የዲማ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ብራንጎናትርን » Sun Sep 28, 2008 7:33 pm

ግጥም እንደአትክልት ነው ...ከኮተኮትከው እንደጉድ ይፈልቃል ...


ውይ አፌ ቁልጥ ይበል የኔ ትልንጎ ... :lol: በውነት የሳምንቱ ምርጥ ጥቅስ ብዬዋለሁ:: :)

ምረቱ ነፍሴ ግጥሞችህን ወድጃቸዋለሁ:: የትርንጎን አባባል የጠቀስኩት ያለምክንያት አይደለምና በርታ ወንድሜ ...

ሁላችንም አማተሮች ነን ... ስለአማተርነት ካወራህማ .... :lol: እኔም እስኪ ለመቀበጣጠር እሞክራለሁ ንሽጥ ሲያደርገኝ .... :)
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

ምስጋና

Postby ምረቱ » Sat Oct 04, 2008 1:41 am

ብራንጎናትርን� wrote:
ግጥም እንደአትክልት ነው ...ከኮተኮትከው እንደጉድ ይፈልቃል ...


ውይ አፌ ቁልጥ ይበል የኔ ትልንጎ ... :lol: በውነት የሳምንቱ ምርጥ ጥቅስ ብዬዋለሁ:: :)

ምረቱ ነፍሴ ግጥሞችህን ወድጃቸዋለሁ:: የትርንጎን አባባል የጠቀስኩት ያለምክንያት አይደለምና በርታ ወንድሜ ...

ሁላችንም አማተሮች ነን ... ስለአማተርነት ካወራህማ .... :lol: እኔም እስኪ ለመቀበጣጠር እሞክራለሁ ንሽጥ ሲያደርገኝ .... :)


ብራትርንጎን

አመሰግናለሁ ለሰጠኽው አስተያየት:: የትርንጎን ምክር ተቀብየ ለመኮትኮት እየሞከርኩ ነው:: ሁለት ትምህርት ቤትን የሚያስታውሱ ግጥሞች እንካችሁ ብያለሁ::

ምረቱ ዘብሔረ የጁ!
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የትምህርት ቤት ትዝታዎች

Postby ምረቱ » Sat Oct 04, 2008 2:21 am

የረሐብ አድማ!

ቆሽቱ ሲጨስ እርር ሲል
አሳራሪውን ያሳርር ይመስል
ተሜ እንደውም አልበላም ቢል
አሳራሪዎቹ ስለገባቸው
አልበላሙ እንደማይጎዳቸው
ለምደውት ፈለጉና ሊላጡበት
ይሉ ጀመር ተውት አትለምኑት::

እውነትም ምን አስራበው?
ምሳ እያለው ቁርስ እያለው
ቅንጨው ዳቦው ሞልቶ በየካፌው
እራቱንም ሳያጣው!
ተሜ ያንማ መች ሳተው?!

እርር ያለው የተራበው
ባገሩ ላይ በሚሆነው
ወገኑን ሲያየው ሰልስሎ
ያለ ዕድሜው ተጎሳቁሎ
ቀንበር ጠቦት ተመሳኩኖ
ማደሪያ መሬቱ ተሸንሽኖ
እንደሚራብ ስለገባው
ተሜ የካፌውን እንዴት ይብላው?!

የገበሬው እኗኗሩ
መኳተኑ በባዶ እግሩ
እንደማያርስ ጦም ማደሩ
ያም ሳያንሰው ዱላና እስሩ
ሰቆቃው ስለገባው
ተሜ የካፌውን እንዴት ይብላው?!

መናገር ዳዳው
ግና ዱላ እስሩ አፈናው ትዝ አለው
ዙሪያውን ሲማትር
ባለክላሽንኮቭ አጋዚ ወታደር
አብሮት ያለው ወሬ ሰላይ የታጠቀ
በግቢው ውስጥ የሸመቀ
ዝም እንዳይል
ለህሊናውስ ምን ይበል?!

ያን ሲያነሳ ይኼን ሲጥል
ሲብሰከሰክ ሲያሰላስል
የካፌው ወጡ ቀጥኗል
ላይብራሪው መጽሐፍ አንሶታል
መች ተወው መብሰልሰል
የግንባሩን ጸጉር ሲፈትል ሲፈትል
ሲያስታውስ ለካስ አለ የራብ አድማ
ባጋዚ ቆመጥ የማያስደማ::

እሱም ቢሆን በሰበብ ነው
የወገንን ጉዳይ ማን ሊደፍረው
ባሳራሪው ቋንቋ ያ ፖለቲካ ነው
እሱ ደሞ ወንጀል ነው ላሳራሪው
ማንስ ሊያስወራው
ምን ሊሰራ ጆሮ ጠቢው
የታጠቀ በጊቢው ውስጥ የሸመቀው
የተሻላው የራብ አድማ
በቆመጥ የማያስደማ::

እስቲ በየት ሀገር
ታይቷል ራብ ሲያስጨፍር
አድማው ሲጀመር
ልክ መራብ እንደሚያጠነክር
ይጀመራል ፉጨት
ግንብ አጥር ላይ መወራጨት::

ቀረርቶው ሌልኛ በእንግሊዝኛ
ባማርኛ በኦሮምኛ በትግሪኛ
""ጥያቄያችን የዳቦ ነው!""
ዳቦ ሞልቶ በየካፌው

የኮሌጁ አስተዳዳሪ
ባለ ጊዜ የተሾመ ባሳራሪ
ይመጣና ይለፍፋል
ማን ይሰማዋል
ተሜ ፉጨቱን ቀጥሏል::

እባካችሁ ተማሪዎች ችግሩን ደርሰንበታል
በተቻለ መጠን ባጨር ጊዜ ይቀረፋል
አሁንም ይፋጫል ማን ይሰማዋል
አስተዳዳሪው ተማሮ
ተመለሰ ወደ ቢሮ
ማፈሪያ ነሆለል
ችግሩን ደርሶበት ሞቷል!

በተሜ ቤትማ
የተፈለገው የራብ አድማ
የወገን ብሶት ሊያሰማ
ወኔ እየፈነቀለው
አሳራሪውን መተናነቅ እያሰኘው
ሲያየው ዙሪያው ገደል ቢሆንበት
አሳራሪውን የሚወጋበት
በተገኘው ሊወናጨፍ
የራብ አድማ አውጆ እርፍ!

የራብ አድማ ስሪቱ
መቁረጫው ስለቱ
ሆኖ ወዳራሪው
የበለጠ ጎዳው::

እዚህ ላይ ነው ክፋቱ
የራብ አድማ ብልሽቱ
አሳራሪ አለመጉዳቱ::

የሚሻለው ባያደማም የሚያደብነው
ባያሳርርም የሚያምሰው
ድንጋይ መወርወሩ ነው
እስከሚደርስ ማሳረሪያ ጊዜው::

መስከረም 22 , 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የት/ቤት ትዝታዎች

Postby ምረቱ » Sat Oct 04, 2008 6:21 am

የመርካቶ ቸርቻሪ


ሸቀጥ አልባ ቸርቻሪ
ድብርት ዱካክ ያናወዘው ዘዋሪ
ተገኘ መርካቶ ኬኔዲ ላይብራሪ
ዱካኩን ሊያባርር
ወሬውን ይዞ ሲያዘዋውር
እነ ቤቲ አዩትና
ጠሩት ...ዳኒ ናና..ና
ምላሱ ጫፍ ላይ የደረሰውን
የቅምቀማውን የፊልሙን
ወሬ ሊካፈሉት
ዙሪያውን ከበቡት::
ወሬው እንደተጀመረ
ሁካታው የመርካቶውን መርካቶ ተወዳደረ
ያኔ ጨምጫሚው ቀና ብሎ ገልመጥ
ወግ ጠራቂውም 'አቦ ተወና አርፈህ ተቀመጥ'
አጣራቂዎቹም አብረው ማፍጠጥ
የሁሉም ዐይን ጎረጥረጥ
ጨምጫሚው ቦታ እንዳይቀይር
በጠፋ ወንበር
ዳኒም አጣራቂዎቹም የሚፈልጉት ነገር
ከዚያ ጨምጫሚውም ማጉረምገም
'ሁሉም እኮ አለው የራሱ ዓለም'
ሰው በቃ አይጨመጭምም?!
ማጉረምረም...
ፈልጐ ነገር እንደላስቲክ መለጠጥ
ጨምጫሚው በኃይል ጭብጨባውን ቢያቀልጥ
ወዲያው ግልምጫ ሲበዛ
ቢገባቸው ነገሩ እንዳልሆነ የዋዛ
ወሬ ቸርቻሪው ፍትልክ
እነ ቤቲም ቀስ ብለው ሹልክ
የኬኔዲ መርካቶ ቸርቻሪ
ጥናት ትቶ የሚቸረችረው
ወግ እና ጉራ ነው
ለነ ቤቲ ግን ""ሙድ"" አለው::

ምረቱ
መስከረም 22, 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

..........ፋጤን እልካለሁ

Postby ወልዲያ » Sat Oct 04, 2008 7:41 am

ሠላም ምረቱ!Image

ንም ቃላት የለኝ በርታ እልሃለሁ:
ሥተኽው ከሆን ፋጤን እልካለሁ:
ጃር እንኳን ባልሆን በየጁ እኮራለሁ::


መልካም ቅዳሜ
ወልዲያ - የጁ

ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

gud now

Postby harar_beer » Sat Oct 04, 2008 9:40 am

ሠላም ምረቱ !

ም ንም ቃላት የለኝ በርታ እልሃለሁ :
ረ ሥተኽው ከሆን ፋጤን እልካለሁ :
ቱ ጃር እንኳን ባልሆን በየጁ እኮራለሁ ::


መልካም ቅዳሜ
ወልዲያ - የጁ

ክክክክ this you anet mean
harar_beer
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Oct 02, 2008 1:10 pm

Postby ናፖሊዮን ዳኘ » Sat Oct 04, 2008 9:32 pm

ውድ ምህረቱ:

ግጥሞችህን አነበብኩአቸው:: የረሐብ አድማ ያልከው የት የነበረውን ነው?! ጥሩ መልዕክት ያስተላለፈ ግጥም ነው::
የኬኔዲውን ደስ ይላል:: ለኔም አተካራውን አስታወሰኝ:: በርታ ጥሩ ግጥሞች ናቸው:: ነጻነት የሚለውም እንዲሁ በጣም ጥሩ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሆኖ ነው ያገኘሁት:: በርታ!

ከአክብሮት ጋር
ናፖሊዮን
ናፖሊዮን ዳኘ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1943
Joined: Fri Apr 18, 2008 4:52 am

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Mon Oct 06, 2008 9:43 am

ሰላም ምረቱ አማን ነው? በጣም ጥሩ ጅምር ነው በርታ: ከላይ ሰለ ረሐብ አድማ የፃፍካትን ግጥም ሳነብ ብዙ ነገር አሰታወሰከኝ ትምህርት ቤት እያለን የረሐብ አድማ አድርገን ያጋጠመንን:: ለዛሬ ሰለ ታክሲ ብየ ልወጣ::

ታክሲ

<< ግቡ - ግቡ መሄ ነው !
የሞላ ! የሞላ ነው !>>
ከፊት ቆሞ እንዳያልፈው:
መንገድ ዘግት
ግፍትር - ግፍትር
ጉትት-ጉትት
ያንንም - ያንንም
-----እንደሽቀጥ::

ደሞ -
እፍስ አርጎ ክትት
ሳትጠይቀው :
የት እንደሚሄድ ሳታወው::
እና --
በሩ ዝግት
<<ኧረ - እባክህ
ወዴት ነህ ?>> ማለት
ታፋሽ ተጓዥ::
<< ክፈል ክፈል - ዘጠና አምስት>>
<<ኧረ-ምነው ? >>
በቃ ! በቃ ! ሂሳቡ ነው:
አቦ አትነጅሽኝ ነብሱ --
እና - መሄድ ::

<< ውረድ - ውረድ >>
ካሰብኩበት ሳልደርስ ?
ተመላሽ ነኝ ከዚህ ወዲያ የትም አልሄድ !!
------በቃ ውረድ !!

አንድ ጥያቄ ብትጨምር :
ይፈጠርና ግርግር
የጥንቁቋን የሩኅሩኍን
የማማህን ገበና
አዝረክርኮ ሊዘርራት በጎዳና!!

አንተው አፍረህ
በገዛ ገንዘብህ
መዋረዱ :
ያንተው አንሶህ:
የናትህን ውርደት ሰምተህ
አዝነህ ጭስህ ትውላለህ::
እና ነገም ይደገማል
ይለምድሀል
ትለምዳለህ!!

በጨዋ አገር
በህግ አገር
ህግ ጠብቆህ!

እንዲህ - እንዲህ - ትኖራለህ::


ወረኢሉ
ከወሎ ገራገሩ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ምረቱ » Sun Oct 12, 2008 5:16 am

ወልድያ እና ወረኢሉ

ለሰጣችሁት አስተያየት ምስጋናይ ይድረስልኝ::

ናፖሊዮንም እንደዚሁ ለሰጠኸው አስተያየት አመሰግናለሁ:: የረሀብ አድማው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1988 ዓ. ም ኮተቤ የነበረውን ነው ለማስታወስ የሞከርኩት::

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ናፍቆት

Postby ምረቱ » Sun Oct 12, 2008 5:28 am

ናፍቆት

አሁን እዚህ ሆኘ ከሰው ጋ እያወራሁ
ወሬውን ዘንግቸ እኔ ነጉጃለሁ
"እዚህ' እና 'አሁኔን' 'ያ' እና 'ትላንት' ነጥቀው
አገር ቤት ወሰዱኝ ድንገት አንከብክበው
እነሱን ገፍትሬ ወደ ""አሁን-እዚህ"" ስመለስ
እንደቀጠለ ነው ወሬው ሳይደፈርስ
እኔም የመንተፍረት የት ሄደ እንዳልባል
ትክ ብየ ማየት ያዳመጥኩ ይመስል
ግን ምን አበረታው "ትላንትን" እንደዚህ
""አሁንን"" ቀምቶ የሚወስደው ከዚህ
እርጂናም ቢጫነው እንደዛሬም ባይሆን
የ'ትላንት' ጉልበቱ በናፍቆት ላይ ቢሆን
ትላንትም ቢደክም መች ይተኛል ነገ
እንዲሁ በተራው ሊወስደኝ ፈለገ
እሱ ግን ተሻለ ተስፋ ስላዘለ
የመሆን እድሉ ከትላንት ያየለ
እንደዚያ ከሆነ ትላንትን ቀንሶ
....ዛሬ ላይ መከተም
እሱን እየንኖሩ ነገን ለመተለም


ምረቱ ዘብሄረ የጁ!!
ጥቅምት 2, 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ዋኖስ » Tue Oct 14, 2008 12:01 am

ግሩም ነዉ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ምረቱ » Sun Oct 19, 2008 5:54 pm

ዋኖስ wrote:ግሩም ነዉ::


አመሰግናለሁ ዋኖስ::
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

የዘመናዊነት ልክፍት!

Postby ምረቱ » Sun Oct 19, 2008 6:37 pm

የዘመናዊነት ልክፍት

ጦር ጋሻ ጎራዴ; እንዲሁም ጾም ጸሎት
በነቂስ ወጥተው የተሰለፉበት
ምድረ አበሻ ተኮልኮሎ የከፈለበት -በደም; ባጥንት
ጎበዝ እንስት ወጣት አዛውንት የሞተበት; የሞተለት
ድፍረት;ቀናዒነት; ፍቅር ;እምነት ተገምደው የሰሩት
ክቡር ማንነት; ሌላው አንገት ሲደፋ ዘለግ ያልንበት
የኛም ያሁኖቹ እትብት የተቀበረበት; ያደግንበት
ክቡር ማንነት...
አሮጌ ነው ብሎ""የነቃ"" ግልገል ሲሳለቅበት
ማን ያስረዳኝ ግልገሉን እንዳልነካው ልክፍት?!!

የተሞተው ለመሬቱ; ላዛውንቱ; ለህጣኑ-ላላደገው
ለሴቱ ላሮጊቱ ገና ለሚወለደው
ለሚያምኑት ክርስቶስ ሰውን ለማዳን የሞተው ....እንደማያረጀው
ከገባን ማንነትም የእምነት ያህል ነው ማን ሊያስረጀው?!
እስቲ ይምጣ አዋቂ አፉን ሞልቶ የሚያብራራ
የፈተነም ካለ ማንነት እንደሚያረጂ በቤተ-ሙከራ
ልክፍት እንጂ የሚሉት ""ዘመናዊነት""
""ነቅቻለሁ"" የሚለውን ግልገል የሚጫወትበት
በውል ያልተጤነ ""ዘመናዊነት""
ማንነትን መናቅ; እራስን መጠየፍ አስታቅፎት
ማንነትህ አሮጌ ነው እያስባለ የሚያስወተውት
የሰውን አሽቃብጦ የራሱን ሲሳሳት
ቢቻል ኖሮ መውሰድ ጠበል ሁለት ሰባት
መሞከር ነበረ ቢሆነው መዳኒት::

አዲስ ነው የሚለው አብዛኛውን ዓለም ድሮ የጨቆነ
በመሳሪያ ብርታት ረግጦ የገዛ ሕዝብን እያፈነ
ጠመንጃ ደብቆ እጂ አዙር ቢያደርገው
""የነቃው"" ግልገሉ አዲስ አደረገው
ግልገሉ እንደሚለው እንዲህ እንዳሁኑ
ምኞትን ደብቀው አገር ገለው ሊከፉኑ
ጦቢያ እናስልጥን ቢሉ ፈቃድ ስጡን
የውነት የነቃው ያ የድሮ ግልገል...
ፍርጥም በማለት -እኛ የማንን ጐፈሬ እናበጥራለን?!
ይልቅ አያያዙን አሳዩን እኛስ ምን ሊያቅተን!

ያኔ ገሸሽ ሲል ላሰልጥናችሁ ባይ
ግልገሉም ሲረዳ መሆኑን ቃል አባይ
በል ዓይንህን ላፈር ወደዚህ እንዳታይ!

አሰልጣኝ ቁርጡን ሲያውቅ ዘራፍ አለ አጓራ
ዘራፍ ባይ አላየ የሚወድ ተራራ
በሌላው ዓለም ሲያይ ወራሪ ሲስፋፋ
አበሻንም ወሮ አንገቱን ሊያስደፋ
በጦር አንበርክኮ አበሻ ምድር ሊስፋፋ!

መድፍ ታጥቆ ቢያየው መች ፈራው አበሻ-ፊት ልፊት ...ገጠመ
ዘራፍ ያለው ጨቋኝ እንኳንም ሊጨቁን እራሱ ወደመ
ያበሻም ማንነት በድል ተሽልሞ
ልዩ ታሪክ ሆነ ዓለም አስገርሞ

በውነት የነቃው የተገለጠለት አላስነካም ያለው
የድሮው ግልገል ነው ማንነቱን ወዶ ለዚያ ሲል የሞተው
ይኼ ልክፍታሙ በሰው የሚኮራው
ራሱን ቸርችሮ ላሰልጣኝ የሸጠው...በዛ የሚያተርፈው
መንተፍረቱም ቀርቶ ክብር ማንነት""አሮጌ"" እያለ ሚጠራው
እራሱን የማያውቅ የሆነ በዋል ፈሰስ
ጸሐፊው ይለዋል የማንነት ልክስክስ::

ጥለት ሆኖ ሳይቸግር ጤፍ ብድር
የማያረጀውን የማንነት ጥሪት አሮጌ እያሉ መደናገር
ማንነትን ሸጦ ባልባሌ ነገር
መቸስ ከወደደ እራሱ ይጋተው ሌላውን አያሳክር!!

ለሚያምኑት ክርስቶስ የሞተው እንደማያረጀው
ማንነትም የእምነት ያህል ነው ማነው የሚያስረጀው?!

ምረቱ

ጥቅምት 11, 2001 ዓመተ ምህረት

ለብራትርንጎን
Last edited by ምረቱ on Wed Apr 08, 2009 12:47 am, edited 3 times in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ሙሐመድ » Mon Oct 20, 2008 7:10 am

ቴክኖሎጅ ወይስ ተንኮል ነጅ
ካለ እድሜ የሚያስረጅ
በዘመናዊ ጦር መሳሪያ የሰው ዘር አስፈጅ
እኔ የምለው ቴክኖሎጅ ሰልጥኖ
የት ደረሰ ሮጦ ፈጥኖ
የጥንቱ የጠዋቱ ጆሮየ
የድሮ ሞዴል መሆኑን እያየ
ምን ነው ዝም ጭጭ አለ ቴክኖሎጅ
ሰውን ከሰው ለማጋደል ይሩጥ እንጅ
በላቦራቶሪው ኬሚካሉን ቀምሞ
በሰው ልጅ ላይ ለመጣል አዥገምግሞ
ክላስተር ቦንብን ፈልስፎ
የአዳምን ልጅ አጥንት እና ስጋውን ቆራርጦ ቀስፎ
ቴክኖሎጅ
ለጥፋት እንጅ
ረጋ ብየ ሳስበው
ተንኮል ነጅ ነው
ሙሐመድ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Wed Aug 11, 2004 2:10 pm
Location: ethiopia

የሰፈር ትዝታዎች

Postby ምረቱ » Sun Nov 02, 2008 8:06 pm

የሰፈሩ አዛውንት እና ፍንዳታ

ወደ ማታ ሲሆን ሰፈር ሰብሰብ ብለን
ወሬ ስናወራ ግንብ ተደግፈን
አንድ ፍሬ እያለን ምንነቱን ሳናቅ ሴት ለካፊ ሆንን::

ተሰብስበን ያዪት የሰፈሩ አዛውንት ሀሳብ ቢገባቸው
የምናውካካበት ምክንያት ባይገባቸው
ኧረ እናንተ ልጆች እባካችሁ አጥኑ
ሰዐቱም ጊዜ አይደል መሽቷል እኮ ቀኑ
ፍንዳታው ሲያማርር ያዛውንቱን ምክር
ድምጹን ከፍ አድርጎ መዘርጠጥ ሲጀምር
የመንደሩን አዛውንት ጓደኛው ይመስል
""ይኼ አራጌ ደሞ በጣም ያበዛዋል""
ገና ከመምጣቴ ደርሶ ይለክፈኛል
"አንተ ምን አገባህ'
'ቦታው ያንተ መሰለህ?'

መሄድ ተስኗቸው በከዘራ ብርታት እየተራመዱ
የሰፈሩ አዛውንት ልባቸው አልሞተም...
የኮሪያን እና የኮንጎውን እልህ ሊያወጡት ወደዱ
ዘርጣጩ ሲያበዛው በጣም በስጨት ብለው
ምን የተረገመ አሁን በዚህ ብለው ለማነካካት ነው::
እናንተ ግን ተባረኩ
እንዳይን በጠፋ እንዳትማረኩ
ብናገር አጥኑ ብላችሁ ልጆቼ ስለሆናችሁ
አስኮላውን ጨርሳችሁ ኮሌጅ በጥሳችሁ
ዲግሪውን ጭናችሁ ለራሳችሁ ለናት ላባታችሁ

እኔማ ምናለብኝ
ዕድሜ አላደኽየኝ
የተጠናቀኩኝ ቀኔ የደረሰ
ልጤ የተራሰ ቀብሬ የተማሰ
አጥኑ ማለቴ መናገሬ ለናንተው
በሉ እስኪ እግዜር ያብጀው::

ምረቱ

ጥቅምት 25, 2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 5 guests