WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
መርድ 09

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 May 2009
Posts: 797

PostPosted: Tue Feb 21, 2012 4:47 pm    Post subject: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

US Already Looks to Post Meles Zenawi: Indian Ocean Newsletter
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዱራሰንበት

ዋና አለቃ

Joined: 01 Apr 2004
Posts: 4079
Location: Dedessa Death Camp, Tach Birr Sheleko

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 10:15 pm    Post subject: Re: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

ሰላም ወንድም

ይህንን አዕምድ ስትከፍት ---> የራስህን አስተያዬት ብትጨምርበት ለውይይት የበለጠ ዕድል ይሰጥ ነበረ ::
እንዲሁ ያለምንም ሀሳብ ስለዘጋኸው በይዘቱ የተስማማህ ይመስላል :: አሜሪካ የኢትዮጵያ ምንም አይደለችም :: ጠላትም ወዳጅም አይደለችም ::
ለአሜሪካ ኢትዩጵያ ብትኖር ባትኖር ---ብትከበር ብትዋረድ ----ብትጎሰቁል በርሀብ ብትነድ ጉዳያዋ አይደለም :: የአሜሪካ መንግስት የሚፈልገው የልዩ ልዩ ባለሀብቶቹ ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ እንዲከበር ነው ::
አሜሪካ ሌላ ባንዳ እንድሰቅልልን ከሆነ የምንጠበቀው መቼስ ምን ይባላል በማፈሪያው ትውልድ ከማፈር በስተቀር ::

መርድ 09 እንደጻፈ(ች)ው:
US Already Looks to Post Meles Zenawi: Indian Ocean Newsletter
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ደብረብርሀን 33

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2011
Posts: 262

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 10:39 pm    Post subject: Re: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

ወንድሜ ዱራሰንበት ,

በጣም ትክክል ነህ Exclamation እኔ ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገርመኝ : ይህ የተሳሳተ የአስተሳሰብ ቅኝት ነው :: አሜሪካ ሆነች ሌሎች የምዕራብ አገሮች በየትኛውም አገር ቢሆን ከዋናው ሕዝቡ ማንንም ነገር የመጫን ፍላጎት የላቸውም :: እነሱን እንደ ፈጣሪ አምላክ ማየቱ ስህተት ነው :: የአገራችንን ዕጣ ፋንታ መወሰን እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን :: አሜሪካ እንዲህ አስባለች , ይህን ልታደርግ ነው እያልን እነሱን ከሰማይ መና እንዲያወርዱ ከመጠበቅ እራሳችን ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ Exclamation ወሳኞች እኛ እንጂ አሜሪካ ወይም እንግሊዝ አይደሉም Exclamation Exclamation

ዱራሰንበት እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወንድም

ይህንን አዕምድ ስትከፍት ---> የራስህን አስተያዬት ብትጨምርበት ለውይይት የበለጠ ዕድል ይሰጥ ነበረ ::
እንዲሁ ያለምንም ሀሳብ ስለዘጋኸው በይዘቱ የተስማማህ ይመስላል :: አሜሪካ የኢትዮጵያ ምንም አይደለችም :: ጠላትም ወዳጅም አይደለችም ::
ለአሜሪካ ኢትዩጵያ ብትኖር ባትኖር ---ብትከበር ብትዋረድ ----ብትጎሰቁል በርሀብ ብትነድ ጉዳያዋ አይደለም :: የአሜሪካ መንግስት የሚፈልገው የልዩ ልዩ ባለሀብቶቹ ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ እንዲከበር ነው ::
አሜሪካ ሌላ ባንዳ እንድሰቅልልን ከሆነ የምንጠበቀው መቼስ ምን ይባላል በማፈሪያው ትውልድ ከማፈር በስተቀር ::

መርድ 09 እንደጻፈ(ች)ው:
US Already Looks to Post Meles Zenawi: Indian Ocean Newsletter
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 12:14 am    Post subject: Re: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

ከአምስት አመት በፊት ዱራሰንበት ከዚህ በታች የጻፈውን ይጽፋል ቢባል ማን ያምን ነበር :: እኔ እስከማስታውሰው Anglo-Saxon , አሜሪካና በጠቅላላ ምዕራብያውያንን በራሱ መንገድ ዋርካ ላይ እየተፋለማቸው ነበር ::

ዱራሰንበት እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወንድም

ይህንን አዕምድ ስትከፍት ---> የራስህን አስተያዬት ብትጨምርበት ለውይይት የበለጠ ዕድል ይሰጥ ነበረ ::
እንዲሁ ያለምንም ሀሳብ ስለዘጋኸው በይዘቱ የተስማማህ ይመስላል :: አሜሪካ የኢትዮጵያ ምንም አይደለችም :: ጠላትም ወዳጅም አይደለችም ::
ለአሜሪካ ኢትዩጵያ ብትኖር ባትኖር ---ብትከበር ብትዋረድ ----ብትጎሰቁል በርሀብ ብትነድ ጉዳያዋ አይደለም :: የአሜሪካ መንግስት የሚፈልገው የልዩ ልዩ ባለሀብቶቹ ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ እንዲከበር ነው ::
አሜሪካ ሌላ ባንዳ እንድሰቅልልን ከሆነ የምንጠበቀው መቼስ ምን ይባላል በማፈሪያው ትውልድ ከማፈር በስተቀር ::

መርድ 09 እንደጻፈ(ች)ው:
US Already Looks to Post Meles Zenawi: Indian Ocean Newsletter
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 2:47 am    Post subject: Re: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

ሰላም ዱራሰንበት !

ከምን አቅጣጫ ተነስተህ ይህንን አስተያየት እንደሰጠኽ በደንብ የገባኝ ይመስለኛል :: የኔም የስጋት ምንጭ ይኼው ነው :: የነ / ፍስሀን ተንደርድሮ ወደ ፖለቲካ መግባት ተከትሎ አሜሪካ የኤግዚት ስትራቴጂ እያሰበች እንደሆነ ሰማን :: እንደገመትነው ::

ከቅንጂት ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የተስተዋለውን ነገር በድጋሚ ላንሳ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝን ሀሳብ እቋጫለሁ ::

2005 ቅንጂት ያለ ወታደራዊ ሀይል ዙሪያውን በመሳሪያ አጥሮ ሀገር እየዘረፈ ያለውን የህወሀት መንግስት ውሀ ውሀ ሲያሰኝ ; የነበረውን የህዝብ ተነሳሽነት መንፈስ እና እንደጉድ ያንሰራራውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ግምት ውስጥ በማስገባት ቅኝጂት በዚያ አይነት ሁኔታ ስልጣን ቢይዝ ኖሮ ፍጹም ናሺናሊስት የሆነ መንግስት እንደሚፈጠር አሜሪካኖቹ ቁልጭ ብሎ ስለታያቸው ህወሀትን አጥብቀው መያዝ ነበረባቸው :: በጸረ -ኢትዮጵያዊነት የተፈረጀ መንግስት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እና ከእሱ የተሻለ የሚያገለግላቸው ስለማያገኙ :: ከቅንጂት አመራሮች ግለኝነት እና ድክመት ጋር ተዳምሮ የነጮቹ እና የህወሀት ሴራ ቅንጂትን ያለ ዕድሜው ግብዐተመሬቱ ሲፈጸም አየን ::

እንደዛም ሆኖ ግን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከቅንጂት ጋር አብሮ አልሞተም :: መልኩን እየቀያየረ የነገሮችን አመጣጥ እየመዘነ ውስጥ ለውጥ ተቀጣጠለ :: ህወሀት 99 % ድምጽ አሸንፌያለሁ በሚልበት እንኳን ሁኔታ :: ጋሞው ጋምቤላው ሲዳማው አፋሩ ጉራጌው ኦሮሞው ...እናንተ ቁጠሩት በህወሀት ፖለቲካ ያልደማ እና ቅጥ ባጣ ዘረፋቸው ጥርስ ያልነከሰባቸው የለም :: ምን ይቀራል ህወሀት እና የብሄር ብሄረብ ዘፈኑ ብቻውን :: አሜሪካኖቹ ደሞ ህወሀት አንገት ውስጥ የገባው የፖለቲካ ገመድ ቀስ በቀስ እየተሸመቀቀ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ታያቸው :: ህወሀት በታነቀም ማግስት የሚነሳው ፖለቲካ ፍጹም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ታያቸው :: ህወሀትን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ይታረቃል ብሎ ማሰቡ የሚሆን መስሎ ስላልታያቸው የተሻለው ከበስከጀርባ እየተነጋገሩ የህወሀትም ሰዎች የያዙትን ይዘው ሹልክ እንዲሉ እና የፖለቲካ አብዪት በሚመስል ትይንት ሌላ ደንበኛቸውን ወደ ስልጣን ማምጣት :: አሁን ነገሮችን እየቀጣጠልኩ ሳያቸው ጉዳዮን ከጀመሩት ከወራቶችም እድሜ በላይ ሳይሆን አይቀርም :: የብርቱካን ሚዴቅሳ የፖለቲካ ባህሪ በጥቂት ሰንበቶች ተቀይሮ አሜሪካዊ የሆነበትን ምክንያት ...ሌሎች በውጭ ያሉ የቅንጂት ደጋፊ ነን የሚሉ ቡድኖችም የሚያደርጉት ሽር ጉድ ሁሉ የነ / ፍስሀ ተንደርድሮ መጥቶ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሀይል ዮናይት አድራጊ መሆን ግምት ውስጥ ሳስገባ ነገሩ እንደተባለው ህወሀት ---በተለይ ከላይ ያሉት አመራሮች ሴፍ በሆነ ሁኔታ እንደነሙባረክ ያካበቱትንም ሀብት በማያጡበት ሁኔታ ሹልክ እንዲሉ እንደፈለጉ ነው :: ክራሱ ከህወሀት ውስጥ ጭርም ያልዘረፉ (ቁጥራቸው ቢያንስም ) ሊኖሩ ስለሚችሉ እንዲህ ያለው ንግግር ስሰማ በራሱ በህወሀት ውስጥ የሚፈነዳ የርስ በርስ ጦርነት ስለሚኖር ነገሩን በከፍተኛ ሚስጥር እንደሚይዙን አንድ እና ሁለት የለውም :: የሆነ ሆኖ ግን ህወሀት ከሄደ በኍላ በለውጥ ስም ተከልለው የሚመጡት ሌሎች የአሜሪካ ደንበኞች ከሆኑ ---ምናልባት ጎሰኝነቱ ይቀርልን ከሆነ አላውቅም እንጂ በሌላ በሌላው አንስፃር ---በተለይ በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በባህል (ምናልባት በእምነትም ጭምር ) የአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያኖች አጀንዳ መራመዱ እንደማይቀር ነው ::በሌላ አንጻር ደሞ ኢትዮጵያዊ የሆነ ንቃተ ህሊና ብቅ ብቅ እያለ ነው :: ይሄ ንቃተ ህሊና ደሞ በአግባቡ ከተያዘ አና አደረጃጀቱ መልክ ከያዘ በፍጥነት ከተከላካይነት እና ከተጠቂነት ወጥቶ በህወሀትም ላይ ይሁን በሌሎች ባንዳዊ አጀንዳዎች ላይ የጥቃት ርምጃ መሰንዘር የሚችልበት አና ኢትዮጵያን ፍጹም ኢትዮጵያዊ በሆነ መልኩ ማዳን የሚቻልበት ሁኔታ አለ :: እንዲህ አይነቱ እንቅስቃሴ የሚተክለው ነገር ቢኖር ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ መንፈስ እና ብሄራዊነት ነው :: እሱ ነው የተፈራው በነጮቹ በኩል :: በነ ፊሽ እና (አሁን ደሞ በነብርቱካንንም ጭምር ) ወያኔን አስወግዶ ሌላ አስበዝባዥ መትከል :: እኛ ደሞ የሚጠቅመን ሁለተኛው አማራጭ ነው :: ብዙ ጀግና ወጣት ፀሀፍት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተነሱ ነው :: የዛኑ ያህል ታጋዮም እየተፈጠረ ይሄዳል :: ህወሀት እና ከህወሀት ወገን የሆነ በየቦታው ሰለባ የሚሆንበት ነገር ሲፈጠር ራሱ የትግራይ ህዝብ ጭምር ---አሉ የሚባሉትን የህወሀት አመራር አንገታቸውን ይዞ ለህዝብ ትግል እንደሚሰጣቸው ነው :: በዚህኛው አማራጭ ነው መገፋት ያለበት ባይ ነኝ ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::ዱራሰንበት እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወንድም

ይህንን አዕምድ ስትከፍት ---> የራስህን አስተያዬት ብትጨምርበት ለውይይት የበለጠ ዕድል ይሰጥ ነበረ ::
እንዲሁ ያለምንም ሀሳብ ስለዘጋኸው በይዘቱ የተስማማህ ይመስላል :: አሜሪካ የኢትዮጵያ ምንም አይደለችም :: ጠላትም ወዳጅም አይደለችም ::
ለአሜሪካ ኢትዩጵያ ብትኖር ባትኖር ---ብትከበር ብትዋረድ ----ብትጎሰቁል በርሀብ ብትነድ ጉዳያዋ አይደለም :: የአሜሪካ መንግስት የሚፈልገው የልዩ ልዩ ባለሀብቶቹ ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ እንዲከበር ነው ::
አሜሪካ ሌላ ባንዳ እንድሰቅልልን ከሆነ የምንጠበቀው መቼስ ምን ይባላል በማፈሪያው ትውልድ ከማፈር በስተቀር ::

መርድ 09 እንደጻፈ(ች)ው:
US Already Looks to Post Meles Zenawi: Indian Ocean Newsletter

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 4:44 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለቤቱ ..

ምንም ሁሉም የኢንዲያን ኦሺን የዘገበው ተአማኝነት አለው ባይባልም ..አንዳንድ ፍንጭ ግን ይሰጣል . Exclamation የአሜሪካኖቹ ዋና አላማ ወይም ጥቅም የኢትዮጲያ ሰራዊት ሳይበተን ...በፀረ -ሽብር ስም በምስራቅ ኢትዮጲያ ከአልሸባብ ጋር ለሚያደርጉት ጦርነት አመች መሪ ሊሆን የሚችል ማነው እንጂ ለኢትዮጲያ የህግ የበላይነትን እና ዲሞክራሲ ሊያመጣ የሚችል መሪ ብለው ትናንትም አስበው አያውቁም ...ዛሬም አያስቡም ...ነገም ማሰብ አይደለም ..አያልሟትም Exclamation እናም ያዘጋጁልንን አማራጮች እንመልከት ...
በሁለት ግሩፕ ከፍለነም ማየት እንችላለን ...ወያኔ እና የአንድነት ሀይሎች :

(1) የመለስ (የህወሀት ) ተከታዩ መሪ የሚሆነው በመለስ ዜናዊ ተጠቁሞ ...በወያኔ አባላት የተጨበጨበለት ማለትም ከወያኔ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ውስጥ የሆነ ... እናም በመጨረሻ በአሜሪካኖች የፀደቀ ሲሆን ነው :: በዚህ ግሩፕ ውስጥ ለእጩነት ከሚቀርቡት ቢያንስ የሚከተሉት ይገኛሉ ..

[b]GROUP I
1/ ቴዎድሮስ አድሀኖም
2/ አርከበ እቁባይ
3/ / ፃድቃን
4/ (/ ዘረፈሽዋል ጎላ ??) ምን ያንሳታል . Very Happy

GROUP II
ይሄ ደግሞ ጥምረት የሚባለው ክፍል ሲሆን ..
1/ ግንቦት 7
2/ ኦነግ (የነ / ከማል ገልቹ ) ልክ አሁን እየተደረገ እንዳለው ፓብሊክ ፎረም እንደ ማለት ነው ....ለዳውድ ኢብሳ እንኳን ይጠራል ግን የጎሪጥ ነው የሚያዩት የዛሬ 20 አመትም እድል ሰጥተውት ስላልተጠቀመበት ...ልክ በየአመቱ F እያገኘ እንደሚነጥር ተማሪ . Laughing በአርባ አመት ትግል ... የጦርነቱ ቀርቶ ...የፀባይ እንኳን በሰላም አብሮ መኖር -ሰርተፊኬት የሚል ወረቀት ማግኘት ያልቻለ 21ኛው /ዘመን የሰነፍ ታጋዮችች ምሳሌ ነው .. Wink መጣ ቀረ ..ቁጥር ከማሟላት ውጭ ምንም ትርፍ የለውም . Wink

GROUP III
አቶ ስዬ አብርሀ
/ ብርቱካን ሚዴቅሳ
መድረክ ..ናቸው
..በተለይ አቶ ስዬ እና / ብርቱካን ሀርቫርድ ውስጥ ገብተው እንዲማሩ የተደረገበት የራሱ ታሪክ አለው .. Rolling Eyes

GROUP IV
http://www.facebook.com/pages/Ethiopian-National-Transition-Council/304348176279629?sk=wall&filter=12
http://etntc.org/ENTC_Terms_and_Roles.html

/ ፍስሀ እሸቱ ..ይህ አቋሙም ይሁን ልዩ ሚሽኑ ወዴት ሊሄድ እንደሚችል ያልታወቀ ..እና በዲያስፖራው አማራጭ ሀይል ሆኖ ለመቅረብ እየሞከረ ያለ አዲስ ጅምር ነው . Exclamation
ታዲያ ጥያቄው ..ዲያስፖራ ከሚንቀሳቀሱት ጥምረት ከሚባለው የነ / ብርሀኑና / ከማል ገልቹን ይቀላቀላል ወይ ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው ...በኔ እምነት ፍፁም በጭራሽ አይቀላቀልም ባይ ነኝ .. Exclamation Exclamation ይህ እንቅስቃሴ ልዩ ሚሽን እንዳለው ነው የሚታየኝ . Exclamation Exclamation ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል Exclamation

አላማው በቅንጭብ ...
ENTC is in the process of organizing the Post Meles New Ethiopia conference whose primary outcome will be the launching of New Ethiopia Charter, the adoption of New Ethiopia Human Rights Declaration, development and adoption of civil activism strategies, the endorsement of transition roadmap and action plan, and the endorsement of the New Ethiopia development strategy.

The conference is planned for April 27 29, 2012 in Washington, DC, USA and delegates are invited representing Ethiopian community organizations from all cities in USA and other countries around the world, Ethiopian political parties, youth movements, civil activism movements, human rights organizations, professionals, religious organizations and others who are interested to participate in this momentous and epic Ethiopian civic tsunami. Please register by filling the guest form on www.etntc.org indicating your interest to participate in the conference. If you need further clarification please send your question(s) on the contact form on the website and we will respond promptly.እንግዲህ ስልጣን የምትመነጨው ከህዝብ ብሶት ሳይሆን ከሎቢ ይሆናል ማለት ነው ... ሁሉ ህዝብ ያለቀበት ...የሞተለት ...የተሰደደለት ...የታሰረበትን ህዝባዊ ትግል የሚወክለ ድርጅት ማን ይሆን . Question የአሜሪካንን ጥቅም ከማስቀደምና አገራችንን ከሽያጭ አትርፎ ለሚቀጥለው ትውልድ አስረካቢው ማን ይሆን . Question በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን .. Question እድሜ ይስጠን አብረን እናያለን .. Exclamation
_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 6:21 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን

ለዚህኛው ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው :: እንተ እራስህ ለዳውድ ኢብሳ የሰጠህውን F ለእነዚህ ደግሞ ምንም ውጤት ባለማምጣት double FF አሸክሞ በክብር ጥሮታ እንዲወጡ ማድረግ ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1211
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 6:23 am    Post subject: Reply with quote

አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለቤቱ ..

በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን .. Question እድሜ ይስጠን አብረን እናያለን .. Exclamation

ናፖሊዮንም አንፌቃም እንዲሁም ሌሎቻችሁ ያነሳችሁት ሀሳብ አወያይ ነው ቀጥሉበት አንድ ግን ዋነኛ ችግር ነው ብዬ የማስበው ሰላማዊ ሽግግርን ነው :: ይህ እንደ አጀንዳ መታሰብ አለበት ደቡብ አፍሪካ ዛሬ እዚህ የደረሰችው እነ ዴዝሞንድ ቱቱ ሁሉ በተሳተፉበት የእውነት አፈላላጊና የንስሀ ስብስብ ነው ::

መቸም 5-7 ሚሊየን የፓርቲ አባላት ያሉት ድርጅት በመጪዋ ኢትዮጵያ ተገቢው ቦታ ካልተሰጠው ሽግግርስ ይኖራል ወይ ነው ? እስኪ አስቡት ሰሞኑን በተከታታይ ዜና እንሰማለን አዜብ ጎላ በሽርክና እንስራ አለች .... ጄነራሎቹ ህንጻ እየገነቡ ነው ... የፓርቲ አባላት ንግድ ውስጥ በሀይለኛው እየተሳተፉ ነው የሚል ምን ማለት ነው ይህ ዜና ? መሬት ላይ ካፈሰሱት ገንዘብ ጋር ይሞታሉ ማለት እኮ ነው :: ታዲያ ለነዚህ ሰዎች ቀጣይ ህይወት ሰላማዊ መንገድ ማሰብ የለብንም ለመጪዋ ኢትዮጵያ ስንል

በደግ በሌላውም መንገድ ካያችሑት ይህ ያገር ንብረት ነው መጪዋ ኢትዮጵያ ይህ ሀብት እርሾዋ ነው ያስፈልጋታል ...

ሌላው አንፌቃ እንዳለው የብሄር ፓርቲዎች ጉዳይስ የሀይማኖት ፓርቲዎች ጉዳይስ ? እንዲሁ ትርምስምስ እንዳለ ይቀጥላል ? ለምሳሌ ኦነግ ለልጣን ቢንቀሳቀስ አማራውን ትግሬውን ደቡቡን አፋሩን ምን አርጎ ነው ? የብሄረሰብ ፓርቲዎች እና የሚወክሉት ብሄረሰብ መብት በተመለከተ ግልጽ ያለ አካሄድ መጪዎቹ የስልጣን ተፎካካሪዎች ሊኖራቸው ይገባል - አለበለዚይ እድሜ አይኖራቸውም

ይቅር ለእግዚአብሄር - የማርያም መንገድማ የግድ አስፈላጊ ነው :: አዲሶቹ ስልጣን ተረካቢዎች እንኝህን ጉዳይ በትኩረት ማሰብ አለባቸው
አበቃሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 6:45 am    Post subject: Reply with quote

Very Happy ዋው ..አስተማሪ ብትሆን በጣም ያምርብህ ነበር ..ቅቅ ውጤት ላላመጣው 40 አመቱ ታጋይ (ያውም በጦር መሳሪያ ) አንድ F ከተሰጠ .. 20 አመት ለሞላቸው (በብእር ለታጠቁ ተቃዋሚዎች ) የፖለቲካና የሲቪል ድርጅቶች FF Razz እንዳው ላፍህ እንኳን ከሳ ያለች D ብትል እኔም እቀበል ነበር .. Wink

የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን

ለዚህኛው ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው :: እንተ እራስህ ለዳውድ ኢብሳ የሰጠህውን F ለእነዚህ ደግሞ ምንም ውጤት ባለማምጣት double FF አሸክሞ በክብር ጥሮታ እንዲወጡ ማድረግ ነው ::

_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 7:20 am    Post subject: Reply with quote

በመጀመሪያ እንሰት ባነሳህው የተወሰነ እስማማለሁ :: አንተ እንዳልከው ወያኔ እንኳን ስልጣን ለማጋራትም ሀሳብ የለውም :: እኛ ጫፍ ይዘን በባዶ መዳ እራሳችንን ማጽናናት ልማድ አድርገን ይዘነው እንጂ መለስ ቢለቅ እንኳን ሌላ ጓደኛውን ወይም ዘመዱን ተክቶ ይወርዳል እንጂ ስልጣኑን አያጋራም ::

አሜሪካኖች ጥቅማቸውን ከመጣው መንግስት ሁሉ ጋር ለማስከበር ይሞክራሉ እንጂ አንተ ግባ አንተ ውጣ የሚሉ አይመስለኝም :: ለማለት ቢከጅሉ እንኳን የመለሰ ከቻይና ጋር በያዘው ፍቅር ምክንያት እንደማይሰማቸው ያውቃሉ ::

ተቋዋሚዎች ለውጥ ምዕራብያውያን ያመጡልናል ብለው ለስልጣን ድልደላ ባይዘጋጁ መልካም ይመስለኛል :: ወያኔ የሚወድቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ተተባብረው ሲታገሉ ነው :: መተባበሩ እውን እስኪሆን ድረስ ከኑሮ ውድነት በስተቀር ቢያንስ በኢኮኖሚው መስመር የሚጠበቅበትን እያደረገ ስለሆነ የሚነቀንቀው ነገር ያለ አይመስለኝም ::

እውነት ለመናገር ይህ የስለላ ተብሎ የቀረበው ያሬድ ጥበቡ ጽሁፍ የተወሰደ እና ተቋዋሚዎች እንዲህ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ የሚልለውን ከመዘገብ የዘለለ ምንም ተጨባጭ አዲስ ኢንፎርሜሽን የለውም ::

አንፌቃ ለዳውድ ኢብሳ ክፍት የሆነው ሜዳ 20 አመት ባከኑ ላልካቸው ሰዎችም ክፍት ነበረ :: እነሱ ያዋጣናል ባሉት መንገድ ተጓዙ :: እንዴት ተጓዙ የሚለው የግለሰቦቹ /ድርጅቶቹ ምርጫ ነው :: ዋናው ቁም ነገር 20 አመት ታገልን ያሉት ውጤቶ ዜሮ መሆኑ ነው :: በነገራችን ላይ ስለ ግሬድ አሰጣጥ የረሳህ አልመሰለኝም :: ለምሳሌ ማለፊያው 65% ከሆነ 64 ያገኘውም 0 ያገኘውም ተማሪ የሚያገኙት F እንደሆነ አትርሳ :: የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ የሚባል ምክንያት አይሰራም ::አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው:
Very Happy ዋው ..አስተማሪ ብትሆን በጣም ያምርብህ ነበር ..ቅቅ ውጤት ላላመጣው 40 አመቱ ታጋይ (ያውም በጦር መሳሪያ ) አንድ F ከተሰጠ .. 20 አመት ለሞላቸው (በብእር ለታጠቁ ተቃዋሚዎች ) የፖለቲካና የሲቪል ድርጅቶች FF Razz እንዳው ላፍህ እንኳን ከሳ ያለች D ብትል እኔም እቀበል ነበር .. Wink

የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን

ለዚህኛው ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው :: እንተ እራስህ ለዳውድ ኢብሳ የሰጠህውን F ለእነዚህ ደግሞ ምንም ውጤት ባለማምጣት double FF አሸክሞ በክብር ጥሮታ እንዲወጡ ማድረግ ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 7:49 am    Post subject: Reply with quote

የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ ():
Quote:
ለምሳሌ ማለፊያው 65% ከሆነ 64 ያገኘውም 0 ያገኘውም ተማሪ የሚያገኙት F እንደሆነ አትርሳ :: የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ የሚባል ምክንያት አይሰራም ::

Very Happy ነገርኩህ እኮ ...በጣም ዋው የተባል ግሬድ ሰጭ ነህ ...64% ያገኘ ተማሪ 0 ሲሰጠው አላየሁም ..ሲሆን D ነው እንጂ ...የግሬድ ነገር ካመታህ ...እነደየአገሩ ይለያያል .. አንድ ወጥ አይደለም Exclamation http://en.wikipedia.org/wiki/Grade_ and click on Grade (education) under In education
የኔ ጥያቄ እንዴት አድርገህ ሙሉ ትጥቅ እና የአርባ አመት ልምድ ያለው ..በአንድ ወቅት ለንደን ውስጥ ከተደራዳሪዎች አንዱ የነበረውን ድርጅት ...ምንም ትጥቅ ከሌለው .. 20 አመት ካልሞላው ሰላማዊ ታጋይ ጋር ማወዳደርህ ብቻ ሳይሆን ..የግሬድ አሰታጥህ . ስለገረመኝ ነው ....አሁንም ከምር ዋው የሚያሰኝ ነው . Razz አንተ ግን ቀስ ብለህ ሽል አልክና ሰለ 65% ማውራት ጀመርክ . Very Happy ስማ ...እንኳን የምዬ መቀነት ...የሻቢያም አደናቅፎኝ አያውቅም . Laughing
_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ስሙ ይናገር

ዋና ኮትኳች

Joined: 14 Mar 2008
Posts: 695

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 10:41 am    Post subject: Reply with quote

አይ አንፌቃ አንዲያው የመስልሀል እንጂ ነገሮች አንተ እንደምታያቸው እየሔዱ እንዳልሆኑ ልንገርህ :: የኦእነግን 40 አመት የትግል ተሞክሮ እንዲህ እያንቋሸሽክ ትዘልቀዋለህ ? እኔ ደግሞ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ግሬድ ስጥ ብትለኝ B የምሰጠው የኦነግ ነው ምክንያቱም አቺቭ ያደረገውን ከሆነ የምናወራው እርሱም ብቻ አይደለም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጆከሩን ቦታ ይዞ ያለው ኦነግ ለመሆኑ ፖለቲካውን በሚገባ ከተረዳህና በስሜት የምትጋልብ ካልሆንክ ታያለህ በመሰረቱ አሜሪካ በሀገራችን ፖለቲካ የመወሰን ብቃቷ እጅግ ግዙፍ ቢሆንም ወያኔ ልክ አዝማሚያውን እንዳገኘ ቁሞ የሚጠብቅ አይመስለኝም ታዲያ ሊያደርጋቸው ከሚችለው ነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹ
1. የፖለቲካ ምህዳሩን ማወሳሰብ የይዘት ለውጥ ሳይሆን ሳይሆን ቴክኒካዊ ለውጥ ማድረግ
2. ኦነግን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለድርድር ማቅረብ በእኔ እመንት ደግሞ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከለለው ኦነግ ሊደራደር ይችላል
3. 99.6 ማሸነፉን ይተውና ለማያሰጉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቂት ወንበሮችን ይለቅላቸዋል
4. ነጻዋንና ዲሞክራሲያዊት ትግራይን አንቀጽ 39 ጠቅሶ ይገነጠላል እንግዲህ ያንንም ሲያደርግ ቢያንስ ኢሳያስን ወይ በእርቅ ወይም በጉልበት ያወደውና ነው እንግዲህ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ምክንያቶችና የፖለቲካ መስመሮች ይዞ አሜሪካንን ተቀምጦ ይጠብቃል ማለት የማይመስል ነው :: ብርሀኑም ሆነ አዲሱን የፖለቲካ ሰው የዩኒቲ ኮለጅ መስራቹን ማለቴ ነው አስታጥቆ ወያኔን መማሸነፍ የሚያበቃ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ታደርጋለች ብሎ ማሰብ በራሱ የዋህነት ነው ሰለዚህ በዛ በኩል ማሰቡ ትንሽ ሁኔታዎችን ካለማገናዘብ የሚመነጭ ነው በመሰረቱ አሜሪካ ምን ጎድሎባት ነው ወያኔን ለማንሳት የምትገደደው ? ይህንንም ነግር ማንሳቱ ተገቢ ነው መቸም ለኢትዮጵያ ህዝብ አስባ ነው እንደማትሉ አስባለሁ ቅቅቅቅቅ ወደድንም ጠላንም ወያኔ ለፍጻሜው ጦርነት እየተዘጋጀ ነው በለስ ቀንቶት ካሸነፈ ኤርታራን አስገብሮ ትጋራይ ትግሪኝን ይመሰርታል ያም ቢሆን ደግሞ የተጠነከረችና አንድነቷን የምትጠብቅ ኢትዮጵያን አስቀምጦ አይሔድም ምክንያቱም የተጠናከረች ኢትዮጵያ ነገ እንደምታጠፋው ያውቃልና ስለዚህ በህገመንግስቱ እንዳስቀመጠው ኦሮሚያን ለኦሮሞ ሰጥቶ አፋርን ይዞ ይሔዳል አማራ ብቻውን ኤርትራንና ትጋራይን ወግቶ ድል እንማያደርግ ያውቃልና ሀግሪቷን በትኗት ይሔዳል አሁን ያላደረገበት ዋናው ምክንያት ኤርትራ ናት ካልሆነ እንደ ገና ዳቦ ካላይና ከታች ሊቃጠል ነው የትግራዩን ካደረገ ቦኃላ የቀረውን የቤት ስራውን ይሰራል በዚህስ መንገድ አይታችሁታል ወይ ? ወይስ የማየት ፍላጎቱን የላችሁም ቅቅቅቅቅቅ አንድም ሰው ይህንን ያላየበትን ምክንያት ሳስብ ይገርመኛል ቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
God is Great
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 7:08 pm    Post subject: Reply with quote

በዚህ ጉዳይ ላይ ያለህን አቋም መረዳት ተስኖኛል :: / ፍስሀ ባለፈው ኢንተርቪው ላይ የተናገረው አንዲት ነጥብ ብቻ ነበረች ጎልታ የምትታየው :: ፍላጎታቸውና አላማቸው ሰላማዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም እንደሆነ ነበር ያወራው :: ሌላ የፖለቲካ ቃላት ሲያነሳ እንኳን አልሰማሁትም :: ነገር ግን አንተም ከነዚህ ከተመሰከረላቸው ከብቶች ጋር ሆነህ ስጋትህን ስትሞነጫጭር ነበር :: ዛሬ ደግሞ በከፊል ደግ የሚመስል ነገር ጽፈሀል :: ምንድን ነው ነገሩ ? በእነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ምን የተለየ መረጃ አግኝተህ ይሆን ?

የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው እንደተባለው ሁሉ በድህረ -ወያኔዋ ኢትዮጵያ የሚመሰረት መንግስት ያለ አንዳች ደም መፋሰስ መሆን አለበት :: ለዚህ ደግሞ ከሁሉ አስቀድመን እነ / ፍስሀን ዕድል ብንሰጣቸው ነው የሚመረጠው :: ቢያንስ ብዬ የማምነው :: የወያኔ ልሂቃን የያዙትን ይዘው በሰላም ይውጡ አይውጡ አይደለም እኔን የሚያስጨንቀኝ :: ንጹሁ ዜጋ ደሙን ሳያፈስባት አዲስ ስርዓት የሚመሰርትባት ኢትዮጵያ ማየት ነው የሚያስጨንቀኝ :: እንደ ናፖሊዮን አይነት ከብት በስሜት እየተነዳ የሚደነፋ ውርጋጥ ይህን አይመኝም :: ምኞታቸው አገር ተበጣብጣ : የተከፈለው መስዋእትነት ተከፍሎ ወያኔዎችን (እኛን ጨምሮ ) በደም መበቀል ነው :: አንዳንዴ ያንን ሁላ መሳሪያ ተኝቶበት ለመታረድ ተዘጋጅቶ የሚጠብቃቸው እየመሰላቸው ይሆን እላለሁ ?

ለማንኛውም ስለ ሰላማዊ የሽግግር መንግስት ሊኖረን የሚገባ አስተሳሰብ ከምን አንጻር መቃኘት እንዳለበት ጠቁሜ ውልቅ ልበል ::

ፈዳይት --- የሚባል የደደቢት ፊልም
ፋዳይ -ሕነ --- የሚባል የፕሮፓጋንዳ ቱል
ሕዲኡ ዘይፈዲስ ወዲ አድጊ --- የሚባል ህዝባዊ ይትብሀል (ተረትና ምሳሌ )

ምን ማለት እንደሆኑ : ለምን እንደሚጠቅሙ : ከዚህ በፊት ማን , እንዴት , ለምን እንደተጠቀመባቸው ወዘተ ለማጥናት ሞክሩ Rolling Eyesእንሰት እንደጻፈ(ች)ው:
አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለቤቱ ..

በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላለፈው 20 አመት ሲፋለሙ የነበሩ የፖለቲካ እና የሲቪል ድርጅቶችስ ሚና ምን ይሆን .. Question እድሜ ይስጠን አብረን እናያለን .. Exclamation

ናፖሊዮንም አንፌቃም እንዲሁም ሌሎቻችሁ ያነሳችሁት ሀሳብ አወያይ ነው ቀጥሉበት አንድ ግን ዋነኛ ችግር ነው ብዬ የማስበው ሰላማዊ ሽግግርን ነው :: ይህ እንደ አጀንዳ መታሰብ አለበት ደቡብ አፍሪካ ዛሬ እዚህ የደረሰችው እነ ዴዝሞንድ ቱቱ ሁሉ በተሳተፉበት የእውነት አፈላላጊና የንስሀ ስብስብ ነው ::

መቸም 5-7 ሚሊየን የፓርቲ አባላት ያሉት ድርጅት በመጪዋ ኢትዮጵያ ተገቢው ቦታ ካልተሰጠው ሽግግርስ ይኖራል ወይ ነው ? እስኪ አስቡት ሰሞኑን በተከታታይ ዜና እንሰማለን አዜብ ጎላ በሽርክና እንስራ አለች .... ጄነራሎቹ ህንጻ እየገነቡ ነው ... የፓርቲ አባላት ንግድ ውስጥ በሀይለኛው እየተሳተፉ ነው የሚል ምን ማለት ነው ይህ ዜና ? መሬት ላይ ካፈሰሱት ገንዘብ ጋር ይሞታሉ ማለት እኮ ነው :: ታዲያ ለነዚህ ሰዎች ቀጣይ ህይወት ሰላማዊ መንገድ ማሰብ የለብንም ለመጪዋ ኢትዮጵያ ስንል

በደግ በሌላውም መንገድ ካያችሑት ይህ ያገር ንብረት ነው መጪዋ ኢትዮጵያ ይህ ሀብት እርሾዋ ነው ያስፈልጋታል ...

ሌላው አንፌቃ እንዳለው የብሄር ፓርቲዎች ጉዳይስ የሀይማኖት ፓርቲዎች ጉዳይስ ? እንዲሁ ትርምስምስ እንዳለ ይቀጥላል ? ለምሳሌ ኦነግ ለልጣን ቢንቀሳቀስ አማራውን ትግሬውን ደቡቡን አፋሩን ምን አርጎ ነው ? የብሄረሰብ ፓርቲዎች እና የሚወክሉት ብሄረሰብ መብት በተመለከተ ግልጽ ያለ አካሄድ መጪዎቹ የስልጣን ተፎካካሪዎች ሊኖራቸው ይገባል - አለበለዚይ እድሜ አይኖራቸውም

ይቅር ለእግዚአብሄር - የማርያም መንገድማ የግድ አስፈላጊ ነው :: አዲሶቹ ስልጣን ተረካቢዎች እንኝህን ጉዳይ በትኩረት ማሰብ አለባቸው
አበቃሁ

_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዱራሰንበት

ዋና አለቃ

Joined: 01 Apr 2004
Posts: 4079
Location: Dedessa Death Camp, Tach Birr Sheleko

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 8:54 pm    Post subject: Re: አሜሪካ ከአቶ መለሰ በኍላ የሚለውን እያጠናች ነው ION Reply with quote

የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው:
ከአምስት አመት በፊት ዱራሰንበት ከዚህ በታች የጻፈውን ይጽፋል ቢባል ማን ያምን ነበር :: እኔ እስከማስታውሰው Anglo-Saxon , አሜሪካና በጠቅላላ ምዕራብያውያንን በራሱ መንገድ ዋርካ ላይ እየተፋለማቸው ነበር ::

አይይይይይ ----አሜሪካዊ ተሁኖ ተሙቶ በምድር ላይ ተወዳዳሪ የሌላት የነፃነት ተምሳሌት የትርፍርፍ ሀብት ኑሮ እንደጅረት ለሚፈስባት አገርህ አሜሪካ ተከራካሪ ጠበቃ ካንተ በላይ ላሳር ብለህ እራስህን በአሜሪካዊ አርበኝነት ከማንም ከምንም በላይ ሹመህ ልብህ ወልቆ ሞተ አይደል !?

Code:
አሜሪካ ፍርፋሪዋን እየደነቆለ የሚጮህላት ግብዳ ግብዳ ውሻ በምድረ -አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ተጋድሞ በልቶ በማስበላት ላይ የተሰማራ ገልቱ መቼ ቸገራት !?

የአንተን ነገር ከየት ጀምሬ የት እንደምቋጨው አላቅም :: አንዴ ኢትዮጵያዊ አርበኝነት ሳዋ መግባት ነው እያልህ ስትደነፋ ኖረህ ---አሁን ደግሞ የባዳዎችን ቃል ነጥቀህ ልማታዊ ዲሞክራት ሆነህ ልብ ታደርቃለህ :: ስትፈልግ ደግሞ በአሜሪካዊ አገር ወዳድነት የዋርካ ስዩም ሆነህ አረፍኸው -----ሰውዬው እንኳን በዚህች ምድር ከሞትህም ወዲያ ነፍስህ አታርፍም :: ከራስህ የምትታረቅበት ሰላም አግኝ !

ሰው በዳቦ ብቻ አይኖርም ይላል መጽሀፉ ---- በእኔ እምነት ሰው ለዳቦ ብቻ አይኖርም ባይ ነኝ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዞብል 2

አለቃ

Joined: 30 Jan 2004
Posts: 2031

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 6:17 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወንድም ዱራሰንብት የዘመኑ ጭንጋፍን ደህና አርገህ ነው ያገባህለት Razz ኢፒፒ (የአርበኞች ግንባር ) እያለ ባደነቆረን ማግስት የኢትዮጵያ ባንዲራ አስመራ ሳባ ስታዲዮም ሲረገጥ ቪዲዮውን በዓይናችን እያየን አልተረገጠም እያለ ሲያስተባብል የነበረ ውርጋጥ ሀማሴን ነበር Razz

የተወረሰበት ንብረት ከተመለሰለት በኍላ ልማታዊ ሀማሴን ሆኖ ወያኔ ልማታዊ ነው እያለ ያቀረሽብን ጀመር Evil or Very Mad ከሁሉ ደግሞ የመሬትና የብሄረሰብ ጥያቄ የኮሚኒዝም ነው የሚለው የድንቁርና የሸሸው ደንቆሮ መደምደሚያ ሀሳቡ Razz Laughing Laughing

በል ዱራው ሰላም ሁን Exclamation Exclamation

ዞብል ከአራዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia