WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እንድትጠይቅ ጴቲሽን ተጀመረ ::
Goto page Previous  1, 2
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዲያስፖራ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Apr 2009
Posts: 714
Location: no

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 2:52 pm    Post subject: Reply with quote

ክቡራን በህይወትህ አሁን ገና ቁም ነገር ሰራህ , እኔ የሚያናድደኝ ወያኔ የሚቃወሙ ሁሉ እንዴት የሀገርን ጥቅም እና ሉአላዊነትን ወያኔ ለየተው ማየት አቃታቸው ? ይህ እኮ ግራዚያኒ በመርዝ እና በቦንብ ሲጨርስ ይነበረ ታሪክ ነው :: ያሁኑ በስልጣን ያለው መንግስት ባያነሳው እኛ ለተጨፈጨፈው ህዝባችን አንጮህም ?? ወይስ እና ዝም ብለን ወያኔ ካልሰራው እኛ ምን አገባን እንበል ? ቫቲካን የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ ይቅርታ ትጠይቅ ተባለ እንጂ ወያኔን ትጥይቅ አልተባለም
ሻቢያ እና ኦሌፍ ኦጋዴኖች እናንተን አይምለከትም :: ኢትዮጵያዊነታችሁን ክዳችሁአል እና ነው , ያዛዘነኝ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉት እንደ ጥልቁ አይነት ሰዎች ተቃውሞ ምን እስከም ደርስ መሆኑን ያልተገነዘቡ ፖለቲካ ድርጅት እና ሀገርን ለይተው አለማወቃቸው ወይም አወቀው እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል እንዳልችው እንስሳ ሲሆኑ ሳይ በጣም ያዝነኛል :: ቢገባቸውማ ከሰር መስረርቱ አሁን ላለንበት የዘር በሽታ ነጮቹ የፈጠሩልን መሆኑን መረዳት በተገባችሁ ነበር ::
ክቡራን እንዲህ ከምንግስትም ሆነ ከተቃዋሚ ጋር ያልወገነ ኢትዮጵያን የሚመለከት ጉዳይ በማቅረበህ አመስገናለሁ ::
_________________
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4206
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 3:16 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ቫቲካን በየጊዜው ጳጳሳቷ ለሚሰሩት በደል ይቅርታና ካሳ በመክፈል የታወቀች ነች ::በቅርቡ እንኩዋ በላቲን አሜሪካ ያለውን ኢፍትሀዊ የገበያ ልውውጥና የስደተኞችን መብት ለማስከበር ብዙ በጎ እርምጃ ወስዳለች ::ቫቲካን ድሮ በነሞሶሎኒ ጊዜ ከነበረ ብዙ ተሽላለች ::እዚህ ቫቲካን ይቅርታ ትጠይቅ የሚል የይስሙላ የፖለቲካ ፍጆታ የወያኔን ግፍ ማዘናጊያ ነው ::የገባሩ ልጆች ያኔ ከሩቅ መጥቶ ከጨፈጨፈን የነፍስ አባት ቫቲካን ይልቅ ዛሬ የሚጨፈጭፈን የወያኔነፍስ አባት አባጳውሎስ /ታጋይገመድህን መስቀልአደባባይ የቅርቡ ተቃዋሚዎችን ማጉዋጠጥ በወያኔ ነፍሰገዳዮች ለታረዱ ምንም ያለመተንፈስ ጭራሽ መሳለቅ በግፍ ለታሰሩ ፍትህ ያለመጠየቅ እጅግ ያንገበግበናል ::አዎን ጣልያን ፋሽስት የጨፈጨፋቸው ቫቲካን ያኔ የባረከችው አይረሳም አሁን ግን አንገብጋቢ አይደለም !
ይቅርታ ጥሬ ቃሉ ይቅር አይደገም ለእርምት ይሁን የሚል ድንቅ ባህል ነው ::በደል ማድረጉ የተሰማው በበደላቸው ወገኖች እሮሮና የበዳዩ ወገኖችና የተበዳይ ደጋፊዎች ጫና ይቅርታ ያስገኛሉ ::
እዚህ የተጠቀሰው ቫቲካን የካቶሊኮቹ የሀይማኖት ማእከል ይቅርታ ትጠይቅ ትእይንት በሀገራችን ኢትዮጲያ ተጨባጭ ሁኔታ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጫና ሊደረግበት የሚገባ የክፍለዘመኑ አረመኔ ግፈኛ የወያኔ መንግስት እያለ አንድና ሁለት ክፍለዘመን ያለፈውን ዛሬ ማንሳት ትኩረት የማስቀየር አላማ ያለው የበዳዩ ማዘናጊያ ደባ ነው ::
193 + ተቃውሚ ሰልፈኞችን ባላስፈላጊ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ ያሳረደ የተመራጭ ተሾመ ሚስት እቴነሽ ባሌ አያታሰር ብላ ስለጨህች ያስረሸነ ብላቴናዎች እነኑረዲን እሱባለው ኩዋስ ሜዳ ላይ በአጋዚ ታጣቂ ያስረሸነ ሽብሬ የኮተቤዋን ባዶ እጇን ለፍትህ ስለጮህች ያስገደለ የነጻ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎችን በሺዎች አስሮ ሺዎችን ያሰደደ የሲቪል መብት ታጋይ አበራ ሄይንና ዳዊት ገረቶ ለምርጫ ሲዘጋጁ አሳርዶ ጫካ የጣለ ግፈኛ ወያኔ ያላንዳች ይቅርታ እኒህ ሙታንን አሸባሪ አያለ እንዴት የድሮው የበለጠ አንገብጋቢ ይሆናል ?የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሳሰቢያ መሰረት የራሱ የወያኔ ሹሞች አጣሪ ሆነው ያጋለጡት አረመኔ ለገሰ ዜናዊ ሰርዙ ያላቸው ሀቅ እያለ እንዴት የከረመው ዛሬ እዚህ ይፈተፈታል ጉድ !
ክቡራን ታውረህ አትቅር አምነዋለሁ ለምትል ክርስቶስ ተናዘህ ንስሀ ግባና ከፈጣሪም ከህዝቦችም ታረቅ አለቃህ መለስና ሚስቱ በደንዳና ልባቸው ገሀነም ይወርዷታልና አተከተላቸው ትንሽ ምክር -ለሚያልፍ እንጀራ የማያልፈውን አትጣ !
ዲጎኔ ሞረቴ ሉተር ትክክለኛ አስተማሪ ነበር ብላ ይቅርታ ከጠየቀች ቫቲካን ክልል የነአለቃ ታዬን ሙትበቃ ካላነሳች ማህበር ሩቅ ማዶ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 4:26 pm    Post subject: Reply with quote

በወንድሜ ዲጎኔ ውስጥ ያለውን መንፈስ በዚህ ሰአት እኔ እገስጻላሁ ..ባንድ አጀንዳ ላይ ሁለት ጊዜ ተመሳሳይ ነገር የምትደግም በወንድሜ ዲጎኔ ውስጥ የምትመላለስ መንፈስ በዚች ሰአትና ጊዜ ይሄን አባዜህን እንድታቆም እኔ አዝሀለሁ !! ሻላላሚዶ !!
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዲያስፖራ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Apr 2009
Posts: 714
Location: no

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 4:38 pm    Post subject: Reply with quote

የለም የለም እንደተርዳሁት ብዝዎቻችሁ ስለ ይቅርታ ያለው ትርጉም አልገባችሁም አሊያም ጣቢያው እንደ ተቀላቀለ ራዲዮ ሆናችሁአል ::
የቫቲካን እና የወያኔን እሰቲ ለየት አርገን እንየው መቸም የወንጀል ትንሽም ባይኖረውም በፖለቲካ ሹኩቻ የሚሰራ ወንጀል እና በሀገር ለይ የሚሰራ ወንጀል እኩል አይደለም ::
ቫቲካኖች የጣሊያንን ጦር መርቀው ወይም በለው በለው አንድንም ዘር ሳይመርጡ መላው የኢትዮጵያንን በመርዝ እና በቦንብ ፍጅተዋል (መርዝ ) የሚለው ይሰመርበት ::
ወያኔ በኢሰባብዊነቱ እና በአምባገነንቱ ሊያስጠየቅው ይችል የሆናል እንጂ ከግራዚያኒ ጋር በምንም መመዘኛ አንወዳደረውም ደርግም ቢሆን ሻቢያም ቢሆን አናወዳደራቸውም :: ስለዚህ ግራዚያኒ በአለም አቀፍ ፍርድቤት ስንዳኘው ያኛን ጉዶች ግን በሀገራችን ፍርቤት ነው የምንዳቻቸው :.
ስለ ይቅርታ ደሞ ስንመጣ ደሞ የቅርታ በራሱ ጥፋት ማመን ነው :: ብልጡ ወያኔ ብዙ ግዜ ሰዎችን ይቅርታ በሉና እፈታለሁ ማለቱ እኮ ጥፋትን ከራስ አውርዶ በይቅርታ ተቀባዮች ላይ ማስቀመጥ ነው የኛዎቹ ቅንጅት ይቅርታ ሳይሉ በእውነት ላይ ቆመው ቢሆኑ ኖሮ ዛሬ የተለየ ነገር ተፈጥሮ ነበር :: ማንዴላ 25 አመት ሲታሰር ይቅርታ እንዲል ይልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም :.አለማለቱ በጀው :. የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም :: ከዛ በሁላ እንሆ ወያኔ ይቅርታን የህግ ማምለጫ መሳሪያ አድርጎት እስካሁን ይጠቀምበታል ምናልባት አሁን ያስቸገራቸው አንዱአለም ነው ይቅርታ ብሎ ጥፋተኝነትን በራሱ ጫንቃ ላይ ማስቀመጥ የማይፈለግ ::
ወደ ቫቲካኖችም እንምጣ እስራኤልን ወይም የበለጸጉ አገራትን ይቅርታ መጠየቁ ከሞራል አካያ ካልሆነ ለታዳጊ አገራት ግን በተለይ ለኢትዮጵያ ከይቅርታው በሁላ የሚያመጣውን መዘዝ ስለሚያቁ አገታቸው ላይ ገመድ ማስገባቱን አይፈልጉም ገፍቶ ከመጣ ግን ማምለጫ ስሌለ ከይቅርታው በፊት ድርድር ወይም ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣሉ :: አስትውሳለሁ በፈርንጅ አቆጥጠር 2010 ኦክቶቭር ላይ በድቡብ አፍሪካ መላው አለም አቀፍ የመሪዎች ስብሰባ ላይ አመሪካኖች እና አውሮፓኖች አፍሪካን በቅኝ አገዛዝ (ኮሎኒያል ) ስር ባድረጉበት ዘመን ይቅርታ ይጠይቁ ሲባል አሜሪካኖች እና አውሮፓኖች ከይቅርታው በሁላ የሚመጣውን መዘዝ ስላወቁ እንቢ አሉ ::እንቢታቸው ደሞ በሌላ ማካካሻ ለመተካት በማይነጥፍ ገነዘብ ለመተካት ሀሳብ አቀረቡ ከዚህ ሁሉ ግን በአፍሪካ በዙም ቀኝ ግዛት ይላረገች አገር ጀርመን ግን (ምናልባት ናምቢያን ይሆን ??) ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ነበረች ነገሩ ውጥረት ነበረው እርኩስ sep 11 መቶ ነገሩን ወሀ ደፋበት እንጂ ::
ያም ሆነ ይህ ይቅርታ በራሱ ትልቅ ስፍራ አለው ህጋዊ እውቅና አለው ይህ ስነድ እንደ ቀላል አተዩት ::
_________________
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 367

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 5:33 pm    Post subject: Re: ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እንድትጠይቅ ጴቲሽን ተጀመረ :: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
የፋሺስት ኢጣሊያን መንግስት ኢትዪጵያንና ህዝቦቿን በጋዝ መርዝ ባሰቃቂ ሁኔታ ሲጨርሱ ቫቲካን መንፈሳዊ ተባባሪ ነበረች :: ቫቲካን ከዚህም በላይ ፋሢስቶቹ ወገኖቻችን የፈጁበትን መርዝና ታንክ እንዲሁም አይሮፕላኖች ""ሚሽናችሁ ይሳካ "" እያለች ወታደሮቹን በጸሎት በመባረክ ታሰናብት ነበር :: ቫቲካን ጀርመኖች እስራኤልን በመጨፍችፋቸው ይፋ ይቅርታ ጠይቃለች :: ኢትዮጵያ ግን ከዛ የባሰ ጭፍጨፋ ተካሂዷብት ይቅርታ አልተጠየቀችም :: ባለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቫቲካን በይፋ ወጥታ ለተፈጸመው በደል እጇ አለበትና ይቅርታ እንድትጠይቅ ፔቲሽን ባለም ዙሪያ እያስፈረሙ ነው :: የሚገርመው ፔቲሽኑን ኢትዪጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ቡዙ የውጭ አገር ሰዎች በመፈረም ላይ ናቸው :: የቫቲካንን ዝምታ እንሰብራለን የሚል መልክት ላለም መንግስታት , ለሰባዊ ድርጅቶች ለተለያዩ የእምነት ተቃሞች , የተበተነውን የፊርማ ማሰባሰበያ እዚህ ያገኙታል :: ያገርዎ ጉዳይ ነውና እርሶም ለዚህ ጥሪ ምላሽ ይስጡ :: እቺን ጠቅ ::

አቶ "ይቺን ጠቅ " የሚጠቀጥቅ ይጠቅጥቅህና የዛሬ 3 አመት መስማማት ይህንን ነገር ሲያቀርብ አንተ እምበር ተጋዳልቲ እያልክ በማቀንቀን ቢዚ ነበርክ :: አሁንም ለኢትዮጵያውያን አስበህ ሳይሆን ያንን ዲሪቶ ገጽህን ልታስተዋውቅበት ነው አላማህ :: ለዛ ነው እንጂ ፋሺስት ለጨፈጨፋቸው ኢትዮጵያውያን ደንታ የላችሁም :: ቢኖራችሁማ የሰማዕታትን ቀን ሀገር ወራችሁ ሀገር ልታፈርሱና ሀገር ልትሸጡ አዲሳበባ በገባችሁበት ቀን አትሽሩትም ነበር

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=32390&sid=d74b84afba40b01f923a80795067b7c6

3 አመት ሙሉ የት ነበርክ ? ሀገር ስትቸበችብና ስትዘርፍ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4206
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 6:27 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ዳያስፖራ
በሀገር ላይ ጭፍጨፋ ያረገ ወራሪ የሚጠበቅበት ይቅርታና
በዚህ ይቅርታ የሚገኝ ብሄራዊ ጥቅም ጠፍቶኝ አይደለም ይህ የወያኔ ጀሌ ነገር ሲያቆራኝ ወያኔን ጻድቅ ለማድረግ ተቃዋሚና ነጻ ፕሬስን ለማሳጣት የሚያደርጋቸው ደባዎቹ ጽዋ ሞልቶ ስለፈሰሰ እንጂ ::በመሰረቱ የሳተ ቫቲካን ሊሰጥ የሚችለው ሀይማኖታዊ ምላሽ ብቻነው ::ነገር ግን በፖፕ አሳችነት በቄሳር መንበር ተኮፍሶ በአለማዊ ነገር ኤምባሲ ከፍቶ መንግስት መሆኑ የከፋ ነው :: በትክክል እንዳልከው ብሄርዊ ይቅርታ አሜሪካ ጥቁር ወንድሞቻንና እህቶቻችንን ለተበዘበዙ አልጠየቁም ባለፈ የባርያ ንግድ ስፍራ ምእራብ አፍሪካ ቡሽ ሲሄድ 'በታሪክ የከፋ ' አለ እንጂ ይፋ ይቅርታ አልጠየቀም ያንን ቢያደርግ ለጥቁሮች የተጠየቀ እጅግ ብዙ ካሳ ይከፈላልና ::
ለማጠቃለል ቫቲካን ይቅርታ ፐቲሽን ከወያኔ የፖለቲካ አድቫንቴጅ ያለፈ የሚያመጣው የለም ::ቀልማዳዋ ቫቲካን እንደእምነት ተቁዋም መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ነገር አይጠበቅባትም በህጉ ::ጣልያን ግን በትክክል የቆቃ ግድብን ያሰራበትን ካሳ ከፍሏል ተጨማሪ ብንጠይቅ እሰይ !
በነገራችን ማንዴላ ሮቢን ደሴት የታስረ 27 አመታት ነው ::
እስኪ በዚሁ ወያኔ ለነሽብሬበተሰብኖ በብቨሀላችን ጉማ ምን ያህል መክፈል ይገባዋል የሚለውን እንወያይ !

ለእኛ ሞረቴ ደቡቦቹ ኦሮሞዎቹ ጋላ ጉዴላ ቡዳ ተብለው አያቶቻችን ለተወገሩና ለተገደሉት ቁዋንጃ እየተቆረጠ በባርነት ለተበዘበዙ ይቅርታና ካሳ አይገባም ? እየተስተዋለ !

ዲያስፖራ እንደጻፈ(ች)ው:
የለም የለም እንደተርዳሁት ብዝዎቻችሁ ስለ ይቅርታ ያለው ትርጉም አልገባችሁም አሊያም ጣቢያው እንደ ተቀላቀለ ራዲዮ ሆናችሁአል ::
የቫቲካን እና የወያኔን እሰቲ ለየት አርገን እንየው መቸም የወንጀል ትንሽም ባይኖረውም በፖለቲካ ሹኩቻ የሚሰራ ወንጀል እና በሀገር ለይ የሚሰራ ወንጀል እኩል አይደለም ::
ቫቲካኖች የጣሊያንን ጦር መርቀው ወይም በለው በለው አንድንም ዘር ሳይመርጡ መላው የኢትዮጵያንን በመርዝ እና በቦንብ ፍጅተዋል (መርዝ ) የሚለው ይሰመርበት ::
ወያኔ በኢሰባብዊነቱ እና በአምባገነንቱ ሊያስጠየቅው ይችል የሆናል እንጂ ከግራዚያኒ ጋር በምንም መመዘኛ አንወዳደረውም ደርግም ቢሆን ሻቢያም ቢሆን አናወዳደራቸውም :: ስለዚህ ግራዚያኒ በአለም አቀፍ ፍርድቤት ስንዳኘው ያኛን ጉዶች ግን በሀገራችን ፍርቤት ነው የምንዳቻቸው :.
ስለ ይቅርታ ደሞ ስንመጣ ደሞ የቅርታ በራሱ ጥፋት ማመን ነው :: ብልጡ ወያኔ ብዙ ግዜ ሰዎችን ይቅርታ በሉና እፈታለሁ ማለቱ እኮ ጥፋትን ከራስ አውርዶ በይቅርታ ተቀባዮች ላይ ማስቀመጥ ነው የኛዎቹ ቅንጅት ይቅርታ ሳይሉ በእውነት ላይ ቆመው ቢሆኑ ኖሮ ዛሬ የተለየ ነገር ተፈጥሮ ነበር :: ማንዴላ 25 አመት ሲታሰር ይቅርታ እንዲል ይልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም :.አለማለቱ በጀው :. የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም :: ከዛ በሁላ እንሆ ወያኔ ይቅርታን የህግ ማምለጫ መሳሪያ አድርጎት እስካሁን ይጠቀምበታል ምናልባት አሁን ያስቸገራቸው አንዱአለም ነው ይቅርታ ብሎ ጥፋተኝነትን በራሱ ጫንቃ ላይ ማስቀመጥ የማይፈለግ ::
ወደ ቫቲካኖችም እንምጣ እስራኤልን ወይም የበለጸጉ አገራትን ይቅርታ መጠየቁ ከሞራል አካያ ካልሆነ ለታዳጊ አገራት ግን በተለይ ለኢትዮጵያ ከይቅርታው በሁላ የሚያመጣውን መዘዝ ስለሚያቁ አገታቸው ላይ ገመድ ማስገባቱን አይፈልጉም ገፍቶ ከመጣ ግን ማምለጫ ስሌለ ከይቅርታው በፊት ድርድር ወይም ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣሉ :: አስትውሳለሁ በፈርንጅ አቆጥጠር 2010 ኦክቶቭር ላይ በድቡብ አፍሪካ መላው አለም አቀፍ የመሪዎች ስብሰባ ላይ አመሪካኖች እና አውሮፓኖች አፍሪካን በቅኝ አገዛዝ (ኮሎኒያል ) ስር ባድረጉበት ዘመን ይቅርታ ይጠይቁ ሲባል አሜሪካኖች እና አውሮፓኖች ከይቅርታው በሁላ የሚመጣውን መዘዝ ስላወቁ እንቢ አሉ ::እንቢታቸው ደሞ በሌላ ማካካሻ ለመተካት በማይነጥፍ ገነዘብ ለመተካት ሀሳብ አቀረቡ ከዚህ ሁሉ ግን በአፍሪካ በዙም ቀኝ ግዛት ይላረገች አገር ጀርመን ግን (ምናልባት ናምቢያን ይሆን ??) ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ነበረች ነገሩ ውጥረት ነበረው እርኩስ sep 11 መቶ ነገሩን ወሀ ደፋበት እንጂ ::
ያም ሆነ ይህ ይቅርታ በራሱ ትልቅ ስፍራ አለው ህጋዊ እውቅና አለው ይህ ስነድ እንደ ቀላል አተዩት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 6:47 pm    Post subject: Reply with quote

በጌታ ወንድሜ ዲጎኔ ... ኦነግ ነህ እንዴ ...? Very Happy
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 7:15 pm    Post subject: Reply with quote

ስማ ዳያስፖራ፡ የሌላን ሰው የፖለቲካ አቋም ከመለካትህ በፊት የራስህን የግንዛቤ ሃቅም አዳብር። እስከዛ ድረስ ግን ሌሎቻችን የምንጽፈው አይገባህም። ይህን አጀንዳ ስመልክቶ ቁልጭ አድርጎ ምላሽ ያቀረበልህ “እናመሰግናለን” የሚለው ሰው ነው። ስለቫቲካን ተንስቷልና አንዲት ነገር ልበልህ በርግጥ ከተጠመቅህበት ቅዠት ትድናለህ ብየ አይደለም ግን ውርድ ከራሴ በማለት እጽፍልሃለሁ።

ያኔ ቫቲካን የሞሶሎኒን ጦር መርቃ ስትሸኝ ከተልዕኳቸው አንዱ አገሪቱን ወደ ካቶሊክ ከመለወጥ አላማ ጋር ነበር። እናም እነአቡነጴጥሮስን እና እነ አቡነ -ሚካኤልን ጨምሮ በርካታ የኦርቶዶክስ አባቶች እራሳቸውን አሳልፎ ከመስጠትም በላይ ከድሉም በኋላ በጥንት ጊዜ የነበረውን የካቶሊክና የተዋህዶ ውግዝ ታደሰ። ከወያኔ ጋር የፓትሪያሪክነቱን ስልጣን ከቀኖና ውጭ የያዙት አባ ገብረ መድህን ግን ያንን ጥንታዊ የአባቶቻችንን ውግዝ ጥሰው ከቫቲካኑ ፓፓ ቡራኬ ተቀበሉ። እንደእምነትህ የዚህ ግድፈት ምንነት በውል ላይገባህ ይችላል። እኔ ግን ኦርቶዶክስ ስለሆንሁ እጅግ ትልቅ አገራዊ ጥፋት መሆኑን አቃለሁ። የአለቃ አያሌው ታምሩን የህይወት ታሪክ ስታነብ የምታገኘውም ይህኑ ነው። “ፓትሪያሪክ” የተባሉት ሰው ዝቅ ብለው ከካቶሊኩ ቡራኬ የሚወስዱበት አገር ታቅፈን ቤታችንን ሳናጸዳ ቫቲካንን እንውቀስ ?

እነአቡነጴጥሮስ ያን መሰዋትነት በሚከፍሉ ጊዜ በታቃራኒው ደግሞ የትግራይ ቀሳውስት ለግራዚያኒ ታቦት ይዘው ወጥተው በዝማሬ ያዝናኑት ነበር። እነበላይ ዘለቀ ጣሊያንን በሚዋጉ ጊዜ የትግራይ -ወያኔዎች እንቁላል ጠብሰው ለጣሊያን ያቀርቡ ነበር። ዛሬ የክህደት -ስራ ልምዳቸው ታይቶ ስልጣን ተቸሩ። እና አገሩን ለከሃዲዎች ያስረከበ ትውልድ ነው እንዴ መልሶ እጁ ላይ የሌለችው አገሩን በይቅርታ የሚያስከብር ? እሽ ቫቲካ ይቅርታ ጠየቅን እንበል እና ምን ?!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ጩጉዳ

ውሃ አጠጪ

Joined: 31 Jan 2005
Posts: 1202
Location: Studio City, Wilson Republic

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 10:07 am    Post subject: Reply with quote

ሀሀሀ ! ሀሀ ! ሀይ እነኚህ ሰዎችና ይቅርታቸው ........ ደርግም ያኔ አላወቀበትም እንጂ እነሱ አዲሳባ ሊገቡ ሲቃረቡ የይቅርታ መግለጫ ቢያወጣ ወደ መጡበት ይመለሱ ነበር ማለት ነው Laughing Laughing Laughing

- አሀ ! እናቴ አንድ ኩርኩር በላምባ የምሰራ ወፍጮ አላት ቀረጡ ቆልለውባት ያንድ ዐመት ቀረጥ ሌላ 3 አዳዲስ ወፍጮ የሚገዛ ብር ነው ብላኝ እኔም ስላምልችል አስረክብያቸውና እስቲ ወፍጯችንን ከመብላታቸው በፊት ይደፉ ብለን እየጸለይን ነበር አሁን ግን ይህ ይቅርታ ሚሉት ነገር ሳንሞክር አንቀርም :: Idea
_________________
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 7:31 pm    Post subject: Reply with quote

ብራዘር ጭጉዳ ..ይሄ እኮ በወያነ የተዘጋጀ ሰነድ አይደለም ...አያነብብን እንጂ ነፍሴ ..ወያኔን እኮ የይቅርታ ፓኖሪያ አደረከው ...ነገሮች ሁሉ እዚህ ሲጻፉ 180 ሪቨርስ ይደረጋሉ :: ለምን እንደሆነ አላውቅም :: በጣም የሚያስቀኝ ጉዳይ ደሞ ምን መሰለህ የጌታ ልጆች ይቅር መባባልን መጠየፋቸውና እንደ 7ተኛው አውሬ ይቅርታን መጥላታቸው ነው ..አይገርምህም ?? እኔ የዮሀንስ ራእይ በፊት ለማንበብ በጣም ይከብደኝ ነበር ...አሁን ግን ዋርካ መዋል ከጀመርኩ ጀምሮ ፍንትው ብሎ ተገለጸልኝ :: Very Happy ለማንኛውም ፔቲሽኑ የተዘጋጀው ያገራቸው ጉዳይ እንደ ራሳቸው ጉዳይ አድርገው የወሰዱ ኮንሰርንድ ኢትዪጵዋያን አርበኞች አሉ :: ለበአል ያልተገዙ አንተ የማታውቃቸው ነቢያቶች አሉኝ ብሎት ነበር እጊዚአብሄር ለኤልያስ :: የሽልጦ አርበኞችን አይደለም የምልህ :: አርበኝነት እኮ ዘንድሮ ረከሰ ... ባለፈው አንዱ እኔ እዚህ መጻፍ ስጀምር ነው ኦነግ ጥሪዬን ሰምቶ አቌሙን ያስተካከለው ..እኔን ስሙኝ አርበኛው እኔ ነኝ ሲል አዳመጥኩት :: እኔ ስም አልጠራም በጥይት ነው የሚበጣጥሰኝ !! Laughing ወደ ጉዳዬ ልመልስህና እንደውም አንዱ ለዚህ ጉዳይ ቅርበት ያለው ሰው እንዳጫወተኝ ባመሪካና በጣሊያን ላለው የኢትዮጵያ እምባሲ ይሄ ያገር ጉዳይ በመሆኑ እንዲገቡበት የሚገልጽ ደብዳቤ ይሄ ቡድን ደብዳቤ እንደላከ አጫውቶኛል :: ወያነን ባልሰራው ስራ አትውቀሰው :: ደሞም አታሞግሰው :: Very Happy
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 7:53 pm    Post subject: Re: ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እንድትጠይቅ ጴቲሽን ተጀመረ :: Reply with quote

አይተ ክብሮም

ቫቲካን በመስቀሏ ባርካ የመርዝ ጋዝ የተሸከመ ፋሽስትን ወደ ኢትዮጵያ ላከች ...ያንተ አጎቶች ደግሞ ታቦት ይዘው በቅዳሴ ተቀበሉት ...ነገሩ እኮ ፍጥጥ ብሎ ከፎቶ ማስረጃ ጋር ቀረብልህ ...ምን ይበጅህ አይተ ክብሮም Shocked Shocked

ፎቶዎች Shocked
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO022/AO00001541.JPG
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO009/AO00000609.JPG
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO009/AO00000612.JPG

ቪዲዮ Shocked
http://www.youtube.com/watch?v=_20tOa8C6VU

ቫቲካንን ይቅርታ ጠይቂ ስንላት ...እኔ ብቻየን ምን መጦብኝ ... እዚያ ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ ታቦት ይዘው በቅዳሴና በያሬዳዊ ዝማሜ የተቀበሏቸውም ይቅርታ ይጠይቁ ብትል ምን ልትሉ ነው Embarassed Laughing

ይህ አካባቢ ግን ጠለቅ ያለ አንትሮፖሎጂያዊና ስነ -ልቦናዊ ጥናት ሊደረግበት ይገባል እያልኩ እያሰብኩ ነው ....ምን ይመስልሃል ?

ልጅ ሞንሟናው

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
የፋሺስት ኢጣሊያን መንግስት ኢትዪጵያንና ህዝቦቿን በጋዝ መርዝ ባሰቃቂ ሁኔታ ሲጨርሱ ቫቲካን መንፈሳዊ ተባባሪ ነበረች :: ቫቲካን ከዚህም በላይ ፋሢስቶቹ ወገኖቻችን የፈጁበትን መርዝና ታንክ እንዲሁም አይሮፕላኖች ""ሚሽናችሁ ይሳካ "" እያለች ወታደሮቹን በጸሎት በመባረክ ታሰናብት ነበር :: ቫቲካን ጀርመኖች እስራኤልን በመጨፍችፋቸው ይፋ ይቅርታ ጠይቃለች :: ኢትዮጵያ ግን ከዛ የባሰ ጭፍጨፋ ተካሂዷብት ይቅርታ አልተጠየቀችም :: ባለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቫቲካን በይፋ ወጥታ ለተፈጸመው በደል እጇ አለበትና ይቅርታ እንድትጠይቅ ፔቲሽን ባለም ዙሪያ እያስፈረሙ ነው :: የሚገርመው ፔቲሽኑን ኢትዪጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ቡዙ የውጭ አገር ሰዎች በመፈረም ላይ ናቸው :: የቫቲካንን ዝምታ እንሰብራለን የሚል መልክት ላለም መንግስታት , ለሰባዊ ድርጅቶች ለተለያዩ የእምነት ተቃሞች , የተበተነውን የፊርማ ማሰባሰበያ እዚህ ያገኙታል :: ያገርዎ ጉዳይ ነውና እርሶም ለዚህ ጥሪ ምላሽ ይስጡ :: እቺን ጠቅ ::

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወንዴ _85

ኮትኳች

Joined: 25 Dec 2004
Posts: 338
Location: DownTown

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 8:01 am    Post subject: Reply with quote

ጩጉዳ እንደጻፈ(ች)ው:
- አሀ ! እናቴ አንድ ኩርኩር በላምባ የምሰራ ወፍጮ አላት ቀረጡ ቆልለውባት ያንድ ዐመት ቀረጥ ሌላ 3 አዳዲስ ወፍጮ የሚገዛ ብር ነው ብላኝ እኔም ስላምልችል አስረክብያቸውና እስቲ ወፍጯችንን ከመብላታቸው በፊት ይደፉ ብለን እየጸለይን ነበር አሁን ግን ይህ ይቅርታ ሚሉት ነገር ሳንሞክር አንቀርም :: Idea

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing / ጩጉዳ አንተ ከድሮም የዋርካ ጨው ነህ .... ዋርካ ድሮ ቀረ ለነገሩ ..... በነ ሞኒካ በነ አሰግድ ዘመን Cool Cool Cool ያሁኑ የዋርካ እድምተኛ ቀፋፊ ዝጋታም ብቻ ነው :: አቦ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5043

PostPosted: Sun Feb 26, 2012 3:40 am    Post subject: Re: ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እንድትጠይቅ ጴቲሽን ተጀመረ :: Reply with quote

ነብር ዥጉርጉርነቱን እንደማይለቅ ሁሉ ትግራይ ኢትዮጵያዊነቷን አትለቅም ::

በጊዜ ማጣት ምክንያት የፈለኩትን ያህል ለመጻፍ ባለመቻሌ እያዘንኩ ላሻቢያ የሰለሙ ሰላሜዎች በስመ -ኢትዮጵያዊነት እየገቡ ኢትዮጵያዊነቱን አንድ ጊዜ እንኴን ጠይቆ የማያውቀውን ጀግናውን የትግራይ ህዝብ ባንዳ እያሉ አውዳይ ሲቀመጡ በራሳቸው ጽሁፍ ራሳቸው ሲሲቁ አየን :: ከት ከት ከት :: የጀግና ፍሬ ማፍራት ልማዷ የሆነው የትግራይ አፈር እንደሌላው ክፍለ አገር ህዝብ ከዚህም ከዛም ያደሩ ባንዳዎች አፍርታ ይሆናል ;: ራስ ጉግሳ ሀይለስላሴን ያስታውሷል ...ክመሀል አገር እነ እከሌና እነ እከሌ ስመ ጥር ባንዳዎች እንደነበሩ እንደውም ወደ በኌላ አርበኛ ተብለው በጃንሆይ እንደተሸለሙ ታሪክ በደማቅ ቀለም ጽፎት ይገናል :: ክፉ ታሪካችንንና ገበናችንን የማውራት ባህል የለኝም :: ቤተሰቦቼ እኔን እንደዛ አላሰዱጉኝም :: ባንድ አወደ በአል ላይ ቄሶች ማህሌት በመውረዳቸው አንድ ጾታውን እንኴን ሌላ ሰው ይቅርና ራሱ እንኴን በደንብ የማያውቀው ሰው (ይቅርታ የዋርካ በግ ) በትግራይ ህዝብ ላይ የዲ ኤን ያንትሮፖሎጂ ጥናት አደርጋለሁ አለ :: የሚሉሽን በሰማሽ ዋርካ ላይ ባልወጣሽ አለ ....:: ሻቢያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ይረመሰመስማል ያለው ሰለምቴው ጥልቁ ትግራይ የባንዳዎች አገር ናት ሲል ተደመጠ :: ቀስ በቀስ የለበስከው የኢትዮጵያዊነት ካቦርት ታወልቃለህ በጩሀት አይደለም በርጋታ !! በዳበሳ አይደለም በመረጃ :: ያባ በዝብስ ካሳ አገር ... ያባ ፈንቅል ምድር የነ ግራ ካሱ ሰፈር .... ዮሀንስ በኢትዮጵያዊነቱ አንገቱን የሠጠባት አገር ምን ጊዜም በዳቦ ምስለኔዎች ኢትዮጵያዊነቷን አትነጠቅም :: እንደውም ክማይገባቸው ላይ ትነጥቃለች :: ሀሌሉያ !! መጣሁ ::
የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
አይተ ክብሮም

ቫቲካን በመስቀሏ ባርካ የመርዝ ጋዝ የተሸከመ ፋሽስትን ወደ ኢትዮጵያ ላከች ...ያንተ አጎቶች ደግሞ ታቦት ይዘው በቅዳሴ ተቀበሉት ...ነገሩ እኮ ፍጥጥ ብሎ ከፎቶ ማስረጃ ጋር ቀረብልህ ...ምን ይበጅህ አይተ ክብሮም Shocked Shocked

ፎቶዎች Shocked
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO022/AO00001541.JPG
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO009/AO00000609.JPG
http://151.1.148.223/foto/high/AO/AO009/AO00000612.JPG

ቪዲዮ Shocked
http://www.youtube.com/watch?v=_20tOa8C6VU

ቫቲካንን ይቅርታ ጠይቂ ስንላት ...እኔ ብቻየን ምን መጦብኝ ... እዚያ ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ ታቦት ይዘው በቅዳሴና በያሬዳዊ ዝማሜ የተቀበሏቸውም ይቅርታ ይጠይቁ ብትል ምን ልትሉ ነው Embarassed Laughing

ይህ አካባቢ ግን ጠለቅ ያለ አንትሮፖሎጂያዊና ስነ -ልቦናዊ ጥናት ሊደረግበት ይገባል እያልኩ እያሰብኩ ነው ....ምን ይመስልሃል ?

ልጅ ሞንሟናው

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
የፋሺስት ኢጣሊያን መንግስት ኢትዪጵያንና ህዝቦቿን በጋዝ መርዝ ባሰቃቂ ሁኔታ ሲጨርሱ ቫቲካን መንፈሳዊ ተባባሪ ነበረች :: ቫቲካን ከዚህም በላይ ፋሢስቶቹ ወገኖቻችን የፈጁበትን መርዝና ታንክ እንዲሁም አይሮፕላኖች ""ሚሽናችሁ ይሳካ "" እያለች ወታደሮቹን በጸሎት በመባረክ ታሰናብት ነበር :: ቫቲካን ጀርመኖች እስራኤልን በመጨፍችፋቸው ይፋ ይቅርታ ጠይቃለች :: ኢትዮጵያ ግን ከዛ የባሰ ጭፍጨፋ ተካሂዷብት ይቅርታ አልተጠየቀችም :: ባለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቫቲካን በይፋ ወጥታ ለተፈጸመው በደል እጇ አለበትና ይቅርታ እንድትጠይቅ ፔቲሽን ባለም ዙሪያ እያስፈረሙ ነው :: የሚገርመው ፔቲሽኑን ኢትዪጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ቡዙ የውጭ አገር ሰዎች በመፈረም ላይ ናቸው :: የቫቲካንን ዝምታ እንሰብራለን የሚል መልክት ላለም መንግስታት , ለሰባዊ ድርጅቶች ለተለያዩ የእምነት ተቃሞች , የተበተነውን የፊርማ ማሰባሰበያ እዚህ ያገኙታል :: ያገርዎ ጉዳይ ነውና እርሶም ለዚህ ጥሪ ምላሽ ይስጡ :: እቺን ጠቅ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2
Page 2 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia