መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Sun Apr 04, 2021 4:50 pm

ጠጁን ከመጥመቂያው ይዠላችሁ መጣሁ መእምናን፡፡
ማሩን ካፎቱ ፣ አፌ ቁርጥ ይበልልሽ የኔ አንበሲት፡፡

https://youtu.be/RWn4au1pNH4
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Sun Apr 04, 2021 5:34 pm

ዋው ኢዜማም ጥርስ አወጣ፡፡ መናከስ እንዲጀምር ከፈለገ ግን መሪውን ባራዳ ፎርም ጡረታ ይላከው!! ሰውየው ( የኢዜማው መሪ ) የዶክተር አቢይ አማካሪ እንጂ ተቃዋሚ አይደለም፡፡ በጣም ሲሪየስ የሆኑ ሰዎችን ኢዜማ ውስጥ አያለሁ፡፡ ውጤት ከፈለጉ ግን ባሽከረካሪነት ያስቀመጡትን ሰው በደንብ ሊበረበርብሩት ይገባል!! ፖሎቲካዊ ብርበራ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Mon Apr 05, 2021 3:43 am

ነጻ አስተሳሰብን ነጻ አመለካከትን እንዲህ በሚዲያ እየቀረቡ የሚናገሩ ዜጎችን ፣ የፖሎቲካ መሪዎችን ማበረታታትና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ ይሄን ውይይት ወድጀዋለሁ፡፡ ዛሬ እኮ በደብዳቤ ለመንግስት ሰራተኞች ከደመውዛቹ ላይ ታሳቢ የሚሆን አበል ይከፈላልና ለጠ/ ሚ/ ሩ ሶስተኛ አመት በአለ -ሰሚት ድጋፍ ውጡ የሚል ባጃጃዊ ባህል በድርቅና እያየን ነው ፡፡ ሃሜት አይደለም፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Mon Apr 05, 2021 3:42 pm

የኢዜማው ተወካይ ይህን አሉ
" እዚህ ውስጥ የመንግስት ሚዲያዎች ትኖራላችሁ ብዬ አስባለሁ፣ካላችሁ ውግንነታችሁ ለሚከፍላችሁ ድርጅት ( ለመንግስት ) ሳይሆን ለህዝብና ለእውነት ይሁን ፣ እኛን ደግፉን ብለን አንከራከርም ፣ ቢያንስ ግን ሃቅን ዘግቡ ፣ እውነትን ለህዝብ አቅርቡ!! ቡዙ ጊዜ ስብሰባ ሲኖረን እንጠራችሁና መንግስትን የሚነካ ነገር ስታገኙ ( እውነትም ቢሆን ንኳን ) ህዝብ እንዲሰማው አታደርጉም፡፡ "
ሰሚ የለም እንጂ ሰውየው ተናገሩት ነገር መሬት ጠብ የሚል ነገር የለውም፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ቆቁ » Mon Apr 05, 2021 5:27 pm

ስማ ክቡዬ
ሐይለስላሴን ፊውዳል ደርግን ፋሺሽት ብለን ነው የተምቦጫረቅነው
ወያኔን ጁንታ ብንል ምን የሚደንቅ ነገር አለ ብለህ እስቲ ያቺንን ልጅ ጠይቃት?
ውይይቱ ማራኪ ነበር እሱዋንም አደንቃታለሁ ነገር ግን በአንተ ትንታኔ ስትመጣ ግን ነገሩ ሁላ እየዞረ ስለሚመጣ አንድ ልበልህ

ሐይለስላሴ ፊውዳል ሲባል በዛን ጊዜ ስልጣን የነባራቸው እና የመሬት ባላባቶች ብቻ ነበሩ ፊውዳል የሚባሉት ማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊውዳል አልተባለም ገባህ ?
ደርግ ፋሺሽት ሲባል የደርግ አባላት ናቸው እንጂ ማንም የመከላከያው ሰራዊት ወይም የየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ሕዝብ ይህንን ተቀጥላ ስም አልተሰጠውም ገባህ


አሁን ግን ወያኔ ጁንታ ስለተባለ ለምን እንደዛ ያለ ነገር መጣ ለሚለው መልሱ ቀላል ነው
ወያኔ ሲንደባለል ጥሎት የሄደው ፋንድያው የጎጥ ፖለቲካ ነው መልሱ

ገባህ ነፍሱ
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Mon Apr 05, 2021 5:46 pm

ፍልፌ ሰላም ነው አባ ፣ ስለጠፋህ ሰላም ለማለት ብዬ ነው እስኪ አትጥፋ !! ኑርልኝ፡፡ ሎል፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Tue Apr 06, 2021 2:38 am

ይሄንን ስብሰባ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በጠ/ሚ/ሩ ቀጥታ ትእዛዝ ከስልጣን ተነስተው በዮናታን ተስፋዬና በመሀመድ እድሪስ ( ሁለቱም የፌስ ቡክ ግልገሎች ናቸው ) ቂቂቂ ተቀየሩ የሚባለው እውነት ነው ?? እስኪ አጣሩ መእምናን፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ቆቁ » Tue Apr 06, 2021 6:54 pm

የፈለገው ይሁን ብለን እናልፈዋለን
ዋናው አጀንዳ ልጅቱዋ ያነሳቸው " ጁንታ "ብሎ መጥራቱ ትክክል አይደለም የሚለው ነው ነፍሱ
ስማ ወለጋ ሲገደሉ ምን እየተባሉ ነው የሚጠሩት ?
ስማ መተከል ሲረሸኑ ምን እየተባለ ነው የሚጠሩት?
ማይካድራ በየቤታቸው ግድግዳ ላይ የተለጠፈው ምንድነው የሚለው ?
ከስልጣን ሲባረሩ ምን እየተባሉ ነው የሚባረሩት ?
ስለሆነም ወለጋ የሚጠሩትን ስም ባላወጡት ኖሮ የሚልል ግምገማ ላይ ልትደርስ ነው ነፍሱ
ወያኔ ራሱ ወያኔ ያወጣው ስም ነው በሌላ ክፍል ይህ ስም ሌላ ትርጉም ሲኖረው በክቡዬ ደግሞ ሌላ ለየት ትርጉም አለው
ጁንታም እንደዚሁ ጁንታ የተባለው ወያኔ ነው ? አይደለም እንዴ
ጁንታ = ወያኔ እያልክክ እንደ መደመርና መቀነስስ ስታሰላ ብትኖር አይገባህም ፡ የማይገባህ ደግሞ ሊገባህ ስለማትፈልግ ብቻ ነው

ስማ ይህ የጎስሳ ፖሌቲካ ውጤት መሆኑ ካልገባህ የአህዮቹ ፋንድያ ራስህን ስለቀወጠው ምን ይደረግ ብሎ ያልፍፍሃል ፈላስፋው

ይህ ጉዳይ የስም አጠራር በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም እንደኔ እንደ ፈላስፋው እልም ብለህ በዚህ ፍልስፍና ውስጥ ገብተህ መነከርና መጠመቅ ይኖርብሃል
ለምሳሌ
በሐገርህ በኢትዮጵያ እንደዚህ ያሉ አጠርሮች ና የተለያዩ የእዝማሪና የክራር ግጥሞች አሉ ብለህ እስኪ ለቃቅመህ ለመፈላሰፍ ሞክር
ማነው ይህንን የማሲንቆና የክራር ግጥሞች ከዛም አልፎ ለየት ያሉ ደስ የማይሉ አጠርሮችን የፈጠረው
ቴዎድሮስ
ዮሐንስ
ምኒሊክ
የሆነ ማሲንቆ ገዝጋዥ
የሆነ ክራር ጠብጣቢ
የሆነ መሸታ ቤት የተበወዘ
የሆነ በጨብሲ የበጨጨ
እያልክ እያልክ ብትጠይቅ ነገሩ ሁላ የዞረ ዙራዙር ይሆንብህና ልክ እንደፋንድያው ትሰክራለህ
እዚህ ላይ ነው ነጥቡ አንድ ግለሰብ ባለው ሌላው ጎሳ ነው ያለው የሚለው አስተሳሰብ ባርባርሪክ የሆነ አስተሳሰብ ነው ስለሆነም ትምህርት ቤትና የአስተማሪ መኖር ለምን አስፈለገ የሚለው ጥያቄ ላይ ትመጣለህ
የምትማረው ሰውን እንደሰውነቱ ለመውደድ ፡ ከሰው ጋር ለመስምማት እንጂ በጎጣ ጎጠኛ ፖለቲካ ተዘፍቀህ እንደ አህያ ፋንድያህን በየመንገዱ ለማዝረክረክ አልነበረም ወይም በሌሎች የአህያ ፋንድያዎች ለመስከርም አልነበረም
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Thu Apr 08, 2021 4:58 am

አለመታደል ነው !! እኚህ ሰውዬ ( ጋሽ ዝናቡ ) ባንድ ወቅት ያስተሳሰብ ልዩነት ጸጋና ሃብታችን ነው ብለው ነበር ፣ ቀጠል አድርገውም ካሁን በኋላ ባሃሳብ ልዩነት የተነሳ አሳዳጅና ተሳዳጅ ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም ብለው ነበር፡ ፡ (ምንጭ ራሳቸው ጋሽ ዝናቡ)፡፡
ይሁን እንጂ እሳችውን የሚቃወም ወይንም የሳቸውን ቃላት እይደገመ የማያጠንጥን ካዩ ወይ ከስራ ያስወግዱታል ወይ ምክንያት ፈጥረውና አስፈጥረው ያስወግዙታል ቀጥል አድርገው ደግሞ ታፔላ በማስለጠፍ ጦር ያዘምቱብታል፡፡ ፡ ጁንታ፣ ያልተደመረ ፣ ያልተጨመረ ፣ የቀን ጅብ ፣ የሌሊት ጉጉት፣ የለውጡን ሂደት አደናቃፊ ...፣ የጻፍኩትን መጽሃፍ የማያደንቅ፣ አደናጋሪ ....ወ.ዘ.ተ በማለት፡፡ ያልክትም እውነት ሆነ ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ኮርፕሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ከስራቸው እንዲለቁ የተደረጉበት ዋናው ምክንያት እንዲህ አይነት ሁሉን አቀፍ ( ኤክስኩሊስቭ ) ውይይት እንዲደርግ በመፍቀዳቸው ና እሳቸውም የዝግጅቱ አካል በመሆናቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው እሳቸውን አንስተው በጋሽ ዝናቡ ሳምባ የሚተነፍሱ ግልገሎችን በቦታው ያስቀመጡት!!
አይ አንቺ ሃገር !!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መንግስት ያጠፋው ትልቅ ጥፋት ህወሓትን ጁንታ ማለቱ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Sun Apr 11, 2021 4:18 am

የሚገርመኝ ለብልጽግና የኋላ እሸቱን ለመስጠት ለቅጽበት የማያመነታው ስዩም ተሾመ በዚህ ለፌስ ቡክ ግልገሎች በተሰጠው ጮማ ሹመት እሱ መዘለሉ ነው፣ አብዮት ልጇን ማነከት ስትጀምር እንደዚህ ነው፡፡ ቂቂቂቂ
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8831
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 4 guests