WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ቀዳሹ ቄስ ቐሺ ገብሩ ...ማን ነበሩ ..?
Goto page Previous  1, 2
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3834
Location: united states

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 10:55 pm    Post subject: Re: ቀዳሹ ቄስ ቐሺ ገብሩ ...ማን ነበሩ ..? Reply with quote

ሰላም ለሁላችን
ይህን የነጻው ፕሬስ የግፍ ታሳሪ ደብዳቤ ያቀረቡ እጆች ይባረኩ !
እዚህ ግልጽ ብሎ የሚታይ አንዷለም ላይ ነፈሰገዳይ የመግደል ሙከራ የደረገው በሚገባ የወያነው የእስር በት አስተዳደሪዎች በወያኔው ባለስልጣኖች ድጋፍ ያቀናበሩት መሆኑ ነው ::
ድሮ በአጼውም ሆነ በደርጉ የወንጀል እስረኞች ለገዥዎቹ መሳሪያ እየሆኑ የፖለቲካ ታሳሪዎችን ሲያሰቃዩ እንደነበረው በወያኔም ይህ ሰቆቃ ቄጥሏል ::

Quote:
ለተከበሩ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ
ለተከበሩ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ

ወንድማዊ የአክብሮት ሰላምታዬ ይድረስዎ

በዚህ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በእኔ ላይ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ በተከበረዉ ጋዜጣዎ መዘገቡን ሰማሁ። በቅድሚያ ጋዜጣዎ እዉነትን ለማሳወቅ ስላደረገችዉ ጥረት ከልብ እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። በጣም አመሰግናለሁ !

በዚህ ለኑሮም ሆነ ለማሰብ ፍጹም በማይመች ሁኔታ፣ ለዚያዉም ከተፈጸመብኝ አሰቃቂ ድብደባ ሳላገግም፣ ብእርና ወረቀት እንዳገኝ የጎተጎተኝን ጉዳይ፣ ከዚህ እንደሚከተለዉ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።

ባለሁበት ወህኒ ቤት ጋዜጦችን ቀርቶ መጻህፍትንም ማስገባት ባለመቻሌ፣ እናንተ በምትኖሩባት «አለም» ከሚቀርበዉ የመረጃ ማእጽ መቋደስ አልችልም። እንደሌላዉ እስረኛ ሁሉ በሕገ መንግስቱ መሰረት እንዳልጠየቅ አሳሪዎቼ ቢከለክሉም፣ እንዲጠይቁኝ ከተፈቀደላቸው ሁለት ሶስት ቅርብ የቤተሰብ አባሎች አልፎ አልፎ ወሬ መቃመሴ ግን አልቀረም።

ይህን በመሰለ ሁኔታ ዉስጥ ወህኒ ቤቱ በእኔ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ፣ የሰጠዉን ምላሽ ይዘት በመስማቴ፣ ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ የመናገር ፍላጎት ባይኖረኝም፣ በቀጥታና በዝርዝር ማስረዳት እንደሚገባኝ ከራሴ ጋር ስምምነት ላይ ደረስኩ።

አሁን ካለሁበት የእሥር ሁኔታና ከገጠመኝ የጤና መቃወስ አንጻር ሃሳቤን በወጉ ለማደራጀት መቸገሬን ግንዛቤ ዉስጥ አስገብተዉ፣ ሃሳቤን በሚከተለዉ አኳኋን እንዳቀርብ መልካም ፍቃድዎ እንዲሆን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ለሁለት ወራት ገደማ በማእከላዊ እሥር ቤት ከቆየዉ በኋላ ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት መዛወሬ ይታወሳል። በቃሊቲም ከሌሎች፣ በአንድ መዝገብ ከተከሰስን ሰዎች ተነጥዬ፣ አሰቃቂ ወንጀል ፈጽመዉ ያታሰሩና በተደጋጋሚ እያመለጡ ያስቸገሩ እስረኞች ወደሚታሰሩበት (የቅጣት ቤት ) ተወሰድኩ። ገና እግሬ የወህኒ ቤቱን ቅጥር ከመርገጡ ለምን ወደዚህ አይነት ቦታ እንደተወሰድኩ ለሰሚዉ ግራ እንደሚሆን እገምታለሁ። በወህኒ ቤቱ ዉስጥ ግማሽ ቀን እንኳን ባልቆየሁበት ሁኔታ «ለአያያዝ አስቸግሮን፣ ልዩ ጥበቃ ( Maximum Security Zone) ዉስጥ አስገባነዉ» ሊባል አይችልም። ዉሳኔው ቀደም ሲል መከሰስ እንዳለብኝ ከወሰኑት አሳሪዎች እንደተላለፈ መገመት የሚከብድ ጉዳይ አይደለም።

አሳዛኙ ጉዳይ በዚች እጅግ ጠባብና አራት ማእዘን ሰማይ ብቻ በሚታይባት እሥር ቤት ተወርዉሬ የአሳሪዎቼ የበቀል በትር ያልተለየኝ መሆኑ ነዉ።

በዚች የጭንቅ ማማ ሁለት ወራት እያገባደድኩ በነበርኩበት አንድ ምሽት፣ ድብደባዉን የፈጸሙብኝ አቶ ይብሳ አስፋዉ እንዲቀላቀሉኝ ተደረገ። አብረዉኝ ከነበሩት ከኦፌዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ጋር በመሆን፣ ጎናቸዉን ያሳርፉበት ዘንድ ወለሉን ካመቻቸንላቸው በኋላ፣ የእሥር ሕይወታችንን ቀጠልን። የተከሰስንበትን ሁኔታ፣ ቀደም ሲል ያለንን የእስር ተመክሮዎችና እንዳዴም ግለታሪካችንን መጨዋወታችንን አልቀረም።

ካንደበታቸው በተደጋጋሚ እንደሰማነዉ በበርካታ የነፍስ ማጥፋትና ከባድ የዘረፋ ወንጀል ምክንያት እንደታሰሩ ገለጹልን። አክለዉም ከዶር ታዬ ወልደሰማያት ከአቶ ታምራት ላይኔና ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር እንደታሰሩ አጫወቱን። «ለምን እኝህ ሰዉ ተለይተዉ ከእነዚህ ፖለቲከኞች ጋር ታሰሩ ? » የሚለዉን ጥያቄ ግን መመለስ አልቻልንም።

በሂደት ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸዉ እስረኞች፣ የማረሚያ ቤቱ ሰላይ፣ በእነርሱ አገላለጽ «ወሬ አቀባይ» መሆናቸዉን አስረዱን። እርሳቸዉ ግን ሌላዉን ታሪክ ባይነግሩንም አሁን ያለንባት ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከታሰሩ የመጀመሪያዉ እስረኞች አንዱ ስለመሆናቸው ገለጹልን።

ቃሊቲ ዉስጥም ሆነ ዉጭ፣ ፊት ለፊት መናገር ወይንም መተግበር፣ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ብዬ አምናለሁ። 1998-1999 ባለው ጊዜ በአብዛኛዎቹ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ዞኖችና በከርቸሌ ጨለማ ቤት ድረስም ስታሰር፣ የተከተልኩት ዘይቤ ይሄንኑ ነዉ። በሂደቱም ከአንድም እስረኛ ጋር የኃይል ነገር ይቅርና ሃይለ ቃልም ተለዋዉጬ አላወቅም። «ቦዘኔ» ክልል ተብሎ ይታወቅ በነበረዉ ዞን እንኳን ይህን የመሰለ ነገር አልፈጸምኩም።

በጊዜዉ አብረዉኝ የታሰሩ ጓደኞቼ እንደሚያስታወሱት አልፎ አልፎ ፀቤ ከፖሊስ ጋር ነበር። ከፖሊስም ጋር ቢሆን የነበረኝ አለመግባባት «ለምን የእስረኛ መብት አይከበርም ? ለምን እስረኝ ይደበደባል ? » በሚል ነበር። ይሄንንም በግልጽና በአክብሮትከመግለጽ ዉጭ የተለየ አቀራረብ ኑሮኝ አያዉቅም። አቶ ይብሳ አስፋዉንም ቢሆን ለረጅም አመታት የታሰሩና የዔች አይቪ ታማሚ በመሆናቸው፣ ከማክበርና ከመንከባከብ ዉጭ አንዳች ቅር የሚያሰኝ ነገር ተናግሪያቸው ወይንም ፈጽሜባቸው አላውቅም።

ነገር ግን ገና አንድ ሳምንት ሳይሞላቸው ጀምሮ፣ በጋዜጣ ላይ ሊገለጹ የማይችሉ አያሌ ፈታኝ ነገሮች ያደርሱብኝ ጀመር። መዝለፍ የእለት ተእለት ሕይወቴ ሆነ። እንደ ድመት በጥፍሬ ቆሜ መዉጣትና መግባት የዘዉትር የአኗኗር ዘይቤዬ ሆነ። ከአለፈዉ እሥር ተመክሮዬ በመነሳት ያረጋጋቸዋል ብዬ የማስበዉን ነገር ሁሉ ባደርግም አልተሳካልኝም። ያለ አንዳች ማጋነን ክብራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከተናካሽ ዉሻ ጋር ከመታሰር ፈጽሞ የተለየ አልነበረም። ጊዜዉ እየገፋ ሲሄድ ተራ ስድብ እየተሰደብኩም ሁሉንም በጸጋ ከመቀበል ባለፈ ሌላ አማራጭ አላገኙሁም። አስቀድሜ እንደግለጽኩት ያለሁበት እሥር ቤት ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ የሆኑ እስረኞች በሌሎች የወህኒ ቤቱ ዞኖችማ አደገኛ የተባሉ እስረኞች ለቅጣት የሚመጡባት ቤት ነች።

ታዲያ ሰዉዬዉ እኔና ሌሎች በጣት የምንቆጠር እስረኞች ወዳለንበት ቅጥር ለምን መጡ ? ከቀድሞ የእሥር ቤት ቆይታዬ እንደተረዳሁት እስረኞችን እንዲሰልሉ የሚመደቡ እስረኞች አሉ። ስለደብዳቤዬ ከታሳሪዎች ከተረዳሁትን በላይ፣ በተለያዩ ወቅት ከተለያዩ ፖለቲከኞች ጋር መታሰራቸው ለምን ይሆን ? የሚለዉ ጥያቄ እየተመላለሰ ሳያሳስበኝ አልቀረም። መጀመሪያ ባይገባኝም፣ በእድሜ የተፈረደባቸው እስረኛ በመሆናቸው፣ 16 አመታትም እንደሚሉት የታሰሩ በመሆናቸዉ፣ ክፍለ ሃገር በዝዉዉር ቢሄዱ ኑሮ እስከአሁን ሊፈቱ ይችሉ እንደነበር በማንሳት ይቆጫሉ። ወደ ክፍለ ሃገር ለመዘዋወር ጠይቀዋል። እስከ አሁንም ባይዘዋወሩም ውትወታቸዉን ቀጥለዋል። የወህኒ ቤቱን ሃላፊዎች ከረጅም ቆይታቸው የተነሳ እስከቤተሰብ ድረስ እንደሚያወቋቸዉና የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸዉ በተደጋጋሚ ሊያስረዱን ሞክረዋል።

ከድብደባው 10 ቀናት በፊት ወደ ዋናዉ የወህኒ ቤቱ ሃላፊ ቢሮ ቀን በቀን ማለት ይቻላል፣ በጥበቃ ፖሊሶች አማካኝነት ይመላለሱ ነበር። ሁኔታዉ ለሁላችንም ግልጽ ነበር። የስለላ ስራ እየሰሩ ነበር። በዚያ ወቅት በእኔ በኩል በወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 148 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ለፍርድ ቤት ለማቅረብ በመጻፍ ላይ ነበርኩን። ወረቀቱንም ልነጠቅ እንደምችል የራሴን ግምት ወስጃለሁ። የተለየ አማራጭም ሆነ የሚደበቅ ጉዳይ ባለመኖሩ የመጣዉ ይምጣ ብዬ መጻፌን ቀጠልኩ። የኔ ሃሳብ የነበረዉ ወህኒ ቤቱ በፍተሻ ሰበብ ይወስድብኛል የሚል ነበር። የተፈጠረዉ ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ሆነ።

ግልሰቡ 6/6/2004 . ከሰዓት በኋላ እንደተለመደዉ ዋና አስተዳዳሪዉ ቢሮ ዉለው መጡ። እንደመጡም ፍራሻቸዉን አሁን ወዳሉበት ዞን ለመላክ ሲሞክሩ ግራ ከመጋባት በዘለለ የተለየ ሃሳብ አልያዝኩም። መጻፌን ግን ቀጥያለሁ። በዚያዉ እለት ማታ ሽንት ቤት ገብተዉ ሲወጡ ቧንቧ «ባለመዝጋታችሁ ዉሃ ፈሰሰብኝ » በማላት እናንተ ትናንሾች በማላት ሦስታችንንም በጅምላ ሰደቡን። አሰዳደባቸዉንና ሁኔታቸዉ ከሌላ ጊዜ የከረረና እንደምንም ምክንያት ፈልገዉ አካላዊ ግጭት ዉስጥ ለመግባት የመፈለግ ፍላጎት ይነበብባቸዉ ነበር።

ሶስታችንንም ለመሃላ እንኳን አንዳች ሳንተነፍስ ምሽቱም እየገፋ ነበርና እንደተገረፉ ሕጻናቶች አፋችንን ዉጠን ወለሉ ላይ እንደ አስክሬን ተገጥግጠን አንቀላፋን። በማግስቱ የግድያ ሙከራ ባደረጉብኝ ቀን፣ አርፍደዉ ከእንቅልፍ ነቁ። አቶ በቀለ ገርባ ያነባል። እኔ አሁንም እየጻፍኩ ነዉ። አቶ ይብሳ እንደተነሱ በመጮህ ያዘጋጀሁትን በሶ ትጠጣላችሁ አትጠጡም ?» አሉ። ሁለቱ የነርሱን ድርሻ መጠጣታቸዉን ሲገልጹ እኔ መጠጣት እንደማልፈልግ ገለጽኩላቸዉ። ይሄ የሆነዉ ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ ነዉ።

ስምንት ሰዓት ተኩል ሲሆን በፀጥታ የተቀመጥኩበት ክፍል በር በኃይል ተከፈተ። ደብዳቤዬ ለረጅም ሰዓት ከቤት ዉጭ ቆይቷል። ሃሳባቸው ሌሎች እስረኞች ሲወጡ ጠብቀዉ ዉሳኔያቸዉን ለመፈጸም እየተጠባበቁ ነበር። እንደተረዳሁት። በአጋጣሚ ሁላችንም በስራ በመጠመዳችን ከተቀመጥንበት አልወጣንም። ጊዜ እየመሸባቸው ስለነበር ያላቸው አማራጭ ባለዉ ሁኔታ እርምጃዉን መዉሰድ ነበር። በሩን እንደከፈቱ ተንደርድረዉ በመግባት አሳልፈዉ ይሰጡብኛል ብዬ የሰጋሁባቸዉን ወረቀቶች ከሌሎች ወረቀቶች እየለዩ፣ ጉዳዩን ይከታተሉ ስለነበር፣ ከያሉበት ለቀሟቸዉ። ከማስታወሻ ደብተሮች በተጨማሪ 40 ገጽ ወጥ ጽሁፍና ሌሎችም ሰነዶችን በጄ ላይ የነበረዉን ጨምረዉ ነጠቁኝ።

ይሄ ነገር እንደሚመጣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እጠብቀዉ ነበርና ዝምታን መረጥኩ። በበኩሌ ከማንም ሰዉ ጋር ቢሆን ግብግብ መግጠም አልፈልግም። ዝምታዬ መፍትሄ አልሆነም። ከተቀመጥኩበት ተንደርድረዉ ከኮንክሪት ግድግዳ ጋር አጣብቀዉ ጭንቅላቴን ረገጡኝ። ተንሸራትቼ በቀኝ ጎኔ የሰሚንቶዉን ወልል ላይ ተነጠፍኩ። አሁንም አልበረደም። ከወለሉ ላይ ጭንቅላቴን ሶስት ጊዜ እንደረገጡኝ አቶ በቀለ መሃል በመግባት ለማስጣል ሲሞክሩ በሰመመን ዉስጥ ሆኜ እሰማለሁ። «እገለዋለሁ። ብገለዉ ስድስት ወር ብቻ ነዉ ካቴና የሚገባልኝ» ይላሉ። አቶ በቀለንም ዘወር ካላለ እንደሚደበድቡት ይዝታሉ። «ደብድበኝ እንጂ ስትጨርሰዉ ዝም ብዬ አላይም» እያሉ ግብግብ ገጥሟል።

ከዚህ በኋላ ሌሎች እስረኞች በመጨመራቸዉ ወለሉ ላይ እንደወደኩ ደብዳቤዬን ገፋፍተዉ አስወጧቸዉ። ትንሽ ራሴን ማወቅ ስጀምር ጭንቅላቴ ላይ ድብደባ ስለተፈጸመብኝ ሕክምና የማግኝበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹልኝ ፖሊሶችን ጠየኩኝ።

የተከበሩ አዘጋጅ፡

እስካሁን የገለጽኩልዎ ሁሉ እዉነት ስለመሆኑ በፈጣሩ ስም አረጋግጥልዎታለሁ።

ከፍ ብዬ አጠቃላይ ሂደቱን ልገልጽልዎ ሞክሪያልሁ። አሁንም ደግሞ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር ሁኔታዉን አስመልክቶ በጋዜጣዎ ባወጣዉ ምላሽ ላይ የእኔን እምነት እንድገልጽ ፈቃድዎትንና ትእግስትዎትን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

እዉነቱን ለመናገር የእኔ ጉዳይ በአሳሪዎቼ በአቶ አመለስ እጅ እንጂ በወህኒ ቤቱ አሊያም በፍርድ ቤቱ እጅ ነዉ የሚል አንዳች ብዥታ ኑሮኝ አያወቅም።

ስለዚህ ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎችም ሆነ ከፖሊሶች ጋር ከወንድማማችነትና ከአክብሮት ዉጭ ሌላ የተከተልኩት መንገድ ኑሮ አያውቅም። ደብዳቢዬ አስተዳዳሪው ቢሮ ሲመለሱ ግን ምን እየተጋገረ እንደነበረ ለማሽተት ብዙ አስቸጋሪ አልነበረም። የግድያ ሙከራዉም ቢሆን አሳሪዎቼ የወህኒ አስተዳደሩን በመጠቀም ሊወስዱብኝ ያሰቡት እርምጃ ነዉ የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በታች የማነሳቸዉ ነጥቦች የግድያ ሙከራዉ በአሳሪዎቼ እንጅ በደብዳቤዬ የግል ፍላጎት ላለመፈጸሙ አሥረጅ ናቸዉ ብዬ አምናለሁ።

1 ከሌሎች እስረኞች ተነጥዬ ከመጀመሪያዉ እንዲህ አይነት ቦታ የገባሁት ይኼን መሰል እርምጃ ለመዉሰድ ያመች ዘንድ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

2 እስካሁን በነበረዉ የወህኒ ቤቱ አሰራር፣ በእስረኛ ላይ የግድያ ሙከራ የሚያደርግ ቀርቶ ግጭት እንኳን ቢፈጥር አስተዳደሩ በአፋጣኝ በካቴና አስሮ ማማ በማስገባት ቅጣት ይፈጽም ነበር። እኔን ለመግደል የሞከሩት እስረኛ ግን ሊቀጡ ቀርቶ ከሦስት ሳምንታት በላይ አንዳች ተግሳጽ እንኳን ሳይደርስባቸዉ እኛ ካለንበት በእጅጉ በተሻለ ቦታ ታስረዉ ይገኛሉ።

3 ችግሩ እንደተፈጠረ ተጠርተዉ የመጡት የአስተዳደሩ አባላት ለአቶ ኢብሳ የጀግና አቀባበል ነበር ያደረጉላቸዉ ማላት ይቻላል። «አንተ ፖሊስ ወይንም የአስተዳደሩ አባል ባለመሆንህ ሰነዱን ቀድሞዉንም መንጠቅ አልነበረብህም። አሁንም በአስቸኳይ መልስ» ማለት ሲገባቸዉ ሰነዶቹን በፈገግታ ተቀብለዉ ሰዉዬዉን ወደ ተሻለ ማረፊያ ቤት እኔን ደግሞ ባላሁበት ቅጣት ቤት እንድቀጥል አድርገዋል።

4 ተጎድቼ ወደ ሕክምና እንዲወስዱኝ በምጠይቅበት ሰዓት ቢሮ አስገብተዉ ወረቀቱን የነጠቁኝ የረሃብ አድማ ለማድረግ ሃሳብ ላይ መሆኔን ስለደረሱብኝ መሆኑንና የወህኒ ቤቱ አስተዳደርም ይሄኑ እንደሚጠረጥሩ ገለጹልኝ። በእኔ በኩል የሚባለዉ ነገር ፍጹም ሃሰትና ነገሩን ለማድበስበስ ተብሎ የቀረበ መሆኑን ገልጬ የግድያ ሙከራዉ ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸዉንና ንብረቴን ከእነርሱ እንደምጠብቅ አስረዳሁ።

5 በደረሰብኝ ከፍትኛ ድብደባ እስከ አሁኗ ሰዓት ደረስ ከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ብሆንም ተገቢዉን የሕክምና ክትትል ማግኘት አልቻልኩም፡፡ሌሊትም ሆነ ቀን ከፍተኛ የስቃይ ስሜት ሲሰማኝ፣ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ፖሊሶችና በጤና ጣቢያዉ ያሉ የሕክምና ባለሞያዎች የቻሉትን ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ግልጽ በሆነ የአቅም ዉስንነት ምክንያት ጊዜያዊ ማስታገሻዎችን ከማድረግ ባለፈ፣ ከስቃዬ ሊታደጉኝ አልቻሉም። ይሄ ሁኔታ በዉል እየታወቀ የተሻለ የሕክምና ክትትል በድንገተኛ እንኳን እንዳገኝ አለመደረጉ፣ ያልተፈለገዉ ሕይወቴ ይቀጥል ዘንድ ባይፈለግ ነዉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለኝ።

6 ክስ የምመሰርት ከሆነ በአስተዳዳሪዎቹ ተጠይቄ ነበር። ግለሰቡ በራሳቸዉ ተነሳሽነት አደረጉት ብዬ እንደማላምን በመግልጽ ፈቃደኛ አለመሆኔን ገለጽኹ። አክለዉም ምስክሮች እንዳሉኝ ጠይቀዉ እነርሱ የራሳቸዉን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዉ ቢሄዱም በጉዳዩ ላይ ከዚህ ግባ የሚባል ነገር ሳያደርጉ አያሌ ቀናት አልፈዋል። ይሄም እዉነት በግለሰቡ የተፈጸመ ቢሆን ኑሮ ጉዳዩ በዚህ ሁኔታ በቸልተኝነት እንደማይያዝ መረዳት አያስቸግርም።

7 የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎች የተወሰዱብኝን ሰነዶች ሙሉ በሙሉ እንዲመልሱልኝ ብጠይቅም፣ ቀደም ብለዉ በጋራ እያየን የሚመለስ ካለ እንደሚመለስ የማይመለስ ካለ ለምን እንዳማይመለስ እንደሚገለጹልኝ ነግረዉኝ ነበር፡ በአጋጣሚ አደጋዉ ከተፈጠረ በኋላ ተቀይረዉ የመጡት አስተዳደሮችም በተገለጸዉ መሰረት ይፈጽሙልኛል ብዬ ባስብም፣ አልተሳካም። ከወሰዷቸዉ ሰነዶች የፍርድ ቤት የክስ ወረቀቴንና አንድ የተገነጠለ የደብተር ሽፋንና የተቀደዱ አንዳች ነገር ያልተጻፈባቸዉ የተቀደዱ ወረቀቶችን መለሱልኝ። ብዙ የደከምኩባቸው ጽሁፎች የዉሃ ሽታ ሆኑ። በሁኔታዉ ማዘኔንና አዲስ እንደመሆናቸዉም ከእነርሱ ጋር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት እንደማልፈልግ ገልጬ፣ መብቴን እየገፈፉ ግን በዝምታ እንደማልቀጥል ስገልጽላቸዉ፣ ደብዳቢዬን ወረቀቶቹን ከሰጡዋቸው እንደሚጠይቋቸዉ፣ ካልመለሱላቸው ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ገለጹልኝ። «ዶሮን ሲያታልሏት» የሚባለዉ በእንዲህ ያለ ጊዜ ነዉ። አንድ እስረኛ ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ እንደሆነ ማን ሊያምን ይችላል ? ሰነዱንስ ቀደም ብለዉ ሊመልሱልኝ፣ የማይመመለስም ካላ ለምን የሚለዉን እንደሚያስረዱኝ ተገልጾልኝ እንደነበረ ዘንግተዉት ወይንስ…… . !

8 እየተፈጸመብኝ ያለዉ ግፍ ሳያንስና ጥዋትና ማታ ከሞት ጋር ግብግብ በገጠምኩበት ሁኔታ፣ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር በጋዜጣዎ ላይ ነገሩን ተራ ጉዳይ ተራ ግጭት አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ፣ ሃዘኔን አክብዶታል። ስቃዬንም አብዝቶታል። ከፍ ሲል የገለጽኩት የግድያ ሙከራ ሲፈጸምብኝ አንዳች ቃል እንዳልተነፈስኩ፣ ራሴንም እንኳን ለመከላከል እንጄን እንዳላነሳዉ በሚገባ እየተረዱ፣ ጉዳዩን የግድያ ሙከራ ሳይሆን ግጭት ለማስመሰል መሞከራቸዉ ከበደል ሁሉ የከፋ በደል ነዉ።

በሰዉነት ከተቸረኝ ክብር ዉጭ የምጠቅሰዉ ሌላ ክብር የለኝም። ነገር ግን የወህኒ ቤቱ እርምጃ እኔን ተራ አምባጓሮ ፈጣሪ በማስመሰል ለማብጠልጠል የታቀደ እንደሆነ እገነዘባለሁ።

ለመሆኑ ምንስ የሃሳብ ልዩነት ቢኖረኝ ሰዉነቴን ይጠራጠራሉ ? ወይንስ ኢትዮጵያዊነቴን ? ከእስር አያያዝ ጀመሮ ከፍ ብዬ እስከ 7 ተራ ቁጥር የገለጽኳቸዉ በደሎች ሳያንሱ እኔን እንደ ምግባረ ብልሹ አድርገዉ ለአንባቢ ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዝኖኛል።

በአጠቃላይ ወህኒ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ እያሳየ ያለዉ ነገር በገሃድ የሚያሳየዉ የጉዳዩ ባለቤት አሳሪዎቹ መሆናቸዉንና ያንንም ለመሸፈን ሲሉ ከፍ ያለ ዉጥረት ዉስጥ መግባታቸዉን ነዉ።

ነገር ግን ይሄን መሰሉ ተግባር ለተቋም ግንባታም ሆነ ወንድማማችነትን እና መልካም ሁኔታዎችን ሲፈጠር አይታየኝም። የፓርቲዬ የአንድነት ለዲሞርካሲና ለፍት ፓርቲ አላማ እንዲህ አይነት የሸፍጥኛ የመጠፋፋት አዙሪት ቆሞ ፍትህ፣ ዴሞርካሲ፣ ነጻነትና ወንድማማችነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማማየት ነዉ።

ክቡርነትዎ እንዲረዱልኝ የምፈልገዉ ይሄንን የመሰለ ደብዳቤ ስጽፍ ማንንም ለመበቀል ወይንም ለማንቋሸሽ ሳይሆን እዉነቱ ፍንጥቅ ብሎ እንዲወጣ፣ ስቃዬን ሕዝብ እንዲያዉልኝ ከመሻት የተነሳ መሆኑን ነዉ።

ለዚህ እዉነት ደግሞ ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ።

መቼም እኔ ባለሁበት ሁኔታ ያለ ሰዉ ነገር ቢያበዛ ቅር እንደማይሰኙ ተምምኜ፣ ነገሬን ዘለግ ማድረጌን ይረዱልኝ። ስለትብብርዎ በቅድሚያ እያመሰገንኩ እዉነቱን የማሳወቅ ስራዎ እንዲሳካ እመኛለሁ !!!

እቺን ይጫኑ ::[/quote][/quote][/quote][/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 10:58 pm    Post subject: Reply with quote

THERE IS NOTHING MORE FULFILLING THAN SHARING THE SELFLESS, INCLUSIVE AND DEMOCRATIC JUST CAUSE OF THE GALLANT WOYANES!
KUDOS TO QESHI GEBRU, AMORAW AND THE CHANGE MAKER WOYANES!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:09 pm    Post subject: Reply with quote

እስቲ አውሩ
ቅደዱ
በወሬ - በሀሳብ -
በመኞት ደስ ይበላቹ

እናቸንፋለን - - በሉ
መፈክር አሰሙ
መዝሙር አዚሙ
እመ -አምላክ
44ቱን ጥሩ
ተንጫረሩ

አቅም ጠፋ
ጊዜም ነጎደ
እድሜም ጫረ
ጤና ተቃወሰ
ወሬ እየተናፈስ
ቡልልልልልልልልል
ተገደለ
ተሰቀለ
ወደመ
ተሽጠ
ባንዳ
ሆዳም
ምናምንቴ
እረ

ቀደዱ
ከተቡ
ጫሩ
ቀባትሩ
መቸም አተረቡ
እርባና የለ
ምንም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:31 pm    Post subject: Reply with quote

ደደብ Laughing

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
እስቲ አውሩ
ቅደዱ
በወሬ - በሀሳብ -
በመኞት ደስ ይበላቹ

እናቸንፋለን - - በሉ
መፈክር አሰሙ
መዝሙር አዚሙ
እመ -አምላክ
44ቱን ጥሩ
ተንጫረሩ

አቅም ጠፋ
ጊዜም ነጎደ
እድሜም ጫረ
ጤና ተቃወሰ
ወሬ እየተናፈስ
ቡልልልልልልልልል
ተገደለ
ተሰቀለ
ወደመ
ተሽጠ
ባንዳ
ሆዳም
ምናምንቴ
እረ

ቀደዱ
ከተቡ
ጫሩ
ቀባትሩ
መቸም አተረቡ
እርባና የለ
ምንም

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:42 pm    Post subject: Reply with quote

የተሞናመነው = Dumb twat
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:49 pm    Post subject: Reply with quote

ቁርበት ...የአህያ ...ጣሊያን የተቀመጠበት Laughing Laughing Laughing

ልጅ ሞንሟናው

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
የተሞናመነው = Dumb twat

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:59 pm    Post subject: Reply with quote

የመነመነው ::
ወሬህ ሁሉ ሰል አህያ - ቆርበት - ሰደት - መከራ - - ጣልያን - ጀርመን - መናምን ነው :: ያው የድንቁርናህ መጠኑ መመዝኛው ይህ ነው ::
ያገርክ አህያ ለመሆነማ አልታደልክም - - የፈርንጅ አህያ ሁነሀል :: ነጋ ጠባ ትጫነዋለህ ::
በሬ አደለክ አትታረድ አተታረስ
ፈረስ አደልክ አትጋለብ
እንዳው የፈረንጅ አህያ ቶሽሽሽሽሽሽ

እስቲ ሰደበኝ የኔ መሀይም
ቅደድ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 12:12 am    Post subject: Reply with quote

ዌይ ...ማይ ኔም ይዝ ሞንሟናው ...አያም ፍሮም ጎዣም የንድ ማይ ዬጅ ይዝ 28 የንድ ወልሶ አይም ኖት የፈረንጅ አህያ Laughing እንዲሁም ቁርበቷን ማንሳቴ እኮ አህያን ማሳነሴም አይደለም ...አህያሲምባ ....ያወራሁት ' ስለ አህያ ቁርበት ነው :: የአህያ ቁርበት ዲፋይን ሲደረግ ዴግሞ አህያዋ በጭነት አሊያም በአደጋ ምህንያት ስትሞት የሚቀረው ቆዳዋ ማለት ነው ...ከስጋዋ ከተለየ በዋላ ደርቆ መስለኝ Laughing እና ቆዳዋ እንደሚታወቀው ጅብ ከስጋዋ ጋር ሊበላው ግድ ነበር ....ግን ሳይበላው ቀርቶ ጥሊያን አገኘውና ...ጥሊያን ደግሞ ክብር የለውም አይደል Rolling Eyes እናልህ ርኩስ የጋማ እንስሳትንም ለይቶ ስለማያውቅ በአህያ ቁርበት ተቀመጠ ...እና የአህያ ቁርበት ስልህ ያንን ለማመላከት ነበር Laughing ይንዴት ነኝ ማብራሪያ ላይ ....ለወደፊቱ መምህር የሞን አይመስልህም አህያሲምባ Laughing

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
የመነመነው ::
ወሬህ ሁሉ ሰል አህያ - ቆርበት - ሰደት - መከራ - - ጣልያን - ጀርመን - መናምን ነው :: ያው የድንቁርናህ መጠኑ መመዝኛው ይህ ነው ::
ያገርክ አህያ ለመሆነማ አልታደልክም - - የፈርንጅ አህያ ሁነሀል :: ነጋ ጠባ ትጫነዋለህ ::
በሬ አደለክ አትታረድ አተታረስ
ፈረስ አደልክ አትጋለብ
እንዳው የፈረንጅ አህያ ቶሽሽሽሽሽሽ

እስቲ ሰደበኝ የኔ መሀይም
ቅደድ

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
salar

ኮትኳች

Joined: 10 Feb 2012
Posts: 149

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 12:17 am    Post subject: Reply with quote

what a ---- loser. Laughing Laughing

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
ደደብ Laughing

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1874

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 11:08 pm    Post subject: Re: ቀዳሹ ቄስ ቐሺ ገብሩ ...ማን ነበሩ ..? Reply with quote

እንዴት ተሸውጃለሁ ለካስ ?!

እኔ አንተ የምትለጥፈውን ክሊፕ መክፈት ስለተውኩ እዚሁ መድረክ ላይ የምትለውን ለማንበብ ከጀመርኩ በኍላ እንደ አይን የጠፋው እንግሊዝኛህ አልስኬድ ሲለኝ "ethical' እየሳቅኩ ተመለስኩ :: ዛሬ ጊዜ አግኝቼ ትሬዱን አየት አየት ሳደርግ ...ለካስ የለጠፍከው የህወሀትን ታይታኒክ ነበር Very Happy

ከእንግሊዝኛው ስጀመር እንደገባኝ የስፔሊንግ ስህተት ስልችቶህ በወርድ ፕሮግራም ጀምረኸው ---የሌለ ነገር እየጻፍክ ስታስቸግረው ፕሮግራሙ የገባውን ጻፈልህ :: አንተ ደሞ እሱን ተቀብለህ ቀጠልክ ያቺ የነበረችህ እንግሊዝኛ አፈር በላችብህ :: የስፔሊንግ ስህተቱ ይሻል ነበር ለነገሩ ...ቢያንስ ለማለት የፈለከውን ነገር መገመት ስለሚያስችል ..እርግጥ ነው አንዳንዱ ስህተትህ ለግምት ራሱ ያስቸግራል ! የሆነ ሆኖ እኔ በእንግሊዝኛህ ለመላጥ አይደለም :: እኔ ማን ነኝና ?! የተሰማህ ግን የትንሽነት ስሜት ሳይገርመኝ አልቀረም :: እንዲህ ከምትወለጋገድ ለምን በተሻለ ሁኔታ በምትጽፈው የአማርኛ ቋንቋ አትጽፈውም ነበር ?? ጨናዊም እንደዚህ የትንሽነት ስነ -ልቦና ስለተጠናወተው በየሄደበት ባንተ ቢጤ እንግሊዝኛ ሲንተባተብ ይሰማል ... እነ ፑቲን እነ አህመዲን ነጃድ እነ ማንትሴ ብዙ ጊዜ በሳው ሞተዋል አሉ :: Idea ባንተ ላይ ስለ ቋንቋ ይሄን ያህል ትችት የሰጠሁት የሰው ቋንቋ እተቻለሁ እያልክ ዱብ እንቅም ስለምትል ገርሞኝ ነው ::

ወደ ታች ወረድ ስል ደሞ መንደር ለመንደር ሁሉ ወርደህ ስለነ ደብሬም ስለነ ብርቄም ...እነ ሀዳስን እነ ኪሮስን ግን ረሳቸው :: ሀዳስ ቆረቶር ራሷን ወሯት ቆዳዋ ተላልጦ ጋሜ ሆና የመጣች የምታሳዝን ልጂ ነበረች ... በኍላ ሰፈት ውስጥ እንደማንኛውም ልጂ በፍቅር አድጋ ህወሀት ሲገባ ተመልሳ በለስ ፈጫታ አፈር ተራጭታ (ነው ከአሸንጌ ወዲያ ውሀ አለ ?? የለም የትግራይ ድንበር ላስታ ይደርሳል Rolling Eyes ) ወዳደገችበት መንደር ተመለስች :: እምበር ተጋዳላይ እያለች :: በዚሁ ግን ስለ ስም አወጣጥ አንድ ነገር ልበልህ :: በዚሁ በያዝነው አመት አንዲት ልጂ አገኘሁና ያው ባበሻ ደንብ ሰላምታ ሰጥቼ ስሜን ተናገርኩ እና የሷንም ነገረችን :: 'ሚሊየ ' አለችኝ :: ሚስ ፕሮናውንስ ላደርገው እችላለሁ BUY the way... ግራ ተጋብቼ በምንኛ ነው ምን ማለት ነው አልኳት :: በትግረኛ ነው :: ሚሊየኔ ማለት ነው አለችኝ :: የስሙ ቅላፄ ብቻ ሳይሆን ሀሳቡ ራሱ ዘመንኛ ሆነብኝ :: በሆዴ በቃ እናነተ የገንዘብ ነገር እና የንብረት ነገር አይሆንላችሁም ማለት ነው አለኩ :: እንግዲህ ቅድስቴ ; ደብሬ ...እንዲህ እንዲህ አይነት ስም ሲወጣ ...ንጽጽሩ በመንፈሳዊው ዓለም ዋጋ ከሚሰጠው ነገር ጋር ነው :: ይሄኛው ከላይ የጠቀስኩት ስም ደሞ ሚሊየን ከሰረቁ ወገን ሆኖ እንደገና ሚሊየ ሲባል ...ለሚሊየን ያለውን ግምት ያሳያል :: ለመለጠ ማብራሪያ የብጻይ ጨናዊን "" የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወዴት "" የሚለውን በሳል ስራቸውን አንብብ ::

ወደ ክሊፑ ! እንኳንም ተመልሼ አየሁት ! it was worth it ! የህዋሀት TITANIC ብየዋለሁ ::

1. የፕሮፓጋንዳ ስራችሁን ትንሽ የተሻለ ለማድረግ ብዙ ስራ እንደሰራችሁ በግልጽ ማየት ይቻላል ::

2. በዚህ ክሊፕ ላይ ያላነቆጨ የህወሀት ታጋይ የለም :: የታሪኩ ባለቤትም ሌሎቹም Very Happy Very Happy የትወና ጥብብ ምን ያህል እንደገባቸው የሚያመላክት ተጭማሪ ነገር ሆኖ አግኝቸዋለሁ ::
3. ጦርነቱ እንደታይታኒክ ሙቪ በተዋጣለት ሁኔታ ሾት የተደረገበት ሁኔታ ( በሰዐቱ ህወሀት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እና በቂ የሰለጠነ የቴክኒክ ሰው ያለው ይመስል ) ያስቃል

4. ከሁሉም ከሁሉም ግን አፋቸውን በፈቱ ሰዎች ታሪኩ 'በፍቅር እስከመቃብር ' መንፈስ መተረኩ የማንን ልብ ለመግዛት ታስቦ የነበረ ነው ?? የሕወሓት ፓርቲ የታገለው አንድም የትግራይን መንግስት ለመመስረት አንደም ደሞ ለኤርትራ መገንጠል የበኩልን አስተዋጾ ለማድረግ እንደነበረ የጽሁፍም የቃልም ማስረጃ ባለብት ሁኔታ ለፍትህ ታገልን ብሎ ሁሉ ለቅሶ ...ይገርማል :: ወይ ኢትዮጵያ የተዘረፈችውን ሀብት እንድንረሳ አያደርገን :: ወይ በህወሀት የበታችነት ስሜት ንዴት ምክንያት በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ እና አፈና አያስረሳን :: ህወሀት ለማን ነው የታገለው የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ የረሳ ዶክመንታሪ ነው ::

5. በዚህስ ሰዐት ሴት ገሞራ ፈጥሮ ሌላ መጠነ ሰፊ ወደ ሆነ የፕሮፓጋንዳ ስራ መግባቱ ምን ያህል የፖለቲካ ትርፍ ያስገኛል :: የሴቷ አሞራውን ታሪክ ደክማችሁ ወደ ህዝብ ልብ ሊገባላችሁ ያልቻለውን ያህል ...በቅርቡ እንኳን በአንዱዓለም አራጌ ላይ የወሰዳችሁትን የተለመደ የበታችነት ስሜት የፈጠረው ደንቆሮ ተግባር ያለምንም ፕሮፓጋንዳ እንዴት ህዝቡ ውስጥ እንደገባ ብታውቅ ክብሮም !

6. እናንተው በፈጠራችሁት ታሪኩ ውስጥ ሌላ የተንጸባረቀ ሌላ ሀቅ ግን ያለምንም አሻጥር የኢትዮጵያ ወታደር ሲዋጋ የዶጋ አመድ እንደሚያደርጋችሁም አየን ! የኢትዮጵያን ሰራዊት ህወሀት አሸነፈው የሚለውን ነገር ሀሰትነት ለማሳየት ... እዚሁ ዋርካ ላይ በተለያየ ጊዜ ያደረግናቸውን ውይይቶች መለስ ብሎ ማየት !

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
This is not just the story of one ethical group ( tigrian gorillas ) as you claimed here , in fact it is one account of Ethiopianism , it justifies , the true picture of Ethiopians , I am very well aware of your motive , that tigreans are not part of Ethiopians , eat another, ( ሌላ ብላ ) it is just one description of the gallant sons and daughters of tigeans, (who are indeed Ethiopians no question about that..) Struggled inside Ethiopia to remove the tyrant regime. This is not a Hollywood made fiction clip but demonstrates the deep truth occurred in the northern mountains, valleys and gorges of tigrai region. The more I see a clip like that , the more I understand how we Ethiopians are committed and stand behind the cause even at the cost of our life! Last but not the least to learn true Ethiopianism , be Weyane first , and go to the bush not to a four star Marriott Hotel ! ቁረጽ በሎ ግፋ በሎ ..ብርቄ በሎ .. ወርቄ በሎ ..ደብሬ በሎ ..በሎ በሎ Laughing

ትልቅ ሰው እንደጻፈ(ች)ው:
You untrained and unethical tigrean, please do understand that this is a forum to discuss about Ethiopian issues, not for posting here and there your unvisited websites which are full of tigrean trashes Razz Here for example, I became so patient and clicked to visit what you, the tigrean racist posted. It is about your usual fictious stories of tigreans, while the facts tell us otherwise. You , the narrator in the clip and the actors in the fictious story are all racist tigreans and the story is of tigrean; nothing smells Ethiopian Razz

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
የሙሉ /እጊዚአብሄር እውነተኛ ታሪክ ::
እቺን ይጫኑ ::

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 4262

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 3:17 am    Post subject: Reply with quote

ቶማስ ጄፈርሰን ነው ማነው ...? ትንንሽ ጭንቅላቶች ፊደላትና ሆሄያት ላይ ትልልቅ ጭንቅላት ያላቸው ደሞ አስተሳሰብ ( ኮንቴንት ) ላይ ያተኩራሉ ያለው ...? በቶማስ አባባል ውስጥ ራስህን ፈልግና አግኘው አይተ ናፒ እኔን አትጨቅጭቀኝ :: Very Happy
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1874

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 5:40 am    Post subject: Reply with quote

Laughing ወይ እግዚያብሄር ! አንተም እንደዚህ አልክ ?!

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ቶማስ ጄፈርሰን ነው ማነው ...? ትንንሽ ጭንቅላቶች ፊደላትና ሆሄያት ላይ ትልልቅ ጭንቅላት ያላቸው ደሞ አስተሳሰብ ( ኮንቴንት ) ላይ ያተኩራሉ ያለው ...? በቶማስ አባባል ውስጥ ራስህን ፈልግና አግኘው አይተ ናፒ እኔን አትጨቅጭቀኝ :: Very Happy

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 2:30 pm    Post subject: Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
Laughing ወይ እግዚያብሄር ! አንተም እንደዚህ አልክ ?!
ናፖሊዮን ዳኘ ::

ያቶ ዳኘ ልጅ - ናፖሊዮን

እንዴት ሰነባብተሀል - በጅጉ ባያሌው :: ጩኅትህን ሰምቼ የወገን ሰቆቃ አላስችል ብሎኝ ልፈውስህ ላድንህ እነሆ መጥቻለሁ ::
ክታብህ እንደሚተረከው ባግርሞት የተዋጥክ የጥንት የጥዋት ወገን ትምሰላልክ ::

የጠዋት ጸሀይ ጮራ ሳይፈነጥቅ
አገር ጥሎ ወገን ድንገት ሲርቅ
ምንም ይሁን ምንም የያኔው ትውስታ
ጭራስ አይረሳ
አድማጭም ቢጠፋ
እድሜ ቢገፋ

ወገኔ የናፖልዮኑ
የዋሽራን ቅኔ እንዳልቅኝ
የወሎን ዝየራ
የሀረርን ምለላ
እንዳላሰማህ አቅም የለኝ
ታድያ ወገኔ
ሆዴ አንጀቴ
እንደዚህ የሚያጉዋራህ
እረፍት የነሳህ
እንዳው ምን ልክፍት ይሆን ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2
Page 2 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia