toolbar creator
View previous topic :: View next topic
Author
Message
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Jun 19, 2012 8:51 pm Post subject:
ሰላም ሞንሟናው :-
የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው : የሚገርመው ነገር ክላስ ውስጥ እያስተማረ ሁሉ ያጨሳል ደግሞም ቃሚና ዝርክርክ ቢጤ ነው :: አንትሮፖሎጂ ማስተማሩ ላይ ግን ጎበዝ ነው በተለይም ቲዮሪውን በደንብ ይችለዋል ... ክላስ ውስጥ ፈኒ ስለሆነም ተማሪ ይወደዋል :: ስለ እሱ ብዙ አውቃለሁ በደንብ አውቀዋለሁ ...አይ ገሜ አፈር ይብላ ይህ ዝርክርክ
ክፍል ውስጥ ሲጃራ እያጨሠ የሚያስተምረው አንድም ፍፁም የመምህርነት ሥነ -ምግባር ስለሌለው በተጨማሪም ከዋናው የወያኔ ቁንጮ ጨምሮ አጫሾች ስለሆኑና ሕጉንም በሚመቻቸው መንገድ ስላጣመሙት ነው :: በደርግ ዘመን ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ ይቅርና በሥራ ቦታና ሕዝብ በብዛት በሚሠበሠብባቸው ሥፍራዎች እንኳን ማጨስ አይፈቀድም ነበር :: በአሁኑ ዘመን በዓለም ዙሪያ ሲጃራ ማጨስን ለማስቆም በሕግ ድጋፍ ምን ያህል ጥረት እንደሚደረግ እናያለን :: ስለሆነም ዶክተር ገመቹ መገርሣ : ፕሮፌሠር እንድርያስ እሸቴ እና የመሣሠሉት 'የሥም ምሁራን ' ከዚያው ከተጠናወታቸው የማርክሲስት -ሌኒኒስት -ስታሊኒስት -ማዖይስት -ኤንቨር ሆዣይስት ዛር ጋር ስለቆረቡ ምግባረ -ብልሹነታቸውን በአደባባይ በሕዝብ ፊት እያሣዩ ወደ መቃብራቸው ያዘግማሉ ::
እኔን የገረመኝ ግን በምን ተዓምር ነው የእርሱ ጭንቅላት ከለገሠ ዜናዊን ጭንቅላት ጋር ሲመዛዘን 1/91,000,000 እንኳን አይሆንም ብሎ የሚያምን የምድር ጉድ ስለ አንትሮፖሎጂ ጽንሰ -ኃሣብ ጥሩ ዕውቀት አለው የሚባለው ይህ አገላለጽህ አልገባኝም :: እኔ ዩኒቨርሲቲውን የማስተዳድር ኃላፊ ብሆን ኖሮ የዶክተር ገመቹ መገርሣ ዓይነት ሰው ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እንዲያስተምር ሣይሆን ጥሩ የሥነ -ልቡና ሐኪም ከዝቅተኝነት የአዕምሮ ሕመም እንዲያክመው እልከው ነበር :: ይህ ሰው እኮ ከእርሱ የባሱ አጎብዳጅ በቀቀኖችን የሚያሠለጥን እንጂ በምንም መለኪያ መምህር መሆን የሚችል ሰው አይደለም ::
የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው : ማነው ይህ መጀመሪያ ያደነቅሁት ጃዋር ሙሀመድ ደግሞ መጀመሪያ ጥሩ መስሎ በኍላ አክራሪ ኦነግነቱን ቀስ እያለ በጽሁፎቹ አሳውቋል :: በተለይ ኦነግ ኢትዮጵያዊነቱን ተቀብሎ ከግንቦት ሰባት ጋር ስምምነቱን ይፋ ሲያደርግግ በጣም ነበር የተንጨረጨረው ....አክራሪነቱ እልም ብሎ ነው የወጣበት ::እንዴውም ለወደፊቱ ከወያኔ ጋር ተሞዳሙዶ ስልጣን ለማግኜት ወደ ኍላ የማይል ቱልቱላ ቢጤ ነው ::
ለመሆኑ ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ ነው ?
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
You cannot post new topics in this forum You cannot reply to topics in this forum You cannot edit your posts in this forum You cannot delete your posts in this forum You cannot vote in polls in this forum