የኮምፒውተር የሶፍትዌር እና ተዛማጅ ጥያቄዎች እና መረዳጃ..

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby አዋሽ98 » Wed Dec 12, 2007 5:36 pm

ocean12 wrote:ሰላም አዋሽ98
ቅቅቅቅቅ.....jpg
ታዲያ በዛች ሸላይ ስልክህ ካነሳሀቸው ፎቶዎች ማቃመሱን አትርሳ...
እንዳትረሳ...ቅቅቅቅቅ

አይ ኦሽኔ ሸላይ እያልክ ትላጥብኛለህ ኧረ ቢቸግር ናት አሮጌው ሞባይሌ ስራ በጭራሽ ሊያሰራኝ ስላቻለ አልበላም አልጠጣም ;) ብዬ ከ second-hand መደብር ነው የገዛሁዋት ናት:: እኔ የመሰለኝ የሞባይሉን memory upgrade ማድረግ የሚቻል ነበር memory stick ሳላስገባበት እንጂ እሱማ አለኝ በዚህ ላይ ደሞ ሊቀበል የሚችለው እስከ 2GB ብቻ የሆነ memory stick ነው:: እኔ 4GB የሆነ USB ስላለኝ USB-Blue-tooth adaptor መግዛቱ ተመራጭ ነው::
ፎቶዎችህን አየሁልህ የጎርጎራውን ዛፍ እንዴት እንደወደድኩት አትጠይቀኝ ግን ምነው እንድዚህ ቋጠርክ ;) እነዛን ብቻ ነው አገር ቤት ሄጄ ያነሳሁት እንዳትለኝ:: በነገርህ ላይ 2ኛውን ጥያቄዬን ያልመለስክልኝ ረስተኽው ነው ወይስ መልሱን አታውቀውም just to refresh ur memory, here's once again
ndave ከPC ላይ delete የተደረጉ ፋይሎችን retrieve ማድረግ ይቻላል ብሎ ነበር ከሞባይልስ ላይ ዲሊት የተደረጉ ፋይሎችን ሪትሪቭ ለማድረግ ተስፋ አለው ወይ?

መልካም ምሽት/ቀን
አዋሽ98
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 172
Joined: Mon Sep 26, 2005 3:22 pm
Location: Lay Sefer

Postby ocean12 » Thu Dec 13, 2007 8:17 pm

ሰላም ለሁላችሁም...
አዋሽ 98

እረ እኔስ ከምሬ ነበር....መፍትሄውንም አንተው እራስህ አምጥተኽው ቁጭ አልክ....ቅቅቅቅ
ያገር ቤቱን ፎቶ ስለወደድከው ደስ ብሎኛል....እረ ብዙ አሉኝ እንዲያው ስንፍና ሆኖ ነው እንጂ ...
አንድ አንድ እያልኩ ላስቀምጣቸው አስቤያለሁ...
ለሁለተኛው ጥያቄ እኔ ብዙም እውቀቱ ስላልነበረኝ ነው ያለፍኩት..ndave ባለፈው የዛን ፕሮግራም ኢንፎ ያመጣው
እሱ ስለነበር ነው እሱ እስኪ ይጠየቅ ያልኩት....ቅቅቅቅቅ
ndaveእረ እባክህ እንደምንም
ብለህ መፍትሄውን አምጣልኝ...ቅቅቅቅ
መስማማት
እረ እንዴት ሆነህ ይሆን?....
[/u]
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby አስታዉስ » Sat Dec 15, 2007 2:01 pm

ስሙ እንጂ

ይህን የመወያያ አርእስት ለከፈተ ሰዉ ምስጋናዬን እያደረስኩ እኔም እስቲ አንዳንድ softwares ሳትከፍሉ (ህምምም.... "ዘመናዊ ስርቆት ልበለዉ"? :lol: :lol: ) የምትጭኑበት ዌብ ሳይት ላካፍላችሁ. ታዲያ አደራችሁን "አስታዉስ ነዉ የፈቀደልን" ብላችሁ እንዳታስፎግሩኝ. :lol: አድራሻዉ
www.9down.com ነዉ.
ብዙዎቹ ፕሮፌሽናል ሶፍትዌሮች ሰሪያል ቁጥር ወይም ኪ ጄኔሬተርስ አሉዋቸዉ. መቼም ያለዉ ካለ ይጸድቅብኝ ይሆናል ብዬ እኔም ትብብራችሁን ልጠይቅ ነዉ. እረ በአራዳዉ ጊዮርጊስ, እስቲ AddisWord Professional ያላችሁ ተባበሩኝ.
P.S.
Your Firewall and internet security/ Antivirus should be up-to-dated. መጠንቀቅ ጥሩ ነዉና! መልካም እድል.
"Nobody can give you freedom. Nobody can give you equality or justice or anything. If you're a man, you take it." Malcolm X
አስታዉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 419
Joined: Fri Oct 17, 2003 11:16 am

Postby ዋናው » Sat Dec 15, 2007 5:21 pm

የድረሡልኝ ጥሪ

ሠላም ለቤቱ
ከዚህ በፊት እጠቀመው የነበረው ፖፕ-አፕ ስቶፐር (ፓኒክዌር) አሁን ምን ሆኖ እንደሆን እንጃ ፈዞዋል... አንድ ነገር ለመፃፍ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረሩን ከከፈትኩኝ ባንድ ጊዜ 3....4.... እየከፈተ የስፓም መዓት ያጨናንቀኛል በነዚህ በኩል ሚመጡ ራሳቸው በራሳቸው ወርደው ሚጫኑ ቫይረሶች ደግሞ ፒሢን ዳሜጅ ሚያደርጉ ናቸው ...እስቲ ምታውቁት ፕሮፌሽናል ፖፕ አፕ ስቶፐር ካለ የዘውትር ትብብራችሁን እጠይቃለው:: (ታዲያ ክፍል እንዳትሉኝ ድሕነቴን እያወቅኩኝ ቅቅቅ)

መልሡን እጠብቃለሁ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby አስታዉስ » Sat Dec 15, 2007 10:56 pm

ሰላም ዋናዉ

እኔ Zone Alarm Internet Security እና McAfee Security Center ነዉ የምጠቀመዉ. በነገራችን ላይ ሁለቱም የራሳቸዉ Antivirus ስላላቸዉ አንዱን inactivate ማድረግ የግድ ነዉ. በተረፈ እነዚህን አቀናጅቼ ኢንተርኔት ስገባ pop-up, Virus ... ምናምንቴ ሁሉ ጸጥ ረጭ ነዉ የሚለዉ. እስቲ Zone Alarmን ሞክር.
"Nobody can give you freedom. Nobody can give you equality or justice or anything. If you're a man, you take it." Malcolm X
አስታዉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 419
Joined: Fri Oct 17, 2003 11:16 am

Postby ocean12 » Sun Dec 16, 2007 1:45 am

ሰላም ዋናው
ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ? ..... ወንድሜ ምነው ለምን ፓፕ
ብቻ ሌላም ቫይረስ ቢያጠቃህ እንዳትገረም...
እንደኔ እንደኔ ለማንም ሰው የምመክረው
IE (Internet explorer)ን እርግፍ አድርጎ መተው....
ባይገርምህ ከዴስክ ቶፔ ላይ እንኩዋ ዲሊት አድርጌያለሁ
ምናልባት በስህተት ላለመጠቀም::
አንደኛ Firefoxን እመርጣለሁ በፓፕ አፕም ሆነ በሴኩሪቲው በኩል በጣም የተሻለ ነው
እንደምትፈልገው አይነት ከስተማይዝ ማድረግ ከመቻልህም
በላይ በጣም ፈጣን ነው
ሌላው Netscape navigater ነው ይህም በጣም ከ IE
የተሻለ ነው ....
አይ IE ን መጠቀም ነው የምፈልገው ካልክም ሌሎቹ
አማራጮች ከዳውን ሎድ .ካም ላይ በቀላሉ የምታገኛቸው
ፕሮግራሞች ብዙውን ጊዜ ጠቃሚ ናቸው...
ይህኛው አንዱ ነው ፕሮግራሙ በፓፕ አፕ ታዋቂ
ከሆኑ ሳይቶች የሚከላከል አይነት ነው...ተጨማሪ
ዝርዝር አለው..
http://www.download.com/SpywareBlaster/ ... ?tag=lst-2
ሌላው ያሆ ቱል ባር ነው...ብዙ ጊዜ ቀለል ያሉትን ለማቆም
ያገለግላል...
http://www.download.com/Yahoo-Toolbar-w ... 83137.html
ሌላው በcnet ኤዲተሮችም ጭምር ጥሩ እንደሆነ የተመሰከረለት...
Pop-Up Stopper Free Edition 3.1.14 ነው..
http://www.download.com/Pop-Up-Stopper- ... ag=lst-0-9
እንግዲህ መልካም እድል...
ሰላም ጊዜ.
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ocean12 » Sun Dec 16, 2007 3:27 am

አስታዉስ wrote:ስሙ እንጂ

ይህን የመወያያ አርእስት ለከፈተ ሰዉ ምስጋናዬን እያደረስኩ እኔም እስቲ አንዳንድ softwares ሳትከፍሉ (ህምምም.... "ዘመናዊ ስርቆት ልበለዉ"? :lol: :lol: ) የምትጭኑበት ዌብ ሳይት ላካፍላችሁ. ታዲያ አደራችሁን "አስታዉስ ነዉ የፈቀደልን" ብላችሁ እንዳታስፎግሩኝ. :lol: አድራሻዉ
www.9down.com ነዉ.
ብዙዎቹ ፕሮፌሽናል ሶፍትዌሮች ሰሪያል ቁጥር ወይም ኪ ጄኔሬተርስ አሉዋቸዉ. መቼም ያለዉ ካለ ይጸድቅብኝ ይሆናል ብዬ እኔም ትብብራችሁን ልጠይቅ ነዉ. እረ በአራዳዉ ጊዮርጊስ, እስቲ AddisWord Professional ያላችሁ ተባበሩኝ.
P.S.
Your Firewall and internet security/ Antivirus should be up-to-dated. መጠንቀቅ ጥሩ ነዉና! መልካም እድል.

ሰላም አስታውስ
ጥሩ ጥቆማ ነው ....ከዚህ በፊት አጋጥሞኝም አያውቅም
ነበር...ምናልባት አንተ የምትጠቀበት ከሆነ ከፕሮግራሞቹ ጋር አብሮ የሚመጣ ቫይረስ
ምናምን እንደሌለ የበለጠ ታውቃለህ የሚል እምነት አለኝ...
የኔ ጥያቄ ሴሪያል ቁጥሮቹ አብረው ይመጣሉ ወይስ ይህስ ኪ ጄኔሬተር እንዴት ነው የሚሰራው?...
ብዙ ጊዜ ሴሪያሎችን ከተለያዩ ሳይቶች ነው የማገኘው...
ሴፍ ባይሆኑም...
የ addis word pro ን ነገር እኔም ያላችሁ
እጃችሁን ዘርጉ ብያለሁ.. :D
ሰላም ጊዜ
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby ዋናው » Sun Dec 16, 2007 4:32 am

ሠላም ኦሺን እና አስታውስ

ለምክራቹ አመሠግናለው: ኦሽን እንዳልከው በያሁ ቱል ባሩ መጠቀሙ ሳይሻል አይቀርም
ግን የሠጠህኝ ሊንክ የስፓይዌር ብላስተሩ ብዙም የነቃ ሆኖ አላገኘውቱም ከሣምንት በፊት አውርጄ ጭኜው ውስጥ ለውስጥ እንደሚሠራ ይነግረኛል ግን ያን ያህል ችግሮችን ሲያስወግድ አላየውትም እስካሁን ....
ይልቅ ባለፈው ካንተ በወሰድኩት ሊንክ የጫንኩት አቫስት በጣም ጥሩ ነው በተለይ ለሪል ታይም ፕሮቴክሽን.... ግን እሱ ደግሞ ከዚህ በፊት በአኑአል ብዙ ፓውንድ ከፍዬ የጫንኩትን ሕጋዊ ዊንአንቲስፓይዌር ድመሠሠብኝ:: ደግነቱ የተሻለ ሆኖ ነው የደመሠሠው .... የዚህ አቫስት ችግር ደግሞ ስካን ሲያደርግ በጣም ይቆያል:: ስለዚህ ስካን ሳደርግ በማካፊ እየተጠቀምኩኝ ነውማካፊ ሲቲንገር በጣም አሪፍ ነው ሞክሩት::

ዳውንሎድ ላይ አንድ ፖፕ-አፕ ስቶፐር ነፃ ነው ብዬ ጭኜው ብዙ ችግር ፈታው ብሎ ካነጀበ በዋላ ተመዝገብ ሲለኝ .... እቺ ዳር ዳር ሳንቲም አምጣ ናት ብዬ አሰናበትኩት ... ይሄው እስካሁን ግን ሠላም ነኝ በያሁ በመጠቀሜ ይሆን እንጃ
በተረፈ ለአማርኛው ግህዝ ዩኒ ኮድን ከጫንኩኝ በኌላ ብዙም አልቸገርም እስቲ አማርኛው ግህዝ ሜይል ላይ ፈልጉት::

ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

አሪፈ አምድ ነው የከፈታችሁት

Postby ትብብር » Sun Dec 16, 2007 10:50 am

ሰላም ወገኖች::
በአዶቤ ፎቶሾፕ አማርኛ መጻፍ ካስቸገረህ እንደዋሸራ ያለ ሙሉ የአማርኛ ሶፍትዌር ኢንስቶል ማድረግ ይኖርብሀል:: ዋሸራ በነጻ ታገኘዋለህ:: ዋሸራ ከሚደግፋቸው ሶፍትዌሮች ውስጥ ፎቶሾፕ አለበት:: ፎቶሾፕ ቨርዥን 7 በመጠኑም ዩኒኮድ ስታንደርድን ሊያማላ ተሞክሮዋል ነገር ግን አንዳንድ ፊደላት ላይ ችግር አለበት::

እመለሳለሁ,
መልካም ጊዜ
ትብብር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Mon Oct 04, 2004 6:34 am
Location: united states

Postby አስታዉስ » Sun Dec 16, 2007 1:50 pm

ocean12 wrote: ሰላም አስታውስ
ጥሩ ጥቆማ ነው ....ከዚህ በፊት አጋጥሞኝም አያውቅም
ነበር...ምናልባት አንተ የምትጠቀበት ከሆነ ከፕሮግራሞቹ ጋር አብሮ የሚመጣ ቫይረስ
ምናምን እንደሌለ የበለጠ ታውቃለህ የሚል እምነት አለኝ...
የኔ ጥያቄ ሴሪያል ቁጥሮቹ አብረው ይመጣሉ ወይስ ይህስ ኪ ጄኔሬተር እንዴት ነው የሚሰራው?...
ብዙ ጊዜ ሴሪያሎችን ከተለያዩ ሳይቶች ነው የማገኘው...
ሴፍ ባይሆኑም...
የ addis word pro ን ነገር እኔም ያላችሁ
እጃችሁን ዘርጉ ብያለሁ.. :D
ሰላም ጊዜ


Ocean12

ሰላም ቢያለሁ. ብዙዎቹ 9down.com ላይ የምታገኛቸዉ ፕሮግራሞች በትክክል ይሰራሉ. አንዳንዴ የሚለጥፈዉ ሰዉ Serial number / key generator አያይዞ ይለጥፋል. ፕሮግራሞቹን ዳዉንሎድ አድርገህ ስትጨርስ PC ከኢንተርኔት አለያይ. ሶፍትዌሩ ኪ ጄኔሬተር ካለዉ መጀመሪያ እሱን ክፈተዉ እና Registration key or serial number ይሰጥሀል. ከዚያ ሶፍትዌሩን ኢንስታል አድርገህ ስትጠየቅ ቁጥሩን ማስገባት ነዉ. እንዳልኩህ ቁጥሩን ተቀብሎ እስከሚያመሰግንህ ድረስ ኢንተርኔት አትክፈት. Because it checks whther the serial number is black listed or not. ሌላዉ ብዙ ጊዜ ሬጊስተር ማድረግ የለብህም.
በጣም ጠቃሚዉ ነገር ሶፍትዌሩ ፖስት የተደረገበት ቦታ ሰዎች የሚወያዩበትን ማንበብ ይጠቅማል. አንዳንዶቹ "እረ ወገን እኔን እምቢ አለኝ" ሌሎቹ ደግሞ "ሲሪያል ነምበሩ አልሰራ አለኝ" እያሉ ጩህእታቸዉን ሲያሰሙ :lol: የሰራላቸዉ ደግሞ "እንደዚህ አድርጉ ... ወይም ይህን ቁጥር ይሞክሩ" እያሉ ይመልሳሉ. እና ያንን ከተከታተልክ ምንም ችግር የለም.
በሌላ በኩል በተለይ ኪ ጄኔሬተሮች malware/ spyware/ virus ... ሊሆኑ ስለሚችሉ ከመክፈትህ በፊት ባለህ antivirus check ማድረግ ጥሩ ነዉ. ሌላዉ እንደኔ Zone Alarm Internet Security የምትጠቀም ከሆነ ኢንስታሌሽንህን ከጨረስክ ቦሀላ Zone Alarm ለkey generator ኢንተርኔት ላይ መግባትን እንዳይፈቅድ ማድረግ ዋና መፍትሄ ነዉ. ሲሪያል ቁጥር የተጠቀምክ ከሆነ ደግሞ don't register your software online! ለምን ብትል "አያ ሌቦ, ነቃንብህ. በተሰረቀ ቁጥር ልትጠቀም? ሲመችህ ብቅ በል" ብለዉ ፕሮግራሙን block ያደርጉብሀል. እና ይሄዉ ነዉ መልሴ. እስቲ ከኔ የተሻለ ልምድ ያላችሁ ደግሞ ምክራችሁን ለግሱን.
ከሰላምታ ጋር
"Nobody can give you freedom. Nobody can give you equality or justice or anything. If you're a man, you take it." Malcolm X
አስታዉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 419
Joined: Fri Oct 17, 2003 11:16 am

የኮምፒዩተር ጤንነት

Postby ትብብር » Sun Dec 16, 2007 9:57 pm

በመጀመሪያ ይህንን ፕሮግራም ያዘጋጀህ ወንድማችን ልትመሰገን ይገባሀል::
የኮምፒዩተራችንን ጤንነት እንዴት እንጠብቃለን?
ይህንን ለመመለስ ችግሮቹን ማወቅ ያስፈልጋል:: የሚከተሉት ምናልባት መነሻ ችግሮች ናቸው::
1. ተጠቃሚው ኢንተርኔት ላይ የተቀመጠን የነጻ ሶፍትዌር ሁሉ ዳውንሎድ ማድረግ::
2. የሴኪዩሪቲ ሶፍትዌር ያላቸውን አጠቃቀም በደንብ አለማወቅና የቫይረስና ስፓይዌር አውቶ-ስካንና ላይቭ-አፕዴት ያላቸውን ጥቅም መርሳት::
3. በጊዜው ሲስተም ኦፕቲማይዜሽን አለማድረግ
4.. ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዲፎልት ክንውኖች የሚኖራቸውን ጉዳት ባለመገለጻቸው ምክንያት የተከፈቱት ፖርቶች ቮነረብሊቲን ሲጋብዙ, ቢያንስ መኖራቸውን እንደ አማራጭ ሲስተሙ ሊጠይቀን ይገባ ነበር:: እነሱን መረዳትና ግልጋሎታቸውንና ጉዳታቸውን መመርመር::
5. ከውጭ ያለንን ግንኙነት ሞኒተር ማድረግ::
ሲሆኑ, በርካታ ሌላም ችግሮች ይኖራሉ ነገር ግን እነዚህ አይነተኛ ናቸው::

መፍትሄ:
1. ለማይክሮሶፍት ሲስተምስ የቀረበ ነጻ ሶፍትዌር አብዛኛው በስያሜ ነጻ ቢሆኑም ከሆነ ፋይናሺያል ድጋፍ ሰጪዎች ግንኙነት አላቸው:: ስለዚህም አንዱ አድቨርታይዝመንት ሲሆን ሌላው ያለንን ብራውዚንግ ልማድ ማጥናትና ከአድቨርታዘርስ ጋር መጋራት ሲሆኑ, ሌላም በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ:: በአሰራር ጸባይ በነጻ የሚታወቀው የሊኒክስ ሶፍትዌርና ለሱ ተብለው የተሰሩ ሶፍትዌሮች ብቻ ናቸው:: ዳዎንሎድ ማድረግ ካለብን, እንደፒሲ መጋዚን ያሉ ግምጋሚዎችን ዳውንሎድ ካምድረጋችን በፊት መመልከት ይጠቅማል::

2. በኮምፒዩተራችን ውስጥ ያሉ ሴኪዩሪቲ ሶፍትዌሮች መስራታቸውን በየጊዜው ሞኒተር ማድረግ, በተለይም ላይቭ-አፕዴት መካሄዱን ማወቅ:: ሌላው ከአንድ በላይ አንታይ-ስፓይዌር ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ከአንድ በላይ አንታይ-ባይረስና ፋየርወል ሊኖረን አይገባም:: ከሆነም ኮምፒዩተራችን በድንብ ሊሰራ አይችልም:: ከዚህም ሌላ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 7 ካለን ፊሺንግ ፊልተር (phising filter) የሚባል ፋየርወል አብሮት ይመጣል:: ሌላ ፋየርወል ካለን እሱን ማቆም አለብን::

3. ሲስተም ኦፕትማይዜሽን ለማድረግ ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር እንጀምራለን: ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ሜኒዩ ክሊክ Tools/Internet Options, ከዚያም Delete cookies/Ok, Click Delete Files/Delete all offline folders then OK, ሲጨርስ Delete History/Yes ሲጨርስ ክሊክ Security tab/ ከዚያም አራቱም ዞኖች ዲፎልት ሌቭል ሴታፕ መሆናቸውን ማረጋገጥ:: ከዚያም ከሊክ Connection ከዚያም ግንኙነታችን ሃይ ስፕዲ ከሆነ, ክሊክ LAN Settings ዳያላፕ ከሆነ ከሊክ Settings, ምንም ፕሮክሲ ሴታፕ አለመሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል::
ከዚያም ዲፍራግመንቴሽን ያስፈልገው እንደሆነ መመርመር:: ይህንን ለማድረግ ክሊክ Start/All Programs/Accessaries/System Tools/Disc Defragmentor ከዚያም ክሊክ Analyze የሚለውን, ሲስተሙን ከመረመረ በኍላ ፍራግመንትድ ከሆነ ዲፍራግመንቴሽን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል, አለበለዚያም አይስፈልገውም ብሎ ይመክረናል::

4. ሲስተሙ በተለምዶ የከፈታቸው ፖርቶች ሆን ተብለው ተጠቃሚውን ለመጉዳት ሳይሆን የተለያዩ ሰርቪሶችን ማይክሮሶፍት ለመስጠት የከፈታቸው በሮች ናቸው:: ለምሳሌም ዊንዶውስ አፕዴት ሲካሄድ አውቶማቲካሊ ሳናየው ነው የሚመጣው:: ስለዚህም ሲስተማችን ከማይክሮሶፍት ሰርቨሮች ጋር ኢንተራክቲቭሊ ይሰራል ማለት ነው:: ነገር ግን እነዚህ ለመልካም የተከፈቱ በሮች ለቮንረብሊቲ በር ናቸው:: ስለዚህም የሚከተሉትን ወይ ማገድ ወይም በጥንቃቄ መመርመር:
ህ) የሲስተሙን መሴንጀር ከአድምንስትሬቲቭ ቱልስ ውስጥ ዲስኤብል ማድረግ::
ለ) ሪሞት ሄልፕ Remote help)ን ዲስኤብል ማድረግ::
ሐ) የዊንዶስ ስክሪፕት ሆስት ዲስኤብል ማድረግ::
መ) ኮምፒዩተሩ ሁሌም የመጨረሻ ተጠቃሚን ዩዘር አካውንት ይጠብቃል:: ይህንን ስክሪፕት ዲስኤብል ማድረግ::
ሠ) የታይም ሲንከርናይዜሽንን ዲስኤብል ማድረግ
ረ) ሲስተማችን ውስጥ ችግሮች ሲኖሩ, ለማይክሮሶፍት መላክ ትፈልጋለህ ወይ የሚል ጥያቄን ያዘለ ሳጥን ይመጣል:: ይህንን አይነት ሰርቪስ የሚሰጠውን ስክሪፕት ዲስኤብል ማድረግ::
ሸ) የሲስተሙን ዩኒቨርሳል ፕላግ ኤንድ ፕለይ ዲስኤብል ማድረግ::
ቀ) Active-X Control ን ዲስኤብል ማድረግ
በ) ከ NetBIOS ጋር ባለ ግንኙነት የተከፈቱ ፖርቶችን ዲስኤብል ማድረግ, ለምሳሌም: ፖርት 137, 139, 145 እና ሌላም::
ባጠቃላይ ወደ 25 ለቮነረብሊቲ ምክንያት የሆኑ ክንውኖች አሉ:: እነሱን በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው::

5) ከውሽ ያለንን ግንኙነት የሚያሳየው ስታተስ አይከን ያለውን አክቲቪቲ ማጤን ይጠቅማል:: ምን ነገር ከኢንተርኔት ሳንጠይቅ የትራፊክ አክቲቪቲ ካየን ችግር አለ ማለት ነው:: በኛ ሲስተም ውስጥ ያለ ሆስት ነው ወይስ ከውሺ ይህንን ዴዲኬትድ ኮምኒኬሽን የሚያካሂደው? ይህንን መለየት::

ይበለጠ ወደፊት እመለስበታለሁ::
አመሰግናለሁ
ትብብር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Mon Oct 04, 2004 6:34 am
Location: united states

Postby ndave » Mon Dec 17, 2007 6:05 am

ሰላም ሰላም ወገኖች
ግዜ እምትባለዋ አልያዝ እያለችን ያለችንን ለመጣል እንዘገያለን ::

ጓዶች ይህች ከዚህ በታች እማስቀምጥላቹ አድራሻ ትጠቅማችኋለች በእርጋታ አርፏት ::
http://www.sysinfo.org/startuplist.php? ... offset=150
ndave
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Mon Sep 22, 2003 10:29 am

Postby አንበርብር » Mon Dec 17, 2007 8:56 am

እንዴ? ምን አይነት ደንባራ ነኝ? ባለፈው እንደዚህ አይነት ውይይት የሚካሄድበት ፎረም ካለ ጠቁሙኝ ብየ ጉሮሮየ እስከሚሰነጠቅ ስለፈልፍ ነበር:: ያው ይህ ፎረም ከተከፈተ ደግሞ ልክ ዛሬ አንድ ሙሉ ወር ደፈነ......... እኔ ያየሁት ደግሞ ዛሬ.......... ለሁሉም ፎረሙን ለከፈተው ኦሺን እና እንዲሁም ሳትታክቱ እውቀታችሁን እና ምክራችሁን ለምትለግሱ በሙሉ ምስጋናየ ይድረሳችሁ!!!!!! መረዳዳት ማለት ይህ ነው..... እውቀት የሚሸመትበት ነፃ ገበያ ብየዋለሁ..... አሁን እያነበብኩ 3ኛውን ገፅ ጨርሸ ወደ 4ኛው እየገባሁ ነው........ መልካም መልካሙን ለእናንተ!!!!!!
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ocean12 » Tue Dec 18, 2007 2:15 am

ሰላም ወገኖቼ...
ይህቺን የትብብር አምድ በማንበብም ሆነ ጥያቄዎቻችሁን
በማቅረብ የምታውቁትንም በማካፈል እየተሳተፋችሁ
እዚህ ያደረሳችሁዋት ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ...

አስታውስ ልጀምር...
ሰሞኑን እጠቀምበት የነበረውን ፎቶሻፕ ለማሻሻል ብዬ
ፍለጋ ላይ ነበርኩ እናም ቀንቶኝ...ንጹህ የሆነ CS2 አገኘሁ
ሴሪያል ቁጥር አክትቬሽን ቁጥር እናም አውቶራይዜሽን ቁጥር ሁሉ አለው ነገር ግን አክትቬት ላደርገው ስሞክር
ኢንቫሊድ እንደሆነ እየነገረኝ እምቢ ቢለኝ ጊዜ ሌሎች
ሰዎች እንዴት እንደሚያደርጉ ለማየት ሞክሬ ነበር...
እናም አንተም እንዳልከው ኪይጄን ማድረግ እንዳለብኝ
ነው የተረዳሁት...ነገር ግን እኔ ብዙም እንዲህ አይነቱን ነገር ብዙም አላውቅበትም እና ድንግርግር ቢለኝ ጊዜ ነው ጥያቄዬ....
ኪይጄን የሚደረገው እንዴት ነው?
ምንስ መጥፎ ጎኖች አሉት?...
የምታውቁ ካላችሁም መልሳችሁን እጠብቃለሁ...

በነገራችን ላይ ፎቶሻፕ መጠቀም የሚፈልግ ካለና
ቁጥሩን አስገብቼ እጠቀምበታለሁ የሚል ካለ
(CS2 ንጹህ )ለማጋራት ፈቃደኛ ነኝ...ቅቅቅ :D :D
ስርቆት ይሆን?...
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby አቡቲ » Tue Dec 18, 2007 1:34 pm

ሰላም ውቅያኖስ 12 እንዲሁም ሌሎች

አክቲቬት ሳደርገው እምቢ አለኝ ላልከው...አክቲቬት ከማድረግህ በፊት ኢንተርኔት ዲስኤብል በማድረግ አክቲቬት ባይ ፎን የሚለውን ኦፕሽን ምረጥ..ከዚያም አክቲቬሽን ቁጥሩን መዝግብና ከአዶቢ አፕሊኬሽኑ ስምና ቨርሽን ቁጥር ጋር አያይዘህ ላክልኝ ከዚያም አውቶራይዜሽን ኮዱን እልክልኃለሁ :: ስለ ኪ ጀነሬተር ላነሳኸው ጥያቄ.ብዙውን ጊዜ እዚያው አዶቢ ውስጥ የሚሰሩ ደቨሎፐርስ ወይም ኪ ጀነሬተሩ የሚጻፍበትን ሶርስ ኮድ የሚያውቁ ናቸው ስክሪፕቱን ደቨሎፕ የሚያደርጉት ስለዚህ ፈጽሞ ሕገ ወጥ ነው :: እጅህ ላይ ቢገኝ ትልቅ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ኮምፒውተርህም ውስጥ ሴቭ ማድረጉ ፈጽሞ አደገኛ ነው የሚሆነው :: በተቻለ መጠን ለግል ጥቅም ብቻ አዶቢ አፕሊኬሽኖችን ለምትጠቀሙ አፕሊኬሽን ሲሪያል ቁጥር ወይም አውቶራይዜሽን ኮድ ላካፍል እችላለሁ ::
አንድ ነገር ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገው ነገር ቢኖር...በተቻለ መጠን ስለ ኪ ጄን ሲሪያል ወይም አክቲቬሽን እንዲሁም ትንሽ ሴንሴቲቨ የሆኑ ነገሮች ከሕግ አኳያ ሲታዩ ቫልነሬብል ሊያደርጉን ስለሚችሉ ቃላትን እየቀየርን እንጠቀም መግባባት ከቻልን ካልሆነ ግን በግል ሳጥን መልዕክት መላላኩ ሴፍ ነው ::

:)
አቡቲ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 138
Joined: Wed Mar 09, 2005 2:59 am
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests