በጽንፈኛ ፍንዳታ
በነወጠኛ ተኩስ ቃታ
ሳትሸማቀቅ ፈርታ .....
...................ላንዲት ነፍሷ ሳትሰጋ
ለነጻነቷ ክብር - ለስብዕናዋ ዋጋ
..................አንገቷን ቀና አድርጋ
'እምቢ አልገዛም ' ስትል - ላቅመ -ሔዋን ያልበቃች ጨቅላ
ጢባ ጢቤ ያልጨረሰች - ሰኞ ማክሰኞን ዘላ ......
ባድናቆት ሲቃ ስሜት - ዓይኔ የምባ ዘለላ ሞላ ....
'ምነው የኢትዮጵያ ማሕጸን - አልወልድ አለ "ማላላ "
http://www.bbc.co.uk/news/world-europe-24475305
http://www.bbc.co.uk/news/magazine-24379018