ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ናፍቆት » Wed Jul 29, 2009 7:43 am

ክረምት የምሩን የመጣው ዛሬ ነው ብል አላጋነንኩም:: ከቅዝቃዜው .. ችክ ካለ ስስ ግን ደሞ አበስባሽ ዝናብ .... እና ንፋስ ጋር .... ምናምን ....

ግን ደስ ይላል:: ክረምት እወዳለሁ::

ክረምት ሲባል ምን ትዝ ይልሀል? በቆሎ እንዳትለኝ:: ግን በተለይ ዘንቦ አባርቶ በስሱ የሚወጣ የወደማታ ጸሀይ ላይ ዎክ ማድረግ .... የተጠበሰ በቆሎ ካንድዋ ምስኪን ከመንገድ ላይ ገዝተህ እየጋጥክ ... ምናምን ... ደስ አይልህም? በነገርህ ላይ ጥብስ በቆሎ በጣም ደስ ይለኛል:: ከማስቲካ በቀር ሌላ ነገር እየበላሁ መንገድ ለመንገድ ስሄድ ራሴን አላስታውሰውም - የበቆሎ ጥብስ እየበላሁ ግን ብዙ ጊዜ ....

ይሄ ወደማታ ላይ አንዳንዴ የግቢ በርህ ላይ ቆመህ ወጪ ወራጅ ማየት .... ኑሮን ማየት .... ከ11 ሰአት በሁአላ ባጋጣሚ ቤት ሆኜ በር ላይ ቆም ብያለሁ .... እንትን....... ወተት! ...... እዚህ አገር ታውቃለህ መቼም አብዛኛው ሀበሻ ቤተሰብ ወተት ተከራይ ነው .... እና ወተት የሚታለበው ይሁን ወይም ደሞ አላቢዎቹ የሚያከፋፍሉት በዚያ የወደማታ ሰአት አካባቢ ነው መሰለኝ .... መንደር በርህ ላይ ወደ ዚያ ሰአት ቆም ካልክ ... የወተት እቃ የያዙ ግለሰቦች ወደላይ ባዶውን ይዘው ሲሄዱ ወይም ከወተት ጋር ሲመለሱ ማየት የተለመደ ነው .... ብዙዎቹ የቤት ሰራተኞች ናቸው .... አንዳንዶቹ ይችን 'regular' የሆነ ተደጋጋሚ ከቤት መውጫ እድል ወንዶቻቸውን የሚገናኙበት አጋጣሚያቸው ይመስለኛል .... በረጅሙ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ላይ ሲሄዱ .... ትንሽ ከፍ እንዳሉ ካንዱ ጋር ሲገናኙና እያወሩ ሲሄዱ ... ከዚያ ሲመለሱ ደሞ ልጁ የተነሳበት ቦታ ድረስ አብረው መጥተው ሲለያዩ .... ምናምን ነገር .... ወተታቸውን በጆግ ወይም በላስቲክ (ጀሪካ) .... ወይ ምናምን ብቻ .. አንጠልጥለው ወይ አቅፈው ... .... እና አየሁ አየሁና ... ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው ... ሌሎቹ ደግሞ በግምት ከ10-15 አመት የሚደርሱ ወንዶች ልጆች .... ዝናቡ በፈጠረው ትንሽዬ ጎርፍ መሳይ የምትወርድ ውሀ ውስጥ ጫማቸውን ነከር ወጣ እያርጉ እየተጫወቱ ....

በሁአላ አንዱ መጣልሀ ... ትልቅ ወንድ ... ባንድ እጁ በፌስታል መጽሀፍ ወይም ወረቀቶች ነገር ይዞልሀል ... በሌላው እጁ ወተት በትንሽዬ ማንጠልጠያ በሌለው ጀሪካ እቅፍ አድርጎ ..... ዝርክርክ ያለ ወንድ .... እስቲ ባይጠጣስ ቢቀር ...... እኔ ለራሴ ወንድና ፌስታል አብሮ አይሄድልኝም .... ጭራሽ ደማቅ አረንጓዴ ማንጠልጥያ-የለሽ ጀሪካ ጨምሮበት ... ዝብርቅርቁ የወጣ ወንድ ..... paper bag ይሻለኛል በትንሹም ቢሆን....... እናልህ .... ሳይ የነበረውን 'peaceful' የእለት ተእለት scene ብልሽት አርጎብኝ ... ጥዬው ግብት::

በዚህ ብርድ ምን እንዳማረኝ እንዳትጠይቀኝ! ከምር

ውይ .....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ገብርየ » Sun Aug 02, 2009 12:29 pm

ናፍቆትየ እንዴት ነሽ ድህና ነሽ እህቴ እኔ ክ ጎንድር ስሆን አሁን ድግሞ አውስትራሊያ ነው እምኑርው.ክመጅመሪያ እስክ አሁን ድርስ ያልውን አንበቢ በጣም ነው የውድድኩሽ አጻጽፊ ትንሽ የባላገር ነገር ነው......ግን ሲሚኝማ .... በዙ በጽፍ ድስ ባለኝ ግን ስው የትለያይ ስጡታ ነው ያልው ስናገር ትንሽ ድፍረ እላልሁ አታውቂ ክሆን በአለም ላይ ሁለት ድፋር አሉ አንዱ ፍርንጅ ነው አንዱ ደግሙ ባልገር ነው .....ያው ማለት አንዱ በ ማውቅ ሲሆን አንዱ ድግሞ ባለማውቅ..... :D :D . እስኪ እንግዳ አክባሬንትሽን ተቅባይነትሽን በኔ ልየው>>>> እቅጠላልሁ..
ውንድምሽ
ገብርየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Thu Dec 16, 2004 2:05 pm
Location: united states

Postby ገብርየ » Sun Aug 02, 2009 12:47 pm

ናፍቆትየየየየየየየ...............ለንግርሽማ ሲሚኝማ እናታለም ጥሩ ስው ነሽ እግዚአብህእር በዙ አምት ያኑርሽ 123456 አምት እኔ ክ ጉንድር አውስትራልያ ውድቂለሻለሁ በዙ አለልሽም መጽፍ ባንች ያምራል እኔማ ውንድ ነኝ ይፍታትንኝል::..........እንግዳ ትቅባይ ነሽ አውቃልሁ ተቅበይኝ ...አንድ ጨዋታ ለንግርሽ ይናቴ እህት ድውይ ሥናግርተ እሱ ይምስላት አሚሪካ ነበርና ሌሉቹን ቤተስብ ምናምን .......ስተጠይቅኝ ...እኔም በጣም ትልቅ ስልሆንች ታትየ ነው እምላት እና ....ታትየ እኔኩ አውስትራሊያ ነው ያልሁ ሰላት ደሞ እሱ የት ነው ? ከዛው ቅጠለ አርጋ ምን ውስድህ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እንዲው ተበታትንናል ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ላዛሬ ድሞ ለነገ ስው የበለን::
ገብርየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Thu Dec 16, 2004 2:05 pm
Location: united states

Postby ናፍቆት » Mon Aug 03, 2009 10:29 am

...
Last edited by ናፍቆት on Thu Aug 06, 2009 9:38 am, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Mon Aug 03, 2009 1:39 pm

አሁን ስመጣ በሬድዮ ..... ያ ሰይፉ ፋንታሁን ደህና አድርጎ ያብጠለጥላችሁአል ይዞ .... ሰሞኑን ከወደናንተ ደርሶ አይደል የመጣው? እሱ እንደሚለው ከሆነ የሰዎች ዘፈኖች - ግጥሞች - የተለያዩ ስነጽሁፎች - የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ... ምናምን ... ምናምን .... አሳታሚው ማን እንደሆነ በማይገልጹ ዲቪዲዎችና ሲዲዎች ምናምን .... እየታተሙ ካላሳታሚ ስም ዝም ብለው እየተቸበቸቡ ነው ይላል..... እና ምናለ እነዚህ ሰዎች ቢያንስ እዚህ ካሉት የአርቲስቶች ህይወት የተሻለ ኑሮ ላይ ያሉ ናቸው (Is that really true? ) እና ሌላው ቢቀር ትክክለኛ ደራሲዎችና የሙያው ኦሪጂናል ባለቤቶችን እያሳወቁ - እያስፈቀዱ - የሚገባቸውንም መክፈል አለባቸው ነው የሚለው (And I agree with him) ....

ባሁኑ ሰአት በአሜሪካን አገር 'ባለጉዳይ' የተሰኘው ተወዳጅ ተከታታይ የቲቪ ድራማ እየተቸበቸበ አንደሆነ እና በባለቤትነት የማንንም ስም ያልያዙ ቅጂዎች ብዙ እንዳሉ .... ሰዉም ዝም ብሎ እየገዛ እንደሚጠቀም..... እና ሌላው የገረመኝ 'ፋሲል ደሞዝ' የሚባል ዘፋኝ በጣም ስሙ እንደገነነ .... ብዙ ሰዎች ስለሱ እንደጠየቁት አውርቷል ... እኔ የምልህ? Do you know this guy? I mean ፋሲል ደሞዝ. I've never heard of this name before. But most likely, I've heard his music in one of the radio stations.

በል የቅጂ ሰረቃው ላይ ካለህበት ... ትንሽ ትንሽ ላክ ላክ አድርግላቸው ለስራው ባለቤቶች .... ሰይፉ እንዳለው ከሆነ እነዚህ ሰዎች የልፋታቸውን ዋጋ በጊዜው እንዳግባቡ ቢያገኙ እኮ ሲደክሙ ወይም ሲታመሙ ልመና አይወጡም ....

በናትህ ጾም እኮ ሊገባ ነው - ቸኮሌት የለህም? እኔ አልቆብኛል::

...
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Thu Aug 06, 2009 10:44 am

???
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ከምካሚው » Thu Aug 06, 2009 1:28 pm

ናፍቆት wrote:በዚህ ብርድ ምን እንዳማረኝ እንዳትጠይቀኝ! ከምር

ውይ .....


ወይ ጉድ ምን እንድሆነ አወኩት
please tell us about the night life in addis,
ክ አክብሮት ጋር
ከምካሚው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sun Mar 23, 2008 12:24 am

Postby ገብርየ » Thu Aug 06, 2009 4:12 pm

እኔ እምለሽ ምነው ዘጋሽኝ አጠፈሁ እንዴ???....ደሞ አላጠፈሁም ባጠፋስ ያገርሽ ልጅ አይድለሁ አሁን መሬት ለገዛ ለመጣ ነው እና ታጋዥኛልሽ ? ጥሩ ቦታ መሬት ስንት ነው ለምሳሌ ብዩ ስም አልጥራም አላውቅውም ጎንድር ገዝቻለሁ አሁን አዲስ አበባ ነው እምፈለገው ምክኒያቱን ለንግርሽ እኔ ያለሁብት አገር አለገዛም ለምን በትይ የምትገዥው ቤት 300,000 ዶላር ቢሆን ክፍል አርግሽ እምትጨርሽው 20 አምት ነው እሱም ኢትዮ ዘመድ ምናምን ክለልሽ ነው ስልዚህ እኔ ለምን ኢትዮ ግዝቸ በሁለት አምት በጨርስው ብየ ነው ከዛ ......
ኖ ሙር ስድት ::እስኪ ህሳቤን የሁን ነግር ብይው .
ውንድሽ
ገብርየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Thu Dec 16, 2004 2:05 pm
Location: united states

Postby ዞብል2 » Thu Aug 06, 2009 7:17 pm

ገብርየ የማነህ ጀጋ :P :lol: :lol:


መጀመሪያ ዋርካ የተመዘገብክበትን ቀንና ሎኬሽን ተመልከት :wink:


ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2381
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ባቲ » Thu Aug 06, 2009 7:41 pm

ዞብል2 wrote:ገብርየ የማነህ ጀጋ :P :lol: :lol:
ዞብል ከፒያሳ


ዞብል2 :lol: :lol: :lol: :lol:
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ገብርየ » Thu Aug 06, 2009 8:29 pm

ባቲ wrote:
ዞብል2 wrote:ገብርየ የማነህ ጀጋ :P :lol: :lol:
ዞብል ከፒያሳ


ዞብል2
ዞብል እንድምነህ ይቅርታ ጅጋ ምንድን ነው ብየ አልጥይቅህም ምክኒያቱም አንት ነህ ትላልህ ግን ምንድን ነው? ሁለትኛ ይተምዝግበኩት ቅኑ ምን ሆን ? ሎኪሽን ላለክው እኔ 2004 ሳይብር ስመዝግብ ብዙ እውቅት አለንበርኝም አሁንም በዙ ይለኝም ገንዝብ ግን አለኝ ገንዝቡንም አለኝ ያልኩብት ስለማታይኝ ነው ውንድሜ ግን መች ነው እምታውቅውን እምታሳውቅ ያንድ አገር ልጁች አይድልንም እኔ ተስፋ እድቆርጥ አታድርግኝ እባክህ ነጩቹ ሳይንጋግሩ በቅዳችው ይግባባሉ እንዲያው ትንሽ ልብልህ በይ ነው እንጅ እንኩን አኔ ትንሹ ብዙ ስው ምክሮንም አልገባን :: እድምታይው በይቤቱ ጥሪ ምናምን ትቻለሁ ምክኒያቱም ህሚት ብቻ ስለሆን አሁን ስባት ቅን እስራለሁ አይምስለህም እንዳንት ትንሽ እሚያውቅ ብዙ ተሳስቱ ስለሚያሳስት ራቅ ማለቱ አይሽልም ...በዙ እል ነበር ግን ነፍቆትን ፍርች ነው::
ለውድ ፊቱ ግን ዝም በለህ አትሳድብ ክትሳድብክ እኔ አልጽፍለህም ቻው ውንድምየ .
ገብርየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Thu Dec 16, 2004 2:05 pm
Location: united states

Postby ረቂቅ 2 » Sun Feb 07, 2010 3:38 pm

ናፍቆት wrote:
ይሄ ወደማታ ላይ አንዳንዴ የግቢ በርህ ላይ ቆመህ ወጪ ወራጅ ማየት .... ኑሮን ማየት .... ከ11 ሰአት በሁአላ ባጋጣሚ ቤት ሆኜ በር ላይ ቆም ብያለሁ .... እንትን....... ወተት! ...... እዚህ አገር ታውቃለህ መቼም አብዛኛው ሀበሻ ቤተሰብ ወተት ተከራይ ነው .... እና ወተት የሚታለበው ይሁን ወይም ደሞ አላቢዎቹ የሚያከፋፍሉት በዚያ የወደማታ ሰአት አካባቢ ነው መሰለኝ .... መንደር በርህ ላይ ወደ ዚያ ሰአት ቆም ካልክ ... የወተት እቃ የያዙ ግለሰቦች ወደላይ ባዶውን ይዘው ሲሄዱ ወይም ከወተት ጋር ሲመለሱ ማየት የተለመደ ነው .... ብዙዎቹ የቤት ሰራተኞች ናቸው .... አንዳንዶቹ ይችን 'regular' የሆነ ተደጋጋሚ ከቤት መውጫ እድል ወንዶቻቸውን የሚገናኙበት አጋጣሚያቸው ይመስለኛል .... በረጅሙ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ላይ ሲሄዱ .... ትንሽ ከፍ እንዳሉ ካንዱ ጋር ሲገናኙና እያወሩ ሲሄዱ ... ከዚያ ሲመለሱ ደሞ ልጁ የተነሳበት ቦታ ድረስ አብረው መጥተው ሲለያዩ .... ምናምን ነገር .... ወተታቸውን በጆግ ወይም በላስቲክ (ጀሪካ) .... ወይ ምናምን ብቻ .. አንጠልጥለው ወይ አቅፈው ... .... እና አየሁ አየሁና ... ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው ... ሌሎቹ ደግሞ በግምት ከ10-15 አመት የሚደርሱ ወንዶች ልጆች .... ዝናቡ በፈጠረው ትንሽዬ ጎርፍ መሳይ የምትወርድ ውሀ ውስጥ ጫማቸውን ነከር ወጣ እያርጉ እየተጫወቱ ....

በሁአላ አንዱ መጣልሀ ... ትልቅ ወንድ ... ባንድ እጁ በፌስታል መጽሀፍ ወይም ወረቀቶች ነገር ይዞልሀል ... በሌላው እጁ ወተት በትንሽዬ ማንጠልጠያ በሌለው ጀሪካ እቅፍ አድርጎ ..... ዝርክርክ ያለ ወንድ .... እስቲ ባይጠጣስ ቢቀር ...... እኔ ለራሴ ወንድና ፌስታል አብሮ አይሄድልኝም .... ጭራሽ ደማቅ አረንጓዴ ማንጠልጥያ-የለሽ ጀሪካ ጨምሮበት ... ዝብርቅርቁ የወጣ ወንድ ..... paper bag ይሻለኛል በትንሹም ቢሆን....... እናልህ .... ሳይ የነበረውን 'peaceful' የእለት ተእለት scene ብልሽት አርጎብኝ ... ጥዬው ግብት::

በዚህ ብርድ ምን እንዳማረኝ እንዳትጠይቀኝ! ከምር

ውይ .....


በጣም ብዙ አመት በጣም ወደ ኋላ ሄድኩ በትዝታ በተለይ ባለ ወተቶቹ....
ረቂቅ 2
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Mon Jan 29, 2007 5:16 pm

Postby ናፍቆት » Thu Jul 22, 2010 5:53 pm

እኔም!
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

እንኳን ደህና መጣሽ!

Postby ዋኖስ » Thu Jul 22, 2010 6:05 pm

እንኳን ደህና መጣሽ! ናፍቆት

ረዥም ጊዜ ጠፋሽ ከዋርካ በሰላም ነው?

ለማንኛውም እንኳን በሰላም መጣሽ!


ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: እንኳን ደህና መጣሽ!

Postby መስለ መላጣው » Wed Jul 28, 2010 11:20 pm

ዋኖስ wrote:እንኳን ደህና መጣሽ! ናፍቆት

ረዥም ጊዜ ጠፋሽ ከዋርካ በሰላም ነው?

ለማንኛውም እንኳን በሰላም መጣሽ!


ናፍቆት የጠፋችው ልጆች ወላልዳ ነው
ዋኖስ ደህና ነህ ወይ የጎጃሙ ነኝ
መስለ መላጣው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Wed Jul 28, 2010 10:42 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests