WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የወያኔ የኢኮኖሚ ዕድገትና የሸገር የጎዳና ላይ ለማኞች

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጋንች .

ጀማሪ ኮትኳች


Joined: 16 Dec 2011
Posts: 99

PostPosted: Mon Mar 19, 2012 9:30 pm    Post subject: የወያኔ የኢኮኖሚ ዕድገትና የሸገር የጎዳና ላይ ለማኞች Reply with quote

ከዓለማየሁ ገላጋይ
አይን -አፋር አዳዲስ አረጋውያን የኔብጤዎች በየጐዳናው ተረጭተዋል፡፡ የእለት ጉርሳቸው እንጂ የአመት ልብሳቸው ገና ያላለቀ አዛውንቶች፣ ድህነት አለሳልሶ ሥር የሰደደባቸው፣ ችግራቸው በቅጡ ያልታወቀላቸው፣ እንዴት ምፅዋት መጠየቅ እንዳለባቸው ግራ በመጋባታቸው የሚቁለጨለጩ… ይመስላሉ፡፡ በአጠገባቸው ሰው ሲያልፍ በፈራተባ እጃቸውን ሾከክ አድርገው ለልመና ይዘረጋሉ፡፡ የሚሉት ባይሰማም (በሐፍረት ) ያልጐመጉማሉ፡፡

ከሀገር ፍቅር ቴአትር በታች ያለች አንድ ካፌ በረንዳ ላይ እንደተቀመጥኩ ወይዘሮዋ ከላይ ታች ሲሉ ለረጅም ጊዜ አየኋቸው፡፡ በመጨረሻ ጠርቻቸው አብረውኝ እንዲቀመጡ ጋበዝኳቸው፡፡ በምርጫቸው ሻይ አዘዙ፡፡ መደበኛ ያልሆነ ወግ ያዝን፡፡ ወይዘሮዋ ሁለት ወንድ ልጆች ያሏቸው ቢሆንም አንዱ ከቤት ከወጣ እንደቆየ ይናገራሉ፡ ይሙት ይዳን አያውቁም፡፡ እንደገመቱት ከሆነ ውትድርና ተቀጥሮ ነው ድምፁን ያጠፋባቸው፡፡ ሁለተኛው ልጃቸው ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የመንግስት ሰራተኛ ነበር፡፡ አሁን በማያውቁት ምክንያት ተባርሮ የእናቱን እጅ የሚቀላውጥ ስራ ፈት ሆኗል፡፡ ባለቤታቸው አስር አለቃ ጉሩሙ ሰንበታ ሲሞቱ የጡረታ ጡረታ ሰላሳ ብር ከሰባት ሳንቲም መተዳደሪያ ከመንግስት ተቆርጦላቸዋል፡፡ ከሰባት አመት በፊት በወጪ ሳይቀናጡ
ልጃቸው ጣል ከሚያደርግላቸው መጠነኛ ብር ጋር ጡረታቸውን አብቃቅተው ይኖሩ ነበር፡፡ አሁን ግን ‹‹ኑሮ ጣሪያ ወጣ›› ይላሉ በደፈናው፡፡

‹‹ጡረታዬ የተጨመረ ቢሆንም እንኳን ለመቅመሻ ለመላሻም አልበቃ አለ፡፡ ምን ላድርግ ? በስተርጅና የሰው ፊት የሚገርፈኝ ወድጄ ነው ? የኖርኩት’ኮበቂ ነው፡፡ ይሄን ከሚያሳየኝ ቢገድለኝ ይሻለኝ ነበር፡፡››

የአሮጌው ትውልድ መጐሳቆል የአዲሱ ትውልድ ገመና መሆኑ ተዘንግቷል፡፡ ስድባችንን በየጐዳናው ረጭተናል፡፡ ውርደታችንን አደባባይ አስጥተናል፡፡ ንገሩን ባይነታችን አይን አውጥቷል፡፡ እጅግ ብዙ -ብዙ አፋራም አዛውንቶች ነፍስን ከስጋ በሚለይ ሰቀቀናም የልመና ኑሮ እየተፍገመገሙ ነው፡፡ እንዲህ ያሉ እናቶች የሚፈሩት መጽዋቹን ብቻ አይደለም፡፡ የአካባቢያቸውን ሰዎች ጭምር ነው፡፡ ‹‹ለማኝ ሆነች›› እንዳይባሉ ይጠነቀቃሉ፡፡ ለገበያ፣ ለዘመድ ጥየቃ፣ ለለቅሶ ወይም ለፀሎት የወጡ በመምሰል ወደ ልመናቸው ይሰማራሉ፡፡ ስለዚህ ዘወትር ልብሳቸው ፅዱ ከመሆኑም በላይ አንዳች ነገር ማንጠልጠል ወይም ሸጐጥ ማድረግ መለያቸው ነው፡፡ አለማመናቸውም አልፎ -አልፎ በፈራተባ ነው፡፡ የሚያውቃቸው ሰው እንዳያጋጥማቸው አብዝተው ይገለማመጣሉ፡
በየኔ -ቢጤ ወግ አንድ ቦታ ቆመው ሳይሆን በቀስታ ከላይታች እያሉ መንገደኛ መለመንን ይመርጣሉ፡፡
ለማንም ሰው ግልፅ እንደሆነው የእነዚህ እናቶች ኑሮ ሰቀቀን የሞላው ነው፡ በእድሜ መገባደዳቸው ላይ ያጋጠማቸውን የተዋረደ ህይወት ለመቀበል አለመቻላቸው ሰቀቀናቸውን ያከፋዋል፡፡ ምናልባትም ወደ ጎዳና ለመውጣት ከመወሰናቸው በፊት እጅግ ብዙ ጊዜያትን ከነችግራቸው ለመሞት ባዶ ታቸውን
ዘግተው ቆይተውም ይሆናል፡፡ አማራጭ የሌለው የልመና ኑሯቸው የዚህ ምድር ህይወታቸው መጠናቀቂያ መሆኑ ለማንም የማያጫውቱት ቅሬታቸው ነው፡፡
ለመሆኑ ጉዟችን ወደፊት ነው ወደኋላ ? ጥንታዊ ማህበረሰብ ነበር አዛውንቶቹን እንደሚጥልና ለቀን ጅብ እንደሚሰጥ ከታሪክ ድርሳናት ያነበብነው፡፡ ቀደም ሲል ያነሳነው ጥንታዊ ታሪክ ፀሐፊ ሔሮዶቱስ ‹‹ሽማግሌዎቻቸውን እንደ አበቃለት እቃ በመቁጠር ይጥላሉ፣ ይገድላሉ›› በሚል የሚወቅሳቸው ጎሳዎች ነበሩ፡፡ እናስ ? እኛ እንዚያ ጐሳዎች ድርጊትና ዘመን ላይ መድረሳችን ጓዟችንን ወደፊት (ወደ ሥልጣኔ ) ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ?

አዛውንቷ ሻያቸውን እያገባደዱ ነው፡ ብሶታቸው በነገር ዘንግ ቆስቁሼባቸዋለሁ፡፡አይናቸው ላይ እንባ አንቆርዝዟል፡፡ ልባቸው ላይ ተስፋ ተንጠፍጥፏል፡፡ ከእኔና ከአካባቢው መራቅ ፈልገዋል፡፡ እጄን ወደኪሴ ከትቼ ዘረጋሁላቸው ገጣሚ ደበበ ሠይፉ እንዲህ ያለችውን እንበለ -ደግነት ‹‹የንፉግ ምፅዋት›› ይላታል፡፡ ከንፈር ከመምጠጥ ያልዘለለች፡፡ ለሴትየዋ ግን እንደዚያ አልነበረም፡፡ መጀመሪያ ደነገጡ፣ ከዚያም ለእሳቸው የተዘረጋ እጅ መሆኑን አረጋገጡ፡፡
ስሜት ፈንቅሏቸው ብድግ አሉ፡፡ ብሩን ከእነእጄ ይዘው ወደ አፋቸው በማስጠጋት ሳሙት፡ ተቀበሉኝ፡፡ ተቁነጠነጡ፡፡ የሰጠኋቸው ጥቂት ነው፡፡ እዚያ ግን ወና ቤት እና አፍን ያላሟሸ ሥራ -ፈት ልጅ አለ፡፡ ለእነሱ ጥቂት አይደለም፡ ነጠላቸውን በጥድፊያ ከላያቸው ላይ ገፍፈው ጥለቱን ዘቀዘቁ፡፡ ለቅሶኛ መሰሉ፡፡ ለሚያውቃቸው ተመልካች እየተወኑ እንደሆን ገብቶኛል፡፡

‹‹አሁን ወዴት ይሄዳሉ ?›› ስል ጠየኳቸው፡፡ ‹‹ወደ አትክልት ተራ፡፡ ከዚያ ወደ ቤቴ›› ለዛሬ የአዛውንት ወግ ሊደርሳቸው እንደሆን ገብቶኛል፡፡ ምናምኑን ለማዘጋጀት ቤታቸው ውስጥ ጉድ -ጉድ ይላሉ፡፡ ምናልባት እስከ ነገና ከነገ ወዲያ ቀድሞ ያጡትን የሞላለት ቤት ያገኙ ይሆናል፡፡ ጥቂት የማይባል ምርቃት አዥጐድጉደው በሀገር ፍቅር ዳገት ሽቅብ አመሩ፡፡

የአንድ ሰው ምፅዋት ከምን የቀን ጅብ ሊያስጥል ? ከምን ችግር ሊያስጠልል ? መንግስት የጣለውን ግለሰብ ያነሳዋል ? ዘመን ያባረረውን አንድ ሰው ያስጠጋዋል ? ለመሆኑ ወደ ልማት እየተጓዝን ነው ወይንስ ወደ ውድቀት ? ሰውን ያላማከለ ስልጣኔ መዳረሻው ምንድን ነው ? ኑሮ ላይ ያልታየ እድገት መለኪያው ምን ሊሆን ነው ? አለ ያልነው አድሮ እየሻሸረ፣ የጨበጥነው ህይወት ላይ ዋስትና ካጣን የራዕያችን መቆናጠጫ የት ላይ ነው ?...ኤጭ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጋንች .

ጀማሪ ኮትኳች


Joined: 16 Dec 2011
Posts: 99

PostPosted: Mon Mar 19, 2012 9:51 pm    Post subject: Reply with quote

""እድገት ያመጣው የዋጋ ግሽበት ነው ሲባል ግርም ይለኛል ""
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia