View previous topic :: View next topic
Author
Message
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun May 20, 2012 2:24 am Post subject:
የንጋት ጮራ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ለዚህ ቤት
የማህበረ ቅዱሳን ዘገባ የተዋህዶ ርስት ዋልድባ መሬቱ እንደታረሰ የግድብ ውሀ ማጠራቀሚያ እንደሚሆን በአሀዝ አስደግፎ አቅርቧል :: ይህ ጥሩ ሆኖ እያለ ከዚህ ቀደም አይቼባቸው የማላውቀው ጉድፍ ነገር በዚህ ዘገባቸው ላይ አይቼ ቅር አለኝ :: ፕሮቴስታንት / ተሀድሶ ሰርጎ ገብቶባቸው ካልሆነ በቀር እንደ ፕሮቴስታንት አይነት አመለካከት እሱም - "የተቀደሰው ቦታ ከተወሰደ በምትኩ ሌላ ቦታ ይሰጥ " ማለታቸው ከየት የመጣ ፍልስፍና ነው ? ይሄ አስተያየታቸው እኔን በጣም አሳዝኖኛል ::
በነገራችን ላይ የነሱ ዘገባ የዋልድባን መሬት አልነካንም ያለው ወያኔ ውሸታም መሆኑን በአሀዝና በስእላዊ ማስረጃ ያረጋግጣል :: እንዲዋሹ በአቡነ ጳውሎስ የተወከሉት ካህን ነን ባዮችም ሀሰት እንደተናገሩ ማስረጃው ያረጋግጣል ::
በከተማ ያሉት ፍርሀት ሊኖርባቸው ይችላል ::
ውድ እህቴ ኢትዮጵያዊት ጮሪት :-
ከሰው ልጅ ፍፁም ሥራ አትጠብቂ :: ማኅበረ ቅዱሣን ውስጥ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንደሚኖሩ አትጠራጠሪ :: ቢያንስ : ቢያንስ እኒህ የቤተክርስቲያን ልጆች በሥፍራው ተገኝተው ያዩትን እና የተገነዘቡትን ሲዘግቡ በተቃራኒው ደግሞ ወደ ሥፍራው ሣይሄዱ አዲስ አበባ በሞቀ ቢሯቸው ተዘፍዝፈው የሌለ ከሚያወሩት የአባ ገብረመድህን አፈቀላጤዎች እነ 'ስታሊን ገብረሥላሤ ' እና ምንኩሥናቸውን ከሚያዋርዱ የከተማ ተኩላዎች ጋር ሲነፃፀሩ ያከናወኑት ተግባር ፍሬ ያለው ሆኖ እናገኘዋለን ::
የንጋት ጮራ እንደጻፈ(ች)ው : የእግዚአብሄር ፍቅር ከልባቸው ያልተለየው የጎንደር ገበሬዎች ግን አስደስተውናል :: እንደቆራጦቹ የጎንደር ገበሬዎች (የተዋህዶ ልጆች ) እኛም በውጭ ያለን የተዋህዶ ልጆች ወለም ዘለም ሳንል ገዳማችን ማስከበር አለብን ::
ኢትዮጵያዊት ጮሪት
አዎን እግዚአብሔር የራሱን ቤትና ርስት ለማስከበር የሚሣነው አምላክ አይደለምና ይህ የሚያልፍ የፈተና ዘመናችን መሆኑን አምነን በፀሎትም ሆነ በሥራ እንትጋ ::
አክባሪሽ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Thu May 31, 2012 12:34 am Post subject:
ሰላም የተወደዳችሁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች :-
"ዋልድባን እንታደግ " የተሠኘ አዲስ የውይይት መድረክ ተከፍቷል :: ስለዚህ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘትና ኃሣብ ለመለዋወጥ ይህንንም ድረ -ገፅ ጎብኙት ::
ምንጭ :- "ዋልድባን እንታደግ ::"
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sat Jun 02, 2012 2:20 am Post subject:
ሰላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች :-
ትላንት ሐሙስ ግንቦት 23 ቀን በቀረበው የአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ የአማርኛው መርኃግብር ወያኔ በዋልድባ ገዳም ይዞታ በማካሄድ ላይ ያለውን የስኳር 'ልማት ' ፕሮጀክት የተቃወሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ስለደረሱበት ድምዳሜ የሚያብራራ ዝግጅት ነበር :: ከዚያ የቃለ -መጠይቅ ውስጥ የ "አንድ አድርገን " ድረ -ገፅ አምደኛ አጠናቅሮ ያቀረበውን ተመልከቱት ::
ምንጭ :- አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ .ም .::በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል ::
Quote: . ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
. “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
. ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ 60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃጥሏል
ቃለ መጠይቁን ለማድመጥ ይህን ይጫኑ
(አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ .ም )፡ - ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡
የገዳሙ መነኩሴም እንደተናገሩት በተከዜ አካባቢ የሚገኙ እጣን አምራቾች እጣናቸውን የሚያስቀምጡበት 5 ጎጆ ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸው በእሳት መውደማቸውንና እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማጥፋት እደተሳናቸው ጎጆዎቹም የዶግ አመድ እንደሆኑ ጨምረው ገልጸዋል ፤ በሌላ በኩል ግንቦት 3 ፤ 2004 ዓ .ም ሌሎች እጣን ለቃሚዎች የለቀሙት 60 ኩንታል እጣን በእሳት እንደተቃጠለ አክለው ገልጸዋል ፤ ይህን የማቃጠል ስራ ማን እንዳከናወነው ሆን ተብሎ ይሁን ወይም በአጋጣሚ ለማወቅ አልተቻለም ፤ “ዋልድባ ገዳም በዚህ አጋጣሚ እጣን እጣን ሸታለች” በማለት በቀልድ መልክ ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡
ገዳሙን በአሁኑ ሰዓት ለጸጥታ እንዲያመች በማለት በጎንደርና በትግራይ ክልል የሚገኝውን አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ሰራዊት በመጠበቅ ላይ ይገኛል ፤ መንግስት ይህን ስራ ሲሰራ 27 አስከሬኖች በክብር አንስቼ በተገቢው ቦታ አሳርፌአለሁ ቢልም የገዳሙ መነኮሳት ግን የተነሳው የአስከሬን ብዛትም በውል አይታወቅም ፤ ይሁን እንጂ ገለልተኛ አጣሪ አካል ከመጣ እና ማጣራት ከቻለ በአግባቡ ሁሉን ነገር ለማሳየት እንችላለን ብለዋል ፤ መንግስት የገዳሙን አባቶች እንደ ድኩላ ማሳደዱን እንዲያቆምና የገዳሙን የወደፊት ህልውና የሚፈታተን ስረ -መሰረቱን የሚንደውን የስኳር ልማት ከወዲሁ እንዲያቆም አሳስበዋል ፤
የዛሬ ወር አካባቢ ገዳሙን መንግስት በላካቸው የጨለማ ሰዎች አማካኝነት ከ 60 ሺህ ብር በላይ ገዳሙ መዘረፉን እናታውሳለን ፤ ይህን የሰሙ ምዕመና ባሳለፍነው ሳምንት ከተለያዩ ቦታዎች ገዳሙን ሊረዱ ሲመጡ በእጃቸው ለገዳማውያን አቡጀዴ ፤ ሙዳይ ምጽዋት ሳጥንና መሰል የመነኮሳት መገልገያዎችን ይዘው ነበር ፤ ነገር ግን እነዚህ ምዕመናን በሰላም ገዳሙ ጋር ቢደርሱም በሰላም ወደ መጡበት ቦታ መመለስ አልቻሉም ፤ ማይጸብሪ ሳይደርሱ በፖሊስ ታግተው እስከ ለሊቱ 3 ሰዓት ድረስ በአካባቢው ፖሊስ ምርመራ እና ፍተሻ ሲካሄድባቸው ነበር ፤ ምን ይዛችሁ ነው የሄዳችሁት ? ፤ ለምን መጣችሁ ? ፤ ሙዳይ ምጽዋት ውስጥ ምን አለ ? ፤ ከየት ከየት አካባቢ ነው የመጣችሁት ? ፤ ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት ስፍራ ሄዳችኋል ወይ ? በማለትና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ሊለቀቁ ችለዋል ፤ ከወራት በፊት አቶ ሲሳይ መሬሳ የተባሉት የአካባቢው አስተዳዳሪ ማንም ምዕመን ቦታው ድረስ በመምጣት እየተሰራ ያለውን ነገር መመልከት እንደሚችልና እየተወራ ያለው ነገር ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸው ነበር ፤ ነገር ግን የመንግስታችን አንዱ ባህሪው “በአደባባይ ፈቅዶ በጀርባ ማባረር” ስለሆነ እነዚህን ሰዎች በሰላም ገዳም ወርደው እንዳይመለሱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡
መንግስት የማረስ ስራውን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉን የተመለከቱ ከአድርቃይና በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ቁጥራቸው ከ 3000 ሺህ እንደሚበልጥ ለማወቅ ተችሏል ፤ “በዚህ ጉዳይ አንስማማም ገዳማችን ሲታረስብን ዝም ብለን አናይም ፤ ይህ የስኳር ልማት አሁኑኑ መቆም አለበት” በሚል አቋም ሰብሳቢ ሳያስፈልጋቸው በአንድ ቀን አንድ ቦታ ላይ መንግስትን ተቃውመው ወጥተዋል ፤ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በጸጥታ ሀላፊው አቶ ሙሉጌታ አስናቀ በተገኙበት ስለ ስኳር ልማቱ ሁኔታ ቀኑን ሙሉ መወያየት ችለዋል ፤ ስብሰባውንም አቶ ማሩ የተባሉ ሰው በሚገባ ሲመሩ ቆይተዋል ፤ በውይይቱ ላይ “ ይህን ጉዳይ የሚያጣራ ገዳሙ ላይ ልማቱ ጉዳት ያድርስ አያድርስ የሚያጣራ ኮሚቴ እናቋቁም” የሚል ሀሳብ ከወደ ሰብሳቢዎቹ ቢመጣም ተሰሚነትንና ተቀባይነትን አላገኝም ፤ “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገን የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የሚል መልስ ከተሰብሳቢዎቹ አግኝተዋል ፡፡ በስተመጨረሻም ሰብሳቢዎቹ “ከመንግስት ጋር ተነጋግረን ስራውን እናስቆማለን” የሚል መልስ ሰጥተዋቸው አመሻሽ ላይ ስብሰባው ሊጠናቀቅ ችሏል ፡፡ይህን ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን ያወቁት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና እየከነፉ ወደ ዋልድባ እየመጡ ሳለ መኪናው መገልበጡን ለማወቅ ተችሏል ፤ የደረሰውም አደጋ ለጊዜው በውል አልታወቀም፡፡
አሁንም ጊዜው አልረፈደም ከእኩይ ስራችሁ ተመለሱ ፤ ገዳሙን የማፍራረስ ተልዕኳችሁን አቁሙ ፤ ባለፈው ከጎንደር የነጎደውን ምዕመን አባብላችሁ በሰላም የሚፈታ ጉዳይ ነው በማለት አዘናግታችሁታል ፤ ቃላችሁን ግን ልትጠብቁ አልቻላችሁም ፤ ህዝብን አንዴ ሁለቴ ማታለል ይቻላል ለዘለቄታው ማታለል ማሰብ ግን ሞኝነት ነው አይቻልም ፤ እንደ ግብጽ ያሉ 90 በመቶ ሙስሊሞች ባሉበት ሀገር የኦርቶዶክሶችን ገዳም የሀገር ቅርስና ሀብት ስለሆነ 14ሚሊየን ዶላር እስላማዊ መንግስቱ በጅቶ ሲያሳድስ እናንተ ግን 45 በመቶ ኦርቶዶክሳውያን ባለንበት በዚች ሀገር የዋድባን ገዳም መሬት ለማረስ 8 ቢሊየን ብር መድባችኋል ፤ ይህ የዝቅጠታችሁ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጎንደርና አድርቃይ አካባቢው ላይ ያለ ክርስትያን ዋልድባ ሲታረስ እያየ ዝም እንደማይላችሁ እወቁ ፤ በ 16ተኛው ክፍለ ዘመን በሱስንዮስ ዘመነ መንግስት የተፈጠረውን የሀይማኖት ወረራ ለመመከት ምዕመኑ እንዴት በእምነቱ እንደቆመ ታሪክን ወደ ኋላ ብትመለከቱ ኖሮ ከታሪክ መማር ብልህነት መሆኑን ትረዱ ነበር ፤ የፍርሀታችንን ቆብ የምንጥልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፤ የዛኔ ለማንም የማይጠቅም ነገር ሊፈጠር አለመቻሉን እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ በዋልድባ ጉዳይ 1000 ሺህ ጊዜ ጥናት ቢካሄድ ሪፖርት ቢቀርብ መደምደሚያው ግን የስኳር ፕሮጀክቱን ማቆም ብቻ ሊሆን ይገባዋል ፤ ከ 1000 ዓመታ በላይ በሰላም የቆየን ገዳም ዛሬ ምን ተገኝ እና ነው አይናችሁን ያሳረፋችሁበት ? በተጨማሪም ከዚህ በፊት ስራ ከጀመራችሁበት ጊዜ አንስቶ በቦታው ላይ የተከናወኑትን ገቢረ ተዓምራት ባታምኑበት እንኳን መለስ ብላችሁ ተመልከቱ ፤ የትላንትናው የመኪና አደጋም ትምህርት ይሁናችሁ ፤ እስከ አሁን እግዚአብሔር ዝም ያላችሁ ትእግስቱ የበዛ አምላክ በመሆኑ እንጂ በሌላ አይምሰላችሁ ፤ መሬት አፏን እንደማትከፍት የዘራችሁት ሸንኮራ እባብ እንደማይሆንባችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ መናገር አትችሉም ፤ አባቶች አገልግሎታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አካባቢው ላይ ያሰፈራችሁትን የመከላከያ ሀይል ዞር አድርጉላቸው ፤ መሳሪያ ፈርቶ ገዳም ለቆ የሚሂድ መነኮሴ ያለ አይምሰላችሁ ፤
<><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><>
“የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም። ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ ! ምን እናደርጋለን ? አለው።
እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው።
ኤልሳዕም። አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር።
ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ። ይህን ሕዝብ ዕውር ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል ዕውር አደረጋቸው።”መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፤ 15-18
“ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፤ 16 ይላል የእግዚአብሔር ቃል ፤ እናንተ ጋር በአይን ከሚታዩት የታጠቁ ሰራዊቶቻችሁ ይልቅ አባቶቻችን ጋር ያለው እግዚአብሔር አስር እጥፍ ይበልጣል ፤ ከመነኮሳቱ ጋር ያሉት ጻድቃን ሰማእታት በእጥፍ እንደሚበልጡ እናምናለን፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ነው ፤ የኤልሳን ጸሎት የሰማ እግዚአብሔር ነው ፤ ሰራዊቱን እውር ያደረገው በኤልሳ ላይ ያደረው እግዚአብሔር ነው ፤ አሁንም በኦሪት ዘመን ነገሮችን ሲያከናው የነበረው እግዚአብሔር ፤ የያእቆብ አምላክ ፤ የይስሃቅ አምላክ የአብርሀም አምላክ አሁንም ከአባቶቻን ዛሬም ወደፊትም እንዳለ እወቁ ፡፡ ቦታው ላይ የሚደረገውን ነገር እየተመለከታችሁ ልቦናችሁ ደንድኖ በስራችሁ ከገፋችሁ ከባለቤቱ ከመድሀኒዓለም ጋር እንደምትገዳደሩ እወቁ ፤ እርሱን ታግሎ በታሪክ ያሸነፈ ማንም የለም ወደፊትም አይኖርምም ፤
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jun 06, 2012 1:10 am Post subject:
ሰላም የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች :-
ስለዋልድባ ገዳም ወቅታዊ ችግር በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን እያስተባበሩ ነው :: ትላንት ሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ .ም . በዋሽንግተን ዲ .ሲ በተደረገው የተቃውሚ ሠልፍ የነበረውን ሥነ -ሥርዓት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ እንዲህ ዘግቦታል ::
ምንጭ :- DejeSelam, Published on Jun 4, 2012. "ዋልድባ ገዳምን እናድን " የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ::
ወያኔ ጭራው ተይዟል
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jun 06, 2012 9:36 pm Post subject:
ሰላም ውድ ወገኖቼ :-
ዘንድሮ እኒህ የሣጥናኤል ቁራጭ የሆኑ ወያኔዎች በቤተክርስቲያን ላይ በገሃድ ጥፋታቸውን አጠናክረዋል :: ትላንት ደግሞ የግጭቱ ሥፍራ አዲስ አበባ ቀራኒዮ የሚገኘው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ነበር :: ሙሉ ዜናውን ከደጀሰላም ተከታተሉት ::
ምንጭ :- ደጀ ሰላም ፤ ግንቦት 29 ቀን 2004 ዓ .ም .:: በደብረ ይድራስ ቅ /ጊዮርጊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን የተሰማራው ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ይዞ ቤተ መቅደስ ገባ ::
Quote: · በአስለቃሽ ጢሱ ጸሎተ ቅዳሴው ታጉሏል፤ ሕፃናት፣ ምእመናንና አገልጋዮች ታፍነዋል ::
· ለውዝግቡ መፍትሔ ያፈላልጋል የተባለ ጥምር ኮሚቴ ተቋቁሟል ::
· ከ 70 - 80 የሚደርሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን እንደታሰሩ ናቸው ::
· ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሊቀ ጳጳሱን በስልክ አነጋግረዋል :: በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ትናንት፣ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ .ም ጠዋት በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ ስድስት ፖሊሶችና በርካታ ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ብዙዎቹን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላትንና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ በቁጥር ከ 70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣት እና አዛውንት ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡
ግጭቱ እየቀጠለ በነበረበት ኹኔታ ለጸሎተ ቅዳሴ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመበተን በሚል ፖሊስ ወደ ቤተ መቅደሱ ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተመልክቷል፤ በዚህም በመካሄድ ላይ የነበረው ጸሎተ ቅዳሴ ታጉሏል፤ ለቍርባን የተዘጋጁ ሕፃናት፣ ሌሎች ምእመናንና አገልጋዮችም በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በሮችና መስኰቶች መንሥኤው ለጊዜው ባልታወቀ ኹኔታ የተበሳሱና የተሰባበሩ ሲሆን የደብሩ አስተዳደር ቢሮዎች፣ የጥምቀተ ክርስትና ቤትና ሌሎችም በሮች “የተደበቁ ሰዎችን ለማሰስ” በሚል መዝጊያዎቻቸው እየተሰበረ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ተገልጧል፡፡
ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ‹የፓትርያሪኩ ልዩ ሀገረ ስብከት› በሚል ከሚታወቀው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የረዳት ሊቀ ጵጵስና ሓላፊነታቸው እየለቀቁ ያሉት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በጉዳዩ ላይ በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል፤ በግጭቱ አንድ ፖሊስ መሞቱንና ሌሎች ስድስት አባላት መቁሰላቸውን የተናገሩት ከንቲባ ኩማ የታሰሩት ምእመናን እንዲፈቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉ ተሰምቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት የደብሩ የክብረ በዓል (ንግሥ ) እና መስቀል ደመራ ሥፍራ የነበረውን ይዞታ የቀበሌ 06 ጽ /ቤት (የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ) ለመከለል የጀመረው ሂደት እንዲቆም ተደርጎ ውዝግቡን የሚያጣራ ኮሚቴ መቋቋሙ ተነግሯል፡፡ ኮሚቴው ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ ከአጥቢያው ምእመናን፣ ከክፍለ ከተማው አስተዳደርና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የተውጣጡ አባላት የሚገኙበት ነው፡፡
ግጭቱ ትናንት ጠዋት ከመቀስቀሱ ቀደም ብሎ የአጥቢያው አስተዳደር፣ አገልጋዮችና ምእመናን በፖሊስ ታጅቦ የመጣውን ግብረ ኀይል በባንዲራው እያሉ ሲማፀኑ ነበር፤ እነርሱ ራሳቸው ይዞታቸውን ለማስከበር በተደጋጋሚ ሲያመለክቱበት የቆዩበትና አሁንም ከፓትርያርኩ ጋራ እየተነጋገሩበት በመኾኑ ግብረ ኀይሉ ወደ ርምጃ ከመግባቱ አስቀድሞ ሁለት ቀናት እንዲሰጣቸው ሲጠይቁም እንደ ነበር ተዘግቧል፡፡
ምእመናኑ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ለሚያቀርቡት ተማጽኖ ቦታ ያልሰጠው ግብረ ኀይሉ ግን አጥሩን ወደ ማፈራረስና ችካል ወደ መቸከል ተግባር በመግባቱ ምእመናኑ ርምጃውን ድንጋይ በመወርወር ሲከላከሉ የአድማ ብተና ፖሊስ ደግሞ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ ምእመናኑን ለመበተን መሰማራቱ ተገልጧል፤ ጥይትም ተተኩሷል፡፡ የችካል ምልክቱ የሚያርፍበት ቦታ ከዐውደ ምሕረቱ ያለው ርቀት ከኀምሳ ሜትር እንደማይበልጥ የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የደብሩ አስተዳደር በዚህ ይዞታው ላይ በአንደኛ ደረጃ ት /ቤት ግንባታና በሌሎችም ትልሞች የራሱን የራስ አገዝ ልማት ዕቅዶች ለማካሄድ ሲንቀሳቀስ እንደ ነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ በርካታ አድባራትና ገዳማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዳገኙ ተዘግቧል፡፡ በአንዳንዶቹም÷ ለአብነት ያህል በኮተቤ ደብረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል÷ የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ለግለሰብ ጥቅመኞችና ለፕሮቴስንታቶች በመሰጠቱ የወረዳው ፖሊስ ጽ /ቤት የየካ ክፍለ ከተማ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በጉዳዩ እንዲያስብበት ያቀረበው ጥያቄ ይገኝበታል፡፡
በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንም የትናንቱ ችግር በተዘገበው ደረጃ እንዲባባስ ያደረገው አሁን እስከ ዐውደ ምሕረቱ የዘለቀው የይዞታ ነጠቃ ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ጽ /ቤት ቀደም ብሎ የደብሩ ካህናት መኖሪያ ቤት ተሠርቶበት የነበረውን ቦታ በመውሰድ ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ጽ /ቤት ሲሠራበት በዝምታ በመታለፉ መሆኑን አስተየየታቸውን ለዜና ሰዎች የሰጡ የሰበካው ምእመናን ገልጸዋል፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ (ከፍተኛ 24 ቀበሌ 14 59 ቁጥር ማዞርያ ) አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከ 23 ዓመት በፊት፣ በ 1981 ዓ .ም የተመሠረተ ደብር ነው፡፡
ይድራስ የዱድያኖስ ጭፍሮች የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ዐፅም አቃጥለውና ፈጭተው የበተኑበት ተራራ ስም እንደ ኾነ ይታወቃል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Wed Jun 06, 2012 11:01 pm Post subject:
ይገርማል እኮ ! አስለቃሽ ጭሱን እጣን አድርገውት አረፉ ! ቤተ መቅደስ ውስጥ ዘው ብሎ የተቀደሰውን ነገር ለማርከስ መሞከር ምን ይባላል ?? "ጀግናው ተጋዳላይ አይ ጀግንነት
ሰሞኑን እንዲሁ ጎንደር ውስጥ ተታኩሰዋቸው የሞቱ ሰዎችን አስከሬን መሬት ለመሬት ማስጎተት በህወሀት ቤት የሞተ ሰው መጎተቱ ጎንደርን ማስፈራራቱ ነው :: መቀጣጫ ማድረጉ ነው እንደጀግና ያለፉ ሰዎችን አስከሬን የሚያስጎትት እና የሚጎትት ነው የሞተው :: እንደ ሰው ተታኩሶ ገሎ የሞተማ ክብሩ ያለው ሞቱ ላይ ነው :: ጣሊያንም ከገደለ በኍላ አንገት እና እጂ እየቆረጠ ለናሙና በእግዚቢት ያሳይ ነበር :: አርበኞቹ ግን አርበኛ ነበሩ ! ዛሬሞ ሞተውም አርበኛ ናቸው ! መጥፎ ማለት ህወሀት እጂ ላይ ተልፈስፍሶ መውደቅ ነው :: እነዛን ጎበዞች የምንዘክርበት ቀን ሩቅ አይሆንም !!
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወርቅነች Joined: 03 Oct 2010 Posts: 568
Posted: Sat Jun 09, 2012 6:44 am Post subject:
Quote: ዋልድባ አሁንም ጭንቅ ላይ ናት ::
ቅቅቅቅቅ ..ፈዛዛው ቄሰ እንደምን ሰንብተሀል ...ሰሞኑን ዋርካን እየተቆጣጠርክ ለዚህ ነው ያበድከው እንዴ በል በል ይለሀል እንዴ የዘፈን ዳር ዳሩ እስከስታ ነው እብደትም ሲጀምር እኮ ነካ ነካ ያደርጋል ... አሁን መዳኛህን ፈልገው ዋልድባ እንደሆን አንተን አይታ ነው የተጨነቅቸው ...አርግዛለች አሁን አንተ እሷ ጋ ባትደርሰም በውነቱ አንተን ያይች እንደሆን ካሁን ወዲህ ትፈንዳለች ...እንዳትፈነዳ የፈለክ እንደሆን ቄሶቹን ሰብሰበህ ጥቁር አህያ ማረድ አለብህ እንዳትፈንዳ ...ጀሚላ ትለሀለች ከቸርችል ጎዳና
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-
ዋልድባ አሁንም ጭንቅ ላይ ናት ::
ምንጭ :- ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 25 ቀን 2004 ዓ .ም፤ ሰበር ዜና - የዋልድባ ገዳም ተመዘበረ !!
Quote: . የገዳሙ ዕቃ ቤት በሮች ተሰባብረው 65,000 ብር ተዘርፏል፤ ሙዳየ ምጽዋት እና የመጻሕፍት መያዣ ሣጥኖች ተገለባብጠዋል፤ አርድእቱ ተንገላተዋል።
. የማይ ፀብሪ ወረዳ ፖሊስ "እናንተው ራሳችኹ ኾነ ብላችኹ የፈጠራችኹት ችግር ቢኾንስ " በሚል መነኰሳቱን ተዳፍሯል።
. ሕዝቡ በዛሬማ አቅጣጫ ወደ ፕሮጀክቱ ቦታ መትመሙን እንደቀጠለ ተገልጧል።
ከዋልድባ ገዳም ዕቃ ቤት እና የአትክልት ቦታ ይዞታዎች አንዱ የኾነው ማይ ለበጣ ትናንት፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2004 ዓ .ም ሌሊት ማንነታቸው ባልታወቁ ኀይሎች መመዝበሩ ተገለጸ፡፡
የገዳሙ መነኰሳት ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት÷ መዝባሪዎቹ ማይ ለበጣ ወደሚገኘው የገዳሙ ዕቃ ቤት የገቡት መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው፡፡ ለሁለት ሰዓት ያህል ሥፍራውን ድራሽ አምላኩን እያጠፉ የቆዩት እኒህ አፍራሽ ወራሪዎች አርድእቱንና መነኰሳቱን አግተው ከዕቃ ቤቱ ስድስት በሮች ሦስቱን በመሰባበር ለኑግ መግዣ የተቀመጠውን ብር 65,000 ዘርፈዋል፤ ከቦታው ሞቃታማነት የተነሣ በሜዳው የዕንቅልፍ ዕረፍት ላይ የነበሩትን ዐሥር አርድእት ቤት ውስጥ አስገብተው ከዘጉባቸው በኋላ "የምንፈልገው ሰው አለ " በሚል ፊታቸውን በባትሪ ብርሃን እያዩ አንገላተዋቸዋል፡፡
ስለ ዘራፊዎቹ አኳኋን እንዲገልጹ የተጠየቁት አንድ አባት፣ "ቁጥራቸው ከ 5 - 7 ይሆናሉ፤ በአለባበሳቸው ሚሊሻ ይመስላሉ፤ እንዳንለያቸው ፊታቸውን በጨርቅ ሸፍነውታል፤ ያልከፈቱት ሙዳየ ምጽዋትና መጻሕፍት መያዣ ሣጥን የለም " በማለት አስረድተዋል፡፡
መዝባሪዎቹ ስፍራውን ለቀው ከሄዱ በኋላ ከመነኰሳቱ ለማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳደር በስልክ በተገለጸው መሠረት ዛሬ ጠዋት ወደ ማይ ለበጣ የመጡት ሓላፊዎች "እናንተው ራሳችሁ ኾነ ብላችኹ የፈጠራችሁት ችግር ቢኾንስ " በሚል መነኰሳቱን መዳፈራቸው ተዘግቧል፡፡
ባለሥልጣናቱ ወደ ማይ ለበጣ በመጡበት መኪና ወደ ወረዳው የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ያመሩት ገዳማውያኑ ኹኔታውን በዝርዝር በማስረዳት ማመልከታቸውንና "ጉዳዩን እንከታተለዋለን " የሚል ምላሽ ብቻ ተሰጧቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል፡፡
የዋልድባ ገዳም ከቀናበት ከ 485 ዓ .ም ጀምሮ ገዳማውያኑ በተለያዩ ወቅቶች ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ በ 875 ዓ .ም ዮዲት ጉዲት መነኰሳቱን በሰይፍ አስፈጅታቸዋለች፤ በ 1277 ዓ .ም ገዳሙ በተተኪ መጥፋት ጠፍ ኾኖ ከቆየ በኋላ በ 1319 ዓ .ም በጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንደገና ተቋቁሟል፤ በ 1870ዎቹ ተከዜን እየተሻገሩ በገዳሙ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ይሰነዝሩ በነበሩ ደርቡሾችና ኢአማንያን ምክንያት በተለይም በማይ ለበጣ በኩል አትክልት የሚያለሙ በርካታ አርድእት - መነኰሳት በሰይፍ ማለቃቸውን የገዳሙ ታሪክ ይናገራል፡፡
ታላቁና ጥንታዊው የዋልድባ ገዳም ከሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት የሚለየው በዋናነት በገዳሙ መሬት እህል ስለማይበላበት ሲኾን አትክልትና የሥራ ሥር ተክሎች በብዛት የሚገኙበት ሰፊ መሬት ያለው መኾኑም ሌላው ምክንያት ነው፡፡ በማይ ለበጣ በቁጥር እስከ 30 የሚደርሱ ሰፊና ውኃ ገብ የአትክልት ቦታዎች ይገኛሉ፤ በተለይ በበጋ ወራት የመነኰሳቱ ምግብ የኾነውን ፍራፍሬና ሥራ ሥር ተክሎች በመስኖ የሚያለሙት አርድእት አትክልተኛ ወይም ወንዘኛ ተብለው የሚጠሩ ሲኾን ምግቡን በቋርፍ መልክ የሚያዘጋጁት ደግሞ ተለሽ ይባላሉ፡፡
ይህም ገዳሙ አበው መናንያንና መነኰሳት መቲረ ፈቃድን በማሳየት የሥጋ መሻቱን የዐይን አምሮቱን በልቡናቸው ወስነው ለእግዚአብሔር በመገዛት የሚኖሩበት፣ ሠርተው በሚያገኙት ገቢ የሚተዳደሩበት የሥራ እና የሕርመት ቦታ እንጂ የሰነፎች መጦርያ አለመሆኑን በተግባር የሚመሰክር ነው፡፡
በሌላ በኩል ሕዝበ ክርስቲያኑ ካለፈው ሳምንት ኀሙስ ጀምሮ ከዓዲ አርቃይ፣ ደባርቅ ዙሪያ እና ዳባት ወረዳዎች ከሚገኙ የሳንቅ፣ ቀላ ወገራ፣ አጅሬ፣ አሳቦ፣ ዳልዲማ፣ ኮታ፣ ድምጦ፣ ጅሮ ሳም፣ ቦዛ፣ አንጓ፣ ቀርነጃ እና ዓሊ ከመሳሰሉት ገጠር ቀበሌዎች የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ወደሚካሄድበት ስፍራ ማቅናቱን እንደቀጠለ የገዳሙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በገዳሙ ላይ ስለሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ ሕዝቡ በየሰንበቴው፣ በየማኅበሩ እና በየልቅሶው ሲመክርበት መቆየቱን የሚገልጹት ምንጮቹ÷ ካለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ ሚያዝያ 18 ቀን 2004 ዓ .ም አንሥቶ የሰማው ላልሰማው እያሰማ ከነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች ጀምሮ ዲጅኖ፣ ፋጤ ፋስ፣ ገጀራ፣ አካፋ እና ዶማ በመያዝ፣ ደረቅ ስንቁን (ድርቆሽ፣ በሶ፣ ቆሎ ) በመጫን በቡድን በቡድን መትመሙን ተያይዞታል፡፡
በማይ ፀብሪ - ማይ ለበጣ በኩል የሚያልፉ መንገደኞች ከአምስትና ስድስት ጊዜያት በላይ መታወቂያ በተደጋጋሚ እየተጠየቁ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚካሄድባቸው ሕዝቡ ወደ ፕሮጀክቱ ስፍራ እየወረደ የሚገኘው በዛሬማ በኩል መኾኑ ተመልክቷል፡፡
በሰሜን ጎንደር የዓዲ አርቃይ ወረዳ ም /ቤት አባላት እና የብአዴን ጽ /ቤት ሓላፊዎች የተወሰኑ ተጓዦችን በመኪና ተከትለው ዓሊ በተባለው ቀበሌ (ከዋልድባ ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ዝቅ ብሎ የሚገኝ ) ላይ ደርሰው ያነጋገሯቸው ሲኾን ሕዝቡ "እናንተ አይመለከታችኹም፤ ከእኛ ጋራ መሣርያ መዋረድ ትፈልጋላችኹ ወይ ? የእኛ ጥያቄ ገዳሙን ከደፈረውና ካረሰው አካል ጋራ በመኾኑ እዚያው ደርሰን ይህንኑ በዐይናችን አይተን ማረጋገጥ እንፈልጋለን፤ " በሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ተገልጧል፤ ሓላፊዎቹም መልሰው "ወደ ገዳም የሚኬደው ጦርና ጎራዴ ተይዞ ነው ወይ ?" ላሉትም "እናንተስ ገዳሙን እያፈረሳችሁ አይደለም ወይ ?" በሚል እንደተመለሰላቸው ተዘግቧል፡፡ ለወረዳው ፖሊሶችም "ግድቡ ቆሞ ቦታው ከተለቀቀ እኛ ሌላ ጠብ የለንም፤ ከእኛ ጎን ሆናችሁ የገዳሙን ክብር ማስጠበቅ አለባችሁ፤ " የሚል ምክር ተሰጥቷቸዋል - በሕዝቡ፡፡
ከወረዳው ባለሥልጣናት አንዳንዶቹም "ፕሮጀክቱ ገዳሙን የሚጎዳ ኾኖ ከተገኘ ሁላችን የድርሻችን መወጣታችን አይቀርም፤ ከጎናችኹ እንቆማለን፤ " ሲሉ መደመጣቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡
በምዕራብ ትግራይ የማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ የሕዝቡ ተመማ ወሬ እንደተሰማ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ሥራውን አቁመው ከአካባቢው ዘወር እንዲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፤ ሥራውም ለጊዜው ቆሟል ተብሏል፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ መረሳ ትናንት ለቪኦኤ የአማርኛ አገልግሎት ሲናገሩ የሕዝብ ተመማ አለ የሚባለው መረጃ ፈጽሞ የተሳሳተ መኾኑን በማስተባበል የፕሮጀክቱ ሥራ ሌት ተቀን እየተፋጠነ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለው የአህጉረ ስብከት አወቃቀር መሠረት የዋልድባ ገዳም አጠቃላይ ይዞታ በሦስት አህጉረ ስብከት ውስጥ ተከፋፍሎ የሚገኝ ነው፡፡
የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ዋሊ ቅድስት ደቂቁ ለሳሙኤል እና የዋልድባ ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የሚገኙ ናቸው፤ ሊቀ ጳጳሱም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ናቸው፤ ከዋልድባ አብረንታንት ገዳም፣ አባ ነጻ እስከ ዛሬማ ወንዝ ድረስ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት የሚገኝ ሲሆን ሊቀ ጳጳሱም ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ናቸው፤ ከዛሬማ ወንዝ ማዶ የወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ሀገረ ስብከት ሲሆን የገዳሙ ሞፈር ቤቶች ያሉባቸው፣ እርግና የተጫናቸው፣ ከሕመም የተነሣ ቋርፍ የከበዳቸው አባቶች እና ሴት መነኰሳዪያት የሚገኙባቸው ሦስቱ ተነሺ አብያተ ክርስቲያን ያሉባቸው ናቸው፤ ሊቀ ጳጳሱም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ናቸው፡፡
ግድቡ ከሚሠራበት ዛሬማ ወንዝ በመኪና የ 30 ደቂቃ፣ በእግር የአንድ ሰዓት መንገድ ርቆ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጽ /ቤት እና የሠራተኞች መኖርያ ካምፕ (በወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ሀገረ ስብከት ) ይገኛል፡፡
ዋነኛው የዋልድባ ገዳም ይዞታ የሆነው የአብረንታንት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ቦታ ላይ (ከባሕር ጠለል በላይ 1270 ሜትር ) የሚገኝ ሲኾን በግድቡ ውኃ የተነሣ በመጥለቅለቅ ስጋት ውስጥ የሚገኘው የአባ ነጻ አካባቢ ደግሞ በዝቅተኛ (ከባሕር ጠለል በላይ 1073 ሜትር ) ላይ ይገኛል፡፡
በዓዲ አርቃይ በኩል ወደ ገዳሙ ሲገባ የዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለምን ለሁለት በመክፈል ሰፊና ለሙን የገዳሙን ክልል በስተቀኝ የያዙት የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ሲኾኑ በስተግራ ደግሞ የቤተ ጣዕማ መነኰሳት ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Jun 10, 2012 3:04 am Post subject:
የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
በአውሬው ተከታዮች (ወያኔዎች ) እና በቤተክርስቲያን ልጆች መካከል ፍልሚያው ቀጥሏል :: ዋልድባን የእነርሱ የአውሬው ሠራዊት መፈንጫ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም : አልተሣካላቸውም : ምንጊዜም አይሣካላቸውም :: ከሚከተሉት የዜና ምንጮች ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ ::
ምንጮች :-
1 ..... አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ .ም .:: በዋልድባ ጉዳይ ከ 20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል ::
2 ..... የአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ የአማርኛ መርኃግብር : አርብ ሰኔ 2 ቀን 2004 ዓ .ም . :: ከ 38ኛው ደቂቃ ጀምሮ ::
Quote: የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ 3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ .ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ወደ እስር ቤት ገብተዋል ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን ?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤ ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤ 28
በቦታው ላይ የሚገኙ የባለስልጣናቱ የስብሰባ መከራከሪያ ነጥብ “ቤተክህነቱ የፈቀደውን እናንተ ምን አገባችሁና ነው የምትቃወሙት” የሚል ነው ፤ እውነታቸውን ነው በቤተክህነቱ የተላኩት ቡድኖች ሪፖርት መፍቀዱን በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን አስታውቋል ፤ ስኳር ልማቱ ገዳሙ ላይ የሚያመጣበት ተጽህኖም እንደሌለ አስረግጦ ተናግሯል ፤ የአባቶች የሲኖዶስ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ቀንም ጉዳዩን እንደተነጋገሩበት በማስመሰል የማጠናቀቂያ ሪፖርቱ ላይ ለማገባት ሞክሯል ፤ ይህን የቤተክህነቱን ሪፖርት ግን ምዕመኑ የሚቀበለው አይደለም ፡፡
ባለፉት ሶስት ቀናት የታሰሩት ወጣቶች ቁጥር ከ 20 እስከ 30 የሚደርሱ ሲሆን በትላንትናው እለት 3 ወጣቶች ከእስር ሲፈቱ በእነርሱ ምትክ ከአድርቃይ ወደ ገሪማ 7 ሰዎች በፖሊስ እና በገዳሙ ውስጥ በሚሰለጥኑ የሚኒሻ ሃይሎች ካበት ተይዘው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል ፤ በተጨማሪም ለታሰሩት ወጣቶች ብር ሲሰበስቡ የነበሩ ተጨማሪ ወጣቶችን ወደ እስር አውርደዋቸዋል ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jun 13, 2012 7:32 pm Post subject:
ሰላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች :-
ዛሬም ነገም ስለጥንታዊ ገዳሞቻችን ለማወቅ መጣር ይጠበቅብናል :: ጥቂት ስለ ዋልድባ ገዳም :-
ምንጭ :- ዋልድባን ከቅርብ ርቀት (ልዩ ጥንቅር ከአዲስ አበባ )::
Quote: መንግስት በልማት ስም ቅዱስና ታሪካዊ የሆነውን የዋልድባን ገዳም ተጠግቶ የስኳር ፋብሪካ እገነባለሁ ካለ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ ከአገር አልፎ በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በስፋት ሲያነጋግር ሰንብቷል። ዋልድባ ለክፍለ ዘመናት ታፍሮና ተከብሮ "በጥብቅ " ሀይማኖታዊ ስርዓት የቆየ፣ ፍጹም ልዩ የሆነ መንፈሳዊና ታሪካዊ ዋጋ ያለው ስፍራ እንደመሆኑ በስፋት እየቀረበ ያለው ተቃውሞም በከፍተኛ ስሜት እና ቁጣ የታጀበ ሊሆን ችሏል።
እኔም ችግሩ የአንድ ወቅት ትኩሳት ሆኖ የማይቆም፤ ይልቅስ የማንነት፣ የታሪክና የዕምነት ፅናት ጥያቄ መሆኑን በማመኔ ነበር በስፍራው ተገኝቼ ሁኔታውን መመርመር እንዳለብኝ የወሰንኩት። ያዩ፣ የሰሙትንና የታዘቡትን ለህዝብ ማካፈሉ ደግሞ የሙያ ብቻ ሳይሆን የዜግነትም ግዴታ ይመስለኛል።
ዋልድባ ደርሼ የሆነውን ሁሉ ለመመርመር ያደረኩት ጥረት ግን በመስዋዕትነት የተከበበ፣ ብዙ ዋጋም ሊያስከፍለኝ ይችል የነበል እንደሆነ መሸሸግ አልችልም። ከአ .አ . ጎንደር፣ ከጎንደር ዋልድባ ለመድረስ ያለው የጉዞ ርዝማኔ እንዳለ ሆኖ ከገዳሙ ለመድረስ ከ 30 በላይ ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩን ጀምሮ ያለው ጥብቅ ጥያቄና ምዝገባ ሁሉ እጅግ አስደንጋጭና ያልተለመደ ነው።
የተሳፈርኩበት አውቶብስ ዋልድባ ሊደርስ 35 ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው ወደ ቀኝ ወደወልቃይት ፣ ቀጥታውን ደግሞ ወደ ዋልድባ የሚዘለቅበት መንገድ መገናኛ ስፍራ ላይ ትልቅ ኬላ ተሰርቷል። ይህ ስፍራ በአካባቢው ስዎች "ጉምድኝ " ተበሎ የሚጠራ ሲሆን ረቡእ እና ቅዳሜ የደራ የገበያ ስፍራ እንደሚሆንም ተነግሮኛል። እዚህ ስፍራ ሲደረስ የዋልድባ ተጓዥ ወርዶ በሌላ መኪና መሳፈሩ የተለመደ ነውና እኔም ከዋልድባ መንገደኞች ጋር መውረድ ነበረብኝ። ነገር ግን ቀደም ብሎ በደረሰኝ መረጃ መሰረት እዚያ ስፍራ ላይ ያሉት የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ዋልድባ የሚሄዱ ሠዎችን ስም በማጣራት 'ወዴትና ለምን ?' እንደሚሄዱ በመጠየቅ የሚመዘግቡ በመሆናቸው የእኔ እዚያ ቦታ ተገኝቶ መመዝገብ አደገኛነቱ የታሰበኝ ከመኪና ሳልወርድ ነበር።
በ«ሰው በላ» መንግስት አንጋቾች እጅ መውደቅ ምን ሊያስከትል እንደሚችል እያሰላሰልኩ የጉዞዬን ዓላማም ጭራሽ የማላሳካበት ዕድል እንዳይፈጠር ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ። . . . በዚህም ወደቀኝ ታጥፈው ከሚዘልቁት የወልቃይት መንገደኞች ጋር ከመሄድ ውጭ አማራጭ አልነበረኝም። በጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ውስጥ በወደቀው የአካባቢው ሁኔታ እየተገረምኩ ሁሉን በፍርሃትና በጥርጣሬ አይን እየቃኘሁ ለግማሽ ቀን በወልቃይት ዙሪያ "መክፈልት " በምትባለው የገጠር ቀበሌ ሆኜ ዋልድባን ከሩቅ በሃሳብ እየዋኘሁበት ተከታዩን ዘገባ አጠናቀርኩ።
በወልቃይትና በዋልድባ መካከል በሚፈሰው ዘረማ (ዛሬማ ) ወንዝ መንግስት ለስኳር ልማት እየገነባ ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ይሄን ያህል እንዴት ትኩረት ሊሰጠውና እንዲህ ሊያጨቃጭቅ ቻለ ? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢና ወቀታዊም ይመስለኛል።
ዋልድባ ሲባል እንደ ደብረ ሊባኖስ፣ ዝቋላ አቦ፣ ግሸን ማሪያም ....ወዘተ በአንድ የተወሰነ ጠባብ ቦታና አጥር የተከለለ የሚመሰላቸው ሠዎች ጥቂት አይደሉም።
ዋልድባ ገዳምን ከበው ከያዙት (ከሚያዋስኑት ) ወንዞች መካከል በምእራብ አቅጣጫ የሚገኘው ዘረማ ወንዝ አሁን ለስኳር ልማት ተብሎ የመስኖ ፕሮጀክት የተጀመረበት ነው። ይህንኑ ፕሮጀክት በሚመለከት ያነጋገረኩት አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ቅዱሳን አባቶች የሚጠልቁት ወንዝ በመሆኑ መንግስት ለስኳር ልማት መስኖ ፕሮጀክት መጠቀሙ መንፈሳዊነቱን ይጻረረዋል ብሎኛል። በገዳሙ ዙሪያ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንዱ የሆኑ አባት ግን «ቅዱሳት አባቶች ከማየ ዮርዳኖስ እንጂ ከዘረማ አይጠልቁም» ብለውኛል።
በገዳሙ አዋሳኝ ከሚገኘው ዘረማ ወንዝ ተጠልፎ እየተስራ ያልውን የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚመለከት ያነጋገርኳቸው ሌላ አባት ደግሞ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ከገዳሙ ውጪ የሚገኝ ቢሆንም ዘረማ ወንዝ በቅዱሳን መነኮሳት ዘንድ ከገነት የሚፈስ ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ ‘ባይነካ ነበር ደግ’ ብለውኛል።
በወልቃይት እና በዋልድባ ገዳም አማካኝ ስፍራ ላይ የሚፈሰው የዘረማ ወንዝ ለአካባቢው ነዋሪ አርሶ አደሮች ከብቶቻቸውን ውሃ የሚያጠጡበት፣ ራሳቸውም እየጠለቁ ለቤት ውስጥ ፍጆታ የሚጠቀሙበት እንደሆነ የገለጹልኝ አንድ የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው የሰኳር ልማት ፕሪጀክቱ ከገዳሙ ውጪ ያለ ቢሆንም ከስኳር ልማቱ ጋር በተያያዘ የሚመሰረተው መንደር የአካባቢውን ሠላማዊነት ሊረብሸው እንደሚችል ገልጸው ለፕሮጀክቱ ስራ ተብሎ በሚመሠረተው መንደር የሚሠፍሩት ሠዎች የመሃል አገር ሰዎች መሆናቸውና የአካባቢውን ጥብቅ መንፈሳዊ ህግጋት የማያውቁ መሆናቸው መጪውን ጊዜ እንድንናፍቀው አያደርገንም ብለዋል።
በዋልድባ ገዳምና የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በሚሰራበት ስፍራ መካከል ርቀት መኖሩን የተረዱ ሠዎች ቁጥር በርካታ ቢሆንም ግንዛቢያቸው ከስጋት ነፃ አይደለም። ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው መንደር ከመንደሩም ጋር ተያይዞ የሚመጡ ሰዋዊ ባህሪያት የሚፈጥሩት ያልተገባ ድርጊት በርቀትም ቢሆን የገዳሙን መለኮታዊ መልክ ሊረብሸው ይችላል የሚል ስጋት አለ።
እዚህ ጋ ቀደም ብለን ያነሳነው አንድ ጥያቄ ተመልሶ ሊነሳ ይችላል።’ የዋልድባ ጉዳይ ይሄን ያህል እንዴት ትኩረት ሊሰጠውና ሊያጨቃጭቅ ቻለ ?’ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመሻት አጠቃላዩን የገዳሙን ሁኔታ መቃኘቱ ተገቢ ይመስላል።
መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ
ዋልድባ በአራት ወንዞች የተከበበ /የታጠረ ቢባል ይሻላል / አራት ማእዘን አይነት ቅርጽ ያለው የአንድ ወረዳ /አውራጃ / ግዛት ያህል ስፋት ያለው አካባቢ ነው። በሌላ አገላለጽ ከደቡብ እስከ ሰሜን / ከአርማሕ ደጋ እስከ ተከዜ / ያለው ርቀት በግምት ከ 120-150 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ማለትም ከእንስየ ወንዝ እስከ ዘረማ ወንዝ ያለው ርቀት ደግሞ ከ 60-70 ኪሎ ሜትር ይሆናል።
እንደዛም ሆኖ የዋልድባ ገዳም በደቡብ ሰፋ ያለ ሆኖ ወደ ተከዜ ወንዝ እየተጠጋ በመጣ ቁጥር እየጠበበ ሄዶ እስከ 30 ኪ .ሜ ይሆናል። አራቱ የዋልድባ አዋሳኝ ወንዞች በምስራቅ እንስየ፣ በምዕራብ ዘረማ፣ በሰሜን ተከዜ፣ በደቡብ ወይባ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ትንሹ ወይባ ሲሆን በዋልድባ ደቡብ ካሉ ተራሮች ተነስቶ ጨው በርንና ዋልድባን እየለየ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ወደ እንስያ ይቀላቀላል።
"እህል አይቀመስበት፣ ሓጢያት አይሻገርበት " የተባለለት ዋልድባ በውስጡ ወይና ደጋና ቆላማ የአየር ንብረቶች ያካተተ በመሆኑ በቦታው የሚበቅሉ ዕጽዋት አይነት ቁጥር እጅግ በርካታ ናቸው። ለአብነት ያህል ደቅማ፣ ማቅማ፣ ጣበሌ፣ ወይባ፣ ዲማ /ፍርጣጣ /፣ ሸመል፣ እንኮይ፣ግራር /ሦስት አይነት /፣ወይላሆ፣ በትረ ያሬድ፣ አምፋር፣ አጋም፣ ኮርች፣ ወዘተ በዋልድባ በብዛት የሚበቅሉ ናቸው። ከትላልቅ ዛፎች በተጨማሪ ቁጥራቸው የበዛ የሐረግና የሣር አይነቶችም ይበቅላሉ።
በሃገራችን ውስጥ ካሉት ከሁለት ሺ ጥንታዊያን ገዳማት መካከል የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ከሚለዩባቸው ነገሮች አንዱ የሚለመሱት የልብስ ቀለም አይነት ነው። ሁሉም በወይባ ዛፍ ልጥ የተነከረ ቢጫ ልብስ ነው የሚለብሱት። አንድ አባት ጠይቄ እንደተረዳሁት የዋልድባ መነኮሳት ነጩን አቡጅዲድ ጨርቅ በውሃ በተፈላ የወይባ ዛፍ ልጥ እየነከሩ ወደ ቢጫነት የሚለውጡት በሁለት ምክንያት ነው።፡የመጀመሪያው ራሳቸውን ከአካባቢው ለማመሳስል (ከሩቅ ላለመታየት ) ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ግን አካባቢው ወባማ በአካባቢው አጠራር «ንዳድማ» በመሆኑ በወይባ የተነከረ ጨርቅ የወባ ትንኝ ስለማይጠጋው ከወባ በሽታ ለመከላከል ስለሚረዳ ነው። ይህንን ሚስጥር ግን ብዙዎቹ አያውቁትም።
ሁለተኛው የዋልድባ ታሪካዊ ዛፍ ዲማ ነው።፡ዲማ እጅግ በጣም ወፍራምና ረዥም የሆነ (አንዳንዴ የዛፉ ግንድ ውፋሬ ከመለስተኛ ቤት ይበልጣል )፣ የሚበላ ፍሬ የሚያፈራ ግዙፍ የዛፍ አይነት ነው። እንደዛም ሆኖ የዛፉ ግንድ የተደራረበ ቅርፊት (ልጥ ) እንጂ የሚፈለጥ፣ የሚሰነጠቅ ጠንካራ እንጨት የለውም። በመሆኑም ለቤትም ሆነ ለቁሳቁስ መሥሪያነት አያገለግልም። ይሁን እንጂ ዲማ በዋልድባ የተለየ ጠቀሜታ አለው። አባቶች ወደ ብቃት ደረጃ በሚሸጋገሩበት ግዜ ግንዱን ይቦረቡሩና (በቀላሉ ስለሚቦረቦር ) ውስጥ ገብተው ቁጭ ይላሉ። በዚህ መልክ ሱባኤ የሚይዙ አባቶች በሳምንት አንዴ ብቻ ነው ቋርፍ የሚመገቡት። ከሁሉ የሚገርመው በዚህ አይነት ሆነው (ኩርምት ብለው እንደተቀመጡ ) እስከ 40 አመት በሕይወት የቆዩ አባቶችና እናቶች እንደነበሩ አስረጂው ስማቸው በክብር ተመዝግቦ መገኘቱ ነው።
የዲማ አስገራሚነት ለመነኮሳቱ እንደ ቤት ሆኖ ማገልገሉ ብቻ አይደለም። አባቶች በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ጊዜ የተቦረቦረው የዛፍ ክፍል በራሱ እየሞላ ይሄድና መቃብር ይሆናቸዋል። በዚህ መልክ የቅዱሳን አፅም በሆዳቸው እንደያዙ የቆሙ በርካታ የዲማ ዛፎች አሁንም አሉ። ከዲማና ወይባ ሌላ ለተለያዩ ቁሳቁስ (መቁጠሪያ፣ መቋሚያ፣ ሙቀጫ፣ ጭልፋ፣ መስቀል . . .ወዘተ ) መስሪያ የሚያገለግሉ የዕፅዋት ዓይነቶችም አሉ።
ዋልድባ በደን የተሸፈነ በመሆኑ በውስጡ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የዱር እንሰሳት ያለ ስጋት የሚርመሰመሱበት፣ የተለያየ ዓይነትና መጠን ያላቸው አእዋፍ የሚኖሩበት የገነት አምሳያ ቦታ ነው። አንበሳ፣ ነብር፣ አጋዘን፣ ወንድቢ (በሬ መሳይ )፣ ድኩላ፣ ሚዳቋ፣ ስስ፣ አሳማ፣ ጃርት፣ ተኩላ፣ ዥግራ፣ ቆቅ፣ ጦጣ፣ ዝንጀሮ፣ ዘንዶ፣ አዞ (ውንዝ ውስጥ ) ይገኛሉ።
“አንዳንዴ በዋልድባም ይዘፈናል” የሚባል ዝነኛ አባባል አለ። ብሂሉ ከዱር እንሰሳት ጋር የተያያዘ ታሪክ ያለው ነው። ከጥንት ጀምሮ በዋልድባ ክልል ውስጥ ጥይት ተኩሶ እንሰሳ መግደል፣ በወጥመድ የዱር እንሰሳ መያዝና መግደል ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ቢሆንም ከዋልድባ ባሻገር ያሉ ቦታዎችም በደን የተሸፈኑ ስለነበሩ አዳኞች ከሩቅ ቦታ እየመጡ በአካባቢው ያድኑ ነበር።
በተለይ ደግሞ ዝኆኖች በብዛት በክልሉ ይገኙ ስለነበር ነገስታት ሳይቀሩ ለአደን ወደ አካባቢው አዘውትረው ይመጡ ነበር። ታዲያ በዋልድባ ውስጥ ገብቶ ማደን ባይቻልም ነገስታቱና ሹማምንቱ ሰራዊታቸውን ወደ ገዳሙ ክልል በማስገባት በውስጡ ያሉትን ዝኆኖች በመረበሽ ከገዳሙ ክልል እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ ጠብቀው ይገድሉዋቸው ነበር። ዝሆንን አድኖ ለመግደል ጊዜ ስለሚጠይቅ ነገስታቱ አደናቸውን እስኪያከናውኑ ድረስ በአካባቢው ድንኳን ተክለው ይቀመጣሉ።
በዚህ መካከል በለስ ሲቀናቸው በድንኳኖቻቸው ሆነው /ዋልድባ ድንበር / ይሸልላሉ ፣ይዘፍናሉ፣ያዘፍናሉ። በዚህ መነሻነት መነሻነት ነው አንዳንዴ በዋልድባም ይዘፈናል የተባለው።
ታሪካዊ አመጣጡ
በዋልድባ ውስጥ ሦስት ገዳማት ይገኛሉ እነርሱም ፦
1/ ዋልድባ አብረንታንት
2/ ዋልድባ ድልሽህ
3/ ዋልድባ ስቋር ይባላሉ።
ከእነዚህ መካከል ትልቁና አንጋፋው ዋልድባ አብረንታንት ነው። ይህ ገዳም (በገዳምነት በይፋ የተቋቋመው በ 1398 አ .ም ) ሲሆን ከ 485 አ .ም ጀምሮ ግን መናንያን በቦታው ይኖሩ እንደነበር ይታመናል። ዋልድባ ድልሽህና ዋልድባ ሰቋር ግን በቅደም ተከተል በ 1505 አ .ም እና በ 1658 አ .ም ነው የተመሰረቱት። በዋናው አብረንታንት ገዳምና በሁለቱ መካከል ያለው ርቀትም ቢሆን ትልቅ ነው። ለምሳሌ ያህል ከዋልድባ አብረንታንት እስከ ዳልሽህ ያለው ርቀት 50 ኪ .ሜ ይሆናል።
ዋልድባ ከስፋቱ በተጨማሪ በበርካታ አስደናቂ ነገሮች ከሌሎች ገዳማት ይለያል። የዋልድባ መነኮሳት በልብሳቸው ብቻ ሳይሆን በአመጋገባቸውም ይለያሉ። ገዳማውያኑ የጣመና የላመ ምግብ ብቻ ሳይሆን ከሙዝ፣ ከተልባ፣ ከጨውና ከኑግ በስተቀር የእህል ዘር አይመገቡም። ከሙዝና ከኑግ የሚሠራውን መብል “ቋርፍ” ይሉታል። በዋልድባ ከሙዝና ከኑግ የተሰራ የቋርፍ ምግብ መብላት የተጀመረው ከ 1566 ዓ .ም . ጀምሮ ነው። ከዛ በፊት መናኒያኑ ይመገቡት የነበረው ጣብሌ፣ ገመሎና ሳዳ ከተባሉ ዕፅዋት ስር የሚዘጋጅ መራራና ጎምዛዛ ቋርፍ ነበር።
በነገራችን ላይ ሙዙን የሚመገቡት ገና ሳይበስል በጥሬው እያለ በመቁረጥና በመቀቀል ነው። ሙዙን ቀቅለውና በቋንጣ መልክ አዘጋጅተው ያስቀምጡታል። በዚህ መልክ በጥንቃቄ የተዘጋጀው የሙዝ ቋንጣ ሳይበላሽ እስከ ሰባት ዓመት ይቆያል።
በዋልድባ ቀደም ሲል ከተጠቀሱት አራት ትላልቅ ወንዞች በተጨማሪ ሙዝ የሚመረትባቸው 30 ወንዞችና ምንጮች ይገኛሉ። በእነዚህ ቦታዎች እንደ ልማት ቦታው ስፋት መነኮሳት ተመድበው የመስኖ ሥራና ንብ የማነብን ተግባር ያከናውናሉ። በዋልድባ በመስኖ ስራ የተሰናራ መነኩሴ “ወንዘኛ” ይባላል። በዋልድባ ማር የሚመረት ቢሆንም (ያውም ምርጥ ማር ) መነኮሳቱ አይጠቀሙበትም (አይመገቡትም ) ፤ ለገበያ ወጥቶም አይሸጥም። ይልቅስ የበሰለ ሙዝና ማር ገዳሙን ለመሳለም ለሚመጡ እንግዶች (ምእመናን ) ብቻ ነው የሚሰጥ። ያም ሆኖ ግን በዕድሜና በስራ ምክንያት ደክመው ለተኙ መናንያን ከድቁስ ጋር ተበጥብጦ የሚሰጥበት ጊዜ አለ። በሰሙ ግን ጧፍ በማዘጋጀት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም ይተርፋሉ።
በሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት የማይገኝና የዋልድባ ብቸኛ መለያ ከሆኑት አንዱ ‘ስምረት’ የሚባለው ስርዓት ነው። ስምረት ባጭሩ የሳሙኤል ልጅነት የሚገኝበት ስርዓት ማለት ነው። (አቡነ ሳሙኤል የመጀመሪያው የገዳሙ አበመኔትና ጻድቅ ናቸው። ) እንደ ምንኩስና ሁሉ ስምረት በከባድ ጸሎትና ስግደት የታጀበ የራሱ የሆነ ሥርዓት አለው። ይሁን እንጂ በዓመት ውስጥ ሥርዓተ ስምረት የሚፈፀምባቸው ቀናት የተወሰኑ ናቸው። እነዚህ ቀናትም ለወንድ ሀምሌ 5 ቀን ሲሆን ለሴቶች ደግሞ የካቲት 16 ቀን ናቸው። ይሁንና እንደ አጋጣሚ ሀምሌ 5 ቀን ረዕቡ ወይም አርብ ከዋለ የወንዶቹም በየካቲት ይከወናል።
ሴት መነኮሳይት ወደ ቤተ መቅደስ (ገዳሙ ውስጥ ) መግባት ስለማይችሉ ሥርዓቱ የሚፈጸምላቸው ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ (ማየ ዮርዳኖስ ሳይሻገሩ ) ካለው ቦታ ነው። ቡራኬ ለመቀበልም ሆነ ለማስቀደስ ሲፈልጉ ከቤተ መቅደሱ 300 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ቆመው ነው የሚያስቀድሱት። በተረፈ ወደ ገዳሙ ለመምጣት ለማይችሉ አንዳንዴም ለማይፈልጉ መነኮሳትና መነኮሳይት ማይለበጣ እና አባ ነፃ እየተባሉ ከሚጠሩ ስዕል ቤቶች ስርዓቱ ይፈፀምላቸዋል። ስዕል ቤት የሚባለው ታቦተ ህግ የሌለበት ማህበረ መነኮሳቱ በጋራም ሆነ በግል ፀሎት የሚያደርጉበት የተለየ ቤት ማለት ነው።
ሴት መነኮሳይት በዋልድባ መኖር የማይፈቀድላቸው ቢሆንም ከገዳሙ ክልል ውጪ ለሴቶች ተብለው የተዘጋጁ ቦታዎች አሉ። እነርሱም ጉብታ፣ ማይ፣ ሐርገፅ (የአዞ ወንዝ ) እና ቤት ሞሎ ይባላሉ። በዐጼ ባካፋ ዘመን የወልቃይትና የጠገዴ ባላባትና ገዢ የነበሩት ደጃዝማች አያና እግዚእ ያሰሩት ታሪካዊ ግንብ የሚገኘው ከሶስቱ የሴት መነኮሳይት መኖሪያ አንዱ በሆነው በሞሌ ነው።
ቀደም ሲል በገዳሙ የተለያዩ የዱር እንሰሳት እንደሚገኙ ገልጫለሁ። በዋልድባ ደግሞ በገዳማቱና ቤተ መቅደሶች ዙሪያ ከሚኖሩ መነኮሳት ይልቅ በግላቸው በየጫካው በፅሞና የሚኖሩ በቁጥር ይበልጣሉ። እንደዛም ሆኖ የዱር እንሰሳቱ (አውሬዎቹ ) ስምረት የገባ መነኩሴን ፈጽሞ አይተናኮሉም። መነኮሳቱም ቢሆኑ አደጋ ያደርሱብናል ብለው አይሰጉም። አንድ የከብት እረኛ በከብቶች መካከል ያለስጋት እንደሚያልፍ ሁሉ መነኮሳቱም በነጻነት በአንበሳና በነብር መንጋ መካከል ይዘዋወራሉ። የተኛ ዘንዶም ተሻግረው ይሄዳሉ።
አባቶች እንዳወጉኝ ከሆነ አልፎ አልፎ (ለፈተና ) አንበሳ መነኩሴውን የሚያልፉበትን መንገድ ጠብቆ ከመንገድ መካከል በመተኛት አላሳልፍም የሚልበት አጋጣሚ አለ። በዚህን ጊዜ መነኩሴው ሥርዓተ ስምረት በሚቀበሉበት ወቅት የተገለጸላቸውን ልዩ ቃል መጠቀም ይኖርባቸዋል። የዚህ ዓይነት ሁኔታ የገጠማቸው መነኩሴ “ግፍአ አበው” ሲሉ አንበሳው ጅራቱን እንደ ለማዳ ውሻ እየወዘወዘ ተነስቶ ይለቅለታል። ግፍአ አበው ወደ አማርኛ ሲመለስ “በአባቶች አምላክ” እንደ ማለት ነው።
በተረፈ በዋልድባ የስምረት ሥርዓት ያልተፈፀመለት መነኩሴ (ጳጳስም ቢሆን ) ማየ ዮርዳኖስ አይቀዳም። በገዳሙ አይቀድስም። አይቆርብም። ቢሞትም ከአበው መቃብር አይቀበርም።
እንግዲህ የዋልድባ ገጽታ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል። የአይነኬነቱ መሠረቶች፣ የአይደፈሬነቱ ምስክሮች እኒህ ናቸው። የአነጋጋሪነቱ ዓይነተኛ ምክንያትም ይህ ፍጹም የሆነው መንፈሳዊነቱና ታሪካዊነቱ ነው።
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Jun 19, 2012 11:08 pm Post subject:
ሰላም የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
ወያኔ ይህቺን ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ምን ያህል እየሠራ እንደሆነ በራሱ ልሣን በይፋ ግልጽ በማድረግ ላይ ይገኛል :: የ 'አንድ አድርገን ' ድረ -ገፅ ወያኔ 'አዲስ ራዕይ ' ብሎ በሠየመው ልሣኑ ያሠራጨውን አቋሙን በመተቸት አንድ ሠፋ ያለ ትንታኔ አቅርቧል :- እስኪ አንብቡት ::
ምንጭ :- አንድ አድርገን : ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ .ም .:: ኢህአዴግ “በአዲስ ራእይ” መጽሄት ምን እያለ ነው ?
Quote: . በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ የተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡”
. "ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት " ከሚል ቅዥት ባለፈ "አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” " የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ ::
. ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል : የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው ::
. ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡
. በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ .........
. እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው ::
PART 1
'አዲስ ራዕይ ' በየሁለት ወሩ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡
እንደ መረጃዎች ይች መጽሄት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ታጠነጥናለች አንዳንዴም ጸሀፊው እርሳቸው ናቸው የሚባልም ወሬ አለ፤ አቶ መለስም ጻፉት ሌሎች አባላት ታትሞ ከወጣ የድርጅታቸው አቋም ነው : አመለካከታቸው እሳቤያቸውንና ተግባራቸውን ከሞላ ጎደል የምታዩባት ክፍል ነች ፤ ይህች መጽሄት ተደራሽነቷ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ፤ መንግስት በሹመት ያስቀመጣቸው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ኃላፊዎች ፤ ከህዋስ ደረጃ ከፍ ያሉ አባላት ብቻ በመሆኑ እንዲህው በቀላሉ በማንም እጅ ላይ የመታየት እድሏ እጅጉን አናሳ ነው ፤ እዚች መጽሄት ላይ የሰፈረውን ሀሳብ መሰረት በማድረግ የኢህአዴግ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሚኒስትርነት ያስቀመጣቸው ሰዎች በድርጅታዊ ጉባኤ እንደሚነጋገሩበትና ይዘቷን የሚፈትሹበት ፤ ጽሁፉን ላነበቡትም ሆነ ላላነበቡትም አባላት የመንግስትን አቋም የሚያውቁበት መድረክ በየጊዜው እንዳላቸው ውስጥ አዋቂዎች ተንፍሰውልናል፡፡ አዲስ ራእይ በ 2ኛ ዓመት ቅጽ 3 ግንቦት -ሰኔ 2004 ዓ .ም ለመዳሰስ የተፈለገው ዋናው ጉዳይ በፖለቲካ አምዷ በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ የእግር እሳት የሆነባትን የሀይማኖት ጉዳይ ነው ፤
ኢህአዴግ በዚች 70 ገጽ በማትሞላ መጽሄት በአሁኑ ሰዓት ያለውን የሀይማኖት ችግር መሰረት በማድረግ 41 ገጹን በሚሸፍን መልኩ መተንፈስ ችሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ከሰጡት የሰዓታት ትንታኔ ጠለቅ ባለ መልኩ ነገሮችን በስፋትና በጥልቀት በደፈረሰ አይኑ ተመልክቶ ሀሳቡን ማስቀመጥ ችሏል ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን “አንዳንድ አማኞች” በማለት በግልጽ ያለውን እና የያዘውን አቋም ሲያንጸባርቅ አስተውለናል ፤
አክራሪነትን ከህገ መንግስቱ አንጻር የተመለከተ መስሎት የማይመለከተንን እኛንም በደንብ አድርጎ ወርፎናል ፤ በየቢሮው የሚለጠፉ የቅዱሳን ስዕላትንና የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስን እንዲህ በማለት ገልጾታል “የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎች : ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ…” በማለት አስቀምጦታል ፡፡ይህ ሁኔታ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢታይም የሰውን የእምነት ነጻነት ከማክበር አኳያ ይህን የመሰለ የማንቋሸሽና የማጥላላት ጽሁፍ መንግስትን ወክሎ ወጥቶ መመልከት መቻል እንደ አንድ ዜጋ ያሳፍራል፡፡ እዚህ ላይ የማህበረ ቅዱሳንን ስም በማይገባው ቦታ ከውሀቢያ እና ከአመለካከቱ ጎን አስቀምጦት ማየት ችለናል ፤ ለምሳሌ በገጽ 33 ላይ [color="red"]“በአንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነኝ ባዮች ከማህበረ ቅዱሳንም የተለየ ሚና ያለው ኮር ሃይል የሚያስተጋባው "አንድ ሀገር አንድ እምነት " የሚለው ቅዥት ጸረ -ህገ መንግስታዊ ነው ፡፡ ወሀብያ ይሁን የሌላ እምነት ተከታይ ጸረ ህገ መንግስት አቋሞቹንና ተግባሮችን አውግዞ እንደማኛውም ዜጋ ወይም ቡድን የራሱ መብት እንዲከበርለት የሚፈልገው ሁሉ የሌላውንም መብት አክብሮ እስካልተንቀሳቀሰ ድረስ ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጋጭትና የእምነቱን አስተምህሮ የሆኑት ጉዳዮች ላይ መንግስት የመምረጥም የመተቸትም ፍላጎት የለውም ፤ ይህንም አድርጎት አያውቅም” [/color] በማለት ያትታል ፤ አሁን እንደ ነጥብ የማህበሩን ስምና የጽሁፉ ይዘት አብሮ የሚሄዱ ሆነው አያገኟቸውም ፤ “ሊበሏት ያሰቧትን … ..” የሚባል ተረት ትዝ ያሰኞታል ፤ እኛ በርካታ የጥምቀት በዓላት ላይ ስንመለከት “አንድ ሀገር አንድ እምነት” የሚል ተጽፎ ለመመልከት አልቻልንም ፤ እነሱ ካዩ ከተመለከቱና መረጃው ካላቸው ቢያሳዩን መልካም ነው ፤ መጽሀፉ ደግሞ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ነው የሚለው “አንዲት ሀገር” የሚል የለበትም ፤ ይህ ጥቅስ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ ቢመስላቸውም እኛ ምን ማድረግ እንችላለን ? ከህገመንግስታችሁ ጋር እናጣጥምላችሁ ? ምን እንበለው ? ምንስ ብለን ቲሸርታችን ላይ ጽፈን እንልበሰው ? እኛ ቃሉ የመፈጸም እንጂ የማስተካከል የመለወጥ መብቱ የለንም ፤ ቃሉ ደግሞ እንደማይለወጥ በግልጽ መጽሀፉ ይነግረናል ፤ እኛ የተጻፈልንን ማመን ብቻ ነው ፤ ደግመን እንበለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ስለ ሀገሩ ተውትና “አንድ ሃይማኖት” የተባለችው ቀጥተኛዋ በደም የቆየችልን አሁን እኛ ያለንባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት ብለን እናምናለን ፡፡
በሌላ በኩል በገጽ 37 ላይ ይህን ሰፍሮ ያገኙታል “በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ እና በመሰረቱ ጸረ -ህገመንግስት መገለጫ ያላቸው አቋሞች የተላበሱበትና አንዳንድ የእኛ አባላትና አመራሮችም ኢህአዴግነትንም ጸረ ኢህአዴጋዊ አቋሞችን የያዙ ይዘቶችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሀድ የሚታይ ነው፡፡ አባላችን ወደ ሃይማኖት ሲሄድ ኢህአዴግነቱን ትቶ ፤ ወደ ኢህአዴግ ሲመጣ ደግሞ ሀይማኖቱን ትቶ ሊሆን አይችልም ፡፡ ጠንካራ አማኝም ጠንካራ ኢህአዴግም በመሆን መካከል ግጭት የለም ፡፡ ግጭት የሚፈጠረው ድንበሮችን ስናደበላልቅ ነው ፡፡ ስለዚህም በዚሁ አግባብ ግልጽነት ተፈጥሮ አባላችንን አመራራችን ሰልፉን ያስተካክል ፤ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ በሰበባ ሰበብ ሳይሸፋፈን ከድርጅቱ መጽዳት አለበት በማለት ያስቀምጣል” ይህን ያህል አትኩሮት ሰጥቶት ማስቀመጥ ከቻለ መንግስት ጊዜው ራስ ምታት እንደሆነበት ያሳያል ፤ በብሎጋችን ላይ ከወራት በፊት የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ በተመለከተ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ አንዱ ፍርድ ቤቶች ውስጥ 13 የሚደርሱ ሙስሊም ጠበቃዎች እና ዳኛዎች በእለተ ቅዳሜ በአሳቻ ሰዓት ተሰብስበው መገኝታቸውን ጽፈን ነበር ፤ ይህን ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ “በሀይማኖት ላይ የለዘበ አቋም እንዳታሳዩ ፤ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጋችሁ ብቻ ስራችሁን ስሩ” በማለት ቀጭን ትዕዛዝ ማስላለፉን ገልጸን ነበር ፤ አሁንም መናገር የፈለገውን ነገር ግልጽ ባለ መልኩ መናገር ባይችልም ኢህአዴግ አቋሙን ግን ሲያስቀምጥ ይመለከታሉ፡፡ ይህን የሚያገኙት ለአመራራቹ “ቀጣይ የትግል ግባችን ምን ይሁን” በሚለው ውስጥ ነው፡፡
በገጽ 17 ላይ አክራሪነት እና የመንግስት አመለካከት እንዲህ በሚል ሲያስቀምጥ እናያለን “ ..የሀይማኖት አክራሪነት የሚለው አገላለፅ የተለያዩ ሰዎች ከተለያዩ መመዘኛ በመነሳት ይተረጉሙታል ፡፡ የሃይማኖት መሪዎች አክራሪነትን ከሚመሩት ሃይማኖት መጻህፍት በመነሳት የቅዱሳን መጻህፍቱን መሰረታዊ መርህዎች የሚጻረር እንደሆነ በዝርዝር ያስረዳሉ ፤ ከዚህ በመነሳት ያወግዙታል ፡፡ የሀይማኖቱ እምነት ምን እንደሆነ ከሀይማኖት መሪዎቹ በላይ የሚያውቅ የለምና እነዚህ መሪዎች ከሚያውቁት ነገር ተነስተው አክራነትን ቢተነትኑትና ቢያወግዙት መብታቸው ነው ፡፡ ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅታችንና መንግስታችን ግን በሃይማኖት ሊቃውንት የተገነቡ ስላልደሉ አንድን ወይም ሌላ ሃይማኖትን ለማራመድ ሳይሆን ሁሉንም ዜጎች ለልማትና ዴሞክራሲ ዙሪያ ለማንቀሳቀስ የተደራጁ በመሆናቸው አክራሪነትን የሚመለከቱት ለልማትና ዴሞክራሲ አጀንዳ ካለው ተጽህኖ በመነሳት ብቻ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ ሲታይ የሃይማት አክራሪነት ጸረ ልማትና ጸረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሆኖ ይገኛል ፡፡
የዴሞክራሲ ስርአታችን ሁሉም ዜጎች የእምነት ነጻነት እንዳለው ያስቀምጣል ዜጎች የራሳቸውን እምነት ነጻነት ማስከበር ይችሉ ዘንድ የሌላውን የእምነት ነጻነት ማክበር እንዳለባቸው ያስቀምጣሉ ፡፡ አክራሪነት የምንለው ይህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ መርህ በሃይማኖት ሽፋን መቃወም ነው፡፡ ይህን የአክራሪነት አመለካከት ለሁሉም ሃይማኖቶች ሊታይ የሚችልና አልፎ አልፎም በተግባር የሚከሰት ነው፡፡ በዚሁ መሰረት አንዳንድ ሙስሊሞች ሌላውን ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሙስሊሞች እንኳን ሳይቀሩ ሀቀኛ ሙስሊሞች አይደሉም ብለው በመፈረጅ የእምነት ተቋሞቻቸውን ለማፍረስ ፤ የሃይማኖት አባቶችን መቃብሮች ቆፍረው ለማውደም ይከጅላቸዋል፡፡ በተግባር ሲፈጽሙት ታይተዋል ፡፡ የራሳቸውን የእምነት ነጻነት ለማስከበር የሚሞክሩት የሌላን ነጻነት በማክበር ሳይሆን የሌላውን ነጻነት በመድፈቅና በማፈን ነው፡፡ በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡” በማለት ያስቀምጣል ፤ ከላይ እንደመነሻ የተንደረደረበት ሀሳብ አክራሪነት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ አክራሪ ሙስሊሞችን ስራዎቻቸውን ያስቀምጣል ፤ በስተመጨረሻ “አንዳንድ ኦርቶዶክሶች” በማለት በእኛ ላይ አክራሪነትን ቋጭቶ ይደመድማል ፤
እኛ ተሀድሶያውያንን ተከታትለን ከቤተክርስትያኒቱ አስተምህሮ ውጪ የሆነውን ምንፍቅናቸውን ለህዝብ ስላሳየን አክራሪ ተብለናል ፤ በመሰረቱ ቤተመንግስትን በወታደር መጠበቅ ይቻላል እምነትን ግን እንደ እነርሱ በወታደር መጠበቅ አይቻልም ፤ አባቶቻችን ይችን እምነት ከመናፍቃን ጠብቀው ያቆዩልን ክፉ ትምህርታቸውን በማውጣት መክረው አልመለሱ ሲሉ በጉባኤ በማውገዝ መሆኑን እኛ እንጂ እነርሱ ሊያውቁልን አይችሉም ፤ ተሀድሶያውያንን የእምነት ነጻነታቸውን አልተጋፋንም ፤ የፈለጉትን እምነተ ማመን መብታቸው ነው ነገር ግን “ቤተክርስትያናችን የእነሱ አመለካከት ማራመጃ መድረክ አትሆንም” በማለታችን “አንዳንድ ኦርቶዶክሶች” ተብለን ስም ተሰጠን ፤ አሁን ብቻ አይደለም ወደፊትም እነዚህን መሰል የቤተክርስትያን የእግር ውስጥ እሳቶችን ስራቸውን ከመቃወም ፤ መግባርና ተግባራቸውን ከማጋለጥ ወደ ኋላ አንልም ፤ ጽሁፉ ጉደኛ ነው ብዙ ነገር አለበት እንቀጥል፡፡
“የዲሞክራሲ ስርአታችን መንግስትንና ሃይማኖት መለያየት እንዳለባቸውና አንዱ በሌላው ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት እንደማይገባው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ብሎ ነገር በፍጹም የማይታሰብ ነገር መሆኑን ያረጋግጣል ፡፡ የሃማኖት አክራሪነት የምንለው ይህንኑ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መርህ በሀይማኖት ሽፋን መናድ ነው ፤ ይህው አመለካከት በተለያየ መልኮች ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰፊ ቁጥር ባይኖራቸውም ጥቂት ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች እንደ ድሮ ሁሉ ኦርቶዶክስ ክርስትና የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ፡፡ ከሌሎች የተለየ መብትና ጥቅም እንዲኖረው ይመኛሉ፡፡ ይህ አመለካከት ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው የከሰመ ቢሆንም አክራሪነት የሚገለጽበት አንዱ ገጽታ መሆኑ አልቀረም ፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ሙስሊሞች የሀይማኖት ብዙሀነት ባለበት ሀገር እስልምና ነው ብለው ያመኑበት መመሪያ በመንግስትና በመንግስት ተቋች አማካኝነት እንዲፈጸሙ እስልምና መንግስት ሃይማት እንዲሆን ሲከጅሉ ይታያሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁለቱም እዚህው ሀገር የተፈጠሩ ይመስል የኦርቶዶክስም ሆነ የእስልምና አንዳንድ ተከታዮች ዘንድ የሚስተዋለው የተዛነፈ አስተሳሰብ ሁለቱም ነባር እንደሆኑና ሌላው መጤ በመሆኑ የሁለቱን ያህል ስፍራ እንደማይገባቸው አድርጎ የማሰብ ነው፡፡ ሌሎችም ሀይማኖቶች ደረጃው ቢለያይም ተመሳሳይ አክራሪነት ዝንባሌ የተጠናወታቸው አባላት አሏቸው፡፡ እነዚህ የተዛነፉ አስተሳሰቦች በአደባባይ የሚነገሩ ጭምር ናቸው ፡፡ እዚህ ላይ መዋቅራችንም ለችግሩ የራሱን ድርሻ መውሰድ አለበት ፡፡ የሁሉም ዜጎች የጋራ ንብረት የሆኑ አደባባዮችና መንገዶች በየበአሉ ከኃይማት ጋር በቀጥታ ባልተያያዙ ጸያፍ መፈክሮች ሲጥለቀለቁ መዋቅራችን ጭምር አይቶ እንዳላየ የሚያልፍበት ሁኔታም ይታያል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎችና ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡፡ በአንድም በሌላ መንገድ ይህንኑ አደገኛ መንገድ መከተል መደገፍ ነውና፡፡” በማለት ያስቀምጣል፡፡
ይህ ጽሁፍ በጣም ገራሚ ከመሆኑ የተነሳ ሰዳቢዎቹ ሲሳደቡ ጠያቄ እንደማይመጣ እርግጠኛ ሆነው ነው ፤ እውን ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት አይደለችምን ? በቁጥር የምናውቃቸው በቁጥር የማናውቃቸው ከ 20ሺህ በላይ አብያተክርስትያኖቻችን ቋሚ ምስክሮቻችን ናቸው ፤ ይህ ለናንተ ቅዥት ነው የማይፈታላችሁ ነገር ነው ፤ እንደ “ማኔ ቴቄል ፋሬስ” ፈቺ የሚያስፈልጋችሁ ይመስለናል ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት መሆኗ እኛ ዝም ብንል ምድሪቷ አፍ አውጥታ ትናገራለች ፤ትላንትና በእርዳታ ስም የመጡትን እምነቶች የተከፈቱትን አዳራሾች አትመልከቱ ፤ ይች ሀገር እንደ ሀገር እዚህ የደረሰችው በዚችው ቤተክርስትያን አስተዋጽኦ ነው ፤ የመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ 10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም ፤ ሌላው ደግሞ “ነባር አይደላችሁም” መባላችን አስገርሞናል ፤ ታሪክ ይናገራል ሙስሊም ወንድሞቻችን ወደዚች ሀገር የመጡት ከ 5ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ መሆኑን ተጽፎ የተቀመጠ እነርሱም የማይክዱት ሀቅ ነው ፤ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ 34 ዓ .ም ክርስትናን የተቀበለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆኑን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሮ እናገኝዋለን ፤ ታዲያ ማነው የነበረው ? ማንስ ነው በሂደት የመጣው ? ፤ ማንስ ነው መጤ ? እናንተም እኮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለአዲስ አበባ መጤዎች ናችሁ ዘነጋችሁት እንዴ ? ፤ ስለዚህ የኦሪት መስእዋት ስታቀርብ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስጠጊ እንጂ ተጠጊ አለመሆኗ እወቁ ፤ በሌላ በኩል ኦርቶዶክሳውን ሆንን የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስ በቲሸርቶቻችን ላይ አድርገን ስንሄድ ሀፍረት እንዴት እንደማይሰማን ጸሀፊው ሀሳቡን ያስቀምጣል ፤ “ነገሩ እንዴት ነው” አለች አይጥ የድመት ጓደኝነት ያላማራት ፤ ሌሎች በእምነታቸው ሊያፍሩ ይችሉ ይሆናል ፤ ሳያውቁ ገብተውበት መውጫው ጉድጓድ ጠቦባቸው ያሉበት እምነት ያሳፍራቸው ይሆናል ፤ እኛ ግን አንዳች የምናፍርበት የምንሳቀቅበት አንገት የምንደፋበት ነገር የለንም ፤ ለምንስ እናፍራለን ፤ በጣም ደስ ብሎን እንደምናደርገው በዚህ አጋጣሚ እወቁልን ፤ ለኛ ስብከት ነው ፤ ካስተዋላችሁ 4ኪሎ አካባቢ አንድ አይምሮው ትንሽ የሚያመው ወንድም ከፊት ለፊቱ ላይ የእመቤታችንን ነገር ለመንገር “ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል” የሚል ጽሁፍ ሲለጥፍ በጀርባው ደግሞ አሁን የማላስታሰውን አንድ በጣም ደስ የሚል ጥቅስ በጀርባው ላይ ለጥፎ ሲዞር ተመልክቻለሁ ፤ አደራችሁን አሸባሪ እንዳትሉት ፤ እሱ ኑሮ ያሸበረው ይበቃዋል…… .
“…እዚህ አገር የተፈጠሩ ይመስል ..” ማለትስ ምን ማለት ነው ?፤ ዛሬ ጠያቂ ባይኖራችሁ ነገ ግን ይኖራችኋል ፤ ቀን የራሱን ነገር ይዞ ይመጣል ፤ ጊዜ በራሱ መፍትሄ የሚሆንበትም ወቅት ሩቅ ላይሆን ይችላል ፡፡ በምድር የማይሻር ስልጣን የማይነቀል መንግስት የለም፡፡
በተለያዩ የመንግስት ፤ የግል እና መንግስታዊ ያልሆነ ቢሮዎች የሚሰሩ ሰዎች የመስሪያቤታቸው ደንብና መመሪያ ባይፈቅድም የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስና ቅዱሳን ስእላትን በግድግዳ ላይ ለጥፈው ይታያሉ ፤ ነገር ግን ይህ ነገር አግባብ አለመሆኑን በመንገር የሚያወርዱበትን መንገድ ከማመላከት ውጪ “በምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ” በማለት ድርጅታዊ አቋምን በሚያንጸባርቅ መጽሄት ላይ ሰፍሮ መመልከት ያሳዝናል ያሳፍራልም፡፡ እንቀጥል ..
ይህ ጽሁፍ ጽንፈኞችን በአንድ አንቀጽ አንዲህ ብሎ ይገልጻቸዋል “ሁል ጊዜም ጽንፈኞች ማንኛውም ሰው በሚከተለው እምነት የግል መብት የለውም ብለው ያምናሉ ፡፡ ውይይትና መግባባት ፤ ሰላማዊ ውይይትን በማውገዝ በአመጽ ተደግፈው የራሳቸውን አተያይ ይጭናሉ ፡፡ ከፍቅር ጥላቻን ፤ ከርህራሄ ጭካኔን ፤ ከመቻቻል መናቆርን ፤ ከእውቀት ድንቁርናን ፤ ከውይይት ጉልበትን ይመርጣሉ ፤ ያበረታታሉ ፡፡ ጽንፈኞች የመንግስትና የሃይማኖት መለያየትን አይቀበሉም ፤ ይልቅ እነሱ እምነት የተለየ የበላይነት እንዲኖረውና መንግስታዊ ድጋፍ ጡንቻ እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ይህ አመለካከት በተለያዩ የእስልምና እና ክርስትና ሃይማኖቶች ውስጥ በመሸጉ የተወሰኑ ቡድኖች የሚስተዋልና በተለያየ መልክና ደረጃ የሚንጸባረቅ ነው፡፡” በማለት ይገልጻቸዋል ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ነገር ግን አክራሪ ኦርቶዶክስ ግን ሊኖር አይችልም ፤ ሁለታችንንም በአንድ ሚዛን አስቀምጦ በአንድ መነጽር እየተመለከቱ መጻፍ አግባብ አይደለም ፤ ባይሆን ባሳለፍናቸው ጥቂት አመታት በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በጅማ እና እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አክራሪ በሆኑ ሰዎች መከራን ተቀብለዋል በመቀበልም ላይ ይገኛሉ ፤ በተለይ በጅማ የበርካቶች ደም ሲፈስ መመልከት ችለናል ፤ ነገር ግን መንግስት ይህ ነው የሚባል ርምጃ ሲወስድ መመልከት አልቻልንም ፤ የተጎዳነው በደልና ግፍ የደረሰብን እኛው ሆነን ሳለን ከአድራሽ ሃይሎች ጋር ደምሮ ሂሳብ ማወራረድ ተገቢ አይደለም ፤ የዛሬ ዓመት አካባቢ በጅማ አውራጃዎች ከ 35 በላይ የሌሎች የእምነት ተቋማት አዳራሾቻቸው በእሳት ሲጋዩ ፤ ሰውም ሲፈናቀል በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ጆሯችን ሰምቷል ፤ ከጋዜጦች ላይም አይኖቻችን አንብበዋል ፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህን አደረሱ የተባሉት ሰዎች ማንነታቸውን ስናውቅ የመንግስት እርምጃ አለመጣጠሙ ነበር ፤ እነዚህ ሰዎች በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙ ፤ የአካባቢው ባለሀብቶች ፤ የመስጂድ ኢማሞች ፤ የውጭ ገንዘብ ፈሰስ የሚደረግላቸው ቡድኖች እና የኢህአዴግ አባላት ሆነው መገኝታቸው አስደምሞናል ፤ እስኪ የደረሰውን የሞት ፤ የአካል ፤ የንብረት ፤ የሳይኮሎጂ ጉዳት አስቦ የተወሰደውን እርምጃ ተገቢ ነው የሚል ሰው ማነው ? ፤ እኛስ እውነትን እንናገራለን ጥሩውን እናበረታታለን የማይጠቅሙ አካሄዶችን እንነቅፋለን ፤ እነዚህን የመሰሉ የወረደ አመለካከት ያላቸውን ለራስ : ለቤተሰብ : ለእምነት ፤ ለድርጅታችሁ ኢህአዴግ እና ለሀገር የማይጠቅሙትን ማጥራት ከውስጡም የማጽዳት ስራ መስራት ሲገባው ፤ እጁን ወደ ሌሎች ላይ መጠቆሙ የሚያዋጣ አካሄድ አይመስለንም ፡፡
ጽሁፉ ይቀጥላል…
“ በሀገራችን ዜጎች በሚከተሉት እምነት ምክንያት በሚገፉባቸው ተገደው የሌላውን ሃይማት ካልተከተሉ ከቀያቸው የሚፈናቀሉበት ፤በሚከተሉት እምነት ምክንያት በተወሰኑ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ሀገራቸውን የማገልገል ፤ ከተቀጠሩም ከመሰላሉ ስር ፈቀቅ እዳይሉ ይደረግባቸው የነበሩት በነዚያ ህገ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ጥበቃ በነበራቸው ግፎች በነገሱባቸው የጨለማ ዘመናት እንኳን ጠንክሮ የዘለቀው የሃይማኖት መቻቻል ፤ ይህ ህዝቦች አብሮ የመኖር እና መደጋገፍ ትስስር ለመበጣጠስ በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽንፈኛ አክራሪ ኃይሎች የተፈጸሙ የጥፋት ድግሶች ማስተዋል ጥሩ ነው፡፡ ጥፋቶቹ ማተራመስ የጀመሩት በቅድሚያ የወጡባቸውን የሃይማኖት ተከታዮች ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የተቃጠሉ እና የፈረሱ መስጅዶች ፤ የታዋቂ የእስልምና የመቃብር ስፍራዎች በሙሉ ጥፋት የተፈጸመባቸው እስልምናን እንከተላለን በሚሉ ጥቂት ጽንፈኞች ነበር፡፡ የሙስሊሙን ተቋማት ከማፈራረስ ሳይቦዝኑ ቤተክርስትያናት አውድመዋል፤ በክርስትና በኩል ሌላውን የሚያንቋሽሹ ፤ የተለያዩ የክርስትና ተከታዮችን ጨምሮ መናፍቃን ፤ ኢ -አማንያን በማለት የሚተነኮሱ ኃይሎች አሉ፡፡ ከሁሉም ሃይማኖቶች አንጻር ያሉት እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው፡፡ በእርግጥ ከበርካቶች በስተጀርባ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስፖንሰሮች ያሉአቸው የፖለቲካ አጀንዳ የተላበሱ ጽንፈኞች ናቸው ፡፡ ብዙሀኑ ግን ለእምነታቸው ዘብ የቆሙ እየመሰላቸው በቀላሉ ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ … . ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው ፡፡ መንግስት ሊመርጥላቸው አይችልም፡፡” በማለት ይቀጥላል ፤ የበፊቱን የመንግስት አገዛዝ ማስቀመጣቸው ተገቢ ነው ፤ ቤተክርስትያችንም ከመሀመድ ግራኝና ከዮዲት ጉዲት በኋላ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ወቅት ነው ፤ በጊዜው ከአሁኑ የተሻለ የሀይማኖት መቻቻል እንደነበረ ጊዜውን ያሳለፉ ሰዎች ምስክሮች ናቸው ፤ ነገር ግን ያሳለፍነው ጊዜ ምንኛ ጨለማ ቢሆንም ይህን ወቅት ብርሀን ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ ግን የለም ፤ ሚዛኑ የመድሀኒአለም ነውና እኛ ዝም እንላለን ፤
በተጨማሪ በጥቅምት 11 ላይ ተሀድሶያውያንን በመቃወም ፤ "ቤተክርስትያን አትታደስም " በማለት ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደ ንብ በመትመም የተቃወሙትን ወጣቶች ሁኔታ ሌሎች የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሰዎች ያነሳሷቸው ናቸው " ብሎ ጽሁፉ ያትታል ፤ ይህ ስለ ቤተክርስትያናቸው ብለው ያደረጉት እንጂ የፖለቲካ ጥማት ያለባቸው ሰዎች ገፋፍተው ያስወጧው አይደሉም ፤ በጊዜውም ተቃውሟቸውን የገለጹት ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መንገድ መዝሙር በመዘመር እና እነዚህ ሰዎች ላይ አለን የሚሉትን የቤተክርስትያኒቷ አስተምህሮ ያልሆኑትን መረጃዎች ለብጹአን አባቶቻችን በማቅረብ እንጂ ከውጭ ሀገር የገንዘብ እርዳታ ተደርጎላቸው የፖለቲካ ማራመጃ ሆነው አይደለም ፤ ተቃውሞው የተደረገው በቤተክርስትያን ግቢ እንጂ በቤተመንግስት አለመሆኑን እናተም የምታውቁት ይመስለናል ፤ በጊዜው የነበሩት የሰንበት ተማሪዎች ለእምነታቸው ዘብ ቆመዋል ፤ የአባቶቻቸው እምነት እንዳይሸረሸር ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ፤ ፍጹም አልተሳሳቱም ፤ ለእምነት መቆርቆርን ያሳዩንና ያስተማሩን አይከኖቻችን ናቸው ፤ በሌላ በኩል “መናፍቃን” የሚለውን ስም ባለቤቶቹ ሳይከብዳቸው መንግስት የገደል ማሚቱ ሆኖ ያስተጋባላቸዋል ፤ የእናንተ አባል ያልሆነን "አሸባሪ " በማለት ታፔላ ስትለጥፉ ምንም ያልመሰላችሁ እኛ ግን ውስጣችንን እንደ ነቀዝ ቦርቡረው ሊጨርሱን ጥቂት የቀራቸውን ሰዎች የሚመለከተው አካል ስራቸውን መዝኖ ሲያወግዛቸው እኛም "መናፍቃ ነበሩ " ስንል "ለምን ?" ትሉናላችሁ ፤ "ህገ መንግስቱን ይጋፋል " ትላላችሁ ፤ ይህ ህገ መንግስት እኮ ለሁሉም ነው የሚሰራው ፤ መፎከሪያ ማስፈራሪያም ሆኖ መቀመጥ የለበትም፤ ለማንኛውም በመጽሀፉ ላይ ከሰፈሩት 41 ገጾች ውስጥ 30 ያህሉ ሙስሊሞችን የሚመለከት ሲሆን 10 ደግሞ ቀስቱ ወደኛ ሆኖ አግኝተነዋል ፤ ዋና ሀሳብ ያልናቸውን በጣም በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረናል ፤ መጽሀፉን የምታገኙ ሰዎች አንብቡትና የራሳችሁን ፍርድ ስጡ ፤ በቅርብ ለማታገኙት በሀገር እና ከሀገር ውጪ ላላችሁት ደግሞ መለስ ብለው ብሎጋችንን ይጎብኙ እንደወረደ በፒዲፌ አዘጋጅተን ብሎጋችን ላይ እናስቀምጥሎታለን …… .
አንብባችሁ ሀሳባችሁን ላኩልን… ..
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤ 5

Posted: Fri Jun 29, 2012 10:47 pm Post subject:
የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
"ያዳቆነ ሠይጣን ሣያቀስስ አይለቅም :" ይባላል :- ወያኔዎችን የያዛቸው ክፉ የመንፈስ ደዌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሣያጠፉ እንዳያርፉ አድርጓቸዋል :: እነእርሱ ምን ያድርጉ ያሠለፋቸው እኮ የአውሬው ኃይል ነው :: ነገር ግን ክርስቶስ በደሙ የመሠረታትንና የዋጃትን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት የሚያስችላቸው ምንም ዓይነት ኃይል የለም :: ሠሞኑን ወያኔዎች በዋልድባ ገዳም ይዞታ አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎችና ከገዳሙ መነኮሣት ጋር እሠጥ -አገባ ላይ ናቸው :: ዝርዝሩን ከ 'ዋልድባን እንታደግ ' ድረ -ገፅ ታገኙታላችሁ ::
ምንጭ :- ዋልድባን እንታደግ (Save Waldiba): ሐሙስ ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ .ም .:: የቅዳሜው በዓዲርቃይ የተካሄደው ስብሰባ ዘገባ ::
Quote: . "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም " ከመነኩሳት ወገን ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
. "ልማቱን በግድም በውድም መቀበል ይኖርባችኋል " የመንግሥት ተወካይ
. "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግም " የአካባቢው ነዋሪ
. በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡
ከአበረንታት . ማርገፅ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
. ድል ሰቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
. እጣኑ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን
. ሙሉ ቤት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከአባ ነፃ . ዲዋር ግዛ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
. ማይ ሸረፋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
. አዲ ፈረጅ አብዮ እግዚ ቤተክርስቲያን
. ማይ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
. ታች እጣኖ ቅዱስተ ማርያም ቤተክርስቲያን
. ላይ ኩርማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
. ጎድጓድ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
. ቃሊማ አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን
. ቃሊማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
. ቃሊማ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
. ማይ ዓርቃይ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም ስማቸው ያልተገለጸ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱ ዘገባው ደርሶናል። ለዚህም ነው የገዳሙ መነኩሳት ይልቁንም በሰቋር ኪዳነ ምሕረት የሚገኙት መነኩሳይት (አነስት ) ታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ የሚገኙት፡፡ እንደ መነኩሳይቱ አነጋገር በመጀመሪያ እኛን ገድላችሁ መሬቱን ማረስ ትችላላችሁ አለበለዚያ ግን እኛ በሕይወት ቆመን ቅዱሳን አባቶቻችን በደማቸው እና በአጥንታቸው ያስከበሩት ገዳም በኛ በልጆቻቸው በአረማውያን ሊወሰድ አይችልም በማለት በታላቅ ተጋድሎ ላይ ይገኛሉ። ". . .የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ . . ." መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ ፳ ፥ ፫ የናቡቴ ቃል ዛሬም በእነዚህ መነኩሳይት አድሮ ለእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ያስተጋባል የአባቶቻችን ርስት እንሰጥ ዘንድ ከእኛ ያርቅ በማለት።
እንደመረጃ ምንጫችን ከሆነ በስብሰባው ዕለት የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቦታው ተገኝተው ቡራኬ ለማድረግ ሲነሱ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል "እርሶ እኛን አይወክሉንም " በማለት ተሰብሰባዊ ገዳማውያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ በከፍተኛ ደረጃ በቦታቸው ያልተገኙትን አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ ኮንነዋቸዋል፣ በተያያዘ ዜና በስብሰባው እለት የቤተክህነቱም ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ገዳማውያኑን እና የአካባቢውን ነዋሪ ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበር እና በመጨረሻ የመንግሥት ተወካዮች ቦታው እንደውም "የአማራ ክልል አይደለም " ይህንን በቀጥታ የሚመለከተው "የክልል ትግራይ " ነዋሪ ነው በማለት የስብሰባውን መንፈስ ወደ ዘር እና ጎሳ ሲለውጡት ተመልክተዋል። እነዚሁ የመንግሥት ተወካዮችም በግድም ይሁን በውድ ልማቱን መቀበል አለባችሁ የሃገራችን የሥራ አጥ ቁጥሩን በ 50000 ይቀንሳል በማለት ዲስኩራቸውን መስማት ለሰለቸው ተሰብሳቢ ሲያሰሙ ውለዋል።
በመጨረሻ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተሰብሳቢው የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በኃላ ስብሰባ አትጥሩን አቋማችን የታወቀ እና አንድ ነው የአባቶቻችንን ርስት አትንኩብን፣ አጽመ ቅዱሳኑን አታፍልሱ፣ ካልጠፋ መሬት ለምን ወደገዳማን መጣችሁብን፣ እኛ ጉልበታችን መድኅኒዓለም ነው ያሻችሁን ማድረግ ትችላላችሁ መሬቱንም ስታርሱ እኛንም ገድላችሁ መሆን አለበት በማለት ከፍተኛ የሆነ ሁካታ ተነስቶ በስብሰባው ከተሳተፉትም አንሰበሰብም በማለት በውጭ ቁጭ ብለው ከነበሩ በተለይ ወጣቶችን የመንግሥት ታጣቂዎች በርካታዎችን ጭነው ለእስር ዳርገዋቸዋል በርካቶችም ሸሸተው ወደ ጫካ እንደገቡ ከአካባቢው ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ማኅበረ መነኩሳቱም ምሬት በተሞላበት መልኩ ነዋሪዎችን "መጥታችሁ ቅርሶቻችሁን ተረከቡን " ሲሉ መሰማታቸውንም እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጸውናል።
መንግሥትም በማናለብኝነት አብያተ ክርስቲያኑን እንደሚያፈርስ ሲገልጽ፣ የቤተክህነቱም ተወካዮች ተባባሪ ሆነው ለአብያተ ክርስቲያኑ መፍረስ አይነተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ በሌላ በኩል የዋልድባ ገዳም ማኅበረ መነኩሳቱ፣ የአካባዊ ነዋሪ በተለይ ደባቅ፣ ዛሬማ፣ ዓዲርቃይ፣ እና አካባቢው ላይ ያሉ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ከመንግሥት ሃህሎች ጋር ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት እየከፈሉ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት እኛ እንደክርስቲያን አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል። በማንኛውም በጸሎትም በማቴሪያልም በገንዘብም በማንኛውም መንገድ ልንተባበራቸው እና ቅዱሱን ገዳማችንን የሊቃውንት መፍለቂያ እንዲሁም የበረካታ ዓይናማ መምህራንና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መገኛ የሆነውን ገዳም ልንታደግ ይገባል እንላለን።
የአባቶቻችን አምላክ ድል የማትነሳዋ የተዋሕዶ እምነታችው በእኝም በልጆቻቸው ይደርብን አሜን።
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ፍርዳወቅ Joined: 25 Jun 2012 Posts: 10
Posted: Sat Jun 30, 2012 9:38 am Post subject:
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
ወያኔ ይህቺን ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ምን ያህል እየሠራ እንደሆነ በራሱ ልሣን በይፋ ግልጽ በማድረግ ላይ ይገኛል :: የ 'አንድ አድርገን ' ድረ -ገፅ ወያኔ 'አዲስ ራዕይ ' ብሎ በሠየመው ልሣኑ ያሠራጨውን አቋሙን በመተቸት አንድ ሠፋ ያለ ትንታኔ አቅርቧል :- እስኪ አንብቡት ::
ምንጭ :- አንድ አድርገን : ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ .ም .:: ኢህአዴግ “በአዲስ ራእይ” መጽሄት ምን እያለ ነው ?
Quote: . በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ የተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡”
. "ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት " ከሚል ቅዥት ባለፈ "አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” " የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ ::
. ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል : የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው ::
. ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡
. በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ .........
. እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው ::
PART 1
'አዲስ ራዕይ ' በየሁለት ወሩ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡
እንደ መረጃዎች ይች መጽሄት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ታጠነጥናለች አንዳንዴም ጸሀፊው እርሳቸው ናቸው የሚባልም ወሬ አለ፤ አቶ መለስም ጻፉት ሌሎች አባላት ታትሞ ከወጣ የድርጅታቸው አቋም ነው : አመለካከታቸው እሳቤያቸውንና ተግባራቸውን ከሞላ ጎደል የምታዩባት ክፍል ነች ፤ ይህች መጽሄት ተደራሽነቷ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ፤ መንግስት በሹመት ያስቀመጣቸው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ኃላፊዎች ፤ ከህዋስ ደረጃ ከፍ ያሉ አባላት ብቻ በመሆኑ እንዲህው በቀላሉ በማንም እጅ ላይ የመታየት እድሏ እጅጉን አናሳ ነው ፤ እዚች መጽሄት ላይ የሰፈረውን ሀሳብ መሰረት በማድረግ የኢህአዴግ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሚኒስትርነት ያስቀመጣቸው ሰዎች በድርጅታዊ ጉባኤ እንደሚነጋገሩበትና ይዘቷን የሚፈትሹበት ፤ ጽሁፉን ላነበቡትም ሆነ ላላነበቡትም አባላት የመንግስትን አቋም የሚያውቁበት መድረክ በየጊዜው እንዳላቸው ውስጥ አዋቂዎች ተንፍሰውልናል፡፡ አዲስ ራእይ በ 2ኛ ዓመት ቅጽ 3 ግንቦት -ሰኔ 2004 ዓ .ም ለመዳሰስ የተፈለገው ዋናው ጉዳይ በፖለቲካ አምዷ በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ የእግር እሳት የሆነባትን የሀይማኖት ጉዳይ ነው ፤
ኢህአዴግ በዚች 70 ገጽ በማትሞላ መጽሄት በአሁኑ ሰዓት ያለውን የሀይማኖት ችግር መሰረት በማድረግ 41 ገጹን በሚሸፍን መልኩ መተንፈስ ችሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ከሰጡት የሰዓታት ትንታኔ ጠለቅ ባለ መልኩ ነገሮችን በስፋትና በጥልቀት በደፈረሰ አይኑ ተመልክቶ ሀሳቡን ማስቀመጥ ችሏል ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን “አንዳንድ አማኞች” በማለት በግልጽ ያለውን እና የያዘውን አቋም ሲያንጸባርቅ አስተውለናል ፤
አክራሪነትን ከህገ መንግስቱ አንጻር የተመለከተ መስሎት የማይመለከተንን እኛንም በደንብ አድርጎ ወርፎናል ፤ በየቢሮው የሚለጠፉ የቅዱሳን ስዕላትንና የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስን እንዲህ በማለት ገልጾታል “የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎች : ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ…” በማለት አስቀምጦታል ፡፡ይህ ሁኔታ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢታይም የሰውን የእምነት ነጻነት ከማክበር አኳያ ይህን የመሰለ የማንቋሸሽና የማጥላላት ጽሁፍ መንግስትን ወክሎ ወጥቶ መመልከት መቻል እንደ አንድ ዜጋ ያሳፍራል፡፡ እዚህ ላይ የማህበረ ቅዱሳንን ስም በማይገባው ቦታ ከውሀቢያ እና ከአመለካከቱ ጎን አስቀምጦት ማየት ችለናል ፤ ለምሳሌ በገጽ 33 ላይ [color="red"]“በአንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነኝ ባዮች ከማህበረ ቅዱሳንም የተለየ ሚና ያለው ኮር ሃይል የሚያስተጋባው "አንድ ሀገር አንድ እምነት " የሚለው ቅዥት ጸረ -ህገ መንግስታዊ ነው ፡፡ ወሀብያ ይሁን የሌላ እምነት ተከታይ ጸረ ህገ መንግስት አቋሞቹንና ተግባሮችን አውግዞ እንደማኛውም ዜጋ ወይም ቡድን የራሱ መብት እንዲከበርለት የሚፈልገው ሁሉ የሌላውንም መብት አክብሮ እስካልተንቀሳቀሰ ድረስ ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጋጭትና የእምነቱን አስተምህሮ የሆኑት ጉዳዮች ላይ መንግስት የመምረጥም የመተቸትም ፍላጎት የለውም ፤ ይህንም አድርጎት አያውቅም” [/color] በማለት ያትታል ፤ አሁን እንደ ነጥብ የማህበሩን ስምና የጽሁፉ ይዘት አብሮ የሚሄዱ ሆነው አያገኟቸውም ፤ “ሊበሏት ያሰቧትን … ..” የሚባል ተረት ትዝ ያሰኞታል ፤ እኛ በርካታ የጥምቀት በዓላት ላይ ስንመለከት “አንድ ሀገር አንድ እምነት” የሚል ተጽፎ ለመመልከት አልቻልንም ፤ እነሱ ካዩ ከተመለከቱና መረጃው ካላቸው ቢያሳዩን መልካም ነው ፤ መጽሀፉ ደግሞ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ነው የሚለው “አንዲት ሀገር” የሚል የለበትም ፤ ይህ ጥቅስ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ ቢመስላቸውም እኛ ምን ማድረግ እንችላለን ? ከህገመንግስታችሁ ጋር እናጣጥምላችሁ ? ምን እንበለው ? ምንስ ብለን ቲሸርታችን ላይ ጽፈን እንልበሰው ? እኛ ቃሉ የመፈጸም እንጂ የማስተካከል የመለወጥ መብቱ የለንም ፤ ቃሉ ደግሞ እንደማይለወጥ በግልጽ መጽሀፉ ይነግረናል ፤ እኛ የተጻፈልንን ማመን ብቻ ነው ፤ ደግመን እንበለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ስለ ሀገሩ ተውትና “አንድ ሃይማኖት” የተባለችው ቀጥተኛዋ በደም የቆየችልን አሁን እኛ ያለንባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት ብለን እናምናለን ፡፡
በሌላ በኩል በገጽ 37 ላይ ይህን ሰፍሮ ያገኙታል “በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ እና በመሰረቱ ጸረ -ህገመንግስት መገለጫ ያላቸው አቋሞች የተላበሱበትና አንዳንድ የእኛ አባላትና አመራሮችም ኢህአዴግነትንም ጸረ ኢህአዴጋዊ አቋሞችን የያዙ ይዘቶችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሀድ የሚታይ ነው፡፡ አባላችን ወደ ሃይማኖት ሲሄድ ኢህአዴግነቱን ትቶ ፤ ወደ ኢህአዴግ ሲመጣ ደግሞ ሀይማኖቱን ትቶ ሊሆን አይችልም ፡፡ ጠንካራ አማኝም ጠንካራ ኢህአዴግም በመሆን መካከል ግጭት የለም ፡፡ ግጭት የሚፈጠረው ድንበሮችን ስናደበላልቅ ነው ፡፡ ስለዚህም በዚሁ አግባብ ግልጽነት ተፈጥሮ አባላችንን አመራራችን ሰልፉን ያስተካክል ፤ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ በሰበባ ሰበብ ሳይሸፋፈን ከድርጅቱ መጽዳት አለበት በማለት ያስቀምጣል” ይህን ያህል አትኩሮት ሰጥቶት ማስቀመጥ ከቻለ መንግስት ጊዜው ራስ ምታት እንደሆነበት ያሳያል ፤ በብሎጋችን ላይ ከወራት በፊት የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ በተመለከተ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ አንዱ ፍርድ ቤቶች ውስጥ 13 የሚደርሱ ሙስሊም ጠበቃዎች እና ዳኛዎች በእለተ ቅዳሜ በአሳቻ ሰዓት ተሰብስበው መገኝታቸውን ጽፈን ነበር ፤ ይህን ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ “በሀይማኖት ላይ የለዘበ አቋም እንዳታሳዩ ፤ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጋችሁ ብቻ ስራችሁን ስሩ” በማለት ቀጭን ትዕዛዝ ማስላለፉን ገልጸን ነበር ፤ አሁንም መናገር የፈለገውን ነገር ግልጽ ባለ መልኩ መናገር ባይችልም ኢህአዴግ አቋሙን ግን ሲያስቀምጥ ይመለከታሉ፡፡ ይህን የሚያገኙት ለአመራራቹ “ቀጣይ የትግል ግባችን ምን ይሁን” በሚለው ውስጥ ነው፡፡
በገጽ 17 ላይ አክራሪነት እና የመንግስት አመለካከት እንዲህ በሚል ሲያስቀምጥ እናያለን “ ..የሀይማኖት አክራሪነት የሚለው አገላለፅ የተለያዩ ሰዎች ከተለያዩ መመዘኛ በመነሳት ይተረጉሙታል ፡፡ የሃይማኖት መሪዎች አክራሪነትን ከሚመሩት ሃይማኖት መጻህፍት በመነሳት የቅዱሳን መጻህፍቱን መሰረታዊ መርህዎች የሚጻረር እንደሆነ በዝርዝር ያስረዳሉ ፤ ከዚህ በመነሳት ያወግዙታል ፡፡ የሀይማኖቱ እምነት ምን እንደሆነ ከሀይማኖት መሪዎቹ በላይ የሚያውቅ የለምና እነዚህ መሪዎች ከሚያውቁት ነገር ተነስተው አክራነትን ቢተነትኑትና ቢያወግዙት መብታቸው ነው ፡፡ ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅታችንና መንግስታችን ግን በሃይማኖት ሊቃውንት የተገነቡ ስላልደሉ አንድን ወይም ሌላ ሃይማኖትን ለማራመድ ሳይሆን ሁሉንም ዜጎች ለልማትና ዴሞክራሲ ዙሪያ ለማንቀሳቀስ የተደራጁ በመሆናቸው አክራሪነትን የሚመለከቱት ለልማትና ዴሞክራሲ አጀንዳ ካለው ተጽህኖ በመነሳት ብቻ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ ሲታይ የሃይማት አክራሪነት ጸረ ልማትና ጸረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሆኖ ይገኛል ፡፡
የዴሞክራሲ ስርአታችን ሁሉም ዜጎች የእምነት ነጻነት እንዳለው ያስቀምጣል ዜጎች የራሳቸውን እምነት ነጻነት ማስከበር ይችሉ ዘንድ የሌላውን የእምነት ነጻነት ማክበር እንዳለባቸው ያስቀምጣሉ ፡፡ አክራሪነት የምንለው ይህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ መርህ በሃይማኖት ሽፋን መቃወም ነው፡፡ ይህን የአክራሪነት አመለካከት ለሁሉም ሃይማኖቶች ሊታይ የሚችልና አልፎ አልፎም በተግባር የሚከሰት ነው፡፡ በዚሁ መሰረት አንዳንድ ሙስሊሞች ሌላውን ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሙስሊሞች እንኳን ሳይቀሩ ሀቀኛ ሙስሊሞች አይደሉም ብለው በመፈረጅ የእምነት ተቋሞቻቸውን ለማፍረስ ፤ የሃይማኖት አባቶችን መቃብሮች ቆፍረው ለማውደም ይከጅላቸዋል፡፡ በተግባር ሲፈጽሙት ታይተዋል ፡፡ የራሳቸውን የእምነት ነጻነት ለማስከበር የሚሞክሩት የሌላን ነጻነት በማክበር ሳይሆን የሌላውን ነጻነት በመድፈቅና በማፈን ነው፡፡ በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡” በማለት ያስቀምጣል ፤ ከላይ እንደመነሻ የተንደረደረበት ሀሳብ አክራሪነት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ አክራሪ ሙስሊሞችን ስራዎቻቸውን ያስቀምጣል ፤ በስተመጨረሻ “አንዳንድ ኦርቶዶክሶች” በማለት በእኛ ላይ አክራሪነትን ቋጭቶ ይደመድማል ፤
እኛ ተሀድሶያውያንን ተከታትለን ከቤተክርስትያኒቱ አስተምህሮ ውጪ የሆነውን ምንፍቅናቸውን ለህዝብ ስላሳየን አክራሪ ተብለናል ፤ በመሰረቱ ቤተመንግስትን በወታደር መጠበቅ ይቻላል እምነትን ግን እንደ እነርሱ በወታደር መጠበቅ አይቻልም ፤ አባቶቻችን ይችን እምነት ከመናፍቃን ጠብቀው ያቆዩልን ክፉ ትምህርታቸውን በማውጣት መክረው አልመለሱ ሲሉ በጉባኤ በማውገዝ መሆኑን እኛ እንጂ እነርሱ ሊያውቁልን አይችሉም ፤ ተሀድሶያውያንን የእምነት ነጻነታቸውን አልተጋፋንም ፤ የፈለጉትን እምነተ ማመን መብታቸው ነው ነገር ግን “ቤተክርስትያናችን የእነሱ አመለካከት ማራመጃ መድረክ አትሆንም” በማለታችን “አንዳንድ ኦርቶዶክሶች” ተብለን ስም ተሰጠን ፤ አሁን ብቻ አይደለም ወደፊትም እነዚህን መሰል የቤተክርስትያን የእግር ውስጥ እሳቶችን ስራቸውን ከመቃወም ፤ መግባርና ተግባራቸውን ከማጋለጥ ወደ ኋላ አንልም ፤ ጽሁፉ ጉደኛ ነው ብዙ ነገር አለበት እንቀጥል፡፡
“የዲሞክራሲ ስርአታችን መንግስትንና ሃይማኖት መለያየት እንዳለባቸውና አንዱ በሌላው ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት እንደማይገባው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ብሎ ነገር በፍጹም የማይታሰብ ነገር መሆኑን ያረጋግጣል ፡፡ የሃማኖት አክራሪነት የምንለው ይህንኑ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መርህ በሀይማኖት ሽፋን መናድ ነው ፤ ይህው አመለካከት በተለያየ መልኮች ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰፊ ቁጥር ባይኖራቸውም ጥቂት ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች እንደ ድሮ ሁሉ ኦርቶዶክስ ክርስትና የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ፡፡ ከሌሎች የተለየ መብትና ጥቅም እንዲኖረው ይመኛሉ፡፡ ይህ አመለካከት ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው የከሰመ ቢሆንም አክራሪነት የሚገለጽበት አንዱ ገጽታ መሆኑ አልቀረም ፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ሙስሊሞች የሀይማኖት ብዙሀነት ባለበት ሀገር እስልምና ነው ብለው ያመኑበት መመሪያ በመንግስትና በመንግስት ተቋች አማካኝነት እንዲፈጸሙ እስልምና መንግስት ሃይማት እንዲሆን ሲከጅሉ ይታያሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁለቱም እዚህው ሀገር የተፈጠሩ ይመስል የኦርቶዶክስም ሆነ የእስልምና አንዳንድ ተከታዮች ዘንድ የሚስተዋለው የተዛነፈ አስተሳሰብ ሁለቱም ነባር እንደሆኑና ሌላው መጤ በመሆኑ የሁለቱን ያህል ስፍራ እንደማይገባቸው አድርጎ የማሰብ ነው፡፡ ሌሎችም ሀይማኖቶች ደረጃው ቢለያይም ተመሳሳይ አክራሪነት ዝንባሌ የተጠናወታቸው አባላት አሏቸው፡፡ እነዚህ የተዛነፉ አስተሳሰቦች በአደባባይ የሚነገሩ ጭምር ናቸው ፡፡ እዚህ ላይ መዋቅራችንም ለችግሩ የራሱን ድርሻ መውሰድ አለበት ፡፡ የሁሉም ዜጎች የጋራ ንብረት የሆኑ አደባባዮችና መንገዶች በየበአሉ ከኃይማት ጋር በቀጥታ ባልተያያዙ ጸያፍ መፈክሮች ሲጥለቀለቁ መዋቅራችን ጭምር አይቶ እንዳላየ የሚያልፍበት ሁኔታም ይታያል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎችና ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡፡ በአንድም በሌላ መንገድ ይህንኑ አደገኛ መንገድ መከተል መደገፍ ነውና፡፡” በማለት ያስቀምጣል፡፡
ይህ ጽሁፍ በጣም ገራሚ ከመሆኑ የተነሳ ሰዳቢዎቹ ሲሳደቡ ጠያቄ እንደማይመጣ እርግጠኛ ሆነው ነው ፤ እውን ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት አይደለችምን ? በቁጥር የምናውቃቸው በቁጥር የማናውቃቸው ከ 20ሺህ በላይ አብያተክርስትያኖቻችን ቋሚ ምስክሮቻችን ናቸው ፤ ይህ ለናንተ ቅዥት ነው የማይፈታላችሁ ነገር ነው ፤ እንደ “ማኔ ቴቄል ፋሬስ” ፈቺ የሚያስፈልጋችሁ ይመስለናል ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት መሆኗ እኛ ዝም ብንል ምድሪቷ አፍ አውጥታ ትናገራለች ፤ትላንትና በእርዳታ ስም የመጡትን እምነቶች የተከፈቱትን አዳራሾች አትመልከቱ ፤ ይች ሀገር እንደ ሀገር እዚህ የደረሰችው በዚችው ቤተክርስትያን አስተዋጽኦ ነው ፤ የመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ 10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም ፤ ሌላው ደግሞ “ነባር አይደላችሁም” መባላችን አስገርሞናል ፤ ታሪክ ይናገራል ሙስሊም ወንድሞቻችን ወደዚች ሀገር የመጡት ከ 5ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ መሆኑን ተጽፎ የተቀመጠ እነርሱም የማይክዱት ሀቅ ነው ፤ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ 34 ዓ .ም ክርስትናን የተቀበለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆኑን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሮ እናገኝዋለን ፤ ታዲያ ማነው የነበረው ? ማንስ ነው በሂደት የመጣው ? ፤ ማንስ ነው መጤ ? እናንተም እኮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለአዲስ አበባ መጤዎች ናችሁ ዘነጋችሁት እንዴ ? ፤ ስለዚህ የኦሪት መስእዋት ስታቀርብ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስጠጊ እንጂ ተጠጊ አለመሆኗ እወቁ ፤ በሌላ በኩል ኦርቶዶክሳውን ሆንን የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስ በቲሸርቶቻችን ላይ አድርገን ስንሄድ ሀፍረት እንዴት እንደማይሰማን ጸሀፊው ሀሳቡን ያስቀምጣል ፤ “ነገሩ እንዴት ነው” አለች አይጥ የድመት ጓደኝነት ያላማራት ፤ ሌሎች በእምነታቸው ሊያፍሩ ይችሉ ይሆናል ፤ ሳያውቁ ገብተውበት መውጫው ጉድጓድ ጠቦባቸው ያሉበት እምነት ያሳፍራቸው ይሆናል ፤ እኛ ግን አንዳች የምናፍርበት የምንሳቀቅበት አንገት የምንደፋበት ነገር የለንም ፤ ለምንስ እናፍራለን ፤ በጣም ደስ ብሎን እንደምናደርገው በዚህ አጋጣሚ እወቁልን ፤ ለኛ ስብከት ነው ፤ ካስተዋላችሁ 4ኪሎ አካባቢ አንድ አይምሮው ትንሽ የሚያመው ወንድም ከፊት ለፊቱ ላይ የእመቤታችንን ነገር ለመንገር “ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል” የሚል ጽሁፍ ሲለጥፍ በጀርባው ደግሞ አሁን የማላስታሰውን አንድ በጣም ደስ የሚል ጥቅስ በጀርባው ላይ ለጥፎ ሲዞር ተመልክቻለሁ ፤ አደራችሁን አሸባሪ እንዳትሉት ፤ እሱ ኑሮ ያሸበረው ይበቃዋል…… .
“…እዚህ አገር የተፈጠሩ ይመስል ..” ማለትስ ምን ማለት ነው ?፤ ዛሬ ጠያቂ ባይኖራችሁ ነገ ግን ይኖራችኋል ፤ ቀን የራሱን ነገር ይዞ ይመጣል ፤ ጊዜ በራሱ መፍትሄ የሚሆንበትም ወቅት ሩቅ ላይሆን ይችላል ፡፡ በምድር የማይሻር ስልጣን የማይነቀል መንግስት የለም፡፡
በተለያዩ የመንግስት ፤ የግል እና መንግስታዊ ያልሆነ ቢሮዎች የሚሰሩ ሰዎች የመስሪያቤታቸው ደንብና መመሪያ ባይፈቅድም የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስና ቅዱሳን ስእላትን በግድግዳ ላይ ለጥፈው ይታያሉ ፤ ነገር ግን ይህ ነገር አግባብ አለመሆኑን በመንገር የሚያወርዱበትን መንገድ ከማመላከት ውጪ “በምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ” በማለት ድርጅታዊ አቋምን በሚያንጸባርቅ መጽሄት ላይ ሰፍሮ መመልከት ያሳዝናል ያሳፍራልም፡፡ እንቀጥል ..
ይህ ጽሁፍ ጽንፈኞችን በአንድ አንቀጽ አንዲህ ብሎ ይገልጻቸዋል “ሁል ጊዜም ጽንፈኞች ማንኛውም ሰው በሚከተለው እምነት የግል መብት የለውም ብለው ያምናሉ ፡፡ ውይይትና መግባባት ፤ ሰላማዊ ውይይትን በማውገዝ በአመጽ ተደግፈው የራሳቸውን አተያይ ይጭናሉ ፡፡ ከፍቅር ጥላቻን ፤ ከርህራሄ ጭካኔን ፤ ከመቻቻል መናቆርን ፤ ከእውቀት ድንቁርናን ፤ ከውይይት ጉልበትን ይመርጣሉ ፤ ያበረታታሉ ፡፡ ጽንፈኞች የመንግስትና የሃይማኖት መለያየትን አይቀበሉም ፤ ይልቅ እነሱ እምነት የተለየ የበላይነት እንዲኖረውና መንግስታዊ ድጋፍ ጡንቻ እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ይህ አመለካከት በተለያዩ የእስልምና እና ክርስትና ሃይማኖቶች ውስጥ በመሸጉ የተወሰኑ ቡድኖች የሚስተዋልና በተለያየ መልክና ደረጃ የሚንጸባረቅ ነው፡፡” በማለት ይገልጻቸዋል ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ነገር ግን አክራሪ ኦርቶዶክስ ግን ሊኖር አይችልም ፤ ሁለታችንንም በአንድ ሚዛን አስቀምጦ በአንድ መነጽር እየተመለከቱ መጻፍ አግባብ አይደለም ፤ ባይሆን ባሳለፍናቸው ጥቂት አመታት በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በጅማ እና እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አክራሪ በሆኑ ሰዎች መከራን ተቀብለዋል በመቀበልም ላይ ይገኛሉ ፤ በተለይ በጅማ የበርካቶች ደም ሲፈስ መመልከት ችለናል ፤ ነገር ግን መንግስት ይህ ነው የሚባል ርምጃ ሲወስድ መመልከት አልቻልንም ፤ የተጎዳነው በደልና ግፍ የደረሰብን እኛው ሆነን ሳለን ከአድራሽ ሃይሎች ጋር ደምሮ ሂሳብ ማወራረድ ተገቢ አይደለም ፤ የዛሬ ዓመት አካባቢ በጅማ አውራጃዎች ከ 35 በላይ የሌሎች የእምነት ተቋማት አዳራሾቻቸው በእሳት ሲጋዩ ፤ ሰውም ሲፈናቀል በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ጆሯችን ሰምቷል ፤ ከጋዜጦች ላይም አይኖቻችን አንብበዋል ፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህን አደረሱ የተባሉት ሰዎች ማንነታቸውን ስናውቅ የመንግስት እርምጃ አለመጣጠሙ ነበር ፤ እነዚህ ሰዎች በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙ ፤ የአካባቢው ባለሀብቶች ፤ የመስጂድ ኢማሞች ፤ የውጭ ገንዘብ ፈሰስ የሚደረግላቸው ቡድኖች እና የኢህአዴግ አባላት ሆነው መገኝታቸው አስደምሞናል ፤ እስኪ የደረሰውን የሞት ፤ የአካል ፤ የንብረት ፤ የሳይኮሎጂ ጉዳት አስቦ የተወሰደውን እርምጃ ተገቢ ነው የሚል ሰው ማነው ? ፤ እኛስ እውነትን እንናገራለን ጥሩውን እናበረታታለን የማይጠቅሙ አካሄዶችን እንነቅፋለን ፤ እነዚህን የመሰሉ የወረደ አመለካከት ያላቸውን ለራስ : ለቤተሰብ : ለእምነት ፤ ለድርጅታችሁ ኢህአዴግ እና ለሀገር የማይጠቅሙትን ማጥራት ከውስጡም የማጽዳት ስራ መስራት ሲገባው ፤ እጁን ወደ ሌሎች ላይ መጠቆሙ የሚያዋጣ አካሄድ አይመስለንም ፡፡
ጽሁፉ ይቀጥላል…
“ በሀገራችን ዜጎች በሚከተሉት እምነት ምክንያት በሚገፉባቸው ተገደው የሌላውን ሃይማት ካልተከተሉ ከቀያቸው የሚፈናቀሉበት ፤በሚከተሉት እምነት ምክንያት በተወሰኑ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ሀገራቸውን የማገልገል ፤ ከተቀጠሩም ከመሰላሉ ስር ፈቀቅ እዳይሉ ይደረግባቸው የነበሩት በነዚያ ህገ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ጥበቃ በነበራቸው ግፎች በነገሱባቸው የጨለማ ዘመናት እንኳን ጠንክሮ የዘለቀው የሃይማኖት መቻቻል ፤ ይህ ህዝቦች አብሮ የመኖር እና መደጋገፍ ትስስር ለመበጣጠስ በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽንፈኛ አክራሪ ኃይሎች የተፈጸሙ የጥፋት ድግሶች ማስተዋል ጥሩ ነው፡፡ ጥፋቶቹ ማተራመስ የጀመሩት በቅድሚያ የወጡባቸውን የሃይማኖት ተከታዮች ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የተቃጠሉ እና የፈረሱ መስጅዶች ፤ የታዋቂ የእስልምና የመቃብር ስፍራዎች በሙሉ ጥፋት የተፈጸመባቸው እስልምናን እንከተላለን በሚሉ ጥቂት ጽንፈኞች ነበር፡፡ የሙስሊሙን ተቋማት ከማፈራረስ ሳይቦዝኑ ቤተክርስትያናት አውድመዋል፤ በክርስትና በኩል ሌላውን የሚያንቋሽሹ ፤ የተለያዩ የክርስትና ተከታዮችን ጨምሮ መናፍቃን ፤ ኢ -አማንያን በማለት የሚተነኮሱ ኃይሎች አሉ፡፡ ከሁሉም ሃይማኖቶች አንጻር ያሉት እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው፡፡ በእርግጥ ከበርካቶች በስተጀርባ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስፖንሰሮች ያሉአቸው የፖለቲካ አጀንዳ የተላበሱ ጽንፈኞች ናቸው ፡፡ ብዙሀኑ ግን ለእምነታቸው ዘብ የቆሙ እየመሰላቸው በቀላሉ ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ … . ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው ፡፡ መንግስት ሊመርጥላቸው አይችልም፡፡” በማለት ይቀጥላል ፤ የበፊቱን የመንግስት አገዛዝ ማስቀመጣቸው ተገቢ ነው ፤ ቤተክርስትያችንም ከመሀመድ ግራኝና ከዮዲት ጉዲት በኋላ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ወቅት ነው ፤ በጊዜው ከአሁኑ የተሻለ የሀይማኖት መቻቻል እንደነበረ ጊዜውን ያሳለፉ ሰዎች ምስክሮች ናቸው ፤ ነገር ግን ያሳለፍነው ጊዜ ምንኛ ጨለማ ቢሆንም ይህን ወቅት ብርሀን ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ ግን የለም ፤ ሚዛኑ የመድሀኒአለም ነውና እኛ ዝም እንላለን ፤
በተጨማሪ በጥቅምት 11 ላይ ተሀድሶያውያንን በመቃወም ፤ "ቤተክርስትያን አትታደስም " በማለት ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደ ንብ በመትመም የተቃወሙትን ወጣቶች ሁኔታ ሌሎች የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሰዎች ያነሳሷቸው ናቸው " ብሎ ጽሁፉ ያትታል ፤ ይህ ስለ ቤተክርስትያናቸው ብለው ያደረጉት እንጂ የፖለቲካ ጥማት ያለባቸው ሰዎች ገፋፍተው ያስወጧው አይደሉም ፤ በጊዜውም ተቃውሟቸውን የገለጹት ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መንገድ መዝሙር በመዘመር እና እነዚህ ሰዎች ላይ አለን የሚሉትን የቤተክርስትያኒቷ አስተምህሮ ያልሆኑትን መረጃዎች ለብጹአን አባቶቻችን በማቅረብ እንጂ ከውጭ ሀገር የገንዘብ እርዳታ ተደርጎላቸው የፖለቲካ ማራመጃ ሆነው አይደለም ፤ ተቃውሞው የተደረገው በቤተክርስትያን ግቢ እንጂ በቤተመንግስት አለመሆኑን እናተም የምታውቁት ይመስለናል ፤ በጊዜው የነበሩት የሰንበት ተማሪዎች ለእምነታቸው ዘብ ቆመዋል ፤ የአባቶቻቸው እምነት እንዳይሸረሸር ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ፤ ፍጹም አልተሳሳቱም ፤ ለእምነት መቆርቆርን ያሳዩንና ያስተማሩን አይከኖቻችን ናቸው ፤ በሌላ በኩል “መናፍቃን” የሚለውን ስም ባለቤቶቹ ሳይከብዳቸው መንግስት የገደል ማሚቱ ሆኖ ያስተጋባላቸዋል ፤ የእናንተ አባል ያልሆነን "አሸባሪ " በማለት ታፔላ ስትለጥፉ ምንም ያልመሰላችሁ እኛ ግን ውስጣችንን እንደ ነቀዝ ቦርቡረው ሊጨርሱን ጥቂት የቀራቸውን ሰዎች የሚመለከተው አካል ስራቸውን መዝኖ ሲያወግዛቸው እኛም "መናፍቃ ነበሩ " ስንል "ለምን ?" ትሉናላችሁ ፤ "ህገ መንግስቱን ይጋፋል " ትላላችሁ ፤ ይህ ህገ መንግስት እኮ ለሁሉም ነው የሚሰራው ፤ መፎከሪያ ማስፈራሪያም ሆኖ መቀመጥ የለበትም፤ ለማንኛውም በመጽሀፉ ላይ ከሰፈሩት 41 ገጾች ውስጥ 30 ያህሉ ሙስሊሞችን የሚመለከት ሲሆን 10 ደግሞ ቀስቱ ወደኛ ሆኖ አግኝተነዋል ፤ ዋና ሀሳብ ያልናቸውን በጣም በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረናል ፤ መጽሀፉን የምታገኙ ሰዎች አንብቡትና የራሳችሁን ፍርድ ስጡ ፤ በቅርብ ለማታገኙት በሀገር እና ከሀገር ውጪ ላላችሁት ደግሞ መለስ ብለው ብሎጋችንን ይጎብኙ እንደወረደ በፒዲፌ አዘጋጅተን ብሎጋችን ላይ እናስቀምጥሎታለን …… .
አንብባችሁ ሀሳባችሁን ላኩልን… ..
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤ 5
ተድላ
በዚህ ባለንበት ሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሀይማኖት እና መንግስት መለያየት የለባቸውም የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር :: ግርም ነው ያለኝ :: በመጀመሪያ ደረጃ ሀይማኖት በጣም የግል ነገር ነው :: ያገር ሀይማኖት የሚባል ነገር ሊኖር አይገባም :: ከሰባዊ መብቶች አንዱ የኅሊና ነጻነት ነው :: አንዱን መንገደኛ መንገድ ላይ አስቁሜ "የፈጠርከኝ አንተ ነህ ብዬ ስለማምን ከዛሬ ጀምሮ አምላኬ አንተ ነህ ! አመልክሀለሁ !!" ብለውና ያ መንገደኛው እንዳመልከው ከፈቀደልኝ ሌላ ሰው ምንም የሚያገባው ገዳይ ሊኖር አይችልም :: "ሰውዬው ዛሬ ነው ከ አውሮፓ የመጣው : ልታመልከው አትችልም : መጤ ነው " ብሎ የሚለኝ ሰው ካለ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቴን እንደነፈገኝ ነው የምቆጥረው :: "ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያልኩህ ለምን ሌላ ሰው አመለክ " ብሎ ሊጠይቀኝ የሚችል ታላቁ እግዚአብሄር ብቻ ነው :: እሱ "ይህ ሰው ሰውን እንደ አምላክ ሲያመልክ ለምን ዝም ብለህ አየህ ? እንዴት "መናፍቅ " ብለህ አልገደልከውም ?" ብሎ ማንንም አይጠይቅም :: ለዝሁም ነው ሀይማኖት የግል ነው የሚባለው :: ነገር ግን አምላኬ ነው ብዬ ማምለክ የጀመርኩትን ሰውዬ ምስል አራት ሆነን ከምንሰራበት የመንግስት መስሪያ ቤት ክፍል ግድግዳ ላይ ብለጥፍ ወይም በመንግስት ኮምፒውተር ደስክ ቶፕ ላይ ባኖር የሌላውን ሰው መብት መጋፋት ይሆንብኛል :: እነሱም የመላዕክትንም ሆነ የመስጂድ ወይም የማሪያምን ምስል አምጥቶ የሚለጥፉ ከሆነ እንደተባለውም ክፍሉ ጭምልቅልቁ ይወጣል : የሀይማኖት ግጭትም ይመጣል :: ማንም ሰው በቤቱ ከበር እስከ አልጋው ድረስ በቅዱሳን እና በመላእክት ምስል ቢሞላ ማን የሚጠይቀው ይኖራል :: እምነቱን ግን እኔ ላይ ጫና በሚፈጥር መልኩ ማካሄድ የለበትም :: ሌላው ቀርቶ በህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ውስጥ የሚደመጡት ማንኛውም አይነት ሀይማኖታዊ ነገሮች የሰውን በነጻነት የመጓዝ መብት የሚጻረሩ ናቸው :: እኔ ሙስሊም ሆኜ የክርስትና መዝሙር ተከፍቶብኝ ከአዲስ አበባ መቱ ብሄድ ቶርቸር እየተደረኩ ነው ይውምጓዘው :: ሀይማኖትን የግል ለማድረግ መንግስት ገና መውሰድ የሚገባቸው ብዙ ብዙ እርምጃዎች አሉ ::
ሌላው የገረመኝ "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት " የሚለው አባባል ነው :: ምናልባት አክሱም እና ፋሲለደስ : ላሊበላ እና እዚያ ወደ ሰሜን አካባቢ ያሉ ድንጋዮች ሊባሉ ይችሉ ይሆናል :: ሌላው የቀረው ምዕራብ ምስራቅ ደቡብ እና መካከላዊው የኦርቶዶክስን ስም የሰማው ያ ወራሪው ምኒሊክ እነኝያን አካባቢውችን ከወረረ በኌላ ስለሆነ ያ አባባል አይመለከታቸውም ::
አንዲት ሀይማኖት : አንዲት ጥምቀት ...ያ ጸሀፊ (ሀዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ) ደግሞ እርግጠኛ ነኝ የኦርቶዶክስን ስም ሰምቶ አያውቅም :: ጥቅሱ ትርጉሙ እንደዚያ አይመስለኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Jul 02, 2012 5:39 am Post subject:
ፈጣሪ ሆይ እኒህን የአውሬውን ተከታዮች የምንገላገልበትን ዘመን አቅርብልን ::
ምንጭ :- ደጀሰላም :- ሰኔ 24 ቀን 2004 ዓ .ም .:: ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል ::
Quote: · አራት መነኰሳት በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል፤ ሌሎቹ መነኰሳት እየተደበደቡ ተበታትነዋል።
· የገዳሙ የሱባኤ ወቅት በፖሊስ የኀይል ርምጃ እየታወከ ነው።
· በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግድብ የሚሠራው ሱር ኮንስትራክሽን ለቆ መውጣቱ እየተነገረ ነው፤ በምትኩ የቻይና ተቋራጭ የገባ ቢኾንም በእርሱም ላይ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰምቷል። በሰሜን ጎንደር ሀ /ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከማይ ፀብሪና ዓዲ አርቃይ ወረዳዎች በአምስት መኪና ተጭነው በመጡ የፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ሥምሪት ውስጥ እንደሚገኝ የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላምገለጹ፡፡
ትናንት፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ .ም፣ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ ገዳሙን በተቆጣጠረው የፖሊስ ኀይል አራት የገዳሙ መነኰሳት ተይዘው ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲኾን ሌሎቹ መነኰሳት ደግሞ ለሱባኤ (ሕርመት ) ከተሰበሰቡበት በቆመጥ እየተደበደቡ መበታተናቸው ተጠቁሟል፡፡ ከአራቱ መነኰሳት መካከል ሦስቱ፣ አባ ኀይለ ኢየሱስ፣ አባ ግርማይ፣ አባ ገብረ እግዚአብሔርእንደሚባሉ ተረጋግጧል፤ የአራተኛውን መነኰስ ስም ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ማኅበረ መነኰሳቱን የማሳደዱ ተግባር ከገዳሙ ውጭም የቀጠለ ሲኾን ፖሊስ አባ ገብረ ሕይወት የተባሉ ሌላ የገዳሙ መነኮስን ለመያዝ በደባርቅ ከተማ አሠሣ እያደረገ መኾኑ ተገልጧል፡፡ የአሠሣው እና ስምሪቱ መጠናከር ምክንያት፣ ከግንቦት 22 ቀን አንሥቶ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ሴት መነኰሳዪያት፣ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በገዳሙ ላይ የሚያደርሰውን አካባቢያዊና ማኅበራዊ ጉዳት በመቃወም “ኑና ገዳሙን ተረከቡ፤ እኛ መሰደዳችን ነው” በሚል ለሕዝቡ ጥሪ ካስተላለፉ በኋላ በተለይም በዛሬማ ቀበሌና በእንዳባጉና ወረዳ ዲማ ቀበሌ እየተጠናከረ የመጣው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መኾኑ ተመልክቷል፡፡
በዋልድባ አብረንታንት ገዳም፣ በዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም እና በዋልድባ ዳልሽሐ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም በየዓመቱ ከሰኔ 21 - ኅዳር 8 ቀን የሱባኤ ወቅት ነው፡፡ ገዳሙ ዓመት እስከ ዓመት ሱባኤ የሚያዝበት፣ አባቶች ያለማቋረጥ ከእግዚአብሔር የሚገናኙበት የሰማይ በር ቢኾንም፣ ይህ ወቅት ግን ከሌላው ጊዜ ተለይቶ ማንም አቋርጦ ለመውጣት የማይፈቀድበት ነው፡፡ በአንድነትና በፍቅር ተሰብስበው የሚኖሩትማኅበረ መነኰሳት ጭው ካለው በርሓ ገብተው በቋጥኝና በዋሻ እንደሚኖሩት ግሑሳን ባሕታውያን ከሰው ተለይተው በአንድ ቦታ ተወስነው በጾም፣ በጸሎትና በስግደት መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን የሚያጠናክሩበት ወቅት ነው፡፡
ዋልድባን በአራቱም ማእዝናት የከበቡት የእንሰያ (ምሥራቅ )፣ ዛሬማ (ምዕራብ )፣ ተከዜ (ሰሜን )፣ ዛሬማና ወይባ (ደቡብ ) የተሰኙት ታላላቅ ወንዞችም በሰኔ የሞሉ እስከ ኅዳር አይጎድሉም፡፡ ከሱባኤው ፍጻሜ በኋላ፣ ኅዳር ስምንት ቀን የአርባእቱ እንስሳ ክብረ በዓል ቀን፣ ወንዞቹን ተሻግረው በምሥራቅ - ፀለምትና በምዕራብ - ወልቃይት በሚገኙ የገዳሙ እርሻ ቦታዎች ከተዘጋጀው ድግስ የሚቀምሱ አሉ፡፡ ለዚህም በተለይም ማይ ለበጣታላቁ የማኅበሩ መገናኛ ቦታ ነው፡፡
የዘንድሮው የገዳሙ የሱባኤ ወቅት ግን ይህን ለዘመናት የቆየ የአበው ሥርዐትና ትውፊት የሚደግምበትን የጥሞና ጊዜ የታደለ አይመስልም፡፡ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በገዳሙ ህልውናና ክብር ላይ በጋረጠው ስጋት ሳቢያ የሰቋር ኪዳነ ምሕረት ማኅበረ መነኰሳት በተለይም ከግንቦት 22 ቀን ጀምሮ “ኑ ፣ ታቦቱን፣ ቅርሱን ተረከቡ፤ እኛ እንፈልሳለን (ወደ በርሓ እንሰወራለን )” በሚል ለምእመኑ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከስድስት ያላነሱ የዓዲ አርቃይ ወረዳ ቀበሌዎች (ሳንቅ፣ ዛሬማ፣ ያሊ፣ የጥራይና፣ ጅሮሰ፣ ነብራና ፍድቃ ) አርሶ አደሮች ከግንቦት 23 እና 24 ቀን አንሥቶ ዛሬማና ሰቋር ላይ በመሰብሰብ ተቃውሟቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተነግሯል፡፡
የአማራ ብ /ክ /መ ፖሊስ ኮማንደርና የሰሜን ጎንደር ዞን ብአዴን ጽ /ቤት ሓላፊ ግንቦት 27 እና 28 ቀን ዛሬማ ቀበሌ ላይ የወረዳ አመራሮችንና ምእመኑን በአንድነት ጠርተው ስለ ፕሮጀክቱ ለማሳመን ስብሰባዎችን አካሂደዋል፡፡ ይኹንና በዚያው ዛሬማ ቀበሌ የመድኃኔዓለም ታቦት ማረፊያ ዋርካ ሥር በመገናኘት ስብሰባው አሳታፊ አለመኾኑንና በስብሰባው ላይ ተገኝተው አቋማቸውን እንዳይገልጹ መከልከላቸው አግባብ አለመኾኑን በመቃወም እስከ 50 ያህል ወጣቶችን ለእስር ከመዳረግና በጭከና ከመደብደብ በቀር ውጤት እንዳላስገኘላቸው ነው የተዘገበው፡፡ ግንቦት 29 ቀን ከታሰሩት ኀምሳዎቹ ወጣቶች መካከል “ወጣቱን ለስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ቀስቅሰዋል፤ ከተቃዋሚዎች ጋራ በመገናኘት እንቅስቃሴውን አስተባብረዋል፤” በሚል ስምንት ወጣቶች ተለይተው ከዛሬማ ቀበሌ 40 ኪ .ሜ ወደሚርቀው የወረዳው ከተማ (ዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ ) ሲወሰዱ ሌሎቹ በዋስና በገንዘብ ቅጣት ደረጃ በደረጃ መለቀቃቸው ተገልጧል፡፡
ይህ ሁሉ ሲኾን የዋልድባ ገዳም የሚገኝባቸው ሦስቱ አህጉረ ስብከት ይኹን ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ /ቤቶች ድምፃቸውን ባለማሰማታቸው ምእመኑ ከዘንድሮው ዓመት ጀምሮ “የነፍስ ዐሥራት በኵራት” ሲል የሚጠራውን መባዕና የሰበካ ጉባኤ አስተዋፅኦ እንደማይከፍል ለወረዳ ቤተ ክህነት በጻፈው ደብዳቤ ማስታወቁ ተመልክቷል፡፡ የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ /ቤቱ ጉዳዩን ለአህጉረ ስብከቱ ጽ /ቤቶች ያስታወቁ ቢኾንም ምን ምላሽ እንደተሰጠ ለማወቅ አልተቻለም፡፡
የተቃውሞው ከዕለት ወደ ዕለት መጠናከር ያሳሰበው የክልሉ (የአማራ ብ /ክ /መ ) አስተዳደር፣ ፕሬዝዳንቱን አቶ አያሌው ጎበዜን፣ የክልልና ዞን ጸጥታ ሓላፊዎች እንዲሁም የብአዴን ጽ /ቤት ሓላፊዎች በተገኙበት ሰኔ ሰባት ቀን 2004 ዓ .ም ዓዲ አርቃይ ላይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ ከዋልድባ አብረንታንት ቤተ ጣዕማና ቤተ ሚናስ፣ የሰቋር ኪዳነ ምሕረትና ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት ገዳማት ከእያንዳንዳቸው ዐሥር፣ ዐሥር መነኰሳት፤ 28 የቀበሌ አመራሮችና “የልማት አርበኛ” የተሰኙ አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር፡፡
የክልል፣ የዞንና ወረዳዎች (ደባርቅ፣ ፀለምት - ማይ ፀብሪ፣ ዓዲ አርቃይና ጎንደር ) አመራሮች የታደሙበት ይኸው ስብሰባ ልጆቻቸው በታሰሩባቸው ወላጆች ጥያቄ ከዓዲ አርቃይ ወደ ዛሬማ እንዲዞር የተደረገ ቢኾንም በስብሰባው ከተሳተፉት ብዙኀኑ “ከጎንደር እስከ ማይ ፀብሪ ያሉ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችና የተለየ ሐሳብ የማያነሡ ናቸው” ብለዋል ታዛቢዎች፡፡ ከዋልድባ አብረንታንት ዘቤተ ጣዕማ ስድስት መነኰሳት ቢገኙም ከዋልድባ አብረንታንት ዘቤተ ሚናስ ማኅበር የታየ አልነበረም፡፡ ከሰቋር እና ዳልሽሓ የተገኙትም የተወሰኑት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በጸሎት ሲያሳርጉ ከመሰብሰቢያው ወጥተው ሄደዋል፤ የቀሩትም ባሉበት በመቀመጥ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፤ መስቀላቸውንም ለመሳለም ፈቃደኛ አልኾኑም፡፡
በዚሁ ስብሰባ እንደ ማይ ፀብሪው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ መረሳ ያሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት፡ - “ሃይማኖትን ሽፋን እያደረጋችኹ የፖለቲካ ዘመቻ ታደርጋላችኹ፤ የፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰለባ ኾናችኋል፤ የእነርሱን ድምፅ ነው የምታስተጋቡ” በማለት ግልጽ ዘለፋ ማሰማታቸው ተገልጧል፡፡ “ብትስማሙና ልማት ቢለማ ምናለበት ?” የሚሉ ልመናዎችም ተደምጠዋል፡፡ መነኰሳቱ በበኩላቸው “በልቅሶ ነው ያለነው፤ ዐፅም ወጥቶ ውኃ አይቆምም፤ ቤተ ክርስቲያን እየፈረሰ በሚለማ ልማት አንስማማም፤ ዋልድባ ቅንጣት ያህል አትነካም›፤ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ እንጂ ፖለቲካ አይደለም” በሚል ቁርጡን ማስታወቃቸው ተነግሯል፡፡
በዚሁ ስብሰባ ዋዜማ፣ ሰኔ ስድስት ቀን 2004 ዓ .ም፣ በዓዲ አርቃይ ከተማ አስጋሪት ማርያም በተሰኘችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገናኙ የከተማው ወጣቶች ስብሰባው ወደሚካሄድበት ዛሬማ ቀበሌ በመሄድ ድምፃቸውን ለማሰማት እየተመካከሩ በነበረበት ወቅት የወረዳው ፖሊስ ደርሶ በሽመል በመደብደብ እንዲበተኑ ማድረጉን የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት በምትገኘው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብሰበው የነበሩት ቁጥራቸው ከ 30 የማያንሱ ወጣቶች ከተበታተኑ በኋላ ፖሊስ በየቤቱ በመዞር ወላጆች ልጆቻቸውን ይህን ዐይነቱ የተቃውሞ ምክክር ከማድረግ እንዲቆጠቡ የማይመክር ከኾነ ጥብቅ ርምጃ እንደሚወስድባቸው ሲያሳስብ መዋሉ ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና፣ ንድፉ በትግራይ ውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ተሠርቶ በትግራይ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ግንባታው የተጀመረውን የዛሬማ ወንዝ ግድብ ሥራ ተረክቦ ሲመራ የቆየው ሱር ኮንስትራክሽን ሥራውን አቋርጦ መውጣቱ ተሰምቷል፤ ምክንያቱ ቁፋሮው የሚካሄድበት ቦታ ከመሬት በሚፈልቅ ውኃ እየተሞላ ማስቸገሩና የምእመኑ ተቃውሞ ያሳደረው ግፊት ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስሙ ያልተገለጸ አንድ የቻይና ተቋራጭ የግድቡን ሥራ ለመቀጠል የተተካ ቢኾንም በተመሳሳይ አስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡ የሱር ኮንስትራክሽን መውጣት ከተጠቀሰው ምክንያት ጋራ መያያዙን የሚጠራጠሩ ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው፣ በግድቡ ዲዛይን (የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ውኃ አጠቃቀም ) ላይ መሠረታዊ ለውጥ በማድረግ ሥራውን ለመቀጠል ሳይታሰብ እንዳልቀረ ያላቸውን ሐሳብ ገልጸዋል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን።
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jul 04, 2012 12:51 am Post subject:
ሰላም የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
የአውሬው (666) ተከታዮች የሆኑት ወያኔዎች ቤተክርስቲያንን የማጥፋቱን ሥራ የጀመሩት ዛሬ ሣይሆን ገና ከተፈጠሩበት ዕለት ጀምሮ እንደሆነ የታወቀ ነው :: ዘንድሮ የሚነዳቸው ሣጥናኤል ባዘዛቸው መሠረት የመጨረሻ የሞት ጉዟቸውን አጣጡፈዋል :: ሠሞኑን ደግሞ ከዋልድባ ገዳም ሱባዔ ላይ ያሉትን አባቶች እያፈኑ ወደተለያዩ የማሠቃያ እሥር ቤቶች እየወሠዱ ነው :: ትላንት ሰኞ በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ የአማርኛው መርኃ -ግብር የተላለፈ ዝግጅት አለ : ተከታተሉት ::
ምንጮች :-
1 ..... ዋልድባን እንታደግ : ማክሰኞ ሰኔ 25 ቀን 2004 ዓ .ም .:: በዋልድባ አባቶች ላይ ፈተናው ጨምሯል ከጸሎት በመሣሪያ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው ::
2 ..... Save Waldba, Published on Jul 3, 2012. ዋልድባ በቪኦኤ July 2, 2012.
Quote: በዋልድባ ሰቋር ኪዳነምሕረት የሴቶች አንድነት ገዳም አባቶች እና እናቶች በሱባኤ ባሉበት ወቅት የመንግሥት ታጣቂ ወታደሮች ወደ ገዳሙ ክልል በመግባት 5 አረጋውያን መነኩሳትን ለእስር ዳርገዋቸዋል ምክንያታቸውም ሕዝቡን የምታነሳሱት እናንተ ናችሁ ለዓመጽ እና ለጦርነት አነሳሳችሁት በሚል ሰበብ ነው። እውነታው ግን እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ለሃይማኖቱ እና ለቤተክርስቲያኑ ክብር መቆም ያለበት መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። እነዚህ አባቶች ለሀገር፣ ለወገን፣ ለመሪዎችን እንዲሁም ለአለም በጸለዩ የአባቶቻችንን ርስት አንሰጥም ባሉ እስር መዳረጋቸው ትልቅ ቁጣ አስተስቷል በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ዝም አንበል የአባቶቻችን ደም ይጠራናል የበኩላችንን እናድርግ ስለ እመብርሃን የጭንቅ አማላጇ ብላችሁ ቤተክርስቲያንን እንጠብቅ ::
"እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን " ራዕይ 10:3
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jul 04, 2012 10:02 pm Post subject:
ሰላም የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች :-
ጉዳቸው የማያልቀው የአውሬው (666) አማኞች የሆኑት ወያኔዎች የዋልድባ መናንያንን በገዳሙ ውስጥ በግድብ ሥራ ጥቅም ላይ ሲውል የነበረ ቡል -ዶዘር በመቃጠሉ እነርሱ ኃላፊነቱን እንዲወስዱ አስገድዷል :: ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ወያኔ 'የአማራ ክልል ' ብሎ በከለለው የገዳሙ ክፍል የሚኖሩት እኒህ መነኮሣት ተይዘው የታሠሩት 'ትግራይ ክልል ' በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ መሆኑ ነው :: መቼም የዘንድሮው ለጉድ ነው
ምንጭ :- ደጀ ሰላም፤ ረቡዕ ሰኔ 27 ቀን 2004 ዓ .ም .:: የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና ለተጎዱት ሠራተኞች ሓላፊነት እንዲወሰዱ እየተገደዱ ነው ::
Quote: . የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በአካባቢው ሕዝብ እየተሳደዱ ነው ::
· ነዋሪው ሠራተኞቹን እስከ ማይ ገባ ከተማ ድረስ እንዳሳደዳቸው ተነግሯል ::
· የዓዲ አርቃይና ማይ ፀብሪ ወረዳዎች ሓላፊዎች በታሰሩት መነኰሳት እየተወዛገቡ ነው ::
· ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ናቸው ::
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ .ም÷ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ መኾናቸውን የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡
በተጠቀሰው ቀን በአራት ያህል ቶዮታ መኪናዎች በዓዲ አርቃይ ወረዳ ጸጥታ ሓላፊዎች እና በፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ከገዳሙ ከተወሰዱት አምስት መነኰሳት መካከል ሁለቱ ማለትም አባ ተክለ ሃይማኖት እና አባ ኀይለ ሥላሴ ወደ ዓዲ አርቃይ፤ የተቀሩት ሦስቱ ማለትም አባ ገብረ ማርያም (አባ ግርማይ )፣ አባ ኀይለ ኢየሱስ እና አባ ገብረ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወደ ማይ ፀብሪ (በአንዳንድ ምንጮች ጥቆማ ወደ ዛሬማ ቀበሌ ) በኋላም ወደ ዓዲ አርቃይ መመለሳቸው ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አምስቱም መነኰሳት [በትግራይ ክልል ] በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ በሚገኝ አንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ ሌላ ሰው ሊጠይቃቸው በማይችልበት ኹኔታ ተቆልፎባቸው እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
አምስቱ መነኰሳት ለእስር በተዳረጉበት ኹኔታ ላይ የማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳደር ከዓዲ አርቃይ ወረዳ አስተዳደር ጋራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ የውዝግቡ መንሥኤ አምስቱ መነኰሳት የተወሰዱበት የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በአማራ ብ /ክ /መ ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኝ በመኾኑና በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ወደሚገኘው ማይ ፀብሪ ተወስደው በመታሰራቸው ላይ ሓላፊነት ላለመውሰድ ነው ተብሏል፡፡ የዓዲ አርቃይ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ለአምስቱ መነኰሳት መታሰር የቅርብ ምክንያት የኾነው የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ዶዘር መቃጠልና በሠራተኞቹ ላይ የደረሰው ጉዳት የሚመለከተው በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኘው የማይ ፀብሪ አስተዳደርን እንደሚል ተመልክቷል፡፡
በዚያው በዓዲ አርቃይ ወረዳ የፍትሕና ጸጥታ ዘርፍ ሓላፊው ‹‹ሓላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም›› በሚል ወደ ሲቪል ሰርቪስ እንዲዘዋወሩ መደረጉ ከዚሁ ውዝግብ ጋራ ሳይያያዝ እንደማይቀር ምንጮቹ ያላቸውን አስተያየት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
‹‹ሕዝብን ለተቃውሞ ቀስቅሰዋል፤ ከውጭ ሚዲያዎች ጋራ ይገናኛሉ›› በሚል እየተዋከቡ ከሚገኙት ወንድና ሴት የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት መካከል÷ ቅዳሜ ዕለት የተወሰዱት አምስት መነኰሳት÷ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የዛሬማ ወንዝ ግድብ በሚሠራበት የፕሮጀክቱ ስፍራ ላይ ለተቃጠለው ዶዘርና ለተጎዱት የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ‹‹ሓላፊነቱን ውሰዱ›› የሚል ጫና በጸጥታ ኀይሎች እየተደረገባቸው መኾኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ አምስቱ መነኰሳት ሰኔ ሰባት ቀን 2004 ዓ .ም በዛሬማ ቀበሌ ከክልል፣ ዞንና ቀበሌ አመራሮች ጋራ ስለ ስኳር ልማት ፕሮጀክቱ (ግድቡ ግንባታ ) ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ተገኝተው የነበረ ሲኾን÷ ከእነርሱም መካከል በስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎና ግልጽ ተቃውሞ ሲያሰሙ በነበሩቱ ላይ ጫናው በርትቶ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
የዜናው ምንጮች ጨምረው እንዳመለከቱት÷ ፕሮጀክቱ በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭና ታሳቢ ስጋቶች የተነሣ በአካባቢው የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በያዝነው ሳምንትም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ባለፉት ቀናት ነዋሪው በጦር መሣርያ ሳይቀር የፕሮጀክቱን ሠራተኞች የፕሮጀክቱ ጽ /ቤት እስከሚገኝበት ማይ ገባ ወረዳ (ከተማ ) ድረስ እያስፈራራ ማሳደድ መጀመሩም በአስረጅነት ተጠቅሷል፡፡ ከፕሮጀክቱ ስፍራ በእግር አንድ ሰዓት ወደሚወስደው የሠራተኞች መኖርያ እና የፕሮጀክቱ ጽ /ቤት ወደሚገኝበት ማይ ገባ ከተማ እግሬ አውጭኝ ብለው ከሸሹት ሠራተኞች መካከልም በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ሳይኖሩ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡