የሶስት ትውልድ ደም የጠጣ ጁንታው ህወሓት!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሶስት ትውልድ ደም የጠጣ ጁንታው ህወሓት!

Postby ኳስሜዳ » Thu Apr 15, 2021 9:02 am

ጁንታው ህፃናት እሳት ላይ ማግዶ ለራሱ ግን እግሬ አውጭኝ ብሎ በየበርሃው እየተደበቀ ይገኛል። ጁንታ ህወሓት በ40 አመት ሶስት ትውልድ የበላ የደም መፍሰስ ፍቅር ያለው ሴጣናዊ ስብስብ ነው።

ለስልጣን ሲል የራሱ ህዝብ እንኳ ሳይራራ ይዞ ለመጥፋት ሞክሯል። ስርአቶች ይፈጠራሉ ይጠፋሉ ህዝብ ግን ሁሌም አለ። የትግራይ ህዝብ የ3000 አመት ታሪክ ያለው መንግስትነት የሚያቅ ህዝብ ነው ህወሓት ግን ይሄን ታሪክ ቀምቶ የትግራይ ህዝብ ታሪክ የ40 አመት ታሪክ እንደሆነ አድርጎ ራሱ ሲያገዝፍ ቆይቷል።

ጁንታው እኔ ከሌለሁ ትጠፋላቹህ ብሎም ያለ ህፍረት ይናገር ነበር። ጁንታው በእብሪት ተወጥሮ የማይነካ ቀይ መስመር አልፎ የሃገር መከላከያ ጨፍጭፎ በጀመረው ጦርነት ይሄን የጁንታ ክህደት እና ጭካኔ ለኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ ጁንታው እድሜው ሊያጥር ችሏል።

አሁንም ይሄ የጥፋት ሃይል አለሁ ለማለት ህፃናት የሶስት ቀን ስልጠና እየሰጠ የእሳት እራት እያደረገ ይገኛል። ይሄ ሴጣናዊ ድርጊት ሁሉም ሰው ሊኮንነው ይገባል በህግም የጦር ወንጀል ነው። ጁንታው እንዲነሳ የሚደረግ ሴራ በሙሉ ከንቱ ህልም ነው።
Image
ኳስሜዳ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3000
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 3 guests