የኮምፒውተር የሶፍትዌር እና ተዛማጅ ጥያቄዎች እና መረዳጃ..

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፋኖፋኖ » Tue Aug 31, 2010 5:10 pm

ወንድሜ / ኤህቴ ፋንፉኖ ለመልሱ ምስጋናዬ ይድረስዎ ብለናል ::
ዲቪዲ በኔሮ ወደ ሌላ ዲቪዲ ለመገልበጥ ብዙም ጊዜ አይወስድብኝም ከዩቱብ ላይ በሪያል ፕሌየር ወደ ሙዚቃ ላይብረሪዬ ያስገባሁት መዚቃ ነው ቁጭ አርጎ የሚያውለኝ :: በእርግጥ ኮምፕዩተሬ የበቃች የነቃች ነኝ ብዬ አልከራከርም ሆኖም ግን ይህን ያህልም የደከመች አይደለችምና ያልገባኝ ነገር አለ የሚል ግምት አለኝና መፍትሄ ብጤ ካለ ብታካፍለኝ / ብታካፍይኝ ዴስ ይለኛል :: ካልሆነም ማሊ ጎደኒ ነው !!!!


እስኪ ከሁለት አንዱን ሞክር

1. ሪልፕሌየር ቱልስ ሂድና ዳውንሎድ ስታደርግ ኮምፑተርህ ላይ ሳይሆን በቀጥታ ዲቪዲ(ዲ-ድራይቭ) ላይ ሴቨ አድርገው ( ማለትም በሪል ፕሌየር ቪዲዮ ዳውንሎድ ስታደርግ ዲፎልት ዳውንሎድ ፋይልህን ድራይቭ ዲ አድርገው) :; ሁለት ስራ ከመስራት ያድንሀል: ከዲቪዲ ወደኮምፑተር ኮፒ ማድረጉም ቀላል ነው

2. እስካሁን የቀዳሀቸውን ቪዲዮዎች ወደ ዲቪዲ ለመገልበጥ በቀላሉ ኮፒ እያደረክ ዲቪዲ (ድራይቭ ዲ) ላይ ፔስት አድርገው:: ሀይላይት ቪዲዮ-ቀኝ ክሊክ-ኮፒ.. ከዛ ድቪዲ ላይ ሂደህ ፔስት ማድረግ .......ይህ የሚቀልህ ይመስለኛል::
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

Postby ስማያት » Tue Aug 31, 2010 9:48 pm

ሰላም

የምትጠይቁትን ጥያቄዎች አንብቤ አንድ የተገለጠልኝን ነገር ላካፍላችሁ ወደድኩ:: የእክሉን ወይንም የሳንካውን ርእስ ጉግል ብታደርጉት ብዛት ያላቸውን የመረዳጃ መድረኮች ያቀርብላችሁዋል:: እነዚህ የመረዳጃ መድረኮች በርካታ በአለም ላይ ተሰራጭተው የሚገኙ, እንደናንተው ተጠቃሚ ግለሰቦች ተሰብሰው እክሎቻቸው የሚፈቱባቸው ናቸው:: ትንሽ የሚያስቸርግረው የጉዳያችሁን እቅጭ የሚያወሳ ርእሰ-ውይይት የማግኘቱ ነገር ነው:: ከልምድ ጋር ቅልጥፍና ስለሚመጣ ቆይቶ ክነትን ተካብታችሁ ማንኛውንም አይነት እክል መቅረፍ ትችላላሁ::

ለ17 አመታት በአስሊ ዘርፍ ሰርቻለሁ:: ከ1995 እ.ኤ.አ ጀምሮ እንደ መቅፀፍት ፍጥነት ከተፈለፈሉት መካነ-ድራዊ የመረዳጃ ማእከላት ውስጥ የፈለግሁትን አስሊያዊ መፍትሄ ሳላገኝ የቀረሁበት ግዜ የለም::

ከአስሊው ጋር በተያያዘ ምክንያት ጓደኛዬ በጣም ይደውልልኝ ነበር:: አምና ይህንን ነገር አንስቼለት, ሲደውልም ደጋግሜ ራሱ ፈልጎ እንዲያውቅ ስለገፋፋሁት አሁን የአስሊውን ዙርያ-ገባ በቅጡ አውቆ, አንዳንድ እርዳታ ስጠይቀው ራሱ አስሶ መልሱን ይሰጠኛል::

ይመች
ሰማያት ነኝ
ስማያት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 133
Joined: Tue Aug 18, 2009 7:53 am

Postby ስማያት » Sat Sep 04, 2010 2:48 am

ካለፈው አመት ጀምሮ አንጎሌን ሲበጠብጠኝ የነበረን ሳንካ ላካፍላችሁ:: አስሊዬ ኤክስ.ፒ ሲኖረው, ለብዙ አመታት ያላንዳች ችግር ሲሰራ ቆይቶ ድንገት ከአምና ጀምሮ አልፎ አልፎ በገዛራሱ ይባትል ጀመር:: ብተላው እጅግ የከረረ ከመሆኑ የተነሳ የአስሊው ቁሳቁስ ለምሳሌ ሲ.ፒ.ዩ እና ሜሞሪ የመሳሰሉ 100% ተይዘው ሌላ ከተጠቃሚው የሚመጣ አንዳችም ሥራ በማይሰሩብት ሁኔታ ታቅበው አያቸዋለሁ:: አስሊው በዚህ ሁኔታ ለ 1.30 ሰአታት ያህል በራሱ ብቻ ሲሯሯጥ ይቆይና ጋብ ይላል:: ይህ ሁኔታም በቀን እስከ 5 ግዜ ይደግማል, ማለት ኡደታዊ ይዘት አለው ማለት ነው:: ስሰራበት ቆይቼ ሳንካው ሲጀምር ጥዬ እስኪጨርስ መጠበቅ ይኖርብኝ ነበር:: በጣም የሚያበሳጭ እክል ነበር::

ለብዙ ግዜ ምክንያቱን ልረዳው አልቻልኩም ነበር, ኦ.ኤስ ኡን ጠርጌ አውጥቼ እንደገና እንዳልገጥም ብዙ ሰሪ-ተሰኪዎች (application software) አሉት:: እነሱን ዳግም መግጠም አልችልም, ወይ የበሁር ሲዲ ግልባጮች የሉኝም ወይ ከሰው ተውሼ የገጠምኳቸው ናቸው

አንዴ "ታስክ ማኔጀር" ውስጥ ስመለከት ይህ ሳንካ በጀመረ ቁጥር የሚነሳ አገልጋይ (ሰርቪስ) ልብ አልኩ:: wuauclt.exe ይባላል:: ከሱም ጋር አብሮ ከ ኦ.ኤስ ጋር የሚመጣ svchost.exe የሚባል አገልጋይም አብሮ ይነሳል:: የነዚህን ሁለት አገልጋያት የአስሊ ቁስ አጠቃቀም ይዘት ስመለከት 100% ሆኖ አገኘሁት:: ስለዚህ መገንዘብ የቻልኩት ምንድን ነው, እነዚህ ሁለት አገልጋያት በኡደታዊ ሁኔታ እየተነሱ አስሊዬን የሚያዣብሩት መሆኑን ነው:: ችግሩ የሁለቱንም ስም አለም-መረብ ላይ ፈልጌ ሳጣራ የ ኦ.ኤስ ክፍል እንደሆኑና በተለይ wuauclt.exe የሚባለው አገልጋይ የ ኦ.ኤስ አዝማኒ (MS update) ክፍል እንደሆነ ተረዳሁ:: ያ ከሆነ ይህ አገልጋይ እኔ በመረጥኩት ሰአት እይተነሳ ከ MS የተለቀቀ ዝማኔ መኖሩን አረጋግጦ, አስፈላጊውን አውርዶ ለተጠቃሚው በማሳወቅ ይገጥማል እንጂ በዘፈቀደው እየተነሳ ተጠቃሚውን ማጉላላት እንደሌለብት አወቅሁ:: ይህ ችግር ወይ የአስልዬ ማለት የ አስሊ-ደዌ (Virus) ነው ወይ የ MS ችግር ነው:: ለማንኛውም የ ኦ.ኤስ ዝመና ምርጫ የሚስተጥበት ሳጥን ላይ ሄጄ ይህንን ዝመና ምርጫ በሙሉ ስዘርዘው ሳንካው ተወገደ:: የሳንካው ኡደታዊ ምስረቃ አቆመ::

በነገራችን ላይ እዚህ ገጽ ሄጄ ነው ብዙ መረጃ ያገኘሁት:: እንደምታነቡትም MS ችግሩ የራሳቸው መሆኑን አምነው መፍትሄ ለመስጠትና ለማውጣት ቃል ገብተዋል::
http://social.answers.microsoft.com/For ... dcf9a9a03b
ስማያት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 133
Joined: Tue Aug 18, 2009 7:53 am

Postby ብእሬ » Tue Sep 14, 2010 4:55 pm

ሰላም የኮምፒተር ባለሙያዎች ሰሞኑን አንድ lap top ገዝቸ windwo 7 system ሰልማልቅ ባተርየ ቶሎ ቶሎ እያለቀ በዙ ይጀ መቀሳቀስ አልቻልኩም ስለዚህ የሚነካካ አለ እና እሰቲ የቱን ብጠቀም ነው ረጅም ግዜ ሊያገለገል የምችለው ?
ምላስ አጥንት የለውም
ግን አጥንት ይሰብራል
ብእሬ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 63
Joined: Wed Aug 18, 2010 6:53 pm
Location: no

Postby ፍልፈሉ » Sun Jul 15, 2012 7:41 am

እንደምን አላችሁ ወገኖቼ? አንድ ችግር ቢገጥመኝ ነው መፍትሄ ከናንተ አላጣም ብዬ ብቅ ያልኩት፣ በዚህ አጋጣሚ እዝች የዋርካ ክፍል ውስጥ በፍፁም ቅንነት እውቀታችሁን ለሌሎች ለማካፈል እየተጋችሁ ለምትገኙት ወገኖቼ ምስጋናዬን ሳላቀርብ ማለፍ አልሻም።
ከወራት በፊት 1.5 ዌስተርን ዲጅታል ኤልስተርናል ሃርድ ድራይቭ ገዝቼ አሉኝ የምላቸውን ብርቅዬ ፋይሎቼን ሁሉ ከየኮምፕውተሮቼ በመልቀም እዚያ ውስጥ አጭቄአቸው ነበር። ሆኖም በቅርቡ ልከፍተው ስሞክር ፓወሩ ይሰራል ነገር ግን ከኮምፒውተሩ ጋር ሊገናኝልኝ አልቻለም። (በኤክስ.ፒ፣ ቬስታ እና ዊንዶው 7 ኮምፒውተሮች ሞክሬዋለሁ) ምናልባት ከዪ ኤስ ቢ ገመዱ ይሆናል በማለት የተለያዩ ገመዶችንም ሞክሬአለሁ)
በመጨረሻም ዋራንቲ አለውና ወደገዛሁበት ቦታ በመሄድ ስጠይቃቸው “ከፈልግክ ገንዘብህን አለያም ሌላ ቀይረህ መውሰድ ትችላለህ” የሚል መልስ ሰጡኝ። እኔ ደግሞ ከምንም በላይ ያሳሰበኝ እላዩ ላይ የጫንኩትን ዳታ እንዴት ላገኘው እንደምችል ነው። እስኪ ምን ማድረግ እንደምችል ምከሩኝ?
ፍልፈሉ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 96
Joined: Mon Sep 25, 2006 5:49 pm

Postby ocean12 » Mon Apr 08, 2013 4:06 am

ከስንት ዘመን በሁዋላ ተሳክቶልኝ ዋርካ ብመጣ ይቺ ብዙ የተማማርንባት ርዕስ ወዲያ ጥግ ተወርውራ ባያት ጊዜ አዲስ
ነገር ባይኖረኝም እስኪ ወደፊት ላምጣት ብዬ በማሰብ ነው::
አዳዲሶች ካላችሁ ትማሩባታላችሁ የቀድሞ ተሳታፊዎችም እንደወትሮው ሌሎችን ትረዱባታላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ::

መልካም ጊዜ ለሁላችሁ::
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ሸገር_wind » Mon Apr 08, 2013 6:42 am

ሰላም ለሁሉ ይሁንና ጥሩ ቤት ነበር አንተም ሳትጠፋ ያለህን ጣል አድርግ እንግዲህ እኛም ዋርካ ፍቅር ላይ ተሳዳቢ እስከሌለ ድረስ እንጎበኛታለን::

ለዛሬ ብዙ ሰዎች የሚጠይቁትን አንድ ጥያቄን ልመልስ:: ነገሩ እንዲህ ነው አብዛኞቹ ሰዎች አይፎናቸው ላይ ዋርካን ሆነ አንዳንድ አማርኛ ነክ የሆኑ ፁሁፎችን ለማንበብ ተቸገርን ሲሉ እሰማለው ለዚ የሚሆን አንድ ዘዴ አለ::

በመጀመሪያ Apps Store በመሄድ በነፃ Opera Mini ብለው ዳውሎድ ያድርጉ እንደ ሳፋሪ ነው::

ዳውሎድ ሲጨርስ ይክፈቱትና አድሬስ ባሩ ላይ about:config ብለው ይፃፉ::

የሆነ ፁሁፍ በግራ በኩል በትንሽዬ ቦክስ ውስጥ yes and No ያለበት ፁሁፍ ይመጣል በቀጥታ NO የሚሉ ቦክሶቹን
ወደ yes ይለውጧቸውና ከታች ሴቭ ያድርጉት:: ጨረሱ ማለት ነው ማንኛውንም የማርኛ ፁሁፍ በዚ አማካኝነት ማየት ይችላሉ::

በነገራችን ላይ ይሄ ዘዴ ለአንድሮይድ ፎኖችም ይሆናል::
ETHIOPIA I miss you like a retard misses the point
ሸገር_wind
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Tue Aug 10, 2010 11:30 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests