የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን-በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ...

ስፖርት - Sport related topics

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Sep 02, 2010 7:06 pm

vann wrote:ተድላ እና ገረመው የጀመራቹት ውይይት ደስ ብላኛለች ...ግን አላነበብኩትም ገና :lol: መሳተፌ አይቀርምና እንዳታቆሙ! ፌደሬሽን ላይ የሚጻፍ ማንኛውም መጥፎ ነገር ያስደስተኛል! ያለኝን ለመጨመር ዝግጁነቴን በዚህ አጋጣሚ አሳውቃለው!

በጣም ጥሩ : በተሣትፎህ ቀጥልበት ::
ተድላ ሀይሉ wrote::


የእኔ መሠረታዊ ጥያቄዎች

1 ......... ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯት እንዴት 25 ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ካላቸው እንደ-እነ ካሜሩን እና አይቬሪ-ኮስት ወይም ጋና ያነሠ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?

ተድላ


ተድላ ማን ይሙት......አንድ ካሜሩናዊ ሶስት ተኩል ኢትዮጵያዊ እንደሚወጣው ጠፍቶህ ነው አሁን?

ለወደፊቱ የኢትዮጵያንና የሌሎች አፍሪካውያንን ህዝብ ብዛት በቁጥር ከማወዳደር ይልቅ በኪሎ ብናወዳድረው ጥሩ መለክያ ይሆናል::

ውይይታችሁን ቀጥሉ!

'vann' ኢትዮጵያ ውስጥም ዞር : ዞር ብለህ ብትጎበኝ እኮ ከካሜሩናውያን የሚበልጡ ወገኖች አሉን :: በሰውነት ትልቅነት ብቻ ቢሆን ኖሮ ባለፈው የ19ኛው የዓለም ዋንጫ ትንንሾቹ ደቡብ ኮርያውያን እንዴት አድርገው ነው ግሪክን 2-1 ያሸነፉት ? ከናይጄሪያ ጋር 2-2 የወጡት ? በዓለም ዋንጫ ውድድርስ የደቡብ ኮርያ ቡድን ስንት ጊዜ ተሣትፏል ? ስምንት ጊዜ (እ.ኤ.አ. 1954 : 1986 : 1990 : 1994 : 1998 : 2002 : 2006 እና 2010) ከዚህ ውስጥ በራሳቸው አገር በተደረገው የእ.ኤ.አ. 2002 የ17ኛው የዓለም ዋንጫ 3ኛ ሆነዋል :: የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ የእስፓኝ ቡድን ተጫዋቾችን ተክለ-ሰውነት ብንመለከትም ያን ያህል ግዙፍ የሚባሉ አይደሉም :: ስለዚህ ጥሩ ተክለ-ሰውነት ለስፖርተኛ አስፈላጊ ቢሆንም ብቻውን ግን የእግር ኳስ ውጤት አይሆንም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Sep 02, 2010 7:14 pm

ንፍታሌም wrote:
የእኔ መሠረታዊ ጥያቄዎች
1 ......... ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯት እንዴት 25 ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ካላቸው እንደ -እነ ካሜሩን እና አይቬሪ -ኮስት ወይም ጋና ያነሠ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?


ሰላም ተድላ ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ብለህ ያቀረብከው ሀሳብ ራሱ ሌላ ጥያቄ ፈጥሮብኛል

ቻይና 1 ነጥብ 3 ቢልዮን ህዝብ ኖሯት እንዴት ከ15 ሚልዮን በታች የህዝብ ብዛት ካላቸው ከእነ ኒዘርላንድ ስዊዘርላንድ..አየር ላንድ ያነሰ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ?....

የህዝብ ብዛት በብዙ ነገሮች ላይ ያለው አዎንታዊ እና አሉታዊ ሚና እንዳለ ሆኖ...አንተ ባነሳከው ጉዳይ ላይ...ለእግር ኳስ ውጤት መገኘት ያንድ አገር የህዝብ ብዛት ሊኖረው የሚችለው ሚና ምንድነው?......

ጥሩ ጥያቄ ነው :: ቻይና ለረዥም ዘመን ለእግር ኳስ ስፖርት ትኩረት አትሠጥም ነበር :: እነርሱ ባህላዊ ስፖርት ብለው የሚወስዱት የጠረጴዛ ኳስ ስፖርትን ነበር :: ቻይናዎች ለእግር ኳስ ትኩረት እየሠጡ የመጡት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ነው :: በአሁኑ ሰዓት ከደረሱበት የኢኮኖሚ ዕድገት አንፃር እና የቻይና ሕዝብ ለእግር ኳስ ስፖርት እያሣየ ካለው ፍቅር በመነሣት ይበልጥ ስፖርቱ በቻይና እየተዘወተረ እና በዓለም መድረክም ተሣትፏቸው እየጎለበተ እንደሚመጣ መናገር ይቻላል ::

ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከእግር ኳስ ጋር የጠበቀ ፍቅር አለን :: ከሌሎች ስፖርቶች ጋር ሲነፃፀር የነበሩትም ሆነ ያለው አገዛዝ የተሻለ ድጋፍ ያደርግለታል : በቂ ባይሆንም :: ስለዚህ እኔም ሆንኩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለምን 'በእግር ኳስ ስፖርት ወደኋላ ቀረን ?' ብለን ብንጠይቅ ሊገርም አይገባም :: የሕዝብ ብዛታችንም ብቃት ያላቸውን ስፖርተኞች ለመምረጥ ይበልጥ ይረዳል ከሚል መነሻ ነው አስተያዬቱን ያቀረብሁት ::

'ንፍታሌም' :- ለአስተያዬትህ አመሠግናለሁ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Sep 05, 2010 8:16 pm

ሰላም ወገኖቼ :-

በእግር ኳስ ያለን ደረጃ ይህንን ይመሥላል ...

Ethiopia1-4 Guinea

Ethiopia won the African Nations Cup back in 1962, but since then the quality of the side has suffered, and their last qualification came in 1982. The Syli National of Guinea began brightly, but neither side could break the deadlock in the first 45 minutes, and 0-0 was the half time score in Addis Ababa.

The second half produced a different result however, with the Walya Antelopes keen to make use of home advantage, while Guinea played as if they had nothing to lose, and their tactics allowed them to bulldoze over the home side with a sterling second half display. The final score saw Guinea win 4-1, and take all three points home, while Ethiopia will be disappointed with their terrible start to the qualifying.


ምንጭ:- Goal.com, By Kingsley Kobo & Peter Pedroncelli, Sep 5, 2010 1:46:00. PMAFCON 2012 Qualifying Round Up.

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Sep 13, 2010 8:33 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የኢትዮጵያ ቡድን በአገሩ : በራሱ ሜዳ በራሱ ሕዝብ ፊት 4-1 በመሸነፉ ብዙ : ብዙ ተብሏል :: የሊብሮ ጋዜጣ አዘጋጅ ገነነ መኩሪያ የሚከተለውን አስፍሯል :: ኃሣቡ እያዝናና የሚያስተምር ነው : አንብቡለት ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ :: የዋናውን ብሔራዊ ቡድን ጉዳይ እኔን አይመለከትም›የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ኃላፊ

ሥርዓት አልበኝነት በፌዴሬሽን ዙሪያ

ከአንድ አመት በፊት ‹‹ ሕብረትና ውጥረት›› በሚል በተነሳው ያለመግባባት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፊፋ ታግዶ ለገላጋይ ለከልካይ አስቸጋሪ ሆኖ በመንግሥት ሸምጋይነት ነገሩ መስመር ከያዘ በኃላ በፌዴሬሽኑ አካባቢ እፎይታ ተገኝቶ ነበር፡፡

አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ቦታውን የያዘው በውድድር ነው፡፡ ‹‹ እኔን ብትመረጡ የተሻለ እሰራለሁ›› በሚል ቀደም ሲሉ ከነበሩት የፌዴሬሽን አካሄድ ወጣ ባለና ለውጥ ባለው አሰራር እንደሚሰሩ ነው ቃል የገቡት፡፡

ሕዝቡም ከአዲሱ ፌዴሬሽን ብዙ ነው የጠበቀው፡፡ ነገር ግን ከተለመደው ውድድርን ከመምራት የተለየ ምንም ነገር አላሳዩም፡፡ እንዲያውም ‹‹ ጭንቅላቱ እንግሊዝ የቀረው አካሉ አዲስ አበባ ተብሏል፡፡ ከስፖርት ቤተሰቡና ከክልል ፌዴሬሽኖች ከመወያየት ይልቅ ምክርና ሐሳብ የሚቀበለው ከእንግሊዝ ሐገር ሆኗል፡፡ ሊቀመንበሩም ‹ተጓዥ ፕሬዝዳንት› የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይሄም የሆነው በጣም የውጭ ጉዞ ስላበዙ ነው፡፡

አብዛኛውም የፌዴሬሽኑ ውሳኔ የሳቸው እንደሆነና ስልጣንም እየጠቀለሉ እንደሆነ ይነገርባቸዋል፡፡

ጌታዋን የተማመነች በግ

የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ኤፌም ኦኔራ በአቶ ሳህሉ ተዳራዳሪነት ነው ከእንግሊዝ የመጡት አቶ ሳህሉ እንግሊዝ ሐገር ነው የተማሩት አሰልጣኙም ከዚያ ነው የመጡት ኦኔራ በአሁኑ ሰዓት ተጠሪነታቸው ለአቶ ሳህሉ እንደሆነ የቴክኒክ ሐላፊው አቶ ዮሐንስ በጋዜጣ ላይ ገልፀዋል፡፡

አሰልጣኙ ተጠሪነታቸው ለቴክኒክ ሐላፊው መሆን እንደነበረ ተጠቅሷል፡፡ አሁን ግን ግንኙነታቸው ከአቶ ሳህሉ ጋር በመሆኑ የተለየ መሳሳብ አንዳላቸው ያሳያል፡፡ ምክትል አሰልጣኙ አቶ አጥናፉ ናቸው ይባላል፡፡ ባለፈው ሐሙሰስ ኦኔራ ምክትላቸውን ደብድበዋቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ጉዳዩን የሰሙትን ቅር አሰኝቷቸዋል፡፡ በሥራው ሆነ በሌላ ጉዳይ ያለመግባባት ይፈጠራል፡፡ ይሄ ሲሆን ለሚመለከተወ ክፍል ማመልከት ነው የነበረበት በቡጢ ደበደበው ፡፡

ኦኔራ መደብደብ የፈለጉትና ብደበድብም ማንም አይነካኘም የሚያሻኝ ድርጊት ውስጥ የገቡት ፕሬዝዳንቱ ካለ ማንም አይነካኝም ብለው ነው፡፡ ነገሩ ‹ ጌታዋን የተማመነች በግ..›› አይነት ነው፡፡ ኦኔራም ፕሬዛዳንቱ ሁሉም ነገር እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡ አይዞህ ማንም አይነካህም የተባሉም ይመስላሉ፡፡ ተጠሪነታቸው ለፕሬዘዳንቱ ነው ሲባል ‹ የሥራ ብቻ ሳይሆን ቡጢንም ያማከለ ነው፡፡›

ኦኔራ ጥፋቱን ከፈፀሙ በኃላ ምንም የዲሲፒሊን እርምጃ አልወሰደባቸውም፡፡ ፌዴሬሽኑ ‹ በሕግም በዜግነትም› ለምክትል አሰልኙ መቆም ነበረበት፡፡ ምክትሉ በሐገራቸው ተደብድበው አይዞህ ባይና ደጋፊ በማጣታቸው አስገራሚ ነበር፡፡ ኦኔራ ግለሰብ ሳይሆን ሀገርን ነው የደበደበው በአገር ድብደባ ነው መጠየቅ ያለበት፡፡

በ1960 ናይጄሪያና ኢትዮጵያ ተጋጠሙ፡፡ ግጥሚያው ሹክቻ ነበረው፡፡ ኢታሎ ባሳሎ ከናይጄሪ ተከላካይ ጋር ተፋጠጡ፡፡ ያኛው ሰውነቱ ታርዛን ነው፡፡ በቦክስ ሲለው ኢታሎ ተዘረረ፡፡ ቁጭ ብሎ አየ፡፡ ‹‹ ሰው ጠፋ በገዛ መሬቱ›› አለ፡፡ ግጥሚያው የተደረገው አዲስ አበባ በመሆኑ ኢታሎ በገዛ ሐገሬ የሚያግዝልኝ ልጣ ወይ በሚል ነበር መናገር የፈለገው፡፡ ያሁኑም ድብደብ ናይጄሪያና ኢትዮጵያ ነው ደብዳቢው በትውልድ ናይጄሪያዊ ሲሆን ተደብዳቢው ኢትዮጵያዊው አጥናፉ ነው፡፡ አጥናፉዬ በሀገሩ የሚያግዝለት አጣ ኦኔራ አጥናፉን በጉልበት፣ በቁመት፣ በወርድ፣ በውፍረት፣ በደመወዝ ፣በስልጣን በሁለም ነገር ይበልጠዋል፡፡ ኳስ ሜዳም ላይ ናይጄሪያን ጨምሮ ሌሎች የምዕራብ አፍሪካ ሐገሮች በጉልበት የሚጨመድዱን አቅማችንን እያዩ ነው፡፡ በተክለ ሰውነት ኦኔራና አጥናፉንም ማነፃፀር በቂ ነው፡፡

በነገራችን ላይ የሁለቱ ፀብ ከቡድኑ ውጤት ሆነ ጨዋታ ጋር ምንም የሚያያይዘው የለም ቡድኑ የሚለካው ሜዳ ላይ በያዘው ነገር እንጂ በአሰልጣኞች መስማማትና ያለመስማማት አይደለም፡፡

በ1987 ቡድናችን ከግብፅ ጋር ሊጫወት ሲዘጋጅ ዋናውና ምክትሉ ተደባደቡ፡፡ ለገላጋይ አስቸገሩ፡፡ እንደተኮራረፉ ወደካይሮ ሄዱ ጥግና ጥግ ነው የሚቀመጡት፡፡ ( ቤንች ላይ ) ምግብም አብረው አይበሉም ልጆቹም ተጨነቁ፡፡ ሲመክሩም ነጣጥለው ነበር፡፡ ቡድኑም 5 ለ 0 ተሸነፈ፡፡ ፌዴሬሽኑም አሰልጣኞቹ ባለመፋቀራቸው ነው ውጤት የጠፋው አለ፡፡ ከ2 አመት በኃላ በጣም የሚፋቀሩ አሰልጣኞች ተፈለጉ፡፡ ውጭ አብረው የተማሩ በጣም የሚቀራረቡ፡፡ የቤተሰብ ያህል የሚዋደዱ ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ አብረው ያሰለጠኑ ተመረጡ እነኚህ ለመፋቀራቸው ምስክር አያሻም ነበር፡፡ ቡድኑን ግብፅ ይዘው ሄዱ ፡፡ 8 ጎል ተቆጠረባቸው፡፡

የተጣሉትም የተፋቀሩተም አንድ አይነት ቡድን ነው የያዙት ችግሩ የመፋቀርና ያለመፋቀር ሳይሆን ቡድኑ ሜዳ ላይ ብልጫ የሚያዝበትን ጨዋታ ያለማግኘቱ ነው፡፡ አሁንም የኦኔራና የምክትላቸው ፀብ ከቡድኑ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም ጥፋተኛው ታውቆ የዲሲፒሊን እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ እርምጃ የማይወሰድና ድብድቡን በፀጋ የሚቀበል ከሆነ ፌዴሬሽን ስሙን ቀይሮ ‹‹ የእግር ኳስ› መባሉ ይቀርና ‹ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን› በሚል እንዲጠራና በቦክስ ህግ መሰረት ለሁለቱም ነጥብ መሰጠት አለበት፡፡ የአሸናፊውም ኢትዮጵያን ወክሎ በኦሎምፒክ ቦክስ ይሳተፋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የእኛ ናቸው የሱዳን?

የኢትዮ
ጵያ እግር ኳስ ፕሬዘዳንት አቶ ሳህሉ ካርቱም ላይ ኮንጎና ሱዳን የሚያደርጉት ጨዋታ ለመታዘብ ሄደዋል፡፡ ረቡዕ ነሐሴ 26 እለት የብሔራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች ሰበሰቡና ‹‹ እኔ እንግዲህ ወደሱዳን መሄዴ ነው›› በሚል ተጫዋቾቹን ተሰናብተዋቸዋል፡፡ ተጫዋቾቹም ግራ ተጋቡ፡፡ ምክንያቱም ሰርግ ደግሶ ‹ እኔ አልኖርም› እንደማለት ነው የቆጠሩት፡፡

አንዳንዶቹ እንዲያውም ‹‹ እኝህ ሰው የሱዳን ናቸው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት›› እስከማለት ደረሱ፡፡ የፕሬዘዳንቱ ሐገር ውስጥ መኖር ለብዙ ነገር ይጠቅማል፡፡ አብዛኛውን የፌዴሬሽን ስልጣን ጠቅልለው እንደያዙ ይነገራል፡፡ ስልጣኑ በእጃቸው እስካለ ድረስ እሳቸውን የሚፈልግ ብዙ ውሳኔ ይጠበቃል ስለዚህ ከጨዋታው መዳረሻ አንስቶ እስከ እሁድ ድረስ በግዴታ መኖር አለባቸው፡፡ የእሳቸውን ሞራል ድጋፍ የሥራ ትዕዛዝ ወከባና ሽር ጉድን ጨምሮ መኖራቸው አስፈላጊ ነው፡፡ ከሞራ አንፃር እንኳን ልጆቹ ጋር ሄደው እኔ አልኖርም ሲሉ ታዲያ ማነው የሚኖረው የሚል ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል፡፡ እሳቸው አንዲታዘቡ ጨዋታ ለውድድር ሲሰጣቸው ‹‹ የሐገሬ ቡድን ሜዳው ላይ ሲለሚጫወት ይሄ ታዛቢነት ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልኝ ›› ማለት ይችላሉ፡፡ ካፍ ብዙ ታዛቢ አለው ሊቀይርላቸው ይችላል፡፡

መሄድ ስለፈለጉ ግን ካፍ ተቀብሎአቸዋል፡፡ የእሳቸው ታዛቢ ሆኖ መሄድ በእግር ኳስ ውስጥ ምንም ቦታ የለውም፡፡ ካፍ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶቸን በታዛቢነት ይመድባቸውል፡፡ 40 ፕሬዝዳንቶች ካሉ 40 ቡድን ለውድድር ቢገባ የሚኖረው ጨዋታ ግን 20 ነው፡፡ 20 ታዛቢዎች ትርፍ ሆነው ሌላ ጨዋታ ነው የሚጠብቁት ትርፍ ታዛቢ ስላለ የእኛ ፕሬዘዳንት እዚህ መቅረት ይችሉ ነበር፡፡

በመሄዳቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚጠቀመው ነገር የለም፡፡ ግለሰቦች በግል ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ጉዞው ከፍተኛ አበል አለበት፡፡ ክፍያው በዶላር ነው፡፡ ዶላር ደግሞ አሁን ከፍ ብሏል፡፡ በዚህ መንገድ ጠቀሜታ አለው፡፡ በሌላ በኩል ግን እዚህ ዝግጅት እያለ ጥሎ መሄድ አግባብነት የለውም በታዛቢነት መሄድ እንኳን ቢያስፈልግ ኢትዮጵያና ጊኒ ጨዋታቸውን ኮናክሪ ላይ ቢያደርጉ እዚህ ምንም ዝግጅት ስለሌለ ፕሬዝዳንቱ ወደሌላ ሐገር በታዛቢነት ቢሄድ ችግር የለውም፡፡

አሁን ግን ጨዋታው አዲስ አበባ ላይ ነው የሳቸውን እዚህ መሆን የሚያስፈልጉበት ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አሰልጣኝና ምክትሉ እንኳን ሲጣሉ አሰልጣኙ ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳንቱ ስለሆነ ጉዳዩን የሚፈታ ሰው እንኳን አልተገኘም ብዙ ትርምሶች እያሉ ሰውየው ለጉዞአቸው ቅድሚያ ሰጡ፡፡ አንዳንድ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት በሰውየው ላይ ቅሬታ አላቸው፡፡ ‹‹ የአገር ውስጥ ስራቸውን ትተው የውጭ ጉዞ አብዝተዋል›› ይላሉ፡፡ የውጭ ጉዞ ሲኖር ደግሞ ብቻቸውን ነው የሚሄዱት ለማንም እድሉን አይሰጡም ለዚህም ነው ‹ተጓዥ ፕሬዝዳንት› የተባሉት፡፡

ሽሽት

ፌዴሬሽን አካባቢ ሽሽት ያለ ይመስላል፡፡ የፕሬዝዳንቱም የውጭ ጉዞ ቡድኑን ጥሎ ከሐገር ውስት እንደመሸሽ ይቆጠራል፡፡ የቴክኒክ ሐላፊው አቶ ዮሐንስም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቴሌቪዥንና በጋዜጣ እንደገለፁት ‹የዋናውን ብሔራዊ ቡድን ጉዳይ እኔን አይመለከትም› በሚል ተናግረዋል፡፡ እሳቸውም ሽሽት ነው የያዙት፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ጉዳይ እኔን ይመለከተኛል፡፡ ብሎ ሐላፊነት የሚወስድ አላየንም፡፡ ታዲያ ማንን ነው የሚመለከተው?፡፡

አቶ ዮሐንስ የቴክኒክ ሐላፊ እንደመሆናቸው መጠን በማስሚዲያ እኔን አይመለከትም የሚለው መግለጫቸው በስፖርት ቤተሰቡም በስፖርተኛውም የስነልቦና ጫና መፍጠር ነው፡፡ ሁሉም ከሸሹ ማነው ሐላፊነቱን ወስዶ የሚሰራው? የቴክኒክ ሐላፊው በብሔራዊ ቡድኑ ዙሪያ እኔን አይመለከተኝም የሚለውን ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ‹‹ እኔ የመጣሁት በሁለተኛ ዙር ላይ ነው፡፡ ተጨዋቾቹን አላውቃቸውም፡፡ ስለዚህ ለመስራት ያስቸግረኛል›› ብለዋል፡፡

አሰልጣኙ ከአቶ ዮሐንስ በአራት ወር ዘግይተው ነው የመጡት አንድም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አላዩም ኦኔራ ምንም ለማያውቋቸው ተጨዋቾች ሐላፊነት ወስደው እየሰሩ ቴክኒክ ሐላፊው 6 ወር ተቀምጠው ብዙ ጨዋታ አይተው ልጆቹን አላውቃቸውም ቢሉ ነገሩ አስገራሚ ነው የሚሆነው፡፡ በተጨማሪም ሲናገሩ ‹‹ እኔ አሁን በታዳጊ ቡድኑ ብቻ ነው መቶ በመቶ ሐላፊነቱን የምወስደው›› ብለዋል፡፡ የዋናው ቡድን ሐላፊነት የማይወስዱት ግን ‹ተጨዋቾች ስለማላቃቸው› በሚል ነው፡፡ እሳቸው የመጡት በመጋቢት ነው፡፡ በሰኔ የተመረጡትን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ነው አላውቃቸውም ያሉት ፡፡ በሚያዝያ ለተመረጡት ተዳጊ ቡድን ግን አብረው ሲሰሩ አሳውቃቸውም አላሉም፡፡ አብረው ሰርተዋል፡፡ ለሚያዝያው ነው ለሰኔው ነው ሐላፊነት መውሰድ የነበረባቸው?፡፡

ስድስት ወር ቆይተው ተጨዋቾችን አላውቃቸውም በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ ሐላፊነት አልወስድም ማለት ሽሽትና ብሔራዊ ግዴታን አለመወጣት ነው፡፡ ሁለት ወር የቆየው አሰልጣኙ እንኳን በብሔራዊ ቡድን ላይ ትልቅ ሐላፊነት አለበት፡፡

የአባላት መውጣት

አንዳንድ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴዎች የፌዴሬሽኑ ውሳኔዎች የጥቂት ግለሰቦች ነው በማለት ማውራት ጀምረዋል፡፡አንዳንዶቹም ምን እናደርጋለን በሚል ስብሰባ እየቀሩ ነው፡፡ ሰውየውም ብቻቸውን ነው ወደውጭ የሚሄዱት፡፡ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባልና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ወንድሙ ከስራ አስኪያጅ ኮሜቴ በቃኝ ብለው ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ ሌሎችም ይቀጥላሉ፡፡ ፌዴሬሽን አካባቢ ስርኣት እየጎደለ ነው፡፡

ጊኒ አሯሯጠን

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪየቀው ጨወታ የኢትዮጵያና የጊኒ ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ 30 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ተጋጠሙ፡፡ በውጤቱም ጊኒ 4 ለ 1 አሸነፈች፡፡ ቦታውም አበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው፡፡ አበበ ቢቂላ የዛሬ 50 ዓመት ለኛ የድል ታሪክ አፅፎ ነው የጀመረው? በ50 ዓመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በድል አድራጊው ጀግናችን ስታዲየም ሽንፈት ነው ያሳየን፡፡ በአዲሱ ፕሬዝዳንት በአቶ ሳህሉ መሪነት /ይቅርታ እርሳቸው የሚመለከታቸው የሱዳን ጫወታ ነው/ በከፍተኛ የግብ ሸንፈት ማጣሪያውን ጀምረናል ‹አጀማመራችን የግብ ጎተራ አጨራረሳችን ውራ› እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡

ከአንድ ያላለፈ

ኢትዮጵያ ጊኒ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ1968 በ10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ነው፡፡ ጊኒ 2 ለ 1 አሸነፉ የማሸነፊያውን ግብ ያገቡት ጨዋታ ሊፈፀም 6 ደቂቃ ሲቀር ከክንፍ የመጣ ኳስ ነው፡፡ አገቢው በቴስታ ነው ከ30 ዓመት በኋላ ጊኒ በቴስታ አለቀቀንም፡፡ አሁንም አብዛኛው በቴስታ ነው ያገቡት ኢትዮጵያና ጊኒ አዲስ አበባ ላይ 4 ጨዋታ ነው ያደረጉት የኛ በ4 ጨዋታ 4 ጎል ነው ያገባው የነበረው በየጨዋታው አንድ ጎል ያገባነው ይህም ነሐሴ 30 ተረጋገጠ 1968 2 ለ 1 ተሸነፍን 1974 1 ለ 1 ወጣን፣ 1995 1 ለ 0 አሸነፍን አሁን ደግሞ 4 ለ 1 ተሸነፍን 4ቱንም ጊዜ ከአንድ በላይ አላገባንም ፡፡ ባለፈው እሁድ ኢትዮጵያ ቀድማ አገባችና የአንድ ግብ ኮታውን ጨረሰች ‹‹ ያለዎት ጎል አንድ ብቻ ነው ተጨማሪ ለማግባት ሌላ ጨዋታ ይጠብቁ፡፡››

የጎል ጎተራ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአገር ውጪ ነው ብዙ ጎል የሚቆጠርበት ይህ የተለመደ ነው፡፡ በእግር ኳስ ወጋችንም ባህላችንም ሆኗል፡፡ ጊኒ ግን አገሩ ላይ ሳሆን አገራችን ላይ ነው በጎል ነገር የሚፈልገን፡፡ እኛ አሁን ከጊኒ ጋር 6 ጨዋታ አድርገን 12 ጎል አስቆጥረውብናል፡፡ከ 12 ውስጥ 7 ያገቡት አዲስ አበባ ነው፡፡ ይህም ጊኒ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ የጎል ቅርጫት አደርጋታለሁ ብሎ ነው የመጣው ፡፡ ይህ ማለት እኛ ለጊኒ የጎል ኮርፖሬሽን ነን ማለት ነው፡፡ በ1989 ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ'ግብፅ 'ሞሮኮና ሴኔጋል ተደለደሉ፡፡3ቱ ቡድኖች ኢትዮጵያ ላይ በሚያገቡት ጎል ነበር የተለያዩት ግብፅና ሴኔጋል በነጥብ እኩል መጥተው በጎል ተበላልጠው ነው አንዱ አልፎ ሌላው የወደቀው ሴኔጋል ኢትዮጵያ ላይ ደርሶ መልስ 6 ሲያገባ ግብፅ ደግሞ 9 አገባ ሴኔጋል ወድቆ ግብፅ አለፈ በ 1958 ለ5ተኛ አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ 'ሴኔጋል ' ቱኒዚያ ተደለደሉ ከምድብ አንደኛ የወጣ ነው የሚያልፈው ሴኔጋልና ቱኒዚያ ተጫወቱና 1ለ1 ተለያዩ ሁለቱ ለማለፍ ኢትዮጵያ ላይ በሚያገቡት ነው የሚለው ኢትዮጵያ 2ቱንም አሸንፋ የማለፍ አቅምም መብትም እንደሌላት ነው የተቆጠረው እንደተገመተውም ቱኒዚያ ኢትዮጵያን4 ለ0 አሸንፋት በቀጣዩ ሴኔጋል 5 ለ 1 አሸንፋት ለዋንጫ ማን እንደሚያልፍ ግራ አጋባ ጉዳዩ ለፊፋ ተላከ ፊፋም መልሶ ሲልክ 10 ለ 1 ካሸነፉ ይልቅ 1ለ0 ያሸነፈ ዋጋ አለው በሚል መልስ ስለሠጠ ሴኔጋል ወድቃ ቱኒዝያ አለፈ ይህ ሁሉ የተከሰተው ቡድናችን የጎል ጎተራ ስለሆነ ነው ይህ የቆየ ታሪካችን ነው እስካሁንም ማደስ አልቻልንም የኢትዮጵያ ህጋዊ ፕሬዝዳንት የሚባሉት ሌተናል ኮነሬል ከበደ ገብሬ ናቸው በ 1948 የመጀመሪያውን የነጥብ ጨዋታ ስናደርግ ከግብፅ ጋር 4 ለ 1 ተሸንፈን ነው፡፡ ከ 52 አመት በኃላ በአቶ ሳህሉ ፕሬዝዳንትነትም የ 4 ለ 1 ሽንፈት ታይቷል፡፡ ላለፉት 50 ዓመታት ስተት መድገም ነው የታየው፡፡

አሁንም ከምድባችን አንድ ቡድን ነው የሚያልፈው፡፡ ጊኒና ናይጄሪያ ኢትዮጵያ ላይ ጎል እንሸምታለን ብለው ነው የሚመጡት (እንደተለመደው)

የዶሮ እግር

ነሐሴ 30 በተደረገው ጨዋታ ተጫዋጮቻችን በጉልት ተበልጠዋል ለመጠቀም የሚፈልጉት ደግሞ በጉልበት ነው በጉልበት መብለጥ እንደማንችል እየታወቀ ይህን መጠቀማቸው ለሽንፈት መዘጋጀታቸውን ያሳያል ወጣ ያለ ነገር አይሞክሩም ፡፡ ተጫዋቾቻችን እግራቸው ቀጭን ነው፡፡ አንድ ተጫዋቾቻችን ያዩ የቤት እመቤት እንዳሉት ‹‹የኛ ተጫዋቾች እግራቸው የዶሮ ነው የሚመስለው በዚህ ላይ ዝናብ ሲነካቸው እንደዶሮ ተኮማተሩ ብለዋል ፡፡ ተጫዋቾቹ ዝናቡ ገምባሌያቸውንና ቁምጣቸውን ስላራሰው መሸከም ከብዶዋቸዋል ኳሱም ውሀ ስለጠጣ በዶሮ እግራቸው መግፋት አቃታቸው ይህ የዕግር ቅጥነት ሁሉ ቦታ እያሳጣን ነው፡፡አሜሪካን ሀገር ሀበሾችን ያየ አንድ ፈረንጅ ወጣቱ ሀበሻ በቁምጣ ነው የሚሔደው የሀበሻው እግር ቀጭን ነው (የዶሮ) ፈረንጁ የሀበሻውን እግር አየና ‹‹እነኚህ ሀበሾች በእጃቸው ሲሄዱ ትን አይላቸውም? ›› ብሏል እጅ እንጂ እግር አልመሰለውም፡፡በዚህ ቀጭን እግር የምዕራብ አፍሪካ ቡድኖች በጉልበት መግጠም ከመበለጥ በስተቀር ትርጉም የለውም፡፡ ለቀጭኑ ልጅ ትልቁ ችሎታው ጭንቅላቱ ነው፡፡ጭንቅላቱ ደግሞ ዕውቀትን ነው ያቀፈው መረዳዳትን ማዕከል ያደረገ እግር ኳስ በዕውቀት በመጫወት ጉልበታችን መብለጥ ይቻላል፡፡ ይህንን የሚረዳ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ነው የጠፋው አቶ ሳህሉም የትላንቱን ውድቀት ነው የደገሙት፡፡

አበበና ማሞ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ነች በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍፃሜ ቀርባለች? ከማን ጋር ስትጫወት ነው ለዋንጫው የደረሰችው፣ በግብፅ 4 ለ 0 ተሸንፋለች፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ በፍፃሜ ጨዋታ 4 ለ 0 የተሸነፈ የለም እስካሁን ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሁለተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ግብፅ ላይ ተካሄደ 4 ለ 0 ተሸነፍን በምድብ ጨዋታ ይህ ሪከርድ ነበር ጊዜው 1951 ነው ነው፡፡ በ1952 አበበ ቢቂላ በሮም አሎምፒክ የማራቶን ሪከርድ ሰበረ ከ4 ዓመት በኋላ አበበ በቶኪዮ ሪከርድ ሰብሮ አሸነፈ ብሔራዊ ቡድናችን በሴኔጋል 5 ጎል ተቆጠረበት ይህም በራሱ ተይዞ የነበረው ሪከርድ አሻሻለው፡፡ 1961 ማሞ ወልዴ በስፔን 10 ሺ ኪ.ሜትር ሪከርድ ሰበረ ከ6 ወር በኋላ ብሔራዊ ቡድናችን በ7ተኛ አፍሪካ ዋንጫ 6 ለ 1 በመሸነፍ በብዙ ጎል የመሸነፍ ሪከርድ ሰበረ እስካሁን ይህ ሪከርድ ማንም አልሰበረውም በኛ እጅ ነው ያለው፡፡ ማሞና አበበ በኦሎምፒክ እና በታላላቅ ውድድሮች ሪከርድ ሲሰብሩ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድናችን ለአፍሪካ ውድድር በሽንፈት የብዙ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡ አዲዳይብ የተባለ የግብፅ ተጫዋች በፍፃሜ ጨዋታ 4 ግብ እኛ ላይ በማስቆጠር እስካሁን ሪከርድ ይዟል፡፡ በምድብ ግጥሚያ ደግሞ በአንድ ጨዋታ 5 ጎል በማስቆጠር ሪከርድ የያዘው የአይቮሪኮስት ሎረንት ፓኩ ነው እሱም እኛ ላይ ነው፡፡ በግልም በቡድንም በአፍሪካ የሪከርድ ባለቤት ነን፡፡ እስካሁን የትላንቱ ስህተት የሚያርም የፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ነው ያጣነው የአሁኑ የጊኒ 4 ለ 1 ሽንፈት የተለመደው ስህተት እስካልተሻሻለና ወጣ ያለ አስተሳሰብ ያለው ፕሬዝዳንት እስኪገኝ ውጤቱ ይቀጥላል፡፡

የበረኛ ኮርስ

ቴክኒክ ዳይሬክተሩ የበረኛ ስልጠና ኮርስ ሠጥተው ነበር ነገር ግን ጎሉ በኛ ላይ በዛ ኮርሱ ጥቅሙ ምንድነው? የበረኛ ስልጠና ኮርስ ስለተሠጠ ግቡ አይቀንስም መሆን ያለበት ወደኛ ግብ የሚመጣውን ኳስ ሊቀንስ የሚችለ ስልጠና መስጠት ነው፡፡

የመሸነፍ ልምዳችን

በጊኒ 4 ለ 1 መሸነፋችን ምንም አይደንቅም ለብዙ ጊዜ በሀገራችን ተሸንፈናል ከሀገር ውጭም እነደዚሁ ያሁኑ የ4 ለ 1 ሁኔታ ያካበትነውን የመሸነፍ ልምድ ተጠቅመን ነው የተዘረርነው፡፡ ያለን ልምድ ማሸነፍና መብለጥ ሳይሆን መበለጥና መዘረር ነው፡፡

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby geremew » Mon Sep 13, 2010 10:23 pm

ከውጤቱ ተነስተን የአሰልጣኙን ብቃት መፍረድ የቸኮለ ውሳኔ ቢሆን እንክዋን ከስነምግባር አንጻር ተቻችሎ መስራት ባለመቻሉ እና ለሚያሰለጥናቸው ተጫዋቾች bad example በመሆኑ ከተሰተው ሀላፊነት ቢነሳ መልካም ነው:: ምናልባት ለውጤቱ መጥፋት ተጠያቂ ላለመሆን እና በምክትሉ ለማሳበብ የተደረገ ይመስላል:: ነገር ግን youtube ላይ post ከተደረገው የተጫዋችነት ባህሪ ተነስቶ ሰውየው ግንፍልተኛ እንደሆነ ማወቅ ቀላል ነው::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ንጉሥ ጦና » Thu Sep 16, 2010 11:05 pm

በስፖርቱና በውጤቱ ላይ የተንሸራሸሩትን ሀሳቦች የተሰነዘሩትን ትችቶች እና የተጠቆሙትን አቅማዊ ግምጋሜ በጥሞና ነው የተከታተልኩት: አቅምን ያገናዘቡና አልዳንዶቹም በእውነታ ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸው አስደሳች ነው በውነት እኔም ያለቺኝን እንድል ያነሳሳኝ ጠቃሚ የውይይት መድረክ በመሆኑ ነው::
ከላይ እንዳነበብኩት አሰልጣኙ በወር 13 ሺህ ዶላር አማካሪውም 35 ሺህ ብር ይወስዳሉ ምናልባት አንዱ ጥሩ ተጫዋች የሚከፈለው ደግሞ የአማካሪውን አንድ አራተኛ አያክልም::
እኔ እንደሚመስለኝ ይሄ የስህተቱ መጀመሪያ ነው
ተጫዋቹ በክለብ እስከተቀጠረ ድረስ ለብሄራዊ መጫወት እንደወታደር የግዴታ ያህል እስኪሆን ድረስ በቂ የብሄራዊ ክፍያውን አያገኝም እኔ እስከማውቀው እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ አንድ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የሚያገኘው ክፍያ ኪስ የሚገባ አይደለም::
እነዚህ ነጥቦች ብቻቸውን ለስፖርቱ መቀጨጭ በቂ ምክንያት ናቸው ብዬ አምናለሁ::

ተጫዋቾቹ ከየክለባቸው ይጠሩና ማጣሪያው ወር ሲቀረው ሆቴል ይገባሉ ዝግጅት ይጀምራሉ ጨዋታው ሲያልቅ አስታዋሽ የላቸውም እንደገና ሌላ ጨዋታ ሲመጣ አዲስ ምልመላ ይደረግና ተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላል::

አንድ ጸሀፊ ባለፈው ሰሞን አንድ የሰጠውን አስተያየት አንብቤ ተደንቄያለሁ "" የትምህርት ቤት ስፖርት የማይጀመረው ለምንድነው ? መጀመር ምኑ ነው የሚከብደው ? የሚል ነው::
በጣም ትክክለኛ ቀላልና ዋና መፍሄ ነው ይሄንን የሚያስብ ሰው ግን እውነትም አልተገኘም::
ሁልግዜ ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ነው
ለስፖርቱና ለስፖርተኛው የሚሰጠው ክብር ለቀጣይ ትውልድም ለሀገራችንም ያለው አወንታዊነት ችላ ተብሏል::
አንድ ስመጥር የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረ ከጊዜ በኍላ በሚያሳዝን የኑሮ ወጥመድ ውስጥ ወድቆ ሲገኝ የሚያዩት ልጆች ታዳጊዎች ስፖርተኞችም ሁሉ የሚያድርባቸው የሞራል ክስረት ምን ያህል እንደሆነ መገመት አይከብድም::
አንድ ምሳሌ እንውሰድ
በኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቱ ትውልድ በየትኛው የስፖርት አይነት ነው ራሱን ሲያለማምድና ሲጥር የሚታየው ? አያጠራጥርም በአትሌቲክሱ ነው ::
ይሄ ከላይ የጠቀስኩት ተጽዕኖ ጥለት ነው ስፖርቱ የሚሰጠው ግምት የተፈለገበት ደረጃ ላይ መድረስ አለበት ከምንም በላይ ለስፖርተኞቹ በቂ ክፍያ ሊያገኙ ይገባል:: መንግሥት መደጎም አለበት ፌዴሬሽኑም በቋሚነት ሊያስብላቸው ይገባል::

የኢትዮጵያ ፉትቦል ችግር መፍትሄው ከባድ አይደለም መሪዎቹ ናቸው ከባድ :: የሚገርመው ጋዜጠኞቹም ከትችት የዘለለ መፍትሄ ጠቋሚ የሆነ ዝንባሌ ያለው ሀሳብ በብዛት ሲሰነዝሩ አይታዩም::
በአለም በአፍሪካም ስፖርት እንዴት እያደገ እንደሆነ ያውቃሉ ይመለከታሉ ያነባሉ በሀገራችን ይህ እዲደረግ ከመጋደል ይልቅ ይተቻሉ ይጠይቃሉ የሚሰጣቸውን መልስ እንደቃለ አጋኖ እየደጋገሙ አብረው ይከርማሉ:: ይህም ሆኖ ግን የተሻሉት ታጋዮች እነሱው ናቸው::
ባጠቃላይ ኢትዮጵያ በፉትቦል ታሪክ በአፍሪካ ቀዳሚ ከመሆኗ ጋር ህዝባችን ስፖርቱን ወዳድ ስለሆነ ለፉትቦሉ ማደግ ያለንን ሀሳብ መሰንዘሩ አስፈላጊ መስሎ ስለታየኝ ነው ይህቺን ያልኩት:
ተድላን እና ሌሎቻችሁንም አመሰግናለሁ
ንጉሥ ጦና
ንጉሥ ጦና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Sun Jun 10, 2007 9:12 pm
Location: europe

Postby ኮሎኔል » Sat Sep 18, 2010 8:43 pm

ወንድሜ ንጉሥ ጦና
ልክ እንደ እንደ ትንቢት በተናገርከው ኩዳይ ላይ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የስፖርት ፕሮግራም ላይ እንደአጋጣሚ አንድ ወዳጄ ቤት ሆኜ ተከታተልኩ
ያንተን አንብቤ ስለነበር ገርሞኝ ነው የጻፍኩት
የስፖርተኞች መጨረሻቸው መጥፎ በመሆኑ መንግሥት ሊያስብበት እንደሚገባ ሀሳብ ብቅ እያለ ነው::
በዚህ ላይ እኔ ልጁን አላውቀውም ሲጫወትም አላውቅም አዲስ ልጅ ነው እግሩን ተሰብሮ ለህክምና ህዝባችንን ሲማጸን አይቻለሁ እንግዲህ ሲጫወት በነበረበት ግዜ ያለምንም ዋስትና ነበር ማለት ነው ይህ ሁኔታ ተስፋን ያስቆርጣል አንድ ተጫዋች ጉዳት ሊደርስበት ይችላል ከደረሰበት ህይወቱ አለቅለት ባይደርስበትም ኳስ እስኪያቆም ብቻ ነው እንጂ ጡረታም ሆነ ድጎማ የለውም ስለዚህ አንተ ያነሳህእው ጉዳይ ተገቢ ነው እላለሁ
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Sep 24, 2010 8:35 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

'geremew' : 'ንጉሥ ጦና' እና 'ኮሎኔል' ስለአስተያዬቶቻችሁ አመሠግናለሁ : ቀጥሉበት ::

ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብሁት ትንሽ ለዬት ያለ ጉዳይ ነው :: በወንዶች እግር ኳስ ዕድገት ያንንም ተከትሎ ውጤት እምቢ ካለን ቆዬ :: በሴቶች ግን የተሻለ ውጤት አለን :: ሴቶቻችን እስካሁን በሁለት የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድሮች በተከታታይ መሣተፍ ችለዋል : ለዘንድሮውም ከመጀመሪያው ማጣሪያ በቀጥታ አልፈዋል :: ባለፈው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ውድድር ለመሣተፍ የሚያስችላቸውን ዕድል ያጡት በመጨረሻው ዙር ውድድር ተሸንፈው ነው :: በዚህ ረገድ ከሊብሮ አዘጋጅ ገነነ መኩሪያ ጋር እንስማማለን ::

በሌላ ተመሣሣይ ዜና በዓለም ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ውድድር ጃፓናዊቷ ዩኩያማ 7 የሰሜን ኮሪያ ተጨዋቾችን አብዶ በመሥራት አስደናቂ ጎል አስቆጥራለች :: ጋዜጠኞች 'የሴቶች ማራዶና' ብለው ሠይመዋታል ::

Japanese player pulls a Maradona in Women's U-17 World Cup

የእኛስ ሴቶች ዕድሉን ብንሠጣቸው የተሻለ ማሣዬት አይችሉም ትላላችሁ ?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ንጉሥ ጦና » Tue Sep 28, 2010 11:35 am

ከዛሬ አስራ ምናምን አመታት በፊት አፍሪካዊው ላይቤርያዊው ዊሀ በኢጣሊያን ሀገር እንዲሁ አይነት ተመሳሳይ ጨዋታ አሳይቶ እንደነበር አስታወሰከኝ ::
የዊሀን ጨዋታ አይቼዋለሁ ከጎል እስከጎል ብቻውን ነው የበረረው እና የዛሬውም የ የኩያማ ድንቅ ክህሎት አለምን አስደምሟል::
ጨዋታውን አይቼዋለሁ ዛሬ የተገረምኩት ደሞ በጃፓናዊው ኮሜንታተር ነው በጣም በጣም ነው ደስ የሚለው ::
ታንክስ ተድላ
ንጉሥ ጦና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Sun Jun 10, 2007 9:12 pm
Location: europe

Postby ንጉሥ ጦና » Tue Sep 28, 2010 11:42 am

ንጉሥ ጦና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Sun Jun 10, 2007 9:12 pm
Location: europe

Postby ስጥ እንግዲህ » Tue Sep 28, 2010 12:56 pm

እንዳቂሚቲ እኛም አለን እኮ.......አንድ ጊዜ ጊዮርጊስ ከመቻል ጋር ለሰሚ ፋይናል ዋንጫ ሲጫወቱ ሙሉጌታ ከበደ ቀደም ብሎ ልምምድ ላይ ባለመገኘቱ አልተሰለፈም ነበር:: ጨዋታው ተጀምሮ ትንሽ እንደተጫወቱ መቻል የጫወታ ብልጫ አሳይቶ ጊዮርጊስን 1 - 0 መምራት ጀመረ::ጊዮርጊሶች ትንሽ መረበሽ ታየባቸው አሰልጣኙም አሥራት ጎራዴ ነበር መሰለኝ ትንሽ ደነገጠ:: ከእረፍት በሁዋላ ሙሉጌታ ከበደ ተለውጦ ገባ:: ከዚያም መቻሎችን ቀውጢ አደረጋቸው:: ከትንሽ ደቂቃ በሁዋላ ከሰሎሞን ሉቾ ተቀብሎ ከመሀል ጀምሮ ሁለት የመቻል ተጫዋቾችን አታሎ አስፋው ባዩን (የመቻል ብሎም ለብሕእራዊ ቡድኑ ዝነኛ ተከላካይ የነበረው ነፍሱን ይማረውና) በሚገርም ሁኔታ አልፎ ሲሄድ በሌላ ተከላካይ በድሉ ይመስለኛል ተጠልፎ ወድቆ ከወደቀበት ተነስቶ ኩዋሱዋን ከመረብ አዋህዶዋታል:: ጎሎዋን ካገባ በሁዋላ ክንዱን ሲያይ የወደቀበት ተልጦ ደምቶ ነበር:: ከዚያ በሁዋላ ጊዮርጊስ አንድ ሌላ ጎል አክሎ በጊዮርጊስ 2- 1 አሸናፊነት ጨዋታው ተፈጽሞዋል:: ይህ ትዝ ይለኛል::
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby ኮሎኔል » Thu Sep 30, 2010 10:05 pm

ስጥ አገላለጽህ ደስ ይላል ብዙ ስላስታወስከኝ ደስ አለኝ
እስቲ ትዝ የሚለንን የፉትቦል አስገራሚ ልዩ እና የማይረሱ አጋጣሚዎችን እንጻፍ

ኮሎኔል
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Oct 01, 2010 7:05 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ተሣትፏችሁ ከዚህ የሚከተለውን የሊብሮን ዘገባ ስቤ እንዳመጣ ገፋፋኝ :: ለካምቦሎጆ (ስቴድዬም) ደንበኞችም ብዙ ትዝታ ይጭራል ብዬ አምናለሁ ::

ምንጭ :- ገነነ መኩሪያ : መስከረም 20 ቀን 2002 ዓ.ም. ሊብሮ ጋዜጣ :: የሜዳ መግቢያ ዋጋ ጨመረ ::

የሜዳ መግቢያ ዋጋ ጨመረ
ሊብሮ ዜና - ሊብሮ ዜና

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሜዳ መግቢያ ክፍያ ጨምሯል፡፡ ክቡር ትሪቡን 50 ብር የነበረው 100 ብር፤ ጥላፎቅ 20 ብር የነበረው 50 ብር፤ አንደኛ ማእረግ (ባለወንበር) 10 ብር የነበረው 20 ብር፤ ከማን አንሼ 7 ብር የነበረው 10 ብር፤ ካታንጋ 3ብር የነበረው 7 ብር ምስማር ተራ 2 ብር የነበረው 3 ብር ሆኗል፡፡

በሰታዲየሙ የፅዳት፤ የውሃና ሌሎች ለስፖርት ቤተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ነገሮች ሳይሟሉ ነው ዋጋ የጨመረው፡፡ በ1954 ከ3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኃላ ለጥላ ፎቅ 1 ብር ክብር እንግዶች የሚቀመጡበት ቦታ 2 ብ ይከፈል ነበር፡፡ ሌላ ቦታ ወንበር ስለሌለ ካታንጋና ምስማር ተራ የሚባሉ ቦታዎች ለሰራተኛ .50 ሳንቲም ፤ለተማሪ መታወቂያ እያሳየ .25 ሳንቲም ከፍለው እንዲገቡ ይደረግ ነበር፡፡ ገንዘብ የሌላቸው ደግሞ ውጪ ይጠብቁና ጨዋውታ ሊያልቅ 20 ደቂቃ ሲቀር በሩ ተከፍቶላቸው ይገቡ ነበር፡፡ ወታደሩ በሰራኛ ሂሳብ የሚታሰብ ቢሆንም (ደመወዝተኛ ስለሆነ) ለስፖርት ያለውን ስሜትና ለሐገር አገልግሎት የሚሰጥ በሚል ደመወዙም አነስተኛ ስለሆነ በንጉሡ ትዕዛዝ በተማሪ ዋጋ .25 ሳንቲም እንዲከፍል ተደረገ፡፡

ብዙዎቹ መሬት ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ወታደሩ ግን ሔልሜቱን እንደ መቀመጫ ይጠቀምበት ነበር፡፡ ወታደሮቹ በብዛት ካታንጋ ነበር የሚገቡት ፤ካታንጋ የሚለውም ስም የተገኘው በኮንጎ የዘመቱ የኢትየጵያ ወታደሮች ካታንጋ በምትባል ከተማ ውስጥ ስለነበሩ ስታዲየም ሲገቡ በበዛት ከትሪቡን ፊት ለፊት ስለሚቀመጡ የ‹‹ካታንጋ ጓደኞች ››ቦታ ብለው ሰየሙት፡፡ስፍራው በዛውም ካታንጋ ተባለ፡፡

በ6ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመቀመጫዎቹ ደረጃ ሲሰሩ ምስማር ተራና ታሴራ በር 1 ብር እንዲከፈልባቸው ሆነ፡፡ ከማን አንሼ ቦታና ካታንጋ 2 ብር ሆነ ፡፡ ምስማር ተራ ገንዘብ ለመክፈል አቅም የሌለው ሰው የሚገባበት ቦታ ነው፤ ምስማር ተራ በ49 ዓመት 1.75 ነው የጨመረው ፡፡ያሁኑን ዋጋ የጨመረው ፌዴሬሽኑ ነው፡፡ምን አስቸኮላቸው?ጠቅላላ ጉባኤው እስኪጠናቀቅ ለምን አይጠብቁም? ውድድሩን ሊግ ኮሚቴ ከወሰደ የመጨመር መብቱ የክለቦች ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ሊጉ ለማን እንደሚሰጥ ጠብቆ ቢጨምር ምን ነበረበት ? አንዳንዶቹ በክለቦች ላይ ጫና ለመፍጠር(ውድድሩ ለሊግ ከተሰጠ) የተደረገ ነው ይላሉ ፤ሊጉ ለክለቦች ከተሰጠ ዋጋ መወሰን የእነሱ ይሁን፡፡

ዳቦ ባረረበት አገር : ባልተሟላ የስቴድዬም አገልግሎት (መጸዳጃ ቤቶቹን ያስታውሷል !) እናም በሌለ የእግር ኳስ ጨዋታ ይህን ያህል የዋጋ ጭማሪ ምን ይሉታል ?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Oct 18, 2010 2:05 am

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ገነነ መኩሪያ በየጊዜው ጣፋጭ የጥንት የእግር ኳስ ዜናዎችን እና አስገራሚ ድርጊቶችን ያስነብበናል :: ለዛሬው በ1960 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቡድን ከማዳጋስካር ጋር ለኦሎምፒክ ማጣሪያ ለመጫወት ሲዘጋጅ በወቅቱ የተደረገውን አንድ አስገራሚ ድርጊት ያስታውሰናል : ተከታተሉት ::

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ጥቅምት 7 ቀን 2003 ዓ.ም. : ሊብሮ :: ማዳካስካርን በባልዲ

ማዳካስካርን በባልዲ

ጊዜው በ1960 ነው፡፡ ወሩ ታህሳስ ነበር የማዳጋስካር ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ የመጣበት ወቅት ነው፡፡ ውድድሩ ለሜክሲኮ አሎምፒክ ማጣሪያ ነወ፡፡ የመጀመሪያው ጨዋታ አንታናናሪቭ ላይ ተካሄደ፡፡ ማዳጋሰካር አሸነፈ፡፡ የመልሱን ጨዋታ ለማሸነፍ አዲስ አበባ ላይ ምን ይደረግ? ተባለ፡፡ ማዳጋስካር ደረቅ ሜዳ ላይ እንጂ ጭቃ ላይ መጫወት አይችልም የሚል መረጃ ተገኘ፡፡ ወቅቱ ደግሞ ፀሐይ የጠነከረበት፤ ሜዳው የደረቀበት አዋራ የበዛበት ጊዜ ነበር፡፡ በሰው ሰራሽ ዘዴ ሜዳውን እናጨቅየው ተባለ፡፡ ውሃ ማመላለሻ ባልዲ ተፈለገ፡ በበቂ ሁኔታ አልተገኘም፡፡ የፌዴሬሽኑ የጥገና ሐላፊ አቶ ቪቼንሶ ዩሪያ ‹‹ለብሔራዊ ቡድኑ ዋጋ እንክፈል›› በሚል የስፖርት ቤተሰቡን አሰባሰቡ፡፡ የተነገረውም ሰው ተስማማ፡፡ከየአካባቢው ባልዲ ይዞ ከተፍ አለ፤አላማው ሜዳውን አጨቅይቶ ማዳጋስካርን እጅ ለማሰጠት ነው ፤የተሰበሰበው ሰው ጉባኤ ጀመረ፤ ወሃው በስንት ሰዓት ይፍሰስ አለ፡፡ ጥዋት ከፈሰሰ ፀሐዩ ይመታወና ተመልሶ ይደርቃል ተባለ፡፡ ከምሳ በኃላ ይሁን በሚለው ተስማሙ፡፡ ማዳጋስካ ወደሜዳ ሳይመጣ ዳኛና ኮሚሽነሩ ሳያዩ ‹ በዘመቻ ባልዲ› ስራው ተጀመረ፡፡ የዛሬ 40 አመት ውሃውን ካፈሰሱት ውስጥ አንዱ አቶ ደበበ እንግዳወርቅ እንዲህ ይላሉ ‹‹ የፌዴሬሽኑን ሻይ ቤት ኮንትራት የያዘው አቶ ወልዴ ይባላል፡፡ እኔ ባልዲውን ያመጣሁት ከእሱ ቤት ነው፡፡ አቶ ቪቼንሶ ቶሎ በሉ እያሉ በባልዲ እያመላለስን ማፍሰስ ጀመርን፡፡ በተለይ በረኛው አካባቢና የእነሱ ጎበዝ የሚባለው ልጅ የሚጫወትበት ቦታ ትከሻችን እስኪላጥ ድረስ አፈሰስን፡፡ የጀመርነው 7 ሰዓት ነው አጨቅይተን ወደማብቂያችን ላይ ተመልካቹ እየገባ ነበር፡፡ በጎን ደግሞ ሰጋቱራ እናፈሳልን ምክንያቱም እንዳይታወቅብን ለዘዴ ነው፡፡ ያፈሰስነው ውሃ ለእኛ የሚመች ለእነሱ የሚያስቸግር አደረግነው፡፡ በእርግጥም ማዳጋስካር በጭቃ መጫወት አቃተው፡፡ ቡድናችንም አሸነፈ፡፡ ባልዲ ስራውን ሰራ፡፡ አንድ ቀን ግን ለእኛም መጥፎ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ ሱዳን በጭቃ መጫወት ሐይለኛ ነው፡፡ ቡድናችን 1ለ0 እየመራ ከባድ ዝናብ ጣለ፡፡ ሜዳው ውሃ ሆነ አሰልጣኙ ሉቻኖ ነበር፡፡ እሱ ከእኛ ጋ ሆኖ ውሃውን ከሜዳው ጠርጎ ለማውጣት ብዙ ደከምን፡፡ ግን ውሃውን ማስወጣት አልቻልንም፡፡ ሱዳን በውሃ ላይ ጨዋታ ሐይለኛ ሆነ፡፡ ሁለት ጎል አስቆጥሮ በሜዳችን ላይ ነጥብ አስጥሎን ሄደ››ይላል ፡፡ነገሩ የማዳጋስካር ብድር ይሆን?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Nov 14, 2010 10:17 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

መቼም የካምቦሎጆ (ስቴድዬም) ወሬ ማለቂያ የለውም :: እስኪ የአህያን አገልግሎት አንብቡላት ...

ምንጭ:- ገነነ መኩሪያ : ረቡዕ ኅዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም. ሊብሮ :: የፊርማ ክፍያ ወጌሻ ጋር ደረሰ ::

የፊርማ ክፍያ ወጌሻ ጋር ደረሰ
ሊብሮ ዜና - ሊብሮ ዜና

ዕረቡ ሕዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ወሬ

በ1989 ዓ.ም ፋሲል አብርሃ ለኒያላ ክለብ ለፊርም ሲዘጋጅ ለፊርማዬ ብር ስጡኝ ብሎ እንደ ቀልድ በ1ሺ ብር ያስጀመረው ነገር ዛሬ 250ሺ ደርሷል፡፡ በቀጣዩ አሰልጣኞች የፊርማ ብለው መቀበል ጀመሩ፡፡ በቅርብ ደግሞ ያንድ ቡድን መሪ የፊርማ ወሰዱ፡፡ አሁን ደግሞ ተራው የወጌሻ ሆነ፡፡ ወጌሻ ትልቁ መሳሪያው እጁ ነው፡፡ እጅም ዋጋ አለው በሚል የፊርማ ተጠይቋል አደም የተባለ ወጌሻ አዳማና ፊንጫ እኛ ጋር መሆን አለብህ በሚል ክርክር ይዘውበት የፊርማ ተቀብሎ አዳማ ፈርሟል ዋጋው 10ሺ ብር ነው፡፡ በእርግጥ ፊንጫ 15ሺ ብር ሊሰጠው ፈልጎ ነበር ግን እሱ ቀድሞ ለአዳማ ፈርሟል አደም ኳስ ተጫዋች ሆኖ ያሳለፈ ነው፡፡ ለሐረርጌ ምርጥ፣ ለኢትዮ ሲሚንት እንዲሁም ለጊዮርጊስ ተጫውቷል ግብ ጠባቂ ነው ጥሩ ችሎታ ነበረው፡፡ ተጫዋች እያለ ለምን ለብሔራዊ ቡድን አይመርጡህም ብዬ ጠይቄው ጥሪ ሁሉ በዘመድ ነው እኔ በአየር ላይ ቁምጣዬን ብቀይርም አይመርጡኝም ብሎኝ ነበር፡፡ በትልቅ ክለብ ኳስ ተጫዋች ሆነው ካሳለፉት ውስጥ ለወጌሻነት የበቁት አደምና አቲሞ ናቸው፡፡ ረጅም አመት ደግሞ በአንድ ክለብ ውስጥ የቆዩት ኢሳቅ ሽፈራው (ቡና) ጥላሁን እሸቴ ( መቻል) ናቸው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወጌሻ ሆኖ የሰራው በርሔ ነው ጊዜው 1940 ነው፡፡ በርሔ የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ነው፡፡ ተጫዋች በተጎዳ ጊዜ ከጎል ወጥቶ ለተጎዳ ተጫዋች ህክምና ይሰጣል፡፡ ከጨዋታም በኋላ የተጎዱ ተጫወቾችን ያክማል፡፡ ፉዴሬሽኑ ወጌሻ ብሎ በኋላ የቀጠራቸው ማሚቴ ይባላሉ፡፡ የቡድኑ አጥቂ አመለወርቅ አምደዜና እንዲህ ይላሉ ‹‹ ማሚቴ ቤታቸው ለገሃር ነው ተጫዋቾች ሲጎዶ እሳቸው ጋር ይሄዳሉ በኋላ ፊዴሬሽኑ ቀጠራቸው፡፡ እሳቸው አልፎ አልፎ ነው ሜዳ የሚመጡት የተጎዳ ተጫዋች ግን ወደሳቸው ነው የሚሄደው፡፡

በ1943 አካባቢ ፌዴሬሽኑ አህያ ገዝቶ ነበር አህያዋ ለሜዳው ሳርና አፈር ከተለያዩ ቦታ አምጥታ ትበትናለች ከተለያየ ቦታ በሳምንት ሁለቴ ውሃ እያመጣች ታፈሳለች ሜዳውን ለመስራት ትልቅ አስተዋፆ አድርጋለች ተጫዋች ሲጎዳ በአህያዋ ይጫንና ማሚቴ ጋር ይወሰዳል ከታሸ በኋላ በአህያዋ ወደ ቤቱ ይሄዳል አህያዋ ለፌዴሬሽኑ እንደ ሰርቪስ ነች፡፡ አንዳንዶቹ ተጎዳን ብለው በአህያዋ ይሄዳሉ›› ይላሉ፡፡ከማሚቴ በኋላ በፊዴሬሽኑ ብዙ ወጌሻዎች ተፈራርቀዋል እንደ ማሚቴ ግን ቶሎ የሚፈውስ የለም እጅም ዋጋ አለው በሚል ለፊርማ በቅቷል ቀጣዩ ተረኛ ማነው የተጫዋቾቹን ያህል ክፍያ የሚያገኘው ማን ይሆን?

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests