WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ ::
Goto page Previous  1, 2
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Thu May 10, 2012 6:25 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ክቡራን ወዳጄ

እንደው ከማለፍህ በፊት ወደነጥቤ መለስ ብትልልኝ ብዬ ነው እነዚህ አረቦች ለሽብር ይምጡ ወይንም ሲኒማ ራስ ጫት ለምግዛት ይምጡ በግዜ ሊጣራ የሚችል ጉዳይ ሆኖ ዋናው ነጥቤ ግን ዜናውን (የዜናውን አቀራረብ ) ከጆርናሊዝም ኤቲክስና ፕሪንሲፕል አንጻር እንዴት ትመለከተዋለህ ?ዜናው ተአማኒ ሊሆን የሚችልበትን መስፈርት አሟልትዋል .ወይ ? የሚል ስለሆነ ይህን አትኩሮት ብትሰጠው

የሀጂ አበሻ እና ሌሎች ያነሳሀቸውን ነጥቦች ቀጥለን ልናየው እንችላለን

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Thu May 10, 2012 6:25 pm    Post subject: Reply with quote

አሰላማለኩም ወበረካቱ ወስብሀቱ ..ወዳጄ ወልደያ መጣሁልህ ደሞ ተሸላልሜ ( ማለቴ ባርትክል ) ... Very Happy ስላ ኢትዮጵያዊው ነቢይ ሀጂ አበሻን በተመለከተ የአል አባሽንና አል ዋህቢያን አነሳስ የዳስሰ ድረስ አንድ ጆርናል አገኘሁልህ :: በምራቡ አለም ኢትዮጵያ የክርስታያን ደሴት ተብላ ለዘመናት እንደምትታወቅ ይጠቅስና ለኢትዮጵያ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እንደውም ኢትዮጵያ የእስላም መቀነት እንደሆነችም ይናገራል አርትክሉ :: አንዳንዴ ነቢይ ባገሩ አይከበርም የሚለው የአባቶች አባባል ፊቴ ላይ ግጥም ይላል :: ጸሀፊዎቹ ሙስጠፋ ካሀባና ሀጂ ኤሪልክ የዩነቨርስቲ ሌክቸረሮች ናቸው :: አርትክሉ በመካከለኛው ምስራቅና በኢትዪጵያውያን ሙስሊም መካከል ስላለው ታሪካዊ ግኑኝኝነት ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሂጅራ እንደተኬደባት አስረግጦ የግኑኝነት መስመር ለምን ዛሬ እስላማዊ የመወያያ አጀነዳ ሆነ ሲልም ይጠይቃል :: ስለ አል ሀባሽና አል ዋህቢ አጀማመርና አነሳስ በመስመር በመስመር እያፍታታም ያስረዳል : : ጠለቅ ያለ ጥናት ያለበት ጽሁፍ ነው :; እስኪ ባንተ በኩል እንዴት እንዳየሀው ንገረኝ :: ሰለ ዜናው አውቲንሰቲነት , ፈየርነስ , የጆሪናሊዝምን ኢቲክስ መከተሉን በተመለከተ እመለስበታለሁ :: ኢንሻላህ !! Cool
http://aigaforum.com/documents/Al-Ahbash-whaibyya.pdf

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Sat May 12, 2012 7:36 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም ክቡራን

ሀጂ አበሻ ወደነብይነት አደጉ እንዴ ? ብዬ የሰጠኽኝን ሊንክ ለማንበብ ስሞክር the file is damaged ይላል ስለዚህ ላነበው አልቻልኩም ሆኖም ቁም ነገሩ ግን ሀጂ አበሻ መቼ ተወለዱ ምን አደረጉ የት ሄዱ የሚለው አልነበረም መወያየት ያለብን መርሑ ላይ ነው

-ሀጂ አበሻ (አሕባሽ ) ማስተማር ይችላሉ ወይ ? በሚገባ ይችላሉ እያስተማሩም ነበር መርከዝ (ማእከል ) ነበራቸው አሁንም አላቸው

-ሓጂ ስለፊስ ማስተማር ይችላሉ ? በሚገባ ይችላሉ በማስረጃ የሚታስተምሩት ሀይማኖት ብቻ እስከሆነ ድረስ !

ትክክለኛውን መምረጥ የሚችለው ማን ነው ? መንግስት (መጅሊስ ) ወይንስ ህዝቡ ?

-መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ መግባት ይችላል ? "ህገ መንግስት " መሰረት አይችልም ስለዚህ ህገ መንግስቱ ይከበር !

ሰለዚህ የተወሳሰበ ነገር የለውም መብት የመጠየቅ እንጂ ሌላውን የማገድ ጥያቄ አይደለም ::

_____________________
_____________________

ወደ ጋዜጠኝነቱ እንመለስ

እንደሚታወቀው ፖለቲከኛና ጠበቃ ሀይለኛ ውሸታም ናቸው
ጋዜጠኛ ደግሞ ይህን ለማጋለጥ እስከ ህይወት መስዋእትነት ይከፍላል

አቶ መለስም ከሌላው ፖለቲከኛና መሪ የተለየ ቅዱስ ሊሆኑ ስለማይችሉ ሊዋሹ ይችላሉ

ችግሩ እሱ አይደለም ችግሩ በረከት ስሞኦን እሱን ይደግማል አባይ ጸሀዬ ጁነዲን ሳዶ ... እሱኑ ይደግሙታል .. ፓርላማውም በከፍተኛ ድምጽ ያስተጋባዋል ኢቲቪ እና ሬድዮ 24 ሰአት ይደጋግሙታል ስለዚህ እንኳን ሌላው አቶ መለስም የተናገሩ እውነት እንደሆነ እርግጠኛ እየሆኑ ይመጣሉ ስለዚህ በሚቀጥለው ለሚናገሩት እምብዛም ጥንቃቄ አያደርጎም ምክንያቱም ሲስተሙ ውሸትን ወደእውነት አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ እውነትን ደግሞ ወደውሽት መቀየር እንዲችል ሆኖ የተዋቀረ በመሆኑ !

ለነሱም ግን አንድ ችግር አለባቸው ዘመኑ የኢንፎርሜሽን መሆኑ ! ድሮ አባቴ 9.00 pm, እየጠበቀ አሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ሲጎረጉር ትዝ ይለኛል በከባዱ ተደብቆ ሌላ የኢንፎርሜሽን ምንጭ እጅግ ውስን ነበረና

አሁን ግን ዘመኑ ተቀየረ ሳተላይት ቲቪ ኢንተርኔት ...ኢንፎርሜሽን ጣታችን ላይ ሆነ ስለዚህ ኢቲቪ ውሸትን በመደጋገም ወደእውነት የመቀየር ሀይሉ እየደከመ መጣ ስለዚህ ከዘመኑ ጋር ለመራመድ እውነት መናገር ባይችል እንኳን ውሸቱን ይበልጥ ማሳመርና ተወዳዳሪና ገዢ የሚያገኝ ውሸት አድርጎ ማቅረብ አለበት ትልቅ ውድድር ያለበትም ከናንተ ነጻ ጋዘጠኞች እንደመሆኑ ነበር ጥያቄዎችን ያቀረብኩልህ

ስለዚህ ኢቲቪን እንደመረጃ እንድታቀርበው ሳይሆን በነጻ ጋዜጠኛ እይታ እንድትገመግመው ነበረ አጠያየቄ

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Sat May 12, 2012 1:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወልድያ ወንድሜ እንደምነህ ? የላኩልህ ጆርናል የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ውስጥ ይገኛል :: እኔ ያለ ችግር ይከፈታል :: ምናልባት አዶቢ ኦፕነር ኮምፒተር ላይ ካልጫንክ ወይም አፕ ዴት ካላደርክ ሊያስቸግርህ ይችላል :: ጆርናሉ ወደ 21 ገጽ አለው :: ስሎው ኮኔክሽን ከሆነ ያለህ ላይከፍተውም ይችላል .. ግን በቀጥታ ካምሪጅ ዪኒቨርስቲ ፕሬስ ብለህ ሰርች አድርግና ባውተሮቹ ስም ሙስተፋ ካሀባና ሀጂ ኤልሪክ ብለህ ፈልገው ..ምናልባት ይሄኛው ሊንክ ሊረዳህ ስለሚችል ቼክ አድርገው .. http://www.jstor.org/action/showPublisher?publisherCode=cup& ጋዜጠኝነት ለኔ ሲምፒል ነገር ነው ...መሬት ላይ ያረፈውን እውነታ ለሌላ ማሳየት ነው :: ፋክት ኦን ግራውንድ እንዲል በርናድ ሾው . Smile እንዳልከው ጋዜጤኛ በፖሊተከኞች ""ቲውሲት "" ሳይደረግ በራሱ እምነትም ""ቲዊስት "" ሳይደረግ እውነቱ ይሄ ነው ብሎ መግለጽና መናገር አለበት :: እነደዚህ አይነት ጋዜጠኖች እንዲፈጠሩ ደሞ ነጻ ሜዳ ነጻ ብእር መኖር አለባቸው :: በምእራቡ አለምና ባሜሪካ የምናየውን አይነት የዜና አቀራረብና ነጻነት ወዳ አፍሪካ ስንወርድ ላናየው እንችላለን :: በስጋት የሚኖር ሰው የሾለ ብእር ይፈራል :: አልጋውን በዛፎች ቅርንጫፍ ላይ ያደረገ ሰው ሁሌም የሰላም እንቅልፍ መተኛት እንደማይችል የታወቀ ነው :: ነጻ ህሊና ያለው በሚሰራው ስራ ሙሉ እምነት ያለው ባለ ስልጣን ወይም መንግስት ግን ምንም አይነት የሾለ በእር ይኑር መፍራት የለበትም ባይ ነኝ አሳማኝ ምንጭ ያለው መረጃ እስከተዘገበ ደርስ :: " ትሩዝ ሴት ፍሪ "" ይላ ቅድሱ የእጊዘአብሄር ቃል :: "" እውነት ነጻ ታወጣሀለች እንደማለት ነው :: እና ለኔ ጋዜጠኝነት በውነትና በሀሰት መካክል ያለ ""ሊትማስ ፔፐር "" ነው :: ሜዳው ካለህ መጻፊያው ካለ . ነው እንግዲ ...ይሄ እምነቴ ነው :: ወደ ዜናው ስንሄድ ደሞ የግድ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበ ነገር ሁሉ ፕሮፓጋንዳ ነው ብዬ አልወስድም :: አዎን የመንግስትን ሀሳብ ያንጸባርቃሉ ..ያስፈጸማሉ መረጃዎችን ከመንግስት በኩል እየሆነ ይሰጣሉ :: ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ፍቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖሎቲካ ድርጅቶችም በመንግስት ሚዲያ ድምጻቸው እንዲሰማ ቢደረግ ኢቲቪን ይበልጥ አሁን ከሚያደርገው በላይ ተአማኒ ሊያደርገው በቻለ ነበር :: ቫልዩውንም ይጨምርለት ነበር :: ብዬ ይሄን ካልኩ በኌላ ግን የሁለቱን አረቦች ጉዳይ በተመለከተ እኔ በመንግሰት የተቀነባበረ ፕሮፓጋንዳ ነው አልለውም :: መሬት ላይ ያረፈውን እውነት ነው አንስቶ ለህዝብ ያቀረበው ነው የምለው ..:: እነዚህ ሰዎች ( አረቦቹ ) እኮ ማሽኖች አይደሉም ...ተረሪስት ናችሁ ሲባሉ አፋቸውን ለጉመው አዎ ነን ብለው መቀበል የለባቸውም :: ቃሊቲ አልወረዱም አለም በቃኝ አልሄዱም ...ራሳቸውን ክሊር የሚያደርጉበት ሰፊ አጋጣሚ አላቸው ...ከቦሌ ተነስተው አገራቸው እንደገቡ እኮ ሲሻ ቤት ፈልገው ዱቅ እኮ ነው ያሉት :: ""ተሰድበናል ተዋርደናል መብታችን ተገፍቷል ...እንደ አሸባሪ ታይተን 24 ውስጥ ካገር እንድንባረር ተደርገናል "" አይሉም እንዴ ? ላገራቸው መንግስት አያመለክቱም ?? ለሎካል ሚዲያ አይናገሩም ...ይሄ የኢትዮጵያን መንግስት እንኴን ለዜጎቹ ለኛ ለውጭ ዜጎች እንኴን ፌየር ያልሆነ ነው ብለው መክሰሰ የሚችሉበት አጋጣሚ አይሆንም ነበር ?? ይሄ ደሞ ለነሱ "" ሊፕ ሰርቪስ "" ብቻ ሳይሆን እስከ ካሳ ድረስ ሊያስገኝላቸው ይችል ነበር እኮ !! ዝም ብለው እንደ ዶሮ ቆጥ ላይ ይጫናሉ እንዴ ? ምን አስፈራቸው ?? እውነትን የያዘ ሰው እኮ አይፈራም !! ለምን ? ያሉት ከኢትዮጵያ ክልል ውጭ ነው ;; አንተ እንደጠቀስከው ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው በኢንተርኔት በዩ ትዩብ በብሎጎች ላይ ሳይቀር ""ስላት ለማድረግ አንዋር መስጊድ ደረስ መጠተን እንደ አሸባሪ ታይተን ተባረናል ...የህግ ያለህ የጀስቲስ ያለህ ..!!" ለምን አይሉም ? እኔ አልሰማሁም :: ከዚህ አንጻር ሳየው ለኔ ዜናው ፕሮፓጋንዳ አይደለም :: እውነት ነው :: እውነት ካልሆነ መንግስት ለራሱ ቤኔፊት ሲል ዜናውን ካቀረበው እነሱ ራሳቸውን ዲፌንድ ማድረግ አለባቸው :: ባስተረጔሚም ቢሆን ዋርካ መጠተው ለኢትዮጵያውን መናገር ይችላሉ .. ለማሰተርጎሙ ምክክር አለ ..እረ እንደውም ብትጠይቀው ስልካቸውንም ይነግርሀል :: ሰላም ሁንልኝ ወንድሜ ወልደያ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Sun May 13, 2012 7:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ክቡራን
አንት እንደገለጽከው

Quote:
ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል

ይህ ነው ዜናው ኢቲቭ ደግሞ ስማቸውን ጠቅስዋል

በቃ መረጃው አንድ የመንግስት ባለስልጣን ናቸው በሌላ መንገድ ዜናው እንዳይጣራ የምን አገር ዜጎች እንኳን አልተገለጸም የሽበር ወረቀቶች ሲበትኑ አይተናል ያሉ እማኞች አልቀረቡም ድፍንፍን ያለና ተድበስብሶ የቀረበበት ምክንያት ምንድነው ? እነሱም የቀረበባቸውን ክስ እንዳይሰሙና እንዳያስተባብሉ በችኮላ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ተደረገ ነው የተባለው ዜናው ምንም አይነት ነጻ የሆነ የማረጋገጫ መንገድ የለውም :;

ኢቲቪ :: ኢቲቪ ከዚህ ቀደም ባድሜ ለኛ ተወሰነልን ብሎ ህዝቡን አደባባይ አውጥቶ ያስጨፈረ እንደነበረ አትዘነጋውም በዛው ምላሱ ተመልሶ የድምበር ኮሚሽኑን ያወገዘበት ስዩም መስፍንም ሁለት ምላስ በድፍረት የተናገሩበት ... ይህ ግዙፍ ውሸት የመንግስት ባለስልጣናትንና ኢቲቪን ብቻ እንደተአማኒ የዜና ምንጭ ማቅረብ እንደማይቻል ያሳያል

አንተ ባልከው መንገድ ሰዎቹ ለምን አልተቃወሙም ማለት አይቻልም ሰዎቹ ጫፋቸው አልተነካም (ይህን ግዙፍ ለአገሪትዋ አስጊ የሆነ ድርጊት ፈጽመው ሳለ ) ከሀገር እንዲወጡ ለነሱ የተሰጣቸውንም ምክንያት አናውቅም አቶ መለስ ሲናገሩ የአይናቹህ ቀለም ደስ አላለንም ብለን ማስወጣት እንችላለን ብለዋል እውነት አላቸው ደስ ያላላቸውን ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ለማስወጣት ምክንያት አይስፈልጋቸውም ትልቁ ችግር ለምን ምርመራ አልተካሄደባቸውም ? የሚለው ነው አንተ የዲፕሎማሲ ችግር ለጥበቃ የሚከፈል ብር አለማግኘት ... እንደምክንያት ጠቅሰሀል ግን ከዚህ እጅግ የከፋ የዲፕሎማሲ ችግር የሚያስከትለው የስዊድን ጋዘጠኞችን ማሰር ነው ስዊደን በስንዴ የምትደግፈን አገር መሆንዋ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ ህብረት ላይ ባላት ተሰሚነት ምክንያት አውሮፓ ህብረት ላይ ልታሳርፍው በምትችለው ጫና ጭምር ! አውሮፓ ህብረት ማለት ደግሞ የአገሪትዋን በጀት ከፊሉን የሚዘጋ ነው ወይንም ነበረ (አሁን በቀውስ ላይ ስለሚገኙ ምናልባት ላይረዱ ይችላሉ ) በጠበቃ ወጪ ረገድም መቅዋቅዋሙ የሚከብደው የስዊድን መግስት ሊቀጥር የሚችለውን ጠበቃ ነበረ ! ከዚህ ሁሉ ጋር ግን መንግስት ጋዜጠኞቹን ማሰር የሚያስችለው ምክንያት ነበረው ያለፈቃድ አገሪቱ ውስጥ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገብተዋል ገብተውም ከኦብነግ ወታደሮች ጋር ተይዘዋል ! የሚቀርብ ኬዝ አላቸው እነዚህ አረብ የተባሉ ሰዎች ግን ቅንጣት የሚቀርብ ኬዝ ቢኖርባቸው ለምን ይለቀቃሉ ? አሸባሪነታቸው ሊረጋገጥ የሚችል ቢሆኑ ደግሞ የአገራቸው መንግስትም እፎይ ብሎ ለአገርራችን መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል እንጂ እንደስዊድን መንግስት አይቃወምም ነበር ምክንያቱ ቀላል ነው ነገሩ ዜና ሊሰራበት የተፈለገ ሴትአፕ ነገር እንጂ ጠለቅ ብሎ እንዲፈለፈል የተፈለገ ነገር ስላልሆነ !(አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዳይሆን ነገሩን ማዳፈን ?) ሰዎቹ እንዳልከው በሰላም ሺሻ እየጠጡ ይሆናል ጫፋቸው ስላልተነካ ምን ፍርድ ቤት አስኬዳቸው ? ፍርድ ቤት መሄድ የነበረበት ዋናው አካል እንኳን አርፎ ተቀምጦ የለ ?

ነጻ ኢንቨስቲጌቲቭ ጋዜጠኛ ግን የነገሩን ስር ለማግኘት የተሸፈነውን ለመክፈት መስራት የሚችል መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ ስዩም መስፍን ባድመ ለኛ ተሰጠ ስላሉ በተለያየ መንገድ ቬሪፋይ ሳይደረግ እሱን እንደፋክት መውሰድ ምናልባት ህዝብን ማሳሳት ይሆናል ነጽ ጋዜጠኛ ቅድምያ ታማኝነቱ ለህዝቡ መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ

ለማንኛውም ሀሳብህን ስላካፈልከኝ ከልብ አመሰግናለው

ሰላም ሁን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ምክክር

ኮትኳች

Joined: 26 Jun 2008
Posts: 244
Location: Super Earth

PostPosted: Sun May 13, 2012 8:33 am    Post subject: Reply with quote

ቂቂቂቂቂ አይ ክቡሻ ቁልትልት ያለ ቅብጥርጥር ፍሬ ቢስ ጽሁፍ .... እያምታታህ ከወያኔ ጋር ትበራለህ ለጉድ .....ለማሳመን ! ማመዛዘን ማብሰልሰል የለም .....ፍሬን የለም ግራ ቀኝ ማየት የለም ልክ እንደ ቅዳሜ ሹፌር ወይም እንደ ሱሉልታ አህያ ወደፊት መርሽ ወያኔን አቅፈህ :: ወያኔ ግን ምን ዓይነት ቆለጥ ቢያጎርስህ ነው እንዲህ እየቆላህ የምታቆላምጣቸው ....መችስ ወያኔን እንዳንተ ማሞላቀቅ የሚያቅበት የተፈጠረ እስከማይመስል ድረስ ሄደሃል :: የወያኔ ቅመም እኮ ነሽ ክቡ ...ጥፍጥ ያለሽ ጣፊጦ ! አንዳንዴ ወያኔ እንዴት ቢከንቱህ ነው እላለሁ እንዲህ አልጋቸውን በሀር ምንጥኣፍ እያሰማመርክ ወለሉን ዳማ ከሴ ጎዘጉዘህ ከስራቸው ተጎዝጉዘህ ከላይ የሚገዘግዙህ ....

አንተ ሀቀኛና ነፃ ጋዜጠኛ አይደለህም .....ክቡ የወያኔ ቃል አቀባይ ነህ :: ቢኮዝ ኖው ...ሲምፕሊ ... ሉክ ላይክ ዋን ኦፍ ዘም .

I Like this quote:
"Journalism allows its readers to witness history; fiction gives its readers an opportunity to live it.

ያንተ ጆርናል እኮ እንደ ወይኔ ለዓመታ የሚቆይ ብቻ ነው ማለት ነው .....gone with the wind
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ካለድ

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Jan 2007
Posts: 594

PostPosted: Sun May 13, 2012 11:18 am    Post subject: Reply with quote

አይ ክቡራን ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አቤት አቤት ጭንቅላት ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ጥሩ ውሽታም እንኮን ነበራቹህ አሁን ተባነነባቹሁ
ወልድይ ................... ደስ የሚል ነገረ ግን አይረዳውም እኮ ነፍዞል ልጁ [url][/url]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
anbissa

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Jan 2009
Posts: 63
Location: australia

PostPosted: Sun May 13, 2012 6:10 pm    Post subject: Reply with quote

እስከ መቸ የሙስሊም የክርስቲያን መብት እያልን ወደህላ እንጋዛለን ? ያሁሉም ህብረተ ስብ ችግር ነው በሀይማኖት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ለሁሉም ዚጋ የመብት ጥያቂ ሁኖ ባንድ ላይ ሆኖ መንቀሳቀስ ያለብን ::እምነት በልብ ውስጥ የሚኖር ነው ህዝበ ሙስሊም ሆነ ክርስቲያን በሽኮች ውይንም በጳጳት ብቻ መሽከርክር የለብንም ዲሞክራሲ ሲኖር ለፍትህ የቆመ መሪ ይፈጠራል ;; አለዚያ የአሽባሪዎች መፈንጭያ ነው የሚሆነው ;;
_________________
n/a
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Mon May 14, 2012 7:39 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወንድሜ ወልደያ :: የላኩልህን አርትክል መክፈት ቻልክ ወይ ...? አነበብከው ወይ ?? ምን ይላል ? እንዴት አየሀው ? እንዴት ገመገምከው ?? እርግጠኛ ነኝ ጥሩ ኮኔክሽን ያለበት ቦታ ፈልገህ ብትከፍተው ለምሳሌ ( ላይብረሪ ውስጥ ) ሊከፈትልህ ይችላል ብዬ አምናለሁ :: ይሄ የሙስሊም ስኮላሮች በኛ በኢትዮጵያው ነቢይ ሼክ አብዱል አስተምርሆትና በዋህቢ አስተምሮት ያለውን ልዩነት በሚገባ ያብራሩበትና ምርምርም ያካሄዱበት ስለሆነ በአርትክሉ ላይ ያንተ ""ኢን ፑት "" (አስተያየት ) በጣም እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው :: እውነትን ለምንፈልግና የሙስሊም እምነት ተከታይ ላልሆንን እኔን ለመሰለ ወንድምህ ያንተ የእምንቱ ተከታይ ደረሳ ወይም ሸክ (ማእረግህን ስለማላውቅ ነው ይቅርታ ) ቀናና እውነትን የለበሰ አስተሳሰብ በጣም አስፈላጊ ነው :: ባአላህም በሰው ዘንድም :: እና እባክህ አርትኩሉን ( ጆርናሉን ) እንድታነበው እማጸንሀለሁ ::
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባንድ ወቅት ስዩም መስፍን ባድመ የኛ ሳትሆን የኛ ሆናለች ብሎ መልክት በማስተላለፉ ቴሌቪዥኑ ዋሾ ነውና ምንም አይነት መረጃ እውነት ሊሆን አይችልም ያልከው ለጀመርነው ውይይት ሰብስትንሺያል ማሳመኛ አይደለም :: በዛ ቲቪ ላይ ቡዙ ውሸቶችም ቡዙ እውነትችም ተስተናግደዋል ...ወደፊትም ይሰተናገዳሉ :: ስዩም ስለ ባድመ ያልሆነ ኢንፎሬሜሽን ሰጠ ተብሎ የአረቦቹ መባረር ፕሮፓጋንዳ ነው ስትለኝ ነጥቦችህን ዲፌንድ ለማድረግ ጥይት የጨረስክ ያስመስልብሀል :: ነገርን ነገር ያነሰዋልና ለመረጃ ያህል እንዲሆንህ ኢትዮጵያ እኮ ዛሬም ባድመን አልለቀችም :: ሄግ ወሰነ አለም ወሰነ ሌላ ጉዳይ ነው ...ውሳኔው የሚረጋው ኢትዮጵያ ስትቀበለው ነው :: ይሄ ከጀመርነው ጉዳይ ጋር ምንም ግኑኝነት ስለሌለው እዚህ ላይ ላብቃና ወደ አል ሀባሻችንና አል ዋህቢያችን ልመልስህ :: አንተ ባታስተምረኝም እኔ ወንድምህ ስለ ኢትዮጵያዊ ሸካችን ሸክ አብዱል ( ያል አህባሽ ትምህርት አስተማሪ እያጠናሁልህ ነው :: እባክህ ቶሎ ቶሎ ብለህ እስልምናን አስተምረኝ ...አለበለዛ ቁርአን ቀሪ እንዳልሆንብህና ያንተን የወንድሜን ድርሻ እንዳልወስድብህ :: ዋናው ሉዩንት ያለው በቁራኑ ወይም በህድሱ ወይም በዲናው ላይ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ :: ልዩነቱ ባስተምሮት ላይ ነው .... ልዩነቱ በሚስጥራት አፈታት ላይ ነው ልዩነቱ በቃላት ያለን አንደርስታንዲንግ መገለጥ ላይ ነው :: የዋህቢም ሆነ ያል ሀባሽ ( የኛ የኢትዮጵያዊ የሸክ አብዱል ተከታዮች ) የሚለያዩት በዚህ እንጂ ቁራኑ ያላህ ቃል አይደለም ወይም የነቢዩ መህመድ ትምህርት ትክክል አይደለም በሚል ተቃውመው አይደለም :: ባጠቃላይ የሙስሊም ስኮላሮች ( ስኩል ኦፍ ቶውት ) ልዩነት ነው :: ይሄን ልዩነት ይዞ አብሮ መኖር ይቻላል :: አንዱ ከሌላው ጋር ቁጭ ብሎ መወያየትም ይችላል :: ማሳመንና መተማመን ይቻላል :: ""ኑና እንዋቀስ "" ይላል ነቢዩ ኢሳያስ በብሉይ ኪዳን ....በመጽሀፍ ቅዱስ "" ሳታጣሩ አትዘይሩ "" ይላል አላህ እኮ ነው በቅዱስ ቁራኑ ... መጣሁ ::

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ክቡራን
አንት እንደገለጽከው

Quote:
ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል

ይህ ነው ዜናው ኢቲቭ ደግሞ ስማቸውን ጠቅስዋል

በቃ መረጃው አንድ የመንግስት ባለስልጣን ናቸው በሌላ መንገድ ዜናው እንዳይጣራ የምን አገር ዜጎች እንኳን አልተገለጸም የሽበር ወረቀቶች ሲበትኑ አይተናል ያሉ እማኞች አልቀረቡም ድፍንፍን ያለና ተድበስብሶ የቀረበበት ምክንያት ምንድነው ? እነሱም የቀረበባቸውን ክስ እንዳይሰሙና እንዳያስተባብሉ በችኮላ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ተደረገ ነው የተባለው ዜናው ምንም አይነት ነጻ የሆነ የማረጋገጫ መንገድ የለውም :;

ኢቲቪ :: ኢቲቪ ከዚህ ቀደም ባድሜ ለኛ ተወሰነልን ብሎ ህዝቡን አደባባይ አውጥቶ ያስጨፈረ እንደነበረ አትዘነጋውም በዛው ምላሱ ተመልሶ የድምበር ኮሚሽኑን ያወገዘበት ስዩም መስፍንም ሁለት ምላስ በድፍረት የተናገሩበት ... ይህ ግዙፍ ውሸት የመንግስት ባለስልጣናትንና ኢቲቪን ብቻ እንደተአማኒ የዜና ምንጭ ማቅረብ እንደማይቻል ያሳያል

አንተ ባልከው መንገድ ሰዎቹ ለምን አልተቃወሙም ማለት አይቻልም ሰዎቹ ጫፋቸው አልተነካም (ይህን ግዙፍ ለአገሪትዋ አስጊ የሆነ ድርጊት ፈጽመው ሳለ ) ከሀገር እንዲወጡ ለነሱ የተሰጣቸውንም ምክንያት አናውቅም አቶ መለስ ሲናገሩ የአይናቹህ ቀለም ደስ አላለንም ብለን ማስወጣት እንችላለን ብለዋል እውነት አላቸው ደስ ያላላቸውን ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ለማስወጣት ምክንያት አይስፈልጋቸውም ትልቁ ችግር ለምን ምርመራ አልተካሄደባቸውም ? የሚለው ነው አንተ የዲፕሎማሲ ችግር ለጥበቃ የሚከፈል ብር አለማግኘት ... እንደምክንያት ጠቅሰሀል ግን ከዚህ እጅግ የከፋ የዲፕሎማሲ ችግር የሚያስከትለው የስዊድን ጋዘጠኞችን ማሰር ነው ስዊደን በስንዴ የምትደግፈን አገር መሆንዋ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ ህብረት ላይ ባላት ተሰሚነት ምክንያት አውሮፓ ህብረት ላይ ልታሳርፍው በምትችለው ጫና ጭምር ! አውሮፓ ህብረት ማለት ደግሞ የአገሪትዋን በጀት ከፊሉን የሚዘጋ ነው ወይንም ነበረ (አሁን በቀውስ ላይ ስለሚገኙ ምናልባት ላይረዱ ይችላሉ ) በጠበቃ ወጪ ረገድም መቅዋቅዋሙ የሚከብደው የስዊድን መግስት ሊቀጥር የሚችለውን ጠበቃ ነበረ ! ከዚህ ሁሉ ጋር ግን መንግስት ጋዜጠኞቹን ማሰር የሚያስችለው ምክንያት ነበረው ያለፈቃድ አገሪቱ ውስጥ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገብተዋል ገብተውም ከኦብነግ ወታደሮች ጋር ተይዘዋል ! የሚቀርብ ኬዝ አላቸው እነዚህ አረብ የተባሉ ሰዎች ግን ቅንጣት የሚቀርብ ኬዝ ቢኖርባቸው ለምን ይለቀቃሉ ? አሸባሪነታቸው ሊረጋገጥ የሚችል ቢሆኑ ደግሞ የአገራቸው መንግስትም እፎይ ብሎ ለአገርራችን መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል እንጂ እንደስዊድን መንግስት አይቃወምም ነበር ምክንያቱ ቀላል ነው ነገሩ ዜና ሊሰራበት የተፈለገ ሴትአፕ ነገር እንጂ ጠለቅ ብሎ እንዲፈለፈል የተፈለገ ነገር ስላልሆነ !(አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዳይሆን ነገሩን ማዳፈን ?) ሰዎቹ እንዳልከው በሰላም ሺሻ እየጠጡ ይሆናል ጫፋቸው ስላልተነካ ምን ፍርድ ቤት አስኬዳቸው ? ፍርድ ቤት መሄድ የነበረበት ዋናው አካል እንኳን አርፎ ተቀምጦ የለ ?

ነጻ ኢንቨስቲጌቲቭ ጋዜጠኛ ግን የነገሩን ስር ለማግኘት የተሸፈነውን ለመክፈት መስራት የሚችል መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ ስዩም መስፍን ባድመ ለኛ ተሰጠ ስላሉ በተለያየ መንገድ ቬሪፋይ ሳይደረግ እሱን እንደፋክት መውሰድ ምናልባት ህዝብን ማሳሳት ይሆናል ነጽ ጋዜጠኛ ቅድምያ ታማኝነቱ ለህዝቡ መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ

ለማንኛውም ሀሳብህን ስላካፈልከኝ ከልብ አመሰግናለው

ሰላም ሁን

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Mon May 14, 2012 12:39 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ክቡራን

1 :- ኢሳያስ እንዲህ አለ መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ አለ ቁራን እንዲህ አለ አላህ እንዲህ አለ ...እያልክ ያልተባለ ነገር መቀላቀልህ ከሌላ ሰው እምነት ክብር ጋር , ከውይይቱ መንፈስ ጋር , ከራስህ ክብርም ጋር የማይሄድ ነገር ስለሆነ ቀልድ ካስፈለገም መቀለጃ ቦታና መቀለጃ ነገር መፈለግ እንጂ በቁም ነገር ሳዋይህ መስመሩን የለቀቀ ነገር መጻፍ ተገቢ አይመስለኝም that was tottaly uncalled for !

2 :- የሰጠኽኝን ሊንክ ቤቴ ስሞክረው ይሰራል አላነነብኩትም አነበዋለው ያለኝንም ሀሳብ አካፍልሀለው ሆኖም ግን አሁንም እኔና አንተ ልንወያይ የምንችለው ጠቅላላ መርሆዎች ላይ እንጂ አህባሽ እምነት ላይ ኢን ፓርቲኩላር ሊሆን አይገባም ምክንያቱም አንተ የአህባሽን አስተምህሮት አንብበህ የተቀበልክ ሰው ብትሆን ስህተቱን ነቅሼ አሳይህ ነበር አንተ ግን ሰውየውን ኢትዪጵያዊ ነብይ ማለትህ እራሱ ስለሰውየው ብዙ እንዳላወቅክ ነው የገባኝ ምክንያቱም ሰውየው እራሳቸው ነብይ ነኝ የሚል ድፍረት ፈጽሞ አልተናገሩም አንተ አህባሽ ብትሆን ስለአህባሽ ረጅም ርቀት ልንወያይ እንችል ነበር ግን እኔም አህባሽ ሳልሆን አንተም የአህባሽ ተከታይ ሳትሆን ስለእምነቱ እንወያይ ብንል ብዙም አይስኬደንም ሆኖም አንተ ጋዜጠኛ እንደመሆንህ በዛ ዙርያ ብናጠነጥን አንድ ነገር ላይ መድረስ ይቻል ነበር

3 :- ባድሜን ያነሳሁት ለምሳሌ ብቻ ነው እዚህ ላይ ስዩም አልዋሹም ወይንም ኢቲቪ አልዋሸም ካልክ ሌላ ክርክር ነው ሆኖም ኢትዮጵያ ውሳኔውን አልተቀበለችም ከባድመ አልወጣችም ...ሌላ ነገር ነው ለማስታወስ ያህል ዜናው (የመጀመርያው ) የሚለው ግን ፍርድ ቤቱ እንክዋን የጠየቅነውን ያልጠየቅነውን ጭምር ሰጥቶናል ነበር የሚለው :: አንዱ ምን አለ መሰለህ እኔ የማዝነው አንዴ ስላታለልከኝ ሳይሆን ድጋሚ ላምንህ ባለመቻሌ ነው ኢቲቪ አንዴ ስለዋሸ እውነት አይናገርም ማለት አይደለም እውነት ሊናገር ይችላል ግን እውነቱ የሚጣራበት መንገድ መኖር አለበት ነው የውይይታችን መስመር ምን አይነት ማጣርያ መንገድ አለ ዜናውን ? ይህ ነበር ካንተ ቀጥተኛ መልስ ያጣሁለት ነገር

ጥያቄውን ቀየር ላድርገው

ዜናው እውነት ሊሆን ይችላል ወይ ? ይህን እኔ ልመልሰው አዎን ይችላል (ፕሮባብሊቲው ዜሮ ስላልሆነ )

ዜናው ሀሰት የፈጠራ ሊሆንስ ይችላል ወይ ? ይህንን አንተ በአጭሩ (ያለትንታኔ ) መልሰው እስቲ ?

አርትክሉን አንብቤ እመለስበታለው

አመሰግናለው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Tue May 15, 2012 1:34 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
Code:
ዜናው እውነት ሊሆን ይችላል ወይ ? ይህን እኔ ልመልሰው አዎን ይችላል (ፕሮባብሊቲው ዜሮ ስላልሆነ )

ዜናው ሀሰት የፈጠራ ሊሆንስ ይችላል ወይ ? ይህንን አንተ በአጭሩ (ያለትንታኔ ) መልሰው እስቲ

በዚህ ጉዳይ ላይ አንተ ውስጥ ያለው መንፈስ እኔም ያለ ይመስለኛል :: ያንድ ዜና አውቲስቲነት ( ተአማኒነት ) ሁሌም የሚገመገመው ባንባቢው አይን ነው :: አንተ ስታነበው ውሸቱ ጎልቶብሀል ....መንግስት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ያበጃጃት የካልሲ ኴስ እየመሰለ ይታይሀል :: ባንተ ጥፋት የለም :: ባንተ ቦታ ሆኘ ስመለከው ትክክል ነው :: የሙስሊም ወንድሞቼ ጥያቄና ህጋዊና የመብት ጥያቄ ነው ብለህ ስለምታምን በምንም አይነት ይሄ ዜና አውቲኒቲክ ነው ወይም ጄኒዩን ነው ብለህ አትቀበለውም :: ይሁን እንጂ ፕሮፓሊቲው ዜሮ ስላልሆነ እውነትም ሊሆን ይችላል ስትል ..ዜናው ውሸት አይደለም ( ላይሆን የሚችልበት አጋጣሚ አለ ) ወደሚለው መድመደሚያ ያንደርደርናል :: ለኔ የሰጠሀውን አሳይመንት አንተው መለስክልኝ :: ዜናው የሀሰት ፈጠራ ሊሆን ይችላል ወይ ያልከኝን ስመለከተው በኢቲቪ ከተላለፈው ውጭ መንግስት ምን መረጃ ይዞና አግኝቶ ነው ...እነዚህን ሁለት ሰዎች ባስቸኴይ ውጡ ያለበት ..? ምን አይነት የተጨበጠ ማስረጃ ቢኖረው ነው ? ብዬ ራሴን ጠይቄአለሁ :: ስለእነሱ ከተነገረው ዜና ውጭ እጄ የገባ ማስረጃ የለም :: የበተኑት ወረቀት የሰርግ ጥሪ ይሁን ወይም የቢዝነስ ፍላየር ይሁን አላውቅም :: የዛኑ ያህል የበተኑት ወረቀት ጂሀድ በኢትዮጵያ ይጀመር ...ወደ ጀነት መግቢያው እሱ ነው የሚል ዚቅ ያለው መሆኑንም አላውቅም :: ላገር ደህንነት አስጊ በሆነ ጉዳይ ላይ ስለተሰማሩ ብቻ ካገር ይውጡ ነው የተባለው :: እነዚህ ሰዎች አርብን ጠብቀው ህዝበ ሙስሊሙ በሚሰበስበት ሰአት ለምን እንደመጡ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው ...:: "" አይደለንም እኛ ሰላማዊ ሙስሊሞች ነን ካል ህእባሽና ከዋህቢ ጉዳይ ጋር የሚያገናኝነ ምንም ነገር የለም ...ወደ አንዋር መስጊድ የመጣነው ለግል ጉዳያችን ነው ..ሂጂራ ለማድረግ ነው ...ግን የኢትዮጵያ መንግስት እንግዳ አክባሪ ስላልሆነ እንደ ወንጀለኛ በፖሊስ አስይዞ አስወጣን "" ብለው ራሳቸውን ግልጽ ባደረጉ ነበር :: አልሆነም :: ስለዚህ ዜናው የሀሰት ፈጠራ ሊሆን ይችላል የሚለው ፕሮፓሊቲ አንተ ከላይ ከገለጽክው እውነት ሊሆን ይችላል በሚለው የፕሮፓሊቲ ፓኬጅ ውስጥ አብሮ ገብቷል ማለት ነው :: አጭር ትንታኔ ብለሀኝ አረዘምኩት መሰለኝ ይቅርታ :: ከዚህ በተጨማሪም ይሄን ጉዳይ ስክታተል የቡዙዎች ጥያቄ የሆነውን ማለትም መንግስት በርግጥ አሳማኝ መረጃ ካለው ለቴሬሪዝም መምጣታችው ከተረጋገጠ ለምን ካገር እንዲወጡ አደረገ ..? ለምን ፍርድ እዛው አገር ውስጥ አይሰጣቸውም ነበር ?? የሚል ጥያቄ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ለዶክተር ሽፈራው ባንድ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ የሰጡትን መልስ አግንቼዋላሁ :: ፕሮግራሙ ከዚህ ቤት ውይይት ጋር የማይሄድ ረጀም ጉዳዮችን ያያዘ በመሆኑ ውይይቱን ብቻ ኤዲት አድርጌ አቀርብልሀለሁ :: የተባራሪዎችንም አረቦች አመለካከት ባውዲዮ ቀድቶ የሚያመጣልን ሰው ብናገኝ እንደት መልካም በሆን ነበር ..!!!

Quote:
Code:
አርትክሉን አንብቤ እመለስበታለው

አመሰግናለው

እሺ ሳመሪህን እየጠበኩ ነው ..አላህ ይስጥልኝ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2
Page 2 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia