Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by እቴጌይት » Wed Apr 16, 2008 1:31 am
Last edited by
እቴጌይት on Mon Apr 01, 2013 1:05 am, edited 1 time in total.
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by እቴጌይት » Wed Apr 16, 2008 1:35 am
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by ብርቄነህ » Wed Sep 23, 2009 7:09 pm
ይህን የመሰለ ቁምነገር አደባባይ ላይ ነው መዋል ያለበት::
በእተጌይቱ:-
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ ......
አለም ቢታሰስ -ታሪክ ቢጠና
ሕዝብ ቢመዘን -ቢፈለግ ጀግና
የታሪክ ቀደምት -የሰው መገኛ
ከሁሉ የላቀ -ማን አለ እንደእኛ ?
እኮ ማን ?............እኮ በለኛ
ንገረኛ !!!
አየ ዘራፍ ...አየ ዘራፍ
አየ አካኪ ዘራፍ
አሁን የኛ ኩራት -የኛ ኩፈሳ
ታሪክ ስንዘክር -ወግ ስናወሳ
በትናንት ስኖር - ዛሬን ሳንሰራ
በባዶ ኩራት - ስንንጠራራ
የእጅ ግዞተኛ - በዕርጥባ ኗሪ
የጠኔ አብነት - በራብ ተጠሪ
በወሲብ ቅስፈት - አትራፊ ዝና
እንዲም አርጎ የለ - አንደኛ ጀግና
አይ ጀግና
አይ ጀግና ......
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ቤልጂግ ሳይኖረው -ባሩድ ሳይሰራ
መድፍ ሳይተኩስ -ሳያይ ጢያራ
ሰናድር ይዞ - ወጨፎ አንግቶ
ፈንጁን አክሽፎ -ጥይት መክቶ
ነጣ ባወጣን -በአያቴ ሥራ
አንዴት አልፎክር - አንዴት አልኮራ
እንዴት አልዘክር -ገድሉን አላውራ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
አይ ዘራፍ ..አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
የዛሬ ትውልድ -ሰቆቃ አፍጦ
በረሀብ ሰሎ -ውስጡ ተረግጦ
የአባቱ ገድል - የአያቱ ሥራ
ሲዘከር ቢኖር -ዓመት ቢወራ
ለተደቆሰው -ሰብዓዊነቱ
ጠኔ ላጣጋው -ለዛሬ አንጀቱ
ምኑ ላይ ይሆን -መፍትሄነቱ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
ጊዜ ተጣሞ -ቀን ተወላግዶ
ሥልጣኔያችን -ቁልቁል ተሰዶ
ዛሬን ብንደኸይ -ረሀብ ቢመጣ
ታሪካችንን -ኩራታችንን -እንዴት እንጣ ?
ዘራፍ ዘራፍ
አካኪ ዘራፍ
አይ ዘራፍ -አየ ዘራፍ
አይ አካኪ ዘራፍ
ትናንት ከዛሬ -ካልተቆራኘ
ትውልድ ከትውልድ -ካልተገናኘ
የጊዜ ብልሀት -መሽቶ የመንጋቱ
ታሪክ በታሪክ -የመተካቱ
የቀናት መንጎድ - ትርጉሙ ጠፍቶ
ህዝብ ዛሬን ክዶ - ሰው ዛሬን ጠልቶ
ከትናንት ጓዳ -መሽጎ ገብቶ
እንዴት ይኖራል -አሁንን ጠልቶ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate
-
ብርቄነህ
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 605
- Joined: Thu Jan 22, 2009 5:30 pm
by እቴጌይት » Mon Apr 01, 2013 2:11 am
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by Ahmed-1 » Mon Apr 01, 2013 8:39 am
-
Ahmed-1
- ኮትኳች

-
- Posts: 174
- Joined: Mon Mar 19, 2007 3:17 pm
by እቴጌይት » Sun Apr 07, 2013 6:21 pm
Last edited by
እቴጌይት on Mon Apr 08, 2013 4:17 pm, edited 1 time in total.
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by TAዛBI » Mon Apr 08, 2013 12:37 pm
-
TAዛBI
- ኮትኳች

-
- Posts: 152
- Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am
by እቴጌይት » Mon Apr 08, 2013 10:57 pm
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by እቴጌይት » Tue Apr 09, 2013 3:57 am
ወለል ወይስ ጣሪያ
ምናቤ ሳይከለል -በገሀዱ ዓለም እውነታ
በዕለት ተለት ኑሮ ሀቅ- ተሸቦ ሳይገታ
የተስፋዬን ጉልላት- የነግ ሕልሜን አግዝፎት
የኔነቴ ራዕዬን - እላይ አብርሮ አክንፎት
የሀሳቤ መጥለቂያ -የምኞቴ ጀምበሩን
- የተስፋዬ ድነበሩን
በሀሳብ ሞገድ አቃንቶት - ጣራዬን ብመለከት
-የሁለንተናው ርቀት
ብቧጥጥ ብንጠራራ - ብዘል የማልደርስበት....
ለእኔ ሩቅ ሆኖ የታየኝ-ከታች ቤት ሆኜ ሳየው
ለካስ ከላይ ቤት ላለው - መራመጃ ወለሉ ነው!!
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by እቴጌይት » Fri Apr 26, 2013 10:47 pm
አርባ ቀን
ቀን ከሌሊት ሳንተኛ
ብንሮጥ ብንማስን እኛ
በያሕዌ ጥንተ ዕቅድ - በእሳቤው ታሽጎ
የሕወታችን መንገዱ-ቅድመ ዓለም ተደንግጎ
ካበቃለት ይህ ኑሮ
በአርባ ቀናት ተሰፍሮ...
ላንዳንዱ መሸከሚያ
ለሌላው ደሞ ማሰቢያ
ለምን ጭንቅላት ሰጠ - እጅ እግርስ ለምን ሰራ?
መክሊት ለምን አደለ - ለምን ንግድ አሰማራ?
ደግሞስ የምጻቱ ፍርድ - እንዴት ፍርድ ተብሎ ይጠራ?
Last edited by
እቴጌይት on Sat Apr 27, 2013 12:44 am, edited 1 time in total.
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by ደመላሽ » Fri Apr 26, 2013 11:35 pm
History teachs us that we DON'T learn from History
-
ደመላሽ
- ኮትኳች

-
- Posts: 363
- Joined: Tue Aug 17, 2010 11:21 pm
by TAዛBI » Sat Apr 27, 2013 8:54 am
-
TAዛBI
- ኮትኳች

-
- Posts: 152
- Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am
by እቴጌይት » Sat Apr 27, 2013 9:09 am
ሠላም TAዛBI
በድጋሚ ለመልካም አስተያየትህ አመሰግናለሁ:: አስቲ አንድ ጥያቄ አዘል ግጥም ልመርቅ ደሞ::
ቧልት ወይስ ባልትና
ባህር ላይ አዝንባ - ሜዳውን አድርቃ
ባለው ላይ ትሩፋት - ከሌለው መርቃ
ብዙውን አክስላ -ጥቂቱን አፍክታ
አንዱን ማቱሳላ -አንዱን በእንጭጭ ቀጭታ
ተፈጥሮ ቀመሯ
አካሄድ ነገሯ
ውጥንቅጥ ውጥኗ
ቧልት ነው ባልትና?
Last edited by
እቴጌይት on Tue Apr 30, 2013 3:13 am, edited 8 times in total.
-
እቴጌይት
- ዋና ኮትኳች

-
- Posts: 656
- Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm
by TAዛBI » Sat Apr 27, 2013 10:11 am
-
TAዛBI
- ኮትኳች

-
- Posts: 152
- Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am
by ደመላሽ » Sat Apr 27, 2013 1:43 pm
History teachs us that we DON'T learn from History
-
ደመላሽ
- ኮትኳች

-
- Posts: 363
- Joined: Tue Aug 17, 2010 11:21 pm
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 1 guest