ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ShyBoy » Tue Apr 29, 2008 9:46 pm

ኦ! ናፍቆት የጥንቷ: ከየት ብቅ አልሽ? እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰሽ!!! (ለነገሩ በሰላም ደረስሽ ለማለት ያስቸግራል :lol: እኛ መቸ በሄድን እያልን አንች ሀገርሽን ጥለሽ ወጠሽ):: ደሞ ምን ይሁን ብለሽ ነው በአመትባል ምድር ከሀገር ቤት የወጣሽው? እኛ ወዳለንበት ሀገር ከሆነ የመጣሽው እንኳን ደህና መጣሽ ብያለሁ!!! ሌላ ሀገር ከሆነ የሄድሽው መልካም ጉዞ!!! I hope እንደኛ ወጠሽ እንደማትቆይ:: በሰላም ወደ ሀገርሽ ይመልስሽ ብያለሁ ለማነኛውም!!!

ስለ ቴዲ መታሰር ዋርካ ፍቅር ብዙ ስለተባለ እዛው ሂደሽ አንብቢ........if you are interested at all. ያንች ነገር እኮ: ደሞ ንዋይ ወደ ሀገር ቤት መመለሱንም አልሰማሁም በይኝ አሉ? :lol: ካልሰማሽ አሁን ስሚው::

ናፍቆት: የምር ግን እኔ ያለሁበት ቦታ ከሆነ የመጣሽው ባለፈው እንዳልሁሽ ባገኝሽ ደስ ይለኛል:: ከምሬን ነው!!!

መልካም ከሀገር ውጭ ቆይታ ይሁንልሽ!!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby የኔታ » Thu May 01, 2008 7:25 pm

ShyBoy wrote: ናፍቆት: የምር ግን እኔ ያለሁበት ቦታ ከሆነ የመጣሽው ባለፈው እንዳልሁሽ ባገኝሽ ደስ ይለኛል:: ከምሬን ነው!!!


አይናፋሩ,

I think you can strike a deal with me. I know how to get hold of her, I mean I've the leads .... I say this as I can imagine, what you're plotting already :) ጥሩ ፈረስ አዘጋጅተሀል ለመሆኑ?

no question that you'll give us your line about being timid and ...
ነገር ግን ባንተና በሷ መካከል ያለው click is well described ቦንቡ ፍቅርሽ ሲፈነዳ ብሎ አዝማሪው እንዳለው እስከዛሬ የታፈነው አይናፋርነትህም እንደዛው ነው :) you'll then be capable of almost every thing ... አብዮት አገራችን ላይ ፈንድቶ እንዴት uncontrollable እንደሆነ ታስታውሳለህ አይደል?

In a way this feels strange to see Nafqot askin for an update. Hope she'll be rewarded in a juicy fashion as she was fillin us in ... truth be told, those updates have been extremely helpful to me as I tried to blend in returning home after 11yrs. ግሩም ድንቅ ስራ ነው የሰራሽው!!!

coming to Teddy Afro, I agree with you ቢቻል በመጠንቀቅ ሰው እስር ቤትን avoid ቢያረግ ጥሩ ነው:: it's a great deal of waste for the individual, for the economy ... however, I'm not too sure if it is entirely up to you to run into trouble or not ... in my case, I've managed to run away from it and will try to remain the same ...

እንግዲህ ያይናፋሩን mischief ከተረፈች ሌሎች private audition የምትፈልጉ ሁሉ you just have to line up :P
የኔታ
የኔታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Nov 15, 2003 2:28 am

Postby ShyBoy » Fri May 02, 2008 1:51 am

ኧረረረረረረረ.............የኔታ ምን እያሉ ነው? (እስዎ ያልሁት የኔታ እና ለቅስና መምህራን የሚሰጠው 'የንታ' የሚለው ማረግ አንድ አይነት ስለመሰሉኝ ነው):: ብዙው ያሉት ነገር አልገባኝም: የጻፉት እንግሊዘኛ ትንሽ ከብዶኛል:: ግን ነገር እየጠመዘዙ እንደሆነ ገብቶኛል:: :lol: እኔ ድሮም ጀምሮ በጣም እንደማደንቃት እና በአካል ባገኛት በጣም ደስ እንደሚለኝ ነግሬያት ስለነበር ነው እኔ ያለሁበት ሀገር ከሆነ የመጣሽው ባገኝሽ ደስ ይለኛል ያልሁት:: ከዛ ውጭ ያለውን ነገር እንግዲህ እንደፈለገዎ ይተርጉሙት::

የሆነው ሁኖ በዕስዎ አማላጅነት ብቻ ነው ናፍቆትን ማግኘት የምንችለው ማለት ነው?:lol: እስኪ እንግዲህ ናፍቆት ራሷ መጣ የምትለውን እስከምንሰማ እንጠብቃለን::

ናፍቆት: በሰላም ነው ግን አንዴ ብቅ ብለሽ በዛው የጠፋሽው? ኧር ባክሽ በጣም ተናፍቀሻል በውጭ ሀገር የደረሱብሽን ገጠመኞች ጨምርሽ ይዘሽ ከች በይልን! እኔ ያለሁበት ሀገር ከሆነ የመጣሽው: እንደማገኝሽ አሁንም ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ!!! ቅር ካላለሽ ነው ታዲያ::

በድጋሜ መልካም የውጭ ሀገር ቆይታ እመኝልሻለሁ!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby የኔታ » Fri May 02, 2008 8:55 am

አይናፋሩ

ጨዋነትህ መቼም የትየለሌ ነው ... አንቱ ማለትህ ያስመሰግንሀል!

አይሆንም እንጂ ቢሆንማ ኖሮ ናፍቆትን intimately ጭምር መተዋወቅ ሎተሪ እንደመውጣት ነው የምቆጥረው:: Jokes or ነገር ጥምዘዛ aside, it would be OK to fancy that. I'm not categorically saying that is your intention though ... እዚህ ዋርካ ላይ በብዕር ስም ስለሆነ የምንመጣው ማንነት ተገላልጾ ሰው ይቀራረባል ብዬ ብዙ ተስፋ አላረግም ... አይሆንም ያልኩበት ምክንያት ይሄው ነው::

actually a very good friend of mine has this big dream of bringing all these anonymus identities to the light ... an effective social networking can not be established on such exclusively anonymus identities.

አማላጅነት እንኳን ስልጣን አልሰጠችኝም - - ግን እንዴት እንደምትገኝ 'መረጃም ማስረጃም' ፈልጌ ስለማገኝ ነው :) just kiddin ... all this to tease and tempt Nafqot to come out and fill us in ...

I'm looking forward to see how she'll put things in to perspective. "... እዛ እናንተ አገር ... እኔ ምን አውቄልህ ... እኔጃ ... ይባላል አሉ ..." ወ.ዘ.ተ እያለች የምትወስዳቸው assumptions are always interesting, it would be great now to hear what she makes of them all ...

እባክሽ እባክሽ ስራውን ቶሎ ጨራርሺና ጻፍ ጻፍ አድርጊ ... በስምሽ እንጠብቃለን!
የኔታ
የኔታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Nov 15, 2003 2:28 am

Postby ጉዱ ካሳ » Sat May 03, 2008 11:16 pm

ሰላም Shyboy እንዴት ነህ አባ! መቸም በአሉን በጥሩ ሁኔታ እንዳሳለፍከው እገምታለሁ:: መቸም መልዕክት ማድረስ ግዴታዬ ነውና ጌታ እንዳለህ " እኔ እንጃልህ የኔታን ስጠረጥረው ናፍቆት ናፍቆት ሽቶኛል" ብሎሀል! እንደው የዳግማዊ ትንሳዬን በአል ለማክበር ደፋ ቀና ስል እንዳልረሳው ብዬ ነው! መልካሙን እመኝልሀለሁ!
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
ጉዱ ካሳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 356
Joined: Wed Oct 22, 2003 6:22 pm

Postby የኔታ » Mon May 05, 2008 9:14 am

አሁንስ እንኳን አያናፋሩና ናፍቆት ሸውደውን ተገናኙ መሰለኝ ... ድራሻቸው ጠፋ!

ይሄ አንገት ደፊ ልጅ እኮ አይታመንም ... በ 24 ሰዐት ስንት ገጽ ያነበበና ልጅትዋም ላይ a sort of impression የፈጠረ ይመስላል:: he should be capable of ... የዕውነት ግን እንደዚህ ከሆነ መቼም የሚጥም የሚጥም አይነት ነገር ነው ...

ግን አንዳንዶች እኛም አልተናገርነውም እንጂ በ receord spped ነው የናፍቆትን posts ያነበብነው - - መልካም ፈቃድዋ ቢሆን ልናገኛት እንወዳለን የሚሉ ብዙ ተመዝገበዋል ::

አያንፋሩ:- ላታውቀው ትችላለህ ብዬ ሳይሆን I ended on a very nice clip: http://youtube.com/watch?v=M-a2k-g_Y-w
honestly, it would have been just one more clip like many others had I not read what you wrote about ጎጃም አዘነ - - this song has some depth! ያንተን elaboration ሰለ ግጥሞቹ ብሰማ በጣም ደስ ይለኛል መልካም ፈቃድህ ቢሆን?

አንዳንዴ ስራ መፍታት ይሁን መብዛት አላውቅም ነገሮች ይከመሩና አልንቀሳቀስ ይላሉ:: ከ YouTube ጋር ለመጫወት ጥሩ ይመቻቻል ማለት ነው:- let me share with you what I found: the clip that must have inspired R Kelly(I want to believe so) to write "the world's greatest' is another clip from Ethiopia, check it out: http://youtube.com/watch?v=cdEcHidCa4s
R Kelly በእንግሊዝኛ ተርጉሞት ነው እንጂ the lyrics must have been the same. እንቅስቃሴ, ካናቴራው .... OMG, I love this clip! it makes me appreciate how simple things are supposed to be ... who gives a s... in any way.
ባትሪዬን ግጥም አድርጎ ነው የሞላልኝ ወደ ስራዬ ልመለስ ...
የኔታ
የኔታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Nov 15, 2003 2:28 am

Postby ShyBoy » Mon May 05, 2008 3:25 pm

ጉዱ ካሳ wrote:ሰላም Shyboy እንዴት ነህ አባ! መቸም በአሉን በጥሩ ሁኔታ እንዳሳለፍከው እገምታለሁ:: መቸም መልዕክት ማድረስ ግዴታዬ ነውና ጌታ እንዳለህ " እኔ እንጃልህ የኔታን ስጠረጥረው ናፍቆት ናፍቆት ሽቶኛል" ብሎሀል! እንደው የዳግማዊ ትንሳዬን በአል ለማክበር ደፋ ቀና ስል እንዳልረሳው ብዬ ነው! መልካሙን እመኝልሀለሁ!


ሰላም ጉድሻ: እንኳን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሰህ? የበዓል ሰሞን የሉኳንዳ ገበያ እንዴት ነበር? መቸስ ከገበያው ብዛት መተንፈሻ ሁሉ ሳታጣ አትቀርም:: :lol:

ጉድሻ: የጌታን መልዕክት ስላደረስህልኝ አመሰግናለሁ:: እና ጌታን ስትለው.........እርግጥ ነው የኔታ ትንሽ ትንሽ ናፍቆትን: ናፍቆትን ይሸታል; እንግሊዘኛም ይቀላቅላል ግን መዓዛው ለኔ ተለይቶብኛል በልልኝ:: ወደ ሉኳንዳህ ስትመለስ ለናፍቆት ሀገር ረግማ እንዳትመለስ ቆንጆ ቁርጥ አዘጋጅተህ በFedEx overnight ላክላት:: አሁን ያለችበትን አድራሻ የኔታ ይሰጥሀል:: ክፍያውን እኔ ወደሉኳንዳህ ስመጣ እሰጥሀለሁ: ወይም አሁኑኑ ከፈለግኸው ክሬዲት ካርድ ቁጥሬን በኢሜል እልክልሀለሁ::
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ShyBoy » Mon May 05, 2008 3:55 pm

የኔታ: እንዴት ነህ? ዊኬንድ እንዴት አለፈ? ለዛሬው ከ"አንቱ" ወደ "አንተ" ተመልሻለሁ...........የኔታ የሚለውን ትርጉም እስከምረዳ ድረስ:: እኔ እንዳልሁህ እኛ ሀገር ዲያቆኖቹን የሚያስተምሩ ሰዎች "የንታ" ይባላሉ እና ምናልባት አዲስ አበባ ደሞ "የኔታ" ከተባሉ ብየ ገምቸ ነበር:: ስሁን ግን ተጠራጠርሁ........እስቲ መልሱን ካንተ እጠብቃለሁ::

የኔታ: የእንግሊዘኛው ነገር አሁንም እንደከበደኝ ነው:: ለምሳሌ receord spped የምትለዋን ያለዛሬም አልሰማኋት:: Concorde Speed ለማለት ይሆን ብየም ተጠራጠርሁ:: የሆነው ሁኖ ናፍቆት ናት እንጂ የጠፋችው እኔ በጣም አለሁ:: ባለፈው ላንተ እና ለጉዱ ካሳ መልስ እየጻፍሁ እያለ ኮምፒዩተሬ ፍሪዝ አደረገ:: በጣም ብዙ ነበር እና የጻፍሁት በጣም ተናድጀ መልሸ ሳልጽፍ ቀረሁ:: እዚህ የምሰራበት ቢሮ የኮፒዩተራችንን ስክሪን ሁለት መሆን አለበት ተብሎ ሁለተኛን ስክሪን ከገጠሙልኝ በኋላ አልፎ አልፎ ፍሪዝ ያደርጋል:: እናም ዋርካ ላንተ እየጻፍሁ ባለበት ሰዓት ልክ ሰብሚት ልለው ስል ፍሪዝ አደረገ:: አሁን እንኳን ከIT ዲፓርትመንት መጠው ነካክተውት ስለሄዱ የተስተካከለ ይመስላል:: ኤኒወይ: እኔ አልጠፋሁም ለማለት ያህል ነው:: ናፍቆት ግን ሁሌም ቶሎ ቶሎ እንደማትመጣ የታወቀ ነው:: እንዲያውም ለረጅም ጊዜ ከቤቷ የጠፋሁት ከርማ ከርማ ስለምትመጣ ነው:: እንግዲህ አንተ የሷ Public Relation ስለሆንህ ቅሬታየን አቅርብልኝ...... :lol: :lol: :lol:

ጎጃም አዘነን በተመለከት ስለተዘፈነው ዘፈን ግጥም ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም:: እኔ ብዙ ጊዜ ዘፈን የምሰማው ከግጥሙ ይልቅ ዜማውን ነው:: ይሄም ዘፈን ግጥሙን በደንብ አልሰማሁት:: አስተያየት ለመስጠት ደጋግሜ መስማት ሳይኖርብኝ አይቀርም:: R Kellyን ይመስላል (R Kelly ኮርጆታል) ብለህ የለጠፍኸውን ሰውየ አየሁት የሆነ ነገሩ ደስ ይላል:: ግን ዘፈኑ አመረኛ ይሁን ኦሮምኝ አልሰማሁትም:: ጮህ አድርጌ እንዳልሰማው ሰው ረብሻለሁ ብየ ሰጋሁ:: በኋላ ቤቴ ስሄድ እሰማዋለሁ:: አንድ ነገር ልነግርህ የምፈልገው ግን R Kelly ያልኸውን ዘፋኝ ድሮ ሰይፉ ፋንታሁ አዲስ ዜማ ላይ ስሙን ሲጠራው ነው እንጅ ትዝ የሚለኝ አላውቀውም:: በእርግጥ ከዛ በኋል ጓደኞቸም ስሙን ሲጠሩት ሰምቻለሁ:: ከዛ ያለፈ ግን አላውቀውም............ከምሬ ነው!!! እኔ እንግሊዘኛ ዘፈን እንደማልወድ ድሮም ተናግሬያለሁ::

ባለፈው ልመልሰልህ ያሰብሁት ስለዚህ ጉዳይ ነበር...
actually a very good friend of mine has this big dream of bringing all these anonymus identities to the light ... an effective social networking can not be established on such exclusively anonymus identities.

እኔ ራሴ ሁሌም የምመኘው እዚህ ዋርካ ውስጥ በኒክ ብቻ የሚተዋወቀው ሁሉ ሰው በአካል እንዲገናኝ ነው:: እንዴት ሊሳካ እንደሚችል አላውቅም:: ናፍቆትን ባገኝሽ ደስ ይለኛል ያልሁት እሷ በጣም ለየት ያለች ስለሆነች ነው እንጅ ሁሉንም የዋርካ ተሳታፊ በአካል ባውቀው ደስ ይለኛል:: እስቲ ጓሰናህን በሀሳብህ ግፋበት በለው:: የሚታገዝ ነገር ካለ እኔም አግዛለሁ:: አንተም አግዝ: ደሞ እስኪ ናፍቆትን ከኔ ጋር በማገናኘት ጀምር....... :lol: :lol: :lol:

ውይ!!! በጣም ዘበዘብሁ............ይቅርታ ይደረግልኝ! ናፍቆት: እባክሽ በባዶ ቤት አታስለፍልፊን:: እስቲ ብቅ በይና ስለውጭው ሀገር ገጠመኝሽ አውጊን:: ምናልባት ካዱ ከተማ ወደሌላው ከተማ ዞር ዞር እያልሽ እየጎበኘሽ ይሆናል አንዴ ብቻ ብቅ ብለሽ እንዲህ የተሰወርሽው:: መልካም የመዝናናት ጊዜ ይሁንልሽ!!! (ለቫኬሽ እንደመጣሽ ገምቸ ነው)::

የኔታ..........አንተም መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልህ!!!
ጉድሻ.........አንተ ደሞ መልካም የቢዝነስ ሳምንት ይሁንልህ: ስጋው በደንብ ቸርችር በኋላ ከሰርሁ ብለህ እንዳትዘጋው::

ሁሉም ዋርካዊ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥመው ምኞቴ ነው!!!!!!!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby የኔታ » Tue May 06, 2008 5:31 am

shyboy

ሙዚቃውን በዜማ ብቻ ከሆነ የምታደንቀው ስለግጥሞቹ በግድ ምንም ማለት የለብህም:: embedded የሆኑና ያላየኋአቸው ሰምና ወርቅ ነገር ቢጤዎች ካሉ ብዬ ነው አጠያየቄ ...

ቋንቋው አልገባ ያለህ ዘፈን ጃፓንኛ ሳይሆን አይቀርም ... or at least one of the far eastern languages. there must have been other versions of it for sure. I just liked this one thoug ...

ያለፈው ፖስት ላይ ያስቀመጥኩት የጽህፈት ግድፈት እንጂ ምንም esoteric እንግሊዝኛ ሆኖ አይደለም:- 'record speed'

እንደ Face Book አይነት social networking ውጤታማነቱ ብዙም አሳማኝ አያስፈልገውም:: በሌላው በኩል ደግሞ ከብዕር ስም ጀርባ መደበቁ አያናፋሮች መናገር የሚፈልጉትን ያለፍራቻ እንዲናገሩ መድረክ ይሰጣል:: ሚዛናዊ የሆነውን ነገር በዚህ መካከል ላይ ማግኘቱ ነው እንግዲህ ለውጤቱ መሰረት የሚሆነው ብዬ አስባለሁ ... that's the theoritical part, we've some work to do in order to make this a reality. Thanks for your offer to support, my friend definitely will appreciate any help.

መልካም ጊዜ ...
የኔታ
የኔታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Nov 15, 2003 2:28 am

Postby ShyBoy » Tue Aug 12, 2008 9:53 pm

እንዲያው የደብዚ ጠጅ ቤት እንኳን ከከሰረበት ተመልሶ ስራውን ሲጀምር ይሄ ቤት ተዘግቶ ይቅር? ናፍቆት አንችም እንደኛ ከሀገርሽ እንደወጣሽ ለምደሽ ቀረሽ እንዴ? ሰላም ነሽ ግን? ምኑ ነው እንዲህ ያጠፋሽ ባክሽ? እስኪ ከጎሬሽ ወጣ በይና አለሁ በይን............

ሰላሙን ሁሉ ባለሽበት!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ዋናው » Thu Aug 14, 2008 8:49 pm

ሠላም ቤተ ናፍቆታዊያን
እሷ እስክትመለስ ቤቱን ሻይ እንደሚያስተዳድረው ነው የሰማዉት ምነው ታዲያ ያንድሰሞን ዓይነት ወግህን ወርወር ማታደርገው? ሠሞናቱን ዋርካ ጥላ ስር ምናምን እንደቀበርን እያንዣበብን ነው ለማንበቡ ካሮት እብለላለው እስቲ እንጨዋወት ዓይናፋሩ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ShyBoy » Thu Aug 14, 2008 9:41 pm

ዋናው የዋርካ ግሮሰሪ ቱጃር: እዚህም ተገናኘን? ዛሬ በርከት ብለህ ነው የመጣኸው.........እስቲ ይልመድብህ:: የናፍቆትን ቤት ደሞ ማን አስረክቦኝ ነው? ዝም ብላ አይደል እንዴ ጥላው የጠፋችው እና አሁን ባንድ በኩል ሀገር ውስጥ ገቢ: ባንድ በኩል ባንኮች: ባንድ በኩል ግለሰብ አበዳሪዎች: ባንድ በኩል ጥሬ እቃ በዱቤ ሲያቀርቡላት የነበሩ ድርጅቶች ቤቷን ለመቀራመት ስጅ ስጅ ገጥመው አይደል እንዴ ርስበርሳቸው የሚዳቆሱት:: እኔማ ራሷ መጣ መጀመሪያ ከዕዳ ነጻ ካላወጣችው አልረከብም..... :lol:

ዋንሽ: ከመቸ ወዲህ ነው ደሞ እኔ ወግ አዋቂ የሆንሁት? በል የልቅ አንተም ጨዋታ አምጣና ናፍቆት ቢያንስ በትንሹ እዳዋን የምታቃልልበት ገቢ ማግኘት ትጀምር::

ናፍቆት.........ኧረ ባክሽ ነይና እዳሽን ክፈይ:: ካልሆነም አንዴ ብቅ በይና "ባንክራፕሲ" ፋይል አድርገሽ ሂጂ.......... ከዛ በኋላ አንችም አበዳሪዎችሽም ዘርፈጥ ብላችሁ ትቀመጣላችሁ::
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ተመስጌን » Sun Aug 24, 2008 3:05 pm

ናፍቆት ለትውስታ የዛሬ ሶስት አመት ገደማ ስለ ቅንጅት የጻፍሽውን አገኘሁና ወደፊት አመጣሁት::

ናፍቆት wrote:I should tell you this. ከምር::

በአል ደርሶ አይደል? ፋሲካ .... ከቢሮ ጠፍተን ወጥተን ገበያ ነገር ..... ዛሬ እኮ ነው ... ጠዋት ..... እና ባለሱቁ በሙሉ ሱቁ ፈርሶ ፈርሶ ውጭ ነው የሚሸጠው:: ምን እንደሆነ አላውቅለትም ባሁኑ ጊዜ የመንግስት ዋነኛ አጀንዳ ቤት ማፍረስ ሆኗል:: በሁአላ መልሶ ይስራው አይስራው አላውቅለትም:: እና .... የኛ ደንበኛ ካለችበት ቀጥሎ ቀጥሎ አንዱዋ ሻጭ ጋ አንድ ገዢ ይጨቃጨቃል .... ኑሮው ይሁን ወይም ይሄ አሰልቺው የምርጫ ወሬ ይሁን ወይም ደሞ ናር ናር ያለው የአመትበአል የእቃ ዋጋ ይሁን ብቻ አላውቅለትም ምን ብስጭት ብስጭት እንዳረገው ..... ብቻ ... ሰውየው ቀጠን ረዘም ያለ .... ድክም ያለው የሚመስል .... አይኖቹ ገባ .... ቀላ ነገር.... ፊቱ ለብለብ ነገር ..... ነተብ ያለ ቡኒ ኮት ... ትከሻው ላይ የሰፋ አይነት .... ቄጤማ ነገር በፌስታል ይዟል:: For some reason ፈስታሉ ከሱ ጋር አልሄደልኝም ለኔ ..... እና ከሻጭዋ ጋር ...

ሻጭ - በቃ ተወው አልኮት እኮ ... (እቃዋን መልሳ እየወሰደች)
ገዢ - ለምን እንዴ? መብቴ እኮ ነው ... ብፈልግ መጠየቅ .. መከራከር ..... እንዴ? ቆይ መብት የለኝም? (ምናምን..)
ሻጭ - ሰውየው ጤና የለውም እንዴ .... ዞር ብላ ..... በቃ ይቅር አልኩ እኮ ... (ሌላ ሰው እያስተናገደች)
ገዢ - እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ (ምርር ምርር እያለው) መብት የለኝም እንዴ ... ካልተስማማኝ ጥዬ መሄድ አልችልም?
And I was like what's wrong with this guy?

መጨረሻ ላይ አንድ ሌላ ሻጭ ከወደዛ መጥታ 'እስቲ አንቺ ዝም በይ .... ዝም በሉና ይሂዱ እርስዎ ' እየተለማመጠች ..... ሸኘችው

እና the funniest part ሲሄድም ሰውየው 'መብት የለኝም? ' ምናምን እያለ እያጉረመረመ ሲሄድ ልጅትዋ ወገብዋን ይዛ ቆም አለችና በአይንዋ እየተከተለችው በሀዘን እኮ ነው 'ምስኪን ... ቅንጅት ነው መሰለኝ' ትላለች .... እየው ..... የሳኩት ሳቅ ... ፈረስኩኝ ..... Christ! I am laughing even now .... honestly. ለምን ቅንጅት እንደመጣላት ሴትዮዋ I have no clue.

But it really made me wonder how people perceive this propaganda of election. For example, this lady .... Ok ok. I stop.

ለማንኛውም እኔ ዶሮ ልበላ ሶስት ቀን ቀርቶኛል .... ጾሙ? ት....ክ....ት....
ተመስጌን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 81
Joined: Fri Dec 07, 2007 7:46 pm

Postby ShyBoy » Mon Dec 08, 2008 3:58 am

ቆይ ግን: የናፍቆት ነገር እንደቀልድ ዝም ተብሎ ቀረ አይደል? እሷም እንደኛ ከሀገር ወጣ ቀረች ወይስ ምን ዋጣት?

የዋርካ "አፋልጉን ኮሚቴ" ሊቀመንበር: አቶ ዋናው ዘኪዎስ እባክዎ የአፋልጉን ማስታወቂያ እንዲወጣ ያድርጉልን::
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ናፍቆት » Fri Dec 26, 2008 9:50 am

ሀይ ShyBoy, trust me! አልሞትኩም ገና
ግን ልጠይቅህማ [/b] ዋርካ ላይ ሲጽፍ የነበረ ሰው ሲሞት እንዴት ነው የሚታወቀው?

ተመስጌን - የዛሬ ሶስት አመት የጻፍሽው ብለህ ያመጣህውን አንብቤው ... እየው እንዳዲስ በሳቅ ሞትኩ ነው የምልህ እኮ:: ከምር ..... አንዳንዴ ራሴ የጽፍኩትን ወደ ሁአላ ተመልሼ ሳነበው ልክ ሌላ ሰው እንደጻፈው ነገር እንዳዲስ ያስቀኛል:: ደግነቱ ያየሁትን ትእይንት ዘርዘር አድርጌ ስለምጽፈው ነው መሰለኝ ሳነበው ቦታውና ሰአቱ ላይ ሄጄ ለመቀመጥና ለማስታወስ ጊዜ አይወስድብኝም እንጂ ....

ዛሬ አርብ ስለሆነ ይሁን ወይም because of the holiday season .. አላውቅልህም ብቻ I am in a very good mood. እና ራሴን ቆንጆ የቢሎስ ሚሊፎኒ ጋብዠው እየበላሁ ነው የምጽፍልህ .... [ እንዴት እንደምወድ አታውቅም:: ኬክና ቼኮሌት ... ያን ያህል ግን ዝፍዝፍ እንዳልመስልህ.... ]

ከወደናንተ ጋ ሰንበት ብዬ ስመለስ .. እዛ የኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት በጣም ሲወራልኝ ስለከረመ ሰው እርስ በርሱ የሚባላ ሁሉ መስሎኝ ነበር ... ስመጣ ያየሁትን አትጠይቀኝም? አንዱ ጋ እቃ ለመግዛት ቆም ብትል ሰዉ ከሁአላህ እየመጣ ቀድሞህ ለመግዛት ላይህ ላይ ሲወጣ ብታይ ጉድ ትላለህ:: ሰው እንደጉድ ይከፍላል - ይገዛል ነው እኮ የምልህ .... I don't know what is really going on in the country. ከምር

By the way, how was the European Christmas. አንድ ቺካጎ ያለች ልጅ ኦባማ በማሸነፉ 'የኔ ስቴት ሰው ስላሸነፈ ደስ ብሎኛልና በስሜ ዋይን ክፈቱልኝ' ብላ ትንሽ ፈገግ አስብላኛለች:: ወይ የኔ ስቴት? ... እና የናንተስ ገና እንዴት ሆኖላችሁ ይሆን?

እጽፋለሁ እስቲ
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests