የዲማ ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የዲማ ግጥሞች

Postby ምረቱ » Fri Sep 26, 2008 4:17 am

!!!ነጻነት ምንድነው?

ድፍን ቢሆንበት ትርጉሙ ባይገባው
ይጠይቅ ጀመረ ""ነጻነት ምንድን ነው?""
"'ነጻነት የማን ነው?""
በስተምዕራብ ያሉት ፊደል የቆጠሩት
..... ሎጂክ ያነበቡት
ትርጉሙን ሊያብራሩ ተረባረቡበት

ሩሶ እንደገባው እንደተረጎመው
የሰው ልጂ ነጻነት ገና ከሙጣው ነው
ሲወለድ ያገኘው አብሮት የመጣ ነው
ከዚያ በኁላ ነው ቀማኛ ያገኘው
እስር ቤት ሳይገባ ሰው የታሰረው
ይሁን ትንሽ ትርጉም አለው

ሚል ደሞ የሚለው የሰው ነጻነት ነው
ሌሎችን ሳይነኩ እንዳሻ መሆን ነው
ምን አይነት ሎጂክ ነው?

ሌሎችን ረስቶ
አብሮነትን ገፍቶ
ሰለጠነ መስሎት...
ሲሆን አንቶ ፈንቶ:
በግሩ ሲጠቀጥቅ ያብሮነት እሴቱን
አልነካም ሊባል ነው የህብረተሰቡን
ምን አይነት ሎጂክ ነው ሚል የደረደረው?

ስራስ ቦታ ቢሆን ምኑን ተጠቀመው
በየፋብሪካው ውስጥ አሩን ለሚበላው
ጣቱን ለሚያጣበት ጎደሉ ላረገው
ነጻነት ምኑ ነው ከምንስ አዳነው
በመንግስት ፋንታ የቱጃር ተወካይ
...ቁም ስቅሉን ሲያሳየው
ፍጠን እንጂ "ሱቹፒድ' ሲለው
ልብሱንም ቀይሮ ጺምህን ላጭ ሲለው
ፍሪደም የቱ ነው?

ግራ ሲገባው ስው
'ስትሬሱን' ሲያፍስው
'ሊቭ ሚ አሎን' እያለ ብቻውን የሆነው
እሱ ነው ነፃ ሰው?
ባያውቀው ነው እንጂ እንዲያውም ባሪያ ነው
ግማሹን ነጻነት ለቀጣሪው ሰቶ
የተረፈውንም ከሱስ ጋር አጣብቶ
በስተመጨረሻ ራሱን ረስቶ
ተፈጥሮውን ትቶ ሲሆን አንቶ ፈንቶ
አሁንም ነጻ ነው
ሲናገር ስንሰማው
ምን አይነት ቋንቋ ነው
እጁን ካልታሰረ ነጻ ነው ማለት ነው
ምን ድንፈፍነት ነው
አትንኩኝ ስላለ ነጻ ነው ማለት ነው
እስኪ በደንብ አስሉት
ትርጉሙን ፈትሹት
አትንኩኝ የሚለው
በማን ነው ያመጸው?
...ጉንጩን ብልጥጥ አርጎ ጌቶቹ ጋር ስቆ
ሕዝቡን ሲያኮርፍ ነው
እሱ የሚነቃው ቤተሰቡ ላይ ነው
አትንኩኝ የሚለው ለመሸራገጥ ነው
እሱ ነው ነጻ ሰው
ሚል የሚያሞግሰው
ሚልስ አስመሳይ ነው
አዛኝ ቅቤ አንጉአች ነው

አበሻስ ምናለ ""ነጻነት ምንድን ነው?""
አበሻ ጨዋ ነው
አትንኩኝ የሚልው
ላገር ለመሞት ነው
የህብረተሰቡን ክብር ሊያስጠብቅ ነው
ዜማውም ሌላ ነው
ክንዴን ሳልንተራስ ምን አይነት ወንድ ነው
ባህር ከፍሎ መቶ እኛን የሚገዛው
ያ ነው ያወራጨው
አበሻ ወንድ ነው!!

ማንነቱን ሳይሆን መገዛትን ጥሎ
ወደ መሮት ቀብሮ
ሀገር አስከብሮ
በተከበረ አገር ማንነቱን ተክሎ
ተክሉ አንዳይጠወልግ ደብዛው እንዳይጠፋ
ሲያርም ሲኮተኩት ማታ አያንቀላፋ
.....ጧት አያንቀላፋ
የሴትም ወንድ አለው አብራ ስትለፋ
የኔ አምበሳ አያለች ውስጡን ስታፋፋ
ኑሮውንም ሲኖር ሆዱ ዱጭ ሳይል አንገቱን ሳይደፋ
የነጻነት ትርጉም በልቡ ታትሟል ሆኖ እንደማይጠፋ
ይሄን እንደማያውቅ
የሌባ አይነ ደረቅ
መንገድ ሰብሮ መጣ ነጻነት ሊያሳውቅ
"'ባርነት ምን ሲባል"'ብለው የታገሉት
በለሱ ቀንቷቸው ሕዝብ ላይ ጉብ ያሉት
አዲስ ትርጉም ይዘው ተለቃለቁበት

ከዚህ መልስ ጋሞ
ከዚያ መልስ ኦሮሞ
ከዚህ መልስ ትግሬ
ከዚያ መልስ አደሬ
ይኼ ነው ነጻነት
ሌቦቹ እንደሚሉት
በፊት ያደገውን በብረት ቆረጡት
ተክሉም ጉደኛ ነው የማይለወጥ
በቆረጡት ቁጥር ነው የሚያቆጠቁጥ
ይኼ ነው ነጻነት
ስንቱ የሞተለት


መስከረም 15 , 2001 ዓመተ ምህረት

ጀማሪ ገጣሚ እንደመሆኔ የተለያየ ስህተት እንደሚኖረው ጥርጥር የለውም:: ትኩረቴ ግን መልዕክቱ ላይ ነው:: ያስተዋልኩትን እና የተሰማኝን ነው ለመጻፍ የሞከርኩት:: ለትችት ክፍት ነው:: ግጥም የምትወዱ እና እንደኔ መለማመድ የምትፈልጉ ዋርካውያን ይሄ ቦታ የናንተም ነው ተለማመዱበት:: ግጥም ሲያነቡት ብቻ ሳይሆን ሲጽፉትም የሚያስደስት ነገር ሆኖ አግኝቸዋለሁ::
ሰላም
ምረቱ ዘብሄረ የጁ!!
Last edited by ምረቱ on Fri May 21, 2010 11:23 am, edited 3 times in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ህይወት » Fri Sep 26, 2008 7:43 am

ሀይ ምረቱ!

በጣም አሪፍ ግጥም ነው!! ታለንቱ አለህ ግፋበት ዋናው ይዘቱ ነው ቆንጆ አርገህ አቅርበህዋል!! የነጻነት ትርጉሙ ለማይገባው የአበሻ ደንቆሮ ሁሉ ጆሮው ተከፍቶለት ያንተን ግጥም እንድያሰማው ምኞቴ ነው!!

ቀጥልበት ነፍሴ አሪፍ ነው!!!
ህይወት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 167
Joined: Mon Dec 15, 2003 5:11 pm

Re: አማተር ገጣሚያን

Postby ፋጤ » Fri Sep 26, 2008 6:42 pm

ምረቱ wrote:ነጻነት ምንድነው?

ድፍን ቢሆንበት ትርጉሙ ባይገባው
ይጠይቅ ጀመረ ""ነጻነት ምንድን ነው?""
"'ነጻነት የማን ነው?""
በስተምዕራብ ያሉት ፊደል የቆጠሩት
..... ሎጂክ ያነበቡት
ትርጉሙን ሊያብራሩ ተረባረቡበት

ሩሶ እንደገባው እንደተረጎመው
የሰው ልጂ ነጻነት ገና ከሙጣው ነው
ሲወለድ ያገኘው አብሮት የመጣ ነው
ከዚያ በኁላ ነው ቀማኛ ያገኘው
እስር ቤት ሳይገባ ሰው የታሰረው
ይሁን ትንሽ ትርጉም አለው

ሚል ደሞ የሚለው የሰው ነጻነት ነው
ሌሎችን ሳይነኩ እንዳሻ መሆን ነው
ምን አይነት ሎጂክ ነው?

ሌሎችን ረስቶ
አብሮነትን ገፍቶ
ሰለጠነ መስሎት...
ሲሆን አንቶ ፈንቶ:
በግሩ ሲጠቀጥቅ ያብሮነት እሴቱን
አልነካም ሊባል ነው የህብረተሰቡን
ምን አይነት ሎጂክ ነው ሚል የደረደረው?

ስራስ ቦታ ቢሆን ምኑን ተጠቀመው
በየፋብሪካው ውስጥ አሩን ለሚበላው
ጣቱን ለሚያጣበት ጎደሉ ላረገው
ነጻነት ምኑ ነው ከምንስ አዳነው
በመንግስት ፋንታ የቱጃር ተወካይ
...ቁም ስቅሉን ሲያሳየው
ፍጠን እንጂ "ሱቹፒድ' ሲለው
ልብሱንም ቀይሮ ጺምህን ላጭ ሲለው
ፍሪደም የቱ ነው?

ግራ ሲገባው ስው
'ስትሬሱን' ሲያፍስው
'ሊቭ ሚ አሎን' እያለ ብቻውን የሆነው
እሱ ነው ነፃ ሰው?
ባያውቀው ነው እንጂ እንዲያውም ባሪያ ነው
ግማሹን ነጻነት ለቀጣሪው ሰቶ
የተረፈውንም ከሱስ ጋር አጣብቶ
በስተመጨረሻ ራሱን ረስቶ
ተፈጥሮውን ትቶ ሲሆን አንቶ ፈንቶ
አሁንም ነጻ ነው
ሲናገር ስንሰማው
ምን አይነት ቋንቋ ነው
እጁን ካልታሰረ ነጻ ነው ማለት ነው
ምን ድንፈፍነት ነው
አትንኩኝ ስላለ ነጻ ነው ማለት ነው
እስኪ በደንብ አስሉት
ትርጉሙን ፈትሹት
አትንኩኝ የሚለው
በማን ነው ያመጸው?
...ጉንጩን ብልጥጥ አርጎ ጌቶቹ ጋር ስቆ
ሕዝቡን ሲያኮርፍ ነው
እሱ የሚነቃው ቤተሰቡ ላይ ነው
አትንኩኝ የሚለው ለመሸራገጥ ነው
እሱ ነው ነጻ ሰው
ሚል የሚያሞግሰው
ሚልስ አስመሳይ ነው
አዛኝ ቅቤ አንጉአች ነው

አበሻስ ምናለ ""ነጻነት ምንድን ነው?""
አበሻ ጨዋ ነው
አትንኩኝ የሚልው
ላገር ለመሞት ነው
የህብረተሰቡን ክብር ሊያስጠብቅ ነው
ዜማውም ሌላ ነው
ክንዴን ሳልንተራስ ምን አይነት ወንድ ነው
ባህር ከፍሎ መቶ እኛን የሚገዛው
ያ ነው ያወራጨው
አበሻ ወንድ ነው!!

ማንነቱን ሳይሆን መገዛትን ጥሎ
ወደ መሮት ቀብሮ
ሀገር አስከብሮ
በተከበረ አገር ማንነቱን ተክሎ
ተክሉ አንዳይጠወልግ ደብዛው እንዳይጠፋ
ሲያርም ሲኮተኩት ማታ አያንቀላፋ
.....ጧት አያንቀላፋ
የሴትም ወንድ አለው አብራ ስትለፋ
የኔ አምበሳ አያለች ውስጡን ስታፋፋ
ኑሮውንም ሲኖር ሆዱ ዱጭ ሳይል አንገቱን ሳይደፋ
የነጻነት ትርጉም በልቡ ታትሟል ሆኖ እንደማይጠፋ
ይሄን እንደማያውቅ
የሌባ አይነ ደረቅ
መንገድ ሰብሮ መጣ ነጻነት ሊያሳውቅ
"'ባርነት ምን ሲባል"'ብለው የታገሉት
በለሱ ቀንቷቸው ሕዝብ ላይ ጉብ ያሉት
አዲስ ትርጉም ይዘው ተለቃለቁበት

ከዚህ መልስ ጋሞ
ከዚያ መልስ ኦሮሞ
ከዚህ መልስ ትግሬ
ከዚያ መልስ አደሬ
ይኼ ነው ነጻነት
ሌቦቹ እንደሚሉት
በፊት ያደገውን በብረት ቆረጡት
ተክሉም ጉደኛ ነው የማይለወጥ
በቆረጡት ቁጥር ነው የሚያቆጠቁጥ
ይኼ ነው ነጻነት
ስንቱ የሞተለት


መስከረም 15 , 2001 ዓመተ ምህረት

ጀማሪ ገጣሚ እንደመሆኔ የተለያየ ስህተት እንደሚኖረው ጥርጥር የለውም:: ትኩረቴ ግን መልዕክቱ ላይ ነው:: ያስተዋልኩትን እና የተሰማኝን ነው ለመጻፍ የሞከርኩት:: ለትችት ክፍት ነው:: ግጥም የምትወዱ እና እንደኔ መለማመድ የምትፈልጉ ዋርካውያን ይሄ ቦታ የናንተም ነው ተለማመዱበት:: ግጥም ሲያነቡት ብቻ ሳይሆን ሲጽፉትም የሚያስደስት ነገር ሆኖ አግኝቸዋለሁ::
ሰላም
ምረቱ ዘብሄረ የጁ!!


Image

እንዲህ ነው ገጣሚ ለሃገር ወገን:
በኢትዮጵያ መኩራት አሳየኝ የጁን::

ፋኖ ፋኖ (ካሳ ተሰማ)
http://www.youtube.com/watch?v=QmfpRtdjSPc


ፋጤ
ከአራባቲ - ወረባቦ
Image
አሰደሳችና ጠቃሚ ይሆናል ለምትለው
ነገር ሁሉ በይሉኝታ አትለፈው !!
ፋጤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 107
Joined: Mon Aug 20, 2007 9:25 pm
Location: WolloW

Postby ትርንጎ 123 » Sat Sep 27, 2008 2:10 pm

ምረቱ...ጀማሪ ገጣሚ ነኝ አልክ??? ማለት የምትፈልገውን ሁሉ ቁልጭ አድርገህ አስቀምጠኸዋል...እንዲያውም ቆሽቱ ያረረውን ሰው ሁሉ በሚኮረኩር አይነት...ኧረ ፃፈው ፃፈው!

:D ፈገግ ያስባለችኝ ግን መጨረሻዋ ላይ "ዘብሔረ የጁ" የምትለዋ ነች...ከላይ ምን ስትል ቆየህና ብሄር ውስጥ ገባህ ብዬ...ከተሳሳትኩ ይቅርታ::

በተረፈ ግጥም እንደአትክልት ነው...ከኮተኮትከው እንደጉድ ይፈልቃል...የራስህን ስልት ሳትለቅ የሌሎች ደራሲያን ግጥሞች ማንበብ የቃላት ምርጫዎችንና የአጣጣል ዘዴዎችን ያሰፋ ይመስለኛል...የሳድስ ፊደላትንም በብዛት ከመጠቀም ያድናል:: በርታ! ደግሞ ቡናም ይደገማል እኮ... :)
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ትርንጎ 123 » Sat Sep 27, 2008 2:11 pm

.....
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ትርንጎ 123 » Sat Sep 27, 2008 2:12 pm

,,,,,,,,,
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ትርንጎ 123 » Sat Sep 27, 2008 2:12 pm

ተደጋግሞ ነው
ትርንጎ 123
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 253
Joined: Sun Feb 03, 2008 6:14 am

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 1:18 am

ህይወት wrote:ሀይ ምረቱ!

በጣም አሪፍ ግጥም ነው!! ታለንቱ አለህ ግፋበት ዋናው ይዘቱ ነው ቆንጆ አርገህ አቅርበህዋል!! የነጻነት ትርጉሙ ለማይገባው የአበሻ ደንቆሮ ሁሉ ጆሮው ተከፍቶለት ያንተን ግጥም እንድያሰማው ምኞቴ ነው!!

ቀጥልበት ነፍሴ አሪፍ ነው!!!


ሕይወት አመሰግናለሁ:: ለነገሩ እኔ ገጣሚ የመሆን እቅዱም የለኝም:: ውስጤን መግለጽ ፈለኩና ጀመርኩት ሳላስበው ግጥም ሆነ:: የመጀመሪያው ግጥም መስተካከል እንዳለበት እኔው ራሴ አይቼዋለሁ:: የጎደለውም ነገር ጨምሬ ፖስት አደርገዋለሁ::

ያ ራሴን አጠፋለሁ ባለው ልጅ ምክንያት የራሴን ገጠመኝ የሚገልጽ እና ያስተምራል ብየ ያሰብኩትስ አንድ ሌላ ግጥም ዛሬ ጽፌአለሁ እሱን እለጥፋለሁ::

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Re: አማተር ገጣሚያን

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 1:21 am

Image

እንዲህ ነው ገጣሚ ለሃገር ወገን:
በኢትዮጵያ መኩራት አሳየኝ የጁን::

ፋኖ ፋኖ (ካሳ ተሰማ)
http://www.youtube.com/watch?v=QmfpRtdjSPc


ፋጤ
ከአራባቲ - ወረባቦ


ፋጤነት አመሰግናለሁ:: ወሎ ገራገሩ እመጣለሁ::

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 1:29 am

ትርንጎ 123 wrote:ምረቱ...ጀማሪ ገጣሚ ነኝ አልክ??? ማለት የምትፈልገውን ሁሉ ቁልጭ አድርገህ አስቀምጠኸዋል...እንዲያውም ቆሽቱ ያረረውን ሰው ሁሉ በሚኮረኩር አይነት...ኧረ ፃፈው ፃፈው!

:D ፈገግ ያስባለችኝ ግን መጨረሻዋ ላይ "ዘብሔረ የጁ" የምትለዋ ነች...ከላይ ምን ስትል ቆየህና ብሄር ውስጥ ገባህ ብዬ...ከተሳሳትኩ ይቅርታ::

በተረፈ ግጥም እንደአትክልት ነው...ከኮተኮትከው እንደጉድ ይፈልቃል...የራስህን ስልት ሳትለቅ የሌሎች ደራሲያን ግጥሞች ማንበብ የቃላት ምርጫዎችንና የአጣጣል ዘዴዎችን ያሰፋ ይመስለኛል...የሳድስ ፊደላትንም በብዛት ከመጠቀም ያድናል:: በርታ! ደግሞ ቡናም ይደገማል እኮ... :)


ሰላም ትርንጎ :

ስላስተያየቱ አመሰግናለሁ:: ሳድስ ያልሺውን ነገር ረስቼዋለሁ:: ድሮ ቄስ ት/ቤት እንደተማርኩት ነው:: ፊደል ሊያስፈልገኝ ነው ማለት ነው::

'ብሔረ' የሚለውን ብራትርጎንም እንዲሁ ጠይቆኝ በከፈተው የሙዚቃ መገባበዣ ቤቱ ላይ የማውቀውን ያህል ዘርዘር አድርጌ መልሻለሁ:: እዛ ላይ አንብቢው:: ካጣሺው እኔ ሊንክ አደርግልሻለሁ:: ሌላ አጭር ግጥም አለ:: እሞታለሁ የሚለውን ልጂ በአካል ባገኘው እንዴት ደስ ይለኝ ነበር:: ለሱ ነው የምገጥመው::

ምረቱ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

"እውስጥ ፈልጉት"

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 1:50 am

""እውስጥ ፈልጉት""

አንድ ጊዜ...ራሴ
ጠፍቶብኝ...ለራሴ
ምን ወሰደው ብየ ግራ ተጋብቼ
ፍለጋ ገባሁኝ ጊዜየን ሰጥቼ
"ይኼ ነው?!" ...
ኖ "ራሴ" የታል? ይኼ ራሴ አይደለም
ከመሬት ተነስቶ ራሴ አይከፋም
ሰውም አይሽክክም
ግራም አይጋባም
ጠፋብኝ...
መፈለግ አቅቶኝ
ጓደኛህ ነኝ ሲለኝ ላንደኛው ብነግረው
በማፋለግ ፋንታ ጭራሹን ሊያጠፋው
""ስታንዳርድ"" እያለ ናላየን አዞረው
ምነው ያም በበቃው!
እየተኮፈሰ ""በአክሺን"" አወጀው
መጥፋቴን አሳየው

ያኔ ተናደድኩኝ
ቦክስ ሰነዘርኩኝ
ቅንድቡን መታሁኝ
ደሙን አፈሰስኩኝ
ግን ወዲያው ተጸጸትኩ
እምባየን አፈሰስኩ
የወጣውን እግሬን በምሬት ረገምኩ
በረድ ሲልልኝ ፍለጋየን ቀጠልኩ
አምላኬንም ለመንኩ
ለእግዜር አያልቅበት
በውስጤ አገኘሁት
ራሴን አየሁት
መስሎኝ የነበረው
እንደ ዐይን የጠፋው
በደንብ ሳዳምጠው
ብዙም አልተነካ እንደነበረ ነው
ላምላክ ክብር ይግባው
"እራስ' ሲጠፋችሁ እናንተም እወቁት
እግዜርን ይዛችሁ እውስጥ ፈልጉት
እግዜርም ይርዳችሁ ቶሎ እንድታገኙት

ምረቱ
መስከረም 17,2001 ዓመተ ምህረት
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 4:40 am

ድጋሚ
Last edited by ምረቱ on Sun Sep 28, 2008 3:58 pm, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 3:28 pm

ድጋሚ
Last edited by ምረቱ on Sun Sep 28, 2008 3:45 pm, edited 1 time in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

ለሶስተኛ ጊዜ የተስተካከለ

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 3:43 pm

""ነጻነት ምንድነው ?""

ድፍን ቢሆንበት ትርጉሙ ባይገባው
ይጠይቅ ጀመረ ""ነጻነት ምንድን ነው ?""
"'ነጻነት የማን ነው ?""
በስተምዕራብ ያሉት ፊደል የቆጠሩት
..... ሎጂክ ያነበቡት
ትርጉሙን ሊያብራሩ ተረባረቡበት

ሩሶ እንደገባው እንደተረጎመው
የሰው ልጂ ነጻነት ገና ከሙጣው ነው
ሲወለድ ያገኘው አብሮት የመጣ ነው
ከዚያ በኁላ ነው ቀማኛ ያገኘው
እስር ቤት ሳይገባ ሰው የታሰረው
ሩሶም የሚያየው ግለሰብን ሳይሆን
ሕብረተሰብን ነው
ይሁን ትርጉም አለው

ለየቅል ቢሆንም ማርክስም የሚለው
የሩሶ ቢጤ ነው
ዙሪያውን የሚያየው የታሰረ ሰው ነው
ሰንሰለቱን ያየው አንድ መደብ ላይ ነው
እሱም ሀሰት የለው አሁንም ልክ ነው
ፍዳውን የሚያው አፈር የሚበላው
ከወደታች ያለው አብላጫ የሆነው
ማርክስም የሚለው የሰው ነጻነት ነው
ያንን ገለባብጦ ሰንሰለቱን ፈቶ ሳይጫን ሲኖር ነው
ይሔም ትርጉም አለው

ሚል ደሞ የሚለው የሰው ነጻነት ነው
ሌሎችን ሳይነኩ እንዳሻ መሆን ነው
ብዙሀኑን ትቶ ነጠላ ነው ያየው
ምን አይነት ሎጂክ ነው ?

ሌሎችን ረስቶ
አብሮነትን ገፍቶ
ሰለጠነ መስሎት ...
ሲሆን አንቶ ፈንቶ
በግሩ ሲጠቀጥቅ ያብሮነት እሴቱን
አልነካም ሊባል ነው የህብረተሰቡን
ምን አይነት ሎጂክ ነው ሚል የደረደረው

ስራስ ቦታ ቢሆን ምኑን ተጠቀመው
በየፋብሪካው ውስጥ አሩን ለሚበላው
ጣቱን ለሚያጣበት ጎደሉ ላረገው
ነጻነት ምኑ ነው ከምንስ አዳነው
በመንግስት ፋንታ የቱጃር ተወካይ
...ቁም ስቅሉን ሲያሳየው
ፍጠን እንጂ "ሱቹፒድ ' ሲለው
ልብሱንም ቀይሮ ጺምህን ላጭ ሲለው
ፍሪደም የቱ ነው

ግራ የተጋባው
'ስትሬስ ' ያፈሰው
'ሊቭ ሚ አሎን ' እያለ ብቻውን የሆነው
እሱ ነው ነፃ ሰው?
ባያውቀው ነው እንጂ እንዲያውም ባሪያ ነው
ግማሹን ነጻነት ለቀጣሪው ሰቶ
የተረፈውንም ከሱስ ጋር አጣብቶ
በስተመጨረሻ ራሱን ረስቶ
ተፈጥሮውን ስቶ ሲሆን አንቶ ፈንቶ
አሁንም ነጻ ነው
ሲናገር ስንሰማው
ምን አይነት ቋንቋ ነው ?!
እጁን ካልታሰረ ; እስር ቤት ካልገባ
ነጻ ነው ማለት ነው
ምን ድንፈፍነት ነው
አትንኩኝ ስላለ ነጻ ነው ማለት ነው?
እስኪ በደንብ አስሉት
ትርጉሙን ፈትሹት
አትንኩኝ የሚለው
በማን ነው ያመጸው
...ጉንጩን ብልጥጥ አርጎ ጌቶቹ ጋር ስቆ
ሕዝቡን ሲያኮርፍ ነው ?
እሱ የሚነቃው ቤተሰቡ ላይ ነው
አትንኩኝ የሚለው ለመሸራገጥ ነው
እሱ ነው ነጻ ሰው
ሚል የሚያሞግሰው
ሚልስ አስመሳይ ነው
አዛኝ ቅቤ አንጉአች ነው::

ነገሩ ወዲህ ነው
እሱ የተየበው ለማደናገር ነው
ሰንሰለት ደብቆ ሰው እንዳያየው
እያስፈነጠዘ ሊያደነፍፈው ነው
ሰውም እንዳያብር
ከሌላው እንዳይመክር
እንደፈለክ ሲባል
ራሱን ከልሏል
.....ከሰው አይገናኝ
ማን ይደርስለታል
.....አብሮት እየኖረ
መች ይነጋገራል
ይሄ ነው ነጻ ሰው
ሚል የከተበለት የሚያሞጋግሰው ::

የፈረንጁን ዜማ
አበሻ ቢሰማ
መናገር ይቻላል እንደማይስማማ::
አበሻስ ምናለ ""ነጻነት ምንድን ነው ?""
አበሻ ጨዋ ነው
አትንኩኝ የሚልው
ላገር ለመሞት ነው
የህብረተሰቡን ክብር ሊያስጠብቅ ነው
ዜማውም ሌላ ነው
ክንዴን ሳልንተራስ ምን አይነት ወንድ ነው
ባህር ከፍሎ መቶ እኛን የሚገዛው
ያ ነው ያወራጨው
አበሻ ወንድ ነው !!

ደግነትም ቢሆን አብሮት የሚኖር ነው
እግዜር እንዳረገው
ለሰው የሚሞት ነው::

ማንነቱን ይዞ መገዛትን ጥሎ
ወደ መሬት ቀብሮ
ሀገር አስከብሮ
በተከበረ አገር እኛነትን ተክሎ
ተክሉ አንዳይጠወልግ ደብዛው እንዳይጠፋ
ሲያርም ሲኮተኩት ማታ አያንቀላፋ
.....ጧት አያንቀላፋ
የሴትም ወንድ አለው አብራ ስትለፋ
የኔ አምበሳ አያለች ውስጡን ስታፋፋ
ኑሮውንም ሲኖር ሆዱ ዱጭ ሳይል አንገቱን ሳይደፋ
የነጻነት ትርጉም በልቡ ታትሟል ሆኖ እንደማይጠፋ::

ይሄን እንደማያውቅ
የሌባ አይነ ደረቅ
መንገድ ሰብሮ መጣ ነጻነት ሊያሳውቅ
"'ባርነት ምን ሲባል "'ብለው የታገሉት
በለሱ ቀንቷቸው ሕዝብ ላይ ጉብ ያሉት
አዲስ ትርጉም ይዘው ተለቃለቁበት::

ከዚህ መልስ ጋሞ
ከዚያ መልስ ኦሮሞ
ከዚህ መልስ ትግሬ
ከዚያ መልስ አደሬ
ይኼ ነው ነጻነት
ሌቦቹ እንደሚሉት::

በፊት ያደገውን በብረት ቆረጡት
ተክሉም ጉደኛ ነው የማይለወጥ
በቆረጡት ቁጥር ነው የሚያቆጠቁጥ
ይኼ ነው ነጻነት
ስንቱ የሞተለት::

የምን "'ሊቭ ሚ አሎን ""
እንደማያቅ ጥቅሙን
በህብረት መኖርን
ለህብረት መኖርን::

ያበሻ ግለሰብ እንዳይወጣጠር
አገር በሱ ቆዳ ስለማትቀበር
ጠንቅቆ ይያዘው የህብረቱን ነገር::
እሱ ባገር ቆዳ መቀበሩን አይሳት
ያ የሆነው ታዲያ አትንኩን እያለ ሰው ስለሞተለት::

ተቃዋሚም ይወቅ ይህንን እንዳይስት
በነጻነት ሂሳብ ሳይገባው አይኮትኩት
ድንፈፍ የሚያፈራ የነጻነት ፈሊጥ
የሕብረቱን ያጥብቅ
እንደዋዛ እንዳይደርቅ::

አበሻ ተባርኮአል
"ነግ በኔ " ሲታደል
በብዙ ደርሶታል
ሀዘን ይካፈላል
ደስታ ይካፈላል
መጋራትን ያውቃል
ምን ቁርጥ አድርጎት እኔነት ይነግሳል
ሌላውስ ተረስቶ እሽክትር ይመታል
ሰው የሞተበትስ በእግሩ ይረገጣል?!


አበሻ ጨዋ ነው !
አትንኩኝ የሚለው
ጥቃት ከተቃጣ
ባገር ከተመጣ
ያኔ አያቅም ጣጣ::

ሲፈጥረው አበሻ ጥንቁቅ ነው
አበሻ ንቁ ነው
ወደ ውጭ ወቶ ጥራዝ የነጠቀው
""ፍሪደም"" እያለ ግራ እንዳያጋባው
ከድንፈፍነት ጋር ወስዶ እንዳያጣባው
የሕብረቱን ተክል ያን እንዳያስረሳው
ያንን ቅን አበሻ እንዳያሳስተው
አደራየ ይህ ነው::

አበሻ ገብቶታል
ነጻነቱን ያውቃል
የሰረቀውንም በደንብ አርጎ አውቆታል
የጊዜ ጉዳይ ነው እጁ ያስገባዋል
ሌባም ይታሰራል
የሕብረቱም ተክል እንዳዲስ ያብባል::

አንድ ነገር ልበል
ሀሳብ ለመጠቅለል
እኛ የወጣነው
ያንን እንዳንረሳው
ሰለጠንን መስሎን
እንዳንጥል አውጥተን !
በሞት የቀናውን የነጻነት ትርጉም
ያ ነው የሚስማማን !!

ስማርት ማለትም ትርጉሙ ወዲህ ነው
የብብት ሳይወድቅ የቆጡን ማውረድ ነው
የቆጡም ካልጣመ እዚያው መመለስ ነው
ፍሪደም የሚሉት ጥሩንባ ብቻ ነው
እሱ የሚጠቅመው ለቱጃሮቹ ነው
ሰው እንዳይባንን ለማደንፈፊያ ነው

ምረቱ

መስከረም 17, 2001
Last edited by ምረቱ on Sun Sep 28, 2008 4:54 pm, edited 2 times in total.
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ምረቱ » Sun Sep 28, 2008 3:55 pm

ድጋሚ
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests