WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እነማን ናቸው ?
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወጥመድ

ኮትኳች

Joined: 11 Mar 2005
Posts: 284
Location: Semen Walta

PostPosted: Thu Mar 26, 2009 8:12 am    Post subject: የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እነማን ናቸው ? Reply with quote

ሰላም ወገኖች !!

በኢትዮጵያ ውስጥ 70-80 የሚደርሱ ብሔር ብሄረሰቦች እንዳሉ ከብዙ አቅጣጫ በየቀኑ እሰማለሁ ::

ነገር ግን የነዚህ ብሄረሰቦች ስም እነማን እንደሆኑና የት እንደሚኖሩ አጠቃሎ በጽሁፍ ያቀረበ አላየሁም ወይንም ማግንገት አልቻልኩም :: በመሆኑም የዋርካን ታዳሚ እርዳታ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ :: ለማወቅ የምፈልገው ነገር :

1. የብሄረሰቡ ስም --

2. የት አካባቢ እንደሚኖሩ ? ወይንም በየትኛው ክልል ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጻችሁ ብትጽፉልኝ ለትብብራችሁ በጣም አመሰግናለሁ ::

ወጥመድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 26, 2009 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ወጥመድ የከፈትከው ርዕስ የሊቃውንትን ጭንቅላት ሲበጠብጥ የኖረው ነው ::ምክንያቱም

1)የኢትዮጵያ ካርታ በመቀያየሩ

2)ብሔረሰቦች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የአንዳንዶቹ የቀድሞ መኖሪያ በትክክል አለመታወቁ ::

3)አንድ ብሄረሰብ ይህንን መጠሪያ ለማግኘት ምን ማሟላት እንዳለበት በግልፅ አለመታወቁ ::

4)አንዳንድ ብሄሮች ቋንቋቸውን ረስተው በሌላ ብሄር ቋንቋ መዋጣቸው ::
እና ሌሎችም እዚህ ላይ ያልጠቀስኳቸው ምክንያቶች ይኖራሉ ::እኔ በበኩሌ ግን ወደ ሰባሦስት ስሞች ከተለያዩ ምንጮች ሰብስቤ ፅፌአለሁ (81 ነበር የፃፍኩት የኤርትራዎቹ ስምንት ወይም ዘጠኝ ያቀነሱ በፊት )
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
የስሙኒሎሚ

ውሃ አጠጪ

Joined: 01 Jul 2008
Posts: 1215

PostPosted: Fri Mar 27, 2009 1:13 am    Post subject: Re: የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እነማን ናቸው ? Reply with quote

አንተ ለመሆኑ ማነህ , የተረገምክ ወያኔ ትሆን ? ለምን ርእሱን የኢትዮጵያ ጎሳዎች ... አላልከውም , are you poisoned with the ferenji/woyane ethnic ideology which was created to destroy Ethiopia,ድንጋይ ራስ ,

ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ብሄር ብቻ ነው ያለው !

ወጥመድ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወገኖች !!

በኢትዮጵያ ውስጥ 70-80 የሚደርሱ ብሔር ብሄረሰቦች እንዳሉ ከብዙ አቅጣጫ በየቀኑ እሰማለሁ ::

ነገር ግን የነዚህ ብሄረሰቦች ስም እነማን እንደሆኑና የት እንደሚኖሩ አጠቃሎ በጽሁፍ ያቀረበ አላየሁም ወይንም ማግንገት አልቻልኩም :: በመሆኑም የዋርካን ታዳሚ እርዳታ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ :: ለማወቅ የምፈልገው ነገር :

1. የብሄረሰቡ ስም --

2. የት አካባቢ እንደሚኖሩ ? ወይንም በየትኛው ክልል ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጻችሁ ብትጽፉልኝ ለትብብራችሁ በጣም አመሰግናለሁ ::

ወጥመድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወጥመድ

ኮትኳች

Joined: 11 Mar 2005
Posts: 284
Location: Semen Walta

PostPosted: Fri Mar 27, 2009 7:14 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ወጥመድ የከፈትከው ርዕስ የሊቃውንትን ጭንቅላት ሲበጠብጥ የኖረው ነው ::ምክንያቱም

1)የኢትዮጵያ ካርታ በመቀያየሩ

2)ብሔረሰቦች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የአንዳንዶቹ የቀድሞ መኖሪያ በትክክል አለመታወቁ ::

3)አንድ ብሄረሰብ ይህንን መጠሪያ ለማግኘት ምን ማሟላት እንዳለበት በግልፅ አለመታወቁ ::

4)አንዳንድ ብሄሮች ቋንቋቸውን ረስተው በሌላ ብሄር ቋንቋ መዋጣቸው ::
እና ሌሎችም እዚህ ላይ ያልጠቀስኳቸው ምክንያቶች ይኖራሉ ::እኔ በበኩሌ ግን ወደ ሰባሦስት ስሞች ከተለያዩ ምንጮች ሰብስቤ ፅፌአለሁ (81 ነበር የፃፍኩት የኤርትራዎቹ ስምንት ወይም ዘጠኝ ያቀነሱ በፊት )

ሰላም ዘርዓይ ደረስ
ከላይ ያቀረብካቸው ነጥቦች ሁሉም ትክክል ናቸው :: ነገር ግን ብዙ ችግሮች ቢኖሩም ያለውን እንደተገኘ ሕዝብ እንድያውቀው ማደርጉ አስፈላጊ ይመስለኛል ::

አንተ እስከ 81 የሚደርሱ ከሰበሰብክ ታዲያ ምንቀረው አሉ የሚባሉትም እኮ ከዚህ የሚበልጡ አይመስለኝም ::

እና ሁላችንም እንድንማርበት ወይ እዚሁ ዋርካ ላይ ወይንም በግል አድራሻ ብትጽፍልኝ በጣም አመሰግናለሁ ::

እኔም በበኩሌ 4 ነገሮችን መሰረት ባደረገ ከዚህም ከዚያም እየቃረምኩ ነው ::
ማለትም

1.የብሔረሰቡ ስም

2. የት አካባቢ እንደሚኖሩ

3. የብሔረሰቡ የቋንቋ ስም

4. በቁጥር ስንት እንደሚደርሱ ( ብዛታቸው ) በመመስስትረት ለራሴ እውቀት እንዲረዳኝ እያጠራቀምኩት ነው ::

አንተም ያለህን ጀባ በለኝ :: ለትብብርህም በጣም አመሰግናለሁ ::

ወጥመድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Mar 29, 2009 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወጥመድ :-

ጉዳዩ ቀላል እንዳልሆነ ካሁኑ የተረዳኸው ይመስለኛል ::የስሙኒ ሎሚ ያለው በከፊል ያስኬዳል ::ብሔር Nation የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል የሚተካ ስለሆነ ኢትዮጵያ አንድ ብሔር ብቻ ነው ሊኖራት የሚችለው ::እንደ አማራጭ ያቀረበው ጎሳ ግን ለምንፈልገው ጉዳይ አይሆንም ::ምክንያቱም ለምሳሌ በኦሮሞ ሥር ብቻ የሚጠቃለሉ ብዙ ጎሳዎች አሉና ነው ::በነገራችን ላይ ጎሳ ኦሮምኛ ነው ::ታዲያ ዝርዝሩን ከመጀመራችን በፊት በመጠሪያው ላይ ብንስማማስ ::

1)ብሔር 2)ብሔረሰብ 3)ህዝብ 4)ነገድ 5)ማህበረሰብ 6)ቤት 7)ጎሳ ወይስ ሌላ ?

በነገራችን ላይ ዝርዝሩን ለማቅረብ ቀላል ሆኖ አልገኘሁትም ::በተለይ ኦሪጂናል ቦታቸውን በሚመለከት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ስሙ ይናገር

ዋና ኮትኳች

Joined: 14 Mar 2008
Posts: 692

PostPosted: Mon Mar 30, 2009 1:19 am    Post subject: Reply with quote

አንተ ለመሆኑ ማነህ , የተረገምክ ወያኔ ትሆን ? ለምን ርእሱን የኢትዮጵያ ጎሳዎች ... አላልከውም , are you poisoned with the ferenji/woyane ethnic ideology which was created to destroy Ethiopia,ድንጋይ ራስ ,

ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ብሄር ብቻ ነው ያለው !

ስማ እንጂ ከላይ የጠየከውን ጥያቄ አንተ ብትጠየቅ መልስ ምን ይሆን ?
ቅቅቅ አንዱን ብሔር ንገረን እስቲ እትዮጵያ ውስጥ አለ ያለከን አንድ ብሔር ካልክማ እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ማለት አይገባህም ወይስ አንተ የምትጠራት ኢትዮጵያ ብዙዎቻችን የማናውቃት ናት ? አማራ ብለህ እንዳታርፈው ቅቅቅቅቅቅ
እንኳንስ ዛሬ በፈደራሊዚም ስርአት በደርጉም ዘመን ጎሳ አይባልም ነበር ከላይ አንድ ወንድማችን ለማለት እንደሞከረው በአንድ ብሔረሰብ ወስጥ ብዙ ጎሳዎች አሉ ከላይ 81ዱን ይዣለው ያልከን ወንድማችን ቀጥልና እንወቃቸው እኔ በምእራቡ አካባቢ ሰፍሮ የሚኖሩትን አንድ 12 ብሔረሰቦች አውቃለሁ ያንተ ግን የተሟላ ስለሆነ እንዳይደጋገም አንተው ጀምርልን ካልሆነ የቀሩትን እያየን እንጨርሰዋለን
_________________
God is Great
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትብቃ

አዲስ

Joined: 22 Jul 2008
Posts: 18

PostPosted: Mon Mar 30, 2009 2:11 am    Post subject: Reply with quote

ስሙ ይናገር እንደጻፈ(ች)ው:
እንጨርሰዋለን
Question

እናጨራርሰዋልን :-ተብሎ :ይነበብልህ :ታጋይ :ስሙ ይናገር Question[/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወጥመድ

ኮትኳች

Joined: 11 Mar 2005
Posts: 284
Location: Semen Walta

PostPosted: Tue Mar 31, 2009 3:59 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዘርዓይ ደረስ

ለመንጀምረው ውይይት ተስማሚውን ውይንም ተቀራራቢውን ስም መስጠት አስፈላጊ ነው :: ትክክልም ነው :: ከላይ የእኔን ጥያቄ እንደገና ብታዬው "70-80" የሚደርሱ ብሔር ብሔረ ሰብ እንዳሉ በየጊዜው ከብዙ አቅጣጫ እሰማለሁ ""
ነው ያልኩት ;; በመሆኑም የኔ ጥያቄ ከስሙ ጀምሮ ለመማር ስለሆነ እና ተስማሚውንም ስም ከፖለቲካ አንጻር ወገናዊነትን ይዘን ሳይሆን ጀስት አካዳሚካል በሆነ ይዘት የስነ ሕዝብ ምርምርን ተከትለን በኢትጵያችን ማን የትኛው ቋንቋ ይናገራል የት ይኖራሉ :: ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ነው ::

ይዘቱ ይህንን ከመሰለ ምን አይነት ስም እንስጠው ላልከው በእኔ ግምት ብሔረሰብ ወይንም ዘውግ ብንለው ተመጣኝ አጠራር ይመስለኛል ::

አመሰግናለሁ ::
ወጥመድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Mar 31, 2009 6:59 pm    Post subject: Reply with quote

ወጥመድ ሰላም በድጋሚ !

ያሰያየሙ ጉዳይ አሁንም መልስ ያገኘ አይመስለኝም ::ብሔር የሚለውን ቃል ለአንድ ክፍለ -ብሔር የተጠቀሙበቱም አሉና ነው ::ለምሳሌም ያህል ዘብሔረ ቡልጋ (ተስፋ ገብረ ሥላሴ ;ግርማቸው ተክለሐዋርያት ወዘተ ) ዘብሔረ ዘጌ (አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ) እንዲሁም ሌሎች ::እስክንስማማ ድረስ እኔ ነገድ የሚለውን ቃል መርጫለሁ ::ወደ ዝርዝሩ ስንገባ መጀመርያ ብዙዎቻችን በምናውቃቸው ለመጀመር ወስኛለሁ ::እንዳልከውም በአሁኑ ጊዜ እንደስድብ የሚቆጠሩትን መጠርያዎች በተቻለ መጠን (የማውቀውን ) ላለመጠቀም ሞክሬአለሁ ::

የኢትዮጵያ ነገዶች

የነገዱ ሥም
1)ኦሮሞ

2)አማራ

3)ትግሬ

4)ጉራጌ

5)ሲዳማ

6)ወላይታ

7)ከምባታ

Coolሀዲያ

9)ጌድኦ

10)ከፊቾ

11)ጊሚራ

12)ጋሞ

13)ዶርዜ

14)ኣፋር

15)ሶማሌ

16)ቅማንት

17)ወይጦ

1Coolአገው

19)አርጎባ

20)ሐመር

21)ገለብ

22)ኩሉ ኮንታ

23)ማጂ

24)ዳውሮ

25)የም

26)ሱርማ

27)ጉሙዝ

2Coolበርታ

29)ሺናሻ

30)ኑኤር

31)አኙዋክ

32)አሪ

33)ማኦ

34)ቡርጂ )

ይቀጥላል

*እግረ መንገዴን በቃሌ ለመያዝ እንደያመቸኝ የማስታውሰውን ብቻ ነው የጻፍኩት ::የሚገኙበትን ቦታና ሌሎች መረጃዎችን በሚመለከት ትንሽ ግር ብሎኛል ::የሚገኙበት ቦታ ስንል በአሁኑ አስተዳደር ነው (ክልል ;ዞን ....9ወይስ በድሮው (ክፍለሀገር ;አውራጃ ;ወረዳ ...)
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Tue Mar 31, 2009 9:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም
በቀረበው ጥያቄ ላይ የግል አስተያየቴን መስጠት እፈልጋለሁ .

1. ወጥመድ ........እንዳልከው ያንድን አካባቢ ህዝብ ብሄረሰብ ወይም ዘውግ ብሎ መሰየም የሚቻለው ከአንድ እዮተላእም አንጻር ጉዳዩን ስትመረምረው ነው . ለምሳሌ ከማርክሳዊ ርእዮት አንጻር ህዝቡን ብሄር /ብሄረሰብ /የተወሰኑ መስፈርቶችን በመጠቀም / እንደሚባለው ሁሉ
ከዚያው ባልራቀ ዘዴ ህዝቡን በመደቦች ትከፋፍለዋለህ .
ይህ የማርክሳዊ ሜቶዶሎጂ ሲሆን ኪሳራ ደርሶበት ፉርሽ ሆኖዋል . ከገባበት የትንተና ዉድቀት አንስተን ህዝባችንን በብሄር ብሄረሰብ መከፋፈሉ ዛሬም 19 ኛው ክፍለዘመን አስተምህሮዎች ላይ የሙጥኝ ብለን የቀረን ይመስለኛል .
ስለዚህ ህዝባችንን በቁዋንቁዋና በብሄር መከፋፈሉ እና ወጣቱን ማስተማሩ የት እንዳደረሰን ስለምናዉቅ ህዝቦችን እንደዜጋ ወስደን በሚያተሳስራቸው ላይ ለጋራ ብልጽግና ብናነሳሳቸው ...ብናስተምራቸው ይበጃል እላለሁ .ስለዚህ አማርኛ የምናገር ዜጋ ...ኦሮምኛ የሚናገር ዜጋ ...ጉራጊኛ የሚናገር ዜጋ ወዘተ ብለን ማየቱ ይሻላል እላለሁ . ከቀረብው ጥያቄ ላለመዉጣት ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጌያለሁ .

ከሰላምታ ጋር . ቁጥር 2 አስተያየቴ ይቀጥላል
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Tue Mar 31, 2009 10:13 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም

2.ዘርአይ ...ለወጥመድ በሚመች መልኩ ተራቁጥር አስይዞ ልዩልዩ ቁዋንቁዋ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ለመዘርዘር ሞክሮዋል . የት አካባቢ እንደሚኖሩ የሚለው ሌላው የጥያቄ አካል ገና የሚሞከር ነገር ነው . በዘርአይ ዝርዝር ላይ የምለው ይኖረኛል .
ለምሳሌ አማራ የሚለዉን ስያሜ እንዉሰድ . አንድ ወሎየ ሲፎክር ወይ ኩራቱን ሲገልጽ "ቀብራራው ወሎየ " ይላል .
አንድ አማራ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ካገኘን ግን "ቀብራራው አማራ ' ብሎ ሲፎክር አልሰማንም . የለለውን ከየት አምጥቶ ""ዘራፍ እኔ አማራው ""ይለናል .
ስለዚህ ያለው እና የሚኖረው ጎንደሬ ..ጎጃሜ ..ቡልጌ ...ወሎየ እንጂ አማራ የሚባል ነገድ የለም . የነዚህ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ህዝቦች እራሳቸዉን ከፍ ወዳለ ብሄራዊ ስሜት አሸጋግረዋል . ኢትዮጵያዊ ሆነዋል . ሰማይዝቅ መሬት ከፍ ቢል ከዚያች ብሄራዊ ማንነት ፍንክች አይሉዋትም .
ስለዚህ ይህን የመሳሰለ ግድፈት እና የአሰያየም ችግር በሌሎቹም ብሄራ /ብሄረስብ ህዝቦች ስላለ የዘርአይ ሊስት ትክክለኛ አይደለም ማለት ነው .

አስቀድሞውኑ 70-80 የሚደርሱ ብሄር /ብሄርሰቦች ኢትዮጵያ ዉስጥ አሉ ብሎ ማለት ለማርክሲስቶች እና ትንተናቸዉን በአውሮፓው ሜቶዶሎጂ ላይ መሰረት ላደረጉ ኤሊቶች ካልሆነ ለህዝባችን ብሎም ላገሪቱ መሰረታዊ ችግሮች ጠቃሚ አይደለም . 21ኛው ክፍለዘመን ማርክሲዝም -ሌኒንዝም የህዝቦችን ታሪካዊ ቁርኝት እና ዝምድና በሚገባ መተነተን እና ቁርኝታቸዉን ማሳደግ ባለመቻሉ ግባተመሬት ከወረደ ጥቂት አስርት አመት አለፈን . እና ወጥመድ ለጠይቀው ጥያቄ መልስህ ምንድን ነው ከተባልኩ አቀርባለሁ .

ይቀጥላል

ነቅንቄ
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወጥመድ

ኮትኳች

Joined: 11 Mar 2005
Posts: 284
Location: Semen Walta

PostPosted: Wed Apr 01, 2009 9:39 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዘርዓይ ደረስ እና እንዲሁም ሀሳብ ለሰጣችሁ ወገኖች በሙሉ ::

ነቅንቄ እኔን አስመልክተህ የሰጠኸው ሀሳብ ገንቢ ነው :: ገና ብዙ የምንወያይበትም ነጥብ ነው :: ከላይ እንዳየኸው ለዝርዝሩ አጠራር 3 ስታችንም የተለያየ አሰያየም ሰጥተናል :: ሌሎች ድግሞ የተለየ አጠራር ሊከተሉ ስለሚችሉ ውይይቱ የሚቀጥል ይመስለኛል :: እኔም ገና ብዙ ጥያቄ እና ሀሳብ አለኝ ::

አሁን ዘርዓይ ደረስ የጀመረውን ዝርዝር ሲያገባድድ ሀሳቦቼን ማንሳቴ አይቀርም :: አንተም ለጥያቄው የራሴ መልስ አለኝ ያልከውን ቀጥልበት ::

ዘርዓይ ደረስ --- ቃልህን ጠብቀህ ዝርዝሩን ሰለ ጀመርከው በጣም አመሰግናለሁ :: የት ይኖራሉ ለሚለው ጥያቄ ከህዝብ ስብጥር እና ከቦታ አሰያየም መዋዠቅ አንጻር አስቸጋሪ እንደሚሆን እሙን ነው :: በእኔ አስተያየት ግን ሶስቱንም የአገዛዝ ዘመን ስያሜዎችን እንደ አማራጭ ወስደን እንደ አመቺነቱ ብንጠቀምበት አሰፋፈሩን ሙሉ በሙሉ መግለጽ ባይችልም አካባቢውን ሊጠቁመን ይችላል ብየ እገምታልሁ ::

ለምሳሌ -----
1. በንጉሱ ዘመን የነበሩት የቦታ አጠራሮች >>>

--ክፍለሀገር
--አውራጃ
--ወረዳ
--ምክትል ወረዳ
-- አጥቢያ

2.በደርግ ዘመን የነበሩት አጠራሮች

-ክፍለሀገር --

-የክፍለሀገሩን አቅጣጫ አምለካች ማለትም ለምሳሌ
(ሰሜን ሽዋ , ደቡብ ወሎ , ምስራቅ ሀረር , ምእራብ ትግራይ ... ወዘተ ..
)

-አውራጃ

-ወረዳ

--ቀበሌ ገበሬ ማህበር / ከተማ /ከተማ ቀበሌ ማሕበር

አሁን ባለው ወያኔ /ኢሀድግ ዘመን ያሉት አጥራሮች

--ክልል
-- ዞን
--ገበሬ ማህበር /
---ክፍለ ከተማ ----- ወዘተ ብንጠቀም
ችግሩን በመጥኑ ሊያቃልልን ይችላል ብዬ እገምታልሁ ::

ወጥመድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Thu Apr 02, 2009 9:14 am    Post subject: Reply with quote

ወጥመድ እንደጻፈ(ች)ው:
የሶስቱንም አገዛዝ ዘመን አስያየሜዎችን እንደአማራጭ ......

ሰላም ወጥመድ

ዘርአይ የጀመረዉን እስኪጨርስ እና ጥያቄዎቼን እስከማነሳ ከዚያም የራሴን ሀሳብ እስከምገልጽ መታገሱን እመርጣለሁ .

ያነሳህእው ጥያቄ ላይ ላዩን ሲመለከቱት መልካም ይምሰል እንጂ አከራካሪ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ . እኔ ያንን አልጠብቅም . እዚህ መድረክም ብዙ ዉይይት መደረጉን አስታውሳለሁ . እጥር ምጥን ያለች መሰረታዊ ትምህርት እንደምናገኝባት ተስፋ አደርጋለሁ .

የሶስታችን የአሰያየም ልዩነት የሚጠበቅ ነው .ከሶስት አልመብለጡም ደግ ነገር ይመስለኛል . በምክንያት ላይ ተመርኩዘን በሚያስማማን ላይ እንስማማለን . ጎሳ ማለት የኦሮምኛ ተናጋሪ ዜጎች ቃል መሆኑን በቅርቡ እዚሁ መድረክ ነው ያወቅሁት . አረብኛ ይመስለኝ ነበር !!!ቅቅቅ

መልካም ጊዜ
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Thu Apr 02, 2009 9:18 am    Post subject: Reply with quote

Arrow
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ነቅንቄ

ኮትኳች

Joined: 01 Mar 2005
Posts: 244
Location: bet-amhara

PostPosted: Sat Apr 11, 2009 9:41 am    Post subject: Reply with quote

ሰላማት ወጥመድ

አለሁ .
ይቀጥላል .

ከሚስት የተሸሸገ በቦታው ባይኖር ነው የሚል ይትበሀል አውቃለሁ .
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሰይፍ ከሚመዙት አንዱ ነኝ .

ለእናት ሀገር እትዮጵያ በተጠንቀቅ ዘብ ከቆሙት አንዱ !!!

ነቅንቃቼው !!!!!!
_________________
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 1 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia