by ሙዝ1 » Sun Oct 02, 2022 11:02 pm
ኦህህህህ ትርንጎሻ
በጣም የሚገርም ነዉ። ሰሞኑን ዋርካ ትዝ እያለኝ ጎራ እላለሁና ይህችን ቤትሽን ማንበብ የጀመርኩት ከልጆቼ ጋር ከዙረት መልስ መክሰሴን በልቼ ነዉ። ይሄዉ አሁን በኛዉ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰአት ሆኗል። ከወንበሬም አልተነሳሁ!! የጀመርኩትን ዉስኪ አገባድጄ ወደ ስካሩ እየሄድኩ ነዉ መሰለኝ። ከምር ግን እንደዛሬ ብዙ ጠጥቼ ከደስታ ዉጭ ምንም ያልተሰማኝ ወቅት ማስታወስ አልችልም። ከልጅነት አብሮ አደግ ጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩትን ወርቃማ ጊዜ አያስታወስኩ የምጫወት አይነት ስሜት አየተሰማኝ ነበር --- ድንቄም ወርቃማ!!! የስድብ ወርቃማ አለዉ አንዴ? ። በዩቲዩብ ግጥሞችሽንም ሰሟሗቸው። ግሩም ናቸዉ!!! ድምጽሽን በመስማቴም ደስተኛ ነኝ።
ነገ በጠኋት ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ማድረስ የኔዉ ስራ ነበር፤ በዚህ አያያዜ የምነሳ አይመስለኝም። ማዳም ቀደማዊ እመቤት ጋር ጦርነት ከተከፈተ ምክንያቱ ይሄ ቤት እንደሆነ ይታወቅልኝ።
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...