WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አያያዙን አይተህ ...

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ምረቱ

ኮትኳች


Joined: 14 Jan 2007
Posts: 285

PostPosted: Wed Mar 28, 2012 6:09 am    Post subject: አያያዙን አይተህ ... Reply with quote

""አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው "" ይላል Vaclav Havel ሲተርት ... የዘመናዊነት ክሊያንቶች እንዲያነቡት ያህል አቴንሽን መሳቤ እንጂ አባባሉስ የራሳችን ነው ::

ለነገሩ የህሊና ሰው ባለበት ጭብጧችንን እንዴትም አድርገን ብንይዘው ሊቀማ አይገባም ነገር :: መቀማትም መቀማትም በተለይ በኛ ሀገር ብዙ የተለመደ ነገር አልነበረም ... ጊዜ ተለወጠና ዛሬ ዛሬ ዓለም የቀማኞች ሆና ስታርፍ ቀማኛነትን ከመጋፈጥ ይልቅ ቀማኛነትን ራሺናላይ ማድረግ እየተለመደ መቷል ---ከፖለቲካ እሳቤ የሚጠጋ ሁሉ ቲዎሪ ሊወጣለት ሁሉ ይችላል ... ዓለም የወዛደሮች ትሆናለች የተባለው ቅዥት ሆኖ ቀርቶ ዓለም የሰዱቃውያኖች ...(የቱጃሮች ) ሆናለች :: ማሽቃበጥ የበዛው ግን በፈሪሳውያኑ (ሚድል ክላስ በሉት ...አይ ዶን !)

ለመሆኑ ግን እንደኢትዮጵያውያን ጭብጧችን ምን ነበረ ? እንዴትን አድርገን ይዘነው ነው ቀማኛ አይኑን የጣለበት እና ከእጃችን ላይ መመንጨቅ የጀመረው ??

ከዚህ በፊት እንደጠቃቀስኩት ማህበራዊ ግንኙነታችን ባህላችን እና እምነታችን ሁሉ ለኛ ጭብጧችን ነበር :: እንደ ሀገር ብዙ ችግሮችን እንድንቋቋም ብርታት የሆነልን ነገር ነበር :: ባህልን እና ማህበራዊ ግንኙነትን ለጊዜው በይደር ልተውና ( ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ ) ስለ እምነት ጭብጧችን ትንሽ ልበል ::

በክርስትና በኩል በመጀመሪያ አፍቃሪ ህወሀት የሆኑት እኚህ የተረገሙ ሰውየ ያላግባል ወደ ጵጵስና ሲመጡ ከጭብጧችን ከመንጠቅ ጋር ስለመያያዙ ሳይገባን ነገሩን በቸልታ በዝምታ እና በፍርሀት አለፍነው :: እኚሁ ሰውየ ውስጣቸው ጥቁር ሆኖ ሳለ ጭብጦ የሚቀማ ሰው ላለመምሰል ልብሳቸውን ቀይረው ነጭ ለብሰው ሲመጡ አንድ ሰሞን በነጻ ጋዜጦች ይሄ ነገር ትክክል አይደለም ተብሎ ተነስቶ ከመረሳቱ በስተቀር የተባለ ነገር አልነበረም :: እሳቸው ባስነሱት ቁጣ ምዕመናን በቤተክርስቲያ ሲጨፈጨፉ አሁንም አያያዛችን ልክ አልነበረም :: ቢዮንሴ ከስላሴ ጋር ነግሳ ካህናት ሲያሸበሽቡ አያያዛችን ትክክል እንዳልሆነ አልገባንም ነበር :: ወይንም እያወቅን ፈራን :: ያም አልበቃ ብሎ በህይወት እያሉ ሀውልት ሲያቆሙ ---ከጭብጧችን ጋር የማይገናኝ ይመስል ብዙ አልተባለም :: ቢዘገይም ሲኖዶሱ ነገሩ ልክ አይደለም ይፍረስ ብሎ ከወሰነ በኍላ አብነ ጳውሎስ አያያዛችንን አይተው በሆዳቸው እያላገጡ ሞቸ ነው ቆሜ የሚፈርሰው ሲሉ አያያዛችንን ጠበቅ አላደረግንም ... አሁንም አያያዛችንን ስላዮ የመጨረሻውን የእምነት ጭብጧችንን ---በገዳማቱ እና በገዳማዉያኑ ሲመጡ ጭብጧችንን በደንብ የያዝን ለመምሰል ከምናደርገው የፌስ ቡክ ስታተስ አፕዴት ውጪ ቁጣችንን ትርጉም ባለው እና ጠንከር ባለ ሁኔታ ለማሳየት አልሞከርንም :: ይባስ ብሎ እንደተበዳይ የህወሀት መንግስት ስለገዳሙ በመቆርቆር የተናገሩትን ማሳደድ እና ቤት መበርበር ጀመረ ... የጭብጦ አያያዛችንን ስለሚያውቀው !

በእስልምናውም በኩል ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያላቸውን የሀገር እና የወገን ፍቅር ለመሸርሸር እና ከክርስቲያኑ ጋር ለማጋጨት ብዙ ነገር ተሞከረ ...ጭብጧቸውን በዚህ ረገድ ደህና አድርገው ይዘው ስለነበር በተለያየ ጊዜ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ :: የእስልምና ጉዳዮችን ኢትዮጵያዊ ከሆነው እስልምና እጂ ለማውጣት በተለያየ ጊዜ ሙከራ ተደርጎ አንዋር መስጊድም እንደ እስጢፋኖስ ሁሉ በተኩስ ሩምታ ተቀውጦ ነበር ... እሱም የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጭብጦ ለመንጠቅ አላስቻለም :: በመጨረሻ ሌላ አስተምህሮ አምጥጦ በእንግሊዞቹ ብልጣብልጥነት ዘየ ጭብጦውን ለመቀማት ተሞከረ ..አውሊያን ለመንጠቅ ሞከሩ ...ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሰልፍ ወጣ የጭብጦውን አያያዝ ለማሳመር ሞከረ ...ለቀሚ አልመች አለ

በክርስትናው በኩል ግን ዝቋላ ሲቃጠል ዋልድባ ""የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን "" ቦታ ሆኖ በህወህት ሲመረጥ ቀብር በዶዘር ሲታረስ አሁንም አያያዛችንን ሳየው የሚቀማ ጭብጦውን የሚቀማ አይነት ነው :: ይሄኛውን ጭብጦ ከተቀማን ደሞ እኛ ማን እንደምንሆን ለመገመት አይከብድም ...ማንም !
_________________
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/294762583969356?ref=hl
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia