WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ወግ ..........(ብታምኑም ባታምኑም )
Goto page 1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Sun Jun 10, 2007 11:37 pm    Post subject: ወግ ..........(ብታምኑም ባታምኑም ) Reply with quote

............................ ለሷ እሱ ማለዳ ነው ::..........::እሷ ደግሞ ለሱ የቀትር ጸሀይ ::ይህንን ለምን እንዳልኩ ወደኍላ ላይ ተመልሼ እዘረዝርላችኍለሁ :: አሁን ሳልረሳው ወደዋናው ነጥቤ ልመለስ ::

እንዴትና መቼ የመጀመሪያ ቀን እንደተያዩ ሁለቱም ማስታወሳቸውንም እጠራጠራለሁ ::ብታምኑም ባታምኑም እኔ ግን በደንብ ትዝ ይለኛል ::ልክ ዛሬ እንደሆነ ሁሉ :: እሱ የሰለለ ቁመናውን እየጎተተ በደጅዋ ሲመላለስ መሬት የሚልስ ኮቴው ለጆሮዋ እንግዳ ሆኖባት ከምትለቅምበት ሰፌድ ላይ ያነሳቻቸው አይኖቿን ከአይኖቹ አላግታ ስትመልስ በእውነትም የእኔ አይኖች ታዛቢዎች ነበሩ ::የደነበረ ዶሮ .............ያደፈጠ ድመት ጉርምርምታ ......... ከሰፌዷ ቀና የማያደርጋት አሰለፍ በዚያ ኮቴ ግን መጨከን አልቻለችም :: ተረታች ::የመጀመሪያ ሰሞን እንደአጋጣሚ ባየውም ..........የአይን ግጭቱ የሚወስደው ጊዜ ከቀን ወደ ቀን እያደገ መሄዱን ልብ ያልኩ ለት ነው ነገር እንደተበላሸ የገባኝ ::

እሱ ከሁሉም ነገሩ ቀድሞ ረዝሞ የሾጠጠ ቁመናው ከአይን ይገባል :: ቢሆንም እውነት ለመናገር በሰፊዋ እጀ ጉርድ ካኒቴራው ውስጥ ተንጠልጥለው የተንዘላዘሉትን እጆቹን ቅጥነት ልብ ያልኩት ግን ገና ዛሬ ነው ::ደግሞ ------............ ------:: ከፊት ለፊቱ እንደ ጅብራ ተገትሬ አይኖቼን በክንዶቹ ላይ ሳንሸራሽራቸው ተሰማው መሰለኝ በሁለቱ ዘልዛላ እጆቹ ወገቡን ይዞ ቀጥ ብሎ ቆመ :: ብታምኑም ባታምኑም አሁን ደግሞ በሰውነቱና በእጆቹ መህል የተፈጠረው ክፍተት ከነአዘልኩት ቦርሳ ያሳልፈኛል ብዬ መወራረድ አማረኝ :: እነዚህን የተላጉ እጆች ወደታች ቢለቃቸው ከእግሩ ጉልበት ጋር ተጋጭተው እንዳያስደነግጡኝም ሰጋሁ :: እናም አይኖቼን ሳልፈልግ አነሳሁና በቀለምም ሆነ በቅርጽ አንድአይነት ጫማ ለመሆናቸው እያጠራጠሩ ከመጡት ጫማዎቹ ላይ ለጠፍኳቸው :: አንዱ ወደግራ አንዱ ወደቀኝ ከማዘንበላቸው ጀምሮ ተጨማሪ ሌሎች አስር ልዩነቶችን አውጪ ብባል ከሁለት ሰከንድ በላይ አልፈጅም ::

(ይቀጥላል ............እንቅልፍ ሲጠፋ የተጀመረ ..........)

ያሚ

Last edited by yammi on Fri Feb 22, 2008 7:34 pm; edited 4 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
sleepless girl

ውሃ አጠጪ

Joined: 19 Feb 2006
Posts: 1457
Location: near u!

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 1:21 am    Post subject: Reply with quote

ያሚዬ ......እንደው ምንም ቃላት የለኝም ከምር .............ለዛ ያለው .....የሚያስቅ ...የተጨበጨበለት ወግ ነው .!!........እንደዚህ አይነት ወግ ነበር የናፈቀኝ ከምር .........ዋርካ እግር እግር ባለበት ሰአት እስኪ እንዲህ እየጻፍሽ አስነብቢንማ ...........እጅሽ ይባረክ Wink

አድናቂሽ !!!

_________________
Nothing is impossible!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ንጉሥ ጦና

ኮትኳች

Joined: 10 Jun 2007
Posts: 116
Location: europe

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 12:14 pm    Post subject: Reply with quote

አቦ አንቺንስ እንቅልፍ ያሳጣልነ ነው የሚባለው ...
ክርችምችም ብለው እይታን በሀይለቃል የሚገልጹት አባባሎችሽ የማንበብ ስሜትን ያነቃሉ !
Please ቀጥይ ........................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቸኮሌት

ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2005
Posts: 237
Location: united states

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 4:53 pm    Post subject: Reply with quote

ያሚዬ የኔ ቆንጆ ..........ስሜት መግለጫ ቃላት ጠፋኮ .......እስቲ በርቺልን

አድናቂሽ ቸኮ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 5:37 pm    Post subject: Reply with quote

ስሊፕዬና ቸኮሌት አመሰግናችኍለሁ ............እሙዐዐዐዐዐዐ ::
ንጉስ ጦና አንተንም አመሰግናለሁ ::

ያሚ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 7:01 pm    Post subject: Reply with quote

ቀጠለ ...............

የቱ ጋር ነበር ያቆምኩት ................አዎ ድሮ ድሮ የምንደገፋት አሁን አሁን ግን የምትደገፈንን የቤታችንን አጥር አስደግፌ ...........ያንን ምስኪን በአይኖቼ እያበጠርኩ ነበር .........

የተፈቱት የጫማ ማሰሪያዎቹን በአይኖቼ ለማሰር ስታገል ልብ አለኝ መሰል እጆቹን አስቀደሞ ወደ ጫማዎቹ ቁልቁል ተወረወረ :: የነጋው ቀን አይምሽልኝ በዛው ተለምጦ የሚቀር ነበር የመሰለኝ :: ጫማውን አሳስሮ እንደገና ቀና ለማለት ሲንደረደር ብታምኑም ባታምኑም እኔ በአይኖቼ ወገቡን ደግፌ ነበር ::

ግን ስሙን ነግሬያችኍለሁ ? ካልነገርኳችሁ _ ይባላል ::እኔ ድሌ በጉ ብዬ አስተካክዬዋለሁ :: ዛሬ ከበራችን ላይ ቆሞ የሚጠብቀው አሰለፍን ነው .............የአምስት አመት ደባሌን ::

አሰለፍ ..........ከወገቧ በታች እንደ ጨው ጆንያ የተጠቀጠቀች ..............ጎላ ጎላ ያሉ ግን ከሩቅም ሆነ ከቅርብ አጣርተው የማያዩ አይኖች ያላት ..........የተጎረደ አፍንጫ ከሰፋፊ ቀዳዳዎች ጋር እንዲሁም ሞላ ሞላ ያሉት ከንፈሮቿን ስትገልጥ ቀልባችሁን በመስረቅ ፋንታ የሚያርቁ ባናት ባናት እንደተወለዱ ልጆች የተደራረቡ ጥርሶቿ ያሏት :: (በኔ ግምት የጥርሶቿ ቁጥር አርባ ሳይበልጥ አይቀርም ) ምላሷ አንድ ተብሎ ይጠራ እንጂ የአምስት ምላስ ያህል ጉልበት ያለው ..................... ላለመተያየት የተማማሉ ሸፋፋ እግሮች ከሰፊ መቀመጫ ጋር የታደላት ዝንጅብል መሳይ ፍጥረት ናት :: ደግነቱ ሳይደግስ አይጣላምና ግንድ እንደተሸከመ ወራጅ ወንዝ የሚገላበጥ መቀመጫዋ የተባዕቱን አይን እንደሙጫ እያጣበቀ ስለሚያሰቀረው ቅንፍ እግሮቿንና ሸፋፋ መጫሚያዎቿን ልብ የምንለው እኛ እንስቶቹ ብቻ ነን ::

ምሳሌ :

""አሰለፍ የቷ "" ተብላችሁ ብትጠየቁና እናንተም ""አሰለፍ ሸፋፋዋ "" ብላችሁ ብትመልሱ

""የቷ ናት ሸፋፋዋ አሰለፍ ????"" ተብላችሁ እንደገና መጠየቃችሁ አይቀርም :: ያኔ ታድያ ...

""ያቺ ናታ ......... ባለ ትልቅ ......" ስትንደረደሩ

""......................አሰለፍ "" ትባላላችሁ ::

ማን ነበር ""እሷ ከገባች ከአምስት ደቂቃ በኍላ እቤት የሚገባ መቀመጫ ያላት "" እያለ የሚገልጻት ???

ምናልባት እኮ እንዲህ የሚያስለፈልፈኝ ቅናት ይመስላችሁ ይሆናል ::ብታምኑም ባታምኑም እኔ ግን ቅናት ቃሉንም ያወኩት ከዚች መንታ ምላስ አሰለፍ ጋር ከተዳበልኩ በኍላ ነው ::አሁንም ትዝብቴን የማስቀምጥባት የአእምሮዬ ኮረጆ ስለሞላችና ለአዳዲስ ትዝብቶች ቦታ ማስለቀቅ ስላለብኝ እንጂ ከተጠራቀሙት ትዝብቶቼ እየቆረስኩ የማካፈል ሱስ የተጠናወተኝ አይደለሁም ::

(ይቀጥል ይሆን ??)

ያሚ

Last edited by yammi on Fri Feb 22, 2008 7:38 pm; edited 3 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እህምም

አለቃ

Joined: 19 Dec 2005
Posts: 2392
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 7:11 pm    Post subject: Reply with quote

hehe, ያሚዬ እንዴት ጎበዝ ነሽ ! ወግሽን በጣም ወድጄዋለሁ .... I hope there is more
_________________
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09/homage-to-darkness/

"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
blenn

መንገደኛ

Joined: 04 Jun 2007
Posts: 6

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 7:34 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ያሚ ....
ምርጥ ወግ ናት እሽ .....በርች ......አንድ አንድ ቦታ ስለኔ እየመሰለኝ ድንግጥ እላለሁ ........ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በርቺልን ያሚሚዬ
አድናቂሽ
_________________
selam le hulachin yihun
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቸኮሌት

ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2005
Posts: 237
Location: united states

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 7:43 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
አንድ አንድ ቦታ ስለኔ እየመሰለኝ ድንግጥ እላለሁ

ብሌን አሰለፍ አንቺ ትሆኚ እንዴ ? Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 7:49 pm    Post subject: Reply with quote

ብሌንዬ ............ቅቅቅቅቅ መጠርጠሩ አይከፋም Laughing Laughing

ተጠፋፋን አይደል Laughing Laughing

ያሚ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀምሳለ

ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 238
Location: America

PostPosted: Mon Jun 11, 2007 9:25 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ Very Happy ቅቅቅቅቅቅቅ አጥሩ በሳቅ ገደለኝ Very Happy ጋደል ያለ አጥር አስታወሽኝ Laughing Laughing Laughing

ሀምሳለ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1568
Location: Mars

PostPosted: Tue Jun 12, 2007 7:01 pm    Post subject: ቅቅቅ Reply with quote

ቅቅቅቅ ..ሙች ! ምርጥም ተሳዳቢ ነሽ ! እስኪ ቀጥይ ! ጥሩ ወግ ይመሥላል !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Wed Jun 13, 2007 9:11 pm    Post subject: Reply with quote

ዋኖስ .............ደግሞ ለስድብ :: ጆንያ ሙሉ ነው ያለኝ :: Wink

ሀምሳል ......... የተንጋደደ አጥር እንዳይወድቅ መደገፍ ..............ያልተሞከረ ስራ አይመስልሽም : Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀምሳለ

ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 238
Location: America

PostPosted: Wed Jun 13, 2007 10:19 pm    Post subject: Reply with quote

ያሚዬ በይ 1 ቀን ልዋስ እመጣለሁ በጆንያ ከሞላሽው Very Happy

ያሚዬ አሰለፍ ደህናም አይደለች ምነው ታሪኩ ዝም አለ Rolling Eyes እሷንስ ከፉ አይንካት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፉፊ

ኮትኳች

Joined: 11 Jan 2005
Posts: 209
Location: united states

PostPosted: Wed Jun 13, 2007 10:59 pm    Post subject: Reply with quote

ያሚዬ ስዊቲ በታም አሪፍ ነው ቀጥይበት ....

ለምወዳቹ ጋደኞቼ ሁሉ እዚሁ ሰላምታዬን አቀርባለሁ
ከብዙ ናፍቆት ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3  Next
Page 1 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia