WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ወያኔዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሣያጠፉ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Sat Mar 31, 2012 11:34 am    Post subject: Reply with quote

ፈዛዛው የተዋህዶ ቄስ ዘመድኩንን ወደ ወያኔ ላማላጅነት ላከው ... ምናልባት ሀሳባቸውን እንዲቀይሩና ወደ ተለመደው የተዋህዶ የውሀላ ቀርነት ስርአት ይመለሱ ይሆናል ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Apr 01, 2012 2:21 am    Post subject: Reply with quote

ወርቅነች እንደጻፈ(ች)ው:
ፈዛዛው የተዋህዶ ቄስ ዘመድኩንን ወደ ወያኔ ላማላጅነት ላከው ... ምናልባት ሀሳባቸውን እንዲቀይሩና ወደ ተለመደው የተዋህዶ የውሀላ ቀርነት ስርአት ይመለሱ ይሆናል ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing


እዚህ በማይመለከትህ ቤት ገብተህ ከመዘባረቅ እዚያው የተቀጠርክበትን የአረብ ... ብታጸዳዳ አይሻልህም Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Tue Apr 03, 2012 8:13 am    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅ ..ፈዛዛው ይገርማል ደፋር ሆነህ መሳደብ ጀመርክ እንዴ ..ከቄሰ ሁሌም ትርፉ ይህ ነው ..ሁሌም ሀሳቡ እዚያው ነው Laughing የሰውን ሲያሰብ ገምቶ ይኖራል ..... መጨረሻው ከህጽናት ጋር ይያዛል ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ወርቅነች እንደጻፈ(ች)ው:
ፈዛዛው የተዋህዶ ቄስ ዘመድኩንን ወደ ወያኔ ላማላጅነት ላከው ... ምናልባት ሀሳባቸውን እንዲቀይሩና ወደ ተለመደው የተዋህዶ የውሀላ ቀርነት ስርአት ይመለሱ ይሆናል ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing


እዚህ በማይመለከትህ ቤት ገብተህ ከመዘባረቅ እዚያው የተቀጠርክበትን የአረብ ... ብታጸዳዳ አይሻልህም Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 03, 2012 11:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ሰለ ዋልድባ ገዳማት የወቅቱ ሁኔታ ከደጀሰላም ዘገባ ተከታተሉ ::

ምንጭ :- ደጀሰላም : ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2004 .. :: በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን /ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት )::

Quote:
· በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ ::
· በሊቀ ጳጳሱ አቋም ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዟል ::
· በዋልድባ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ እንዳይደርሱ በፖሊስ ታግደዋል ::
· የማኅበረ ቅዱሳን አጥኚ ቡድን ነገ ወደ ዋልድባ ያመራል ::

በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ከተማ ሰንበት /ቤቶች ጥምረትና የጥምቀት በዓል አከባበር ወጣቶች ማኅበራት ጥምረት ኮሚቴዎች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የስድስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጋራ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡

ወጣቶቹ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ የተነጋገሩት የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ የከተማው ከንቲባ /ቤት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዓምባ አዳራሽ ጠርቶት በነበረው ስብሰባ ላይ ብፁዕነታቸው ቀድሞ ከሚታወቀው አቋማቸው የተለየና ወጣቶቹን ያሳዘነ ንግግር በመናገራቸው ነው፡፡

መጋቢት 21 ቀን ከረፋድ እስከ ቀትር በሀገረ ስብከቱ /ቤት በተካሄደው ንግግር ሊቀ ጳጳሱ ምንም የአቋም ለውጥ እንደማያደርጉ ከመግለጻቸውም በላይ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ወጣቶቹን “በሞተ ጉዳይ ነው የመጣችኹ” ሲሏቸው ተደምጠዋል፡፡ “ከሞተም እናነሣዋለን፤ ቤተ ክርስቲያን አትሞትምና” በማለት በደጅ ጥናት ወደ ውስጥ የገቡት የወጣቶቹ ተወካዮችም በብፁዕነታቸው ንግግር ከፍተኛ ቅሬታ የተሰማውን ወጣት ሊቀ ጳጳሱ በጉባኤ ተገኝተው የሚያረጋጉበት ሁኔታ እንዲመቻች መስማማታቸው ተገልጧል፡፡

መጋቢት 19 ቀን 2004 . አቶ ኣባይ ፀሐዬና አቶ አያሌው ጎበዜ ከዞኑና ሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ጋራ በተገኙበት በፕሮጀክቱ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ዙሪያ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ፕሮጀክቱ በገዳሙ ህልውናና ክብር ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እንዳለው ከቤቱ ሲቀርቡ የነበሩ ተቃውሞዎችን በማጣጣል “የላክናቸውን እንቀበላቸው እንጂ” በሚል ወደ ዋልድባ ስለ ሄደው ቡድን የቀረበውን ዘገባ ተሰብሳቢዎቹ በእምነት እንዲቀበሉ አሳስበው ነበር፡፡ በተወያዮች የተነሡ ተቃውሞዎችን የሌሎችን ጩኸት መልሰው ከሚጮኹ አካላት ጋራ በማመሳሰል “ዝም ብላችኹ የምታስተጋቡ፤ ዋልድባን የመሠረተው ክርስቶስ ነው፤ እነዚያን አራቱን [በግድብ ሥራው የሚፈርሱትን አራት አብያተ ክርስቲያን ] ግን የወልቃይት ሕዝብ ነው የሰጣቸው” ሲሉ ተናጋሪዎቹን መውቀሳቸው ተገልጧል፡፡

በዕለቱ ስብሰባ መጠናቀቂያ ውይይቱን እንዲዘጉ በአቶ አያሌው የተጋበዙት ብፁዕነታቸው “ከዋልድባና ከገነት ማን ይበልጣል ? በሚል ጥያቄ ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት፡፡ ከጥያቄያቸው በኋላ ለቤቱ ባሰሙት በጽሑፍ የተዘጋጀ ንባብ÷ እግዚአብሔር ገነትን አስቀድሞ ካዘጋጀ በኋላ አዳምንና ሔዋንን እንደፈጠረ አስረድተዋል፤ ወዲያውም ገነትን አራት አፍላጋት እንደሚያጠጧት በመጥቀስ ከዋልድባ ገነት እንደምትበልጥ ከዘረዘሩ በኋላ “ወደ ዋልድባስ ውኃ ቢፈስ ችግሩ ምንድን ነው ? ብለዋል :: አያይዘውም “መነኰሳቱ ቋርፍ የሚያዘጋጁበት ስኳር የላቸውም እያላችኹ ከከተማ እየገዛችኹ ትወስዱ የለም ወይ ? አምና እንኳ አራት ኩንታል ስኳር ሰዳችኹ የለ ? ታዲያ ይኸው ስኳር እዚያው ቢመረት ችግሩ ምንድን ነው ? ለምን ታምፃላችኹ ? በማለት ለገዳሙ ህልውና እና ክብር ተቆርቋሪ የሆኑ ምእመናንን አንገት አስደፍተዋል፡፡ አንድ የዐይን እማኝ እንደተናገሩት “ሊቀ ጳጳሱ እንዲህ እያሳዘኑን በነበረበት ሰዓት አዳራሹን ትቶ ለመውጣት ከቋፍ የደረሰው ተሰብሳቢ ቁጥር ጥቂት አልነበረም” ብሏል፡፡

ሌሎች የዜናው ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ቀደም ሲል ባቀረብነው ዜና ዘገባ እንዳስነበብነው ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት ምልዓተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላኩት ጥያቄ በተሰማበት ሰሞን በከተማው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ጸሎተ ምሕላ እንዲያዝ ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማንም ሊገዳደረው በማይችል ሉዓላዊና ክህነታዊ ሥልጣኗ ያስተላለፈችውን ይህን የዐዋጅ ትእዛዝ እንደ ስጋት የተመለከቱ የዞን አስተዳደር /ቤት ሓላፊዎች መጋቢት አራት ቀን 2004 . ሊቀ ጳጳሱን፣ ሥራ አስኪያጃቸውንና ሌሎች የሀገረ ስብከቱን ክፍሎች ሓላፊዎች ስብሰባ ይጠራሉ፡፡

በስብሰባው ላይ በአንዳንድ ሓላፊዎች ዘንድ የጸሎተ ምሕላው ትእዛዝ የተላለፈበት ደብዳቤ እንደማስረጃ ተይዞ ጸሎተ ምሕላው የዐመፅ ቅስቅሳ መሣርያ ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ጸሎተ ምሕላ ለማወጅ ማንም ሊከለክላቸው እንደማይችል ለሓላፊዎቹ ግልጽ ያደረጉት ብፁዕነታቸው እንዲያውም የፕሮጀክቱ ቦታ ድረስ በመሄድ ግድቡ፣ የሸንኮራ ልማቱና የስኳር ፋብሪካው ገዳሙን አይነካም ስለሚባልበት ሁኔታ ከዚህ እስከዚህ ተብሎ ርግጡ እንዲነገራቸው እንደሚፈልጉ ቀጥተኛ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ ፕሮጀክቱ የሚሠራው ከክልሉ ውጭ ባለው የገዳሙ ክፍል (በትግራይ ክልል ) በመሆኑ “እንኳን እኛ [ዞኑ ] አያሌው [የክልሉ ፕሬዝዳንት ] መጠየቅ አይችልም” የሚል ነበር የተሰጣቸው ምላሽ፡፡ ይህን ተከትሎ ብፁዕነታቸው በሰጡት አስተያየት “ዋልድባ ዓለም አቀፍ ገዳማችን ነው፤ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም !! ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

እንግዲህ በሳይንስ ዓምባው አዳራሽ ብፁዕነታቸው የተናገሩት ቃል ከዞኑ ባለሥልጣናት ጋራ በተነጋገሩበት ወቅት ከነበራቸው ፈጽሞ ለመቃረኑ፣ የባለሥልጣናቱ ንግግር፣ ከዚያም ይልቅ ቀደም ሲል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ስም የተሰጠው መግለጫና በስብሰባው ለመሳተፍ ወደ ጎንደር ከመጡት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ //ሥራ አስኪያጅ የተፈጠረባቸው ከፍተኛ ጫና ሳይኖር እንደማይቀር በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች እንደተናገሩት //ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ውብሸት እንደ ዋነኛ ተግባር የያዙት ለመንግሥት አቋም ብቻ ጥብቅና የቆመ ስምሪታቸው (መንግሥት በይፋ ያመነውን እንኳ በጭፍን እስከ ማስተባበል ድረስ ) የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን ይኹንታ ያላገኘ ነው፡፡ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውና በንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ [ከዋልድባ ገዳም የተገኙ መነኮስ ናቸው ] የሚመራው የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የማያውቀው ወይም ተግባራዊ ተሳትፎው ያልተጠየቀበት ነው፡፡

ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ መጋቢት 19 ቀን ተደርጎ በነበረው ስብሰባ በዋልድባ ማኅበረ መነኰሳት ተልከው ወደ አዲስ አበባ የመጡት አባቶች “መዋቅር ጠብቀው ከእኛ ጋራ ባለመገናኘታቸው አጥፍተዋል፤ ጉዳዩን አቅርቡልን ስንላቸውም አላመጡም” በማለት ወቅሰዋል፡፡ “ችግሩን የሰማነው የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎች ባልሆኑት ፍትሕ ጋዜጣ እና ደጀ ሰላም ነው” ያሉት አቶ ተስፋዬ “ከዚያ በኋላ በእኔ የሚመራ ልኡክ ወደ ስፍራው ሄደን አይተን ችግሩ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡ እንዲያውም እኔ እንደ መሪነቴ መናገር ያለብኝ ኢሕአዴግ ለእኛ ያላደረገልን ነገር የለም፤ ደርግ የወሰደውን ንብረታችንን አስመልሶልናል፤ በጀታችን ተቀምቶ ነበር አስመልሶልናል፤ የቤተ ክርስቲያን መብቷ ተከብሮላት ነው ያለው፡፡ አሁንም አገሪቱ እያደገች ነው፤ የኑሮ ውድነት ተፈጥሯል፤ ምእመኑ ለሙዳየ ምጽዋት የሚሰጠው እያጠረው አብያተ ክርስቲያናት እየተቸገሩ ነው፤ ይህ የስኳር ፋብሪካ የልማቱ ውጤት . . . እያሉ በመናገር ላይ ሳሉ ከቤቱ ጉርምርምታ በመሰማቱ በአቶ አያሌው ትእዛዝ ንግግራቸውን እንዲያቋረጡ ተደርጓል፡፡

የአቶ ተስፋዬን ሐሳብ በመደገፍ እንደሚናገሩ ያመለከቱት የሰሜን ምዕራብ ትግራይ - ሽሬ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ተስፋይ ተወልደ፣ “ቦታው [ለፕሮጀክቱ የሚቀርበው ገዳመ ዋልድባ ] በእኛ ሥር ነው ያለው፤ በጎንደር ያለው ደልሽሐና ሰቋር አይደለም፤ ሄደን አይተነዋል፤ ሕዝቡ ስለማያውቅ ነው፡፡ አቤቱታ አቅራቢዎቹ መዋቅር አልፈው ነው የሄዱት፤ ሕገ ወጦች ናቸው” በማለት አሳጥተዋቸዋል፡፡ ነገሩ ሲከፋ ከቤቱ ለንቡረ እዱ የተሰጣቸው ምላሽ “ዋልድባ ለጎንደር ሕዝብ ይጠፋዋል ወይ ? ይህን እርስዎ ሊነግሩን አይችሉም !! የሚል እንደነበር ተመልክቷል፡፡

በኀይለ ቃል የታጀበውን ምልልስ የታዘቡ ወገኖች እንደሚሉት የገዳመ ዋልድባ ህልውና እና ክብር ተጠብቆ የመቀጠል አደጋ ምንጭ የፕሮጀክቱ አሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን ገዳሙ በትግራይም በአማራም ክልሎች መገኘቱን በሰበብነት የሚጠቀም ተቃርኖና መሳሳብ፤ ቤተ ጣዕማ እና ቤተ ሚናስ በሚል በማኅበረ መነኰሳቱ መካከል ተፈጥሮ የቆየና በአሁኑ ወቅት መዳከሙ የሚነገረው የነገረ መለኰት ልዩነት (በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አገላለጽ የሥላሴን አንድነት የሚያመለክተውን መለኰትን ለአካል ግብር ቅጽል አድርጎ በማቅረብ ሦስቱንም ወላድያን፣ ሦስቱንም ተወላድያን ሦስቱንም ሠራፅያን በማለት ግብርንና ስምን የሚያፋልስ፣ አንድነትና ሦስትነትን የሚያጠፋ የኑፋቄ ርዝራዥ ) ዛሬ ስልታዊ መከፋፈያም የመሆኑ አሳሳቢ አካሄድ ነው - በአንድ መቅደስ (መድኃኔዓለም እና ኪዳነ ምሕረት ) የሚቀድሱት የቤተ ጣዕማ ማኅበረ መነኰሳት ‹የልማቱ ደጋፊ› የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ደግሞ ‹የፕሮጀክቱ ተቃዋሚ› ተደርገው ተፈርጅዋልና !!

እውነቱ ግን “በገዳማችን ላይ የተጀመረው የውኃ ግድብ፣ በከባድ መሣርያዎች የአባቶቻችንን የቅዱሳን ዐፅም ማፍለስና የጥርጊያ መንገድ ሥራ፣ የፓርክ መከለል ያልታሰበ ክሥተት ሆኖብናል፤ የልማት ተቃዋሚዎች አይደለንም፤ የመንግሥት አካላት ግን ወደ ማኅበራችን መጥተው ምንም ያሳወቁን ነገር የለም፤ የመንግሥት ዓላማና ዕቅድ አልገባንም፤ መንግሥት ኀዘናችንንና ጩኸታችንን ይስማ ! በማለት ታኅሣሥ 30 ቀን 2004 . በሦስት አበምኔቶች በተፈረመበትና የሦስቱም ማኅተም ባረፈበት ደብዳቤ ጥያቄ ያቀረቡት ግን፡ - የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ምክሆን ለገዳማተ ኢትዮጵያ ማኅበር ዘቤተ ሚናስ፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ዋሊ ቅድስት ደቂቁ ለሳሙኤል ርእሰ ገዳማት ዘኢትዮጵያ አስተዳደር /ቤት፣ በዓዲ አርቃይ ወረዳ ቤተ ክህነት የዋልድባ ዳልሽሐ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በጋራ ሆነው ነው፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ እንደ ቆመ የሚነገረው ፓርክ የመከለል ዕቅድ በዓዲ አርቃይ ወረዳ - ሰሜን ጎንደር በኩል ነው፤ አቶ ኣባይ ‹አሉባልታ› ያሉት መንገድ የማውጣቱ አማራጭ ውጥን በዚሁ በኩል እንደሆነም ምንጮቻችን ያሳያሉ፤ ግድቡ የሚቆምበት የዛሬማ ወንዝ ደግሞ በወልቃይት ወረዳ - ምዕራብ ትግራይ በኩል የሚገኝ ነው፡፡

ማኅበረ መነኰሳቱ በደብዳቤያቸው እንደጠቆሙት፣ በጎንደሩ ስብሰባም ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም ለመረዳት እንደተቻለው “የገዳማችን አፈር /መሬት የደማችን ያህል ይሰማናል” ሲሉ የተደመጡት መነኰሳቱ በልማት ዕቅዱ ዙሪያ ከመንግሥት አካላት ጋራ አልተወያዩም፡፡ ይህም አቶ ኣባይ ፀሃዬ በውይይቱ መግቢያ ላይ “ሕዝብ አወያይተን ነው ወደ ሥራ የገባነው” ካሉት ጋራ የሚጋጭ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እርሳቸው የሚሉትን አምነን እንቀበል ቢባል እንኳ ውይይት የተባለው የተካሄደው በፕሮጀክቱ ከሚነሡት ወገኖች ጋራ እንጂ መነኰሳቱን አያካትትም፡፡

አቶ ኣባይ በሰጧቸው ማብራሪያዎች ከእውነታው ጋራ ተጋጭቶ የተገኘው ይህ ብቻ ሳይሆን÷ ለአፈር ምርምራ በሚል ወደ ገዳሙ ይዞታ የተገባው በዶዘር በማረስ መሆኑ፣ በገዳሙ ክልል ከተቀበሩቱ 27 ዐፅሞች በመንገድ ሥራው መነሣታቸው ሳያንስ መንግሥት ባልተሰጠው ሥልጣን “ቀባሪ ዘመድ የሌላቸው የድኾች ዐፅም እንጂ የቅዱሳን አይደለም” መባሉ ይገኙበታል፡፡
በስብሰባው ዕለት ለአቶ ኣባይ ፀሃዬ ቀርበው አሳማኝ ምላሽ ያላገኙ የተወያዮች ጥያቄዎች ለማስረጃም ለማገናዘብም ይጠቅማሉና እንደሚከተለው አጠቃለናቸዋል፡፡

· በቴሌቪዥን ዜና ሰዓት በሰጡት መግለጫ ገዳማቱ ውስጥ የፖሊቲካ ተልእኮ ያላቸው መነኰሳት እንዳሉ በመጥቀስ ስለ አባቶቻችንንና ስለ ገዳሙ በድፍረት ተናግረዋል፡፡ አባቶቻችንም ገዳሙም እርስዎ እንዳሏቸው የፖሊቲካ ተልእኮ ያላቸውና የፖሊቲከኞች መናኸርያ አይደሉም፡፡ [አቶ ኣባይ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “እንዲህ ያልኹት የመነኰሳቱ አቤቱታ መዋቅር ጠብቆ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ይኹን ለክልሉ ሳይደርስ በውጭ ሚዲያዎች እንደቀረበልን ተደርጎ መነገሩ የመንግሥትን ስም የማጥፋት ዘመቻ ያለው የፀረ ሰላም ኀይሎች ፖሊቲካዊ ተልእኮ በመሆኑ ነው” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ አቶ ኣባይ ይህን ቢሉም መልእክተኞቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፊት ተነስቷቸው ከተመለሱ በኋላ አቤቱታቸውን የያዘውን ደብዳቤ በተለያየ መንገድ ለቢሮው መላካቸውን አልገለጹም፡፡ ]

· በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የቀረቡ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ብዙ የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን እንዳሉ ተናግረዋል፤ ያረጋግጡልን ?
· 50,000 ሰው ይቀጠራል፤ 5000 ቤቶች ይሠራሉ” ብላችኋል፡፡ እንግዲያውስ ገዳሙ ከተማ መሆኑ ነዋ !! መነኰሳቱኮ እዚያ ድረስ የሄዱት ዓለምን ጥለው፣ ጥሞናን ሽተው ነው፡፡
· 27 ዐፅም አንሥተናል ብላችኋል፤ እኒህ ወገኖች የተቀበሩት ቅዱሱ ቦታ ላይ ነው፡፡ እናንተ ግን “አቅም፣ ዘመድ የሌላቸው የድኾች አስከሬን ነው” አላችሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ቀባሪ አጥተው አያውቁም፡፡ እንኳን በዋልድባ በሌላ ቦታ እንዲህ ዐይነት ቀብር የለም፡፡ በዚህ ላይ ዐፅሞቹ የቅዱሳን ዐፅም አይደሉም ብላችኋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንጂ እናንተ ይህን መወሰን ትችላላችኹ ወይ ?
· “ሕዝቡ ሲነሣ ማኅበራዊ ተቋሙ አብሮ ይነሣል” ብላችኋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ተቋም ውስጥ አለችበት ወይስ የለችበትም ?
· “የግድቡ ውኃ ወደ ገዳሙ አይሄድም” በሚል ገዳሙ አልተደፈረም ብላችኋል፤ “ኀጢአት አይሻገርብሽ” ሲባልኮ የገዳሙን ወገብና እግር ትቶ ጭንቅላቱን ሲነካ ብቻ አይደለም፡፡ ውኃው የሚያርፍበት፣ ዐፅሙ የሚነሣበት ቦታ የገዳሙ ይዞታ ነው፡፡
· በመዘጋ በኩል የመነኰሳቱ የአትክልትና ቋርፍ ማዘጋጃ ቦታዎች ይነሣሉ፤ መነኮሳቱ ምን እየበሉ እንዲኖሩ ነው ?
· ደርግ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ አያውቅም፤ እናንተ ግን በልማት ቤተ ክርስቲያን እያፈረሳችኹ ነው፡፡
· የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን እያስፈራራችኋቸው ነው፡፡ ይህ መቆም የለበትም ?
የሚሉ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በስብሰባው ላይ “ወደ ዋልድባ በሄደው የሀገረ ስብከቱ ልኡካን ቡድን ውስጥ የማኅበሩ ጎንደር ማእከል ተካቶ ሳለ ለምን አብሮ አልተጓዘም” በሚል ለቀረበው ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ መልአከ ሕይወት ቀለም ወርቅ ስለ ገዳሙ የሚነሣውን ጥያቄ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን በመግፋት “በመኪና እጥረት የማእከሉን ተወካዮች ይዘን መሄድ አልቻልንም” የሚል ለማንም መስሎ ያልታየ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ልኡክ ተቀባይነት እንዳይኖረው ካደረጋቸው አካሄዶች አንዱም የማኅበሩ አባላት እንዲካተቱ አለመደረጉ መሆኑ ከተሳታፊዎቹ ተነግሯቸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ማኅበረ ቅዱሳን ለሀገረ ስብከቱና ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ደብዳቤ ጽፎ ባገኘው ፈቃድ አምስት አባላት ያሉት አጥኚ ቡድን ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ልኮ ይፋዊ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡ ከማኅበሩ ዋናው /ቤት፣ መቐለ እና ጎንደር ማእከላት የተውጣጡ አባላት የሚገኙበት ይኸው አጥኚ ቡድን በነገው ዕለት ወደ ስፍራው እንደሚንቀሳቀስ የሚጠበቅ ሲሆን ለቤተ ክርስቲያንም ለአገርም ጠቃሚ የሆነ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከዓመታት በፊት (1990 .) ከገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት ጋራ በመተባበር ለዘመናዊ ወፍጮ ተከላ፣ ለመጠጥና መስኖ ውኃ ልማት የአምስት ሚልዮን ብር የልማት ፕሮጀክት ቀርጾ ለሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሀገረ ስብከት /ቤት አቅርቦ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በተመለከተው የቤተ ጣዕማ - ቤተ ሚናስ ልዩነት ሳቢያ አንዱ ቤት ሲቀበል ሌላው ቤት በመቃወሙ ሳይተገበር መቅረቱ ተዘግቧል፡፡ የቡድኑ ጉዞ በዚሁ የልማት ዕቅድም ላይ ያለውን መሳሳብ በማስወገድ አንድ መግባባት ላይ ለመድረስ እንደሚያስችል ተስፋ ተደርጓል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት ዓርብ፣ መጋቢት 21 ቀን 2004 .ም፣ ወደ ዋልድባ ገዳም ያመሩት በጎንደር የስድስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት አባላት የሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ማምሻውን ወደ ጎንደር ከተማ መመለሳቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ መጋቢት 27 በአብረንታንት መድኃኔዓለም የሚከበረውን በዓል በማዘከር፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት በሳይንስ ዓምባው አዳራሽ ስብሰባ “ሄዳችሁ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” በማለት የሰጡትን ማረጋገጫም መሠረት በማድረግ ነበር ወደ ገዳሙ ያመሩት፡፡
ተማሪዎቹ ከቦታው ደርሰው የዋልድባ ገዳም መሥራች የሆኑትን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል (ሳሙኤል ፀሐይ ዘዋሊ ) መቃብርና የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተሳልመዋል፤ የማኅበረ መነኰሳቱ ምልዓተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላኩትን ደብዳቤ ተመልክተዋል፡፡

በደብዳቤው ላይ በተዘረዘረው መሠረት ገዳማውያኑ በፕሮጀክቱ ምክንያት ስለሚነሡት አብያተ ክርስቲያን፣ የሙዝ ተክላቸውና ቋርፍ የሚያዘጋጁባቸው ቤቶች በሚካሄደው እርሻ ስለሚጠፋበት ሁኔታ፣ ስለሚፈርሱት የገዳሙ አብነት /ቤቶችና ይህን ተከትሎ ስደት ስለሚጠብቃቸው መምህራንና ተማሪዎች በዝርዝር እንዳስረዷቸው ተገልጧል፡፡ በተለይ የሙዝ ተክሉ ከተነሣ መነኰሳቱን በስፍራው የሚያቆያቸው ድርጎ ባለመኖሩ ይኸው ጉዳይ በማይ ፀብሪው ስብሰባ በተነሣበት ወቅት ባለሥልጣናቱ “በስድስት ወር የሚደርስ ሙዝ እንሰጣችኋለን” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ገዳማውያኑ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ፕሮጀክቱ ከገዳሙ ጋራ ወደሚገናኝበት ስፍራ መጓዛቸውን የተናገሩት ተማሪዎቹ በፖሊስ ኀይል ከመንገድ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ “በማንኛውም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ መግባት እንደሚቻል ይኹንና በተለይ በፕሮጀክቱ በኩል ከገዳሙ መውጣት የተከለከለ ነው” ስለመባላቸው ያስረዱት ተማሪዎቹ በቋንቋ እንኳ ከፖሊስ ኀይሉ ጋራ መግባባት እንዳልቻሉ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ኾኖ ከገዳሙ ወጥተው ወደ ጎንደር በሚመለሱበት ወቅት በርካታ ምእመናን መጋቢት 27 ቀን ለሚከበረው የመድኃኔዓለም በዓል ወደ ገዳሙ እየተጓዙ መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Wed Apr 04, 2012 7:05 am    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅቅቅ ...ፈዛዛው የእብዶች ጉዞ እንደቀጠለ ነው በለኛ ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Apr 07, 2012 11:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በወያኔዎች የዕመቃ አገዛዝ ሥር ችግር ላይ የወደቀው የዋልድባ ገዳም መናንያን ወቅታዊ ሁኔታ :-

ምንጭ :- ደጀ ሰላም ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2004 . :: ለቪኦኤ የተናገሩት የዋልድባው አባት በፖሊስ እየታደኑ ነው ::

Quote:
· ያሉበትን ካልጠቆማችኹ በሚል ሦስት ገዳማውያን ታስረው ተፈተዋል ::
· እስሩና ‹አደኑ› የቤተ ሚናስ መነኰሳት በተለይም 1997 . ወዲህ ለሚደርስባቸው ልዩ ጫና ግልጽ አመልካች ነው ተብሏል ::
· 1980 . የገዳሙን ሰሜናዊ ክፍል (በእንስያ ወንዝ ) የጦር ካምፕ ለማድረግ የተቃጣው ሙከራ በኅቡኣን አበው ኵናት መወገዱ ተነግሯል ::


የመንግሥት ባለሥልጣናት በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ ከሚያደርሱባቸው ወከባና ማስፈራሪያ እንዲታቀቡ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሦስት የገዳሙ ማኅበር አባላት በፖሊስ ታስረው መፈታታቸው ተሰማ፡፡ መነኰሳቱ ለእስር የተዳረጉት “ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት አባት የት እንዳሉ ተናገሩ” ከሚል የፖሊስ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ መረጃ ኮማንደር በየነ በሚባል የፀለምት ወረዳ ፖሊስ መጋቢት 23 ቀን 2004 . ከገዳሙ የተወሰዱት ሦስቱም ታሳሪዎች በገዳሙ በዲቁና የሚያገለግሉ ሲሆኑ ከሦስቱ ሁለቱ መናንያን መሆናቸው ተገልጧል፡፡

በደረሰን መረጃ መሠረት መጋቢት 23 ታስረው ከሁለት ቀናት በኋላ የተለቀቁት ገዳማውያን በስም ዝርዝራቸው ዲያቆን ገብረ ጊዮርጊስ /መናኝ / ዲያቆን ገብረ ትንሣኤ /መናኝ / ዲያቆን ገብረ ሥላሴ /ረድእ / እንደሆኑ ተረድተናል፡፡ ይህም ሆኖ በማኅበረ መነኰሳቱ ተወክለው ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የዐማርኛው አገልግሎት ጋራ ስለ ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት አሉታዊ ተጽዕኖ ቃለ ምልልስ ያደረጉት አባት (ስማቸውን ለጊዜው በይፋ መግለፁን አልፈለግንም ) እስከ አሁን የት እንደሚገኙ አለመታወቁ ተመልክቷል፡፡

እኒህ አባት ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ቃለ ምልልስ መስጠት ብቻ ሳይሆን በማኅበረ መነኰሳቱ ሙሉ ስምምነት ከፕሮጀክቱ የተነሣ ገዳማውያኑ ያደረባቸውን ሐዘንና ጭንቀት የሚገልጽና ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአድራሻ የተጻፈውን ደብዳቤ እንዲያደርሱ ወደ አዲስ አበባ ከተላኩት መነኰሳት አንዱ ናቸው፡፡ ፖሊስ እርሳቸውን ለመያዝ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደ ቀጠለ እየተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መነኰሱ በገዳሙ እንደማይገኙ ተዘግቧል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን የማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ መረሳ በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሁለቱም ቤቶች ተወክለው ወደ አዲስ አበባ የተላኩት መነኰስ በብዙኀን መገናኛ ቀርበው ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መሆኑን፣ በፕሮጀክቱ ዙሪያ ስጋቶች ሊነሡ እንደሚችሉና ለምን ተነሡ እንደማይባል ነገር ግን አጀንዳው “የምቀኝነትና ኾን ተብሎ ሕዝብን ለማነሣሣት” እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡ ገዳማዊው አባት በበኩላቸው ስለተላኩበት ጉዳይ ለሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን በተመለከተ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ለሚዲያ የተናገርኹት ሃይማኖቴ ስላስገደደኝ ነው” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ እርሳቸው ለቪኦኤ ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎና አሁን በፖሊስ ከሚደረግባቸው ክትትል ቀደም ብሎ “እውነተኛ የገዳሙ መነኵሴ አይደሉም፤ በገዳሙም አይኖሩም” በሚል ስለተነዛባቸው ስም ማጥፋትም “ያመነኰሱኝ አባት በገዳሙ ይገኛሉ፤ የኔ ቆብ ከመርካቶ የተሸመተ አይደለም፤” ብለው መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡ በዕርግና ምክንያት ከአበምኔት ሓላፊነታቸው የተገለሉት መምህር አባ ገብረ ክርስቶስ የተባሉ አባትም ይህንኑ ቃላቸውን ለሬዲዮ ጣቢያው ማረጋገጣቸው ተዘግቧል፡፡

1997 . ምርጫ ውዝግብ ወዲህ ክልላዊ የአስተዳደር አካላት በተለይም የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን “በሽሬ፣ ወልቃይትና ፀገዴ ለተቃዋሚዎች ቀስቅሳችኋል” በሚል የሚያደርጉባቸው ተጽዕኖ የተለያዩ ሰበቦችን ሽፋን በማድረግ ከመቀጠሉም በላይ እያደር እየተጠናከረ መምጣቱ ይነገራል፡፡

በሌላ በኩል ለመነኰሳቱ ቅርበት ያላቸው አንዳንድ ወገኖች ገዳማውያኑን በመጥቀስ እንደሚናገሩት÷ እነአባ አቤቱታቸውን ለክልልና የዞን አስተዳደር ቢሮዎች፤ ለአህጉረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት /ቤቶች በግልባጭ÷ ለፌዴራል መንግሥቱ ርእሰ መስተዳድር አቶ መለስ ዜናዊ በአድራሻ ለማድረስ አነሳስቷቸዋል ብለው ከሚያምኗቸው የማይዘነጉ አጋጣሚዎች መካከል ሁለት ታሪካዊ ክዋኔዎችን ይጠቅሳሉ፡፡

አንዱ ኢሕአዴግ የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት 1980 ግድም የሆነ ነው፡፡ የመረጃው ምንጮች ቁጥራቸው “ከአንድ ሺሕ አያንሱም” በሚል የሚገምቷቸው የኢሕአዴግ ታጋዮች የእንስያን ወንዝ ድልድይ ተሻግረው ወደ ገዳሙ ገብተው ሰፈሩ፤ ገዳሙ አምሳለ ጦር ሰፈር /ካምፕ / ሆነ፡፡ በዚህም ገዳማውያኑ በእጅጉ ቢያዝኑ ከታጋዮቹ 80 ያህሉ ሞተው ይገኛሉ፡፡ ከእኒህም ጥቂቶቹ ለቅዱሱ ቦታ የማይገባ ተራክቦ ሲፈጽሙ የዞረባቸው ዘንዶ ትንፋሽ ያልፈሰፈሳቸው ሲሆኑ የተቀሩትም ቦታው አይረክስም የሚሉ ኅቡኣን ኵናት የቀሠፋቸው ናቸው፡፡ መነኰሳቱ የገዳሙ ክብር የተገለጠበትን ይህን ፍትሐ እግዚአብሔር (ተግሣጽ ) ለህወሓት /ኢሕአዴግ ሊቀ መንበር በማለበም፣ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ዐቃጅና ተግባሪም ፌዴራል መንግሥቱ በመሆኑ የፕሮጀክቱ አግባብነት እንዲፈተሽ ማሳሰብ በሚል ቀናነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጥታ / በአድራሻ ለመጻፍ እንደቆረጡ ምንጮቹ ይናገራሉ፡፡

ለቤተ ክህነቱ አካላት በግልባጭ ብቻ ከማሳወቅ በቀር በአካል ያልሄዱበት ምክንያት ደግሞ ገዳማውያኑ ቢያንስ 16 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲያመለክቱበት ለነበረው ችግራቸው ተቋሙ መፍትሔ ሊሰጣቸው አለመቻሉ ነው፡፡ ይኸውም በሁለት ክልላዊ መስተዳድሮች የባለቤትነት ውዝግብ መካከል የቆየው የዋልድባ ገዳም “ለጸጥታ አጠባበቅ እንዲያመች” በሚል እስከ ዳልሽሓ እና ሰቋር ድረስ ያለው ወደ አማራ ክልል ከማኅደሮ ወዲያ ያለው የገዳሙ ክፍል ደግሞ ወደ ክልል ትግራይ እንዲሆን 2000/01 . መወሰኑን ምንጮቻችን ያስረዳሉ፡፡

ይህም ኹኔታ በቀድሞው መንግሥታት ወቅት ልዩ ሥራ እንዳይሠራበት በዐዋጅ ተከብሮ የቆየው የገዳሙ ክልል ከብቶች እንዲሰማሩበት፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ዕጣን መቃሪዎች (ለቃሚዎች ) እና ወርቅ ጫሪዎች (ቆፋሪዎች ) በተለይ በማይ ሰሪ ወንዝ በኩል ያለከልካይ አልፈው ጎጆ ቀልሰው እንዲሰፍሩ በር ከፍቶላቸዋል፡፡ በዚህም በበጋ ወቅት መንሥኤው በማይታወቅ ቃጠሎ በየጊዜው የሚጠፋው ደን ሳያንስ በርካታ ጠቀሜታ ያላቸው ዕፀዋት ፈልሰዋል፤ የማር አዝመራ የሚቆረጥባቸው ዕፀዋት ሳይቀሩ እረኛው በልምላሜ እየቆረጣቸው በቁማቸው ደርቀው ቀርተዋል፤ የግሑሳን መሳፈርያ የነበሩ የዱር እንስሳት ተሰደዋል፤ መንፈሳዊ ተጋድሎና ቅድስና ሽተው ዓለሙን ንቀው የመጡ አባቶችም ተረብሸዋል፡፡

ማኅበረ መነኰሳቱ ይህንኑ ችግራቸውን መጋቢት 27 ቀን 1989 . በገዳሙ ለተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በወቅቱ አበምኔት መምህር አባ ተጠምቀ ገብረ ኢየሱስ በኩል አቅርበውላቸው ነበር፡፡ ሚያዝያ 30 ቀን 1989 . ታትሞ የወጣው ልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ መጽሔት “ከአምስቱ ፓትርያሪኮች ዋልድባን ለመጎብኘት የመጀመርያው ናቸው” በተባሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በተገኙበት በአበምኔቱ የተሰጠውን መግለጫ እንደሚከተለው አቅርቦት ነበር፡ -

. . . ወኵሉ ፍጥረት ተፈሥሓ በምጽአትከ ባለው መሠረት በቅዱስነትዎ መምጣት ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶናል፤ ደስታውም የእኛ ብቻ ሳይሆን የዓለሙ ሁሉ ደስታ ነው፡፡ በዚህ ገዳም ያለፉት ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ እየተደሰቱ ነው፡፡ አባትዎ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ‹መጥቼ አየዋለኹ› በማለት ተስፋ ሰጥተውን ነበር፤ ነገር ግን እንዘ ወልድየ አንተ ኮንከኒ አበ እንደተባለው እርሳቸው በመንፈስ እርስዎ በአካል በመምጣትዎ ተድስተናል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፡ - ከዚህ ቅዱስ ስፍራ ብዙ ሥራዎች አሉ፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መጥተው ከስውራኖች [ኅቡአን ] ጋራ የተነጋገሩት ከዚህ ገዳም ነው፤ ቀጥሎም አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ 70 ዓመት ተቀምጠው ዐርፈውበታል፤ እንዲሁም በእርሳቸው እግር የተተኩ ብዙ ቅዱሳን ፈልሰውበታል፡፡

ይህ ገዳም በኢትዮጵያ ካሉት ገዳማት ቀዳሚነት ያለውና ተወዳዳሪ የሌለው ገዳም ነው፡፡ በዚህ ቅዱስ ቦታም ብዙ የበርሓ አራዊት ይገኙበታል፡፡ እንደ ድሮው አንበሳ እንኳ ባይገኝ እንደ ነብር፣ አጋዘን፣ ወደንቢ፣ ድኵላ . . .በብዛት ይገኙበታል፡፡ አሁን ግን ችግሩ ይህ የቅዱሳኖች ዋሻና የአራዊት ደን ቦታችን የከብቶች ማሰማሪያ በመኾኑ ቅዱሳኖች በመረበሽ አራዊቱም በመሰደድ ላይ መኾናቸው እንዲታወቅልን እንወዳለን፡፡ . . .ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፡ - . . . በየቦታው ርዳታ ማድረግና የልማት ዘርፎችን መዘርጋት ልማዱ የኾነው ቅዱስነትዎ ረድኤትና ጸሎት በማንኛውም ወቅት ከገዳማችን እንዳይለይብን እንጸልያለን በማለት አሳስበዋል፡፡”

እንደ መጽሔቱ ዘገባ ፓትርያሪኩ በወቅቱ ለገዳሙ መናንያንና አገልጋዮች መነኰሳት የኀምሳ ሺሕ ብር የገንዘብ ርዳታ፣ መስቀሎችን፣ ጃንጥላዎችን፣ መጎናጸፊያዎችንና ምንጣፎችን የመሳሰሉ የንዋየ ቅድሳት ስጦታ፤ በራሳቸው የሚገለገሉባቸውን የራስ አክሊል፣ የደረት አይከን፣ የእጅ አርዌ ብርትና ሙሉ አልባሳት ለገዳሙ መገልገያ ይኾን ዘንድ ጨምረው አበርክተዋል፡፡

ይኹንና ፓትርያሪኩ በቤተ ክርስቲያን ስም እንደሰጡት የተገለጸው የብር ርዳታ ይቅርብን ወይስ እንቀበል በሚል አነጋግሮ እንደነበረው ሁሉ በቃለ ቡራኬያቸውም ወቅት፡ - “ገዳሙ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ከመናንያኑ የቋርፍ ምግብ በስተቀር እህል ውኃ ስለማይቀመስበትና ሴቶች እስከተወሰነ ቦታ ድረስ ስለማይገቡበት መንፈሳዊውን አገልግሎት በአንድነት ለመስጠት አስቸጋሪ ሆኖ የቆየ በመሆኑ ወደፊት ለሁሉም በሚያመች አማካይ ስፍራ ሁሉም በአንድነት አገልግሎት የሚያገኙበት ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ” ሲሉ በትግርኛም በአማርኛም የሰጡት መምሪያ በማኅበረ መነኰሳቱ ዘንድ ከፍተኛ ጥርጣሬና ቍጣ ቀስቅሶባቸው እንደነበርም የመረጃው ምንጮች ያስታውሳሉ፡፡

አሁን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት በፕሮጀክቱ ላይ የሚቀርቡትን የመነኰሳቱን ስጋት አለመልካቸው መልክ መስጠታቸው “ሁሉም አገልግሎት የሚያገኙበት ቤተ ክርስቲያን ይሠራ” በሚል ሽፋን የገዳሙን ሥርዐት ለመከለስ የሚሹትን የአቡነ ጳውሎስን መመሪያ በስኳር ፋብሪካ ግንባታና በሸንኮራ ልማት አጋጣሚ ለማሳካት የሚደረግ መፍጨርጨር ተደርጎ ተወስዷል፡፡

በገዳማውያኑ ጸሎትና ሕዝቡ በጻፈላቸው ግልጽ ደብዳቤ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱ በሚነገርለት በዚሁ የአቡነ ጳውሎስ መመሪያ አዝነውና አልቅሰው በወቅቱ ፓትርያሪኩን ፊት ለፊት የተቃወሙና ያስጠነቀቁት (ከቤተ ጣዕማም ከቤተ ሚናስም ) እንደ አባ ተስፋ ሚካኤል፣ አባ ቃለ ጽድቅ እና አባ ገብረ ሥላሴ የተባሉ አበው መነኰሳት በፓትርያሪኩ ባለሟሎች ‹እብዶች› በሚል ተዘልፈው እንደነበርም ምንጮቹ አይዘነጉም፡፡

ጥቡዐኑ መነኰሳት የተቆጡት “ሰምተነው አናውቅም” ባሉት በዚሁ የፓትርያሪኩ ንግግር ብቻም አልነበረም፤ በጉብኝቱ ወቅት “ገዳሙን የጦር አውድማ አስመስሎት ነበር” በሚል የተነቀፈው ለአቡነ ጳውሎስ የተደረገ ወታደራዊ እጀባ እና ውጠራም ጭምር እንጂ፡፡ ይኸው 1989 . ለሃይማኖት አባት ሊደረግ ከሚያስፈልገው በተጋነነ መልኩ ታይቶ የነበረው የኀይል ስምሪትና ውጠራ ፓትርያሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ገዳሙ በመጡበት 2002 . ከበፊቱ በተጠናከረ አኳኋን መደገሙ በተአምኖ እግዚአብሔር ብቻ ላይ ጸንተው የኖሩትንና የሚኖሩትን አበው ልብ በእጅጉ ያሻከረ እንደሆነ ነው ምንጮቹ ለማብራራት የሚሞክሩት፡፡

እናሳ ? በአጠቃላይ በዘላቂ ሥነ ልማት አስተምህሮ አግባብ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖው በሚዛን ታይቶ ቢታቀድ፣ መንግሥት እንደሚለው የአገር ውስጥ ስኳር ፍጆታን ከማሟላት አልፎ በዓለም አቀፍ ገበያ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘት፣ የኢንዱስትሪ ልማቱን በማስፋፋት የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማረጋገጥና የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ የሚጠቅመው የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ÷ የገዳሙን ህልውናና ክብር የሚፈታተን፣ ከዚህም አልፎ ቀደም ሲል ከተጠቀሱት አጋጣሚዎች ጋራ እየተሸመነ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መለዮ የኾኑ ገዳማትን የማጥፋት ተልእኮ ተደርጎ ባልተወሰደ ነበር !!

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Sun Apr 08, 2012 10:40 am    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅ .... ፈዛዛው ... የስኳር ፋብሪካ ...የልማት ተቋማት ቅብጥርሰ አያስፈለፈውም ተዋህዶ መጥፋቱ የማይቀር ሳይታለም የተፈታ ሀቅ መሆኑ እመን ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Apr 13, 2012 7:14 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-

የሚከተለው ጽሑፍ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊነበብ የሚገባው ነው ብዬ አምናለሁ ::

ምንጭ :- አዲሱ ተስፋዬ መንግሥቱ : ጥር 6 ቀን 2004 ..::የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን የማፈራረስ ሴራና ትግበራ፡ ከደደቢት እስክ አራትኪሎ ቤተ ክህነት ::

Quote:
“የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል”

Addisu Tesfaye Mengistu

የህወሀት ( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በቅርቡ A Political History of the Tigray Peoples Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ÷ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ÷ ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ÷ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች÷ ስለ ጦርነቱ ÷ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።

እኔን ግን የሳበኝ ህወሀት ወይም ወያኔ ÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ ከበረሀ ጀምሮ የሰራውን ደባ የሚያትተው ክፍል ነው።ዶክተር አረጋዊ በዚሁ መጽሀፋቸው ምእራፍ አስር ላይ Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ህወሀት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደተዋጋትና አሁን ቤተ ክርስትያና ውስጥ የሚታዩት አበይት ችግሮች በሙሉ ህወሀት ከበረሀ ጀምሮ ያቀዳቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጠውታል።

ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ ?

ይህን መጽሀፍ ሳነብ ዋናው ጥያቄዬ የነበረው “ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ ? የሚለው ነበር።ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበትን ምክንያቶች ዶክተር አረጋዊ አንድ ባንድ አስቀምጠውታል።በሚገርም ሁኔታ አንዱና ዋናው ምክንያት የቤተክርስትያኗ ብሔራዊ አስተምህሮ ÷ መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ መሆንና በባንዲራና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል።

A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag an act also regularly observed …’ page 244

The pragmatic TPLF understood the churchs role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause page 245

የአኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በህዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና ቤተ ክርስትያና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም እግዚአብሄር የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟና በባንዲራ ላይ ያላት ጽኑ አስተምህሮናና የመገንጠል ተቃዋሚ መሆኗ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ እማኝነታችውን ከገለጡ በሁዋላ ወያኔ ቤተከርስትያኗ ላይ ያሳረፈውን በትር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል።

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ማደንዝዝና መቆጣጠር

በብሔራዊ ማንነትና በሀገር አንድነት ላይ ቤተክርስትያኗ የያዘችው ጽኑ አቁዋም ያበሳጨው ህወሀት ቤተ ክርስትያኗን ለማደንዘዝና ለመቆጣጠር የለኮሰውን ባለ ሶስት ዘርፍ የጥቃት ዘመቻ እንዲህ ሲሉ ይዘረዝሩታል

አንደኛ ቤተክርስትያኗ በህዝቡ ዘንድ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስትያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ

the second step was to try and move the socio economic focus of life from the church to the peoples assemblies. All administrative and social activities were taken over by the associations and the baitos and even church affair such as the rights and obligations of the church and its followers fell under the jurisdiction of the assemblies. The capacity of the church to mobilize and influence waned. The church lost its status as mediator in conflicts, rights over spiritual and familiar issues because the new political authorities.

የሚገርመው ቤተክርስትያኗ በራሷዋ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እንኩዋን ለመወሰን መብቱን አጣች። 1970ዎቹ እና ሰማነያዎቹ ህወሀት ነጻ አወጣሁዋችው በሚላቸው ቦታዎች በሙሉ የቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ውሳኔዎች በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ስብሰባዎች መወሰን ጀመሩ።

ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስትያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስትያኗን አመራረ ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች መተካት እንደነበረ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል

thirdly , the TPLF launched a series of conferences or seminars for selected parish priests in 1970 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigray from the wider Ethiopian Church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial wereda seminars for the priests were conducted by an eloquent TPLF fighter,Gebre Kidan Desta, a graduate of the theological College at Addis Ababa university .The themes of the seminars were to replace the Ethiopian Church authority by TPLF minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity page 246

የቤተ ክርስትያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም በስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ሲባል መዋቀሩን እንዲህ ይገልጹታል

this process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the wel-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo , by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of TPLF

ሌላውና አደገኛው ደግሞ የቤተ ክርስትያኗን አመራር ለሁለት የመክፈል ጉዳይ ነው

1987 እና 1989 (ኣኤአ ) ትግራይ ያለውን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስትያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስትያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ከበረሀ ጀምሮ የታሰበበትና የተተገበረ ጉዳይ መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ እንዲህ ገልጸውታል

in 1987 and 1989 ,regional and national conference for priests were organized by the TPLF in liberated territories to reshape the Tigray Church in line with the TPLF program . A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of Tigray and was supposed to operate under TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to two secretariats…’

አራት ኪሎ ቤተ ክህነት

ዶክተር አረጋዊ በርሄ የጻፉት ይሄ ሁሉ ሴራ የተጎነጎነውና የተተገበረው ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ በረሀ ላይ እያለ ነበር።ወያኔ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በሁዋላ በቤተ ክህነቱ ዙርያ ምን ተፈጸመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስና በበረሀ ታቅደው መተግበር ከጀመሩት ሴራዎች አንጻር ለመመልከት ውሳኔዎቹንና እቅዶቹን ደግመን እንያቸው

1. ቤተክርስትያኗ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስትያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባአኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ
2. የቤተ ክርስትያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማሰመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና ማስሾም
3. የቤተ ክርስትያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስትያኗን አመራር ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች ማስያዝ
4. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስትያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስትያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል
ያልተፈጸምው የቱ ይሆን ? የኢትዮጵያ ትዋህዶ ቤተ ክርስትያን በሁለት ሺህ አመት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲኖዶሷ ለሁለት ተከፍሏል።የቀድሞው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔም ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ እንደገለጹት አባ መርቆሬዎስ ከሀገር የወጡት በፖለቲካ ውሳኔና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ ነው።ከዚህም ጋር ተያይዞ የቤተ ክርስትያኗ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሏል።

የቤተ ክርስትያን ጉዳዮች በቤተ ከርስትያን ሲኖዶስ ሳይሆን በሌሎች አካላት እንደሚወሰን ያባ ጳወሎስ ሀውልት ህያው ምስክር ነው።ሲኖዶሱ ይፍረስ ብሎ ቢወስንም “የማይፈርሰው ሀውልት ብለው የወሰኑት “ምእመናን” ውሳኔ እንደጸና የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው።

ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ ፖለቲካ የሚሰብኩ ጥቁር ራስ መነኮሳትና ነጭ ለባሽ ካህናት በየቤተ ክርስትያኑ ማየትና ማድመጥ የተለምደ ከሆነ በርካታ አመታትን ተቆጠሩ።ሌሎቸም ብዙ ጉዳዮች ሆኑ።

ለጊዜው ሁሉም እቅድ የተሳካ ይመስላል።የመውጊያው ብረት ላይ መቆም ተቸሏል። ለማን እንደሚብስ ግን ወደፊት የምናየው ይሆናል። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል” የሐዋርያት ስራ 9 5 የእግዚአብሄርን ለቄሳር አሳልፈው የሰጡ “ሐዋርያትም” ስላፈሩት ሰልሳና መቶ ከግብር አባታቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ።የቤተ ክርስትያን አምላክም ቤተክርስትያንን ይጠብቃል።

ይቆየን
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 12:58 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-

እንኳን ለወርኃ -ፋሲካ አደረሣችሁ ::

ስለ ዋልድባ ገዳም አንዳንድ ጉዳዮችን ለማወቅ ስለሚረዳ የሚከተለውን የቪዲዮ ጥንቅር መመልከቱ ይጠቅማል ::

ምንጭ :- Published on Apr 10, 2012 by gojoethiopiatour. Waldba Monastery.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 10:01 am    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅ ..ፈዛዛው ምነው ቄሰ አየደለህም እንዴ ..አይ የዋልድብ ቄሶች ... ሰለ ቂጥ ምናምን ሰታወራ አታፍርም ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-

እንኳን ለወርኃ -ፋሲካ አደረሣችሁ ::

ስለ ዋልድባ ገዳም አንዳንድ ጉዳዮችን ለማወቅ ስለሚረዳ የሚከተለውን የቪዲዮ ጥንቅር መመልከቱ ይጠቅማል ::

ምንጭ :- Published on Apr 10, 2012 by gojoethiopiatour. Waldba Monastery.

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የንጋት ጮራ

ኮትኳች


Joined: 01 Jan 2006
Posts: 240

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 11:20 pm    Post subject: Reply with quote

ስለዋልድባ የጎንደር ወጣቶችን ምስክርነት ከዚህ በታች ተመልከቱ።

የትግራይ እናቶችም ከዚህ በታች የቀረበውን ምህላ እንዳደረጉ ወጣቶቹ መሰከሩ።

ወደ ዋናው የአብረንታንት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተመለስን፡፡ እናቶች በአንዲቷ ገጣሚነት እየተመሩ ደረታቸውን እየደቁ፣ ጭናቸውን እየመቱ በትግርኛ የሚቀበሉትን ዜማ ቆመን ስንሰማ ነበር፤ እንዲህ ያለ ዜማ የሰማነው ለክብረ በዓል አኵስም ጽዮን ማርያም ሄደን በነበረ ጊዜ ነው፤ በጣም ያሳዝናል፡፡ አስተርጉመን ስንሰማው “ጌታዬ ለእኛ ስትል ተንገላታኽ፤ ለእኛ ስትል ተሰቅለኽ ሞትኽ” የሚል ነበር፡፡ ከቆይታ በኋላ እኛ ቆመን እያየን ፖሊሶቹ መጥተው መሪዋን እናት ከሌሎች ለይተው እያዋከቡ ይዘዋት ሄዱ፤ የተቀሩትም እናቶች ተበታተኑ፡፡ ለምንድን ነው ብለን ስንጠይቅ አቀንቃኟ በግጥሞችዋ ውስጥ “ዋልድባ ታረሰ፣ ታረሰ፤ ዛሬ ነው ወይ የሚታረስ፤ ቤትኽን ጠብቅ አንተ፤” የሚሉ ሐረጎችን በመጨመሯ እንደ ኾነ ነገሩን፡፡ የገጠሩን ሰው እንዲህ በዱላ ሲጨረግዱት ስናይ ፍጹም ሰላም በምንጠብቅበት ቦታ ላይ ሰላም እንደሌለ ስንረዳ አዘንን፤ ጸሎተ ምሕላ አደረስን፡፡


አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው ወልደ ዲያቢሎስ የዲያቢሎስ ወኪል ከወገናችን ከትግራይ ጋር ለማቃቃር አስቦ “ልማቱን የማደርገው ለትግራይ ነው” ይለናል። አሁን ለጊዜው በስልጣን ኮሪቻ ላይ የተቀመጥከው ዲያቢሎስ ስማ - ምንኩስና እና እምነት የሌላቸውን ካድሬዎችህን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስገብተህ “ልማት የማደርገው ለትግራይ ነው” ብትልም ሃይማኖቱን የሚወደው የትግራይ ህዝብ አንተንም ልማትህንም አይፈልግም። ዲያቢሎስ ሆይ - የትግራይ ህዝብ ነቃብህ ምን ይሻልሃል ?

ፈጣሪ ሆይ ኃጢአታችን ስለበዛ ካንተ በመራቃችን ዲያቢሎስ አገኘን እና ቀንበሩን በላያችን አከበደብን። እነሆ አሁን መመኪያችን አንተ መሆንህን ልብ ብለናልና ወደ እኛ ተመለስ። ዲያቢሎስን እርገጥልን። ወልደ ዲያቢሎስ አስወግድልን። አንተ የመረትከውን አንተን የሚወድ አገልጋይህ የሆነ መሪ ስጠን። የሚፈሩህና ቢትህን በቅንአት የሚጠብቁ በጎችህን የሚጠብቁ ቅዱሳን የኃይማኖት መሪዎችን ስጠን። አሜን።


ምንጭ ደጀ ሰላም

http://www.dejeselam.org/2012/04/blog-post_17.html#more

ሪፖርታዥ፦ የዋልድባ መድኃኔዓለም ተሳላሚዎች ምስክርነት

- ገዳሙ በከፍተኛ የፖሊስ ኀይል ስምሪት ውስጥ ወድቋል።
- መነኰሳት በአባትነታቸው አይከበሩም፤ ይዘለፋሉ፤ ይታሰራሉ፤ ጸሎተ ምሕላ በማኅበር እንዳያደርሱ ተከልክለዋል።
- ከአንድ . ያላነሰ የገዳሙ መሬት የፕሮጀክቱ አካል ኾኗል።
- “ስለሚታረሰው አያገባችኹም፤ ስለተተኮሰባችኹና ስለተደበደባችኹት አያገባንም” /አቡነ ኤልሳዕ ለተሳላሚዎቹ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ /
- “እውነቱን ከማኅበረ ቅዱሳን ልኡካን ሪፖርትና መግለጫ እንጠብቃለን” /ተሳላሚ ምእመናኑ /


(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 8/2004 .ም፤ April 16/2012) መጋቢት 20 ቀን 2004 .ም፤ የመድኃኔዓለምን በዓል በአብረንታንት ዋልድባ ገዳም ለማክበር ወደዚያው ለማምራት ተዘጋጅተናል፡፡ መነሻችን ከጎንደር ከተማ ነው፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋራ ሲነጻጸር ዘንድሮ የተሳላሚው ቁጥር አንሶ ይታያል፤ ከጉዟችን በፊት መንገዱ እንደሚዘጋና በርካታ የፌዴራል ፖሊስ ኀይል እንደተላከ አብዝቶ በመሰማቱ የቀረው ሰው ብዙ ነው፡፡


ይኹንና ከከተማው 44 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት /ቤቶች፣ 18 ወጣት ማኅበራት እና 10 የጉዞ ማኅበራት የተውጣጡ ምእመናን በሚኒባሶች እና በሁለት አውቶቡሶች ተጓጉዘን ዓዲ አርቃይ ደርሰናል፤ የእግር ጉዞውም የሚጀመረው ከዚያው ከዓዲ አርቃይ ነው፤ መንገዱ እስከ ዋልድባ ገዳም ድረስ ለበረታው 12 ሰዓት ለሚያዘግመውም 16 - 18 ሰዓታት ይወስዳል፡፡
ከዓዲ አርቃይ ተነሥተን ዶንዶሮቃ የሚባል ገዳም ደረስን፤ ዶንዶሮቃ ገዳም የዋልድባ ገዳም አካል ነው፡፡ ከዚህ ጀምሮ ፍተሻው ከባድ ነው፡፡ ፖሊሶቹ መታወቂያ አምጡ እያሉ እንግልት ያደረሱብን፣ ሻንጣችንንና ለመንገድ የያዝነውን ኮቸሮ ሳይቀር የበረበሩት ከዶንዶሮቃ ጀምሮ ነው፤ ስንከላከላቸው መልሳቸው ሌላ ነው፡፡
ዶንዶሮቃ ገዳም ጠበል አለ፤ ከጠበሉ ቦታ ላይ ገላቸውን በሳሙና የሚታጠቡ ሰዎች አገኘን፡፡ ባለማወቅ ስሕተት የሚሠሩ መንገደኞች ናቸው በሚል ልናስተምራቸው ስንሞክር “አያገባችኹም” ብለው ሰደቡን፤ ልብሳቸውን ሲለብሱም እነርሱ [ፖሊሶቹ ] ኾነው ተገኙ፤ በያዙት መሣርያ ስላስፈራሩን ለምነናቸው ጉዟችንን ቀጠልንና ማይ ለበጣ ገባን፡፡ ከማይ ለበጣ ወደ ዋናው ገዳመ ዋልድባ - መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ደረስን፡፡


በገዳሙ ዙሪያ የፌዴራል ደንብ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች በብዛት ይታያሉ፤ እኔና ጓደኞቼ ለበዓል ወደ ዋልድባ ገዳም ስንመጣ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው፤ ለወትሮው በተወሰነ መልኩ ከሚታየው ሚሊሻ በስተቀር ይህን ያህል ብዛት ያለው ኀይል ገጥሞን አያውቅም፤ አሁን ግን ሁልጊዜም በገዳሙ የሚታየው ሰላማዊ ኹኔታ ጨርሶ ጠፍቶ የጦርነት ድባብ የሰፈነ ነው የሚመስለው፡፡ እንደገባን ያገኘናቸው አባቶችም “ለሚዲያ መግለጫ ሰጥታችኋል፤ በሳተላይት ስልክ ትደዋወላላችኹ” በሚል የታሰሩና የሚፈለጉ አንዳንድ አባቶች እንዳሉ ነው የነገሩን፡፡

መቃብረ አቡነ ሳሙኤልን ተሳለምን፤ 485 . ከሰሜን ሸዋ ቡልጋ የተነሡ ምእመናን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሪነት መጋቢት 27 ቀን ወደ ዋልድባ ገዳም ከገቡ በኋላ ምእመናኑ “እኛም ከአንተ አብረን ከአንተ ጋራ” ብለው የመድኃኔዓለም ሎሌ መኾናቸውን በገለጹበት ቃል አብረንታንት ተብሎ የተሰየመውን ጌታችንና ከምእመናኑ የተሰወረበትን ሃሌ ሉያ ዋሻ ተመለከትን፡፡


በመቀጠል ማየ ዮርዳኖስ ወደሚባለው የገዳሙ ጠበል ቤት ገብተን ተጠምቀናል፤ ጠበል ቤቱ የራሱ ቅጽር አለው፤ ከጎኑ ለመጠጥ የሚኾን ውኃም ይቀዳበታል፡፡ ወደ ጠበል ቤቱም ይኹን የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወዳለበት ቅጽር የሚገባው ጫማ ተወልቆ ቢኾንም ፖሊሶቹ ከነጫማቸው ሲገቡና ሲወጡ ተመልክተናል፡፡ ከትግራይም ከአማራም ገጠሮች ከመጡ ተሳላሚዎች ብዛት የተነሣ ለመጠመቅም ይኹን የሚጠጣ ውኃ ለመቅዳት በሰልፍ ነበር፤ ምእመኑ እየተገፋፋም ቢኾን ራሱን በራሱ ማስተናበር ልማድ ስላደረገው መብዛቱ ችግር አልነበረም፡፡ ዘንድሮ ግን ፖሊሶቹ በሥርዐት ማስከበር ስም ተሰልፎ ከቆመው ሕዝብ መሀል ገብተው በዘፈቀደ መደብደብና የታጠቁትን መሣርያ ቃታ እያቀባበሉ መደንፋትና ማስፈራራት ሥራቸው አድርገውት ነበር፤ ምላሽ በሚሰጣቸው ሰው ላይማ ይብሱ ነበር፡፡ በዚህ አኳኋን በቦክስ፣ በርግጫ እና በብትር የተመቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተለይ ፖሊሶቹ ጫማቸውን ለምን እንደማያወልቁ የጠየቀ አንድ ልጅ ዐይኑ ላይ በቦክስ መትተውት ፊቱ አብጦ ነበር፡፡ ለመጸዳዳት ወጣ ስንል እንኳ ወከባው ተመሳሳይ ነበር፡፡ ሃይማኖተኝነቱ ቢጠፋ እንዴት ሰብአዊነቱ እንኳ ይጠፋል ?

እስከ አሁን ባለው ቆይታችን ብዙ ወከባ ስላየን ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ተቃርበን ለማየት በነበረን ዕቅድ ላይ ስጋት ገባን፤ የተፈለገውም ይኸው የፍርሃት ቆፈን እንዲያሳስረን ይመስለኛል፡፡ በመጨረሻ መወሰን ነበረብንና የመጣውን ለመቀበል ቆርጠን 17 ያህል ልጆች በሁለት ቡድን ተከፍለን የውኃው ግድብ ወደሚሠራበት አካባቢ ለመጓዝ ተዘጋጀን፡፡ ከአብረንታንት መድኃኔዓለም ተነሥተን ለሦስት ሰዓት ያህል የእግር መንገድ ተጓዝን፤ አባ ነጻ የተሰኘው ቦታም ደረስን፡፡ ከዚህ በኋላ ግድቡ ወደሚሠራበት የፕሮጀክት ስፍራ ለመድረስ ግማሽ ሰዓት (30 ደቂቃ ) ብቻ ነው የወሰደብን፡፡

ግድቡ በሚሠራበት ቦታ ዙሪያ ገባውን ተመለከተን፤ በእይታችን ያረጋገጥነው ሐቅ “አንድ አካፋ አፈር እንኳ አልተዛቀም፤” እየተባለ ሲሰጡ ከነበሩት መግለጫዎች ጋራ ፈጽሞ የሚጋጭ ነው፡፡ ዶዘሮች፣ ኤክስካቬተር፣ ግሬደር የተባሉት ከባድ ተሽከርካሪዎች በሜዳው ላይ ይታያሉ፡፡ በጄኔሬተር የሚሠራ ባውዛ መብራት ተተክሎ የግድቡ ሥራ ሌት ተቀን እየተፋጠነ መሆኑን ጠይቀን ተረድተናል፡፡ በዚህ ሥራ በዋልድባ በኩል ካለው ተራራ ወደ አባ ነጻ አቅጣጫ ባለው የገዳሙ መሬት ጥምዝምዝ (ዚግዛግ ) ጎዳና ያወጣ መሬት ተቆፍሯል፡፡ በዐይን ግምት በዶዘር እየፈረሰ የተቆፈረው መሬት ርዝመት ከአንድ ኪሎ ሜትር አያንስም፡፡ ቁፋሮው የግድቡ መዋቅሮች ግንባታ አካል መኾኑም ተነግሮናል፡፡

ወደ አባ ነጻ ተመለስን፡፡ አባ ነጻ ላይ አባቶችን አግኝተናል፡፡ እዚያው እንደ ቆመን አንድ የፕሮጀክቱ ኤክስካቫተር መኪና መጥታ አፈር እያነሣች ስትቆልል አይተናል፡፡ ስለጉዳዩ አባቶችን ስንጠይቅ “ግድቡ ምን ያህል የደለል ችግር ሊኖረው ይችላል የሚለውን ለመመርመር ተብሎ ነው የሚል ምላሽ ነው የሰጡን” ብለውናል፡፡ የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር ከፈለሰበትና ከረገፈበት በዚሁ በአባ ነጻ ከሚገኘው የአቡነ ተስፋ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በቁፋሮው ምክንያት የፈለሱት ዐፅሞች ጉድጓድ ተቆፍሮ በሲሚንቶ በተለሰነ ቤት ውስጥ መከማቸታቸው ተነግሮናል፡፡ በዚሁ ቦታ አሳዛኙ እውነት ግን በአፈር ምርመራ ስም በገዳሙ ሜዳ ላይ ይህን ሥራ ከሚሠሩ ሠራተኞች መካከል አምስቱ ባልታወቀ ምክንያት መሞታቸው ነው፡፡


የዋልድባ መሬት ከመታረሱ አልፎ የሚፈርሱትን እንደ ዕጣኖ ማርያም፣ ጊዮርጊስ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ባንሄድባቸውም ያሉበትን አቅጣጫ ጠቁመው አሳይተውናል፡፡ ግድቡ ሲገደብ ወደ ገዳሙ ያለው መልክአ ምድር በጣም ሜዳማ በመሆኑ እስከ አባ ነጻ ያለውን መሬት ላለመጠቀማቸው ምንም ዋስትና የለም፡፡ ይህን ያህል ሚልዮን ብር አውጥተው ገድበው ውኃው ወደ አንድ አቅጣጫ ሊሰፋ አይችልም፤ በዋልድባ ወዲህና ወዲያ ማዶ ባሉት ተራሮች መካከል የሚፈሰው የዛሬማ ወንዝ ሲገደብ ውኃው ወዲህም ወዲያም እኩል ስለሚሰፋ ወዲህ ወደ አባ ነጻ አይገቡበትም ብሎ በርግጠኝነት መናገር ያስቸግራል፤ ሁሉንም ነገር ሲጀመር ቀስ በቀስ ነውና፡፡ ይህን ማረጋገጥ የሚቻለው ደግሞ የፕሮጀክቱ ሓላፊዎች አባ ነጻ ላይ ለተሰበሰቡት አባቶች የነገሯቸውን ስንመለከት ነው፡፡ ምንድን ነው ያሏቸው ? - “ውኃ እንሰጣችኋለን፤ ሙዝ የምታጠጡበት ከፈለጋችኹ ወደ እናንተም ስለሚመጣ” ነው ያሏቸው፡፡ የአባ ነጻ አባቶችም እንዲህ በማለት ነው የተከላከሏቸው - “አባቶች ያቆዩን በዚህች ውኃ፣ በዚህች ቋርፍ፣ በዚህች ሙዝ ነው፤ እኛም ባለን ነው የምንቆይ፤ ውኃ አንፈልግም አልናቸው፤” ብለውናል፡፡
እኛ ባይናችን እንዳየነው በመጀመሪያ የግድቡ ውኃ በጣም ብዙ ስለሚሆን የገዳሙ መሬት የመጥለቅለቅ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ አባቶች በዕጣኖ ማርያም ቤተ ክርስቲያኑ ከሚፈርስበት ላይ የቋርፍ ተክል የሚያለሙበት፣ ሲታመሙ የሚያርፉበት (ሞፈር ቤት የሚባለው ) 10 / ያህል መሬት አላቸው፡፡ የፕሮጀክቱ ሓላፊዎች ይህን 10 / መሬት በዕጥፍ አድርገን 20 / ምትክ መሬት ሌላ ቦታ እንሰጣችኋለን እንዳሏቸው የአባ ነጻ አባቶች ነግረውናል፡፡

ከማይ ለበጣ ወዲህ “እህል አይዘራብሽ፤ ኀጢአት አይሻገርብሽ” የሚል ትእዛዝ አለ፤ በፀለምት መሥመር እስከ ዕጣኖ ማርያም መሬቱ በግድቡ ውኃና ብዙ መሬት በሚጠይቀው በሸንኮራ እርሻ ይሞላል፡፡ ለዚህም ሲባል 8 - 10 የገጠር ቀበሌዎች ነዋሪዎች ቁጥራቸውን ለጊዜው በውል ከማናውቃቸው አብያተ ክርስቲያናት ጋራ ተነሥተው በሌላ አዲስ መንደር ይሰፍራሉ፡፡ በዚህ ዐይነት በዕጥፍ እንሰጣችኋለን የሚባለው ምትክ መሬት ከገዳሙ በጣም ይርቃል ማለት ነው፡፡ አባቶች ለዚህ ማግባቢያ ያላቸው አስተያየት “አስፋልት ዳር ወስዶ ሊያፈሰን ነው” የሚል ነው፡፡ በእውነቱ በጣም ይረብሻል፡፡ የገጠር አብያተ ክርስቲያናቱ መፍረስ ከሕዝቡ መነሣት ጋራ የተያያዘ ምክንያት ቢሰጠውም በገዳሙ ይዞታ ውስጥ ያለው የቋርፍ ቦታና አብያተ ክርስቲያናቱ መፍረስ ጉዳይ ግን በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡

በሌላ በኩል የስኳር ፋብሪካው ሲተከል ከፋብሪካው ግዙፍነት ጋራ ሌሎች የአገልግሎት መስጫ /መገልገያ / ተቋማት አብሮ ይተከላል፤ መኖርያ ቤት፣ መዝናኛ . . .ወዘተ፡፡ መንገዱ በዛሬማ በኩል ለዋናው ገዳም እንዲቀርብ ኾኖ እየተሠራ ነው፤ አሁንም ለኮንስትራክሽኑ ተብሎ መኪና እየገባ ነው፡፡ ከዚህም ጋራ አብሮ የሚመጣውን ጣጣ መገመት አይከብድም፡፡

እነርሱ እንደነገሩን ከሰሜን ምዕራብ ትግራይ - ሽሬ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምሥራቃዊ ትግራይ - ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የፕሮጀክቱ ባለሥልጣናቱ ከማኅበረ መነኰሳቱ ጋራ ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ በስብሰባው ላይ ማኅበረ መነኰሳቱ በልማት ፕሮጀክቱ ላይ ያላቸውን ጥያቄ አንሥተው ሲሟገቱ ከጳጳሳቱ አንዳቸው ስብሰባውን በጸሎት ከመክፈት ሌላው በጸሎት ከመዝጋት በቀር አንዳችም አስተያየት አለመስጠታቸው አስገራሚ ነበር፡፡


የአባ ነጻ አባቶች እንደሚናገሩት የችግሩ መፍትሔ መታገሥና ጸሎት ማድረግ ነው፡፡ ይኹንና በማኅበር ጸሎተ ምሕላ እንዳያደርጉ በግልጽ ተከልክለዋል፡፡ የበርካታ መነኰሳት በኣት ከውጭ በሩ ተቆልፎ አይተናል፡፡ ከእኒህ መነኰሳት ብዙዎቹ በየዋሻው መሸሸጋቸውን ተረድተናል፡፡ ከማኅበረ መነኰሳቱ ለአንዳንዶቹ እንደመሰላቸው “ወጣት መጥቶ ጦርነት እንደሚያነሣ፣ መነኰሳቱም ወጣቱም እንደሚያልቁ” አስበው ነበር፡፡ በቡድን ወደ ስፍራው የሄድነው ተሳላሚዎች ግን የዕለት ውዳሴ ማርያም እየደገምን ጸሎተ ምሕላ እናደርስ ነበር፡፡

ወደ ዋናው የአብረንታንት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተመለስን፡፡ እናቶች በአንዲቷ ገጣሚነት እየተመሩ ደረታቸውን እየደቁ፣ ጭናቸውን እየመቱ በትግርኛ የሚቀበሉትን ዜማ ቆመን ስንሰማ ነበር፤ እንዲህ ያለ ዜማ የሰማነው ለክብረ በዓል አኵስም ጽዮን ማርያም ሄደን በነበረ ጊዜ ነው፤ በጣም ያሳዝናል፡፡ አስተርጉመን ስንሰማው “ጌታዬ ለእኛ ስትል ተንገላታኽ፤ ለእኛ ስትል ተሰቅለኽ ሞትኽ” የሚል ነበር፡፡ ከቆይታ በኋላ እኛ ቆመን እያየን ፖሊሶቹ መጥተው መሪዋን እናት ከሌሎች ለይተው እያዋከቡ ይዘዋት ሄዱ፤ የተቀሩትም እናቶች ተበታተኑ፡፡ ለምንድን ነው ብለን ስንጠይቅ አቀንቃኟ በግጥሞችዋ ውስጥ “ዋልድባ ታረሰ፣ ታረሰ፤ ዛሬ ነው ወይ የሚታረስ፤ ቤትኽን ጠብቅ አንተ፤” የሚሉ ሐረጎችን በመጨመሯ እንደ ኾነ ነገሩን፡፡ የገጠሩን ሰው እንዲህ በዱላ ሲጨረግዱት ስናይ ፍጹም ሰላም በምንጠብቅበት ቦታ ላይ ሰላም እንደሌለ ስንረዳ አዘንን፤ ጸሎተ ምሕላ አደረስን፡፡


ወደ ዋልድባ ገዳም ከገባን ስድስተኛ ቀን ኾኖናል፡፡ በማግስቱ የመድኃኔዓለም ክብረ በዓል ነው፡፡ በየዓመቱ አንድ ጊዜ ተራ በተራ ለሚከናወነው ጸሎተ ቅዳሴ የዘንድሮ ተረኛ የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ነበር፡፡ የዛሬ ዓመት የቅዳሴ ተራው የቤተ ጣዕማ ማኅበረ መነኰሳት (ዘጠኝ መለኰት ይላሉ የሚባሉት ) ነበር፤ ልማቱን እንደግፋለን እያሉ ስለመፈረማቸው የሚነገርላቸውና በሚዲያ እየቀረቡ የምናያቸው ቤተ ጣዕማዎች ናቸው፡፡ በጣም የሚገርመው መባዕ ለመሰብሰብ ብቻ ተብሎ የጥንቱን መቃብረ ሳሙኤል ትተው ለእነርሱ በሚያመች ቦታ ሌላ መቃብረ ሳሙኤል ሠርተው ምእመኑ እየተሳሳተ ሲማፀንበትና መባዕ ሲጥልበት ነበር፤ በኋላ ተሳላሚው ወጣት አፈራረሰው፡፡ በዚህ የተነሣ የተፈጠረውን ጠብ የመንግሥት አካል ጣልቃ ገብቶ አስማማቸው ተብሏል፡፡ ዞሮ ዞሮ ያን ያህል ደክመን ሄደን ይህ ዐይነቱ ክፍፍል እዚያ ቦታ ላይ ማየት በተለይ በእምነቱ ላልጠነከረው ምእመን በጣም ጎጂ ነው፡፡

የክብረ በዓሉን ቅዳሴ ጨርሰን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ለመልስ ጉዞ ተነሣን፡፡ ማይ ለበጣ ላይ ገዳሙ ለመድኃኔዓለም በዓል ንፍሮና ጠላ በማዘጋጀት ተሳላሚዎችን ይዘክራል፡፡ እኛም እንደሌላው ተጓዥ እዚያው ቆመን ተዘክረን ማይ ለበጣን ወጥተን ሜዳውን ልናቋርጥ ስንል አንድ አባት በፖሊስ ተይዘው እየተነዱ ሲወሰዱ አየን፡፡ ለነገሩ ቀደም ሲልም የሚፈለጉ፣ የታሰሩም አባቶች እንዳሉ ሰምተናል፡፡

እኚህ አባት ከሕዝቡ ጋራ ተቀላቅለው እየወጡ ነበር፡፡ ፖሊሶቹ ትእዛዝ ተቀብለን ነው በሚል መነኰሱን ወደ ገዳሙ እንዲመለሱ ቢያዝዟቸውም እርሳቸው “መጥሪያ አምጣልኝ፤ አልያ አልሄድም” በሚል ይመላለሳሉ፡፡ ምንድን ነው ብለን ወደያዟቸው አባት ስንቃረብ ፖሊሶቹ “በጭራሽ እንዳትጠጉ ! እግር እግርኽን ነው የምሠብርኽ” ብለው መሣርያ አቀባበሉብን፡፡ እንዴ፤ ችግሩ ምንድን ነው ? አናግሩን እንጂ እያልን ከመነኩሴው ጋራ እኛም እየተነዳን ስንጠይቃቸው የያዟቸውን አባት ወደ ጥግ አቆሙና ወደ ጎን ይኹን ወደ ላይ ተኮሱ፡፡

ከመሃላችን የተመታብን ሰው እንደሌለ ብናረጋግጥም የመሣርያ ተኩስ ባልጠበቅንበት ቦታ ተኩስ በመስማታችን በጣም አዘንን፤ “ይግደሉን” እያሉ የሚጮኹ ወጣቶችም ነበሩ፡፡ ከመሀላችን አንድ ሰው በተኩሱ ተመቶ ቢቆስል ወይም ቢሞት ዓለም ይደባለቅ ነበር፡፡ ብዙዎቻችን በእኛ የተነሳ ችግሩ እንዳይባባስ ውዝግቡን አብርደን ከፊት ቀድመን፣ ፖሊሶቹና የተያዙት አባት ደግሞ ከኋላ ኾነው ወደ ዶንዶሮቃ መጣን፡፡ ዶንዶሮቃ ከደረስን በኋላ የተያዙት አባት “እኔ የመነኰስኹት ለመከራ ነው፤ ይበለኝ፤ ተመለሱ ልጆቼ” በማለት ለእኛ ሰግተው መከታተላችንን እንድናቆም ስለመከሩን፣ ፖሊሶቹም “ምን ይገትርኻል” እያሉ ስላስፈራሩን ክትትላችንን ብናቋርጥም መነኩሴውን እስከ ዶንዶሮቃ ዘልቀው በሚገቡ የገጠር መንገድ ሥራ ድርጅት መኪና ወደ ማይ ፀብሪ ለመውሰድ በሬዲዮ ትእዛዝ ሲቀበሉ ሰምተናቸዋል፡፡ ፖሊሶቹ መነኰሳቱን እንደ አባት ሲያከብሩ ለማየት አልታደልንም፡፡

በማይ ለበጣ እንደተረገው ሁሉ በዶንዶሮቃና በየቀበሌው ሁሉ እንዲሁ የመድኃኔዓለም ዝክር ነበርና እያረፍን ዝክሩን እየቀማመስን ወደ ዓዲ አርቃይ መንገዳችንን ቀጠልን፡፡ ዓዲ አርቃይ ገብተን ከመካከላችን የጎደለ ሰው እንደሌለ ካረጋገጥን በኋላ ወደ ጎንደር ከመጓዛችን በፊት ዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ ጎራ ብለን የኾነውን ነገር ሁሉ አስረዳን፡፡ የፖሊስ ጣቢያው ዋና አዛዥ ሪፖርታችንን ከሰሙ በኋላ “እንኳን እናንተ በሰላም መጣችኹ፤ ለተተኮሰውም ለድብደባውም ሁሉንም ነገር እንከታተላለን፤” አሉን፡፡

ረፋድ ላይ ከዓዲ አርቃይ ተነሣን፡፡ ደባርቅ ላይ ምሳ አድርገን ጎንደር ገብተን ከመበታተናችን በፊት ወደ ሀገረ ስብከቱ /ቤት ሄደን የኾነውን ሁሉ ማስረዳት አለብን በሚል ተስማማን፡፡ ለምን ቢባል በቀደመው ስብሰባ አልታረሰም ያሉት ገዳም ታርሶ አየን፤ አባቶች ሲንገላቱ ተመለከትን፤ በሽብር ምክንያት ገዳሙን ትተው ሊሰደዱ ነው፤ እንደገና ደግሞ በሰላሙ ቦታ ሰላም አጥተናል፤ በእኛ ላይ ተተኩሶብናል፤ ተደብድበናል፤ በሳምንት የዋልድባ ቆይታችን ጀርባና ትክሻቸውን በብትር የተመቱትን ሳንቆጥር ዐይኑን በቦክስ ተመቶ ፊቱ ያበጠው የጎንደር መድኃኔዓለም ዲያቆን ኹኔታ በጣም የሚያሳዝን ነበር፡፡ እኒህን እንኳር ነጥቦች ይዘን ምንም እንኳ በቀደመው ስብሰባ ጥሩ ባይናገሩም ከማንም በላይ ሀገረ ስብከቱ ሓላፊነት አለበት ብለን ሁሉም ተጓዥ ከመኪናው ውስጥ እንዳለ ወደ ሀገረ ስብከቱ /ቤት አመራን፡፡

በሀገረ ስብከቱ /ቤት ስንደርስ ሥራ አስኪያጁን መልአከ ሕይወት ቀለም ወርቅን አገኘናቸው፡፡ ሁሉም ሰው ከአውቶቡሱ ሲወርድ “ይህ ሽብር መፍጠር ነው” በማለት ሊያናግሩን ፈቃደኛ አልኾኑም፡፡ ከመካከላችን ስድስት ሰዎች መርጠን ሰደድን፡፡ ለምን እንደመጣን ስንነግራቸው “ስብሰባ ውለን እየወጣን ስለሆነ ብፁዕነታቸው የሚያናግሯችኹ አይመስለኝም” ብለው ጠቅጠቀውን ሊያልፉ ቢሞክሩም ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ከመረጥናቸው ስድስት ሰዎች ሁለቱ እንዲገቡ ተፈቀደ፤ እንደምንም ከጥበቃ ጋራ ተጋፍተን ሦስተኛ ሰው ጨመርንና ገባን፡፡

ሲጀመር በታላቁ ገዳም በመሰንበታችን የበለጠውን ቡራኬ እዚያ ካሉት አባቶች ተቀብለናል፤ ብፁዕነታቸውም ወጥተው እንኳን ደኅና መጣችኹ ብለው በቡራኬ ሊቀበሉን ይገባ ነበር፡፡ የእርሳቸው ቡራኬ ይቅርና እኒያ የላክናቸውን ሦስት ልጆች እንኳ በአግባቡ ተቀብለው አላናገሯቸውም፡፡ ልጆቹ አምስት ደቂቃ ያህል ሳይቆዩ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ተመለሱ፡፡ ተወካዮቻችን የገዳሙ መሬት ስለ መታረሱ፣ አባቶች እየተንገላቱ ገዳሙ ሰላም ስለማጣቱ፣ እኛም እንደ ተተኮሰብንና እንደተደበደብን ለሊቀ ጳጳሱ ለማስረዳት ቢሞክሩም የብፁዕነታቸው ምላሽ ግን “ስለሚታረሰው አያገባችኹም፤ ስለተተኮሰባችኹና ስለተደበደባችኹት አያገባንም” የሚል አባታዊነትና መንፈሳዊነት በእጅጉ የጎደለው ንግግር ነበር፡፡

ልጆቹ ይህን አማርኛ ከነገሩን በኋላ ጥቂት የማይባል ተሳፋሪ ከአውቶቡሱ ወርዶ ለመዛለፍ ሞከረ፡፡ በዚህ አኳኋን ብንቆይ ሌላ ነገር ስለሚከተለን “አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፤ መነኰስ ኀያል” የሚለውን የዲያቆን እንግዳወርቅ በቀለ መዝሙር በድምቀት እየዘመርን ወደ መስቀል አደባባይ ሄደን በጸሎት እንደተነሣን በጸሎት ዘግተን ወደ የቤታችን ተበታትነናል፡፡

እኛ በመጨረሻ ነገሩን አወጣነው አወረድነው፤ ከእግዚአብሔር ውጭ ምንም አቅም እንደሌለን ነው የተረዳነው፡፡ በርሓው ላይ ተተኩሶብናል፤ እነርሱም መነኰሳቱም ያልቃሉ እንጂ በሰላም ይመለሳሉ ያለንም አልነበረም፤ በከተማውም እንዲህ አይኾንም ለማለት አይቻልም፡፡ ብዙዎቻችን ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ስትዋረድና ስትናቅ አይተን አናውቅም፡፡ ያለን አማራጭ ጸሎት ብቻ ነው፡፡ ወደ ዘጉ አባቶች ቀርበን የእናንተ ጸሎትኮ አይወድቅም ስንላቸው “እናንተም ባላችኹ አቅም በጸሎት ትጉ” ነው ያሉን፡፡
ቤተ ክህነቱ ቤተ ክሕደት ኾኗል፤ አባቶች እንደመከሩን የመጣውን የሚያቆም ምንም ዐይነት ሰብአዊ ኀይል የለም፤ መፍትሔው ይግባኝ ለክርስቶስ ማለት ብቻ ነው የሚያዋጣው፤ እኒያ የትግራይ እናቶች እንዳሉት መድኃኔዓለም ራሱ በአንዳች ተኣምር ቤቱን ይጠብቃልና !!

ከዚህም ጋራ ደግሞ ሌላው ተስፋችን በዋልድባ ሳለን ያገኘናቸው ከአዲስ አበባና ጎንደር የመጡ የማኅበረ ቅዱሳን ልኡካን ናቸው፡፡ መረጃውና ሪፖርቱ ቀርቦ የማኅበሩ አመራር በጋራ ከተመለከተው በኋላ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አረጋግጠውልናል፡፡ አሁን እኛም ኾነ ሌሎቹ ማኅበራት የእነርሱን ትክክለኛ መግለጫና ሪፖርት እየጠበቅነ ነው፡፡ በእውነቱ እነርሱ የፕሮጀክቱን አካባቢ ለማየት ፈቃድ ስላላቸው፣ ባለሥልጣናቱንና አባቶችን አነጋግረው የድምፅም የምስልም ማስረጃ ስለሚይዙ ከሪፖርታቸው ትልቅ እውነታ ነው የምንጠብቀው፡
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 1:47 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም እህታችን የንጋት ጮራ :-

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰሽ : ወርኃ -ፋሲካ የሰላም ጊዜ ይሁንልሽ ::

በእርግጥም ሣጥናኤል ራሱ ወያኔን ሆኖ መጣብን እኮ Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች


Joined: 03 Oct 2010
Posts: 564

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 3:55 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅ ...የንጋት ጭራቅ እኔም እንኳን አደረሰህ እላለሁ ...ሳትበላ ወያኔ በላህ ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing Laughing

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም እህታችን የንጋት ጮራ :-

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰሽ : ወርኃ -ፋሲካ የሰላም ጊዜ ይሁንልሽ ::

በእርግጥም ሣጥናኤል ራሱ ወያኔን ሆኖ መጣብን እኮ Rolling Eyes

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 9:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-

የወያኔ -ናዚ አገዛዝ ራሱ ከውጭ አገሮች አምጥቶ : ቀፍቅፎና አጎልምሶ እዚህ ያደረሠውን የአክራሪ እስላሞች እንቅስቃሴ ልክ በሌላ ኃይል እንደመጣ በማስመሰል ያወራል :: እንዲያውም ከዚህ የከፋው አደጋ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ለመታደግ የሚንቀሣቀሱትን ወጣቶች "አክራሪ " ብሎ በመፈረጅ ልክ እንደ አል -ቃኢዳ ሊዘምትባቸው መነሣቱን ይፋ አድርጓል :: ከዚህ ጀርባ የእነ ዲጎኔ ዓይነት መናፍቅ ሚኒስትሮች (ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ) እንዳሉ እወቁ :: ስለዚህ የወያኔዎችን የጥቃት ዕርምጃ ነቅታችሁ ጠብቁ ::

ምንጭ :- የወያኔ የወቅቱ ሥልት ሠነድ : የካቲት 2004 ..::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የንጋት ጮራ

ኮትኳች


Joined: 01 Jan 2006
Posts: 240

PostPosted: Thu Apr 19, 2012 5:52 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አብሮ አደረሰን :: እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን አሜን ::

በመጨረሻ ካቀረብከው እንደሚገባን አሁን ለጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ኮሪቻ ላይ የተቆናጠጠው ወልደ ዲያቢሎስና ቀጣሪው የምእራቡ ዲያቢሎስ አክራሪ እስላምን እንደ ሺፋን ይጠቀሙበታል እንጂ ስለ እስላም አክራሪ ብዙም አይጨነቁም :: እንዲያውም የእስላም አጋሮች ናቸው : የእስላም አክራሪ የሚሉት ክርስትናን ለማጥፋት መንገድ ፍለጋ ነው :: አሁን የምእራቡም ሆነ አገር ውስጥ ያለው ዲያቢሎስ ትኩረታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማጥፋቱ ላይ ነው :: ትእቢታቸው ከመብዛቱ የተነሳ እንደምናየው በተለያየ አቅጣጫ በፈጣሪ ላይ ጦርነት ከፍተዋል :: እስቲ መጨረሻቸውን እናያለን ::

ተድላ ባልጽፍም ጽሁፎችህን እከታተላለሁ :: ሁሉም እንዲያውቅ ማድረግህ ጥቅም ስላለው በርታ ::

ኢትዮጵያዊት ጮሪት ::



ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም እህታችን የንጋት ጮራ :-

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰሽ : ወርኃ -ፋሲካ የሰላም ጊዜ ይሁንልሽ ::

በእርግጥም ሣጥናኤል ራሱ ወያኔን ሆኖ መጣብን እኮ Rolling Eyes

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
Page 2 of 7

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia