WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
መነበብ ያለበት ጽሑፍ ....

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Apr 13, 2012 7:21 pm    Post subject: መነበብ ያለበት ጽሑፍ .... Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን :-

የሚከተለው ጽሑፍ ለንባብ ከበቃ ሠንበትበት ያለ ነው :: ነገር ግን እጅግ መሠረታዊ ነጥቦችን የሚያነሣ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እየተቀባበሉ እንዲያነቡት እመክራለሁ :: እኔ በተለይ 'ኢትዮጵያውያን ' እንዲያነቡት የማሣሥበው ሌሎች ኢትዮጵያዊነት የማይመለከታቸው ወይም ኢትዮጵያዊነታቸውን የካዱ ግለሰቦች የራሣቸው የሚሉት ማንነት የፈጠሩ ስለሆነ አደጋው እነርሱን አይነካም ::

አዲሱ ተስፋዬ መንግሥቱ : ጥር 6 ቀን 2004 .. :: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን የማፈራረስ ሴራና ትግበራ፡ ከደደቢት እስክ አራትኪሎ ቤተ ክህነት ::

Quote:
“የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል”

Addisu Tesfaye Mengistu

የህወሀት ( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በቅርቡ A Political History of the Tigray Peoples Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ÷ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ÷ ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ÷ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች÷ ስለ ጦርነቱ ÷ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።

እኔን ግን የሳበኝ ህወሀት ወይም ወያኔ ÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ ከበረሀ ጀምሮ የሰራውን ደባ የሚያትተው ክፍል ነው።ዶክተር አረጋዊ በዚሁ መጽሀፋቸው ምእራፍ አስር ላይ Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ህወሀት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደተዋጋትና አሁን ቤተ ክርስትያና ውስጥ የሚታዩት አበይት ችግሮች በሙሉ ህወሀት ከበረሀ ጀምሮ ያቀዳቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጠውታል።

ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ ?

ይህን መጽሀፍ ሳነብ ዋናው ጥያቄዬ የነበረው “ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ ? የሚለው ነበር።ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበትን ምክንያቶች ዶክተር አረጋዊ አንድ ባንድ አስቀምጠውታል።በሚገርም ሁኔታ አንዱና ዋናው ምክንያት የቤተክርስትያኗ ብሔራዊ አስተምህሮ ÷ መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ መሆንና በባንዲራና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል።

A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag an act also regularly observed …’ page 244

The pragmatic TPLF understood the churchs role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause page 245

የአኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በህዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና ቤተ ክርስትያና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም እግዚአብሄር የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟና በባንዲራ ላይ ያላት ጽኑ አስተምህሮናና የመገንጠል ተቃዋሚ መሆኗ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ እማኝነታችውን ከገለጡ በሁዋላ ወያኔ ቤተከርስትያኗ ላይ ያሳረፈውን በትር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል።

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ማደንዝዝና መቆጣጠር

በብሔራዊ ማንነትና በሀገር አንድነት ላይ ቤተክርስትያኗ የያዘችው ጽኑ አቁዋም ያበሳጨው ህወሀት ቤተ ክርስትያኗን ለማደንዘዝና ለመቆጣጠር የለኮሰውን ባለ ሶስት ዘርፍ የጥቃት ዘመቻ እንዲህ ሲሉ ይዘረዝሩታል

አንደኛ ቤተክርስትያኗ በህዝቡ ዘንድ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስትያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ

the second step was to try and move the socio economic focus of life from the church to the peoples assemblies. All administrative and social activities were taken over by the associations and the baitos and even church affair such as the rights and obligations of the church and its followers fell under the jurisdiction of the assemblies. The capacity of the church to mobilize and influence waned. The church lost its status as mediator in conflicts, rights over spiritual and familiar issues because the new political authorities.

የሚገርመው ቤተክርስትያኗ በራሷዋ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እንኩዋን ለመወሰን መብቱን አጣች። 1970ዎቹ እና ሰማነያዎቹ ህወሀት ነጻ አወጣሁዋችው በሚላቸው ቦታዎች በሙሉ የቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ውሳኔዎች በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ስብሰባዎች መወሰን ጀመሩ።

ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስትያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስትያኗን አመራረ ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች መተካት እንደነበረ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል

thirdly , the TPLF launched a series of conferences or seminars for selected parish priests in 1970 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigray from the wider Ethiopian Church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial wereda seminars for the priests were conducted by an eloquent TPLF fighter,Gebre Kidan Desta, a graduate of the theological College at Addis Ababa university .The themes of the seminars were to replace the Ethiopian Church authority by TPLF minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity page 246

የቤተ ክርስትያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም በስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ሲባል መዋቀሩን እንዲህ ይገልጹታል

this process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the wel-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo , by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of TPLF

ሌላውና አደገኛው ደግሞ የቤተ ክርስትያኗን አመራር ለሁለት የመክፈል ጉዳይ ነው

1987 እና 1989 (ኣኤአ ) ትግራይ ያለውን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስትያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስትያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ከበረሀ ጀምሮ የታሰበበትና የተተገበረ ጉዳይ መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ እንዲህ ገልጸውታል

in 1987 and 1989 ,regional and national conference for priests were organized by the TPLF in liberated territories to reshape the Tigray Church in line with the TPLF program . A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of Tigray and was supposed to operate under TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to two secretariats…’

አራት ኪሎ ቤተ ክህነት

ዶክተር አረጋዊ በርሄ የጻፉት ይሄ ሁሉ ሴራ የተጎነጎነውና የተተገበረው ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ በረሀ ላይ እያለ ነበር።ወያኔ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በሁዋላ በቤተ ክህነቱ ዙርያ ምን ተፈጸመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስና በበረሀ ታቅደው መተግበር ከጀመሩት ሴራዎች አንጻር ለመመልከት ውሳኔዎቹንና እቅዶቹን ደግመን እንያቸው

1. ቤተክርስትያኗ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስትያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባአኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ
2. የቤተ ክርስትያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማሰመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና ማስሾም
3. የቤተ ክርስትያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስትያኗን አመራር ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች ማስያዝ
4. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስትያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስትያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል
ያልተፈጸምው የቱ ይሆን ? የኢትዮጵያ ትዋህዶ ቤተ ክርስትያን በሁለት ሺህ አመት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲኖዶሷ ለሁለት ተከፍሏል።የቀድሞው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔም ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ እንደገለጹት አባ መርቆሬዎስ ከሀገር የወጡት በፖለቲካ ውሳኔና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ ነው።ከዚህም ጋር ተያይዞ የቤተ ክርስትያኗ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሏል።

የቤተ ክርስትያን ጉዳዮች በቤተ ከርስትያን ሲኖዶስ ሳይሆን በሌሎች አካላት እንደሚወሰን ያባ ጳወሎስ ሀውልት ህያው ምስክር ነው።ሲኖዶሱ ይፍረስ ብሎ ቢወስንም “የማይፈርሰው ሀውልት ብለው የወሰኑት “ምእመናን” ውሳኔ እንደጸና የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው።

ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ ፖለቲካ የሚሰብኩ ጥቁር ራስ መነኮሳትና ነጭ ለባሽ ካህናት በየቤተ ክርስትያኑ ማየትና ማድመጥ የተለምደ ከሆነ በርካታ አመታትን ተቆጠሩ።ሌሎቸም ብዙ ጉዳዮች ሆኑ።

ለጊዜው ሁሉም እቅድ የተሳካ ይመስላል።የመውጊያው ብረት ላይ መቆም ተቸሏል። ለማን እንደሚብስ ግን ወደፊት የምናየው ይሆናል። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል” የሐዋርያት ስራ 9 5 የእግዚአብሄርን ለቄሳር አሳልፈው የሰጡ “ሐዋርያትም” ስላፈሩት ሰልሳና መቶ ከግብር አባታቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ።የቤተ ክርስትያን አምላክም ቤተክርስትያንን ይጠብቃል።

ይቆየን
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia