WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
....... .... ....

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2615

PostPosted: Fri Mar 23, 2012 5:46 am    Post subject: ....... .... .... Reply with quote

ፕሌቶ /ፕላቶ /ፑልቶ / ....

ፍጥረት ሲጀምር ይለናል ግሪካዊዉ ፈላስፋ ..... ፍጥረት ሲጀምር ሰዉ ጾታ አልባ ነበር :: አሁን የምናዉቃቸዉ ወንዶች ያኔ ወንድ አልነበሩም ..... ሴቶቹም እንዲሁ ለማለት ነዉ ::

ብቻ የሆነ አጠር ደልደል ያለ ቀይ ይሁን ጥቁር ለመለየት አዳጋች ... ምናልባትም ወይኖ የምንለዉ የከብት የቆዳ ስብጥርን የሚያስታዉስ ይመስለኛል :: ይመስለኛል ::

ይህ ቀዳሚ ሰዉ .. አራት እግሮች ነበሩት :: አራት እግሩ ሊደንቃችሁ አይገባም .... ሁለት ፊትም ነበረው (አራት አይኖች ) ... እነዚህ ፊቶችም በአንዴ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያዩ መስሏችሁም እንዳትሸወዱ ..... ሁለት ጀርባቸዉ የተጣበቀ ሰዎች አስቡ ... ስታስቡ ታዲያ ዝም ብላችሁ እንዳታስቡ .... በዛኛዉ ጀርባ የወንድ ብልት ሲኖር በዛናዉ ደግሞ የሴት መሽኛ አለ .... የሴት መሽኛ ::እጆቹም አራት ናቸዉ ::

በዚሁ ሰዉ ፍጥረት ..... ፍጥረቱ የተጎናጸፈዉ አፈጣጠር ቅናት የፈጠረባቸዉ የግሪክ አማልክት ( ቅናቱ ለቅናት ብቻ የተቀና አይደለም .... የፍጥረቱ አይደክሜነት ቢሄድ ቢሄድ አይደክመዉም ባለ 4 እግር ነዉና ... ... ሀብታምም ነዉ ... የሚሰሩ 4 እጆች አሉትና ... ጠንቃቃነቱስ ቢሆን ሁለቱ ፊቶች በአንዴ 360 ዲግሪ ማየት ይችላሉና ) .... በዚህ ፍጥረት ቀዳሚ ቀናተኛዉ ዚየስ ሲሆን እነ አፍሮዳይትና ኪዩፒድም የቀኑ መሳይ አማልክት ነበሩ :: አልቀኑም ግን ምክንያት ? ምክንያቱማ የዚየስ ቅናት ለነሱ የሚያመታዉ በረከት አለ (የፍቅር አማልክት አይደሉ ? ) ...

ታዲያ ከአማልክቱ ጉባኤዎች በአንዱ ዚየስ ይህንን ሀይለኛ ፍጥረት ሀይሉን ልቀማዉ እችላለሁ ብሎ እቅዱን ለማህበሩ አቀረበ .... ተጨበጨበ :: ጭብጨባ ያኔ ሳይጀመር ቀረ የልብህን በልብህ ይዘህ እጆችህን በማምታታት ድምጽ የምታስወጣ ... :: ኤኒዌይ ተጨበጨበ ... እቅዱም ይህንን ፍጥረት በብረት መብረቅ ለሁለት መተርተርና ሁለት ደካማ ፍጥረትን መፍጠር ::

ተተገበረ ....
ዉጤቱ
1. ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ....
2. የሰዉ ጥንካሬ ተዳከመ ... (የወንዱ ጥንካሬ በሴቷ ... የሴቷ በወንዱ ተካፈለ (ተጋሩት ? )) ...

የዉጤቱ ቀጣይነት ለምን በቁጥር 1 ላይ የሰፈረዉ ሆነ ሲባል .... ሆነ በቃ !!! አይባልም ? አይባልም .... የአንዱ ጥንካሬ ሙሉ እንዲሆን ከሌላዉ ወስዶ ለመሙላት ..... ወይንም የአንዱን እንጥልጥል ትርፍ ከሚሆን ማስቀመጫ ቦታ ፍለጋ ? (ደካማ መላምት ):: የሆነዉ ሆኖ እዉነታዉ አካላዊ ጥምረቱ በመንፈስ ሲታጀብ ቅኒያዊ ገጽታዉ ጥንካሬን ፍለጋ (ምናልባትም አህያ በወለደችዉ ታርፋለችም ሊሆን ይችላል ) .... ሰሙ ደግሞ ወሲብ ነዉ :: ሰዉ እንዳለመታደል ሆኖ ሰሙን ያስቀድማል .... በአቦ ሰጥ ሚኒስትሪ እንደሚያልፉ ሰዎች ... ሰሙን ሲፈልጉ ወርቁ ከች ሊል ይችላል ... ::
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Mar 23, 2012 7:37 am    Post subject: Reply with quote

ሚኒስትሪ ስትል ያኔ ከመፈተንህ በፊት ቁንጮህን ሳትላጭ ላጭተህ ቁጭ ያረግሀቸው የበዓሉ ግርማ መጽሀፍት ትዝ አሉኝ Laughing ይሄም እንግዲህ በጊዜው ጭጭ ካረግሃቸው ከትውስታ ማህደርህ ውስጥ አንዱን መዥረጥ አድርገህ መሆኑ ነው Laughing ..... አንዳንዱ ሲፈጠር እንዲህ እንደ ሙዝ እንዲቀድድድድ ሌላው ' እንደኔ የተጻፈን ሁሉ እያነበበ እንዲስቅ ፈርዶበታል Laughing ...ሙዝነት ሰላም ነህ ግን Rolling Eyes
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 313

PostPosted: Fri Mar 23, 2012 1:43 pm    Post subject: Reply with quote

ሙዝ ሚስቲቱ እንደገና አረገዘችልህ መሰለኝ እንደ አይነስታይን ፍልስፍና ገባህ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2615

PostPosted: Sun Mar 25, 2012 11:56 am    Post subject: Reply with quote

-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ሙዝ ሚስቲቱ እንደገና አረገዘችልህ መሰለኝ እንደ አይነስታይን ፍልስፍና ገባህ

ቂቂቂ .... አነስታይን ሁለተኛዉን ሲያገባ ነዉ እንዴ መፈላሰፍ የጀመረዉ ? Wink .....

ጽሁፉ ከባለቤቴ ማርገዝ ባይገናኝም .... ወይንም እሱን አስመልክቶ ባይሆንም .... ባለቤቴ አርግዣለሁ መሰለኝ እያለች ነዉ Laughing .... ደስታ .... ደስታ .... በጣም ብዙ ደስታ ነዋ ብያለሁ ...... ልጅ አይጠገብ ነገር .... ተፈጥሮ እስከፈቀደላት ድረስ እንድትወልድ ፍላጎቴ ነዉ .... ክብርነቷ እጎዳለሁ ምናምን ካላለች መዉለድ ነዉ :: እናቴ እንደዛ ስል ሰምታኝ ..... ኤልፎራ አደረካት እንዴ ብላኛለች Wink (የኤልፎራ ዶሮ ... ዶሮነቱ የሚታወቀዉ ወይንም የሚፈለገዉ በሚጥሉት እንቁላል መጠን ነዉ አይነት ነገር ) .....
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እህምም

አለቃ

Joined: 19 Dec 2005
Posts: 2392
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PostPosted: Mon Mar 26, 2012 2:22 am    Post subject: Reply with quote

ሙዝ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ሙዝ ሚስቲቱ እንደገና አረገዘችልህ መሰለኝ እንደ አይነስታይን ፍልስፍና ገባህ

ቂቂቂ .... አነስታይን ሁለተኛዉን ሲያገባ ነዉ እንዴ መፈላሰፍ የጀመረዉ ? Wink .....

ጽሁፉ ከባለቤቴ ማርገዝ ባይገናኝም .... ወይንም እሱን አስመልክቶ ባይሆንም .... ባለቤቴ አርግዣለሁ መሰለኝ እያለች ነዉ Laughing .... ደስታ .... ደስታ .... በጣም ብዙ ደስታ ነዋ ብያለሁ ...... ልጅ አይጠገብ ነገር .... ተፈጥሮ እስከፈቀደላት ድረስ እንድትወልድ ፍላጎቴ ነዉ .... ክብርነቷ እጎዳለሁ ምናምን ካላለች መዉለድ ነዉ :: እናቴ እንደዛ ስል ሰምታኝ ..... ኤልፎራ አደረካት እንዴ ብላኛለች Wink (የኤልፎራ ዶሮ ... ዶሮነቱ የሚታወቀዉ ወይንም የሚፈለገዉ በሚጥሉት እንቁላል መጠን ነዉ አይነት ነገር ) .....

Laughing such a breath of fresh air...thanx for the laugh Smile
_________________
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09/homage-to-darkness/

"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia