WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አዲሱ የሻዕቢያ ቡችሎች የዘረፋ ስልት በኢትዮጵያ

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ከስደተኛው

ኮትኳች


Joined: 25 Sep 2006
Posts: 258
Location: zxcvb

PostPosted: Tue Feb 14, 2012 10:03 pm    Post subject: አዲሱ የሻዕቢያ ቡችሎች የዘረፋ ስልት በኢትዮጵያ Reply with quote

የወያኔ መንግስት የኢትዮ -ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ የመለስ ዜናዊ እናትን ጨምሮ፣ ከወያኔ ባልስልጣናት ጋር ስጋዊም ሆነ ጥቅማዊ ትስስር ያላቸው ጥቂት ኤርትራውያን ተወላጆች ብቻ ሲቀሩ ሌሎች በውድም ሆነ በወቅቱ በነበረው ተጽእኖ በግድ በሪፈረንደሙ ላይ ድምፃቸውን የሰጡ ኤርትራውያን ቤት ንብረታቸው እንዲወረስ ተደርጎ ከያሉበት ተለቃቅመው በመጋዝ እያለቀሱ በጭነት መኪና ሳይቀር እንደ እቃ ታጭቀው ከአገር መባረራቸው ይታወሳል።
በወቅቱ እንሞታለን እንጂ ወደ ዔርትራ አንሄድም በማለት ከተጫኑበት መኪና ላይ ያለአግባብ ለመውረድ ሲሞክሩ አደጋ ደርሶባቸው ተፈጥፍጠው ሕይወታቸው ያለፈ ኤርትራውያን ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በርግጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወቅቱ አብሮአቸው ማንባቱና ማልቀሱ ምንጊዜም የሚዘነጋ አይደለም።
በሁለቱ ሰይጣናዊ መንግስታት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ በተጫረው ጦርነት ከሁለቱም በኩል ያለቀው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የሰው ሕይወት እንዳለ ሆኖ፤ በኢትዮጵያ በኩል በጦርነቱ ላይ ተማርከው የነበሩ ከፍተኛ የሻእቢያ የጦር አዛዦች በምህረት ሲለቀቁ፤ በምትኩ በሻእቢያ እጅ የወደቁትን ኢትዮጵያውያን ምርኮኞችን ለማስለቀቅ የወያኔ መንግስት ምንም አይነት ጥረት ሲያደርግ አላየንም። በዚህ በኩል በሕይወት መኖር አለመኖራቸውን እንኳን ለማረጋገጥ ያልተቻለው የጀግናው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ / በዛብህ ጴጥሮስ ነገር በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ እስካሁን እያመረቀዘ ያለ ቁስል መሆኑ አይካድም። እንዲያውም የወያኔው መንግስት የእኝህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች አዲስ አበባ ውስጥ ይኖሩበት የነበረው የመንግስት ቤት ልቀቁ እስከማለት የደረሰ ወራዳና ግፈኛ ስርዓት ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ አገሩ መብቱን ሁሉ ተገፎ ከባርነት ሊቆጠር በሚችል መልኩ በግፍ እየተገዛ ነው ያለው። የነጮቹ፤ የህንድና የቻይና ተወላጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው መብት ሲገርመን፣ ትናንት ኢትዮጵያውያን አይደለንም ብለው የራሳቸው መንግስት አቋቁመው የተለዩን ኤርትራውያንም ዛሬ ከኢትዮጵያውያን የበለጠ መብት ተጎናጽፈው ደሃዋን አገራችንን እየቦጠቦጧት ይገኛሉ። በርግጥ የወያኔ ታላላቅ መሪዎች፣ በተለይም ስብሃት ነጋ እና መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ይበልጥ በሚባል መልኩ የኤርትራ ጉዳይ አብዝቶ እንደሚያስጨንቃቸው በተደጋጋሚ በግልጽ ነግረውናል።
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቂ የመማር እድል ሳይኖራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ በነፃ እንዲማሩ እድል ተሰጥቷቸዋል፤
እንደማንኛውም ዜጋ (እንዲያውም በበለጠ መልኩ ) ኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውንም የፈቀዱትን ስራ ሰርተው የመኖር መብት ተጎናጽፈዋል። በዚህም የተነሳ “ኤርትራ የግል፤ ኢትዮጵያ የጋራ” ብለው የተነሱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኤርትራውያን ወደኢትዮጵያ እየፈለሱ በመግባት ላይ ናቸው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በጦርነቱ ወቅት ቤት ንብረታቸውን ተቀምተው ከአገር የተባረሩት፤ ኤርትራውያን “አሚቼ”ዎች የተወረሰባቸው ንብረት እንዲመለስ የወጣውን መመሪያ ተከትሎ በየስደት አገሩ ያሉትን ጨምሮ በርካታ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ በመግባት ላይ ናቸው። አብዛኞቹ ታዲያ የተመለሰላቸውን ንብረት “ቸብ ! አድርገው ገንዘቡን ይዘው መውጣት ስለማይችሉ እዚያ በሚገኙ ወኪሎቻቸው ስም አስቀምጠው በመመለስ እዚህ እኔ የምኖርበት አገር ላይ እንዲያውም በግልጽ ወደኢትዮጵያ ገንዘብ መላክ ስትፈልጉ ንገሩን ማለት ጀምረዋል። እዚህ በዶላር ገንዘባቸውን ተቀብለው አገር ቤት የሚገኘው ወኪላቸው ምንዛሪውን ለተላከላቸው ሰዎች ይሰጥላቸዋል ማለት ነው። “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” ማለት ይህም አይደል ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከስደተኛው

ኮትኳች


Joined: 25 Sep 2006
Posts: 258
Location: zxcvb

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 11:21 pm    Post subject: ታማኝ በየነ ዘርህ ይባረክ !! Reply with quote

Ethiopians ask Eritrea to release fighter pilot

WASHINGTON, DC - Tamagn Beyene, a prominent Ethiopian human rights activist, has asked Eritrean President Isaias Afwerki to release Col. Bezabih Petros, a senior Ethiopian fighter pilot who was captured by Eritrean forces when his MiG-21 fighter interceptor was shot down during the start of the 1998-2000 War.
The audience expressed full support for Tamagne's request by according the activist a standing ovation. This is the first official request from the Ethiopian Diaspora for Asmara to release the pilot jailed since 1998. http://ethiomedia.com/broad/3544.html
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia