WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአፍሪካ የቁንጅና ውድድር !!

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3350
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 4:54 pm    Post subject: የአፍሪካ የቁንጅና ውድድር !! Reply with quote

እውነት ለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም ይቺን ጥሁፍ አዝናኝ ሆና አግኝቻታለሁ :: ወዳጅ ጎረቤቶቻችን ኬንያዎችን በውበት ከአፍሪካ የመጨረሻ ብለዋቸዋል :: እኛን ደግሞ ከሩዋንዳ እና ኮት ዲቯር ለጥቆ ሦስተኛ Laughing Laughing

እንደ ክቡራን ይቺን ጠቅ ያድርጉ
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 8:08 pm    Post subject: Re: የአፍሪካ የቁንጅና ውድድር !! Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
እውነት ለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም ይቺን ጥሁፍ አዝናኝ ሆና አግኝቻታለሁ :: ወዳጅ ጎረቤቶቻችን ኬንያዎችን በውበት ከአፍሪካ የመጨረሻ ብለዋቸዋል :: እኛን ደግሞ ከሩዋንዳ እና ኮት ዲቯር ለጥቆ ሦስተኛ Laughing Laughing
እንደ ክቡራን ይቺን ጠቅ ያድርጉ

ወንድም ጌታ

እኔ ደግሞ የቆንጆ ምስል ይኖረዋል ብዬ ለማየት ተንደርድሬ ስገባ እኒህን ኬንያዊያኖችን ወርደዉባቸዋል :: ያንን አርቲክል በኬንያዊያን ላይ እንዲያ የጻፈው ግን ጥቁር ነው ነጭ Rolling Eyes ነጭ ለጥቁር ያለውን የዘረኝነት አመለካከት በደንብ ይገልጻል :: አካላዊ ገጽታ እንደ ዋና መመዘኛ ከተወሰደ ግን ከጥቁር ውስጥ ኢትዮጵያንና ሌሎቹን ምስራቅ አፍሪካዊያንን አይደርሱባቸውም ::

ስለ ቁንጆዎቹ ከተነሳ ባለፈው ጦቢያ ሄጀ እያለ አንድ የሆነ ከተማ ላይ 'ሚስ ' ተብላ ያሸነፈች ልጅ አንድ ጓደኛየ ጋር ስለሚተዋወቁ ጂንጀና ብጤ ጀምሮ ሸገር ነበረችና ለእራት ጋብዟት አብሬያቸው አምሸቼ ነበር :: እና ልጂቱ እውነትም ቆንጆ ናት ....ገና እንዳየኋት ለጓደኛየ ምንም እሽ እንደማትለው አስልቼ ገመትሁ Wink ...ልጁ ካለን ልምድ አይደለም እሷ ታናናሾቿንም የሚማርክ ወንድ አይደለም :: ብዙ ጊዜ ይሞክራል ግን ባውንስ እያረገ ነው የሚመለሰው :: እና በውስጤ ያንን ይዤ ኮራ ብዬ እሱ ልጂቱን እንደሚፈልጋት ሁሉ ረስቼ እሷ ወይን እኔ ጊዮርጊሴን ይዤ (እሱ ምን እንደጠጣ እንኳን ትዝ አይለኝም Laughing ) እናልህ ፈገግታ የታጀበበት ጨዋታየን ጀመርኩኛ አይን አይኗን እያየሁ Smile :: ለካስ ልጁ ገብቶታልና በወሬያችን መሃል እየገባ አንተ መሸብህ አትሄድም እንዴ ...'ጓደኛየ (ፍቅረኛየን ማለቱ ነው ) ትጠብቀኛለች አላልክም ነበር ..ምናምን እያለ ፍቅረኛ እንዳለኝ ሊያሳውቅ ይቀላቅልልኝ ያዘው ...አፈር ይብላና Rolling Eyes እንዴት እንዳቃጠለኝ :: ልጂቱ ግን ብዙም ጉዳይ ሳትሰጠው አይኗን ወደ እኔ አድርጋ እሱን ችላ ብላ ትብተከተክ ትቅበጠበጥ ጀመር ::በተለይ ለሽንት ሲወጣ መፍለቅለቋ መጨመሩ የበለጠ ተስፋን ጫረብኝ Wink ግን ያው መጨረሻው ባይሳካለትም እሱ ፈልጓት ስለመጣች ለሱ ክብር ብዬ ሂሳብ ከፍየላቸው ትቻቸው ሄድኩኝ ...በኋላ እነሱም ትንሽ ሳይቆዩ እንደተለያዩ ነገረኝ ::

በበነጋታው 'ሚስ ' መባሏም ተጨምሮበት ነው መሰለኝ ፈገግታዋንና እኒያን ተመራጭ አይኖቿን 'ሚስ ' ማረግ ጀመርኩኝ :: ስልኳን ስጠኝ እንዳልለው በጣም ፈራሁት ግን በኋላ ትዝ ሲለኝ ለካስ ሞባይሉ ሳንቲም ጨርሶበት እንዲገናኙ ሲደውልላት የኔንም ሞባይል ሲጠቀም ነበር Wink ...እዚያች ላይ ላጥ አድርጌ ድውውል ...ከምር በደስታ ቅብጥብጥ እያለች ስታዋራኝ መንገድ ላይ ነበርኩኝና መኪና ሁሉ ሊገጨኝ ነበር . Smile ተነጋግረን ስደውል ስንብቼ አንድ ቀን እንደምንገናኝ ተቀጣጥረን መብረሪያየ ቀን ሊደርስ ቀናት ሲቀሩት ከቺኬ ጋር እያለሁ የሆነ ምሽት ደወለችልኝና አሁን ከቻልህ ሜክሲኮ ነኝ መገናኘት እንችላለን ስትለኝ ምን ልበል ...ችኬን ሁሉ ትቻት ላሽ ልል ነበር Smile ከዚያ ያለሁት ባህር ዳር ነው ለምን በዚህ ቀን ወደ ሸገር ስመጣ አንገናኝም ... ስላት አልኖርም ወደ ትውልድ ከተማየ እሄዳለሁ አለችኝና እንዳሰብኳት ደግሜ ሳላገኛት መጣሁ Sad ደግሞ የሴቶቹን ስልክ ፋይል አድርጌ በጥንቃቄ የምይዝ ልጅ ሳይልልኝ ቀርቶ የሷውን ሳልይዘው መጥቼ ይሄው ስንት ጊዜዬ ፌስ ቡክ ላይ ስሟን እያስገባሁ በፍለጋ እዳክራለሁ :: ያንን ጓደኛየን ደውዬ እንዳልጠይቀውም ኦልረዲ ጠርጥሮኛልና ደበረኝ ...ግን በሆነ ልጅ አድራሽዋን ማግኘቴ አይቀርም ...ሸገር ሞዴሊንግ ምናምን እየተማርሁ ነው ስትለኝ ነበር ::

ውይ ወንድም ጌታ ሶሪ ...ከቤቱ ርዕስ ወጣሁኝ ይሆን Confused

ልጅ ሞንሟናው
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3350
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 8:28 pm    Post subject: Reply with quote

ልጅ ሞንሟናው

እላይ ከጣፍከው እንደተረዳሁት እንደስምህ መልከመልካም ሸጋ ሴት አማላይ ነህ ማለት ነው Laughing Laughing Laughing እኔ ደግሞ ከኬንያዎች የምሻል አበሻ ስለሆንኩ በተለይ 'ሚስ ኢትዮጵያ ' ደረጃ ቆንጆ ለሆኑ ሴቶች ብዙም ግድ የለኝም :: ለማየት ደስ ቢሉኝም የቁም ነገር እንጥፍጣፊም ያላቸው አይመስለኝም :: እነሱ አሉ (ለወንድም ይሰራል ) ፍቅር ከመሥራት ይልቅ መስታወት ብታቀርብላቸው ይመርጣሉ ይባላል :: በቃ ከራሳቸው ውበት ጋር ፍቅር ስለሚይዛቸው ያንን ሲያዩ ቢውሉ አይጠግቡትም :: ይህ ሲሆን ታድያ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜም አይገኝ Laughing Laughing

በል እሷን እርሳትና ጓደኛህን ጠበቅ አድርግ Smile
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Feb 10, 2012 9:14 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
ልጅ ሞንሟናው

እላይ ከጣፍከው እንደተረዳሁት እንደስምህ መልከመልካም ሸጋ ሴት አማላይ ነህ ማለት ነው Laughing Laughing Laughing እኔ ደግሞ ከኬንያዎች የምሻል አበሻ ስለሆንኩ በተለይ 'ሚስ ኢትዮጵያ ' ደረጃ ቆንጆ ለሆኑ ሴቶች ብዙም ግድ የለኝም :: ለማየት ደስ ቢሉኝም የቁም ነገር እንጥፍጣፊም ያላቸው አይመስለኝም :: እነሱ አሉ (ለወንድም ይሰራል ) ፍቅር ከመሥራት ይልቅ መስታወት ብታቀርብላቸው ይመርጣሉ ይባላል :: በቃ ከራሳቸው ውበት ጋር ፍቅር ስለሚይዛቸው ያንን ሲያዩ ቢውሉ አይጠግቡትም :: ይህ ሲሆን ታድያ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜም አይገኝ Laughing Laughing

በል እሷን እርሳትና ጓደኛህን ጠበቅ አድርግ Smile

ሃሃሃ ወንድም ጌታ ...መልከ መልካምነቱ ላይ እንኳን ብዙም አይደለሁም ...ይህን ያህል 'ወግድልኝ ' የሚሉት አይነት ባልሆንም ...ዋናው ነገር ...ግንባሬ ሳይሆን አይቀርም ብያለሁ Wink አንተ እንዳልከውም ግን እንዲህ አይነት ሴቶች ለፍቅር ብዙም አይሆኑም ..እኔም እሷን ለዚያ ትሆነኛለች ብየም ሳይሆን ...ግን በቁንጂና ደረጃ ሰጭ ኮሚቴ የተመረጠችዋን 'ሚስ ' እንትን ማለቱ ... አለ አይደል በቃ ለወሬውም ለኮንፊደንስም ጥሩ ነው Smile እንጂ ከኔዋ ችክ ፍቅር አዋቂነትስ አትደርስም ይሆናል ...እሷ ጋር ቆይቼ ወደ እኔዋ ፍልቅልቅ ስሄድም ወዲያው ነው የረሳኋት ...የኔ ችግር ከፍልቅልቄ ጋር አድሬ በጥዋት ደግሞ እዚያችኛዋ ጋር መደወሌ Confused
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሻቬዝ -x

ኮትኳች

Joined: 17 Nov 2009
Posts: 164

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 7:30 am    Post subject: Re: የአፍሪካ የቁንጅና ውድድር !! Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
እውነት ለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም ይቺን ጥሁፍ አዝናኝ ሆና አግኝቻታለሁ :: ወዳጅ ጎረቤቶቻችን ኬንያዎችን በውበት ከአፍሪካ የመጨረሻ ብለዋቸዋል :: እኛን ደግሞ ከሩዋንዳ እና ኮት ዲቯር ለጥቆ ሦስተኛ Laughing Laughing

እንደ ክቡራን ይቺን ጠቅ ያድርጉ

ጌች

ውበት እኮ እንደተመልካቹ መስፈርያ ነው የሚለካው

ኬንያ ውስጥ አሁን መቀመጫዋ እንስራ ያለገመድ የሚያስቀምጠው ከንፈርዋ ዳቦ የሚያክለው አፍንጫዋ ሰፋ ሰፋ ያለው እሷ ነች ገዳይ ሴት የምትባለው እና አዝማሪ ሁሉ የሚቀኝላት
ሞሪታንያ ውስጥ ደግሞ እንደ መኪና ሁለት በር ተከፍቶላት የምትገባው ገልባጭ መኪና የሚታክለው እሷ ነች የውበት ንግስት (ሳያት ደምሴ አንጀሊና ጆሊ ምናምን እዛ ዋጋ የላቸውም )

ትእግስት በቀለ የተባለችው አርቲስት አንድ ግዘ ወደ ደቡብ ልትዘፍን ሄዳ ' አይ እቺ ድምጽ የላትም መልክ ብቻ ነች " አሏት ይላሉ

አንዳንዴ ሚስ ወርልድ ምንምን እያሉ የሚመርጥዋቸው ለኔ ግርም ነው የሚሉኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3350
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 8:00 pm    Post subject: Reply with quote

ትክክል ነህ ሻቬዝ :: ኬንያዎቹ ከታች ያደረጉትን ውይይት ብታይ እነሱ አስጠሊታ ብለው የሚገምቷቸውን አገሮች ጠቅሰዋል ::

ይልቅ እኛ ባገራችን ስለውበት ያለንን /የነበረንን ግንዛቤ እና ዛሬ ሌላ ማኅበረሰብ ውስጥ ሆኜ 'ቆንጆ ' ብዬ የምረዳውን ሳስበው ይገርመኛል :: የድሮ ሰውማ ቀይ ከሆንክ ቆንጆ ከጠቆርክ ደግሞ በጣም ካልተሰለከክ እዚህ ግባም አይልህ Laughing Laughing Laughing
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia