ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ቀንዱ » Thu Apr 09, 2009 2:27 pm

ማናልሞሽ ስለ ሰውየው ችሎታ ስትመሰክር " አለምን አዞርሻለሁ ብለውኝ ነበር ተሳክተዋል" ምናምን ብላለች የሚል ነገር ጋዜጣ ላይ አንብቤ: እና የትና መቼ ነው የዞረችው ብየ ሳስብ ነበር:: ይህ ናፍቆት ያልሽው የምትዞረው ነገር ማለትዋ ይሆን እንዴ ?

ቀንዱ
ቀንዱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Jul 17, 2006 5:14 pm

Postby ናፍቆት » Fri Apr 10, 2009 3:12 pm

ቀንዱ - በሳቅ ገደልከኝ ነው የምልህ ... እንደዚያ ብላ ነበር? እኔ መች ሰማሁላት? ..... Oh God! this is really funny.


ምን ትዝ እንዳለኝ ... አንድ ቆንጆ ጓደኛ አለችኝ .. እና መንገድ ላይ ስንሄድ .... ያው መንገድ መቼም ለሁሉ አይደል? ... ምናምኑም ሰውም ምኑም ይመላለስበታል .... ሳስበው ሳስበው አንዳንዱ እንዲኖር የተፈጠረ አለ ... አንዳንዱ ደሞ እንዲኖር ሳይሆን የሚኖሩትን እያየ እንዲኖር የተፈጠረ አለ - እንደተምልካች ... አንዳንዱ ደሞ አለልህ ይኑር አይኑር እንኳን ላንተ ለራሱም የማያውቀው .. እንዲያው ይመሽለታል ይነጋበታል .... ምናምን..... እና ታድያ ምን ልልህ ነበርማ .... አዎ ልጅትዋ ... ይሄ ጉርድፍድፍ ምናምኑ ጎንተል ወይም ጥቅስ ያደርጋት የለ? ..... 'ውይ ከቤ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ያድራል ቆንጆ ጠቀስኩ ብሎ' ... ትል ነበር .... አሁንም ማናልቦሽ የኢቲቪን ስቱዲዮ ዞራ አለምን ዞርኩ ብላ መልካም እንቅልፍ ተኝታ አድራለች አትለኝም? ወይ ጣጣዬ ....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ብቻ » Fri Apr 10, 2009 9:42 pm

ናፍቆት wrote:.... ሳስበው ሳስበው አንዳንዱ እንዲኖር የተፈጠረ አለ ... አንዳንዱ ደሞ እንዲኖር ሳይሆን የሚኖሩትን እያየ እንዲኖር የተፈጠረ አለ - እንደተምልካች ... አንዳንዱ ደሞ አለልህ ይኑር አይኑር እንኳን ላንተ ለራሱም የማያውቀው .. እንዲያው ይመሽለታል ይነጋበታል .... ምናምን .....
የታሰበውን ሳስበው ባስበው ግራ ግብት ... ጠንከር አለብኝ ... ግን ግን ሁሉም በአፈጣጠራቸው ላይ ምንም ድርሻ ወይም ምርጫ አልነበራቸውም ... እና ...
ብቻ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 61
Joined: Thu Feb 19, 2009 12:38 am

Postby ቀንዱ » Mon Apr 13, 2009 12:16 am

ስምዋ ግን ማናልሞሽ ነው ማናልቦሽ ? ማን አልሞሽ ከሆነ ይገባኛል: "ማን አልቦሽ" ሲባል ግን ማማ ወተት ትዝ አይልሽም? "ላም ነሽ" እንደማለት እኮ ነው:: አማርኛየ እየከዳኝ እንዳይሆን ብቻ::

ቀንዱ
ቀንዱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 125
Joined: Mon Jul 17, 2006 5:14 pm

Postby ናፍቆት » Wed Apr 15, 2009 7:31 am

ቀንዱ - አይ አይ አማርኛ እንኳን እኔን እንጂ አንተን አይከዳህም:: እኔ ተሳስቼ ይሆናል::

የስም ነገር ስታነሳ ትዝ ያለኝን ላጫውትህማ .... ካምፓስ እያለሁ አንድ የክላሳችን ልጅ ነበር .... እና በጣም ሰላምተኛዬ ነው .... ተፎካካሪዬም ነበር .... በማርክ ..... እና በተለይ የፈተና ሰሞን እዛ ግቢ ያለውን ፓኒክ ታውቃለህ .... ጥያቄ ምናምን መለዋወጥ ... አንዳንድ tough questions ላይ መነጋገር ምናምንም ነበር ..... እና ከኔም ከግሩፔም ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበረን .... ያን ያህል የጠለቀ ጓደኝነት ባይኖርም .... እናልህ መጨረሻ ላይ ልንመረቅ አካባቢ ሲሆን .... ልጁ ስሙን አልያዝኩትም ... አስቤውም አላውቅም ነበር .... እና straightforward ሆኜ በቅንነት ስምህ ግን ማነበር? አልኩት .... ሳንተዋወቅ ልንለያይ ነው ብዬ .... እውነት እልሀለሁ በቅንነት ነበር ያልኩት .... ..... ወይ ጉድ .... ልጁ አላበደልህም? ... እኔ ስጠይቀው አይኖቹ ባንዴ ቅልት ብለው አጉረጥርጦብኝ በጄ ልመልስለት የያዝኩትን የፈተና ወረቀት መንጭቆ ወስዶ መልስም ሳይሰጠኝ ሄደ ..... ከዛ ለልጆች የማነች ሞልቃቃ ... ስሜን እስካሁን ሳታውቅ ቀርታ ነው? .... አማረብኝ ብላ ነው? .... ምናምን ብሎ የኔን ግሩፕ ልጆች ጋ ሄዶ ሁሉ ... ማነች እስዋ ብሎ ... ጨፈረ ነው የምልህ ... በሁአላ ስሰማ እረ እኔ ይቅርታም ብጠይቀው ግዴለኝም ብለው ..... በየት በኩል ..... ከዛ በዛው ተመርቀን ተለያየን .... ልጁ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር ... ትንሽ 'weird' የሆነ ጸባይም አለው .... እና በቃ ከፈለገው ይሁንለት ብዬ ተውኩት ......

በሁአላ ላይ የሆነውን አጋጣሚ አትጠይቀኝም አሁን በቅርቡ ወደናንተ መጥቼ አልነበር? ካፌ ውስጥ ከሰዎች ጋር ቁጭ ብዬ ለምን ከች አይልልህም? ማመን አቅቶኝ .... ካልጠፋ ሰው ደሞ እሱን ማግኘቴ ... ከዚያ ሄጄ ላናግረው አልኩና .... በሁአላ ሳስበው እዛ በገዛ አገሬ ላይ ሁሉ ሰላም እያለ እንዲያ ያበደብኝ ... እዚህ በሰው አገር ምንስ ቢያረገኝ ብዬ ተውኩት .... በዚያ ላይ ጨርሶ አብዶስ እንደው .... የውጭ ኑሮ አንጎሉን አዙሮት አሁን ያለውን አስተሳሰብስ በምን አውቃለሁ ... ብዬ ይቅርብኝ አልኩ ... እሱ አላየኝም (ወይም አላወቀኝም - I don't know ) እኔ ግን በደንብ አየሁት ..... ልጅ ነው ... ግን ከመቼው ሽበት በሽበት እንደሆነ አላውቅም ... ፊቱ ግን ጥርት ብሏል .... እሱን ትቼ ቡናዬን መጠጣት ቀጠልኩ .... ያ ቀጭን ቡናችሁን .... ቡናችሁስ ይሁን - ከሁሉ ያስጠላኝ የነበረውን ልንገርህ? ያ የካርቶን ኩባያችሁ .... ውይ ውይ .... ለመጠጣት ያለኝን ፍላጎት በግማሽ አውርዶብኝ ነበር የምጠጣው ..... ትኩስ ነገርን እኮ ከበድ ባለ ሲኒ ከነማስቀመጫው ይዘህ ረጋ ብለህ ቁጭ ብለህ ስትጠጣው ... የሆነ grace and comfort አለው - አይመስልህም? ..... ካርቶን ሲኒህን በናፕኪን ይዘህ ... ሳትቸኩል ቸኩለህ መጠጣት .... ኡ.....ፍ ------ እኔማ አንድ ቀንም የምጠጣውን በቅጡ ጨርሼው አላውቅም ነበር ... ከነሚጠጣው ባስኬት ከትቼ በቃ..... ሲያስጠላ ..... ከምር ....... for that matter ብዙ ነገራችሁ ያስጠላኝ ነበር ... እኔ የተንቀዠቀዠ ነገር አልወድልህም ..... ሌላም ነገር ላይ በተልይ 'relationship' ላይ እንዲህ አቅል የምታጡ ከሆነ .... እንግዲህ አንተ ታውቃለህ .... 'በይ ቶሎ ቶሎ በይ - እኔ ስራ አለብኝ? ' ... በስመአብ

ጾሙ ሊገለኝ ትን.....ሽ ... በቃ ት....ን....ሽ ሲቀረው አለቀ ..... በቆሎና በዳቦቆሎ ብርታት አለቀልኝ ነው የማወራህ .... ድንቹም ጎመኑም ስልች.......ት ... ውይ
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

ባዶ: ጉራ

Postby ከምካሚው » Wed Apr 15, 2009 8:46 am

.... አዎ ልጅትዋ ... ይሄ ጉርድፍድፍ ምናምኑ ጎንተል ወይም ጥቅስ ያደርጋት የለ? ..... 'ውይ ከቤ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ያድራል ቆንጆ ጠቀስኩ ብሎ' ... ትል ነበር .... ....[/quote]

The false ego made a lot of pretty girls remain single, get life beyat
ከምካሚው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sun Mar 23, 2008 12:24 am

Postby ናፍቆት » Tue May 05, 2009 1:49 pm

ከምካሚው - Anything wrong with remaining single? ..... Speaking of which .... አንድዋ ያለችውን ልንገርህማ .... እ.... ያው ሴቶች ጸጉር ቤት የሚሄዱት ለመቆነጃጀት ብቻ እንዳልሆነ መቼም ታውቅ ይሆናል .... ለመገለሻሸጥና ለመላላጥም ሊሆን ይችላል .... እና አንድዋ ባሌ ባሌ እያለች የሴቱን ልብ ስታወልቅ ሌላኛዋ ምናለቻት በለኝማ ... 'አቦ ተይና ... የናንተ ባሎች እኮ የኛ ውሽሞች ናቸው' ...... አይጥምም? ያው ሁሉም የሚካፈለው ያለውን ወንድ ነው ... ሳስበው ..... ሌላ ከየት ይመጣል ... እና It's like ... vicious circle ..... እንደሚሉት ሊሆን ነው መሰለኝ .....

አንድ ልጅ ነበረች .... ባለትዳር ወንድ ያዙ ብላ ከምር የምትመክረን .... ከምሬ ነው የምልህ .... እንደሷ አባባል እነሱ በጣም የሚመቹ ተንከባካቢዎች እና ፍቅር አዋቂዎች ናቸው ..... ለየት ያለ ነገር (ስጦታም ሊሆን ይችላል) ይዘው መምጣትና .... ወጣ ያሉ 'ነገሮችን' ለማድረግ ብዙ ተነሳሽነትና ፍላጎት አላቸው ባይ ናት ..... ኮሌጅ ተማሪ ሆነን ባንድ ጊዜ ሁለት ባለትዳር ወንዶች ታስተናግድ እንደነበር አውቃለሁ .... ውሸቴን አይደለም ...... ሌላው ደሞ የምትለው ብዙ ሰአት አይሻሙም ነጻነትህን ብዙም አይገፉም .. ምክንያቱም የራሳቸው 'ትዳር' ጉዳዮች ቢዚ ስለሚያደርጉአቸው .....

ባክህ እስዋን ተዋትና .... ..... ባለፈው የጥላሁን ለቅሶ ሰሞን ጎሳዬ ባጋጣሚ አንድ BMW garage መኪናውን ሊያሰራ ይመጣል ..... ያው የኛን አገር ዘፋኞች መቼም ታውቃለህ .... attention .. ምናምን ...... እና የሆነ ነገር ሲለው ባለጋራዡ ..... ምን እንዳለው አላውቅም ..... ጎሳዬ ጮክ ብሎ ... 'እንዴ እንደዚህማ አይሆንም ... እንዴ ... ለቅሶ ላይ እኮ ነን ... ምን ማለትህ ነው' .... እያለ ሰውን ደሞ ዞር ዞር እያለ ያያል .... ከዛ እንግዲህ እንደዚያ ነው ምንም ለማድረግ አልችልም ይላል ሰውየው ..... 'እንዴ ለቅሶ ላይ መሆናችንን አታውም እንዴ? ' (ጮክ ጮክ ... ግራ ቀኝ መልከት መልከት) ..... ከዛ ጎሳዬ ሲሄድ ባለጋራዡ ... በንዴት 'እንዴ ሰውየው ጤና የለውም እንዴ? ምናርግ ነው የሚለኝ ' .... ይላል .... እየው ፈረስኩኝ .....

ተማሪ ሁሉ ክላስ ከገባ በሁአላ ... ተብለጭልጫ ... አጭር ቀሚስ ... ወይ ጥብቅ ያለ ጅንስ ... ወይ ብቻ ምናምን ነገር .እያረገች የምትመጣ ... ሁሌ አርፋጅ ልጅ ... ተማሪዎች ምን እንዳልዋት ልንገርህ? ... 'Ms. Attention' ..... ጨርሰን እስክንወጣ በዛው ስም ነበር በብዛት የምትታወቀው .... አንዳንዴ እንደቀልድ የሚለጠፉ ስሞች .... እድሜያቸው ሳይታሰብ ረዘም ሲል አላስተዋልክም? .....

በል በቃኝ ......
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ሚስተር-x » Tue May 05, 2009 3:18 pm

በቃሽ!

10ኛ ክፍል እያለን ስንዱ የምትባል በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ ሁሌ አርፍዳ ነበር የምትመጣው:: አይ ጂንስ አይ መቀመጫ-- ታርቀዋል:: ታዲያ ቤቷ እዛው ትምህርት ቤቱ አጠገብ ነበር:: ወንበሯ ወደመሀል አካባቢ ነበርና አውቃ ታድርገው ወይም ወንበሯ እየተቃወማት... ብቻ መግባቷን የምናውቀው በኴኴታው ነው:: ነፍሱን ይማረውና ፈለቀ አጋ የሚባል ስም ጠሪያችንና ኢንግሊሽ አስተማሪያችን ዳሌዋ ላይ ሲያፈጥ ይቆይና .... "እቱ በቃ በደንብ አይተንልሻል" አሁን ቁጭ በይ ይላት ነበር.::
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
ሚስተር-x
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1448
Joined: Mon Feb 02, 2009 6:16 am

Postby ከምካሚው » Wed May 06, 2009 1:05 pm

[quote="ናፍቆት"]ከምካሚው - Anything wrong with remaining single? ..... ኖ

btw,, ur so funny :wink:
keep posting...we love hearing from u
ከምካሚው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sun Mar 23, 2008 12:24 am

Postby ዶማው2005 » Wed May 06, 2009 10:31 pm

ናፍቆት wrote:ጾሙ ሊገለኝ ትን.....ሽ ... በቃ ት....ን....ሽ ሲቀረው አለቀ ..... በቆሎና በዳቦቆሎ ብርታት አለቀልኝ ነው የማወራህ .... ድንቹም ጎመኑም ስልች.......ት ... ውይ


እንደው አማርኛሽ ደስ ይላል...ባልፈው አገር ቤት ሄጀ ያንቺ አይነቱዋ "ሙ..ት ዶምየ....ልክስ...ክስ ነህ" ስትለኝ ሱስ ያዘኝና መብራት ሲጠፋ እሱዋ ጋ እውላለው....መሞላቀቅ ም አንዳንዴ ካምፕልመንት ይሆናል

እና ቡና...ከበድ ባለ ሲኒ ነው አልሽ...እሱንስ አልጠላም...ግን ትንሽ ሆነቻ ቡናዋ በሲኒ....መቸስ 20 አውንስ ቡና በቀን በቀን እየጠጣሁ...አገር ቤት ካፌ ውስጥ በ ሲኒ ሲሰጡኝ እንባየ ይመጣል....እሽ አንባየ አይመጣም...ግን ድገሙልኝ ስላቸው..."እረ የማነው" አይነት ሉክ ነው ሚሰጡኝ....እና የወረቀቱን ቡና ስትደጋግሚው ትወጅዋለሽ....
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

Postby እህምም » Thu May 07, 2009 9:21 am

ዶማው2005 wrote:እንደው አማርኛሽ ደስ ይላል...ባልፈው አገር ቤት ሄጀ ያንቺ አይነቱዋ "ሙ..ት ዶምየ....ልክስ...ክስ ነህ" ስትለኝ ሱስ ያዘኝና መብራት ሲጠፋ እሱዋ ጋ እውላለው....መሞላቀቅ ም አንዳንዴ ካምፕልመንት ይሆናል


ከምር ግን ችግራቹ ምንድነው? (እናንተ ሚኒንግ ወንዶች...) ከምር አንዱዋ ስጋ ቤት ምሳ እየበላን ድመት ባጠገባችን ስታልፍ ዘላ ለምን ጠረፔዛ ላይ አትወጣም....ክሌይሚንግ ,, "ሊ....በ.....ላ.....ኝ....ነ......ው! " :twisted: it's a funking cat! for pete's sake! :lol: the douche of an uncle that brought her thought it was cute. I had to leave before i punched her!
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ሚስተር-x » Thu May 07, 2009 3:17 pm

እህምም wrote:ከምር ግን ችግራቹ ምንድነው? (እናንተ ሚኒንግ ወንዶች...) ከምር አንዱዋ ስጋ ቤት ምሳ እየበላን ድመት ባጠገባችን ስታልፍ ዘላ ለምን ጠረፔዛ ላይ አትወጣም....ክሌይሚንግ ,, "ሊ....በ.....ላ.....ኝ....ነ......ው! " :twisted: it's a funking cat! for pete's sake! :lol: the douche of an uncle that brought her thought it was cute. I had to leave before i punched her!


በይ ይቺን ቃና ሳትለውጪ ደጋግሚን::
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
ሚስተር-x
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1448
Joined: Mon Feb 02, 2009 6:16 am

Postby ናፍቆት » Thu May 21, 2009 3:58 pm

ስለሞት ወይም ስለ አሟሟት በ funny መልኩ ሰምተህ ታውቃለህ? .... አንድ cheerful የሆነች ሰራተኛ እኛጋ ገብታልሀለች ..... እየው ... መሳቅ ነው መሳቅ ነው ... በምኑም በምኑም .... እና እኛ ጋ ከመምጣትዋ በፊትም የነበረችባቸውን እናውቃቸዋለ ... ዘመዶችዋ ናቸው ..... እና እዛ እያለች አንድ የሚያሳድግዋት የሆነች ልጅ ነበረች ... ከዛ አረብ አገር ሄዳ በጣም ታማ መጥታ (HIV) ከዛ የሞተች .... እና ሰሞኑን በሆነ ወሬ ተነስቶ የሞተች ጊዜ ይቺ ልጅ (ሰራተኛዋ) እዚያ ነበረች እና አንስታ ስታወራልኝ ..... ከምኑ ልጀምርልህማ .... ከሳቅዋ ለምን አልጀምርልህም? ገና ወሬውን ሳትጀምረው ፍ...ር...ስ ...... ልጅትዋ ተሰቃይታለች .... በጣም .... እና አልሞት ብላ አስቸግራ ነበር ምናምን ነገር..... ጠብቀው ጠብቀው መጨረሻ ላይ ይቺን ልጅና አንድ ደሞ ትንሽ የዘመድ ልጅ ቤት ወስጥ አለች ከስዋ ጋር ቁጭ ብለው እንዲጠብቅዋት ..... (ነፍስዋ እስክትወጣ) .... እና ሴትዮዋ ቤተክርስትያን ይሄዳሉ .... ትእዛዙ የነበረው ...... ሁለቱ ልጆች ቁጭ ብለው እንዲጠብቁ ... ታማሚዋ ከቀዘቀዘች አንድዋ ሮጣ ጎረቤት እንድትጠራ .. ቀሪዋ ደሞ በታማሚዋ አንገትና የእጅ ጣት ላይ ያለውን ትልልቅ የአረብ አገር ወርቅ እንድታወጣ ነበር ..... ከዛስ? ..... ልጅትዋ ድርቅ ነገር ትልባቸዋለች .... እና ይቺ የኛዋ ሰው ለመጥራት እየሮጥኩ ወጣሁ አለች ... ከዛ መሀል መንገድ ላይ ስደርስ ትዝ ሲለኝ አለች (በሽተኛዋ አንዳንዴ ራስዋን እንደመሳት እያለች ሰው ለመናከስ ትጋበዝ ነበር አለች ) እና.... 'ወይኔ ጉዴ ይቺን ትንሽ ልጅ ብትነክሳትስ' ብዬ አለች እየተሯሯጥኩኝ ወደቤት ስመለስ አለች ..... ልጅትዋ ከታማሚዋ ላይ እንደምንም ብላ ያንገትዋን ወርቅ አውልቃ ቀጥላ የጣትዋን ለማውለቅ የሞት ሞትዋን ትታገላለች ... ትለኛለች ... እየው እኔ ፈረስኩ..............ኝ ....... ይህን ሁሉ እንደትያትር በሳቅ እየፈረሰች ስትነግረኝ ..... ልጅትዋ ደስ አለችኝ ... ማለቴ የሞተችውም ዘመድዋ ናት ..... ስትሞትም በጣም አብዳለች ..... ግን the way she remembers how the girl died was so funny. .... የዘመድን አሟሟት እንዲህ በሚያስቅ መልኩ እየሳቀ ያወራልኝ ሰው እስካሁን የለም ነበር ... ከምር .....

ብዙ ጊዜ ለቅሶ ቤት ውስጥ በጣም የሚያስቅ ነገር ያጋጥመኝና እቸገራለሁ ..... ሰው ደሞ በጣም ደስታ ላይ ሲሆን ወይም ጥሩ 'event' ላይ ተካፋይ ሆኜ ደሞ እንባዬ ሊመጣ ይችላል ..... እና አንዳንዴ ይህ ጸባይ ከሰዎች ጋር ሊያደባብር ነገር ይችላል..... አንድ ጊዜ አንድ የሆኑ ዘመዳችን ሰውዬ ይሞታሉ .... እና ሰፈሩ የሆነ ትርምስምስ.... ያለ ነገር ሰፈር ነበር .... እና ከተቀመጥንበት ድንኳን ሆነን ... ምግብ የሚያበስሉትን ሴትዮ ታያለህ ..... እና ከምሳ በሁአላ ነው ከቀብር በሁአላ ... እና ...... ሴትዮዋ ይሄ የቤተመንግስት ባሪያ የሚባሉት ወጥ ቤቶችን አታውቅም? እንደዛ ናቸው ..... እና ይጎርሳሉ የሆነ ነገር በጣሳ ደሞ ይጠጣሉ ... ይጎርሳሉ ... ይጠጣሉ ..... አታምነኝም ወደ 1 ሰአት ተቀምጠን the whole time she was on it and I couldn't lift my eyes from her ..... ከዛስ? ..... ፌስታል አምጥተው የሆነ ትርፍራፊ ነገር በትልቅ ..... ምን ነበር ........ ያ ........ እንቅብ ...... ( 'እንቅብ' -በስመአብ አንተ! ይህን ቃል ጽፌው አላውቅም) .... እና በሱ ላይ ተከምሯል ... እና ከሱ ላይ የሆነ ነገር እየመረጡ (አጥንት ይሁን ምን አላውቅልህም) ብቻ በፌስታል ያስገቡ ጀመር ..... (I was like she must be crazy) .......... ከዛ አስገብተው ሲጨርሱ እንደገና ወደመብላታቸው ሲመለሱ .... እንዴ? ብዬ ....... በቃ ..... እኔ የለሁ.........ም ..... በሳቅ እንባዬ ወረደ ነው እኮ የምልህ ..... ከምር ...... እና የሟቹ ልጅ ለዘመድ ሁሉ 'ያባቴ ለቅሶ ቀን አሽካካች ብላ ...... ተወኝ ..... እስካሁን ተቃቅረናል ...... የኔን ችግር ማናየልኝ? አሁን በዛ ሰአት ስለወጥቤትዋ ባወራላት ይገባታል? አይገባትም:: ከምር ...

....

አንድ ጊዜ ደሞ አንድዋ ዘመዳችን ወደናንተ መጥታ ልጅ ወልዳ ትመለስና ክርስትናው እዚህ ይሆናል .... There whole family was at the church ceremony .... ለሊት ሄደን ምናምን ..... እና ትዝ ይለኛል እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ነበር .... እና መሀል ቅዳሴ ላይ ..... የዲያቆናቱ ድምጽ .... እኔ እንደዚያ አጋጥሞኝ አያውቅም ወይም ልብ ብዬ አላውቅም ..... ወይ ድምጽ ... ወይ ቅላጼ .... ወይ harmony! ብቻ አላውቅልህም ...... በጣም በጣም .... ሩ............ቅ ወሰደኝ .... እና ራሴን almost የት እንዳለሁ ከማን ጋር እንዳለሁ ረስቼዋለሁ ..... ከዛ የቅዳሴው rythm ሲቀየር ይመስለኛል ... ከሄድኩበት ስመለስ ፊቴ በእንባ ታጥቦልሀል ... ምን ትለዋለህ? .... አሁን ወላዲቱ እናት ብታየኝ 'በደስታዬ ቀን ይቺ ደሞ ምን ታለቅስብኛለች? ' አትለኝም? .... ያውም የናንተ 'citizen' ተወልዶ? ...... ምናውቅልሀለሁ .... እስካሁን አይታኝ በልብዋ ያለችኝን ብላኝስ እንደሆን .....

ወይ ጣጣዬ ....

.......
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ሚስተር-x » Thu May 21, 2009 7:29 pm

ናፍቆቴ ...እውነትም ጣጣሽ ረጅም ነው:: የለቅሶ ቤት ነገር ሲነሳ አቤ ነው ትዝ የሚለኝ:: ስንት አመቱ እንደሆን ታውቂያለሽ? አስራ አንድ:: ከታላላቆች እህቶቹ አንዷ የኔ ገርል ነበረች በዚያ ሰሞን:: የሁሉም ታላቅ የሆነችው እህቱ የአራት አመት ልጇ ድንገት ይሞትና ለቅሶ ተቀምጠናል:: ሰዉ ይለዋል ... ሙሾ ታውቂ የለ (የእናቶች ኪነት የሚባለውን) ይደረደራል:: ሁላችንም አዝነናል:: ታዲያ አቤ አልሰማም:: ባባቱ መኪና ላይ ገንዘብ ተቀባይ ሆኖ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዷል:: ሲመለስ ድንኴን ያያል:: ድንኴኑ በር ሲደርስ ነው ማን እንደሞተ የሰማው:: አይ አቤ... ራሱን ደፋ አርጎ (ገምቺ ትንሽዬ ያስራ አንድ አመት ጩጬ) ከጎኔ መቀመጫ ኩርሲ ሳብ አድርጎ ቁጭ ይልና በጩኽት ..... ልጄ... ልጄ...ልጄ እያለ ለምን አያስነካው:: እንደባህሉ ከሆነ ለቀስተኛው ቢያባራም ሰው ሲያለቅስ በለቅሶ ማጀብ አለበት:: አጠገቤ ያለችው እህቱ አንዴ በድንጋጤ አይኔን አይኔን ስታየኝ... የሳቅ ቦምብ ለምን አላፈነዳም! የተሰበሰበው ወጣት ሁሉ በሳቅቅቅ ሊሞት:: .... አንዷ (ዘመድ እኮ ናት) ሽንቷ ለምን አያመልጣትም:: እግሯን ገጥማ ከድንኴኑ ወደቤት ሩጫ:: በለው! እንዴት አርገን እናቁም::
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
ሚስተር-x
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1448
Joined: Mon Feb 02, 2009 6:16 am

Postby አባዊርቱ » Mon Jul 13, 2009 4:13 am

ናፍቆት wrote:ስለሞት ወይም ስለ አሟሟት በ funny መልኩ ሰምተህ ታውቃለህ? .... አንድ cheerful የሆነች ሰራተኛ እኛጋ ገብታልሀለች ..... እየው ... መሳቅ ነው መሳቅ ነው ... በምኑም በምኑም .... እና እኛ ጋ ከመምጣትዋ በፊትም የነበረችባቸውን እናውቃቸዋለ ... ዘመዶችዋ ናቸው ..... እና እዛ እያለች አንድ የሚያሳድግዋት የሆነች ልጅ ነበረች ... ከዛ አረብ አገር ሄዳ በጣም ታማ መጥታ (HIV) ከዛ የሞተች .... እና ሰሞኑን በሆነ ወሬ ተነስቶ የሞተች ጊዜ ይቺ ልጅ (ሰራተኛዋ) እዚያ ነበረች እና አንስታ ስታወራልኝ ..... ከምኑ ልጀምርልህማ .... ከሳቅዋ ለምን አልጀምርልህም?
ገና ወሬውን ሳትጀምረው ፍ...ር...ስ ...... ልጅትዋ ተሰቃይታለች .... በጣም .... እና አልሞት ብላ አስቸግራ ነበር ምናምን ነገር..... ጠብቀው ጠብቀው መጨረሻ ላይ ይቺን ልጅና አንድ ደሞ ትንሽ የዘመድ ልጅ ቤት ወስጥ አለች ከስዋ ጋር ቁጭ ብለው እንዲጠብቅዋት ..... (ነፍስዋ እስክትወጣ) .... እና ሴትዮዋ ቤተክርስትያን ይሄዳሉ .... ትእዛዙ የነበረው ...... ሁለቱ ልጆች ቁጭ ብለው እንዲጠብቁ ... ታማሚዋ ከቀዘቀዘች አንድዋ ሮጣ ጎረቤት እንድትጠራ .. ቀሪዋ ደሞ በታማሚዋ አንገትና የእጅ ጣት ላይ ያለውን ትልልቅ የአረብ አገር ወርቅ እንድታወጣ ነበር ..... ከዛስ? ..... ልጅትዋ ድርቅ ነገር ትልባቸዋለች .... እና ይቺ የኛዋ ሰው ለመጥራት እየሮጥኩ ወጣሁ አለች ... ከዛ መሀል መንገድ ላይ ስደርስ ትዝ ሲለኝ አለች (በሽተኛዋ አንዳንዴ ራስዋን እንደመሳት እያለች ሰው ለመናከስ ትጋበዝ ነበር አለች ) እና.... 'ወይኔ ጉዴ ይቺን ትንሽ ልጅ ብትነክሳትስ' ብዬ አለች እየተሯሯጥኩኝ ወደቤት ስመለስ አለች ..... ልጅትዋ ከታማሚዋ ላይ እንደምንም ብላ ያንገትዋን ወርቅ አውልቃ ቀጥላ የጣትዋን ለማውለቅ የሞት ሞትዋን ትታገላለች ... ትለኛለች ... እየው እኔ ፈረስኩ..............ኝ ....... ይህን ሁሉ እንደትያትር በሳቅ እየፈረሰች ስትነግረኝ ..... ልጅትዋ ደስ አለችኝ ... ማለቴ የሞተችውም ዘመድዋ ናት ..... ስትሞትም በጣም አብዳለች ..... ግን the way she remembers how the girl died was so funny. .... የዘመድን አሟሟት እንዲህ በሚያስቅ መልኩ እየሳቀ ያወራልኝ ሰው እስካሁን የለም ነበር ... ከምር .....

ብዙ ጊዜ ለቅሶ ቤት ውስጥ በጣም የሚያስቅ ነገር ያጋጥመኝና እቸገራለሁ ..... ሰው ደሞ በጣም ደስታ ላይ ሲሆን ወይም ጥሩ 'event' ላይ ተካፋይ ሆኜ ደሞ እንባዬ ሊመጣ ይችላል ..... እና አንዳንዴ ይህ ጸባይ ከሰዎች ጋር ሊያደባብር ነገር ይችላል..... አንድ ጊዜ አንድ የሆኑ ዘመዳችን ሰውዬ ይሞታሉ .... እና ሰፈሩ የሆነ ትርምስምስ.... ያለ ነገር ሰፈር ነበር .... እና ከተቀመጥንበት ድንኳን ሆነን ... ምግብ የሚያበስሉትን ሴትዮ ታያለህ ..... እና ከምሳ በሁአላ ነው ከቀብር በሁአላ ... እና ...... ሴትዮዋ ይሄ የቤተመንግስት ባሪያ የሚባሉት ወጥ ቤቶችን አታውቅም? እንደዛ ናቸው ..... እና ይጎርሳሉ የሆነ ነገር በጣሳ ደሞ ይጠጣሉ ... ይጎርሳሉ ... ይጠጣሉ ..... አታምነኝም ወደ 1 ሰአት ተቀምጠን the whole time she was on it and I couldn't lift my eyes from her ..... ከዛስ? ..... ፌስታል አምጥተው የሆነ ትርፍራፊ ነገር በትልቅ ..... ምን ነበር ........ ያ ........ እንቅብ ...... ( 'እንቅብ' -በስመአብ አንተ! ይህን ቃል ጽፌው አላውቅም) .... እና በሱ ላይ ተከምሯል ... እና ከሱ ላይ የሆነ ነገር እየመረጡ (አጥንት ይሁን ምን አላውቅልህም) ብቻ በፌስታል ያስገቡ ጀመር ..... (I was like she must be crazy) .......... ከዛ አስገብተው ሲጨርሱ እንደገና ወደመብላታቸው ሲመለሱ .... እንዴ? ብዬ ....... በቃ ..... እኔ የለሁ.........ም ..... በሳቅ እንባዬ ወረደ ነው እኮ የምልህ ..... ከምር ...... እና የሟቹ ልጅ ለዘመድ ሁሉ 'ያባቴ ለቅሶ ቀን አሽካካች ብላ ...... ተወኝ ..... እስካሁን ተቃቅረናል ...... የኔን ችግር ማናየልኝ? አሁን በዛ ሰአት ስለወጥቤትዋ ባወራላት ይገባታል? አይገባትም:: ከምር ...

....

አንድ ጊዜ ደሞ አንድዋ ዘመዳችን ወደናንተ መጥታ ልጅ ወልዳ ትመለስና ክርስትናው እዚህ ይሆናል .... There whole family was at the church ceremony .... ለሊት ሄደን ምናምን ..... እና ትዝ ይለኛል እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ነበር .... እና መሀል ቅዳሴ ላይ ..... የዲያቆናቱ ድምጽ .... እኔ እንደዚያ አጋጥሞኝ አያውቅም ወይም ልብ ብዬ አላውቅም ..... ወይ ድምጽ ... ወይ ቅላጼ .... ወይ harmony! ብቻ አላውቅልህም ...... በጣም በጣም .... ሩ............ቅ ወሰደኝ .... እና ራሴን almost የት እንዳለሁ ከማን ጋር እንዳለሁ ረስቼዋለሁ ..... ከዛ የቅዳሴው rythm ሲቀየር ይመስለኛል ... ከሄድኩበት ስመለስ ፊቴ በእንባ ታጥቦልሀል ... ምን ትለዋለህ? .... አሁን ወላዲቱ እናት ብታየኝ 'በደስታዬ ቀን ይቺ ደሞ ምን ታለቅስብኛለች? ' አትለኝም? .... ያውም የናንተ 'citizen' ተወልዶ? ...... ምናውቅልሀለሁ .... እስካሁን አይታኝ በልብዋ ያለችኝን ብላኝስ እንደሆን .....

ወይ ጣጣዬ ....
============
:):):)...አንቺ ልጅ, በህይወት አለሽ እንዴ?? ስንተኛው ገጽ ላይ ሄጄ ፈልጌ አገኘሁሽ:):) ያንን መጽሀፍ አገኘሺው??
የመቺሽ አቦ!

.......
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests