትህን በተመለከተ እየተጋለጠ ያለውን ውሸት እንደሚሆን ተከራከረህ ለመከላከል ሞክር እንጂ የኔ እምነት ምንም ይሁን ምን ፋይዳ አይኖረውም ::

ሠላምዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
"የኔ ሀይማኖት ህይወት ነው ".... በዓሉ ግርማ (ኦሮማይ ) Cool :win

ምነው እምነትህን ለመግለፅ ይህን ያህል ምጥ አስፈለገህ ? አሁንም ግልፅ አላደረክልንም በመፅሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር እንደማታምን ሌላ ማስረጃ እነሆ :-

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ ():

Quote:
እርስ በእርሱ የሚቃረነው ምንድነው ?ውጊያ ላይ የተሳተፉ ሁሉ ቅዱሳን አይደሉም ካልክ እግዚአብሄር ራሱ እነ ንጉሥ ዳዊትን እንዲዋጉ ያዝ አልነበረም ወይ ?ፀዋር እንደፃፈው :-

Quote:
ወንድሜ እኔ ሰውን ጻድቅ /ቅዱስ የማድረግ ስልጣን የለኝም :: ምናልባት አንተ የጦር ጄነራል ሁላ ጻድቅ የማድረግ ስልጣን ተሰጥቶህ ሊሆን ይችላል Laughing Laughing Laughing እኔ ጥያቄ ነው ያቀረብኩት :: ጻድቃን /ቅዱሳን እንዴት ጦርነት ላይ ይሳተፋሉ Question እንዴት እግዚአብሔር ቅዱሳንን እንዲዋጉ ያዛል Question

/ ዳዊትን እንዲዋጋ አዘዘው :: ከእስራኤል የተመረጠ ነገድ ቆሞ ሌላውን ጨፈጨፈው :: በውሀ በላቸው :: በእሳት ፈጃቸው :: አንቀጠቀጣቸው :: ዘላለማዊ ሞት ሞቱ :: የገሀነም እሳት ለበለባቸው :: ቅብጥርስ የሚለው እምነት እኮ ያንተ እምነት ነው :: የኔ አይደለም :: እኔ እየጠየቅኩህ ነው ያለሁት ::

ሁሉን ቻይ የፍቅር አምላክ እንዴት ጦረኛ ሊሆን ይችላል Question

ህይወትና ሞትን ; ጊዜና ቦታን ; አተምና ህዋን ; ነፍሳትና ከዋክብትን ; ህያውና ግዑዝ ነገርን ሁሉ የፈጠረ ተአምራዊው ሀይል ; እንዴት ሰዋዊ ባህሪ ተሰጥቶት ክገዛ ራሱ ፍጡራን ጋር ካንዱ ወግኖ አንዱን ወገን ሲወጋ ይኖራል Question

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Jan 06, 2012 10:22 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት በጉልበት (በህግ ) ተግባራዊ ሆነው ፀንተው እንዲቀሩ የተደረጉ አንዳንድ ልማዶችን እናያለን ::

ሀይማኖትን ለመመስረት በኋይል ተጠቀመ

ዘርዓ ያዕቆብ ብርቱ ተዋጊ ከመሆኑም በላይ የክርስትና ሀይማኖት በመላ ኢትዮጵያ እንዲመሠረተና እንዲከበር : አረመኔነትም ተወግዶ እንዲቀር ብዙ ጥረት አድርጎአል :: ሰው ሁሉ ደግሞ እንደ ፈቃዱ እንዲሰራ በሀይል ከመጠቀም አልተመለሰም :: የማይታዘዙለት ቢኖሩ በሀይል ይቀጣቸዋል ::

ለምሳሌ የምንግስቱ ዜጋ ሁሉ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ የሚሉ ቃላት ያሉበትን ክታብ በግንባሩ እንዲሸከም ይሁን : ... የሚል አዋጅ አሳወጀ ::

እንደፈቃዱ ያላደረገ ይቀጣ ነበር :: ይህንን አዋጅ ሰዎችም ቂም መወጣጫ አድርገውት እንደነበረ ተዘክሯል :: እገሌ የንጉስን ትእዛዝ አላከበረም በማለት የሀሰትን ክስ በማበጀት ጥፋት ሳይኖርበት በሞት እንዲቀጣ ይደረግ ነበር ::

ሰለ በዓላትና ስለ ክርስትና ትምህርት ያሳወጀው አዋጅ

የቤተ ክርስቲያን በዓላት ተከብረው እንዲውሉ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ :: እሑድ ብቻ ሳይሆን ቅዳሜም እንደሰንበት ተቆጥሮ እንዲከበር ወሰነ :: ሰላሳ ሶስቱ የማርያም በዓላት : በየወሩም የሚከበረው የሚካእል በዓል : እንዲህውም የክርስቶስ ስደት በዓል በሚገባ ተከብረው እንዲውሉ ለህዝበ ክርስቲያኑ አዋጅ አስነገረ :: የቤተ ክርስቲያኒቱም ደጅ ደግሞ ወንዶችም ሴቶችም ቅዳሜ ቅዳሜ እየተሰበሰቡ ቄሶች የሀይማኖትን ትምህርት እንዲማሩ አዘዛቸው :: ቄሱም በበኩሉ ትዕዛዙ እንዲፈጸም የማድረግ ግዴታ ነበረበት ::

የማርያምና የመስቀል ስግደት
በዚህ አምልኮ ውስጥ ልዩ ልዩ አይነት ስግደት አለ :: ለምሳሌ የአለም ፈጣሪና የመድሀኒታችን እናት ናትና ክርስቲያን ሁሉ ለማርያም ስግደት ማድረግ አለበት የሚል አዋጅ አስነግሮ : በቤተ ክርስቲያን እንዲለመድ አስደርጎአል :: ስግደቱ ለሁሉም እንደግዳጅ የተቆጠረ ነበረ ::

እንዲውም ደግሞ የመድሀኒታችን የመሞቱ ምልክትና መታሰቢያ ነውና ክርስቲያን ሁሉ ለመስቀል መስገድ አለበት የሚለው አዋጁ በቤተ ክርስቲያን ተቀባይነትን አግኝቶ በክርስቲያኖች መካከል ትክክልኛ ነው ተብሎ ተለመደ ::

ሌላም ዓይነት ስግደትና ስን -ምግባር

ሌላው ተመሳሳይ ልዩ ልዩ ዓይነት ስግደትና አክብሮት በምዕመናንን ዘንድ እየተለመደ ስልሄደ በዘምን ብዛት እንደ ህግና ደንብ እስከመቆጠር ደረስ ::

የንጉሱን አዋጅ ተከትሎ ለማርያም ብቻ ሳይሆን ለልዩ ልዩ ቅዱሳንና ለመላእክትም ስግደት ማድረግ ተለመደ :: ለንጉስም ስግደት ማድረግ ተገቢ ነው የተባለበት ጊዜ ነበር :: በደጀ ሰላሙ መሳለም እንደመልካም ምግባር ተቆጠረ :: ቅዱሳን የተባሉትንም ስፍራዎች መጎብኘትና ከዚያም ስግደት ማድረግ እንደ ትልቅ ነገር የሚቆጠር ሆነ :: በአዋጅ Exclamation Rolling Eyes

የቤተክርስቲያን ታሪክ : በመካከለኛው ዘመን ከተሰኘው መጽሀፍ የተቀነጨበ (አንዳንዶቹን ሀተታዎች አሳጥሬያቸዋለሁ )

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘእግዚነ

ዋና ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 609
Location: I am here

PostPosted: Sat Jan 07, 2012 10:40 am    Post subject: Reply with quote

ዘርአይ ደረስ :

ስለምልከታው በጣም አመሰግናለሁ :: እኔ የጻፍሁትንና ጸዋር የጻፈውን በግልጽ አስቀምጠከዋል ::

ሰላም ጸዋር :

አሁንም ደጋግመህ መጽፍህን የሚቃወም ያለ አይመስለኝም :: ብቻ የገደል ማሚቶ አትሁን ::ይህንን ጽሁፍ የጻፉት ሰዎች የሚያምኑትን አምላክ አታምንም :: ስለዚህም ከአንተ እንደሰማነው ውሽት የሆነው ከኦርቶዶክስ አምላክ /ከመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ / ጀምሮ ስለሆነ ከዚያ ጀምረህ ብትነግረን ወይንም ደግሞ ከራስህ ጽፈህ ብታሳየን የሚል ነው :: በተረፈ ዘእግዚነም ሆነ ሌሎች ተሳታፊዎች እንዳትጽፍ ሳይሆን እንዳትጎዳ ስለሚያዝኑልህ እና መንገድህን እንድታስተካክል ለማድረግ እንጅ አንከለክልህም ::ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:

ወዳጄ ዘእግዚነም ጊዮርጊስ ፈረሰኛው የአድዋ ጦርነት ላይ ተካፍሎ ነበር የምትል ሰው ስለ ክርስቶስ ሠምራ ውሸት ምን እንድትለኝ እጠብቃለሁ ?
ዋርካ ጄኔራል ላይ የዛሬ 9 ወር ገደማ እኔ በከፈትኩት ርእስ ላይ ዘእግዚነ ያለው እንዲህ ነበር

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ ():

Quote:
ወደ አድዋ ጦርነትና የጊዮርጊስ ተሳትፎ ስንመለስም እኔ ይህን ጉዳይ ያነሳሁት የጣሊያን ወታደሮች ራሳቸው ምስክርነት ሰጥተዋል ሲባል ስለሰማሁ ምናልባት እዚህ ዋርካ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ የሚችል ሰው ሊኖር ይችላል በሚል ተስፋ ነው ::

ዘእግዚነ እንደፃፈው :-

Quote:
ሰላም ዘርአይ ደረስ :

በጊዜው ሊያወያይ የሚችል ጥያቄ ነው ያቀረብከው ሆኖም መልስ የሰጠ የለም እኔም አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ከመስማቴ ውጭ በቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ወይም ከታላላቅ አባቶች ሲነገር አልሰማሁም ለዚህ ነው አፌን ሞልቸ መናገር ያልቻልሁት ::

ከታች ያያዝሁት ሊንክ ስለዚህ በጥቂቱ ይናገራል ::

http://www.britishmuseum.org/explore/highlights/highlight_objects/aoa/b/the_battle_of_adwa,_painting.aspx
_________________

_________________
በህይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ
ለእኔ በወንጌል ማመኔ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sat Jan 07, 2012 7:22 pm    Post subject: Reply with quote

ዘእግዚነ እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም ጸዋር :

አሁንም ደጋግመህ መጽፍህን የሚቃወም ያለ አይመስለኝም :: ብቻ የገደል ማሚቶ አትሁን ::

ሠላም ዘእግዚነ

ግድየለህም አትናደድ :: የምታምንበትን ነው የጻፍኩት እንጂ የማታምንበትን አይደለም Laughing

ዋርካ ላይ በጣም የሚገርም "ህዝበ ክርስቲያን " እንዳለ ነው የተረዳሁት :: አንገቱን ለሠይፍ የሚሰጠው "የተዋህዶ ልጅ " ምነው አሁን እምነቱን አይታደጋትምሣ Question እውቀት አነሶት ይሆን Question

ስለሚጋለጡት ውሸቶችና የልጆች ተረት ተረቶች አንድም አስተያየት ሳትሰጡ እምነታችሁ እኔ ይመስል ስለኔ ታወራላችሁ እንዴ Laughing ይገርማ እኮ Rolling Eyes

እናንተም ቀጥሉ እኔም እቀጥላለሁ ::

ሠላም
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jan 07, 2012 10:02 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ዘርዐይ ደረስ

የምን ምጥ አመጣህ ወዳጄ :: አካሄዳችሁ ስለገባኝ በዚህ አምድ መናገር ስላልፈልግኩ እንጂ ስለማምንበት ለመናገር ምንም ምጥ የሚያስይዝ ነገር የለውም :: ሆኖም በዚህ አምድ ላይ የኔ ትኩረት በኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስር የሰደደውን ውሸት ማጋለጥ ነው :: ለዚህም የገፋፋችሁኝ ራሳችሁ ናችሁ :: አላስፈላጊ የሆኑትን ልማዶች : ትብታቦችና ትውፊቶችን ለማንሳት ሞክሩ : ሪፎርም ቢጤ ያስፈልጋችኋል እያልኩ በየአጋጣሚው ቅንነት የተሞላውን አስተያየቴን ስሰጥ : የናንተ መልስ የተለመደው ዘለፋ ነበር :: በሰለጠነ መንገድ የሰውን ሀሳብ ማስተናገድ እንኳን አልፈለጋችሁም ::ስለዚህ ለለየለየት ውሸት ራሱን የሚያስገዛና ለጣዖት ሲሰግድ የሚኖር ሰው : ቀና መንፈስ የተላበሰ ሀሳብን ከማስተናገድ ይልቅ በመናፍቅነት እየፈረጀ የሰውን ልብ ሲያደርቅ : ሀቁን ወደ አደባባይ አውጥቶ ማሳየት እንደሚገባ አምናለሁ :: ከዛ ብኋላ እምነቱን (ውሸትን ) መከላከል የሚችል ይከላከላል Laughing ሽምጥጥ አድርጎ የሚክድም ይክዳል Laughing አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ደግሞ ይወስዳል ማለት ነው ::

እናም ይህን ተረድተህ እምነትህን በተመለከተ እየተጋለጠ ያለውን ውሸት እንደሚሆን ተከራከረህ ለመከላከል ሞክር እንጂ የኔ እምነት ምንም ይሁን ምን ፋይዳ አይኖረውም ::

ሠላም
ሰላም ፀዋር :-

................ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር እዚህ ነፃ መድረክ ላይ ርእሱን አንተ ብትከፍተውም በፈለግከው መንገድ ልትመራው አትችልም ::በበኩሌ ከኛ ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ውይይት ከጀመርኩ ወዲያውኑ ነው የእኔን እምነት የሚጠይቁኝ ::ይህም በሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ውይይቶችም ላይ የሚያጋጥም ጉዳይ ነው ::አንተ የእኛን እምነት እያወቅክ የራስህን ግን በተደጋጋሚ ተጠይቀህ ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆንህ ትክክል ካለመሆኑም በላይ እንዲያውም አሰፈላጊ አይደለም ማለትህ ግራ የሚያጋባ ነው ::

.............. አንተ አጋለጥኩ የምትለው 'ውሸት '( ሁሉም አይደለም )እኮ ከላይ እንዳልኩህ አዲስ አይደለም ::አንድ መዘንጋት የሌለብህ ነገር ቢኖር ጊዜው እስኪደርስ ሠይጣን ዲያብሎስ በተለያዩ ፈተናዎች የሰውን ልጅ ሲያሳስት ይኖራል ::ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እንደምናየው ህይወታቸውን እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስትያንን ለማገልገል ቃል ከገቡ በኋላ በተለያዩ ሰይጣናዊ ሥራዎች (ፍቅረ ንዋይ ,ዝሙት ,ጥንቆላ ,..) ውስጥ ከመግባታቸውም በላይ መንፈሳዊ መፅሐፍት ውስጥ ዓለማዊ ነገሮች እያስገቡ ምእመኑን ሲያምታቱ ኖረዋል ::ይህ አንተና መሰሎችህ ስላላችሁ ሳይሆን ማንኛውም ሃይማኖቱን የሚወድ ሰውን ልብ ሲያደማ የኖረ ጉዳይ ነው ::

............ ለነፍሳቸው ያደሩ የሃይማኖት መሪዎችና ሊቃውንት ሃይማኖትን ከነዚህ ዕኩዮች ለማጥራት ቢጥሩም ፍፁማን አይደሉምና ሙሉ በሙሉ አልተሳካላቸውም ::አሁን በኛ ትውልድ በዘመነ ደርግና ወያኔ ኢህአዴግ የምናየውን ተፅዕኖ እንኳ ብናየው ሃይማኖትን ጠብቆ መኖር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ቋሚ ምስክሮች ነን ::ታዲያ 2000 ዓመት የሆነውን እምነት ከሰይጣን ዲያብሎስ ተፅዕኖ ጠብቆ ማቆየት እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ለመገመት የሚያስቸግር አይመስለኝም ::

............. ለምሳሌ በቀላሉ መሐላን እንውሰድ ::በኦሪት ሕግ በሐሰት መማል አይፈቀድም ነበር ::በወንጌል ግን መማል በእውነትም ሆነ በሐሰት ጨርሶ የተከለከለ ነው ::በአሁኑ ዘመን ግን በእግዚአብሔርም ሆነ በፃድቃን እንዲሁም በመላእክት የማይምል ምእመን ይገኛል ማለት ግን ዘበት ነው ::ይህ እንግዲህ የኛ ድክመት መሆኑ ግልፅ ነው ::

............. በተረፈ ከላይ እንዳልኩት የክርስትና መሠረቱ መፅሐፍ ቅዱስ ነውና ማንኛውም ሃይማኖት ነክ ፅሑፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም ::

............. በነገራችን ላይ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰህ ልልህ አሰብኩና አላዊ (Atheist) መሆንህ ትዝ ሲለኝ ተውኩት ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 2:56 am    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:

................ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር እዚህ ነፃ መድረክ ላይ ርእሱን አንተ ብትከፍተውም በፈለግከው መንገድ ልትመራው አትችልም ::በበኩሌ ከኛ ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ውይይት ከጀመርኩ ወዲያውኑ ነው የእኔን እምነት የሚጠይቁኝ ::ይህም በሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ውይይቶችም ላይ የሚያጋጥም ጉዳይ ነው ::አንተ የእኛን እምነት እያወቅክ የራስህን ግን በተደጋጋሚ ተጠይቀህ ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆንህ ትክክል ካለመሆኑም በላይ እንዲያውም አሰፈላጊ አይደለም ማለትህ ግራ የሚያጋባ ነው ::

ሀሳብህ እውነት አለው :: ቢሆንም ከአምዱ ይዘት ጋር የማይሄድ አስተያየት ከመስጠት የመቆጠብ ሀላፊነት እንዳለብኝ ደግሞ መዘንጋት የለብህም ::

Quote:
.............. አንተ አጋለጥኩ የምትለው 'ውሸት '( ሁሉም አይደለም )እኮ ከላይ እንዳልኩህ አዲስ አይደለም ::አንድ መዘንጋት የሌለብህ ነገር ቢኖር ጊዜው እስኪደርስ ሠይጣን ዲያብሎስ በተለያዩ ፈተናዎች የሰውን ልጅ ሲያሳስት ይኖራል ::ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እንደምናየው ህይወታቸውን እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስትያንን ለማገልገል ቃል ከገቡ በኋላ በተለያዩ ሰይጣናዊ ሥራዎች (ፍቅረ ንዋይ ,ዝሙት ,ጥንቆላ ,..) ውስጥ ከመግባታቸውም በላይ መንፈሳዊ መፅሐፍት ውስጥ ዓለማዊ ነገሮች እያስገቡ ምእመኑን ሲያምታቱ ኖረዋል ::ይህ አንተና መሰሎችህ ስላላችሁ ሳይሆን ማንኛውም ሃይማኖቱን የሚወድ ሰውን ልብ ሲያደማ የኖረ ጉዳይ ነው ::

እንደሚታወቀው እኔ በስነ -ሀይማኖት የሰለጠንኩ ሰው አይደለሁም :: ስለማምንበት ነገር ለማወቅ ካለኝ ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ በግሌ ሳነብ ከምቃርማቸው ትምህርቶች (እውቀት ) ውጪ የተለየ ምርምር የማደርግበትና አዲስ ግኝት ለማግኘት ስፈላሰፍ የምኖርበት ምክንያት የለኝም :: ከኔ አዲስ ነገር መጠበቅህ (መጠበቃችሁ ) የሚገርም ነው :: አዲስ ካልሆነ የለመድነውን ደጋግመን መስማት አንፈልግም ለማለት ከሆነ ደግሞ አሁንም ይገርማል :: ከዚህ በፊት የምታውቀውን ድክመት ማስተካከያ እስካልወሰድክበት ድረስ ደጋግመህ መስማትህ አይቀርም :: ዋናው ነጥብ ግን አይደለም :: አንተና ባንተ ደረጃ ያሉ ሰዎች ችግሩን ያውቁታል : ነገር ግን ከችግሩ ለመላቀቅ ወኔያቸው ይከዳቸዋል :: የኔ ፍላጎት ደግሞ ለማያውቀው ያነበብኩትን እያካፈልኩ ማሳወቅ ነው :: ችግሩን አውቆ እንዳንተ ወኔው ከድቶት ከነ ችግሩ መኖር ከፈለገ ይኖራል : ለማስተካከል ከሞከረም ጥሩ :: እውነቱን ሲያውቅ በውሸትና በተራ ተረት -ተረት ላይ እምነቱን ጥሎ ጊዜዉንና ጉልበቱን በከንቱ እያባከነ የሚኖር ሰው ይኖራል ለማለት ግን ይከብዳል ::

Quote:
............ ለነፍሳቸው ያደሩ የሃይማኖት መሪዎችና ሊቃውንት ሃይማኖትን ከነዚህ ዕኩዮች ለማጥራት ቢጥሩም ፍፁማን አይደሉምና ሙሉ በሙሉ አልተሳካላቸውም ::አሁን በኛ ትውልድ በዘመነ ደርግና ወያኔ ኢህአዴግ የምናየውን ተፅዕኖ እንኳ ብናየው ሃይማኖትን ጠብቆ መኖር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ቋሚ ምስክሮች ነን ::ታዲያ 2000 ዓመት የሆነውን እምነት ከሰይጣን ዲያብሎስ ተፅዕኖ ጠብቆ ማቆየት እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ለመገመት የሚያስቸግር አይመስለኝም ::

500 አመታት በፊት ጀምሮ ዘመናቸውን ቀድመው የተፈጥሩ ሊቃውንት እምነቱን ለማጥራት ሲሞክሩ ለሀብትና ንዋይ ባደሩ የደብር ሀላፊዎች አሻጥር እንዴት እንደተወገዱ አየን ' በዚህ አምድ :: ዛሬም ቢሆን ከባዕድ አምልኮ ነጻ ውጡ : ከመግስት ጋር ተጣብቃችሁ ህዝባችንን የግፍና የጭቆና ቀንበር ተሸካሚ አታድርጉ እያሉ የሚጮሁ አሉ : የሚደርስባቸውንም እያየን ነው :: የቤተ ክርስቲያኑን ችግር ሁሉ በየጊዜው በተነሱት መንግስታት ላይ ማላከክ ተገቢ አይመስለኝም :: በግልጽ በሚታይ መልኩ የአንዳንዶቹ ተጽእኖ ቢኖርም : ገድሎቹን ጽፈው ስራ ላይ ያዋሉዋቸው መንግስታት ናቸው ልንል ግን አንችልም :: ከዚህ አኳያ ካየነው አሁንም የማስተካከያ እርምጃው የሚጠበቀው ከቸርቹ ነው ::

Quote:
............. ለምሳሌ በቀላሉ መሐላን እንውሰድ ::በኦሪት ሕግ በሐሰት መማል አይፈቀድም ነበር ::በወንጌል ግን መማል በእውነትም ሆነ በሐሰት ጨርሶ የተከለከለ ነው ::በአሁኑ ዘመን ግን በእግዚአብሔርም ሆነ በፃድቃን እንዲሁም በመላእክት የማይምል ምእመን ይገኛል ማለት ግን ዘበት ነው ::ይህ እንግዲህ የኛ ድክመት መሆኑ ግልፅ ነው ::

ልማድና ህግ ቀያይጠን ማየታችን ይመስለኛል ችግር :: መስቀል መሳለም : ለመስቀል መስገድ ወዘተረፈ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ በአዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን የተደነገገ መሆኑ በዚህ አምድ ተመልክተናል :: መስቀላቸውን ያልያዙ ቄሶች ደግሞ እጃቸውን የሚያሳልሙበት ሌላ ልማድ አለ :: እነዚህ ሁሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውጪ እንደሆኑ የታወቀ ነው :: የመሀላን ልማድ ወደ ምዕመኑ ብታሽቀነጥረውም : በመስቀል ፋንታ እጃቸውን የሚያሳልሙትንና : በብዓል ለምን አረስክ ለምን ጠመድክ እያሉ ሲገዝቱ የሚውሉትን ቄሶችስ የልማድ ተጠቂ /ሰለባ ናቸው እንበል Question መሰረታዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ቸርቹ ያስፈልገዋል የምልበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው :: ቸርቹ ራሱ ሊላቀቃቸው ያልፈለገ ልማዶች ያሉ ይመስለኛል ::

Quote:
............. በተረፈ ከላይ እንዳልኩት የክርስትና መሠረቱ መፅሐፍ ቅዱስ ነውና ማንኛውም ሃይማኖት ነክ ፅሑፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም ::

ጥሩ ! የሚያስማማን ነው ይሄ :: ስለዚህ ባንተ እምነት በዚህ አምድ ያየናቸው ገድሎችና ድርሳናት ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫሉ አይጋጩም Question ለማርያም መስገድና ማምለክ : ለመስቀል መስገድ : በገብረመንፈስ ቅዱስ ማመን : በክርስቶስ ሰምራና በተክለሀይማኖት ተስፋ መጣል : ለነጫጭባ ወታደሮችና መነኮሳት መስገድ : ወዘተረፈ ተገቢ ነው ትላለህ Question ከሁሉም ከሁሉም ለነሱ ተብሎ ስራ እየተፈታ : በድግስ በዝክር እህል ውሀ እየባከነ የሚኖርበት ምክንያት ምን ይሆን Question

Quote:
............. በነገራችን ላይ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰህ ልልህ አሰብኩና አላዊ (Atheist) መሆንህ ትዝ ሲለኝ ተውኩት ::

Laughing
ምነው ኤቲስት ማለት ትርጉሙን በደንብ አላወቅከውም ማለት ነው Question አንተ በምታምንበት ጨካኝና ጦረኛ አምላክ አላምንም ማለት እኮ ኤቲስት አያስብልም :: ፍጹም በሆነ አምላክ የማምን ሰው ነኝ :: የኔ አምላክ በሰው ልጆች ጦርነት ውስጥ እየተሳተፈ ፍጽምናውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም ::

ሠላም
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 10:53 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም በዚህ ርእስ ለተካፈላችሁ እያልኩ :-

ፖለቲከኞች መድረካችንን ልቀቁ እያሉ ነውና ይህን ርእስ ወደ ቦታው (Warka general) ብንወስደው ምን ይመስላችኋል ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 12:01 pm    Post subject: የአርነት መንገድ Reply with quote

የአርነት መንገድ

በምታውቃት እውነት : እግርህን እየጣልክ
ወደፊት ስትዘልቅ : በህይወት ጎዳና
ከመነሻ ቦታህ እርቀህ ሳትርቅ :...
በጉልበት ተይዘህ በሌሎች ሀሳብ
ሳትፈልግ ብትወድቅ መንገድህ ባይቀና

ሀሳብና ምግባር ጀርባና ሆድ ሁነው
በህሊናህ ታስረህ በግዞት ስትደቅ
...............................ሲናን ስትናፍቅ
እንደ እስራኤላዊያን
አርነትን ለማግኘት ሙሴን አትጠብቅ ::

ዛሬ እንኳንስ ሙሴ : አምሳያውም የለ
ሙሴ ቀረ ትላንት !
የአገርህ ቀሳውስት የለበሷት ካባ
የፅድቅ አይደለችም የብርድ ልብስ ናት !

"ለሰው ልጆች ፍቅር የሚሰጥ ተላልፎ "
እንደዚህ ተብሎ ትንቢት አንጠልጥሎ ...
አንተን ነጻ ሊያደርግ : ዳግመኛ የሚሞት የሚመጣ መስሎህ
ስታይ አትደንግጥ

ምህረትን ፍለጋም ወደላይ አንጋጠህ
"ኤሎሄ ! ኤሎሄ !" አትበል "ወዮ ! ወዮ !"
ለሰው ብሎ መሰቀል ለሰው ብሎ መሞት
የዛሬ ስንት አመት ከክርስቶስ ጋራ ቀርቷል ቀራንዮ

እናም !
በህሊናህ ፍቃድ በጠራው ሀሳብህ
በምታውቃት እውነት መጓዝን ከወደድህ
እራስህን ሰዋ አንተ እነሱን ሁነህ !
ስላንተ 'ሚሰዋ ዛሬ ማንም የለ
....አንተ እንደሁ የአንተ ነህ !

በመላኩ ጌታቸው (የአርነት መንገድ (የግጥም ስብስብ ) 2000 ..)

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 10:08 pm    Post subject: Reply with quote

ወዳጄ ጸዋር

ህይወት ማለት ምንድነው ?

አርነትስ ማለት ምንድነው ?

ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Mon Jan 09, 2012 12:54 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ቆቁ

ጥያቄ አትውደድ :: አሰልቺ ነው :: በጥያቄ ፋንታ ውይይት ልመድ :: አንተ ጠያቂ እኔ መላሽ ሆነን መዝለቅ አይቻልም ::

ለመጨረሻ ጊዜ ጥያቄህን አስተናግዳለሁ ::

የህይወትን ትርጉም ለምን እንደጠየቅከኝ ባላውቅም ለእያንዳንዳችን የተለያየ ትርጉም ስላለው የምናገረው ነገር አይመችህም ይሆናል :: ምናልባት ያንተ የህይወት ትርጉም በሠማያው ተስፋ ተሞልቶ በምድር ላይ እንደ ሰው ሳትኖር ኖረህ መሞት ሊሆን ይችላል :: በዕውቀቱ እንዳለው ከሰማዩም ከምድሩም ሳይሆንለት ከሚቀረው "ከንቱ " ተክለሀይማኖታዊያን ትሆን ይሆናል :: ለኔ ደግሞ ህይወት በማይጨበጥ ተስፋ የተሞላ ሳይሆን እንደ ሰው dignified ኑሮ ኖሮ በክብር መሞት ነው :: ከራስ በላይ ለነገው ትውልድ ጭምር መኖር ነው የኔ የህይወት ትርጉም :: ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች : በእግዚአብሄር የተመረጠች አገር ስለሆነች እግዚአብሄር ይታደጋታል : ይደርስላታል እያሉ በመጃጃል አንገቱን አቀርቅሮ በተስፋ መኖር ለኔ የህይወት ትርጉም አይደለም ::

በኔ ግንዛቤ አርነት ማለት ደግሞ ከጨቋኞች : ከድህነት : ከእርዛት : ከርሀብ : ከባዕድ አምልኮ : ከመጥፎ ልማድ : ከአማራጭ እጦት ወዘተ ነጻ መውጣት ማለት ነው :: ነጻነትህን ደግሞ ከራስህ ውጪ ማንም አይሰጥህም Exclamation Exclamation ግንብ ለግንብ ስትታከክ ብትውል : ለስእል አፈንድደህ ስትጸልይ ብትኖር : ለእንጨት ብትሰግድ : ለጦረኛው ጊዮርጊስ ስለት ብትገባ : ወይም ለአቡነ አረጋይ ብትማጸን አርነት አትገኝም :: አርነት ተግባር ናት ! ወኔ ናት ! ድፈረት ናት ! እውቀት ናት ! አሻፈረኝ ባይነት ናት ! ወዘተ ... ከንቱ ተስፋ , ፍርሀት , ተንበርካኪነት , ወኔ ቢስነት , የአርነት ጠላቶች ናቸው !!! ለዚህም ነው ለውጥ ከፈለግን ከለውጥ በፊት የለውጥ እንቅፋት ይወገድ በሚል አምድ ስር እየተወያየን ያለነው :: ለዚህም ነው ከንቱ ልማድ ይወገድ ! ኋላቀሮች ያደረገንን : ለጨቋኞች ተንበርካኪ ያደረገንን በምርምር ያልተደገፈ የሞኝ እምነት ይብቃ ! ለውሸት ለተረት ተረት ቦታ አንስጥ ! ከሁሉም በፊት የለውጥ እንቅፋት ለሆነው ማነቆ የማስተካከያ እርምጃ እንውሰድ ! እንንቃ ! የምለው ::

Liberty is the possibility of doubting, of making a mistake,... of searching and experimenting,... of saying No to any authority - literary, artistic, philosophical, religious, social, and even political.
~Ignazio Silone, The God That Failed, 1950

ሠላም !

ቆቁ እንደጻፈ(ች)ው:
ወዳጄ ጸዋር

ህይወት ማለት ምንድነው ?

አርነትስ ማለት ምንድነው ?

ፈላስፋው ቆቁ

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
Page 7 of 10

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia