by ጌታ » Wed Feb 02, 2022 4:01 pm
የአፍሪካን ዋንጫ ምንም የምከታተልበት አማራጭ ስለሌለኝ ስለዘገባህ አመሰግናለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ኳሊፋይ ማድረጓ ትልቅ ነገር ቢሆንም በፍጥነት ሄደን በፍጥነት መመለሳችን መቀለጃ ሆኖ አይቼዋለሁ፡፡ ፍጥነታችን ስንት የወርቅ ሜዳሊያ እንዳስገኘን ረስተውት ነው አይደል? - ቂቂቂቂ
በፈረንጆቹ 1990 ይመስለኛል ግብጾች ላለም ዋንጫ ኳሊፋይ ሲያደርጉ 'ለአፍሪካ ሳይሆን ለአረቡ ዓለም ክብር ነው የምንጫወተው' ሲሉ ከሰማሁ በኋላ ሁሌም እንዲሸነፉ ነው የምፈልገው፡፡ ይባስ ብሎ በዚያ ዘመን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አንድ ምድብ ይደርሰን ስለነበረ አዲስ አበባ ላይ አንድ ለአንድ እንወጣ እና ካይሮ ስንሄድ ለእያንዳንዱ ተጫዋች የሚበቃ ጎል አስቆጥረው ስለሚያሸንፉን ቂም ቢጤም አለብኝ፡፡ እንዳንተው የሊቨርፑል ደጋፊ ብሆንም ለሳላህ ፍቅር የለኝም፡፡የዛሬ ሦስት ዓመት ቻምፒዮንስ ሊግ ባርሴሎና የመጀመሪያውን ጨዋታ 3-0 አሸንፈው የመልሱ ጨዋታ ላይ ሳላህ ሳይሰለፍ ሊቬ 4-0 በማሸነፉ የሳላህ መኖር ምንም ጥቅም የለውም ብዬ እራሴን አሳምኛለሁ፡፡ ክሎፕ ብነግረው አልሰማ አለኝ፡፡ ሳዲዮ ማኔን ልክ እንዳገሬ ልጅ ነው የምወደው - ነገሩ ያገሬ አፍሪካ ልጅ ነው፡፡
የፍጻሜ ግማሽ ጨዋታ ዛሬ በኔ ሎካል ታይም 1:00 pm እንደሆነ ጉግል ነገረኝ፡፡ ባልከታተለውም ለሴነጋል እና ካሜሩን እወጥራለሁ፡፡ የኳስ ነገር አይታወቅም፡፡
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!